ኢትዮጲያዊው በዩጋንዳ ጉዳይ ይፈተፍታል፣ “ኤርትራዊው” በኢትዮጲያ ጉዳይ ይዳክራል።አግባብ ነው? በክፍሉ ሁሴን

March 13th, 2012 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

“ኢትዮ-ኤርትራዊነት?አልገባኝም!”በሚል ርእስ በአማርኛ ስነጽሁፍ የመራቀቅ ችሎታው የማያከራክረን ተስፋዬ ገብረአብ በቅርቡ የሰቀላት ጽሁፍ ከያዘችው ሃሳብ ጋር መስማማት እንኳ ባይቻል አንጎልን ከመንገላጀጅ አውጥታ እንዲያሰላስል የምታደርግ ሆና አግኝቼያታለሁ።ተስፋዬ “ኤርትራዊ ስለሆነ በኢትዮጲያ ጉዳይ እየገባ ባይጽፍ እንደሚመረጥ”ፍራንክፈርት ምሳ በጋበዘው ኢትዮጲያዊ ወዳጁ ቤት ትሁት ምክር እንደተለገሰውና በበኩሉም ጋባዡ በቤቱ የሰቀለውን ኤርትራንም ጨምሮ የሚያሳየውን ከእንጨት የተሰራ የኢትዮጲያ ካርታ እያመላከተ “ካርታውን በመጋዝም ቢሆን ቆርጦ ዛሬ ካለው እውነታ ጋር ሊያስተካክለው እንደሚገባ”በመንገር የጓደኛውን ትሁት ምክር ከንቱነት ሊያሳየን ሞክሯል።ኢትዮጲያዊ ያልሆነ ሰው በኢትዮጲያ ጉዳይ አይጻፍ፣አይተች የሚል አስተያዬት ከንቱ የከንቱ ከንቱ መሆኑን አንድ በራሴ ላይ በደረሰ አጋጣሚ እመሰክራለሁ።ከአፍሪካዊነቴ በተጨማሪ ላለፉት አምስት አመታት በስደት የምኖርባት ዩጋንዳ ውስጥ የሚከናወነው ሁሉ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ስለሚመለከተኝ በጨዋ ደንብ ከፍ አድርጌ አስተያዬት መስጠት በሰውነቴም ጭምር ያገኘሁት መብት ነው።ዩጋንዳም ባልኖር ባንዳች ምክንያት ካለሁበት ከየትኛውም ስፍራ ቀልቤን የሚስብ፣ስሜቴን የሚጎነትል አንዳች ነገር በዩጋንዳ ቢፈጠር ልተችበት መብቴ የተጠበቀ ነው።የማያጨበጭቡለትን ድህረገጾች፣ባለሞገድ ራዲዮኖች፣ሳተላይት ቴሌቪዥኖች በማፈን እንዲሁም ስልክንና ኢሜይልን በመጥለፍና በመቆጣጠር(tapping & monitoring)የሚታወቀው ጉደኛው የመለስ ዜናዊ አገዛዝ እንደተጠበቀ ሆኖ እጅግ በላቀ ፍጥነት እያደገ በመሄድ ላይ ያለው የመረጃ ቴክኖሎጂ በማናቸውም ጉዳይ ከየትም ቦታ ሆነን እንድንተች ሁኔታዎችን አመቻችቶልናል።በበኩሌ ቴክኖሎጂውንና ለወሬ የሚመቸውን ስደት አቀናጅቼ ያልተቸሁበት የአፍሪካም ሆነ የሌላ አህጉር ክፋይ ቢኖር ጥቂት ነው።ዜግነት እስክወስድ ድረስ በስደት በምኖርባት ዩጋንዳ መምረጥም ሆነ መመረጥ እንዲሁም ወገንተኝነት በመያዝ በአገሪቱ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉዳይ አቋም ይዤ በአደባባይ ልሞግት አልችልም።ከዚህ በመለስ በሰብአዊ መብት፣በህግ ልእልና፣ ከባቢውን በሚመለከቱ ጂኦፖሊቲካዊ ጉዳዮች እስከጥግ ድረስ መተቸት እችላለሁ።ሃሳብን በነጻነትና በጨዋ ደንብ መለዋወጥ ባህል በሆነባት ዩጋንዳ ሃያ ስድስት አመታትን በማስቆጠር የኢዲ አሚንን የእድሜ ልክ ፕሬዝደንት የመሆን ምኞትን በተግባር ባስከነዳው የአሁኑ “ዴሞክራት” ፕሬዝደንት ሙሴቪኒ ላይ በተደጋጋሚ ትችት ሳወርድ ከዜጎችዋ ከአንዴ በቀር ይሄነው የሚባል ግልምጫ እንኳ ደርሶብኝ አያውቅም።በዩጋንዳ የሚኖር ወያኔ ወይም በወያኔ ፍቅር እፍ ብሎ ያበደ የራሴው የወንዜ ልጅ በረቀቀ መንገድ የጻፈልኝ ነው ብዬ እስክጠረጥር ድረስ ራሱን ፒተር ኦኬሎ ብሎ የሚጠራ ዩጋንዳዊ “ይቅርታ ጠይቀህ ራስህን ከዩጋንዳ ጉዳይ አሰናብት”ሲል ሊያስቦካኝ ሞከረ።ፒተርን እንዲህ እንዲያመርብኝ ያደረገው እ.ኤ.እ በ2008 ከሼክስፒር አባባል ተውሼ It’s time to fear when tyrants seem to kiss በሚል ርእስ በዴይሊ ሞኒተር ላይ ያሳተምኳት ጽሁፍ ነበረች።እና ፒተርም አለኝ “ዩጋንዳ የሰጠችህን ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አላግባብ እየተጠቀምክ እስከዛሬ በምትጽፋቸው ጽሁፎች አገሬን ምሽግ አድርገህ የአገርህን መንግስት እንደምትወጋ ስከታተል ቆይቼያለሁ።ያ አልበቃህ ብሎ አሁን ደግሞ የሚያጎርስህን እጅ ለመንከስ ተነሳህ።አንተ የደርግ ኦፐሬቲቭ እንዳልሆንክ በምን እናውቃለን?የምጽፍልህ ሃሳብህን በነጻነት እንዳትገልጽ ለማስፈራራት ሳይሆን ዩጋንዳውያን የራሳቸውን ቅራኔ ለመፍታት አቅም ስላላቸው እንደተቃዋሚ ፓርቲ አባል ታይተህ እርምጃ ሳይወሰድብህ ከዩጋንዳ ጉዳይ ይቅርታ ጠይቀህ ራስህን አሰናብት-ወዘተ ወዘተ”አለኝ።ያኔ የተስፋዬ ገብረአብ የጋዜጠኛው ማስታወሻ እጄ አልገባም ነበርና–እረ ከራሱም እጅ አልወጣም ነበር–ስብሃት ገብረእግዚያብሄር በጻፍከው ነገር ለሚደርስህ ትችት በምንም አይነት መልስ አትስጥ ሲል ተስፋዬን የመከረውን ገና ስላላነበብኩ ለፒተር ደብዳቤ መልስ ሰጠሁ።እናም በሞኒተር ጋዜጣ የተቸሁበት ጉዳይ የዩጋንዳ ብቻ ሳይሆን ከአለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ጋር የተያያዘ ጉዳይ ስለሆነ ወደፊትም እንደምቀጥልበት በቀረርቱ መልክ ጻፍኩለት።ከቀረርቱ በመለስ ግን የተባበሩት መንግስታት ስለአለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች በደነገገው አዋጅ አንቀጽ 19 ማንኛውም ሰው በነጻነት ማሰብ፣ራሱን በነጻነት መግለጽ እንዲሁም ያለማንም ጣልቃገብነት መረጃ መፈለግ፣መቀበልና ማስተላለፍ ሃሳቡንም በፈለገው መገናኛ እንዲሁም ድንበር ሳይገድበው መግለጽ እንደሚችል ደንግጓል።አፍሪካ አፍሪካ በመሆኗ ግን ደንቁረው ከሚያደነቁሩ ገዢዎች ስላልተላቀቀች በተራው ዜጋ ይህ በቂ ግንዛቤ አለማግኘት ብቻ ሳይሆን ሲመቻቸው ስለፓን አፍሪካኒዝም የሚደሰኩሩልን ገዢዎች ከአገሩ ወጥቶ ወደሌላ አፍሪካ አገር የተሰደደ አፍሪካዊ ዝም ብሎ ስደትን ማጣጣም–ይቅርታ ስለስደት መቆዘም–ክብር ለሚሰማው የሚያጣጥሙት ነገር አይደለምና–ካልሆነ በቀር አንዳችም መብት እንደሌለው በድንጋጌ መልክ ሁሉ ያስቀምጡለታል።ለምሳሌ እዚህ ዩጋንዳ በተባበሩት የስደተኞች ኮሚሲዮን መ/ቤት ከፍተኛ ባለሙያ ናቸው ተብለው ገንዘብ በስደተኛ ስም የሚዝቁት የተለያዩ የአፍሪካ አገር ዜጎች የዩጋንዳ መንግስት እ.ኤ.አ በ2009 በአገሩ የሚኖሩ ስደተኞች እንዲተዳደሩበት ያወጣውን ህግ በስደተኛ አያያዝ ለሌሎች የአፍሪካ አገሮችም “እንደሞዴል”የሚያገለግል ሲሉ ያንቆለጳጵሱታል።እርግጥ ነው ህጉ ማንኛውም ስደተኛ እንደአገሬው ዜጋ ሁሉ በዩጋንዳ ግዛት አቅሙ በፈቀደለት ቦታ ሁሉ የመኖሪያ ስፍራ እንዳስፈለገው የመምረጥና የመዘዋወር መብት እንዳለው፣ባለርስት ከመሆን በቀር በማንኛውም ስራና ንግድ ተሰማርቶ ሃብት ማፍራት እንደሚችል ሁሉ ይደነግጋል።ግን ይልና ህጉ “ማንኛውም ስደተኛ የገዛ አገሩን በሚመለከት ሆነ በሌላ ማናቸውም አገር ጉዳይ ምንም አይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማድረግ አይችልም” ሲል ይጠረንፋል።

ከጅል ሃሳብ ተነስተው በሚደነገጉ እንዲህ ያሉ አፋኝ ህጎች የተነሳ በርካታ የዋሆች የኢትዮጲያዊው ክፍሉ ሁሴንን እና የ “ኤርትራዊው”ን ተስፋዬ ገብረአብ ሃሳብን ባገኙበት ቦታ ስለፈለጉት ጉዳይ በነጻነት መግለጽን በማይመለከታቸው አገር ጣልቃ ገብቶ እንደመፈትፈት አድርገው ቢወስዱት አያስገርምም።ለመሆኑ በዘመነ ግሎባላይዜሽን የማይመለከተን አገር ጉዳይ አለ እንዴ? የተሰደድንበትን አገር ለነውጥ ተግባር(subversive action)በማዋል የመተኮሺያ መድረክ(launching pad)እስካላደረግነው ድረስ በነጻነት በማናቸውም ፖለቲካዊም ሆነ ሌሎች ጉዳዮች ለመራቀቅ የሚገድበን ህግ በሰለጠነው አለም ህብረተሰብ አይታሰብም።የተሰደዱበትን አገር መተኮሺያ መድረክ ስለማድረግ ከተነሳ ለአፍሪካ ስደተኞች ሁሉ “ሞዴል”የሚሆን ህግ የሰጠን ሙሴቪኒ ታንዛኒያን ተገን አድርጎ በኢዲ አሚንና በሚልተን ኦቦቴ ላይ እየተኮሰ የነገሰ ሲሆን የእኛው ጉዶች አዲሳባም ሆነ አስመራ የነገሱቱ ሱዳንና ሶማሊያን በተመሳሳይ መንገድ ተጥቅመው ኢትዮጲያን ከተቋረሱ በኋላ ነው።እናም ከሌሎች ነገሮች በተጨማሪ ይኸው በተስፋዬ ዜግነትና በኢትዮጲያ ጉዳይ ላይ በመተቸት መብቱ ላይ እንድንፈላሰፍ አድርገውናል።

በኤርትራ፣ በቅምብቢት ላይ ለምን አልተጻፈም?

ለዚህ ጥያቄ የሚመስለኝን መልስ ከመመለሴ በፊት መሬት ትቅለለውና ስብሃት ገብረእግዚያብሄር አለ የተባለውን ልንደርደርበት።ወያኔ የትግራይን ህዝብ አፉን በፈታበት ቋንቋ በቴሌቪዥን ፕሮፖጋንዳ እንዲጠግብ ነጻ ያወጣበት ፕሮግራም እንደተጀመረ ሰሞን ስብሃት ከመጀመሪያዎቹ ቃለመጠይቅ ተጋቦዦች አንዱ ይሆናል።ጋዜጠኛውም ትግራይን አስቀድሞ “ብሄር ብሄረሰቦችን ነጻ” ያደረገውን የወያኔ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ተጠቅሞ አፍ በፈታበት ቋንቋ ይጽፍ እንደሆነ ስብሃትን ይጠይቀዋል።ስብሃት በሰጠው አጭር መልስ በአማርኛ ካልሆነ በትግሪኛ መጻፍ እንደማይመቸው ይገልጽለታል።በወያኔ ትኩስ ጠበል የተረጨው አዲሳባ አደጉ “የትግራይ” ልጅ ስብሃትን በራሱ ቋንቋ መጻፍ እንዳለበት ሊያሳምነው ሲባጅ ስብሃት “አንተ እኔ ከምትጨቀጭቀኝ ለምን ራስህ አትጽፍም?”ብሎ ቃር ቃር የሚለውን ወያኔያዊ ነገር ዘጋው።የስሚ ስሚ ስለሆነ የሰማሁት እውነትነቱን ራሱ ተስፋዬ ሊያረጋግጥልን ይችላል ብዬ እገምታለሁ።ተስፋዬ እንዳለው ተስጥኦውን ተጥቅሞ የሚጽፍ ብእረኛ የሚጽፍበትን ርእስ ውቃቢው በመራው ይመርጣል እንጂ አይመርጡለትም።ጥያቄው እንደተስፋዬ ያለ ብእረኛ የሚጽፍበትን ርእስ ለመምረጥ የሚያስችል ነጻ ውቃቢ አለው ወይ? የሚለው ሲያነታርከን ውሎ ያለስምምነት ልንለያይበት እንችላለን።ቢያንስ ግን በኢትዮጲያ ጉዳይ እንቁ የሆነ ተስጥኦውን ተጥቅሞ ያሻውን መጻፍ እንደሚችል ስደት ከገባ በኋላ ባቀረበልን ተከታታይ ምርጥ ስራዎቹ ማየት እንችላለን።በመስመሮች መሃል ማንበብን ለምናውቅበት ተስፋዬ ኤርትራን ጨምዶ በያዘው ኢሳያስ አፈወርቂ ላይም ብእሩ ያለርህራሄ ማቆብቆቡን እናያለን ።ለምሳሌ በጋዜጠኛው ማስታወሻ ላይ በሻምበል በለጠ አማካይነት “ሻዕቢያና ወያኔ እነማን ናቸው?ከሜዳ የወጡ ምስጦች!እና ከእነሱ ጋር እየተዋጋሁ እድሜዬ ማለቅ አለበት?”እያለ ለሚገባው የሻዕቢያንም ከወያኔ ያልተናነሰ መሰሪነት ይነግረናል።የናጽነቱን ከንቱነትም በዚያው መጽሃፍ ሲያሳየን ሻዕቢያ አስመራ የገባበትን እለት ለማክበር ከበሮ ይዘው የወጡ አንዲትን አደይ ይስልልንና ለምን ሰልፉ ላይ እንደተገኙ ጋዜጠኛ ላቀረበላቸው ጥያቄ “ከኢትዮጲያ ቅኝ አገዛዝ ነጻ የወጡበትን ቀን ለማክበር”እንደሆነ ከገለጹ በኋላ ስማቸውን ሲጠየቁ “ወ/ሮ ኢትዮጲያ ዝህባል”ብለው እንደመለሱ ጽፎልናል።(በመጽሃፉ በአማርኛ የተጻፈውን በምናቤ በትግሪኛ ሲመልሱ የታየኝን በጥራዝ ነጠቅ ትግሪኛዬ አምጥቼያት ነው) የደራሲው ማስታወሻ ገጽ 346 ላይ “አማርኛ ቋንቋን ኤርትራ ውስጥ የሚያስተምሩ ት/ቤቶች እንዲከፈቱ እኔ ፍላጎት አለኝ” በማለት ሌላ ስእል ይሰጠንና በገጽ 374 ከወያኔ ጋር ያሳለፋቸውን የአድርባይነት ጊዜያት “እንደሱፍ አበባ ጸሃይ እያዩ መገለባበጥ”እንደነበር ማንም ባላደረገው ሁኔታ ራሱን በአደባባይ በመደብደብ ይናዘዝልናል። ሰቆቃወ መህቡባን በተረከበት የመጨረሻው ምእራፍ ገጽ 415 ላይ “እንደብረት የጠነከረ እያልኩ የምመካበት መንፈሴን ይህች የሃያ ሶስት አመት ልጅ ይኸው ድራሹን አጠፋችው። ‘አባቴን ኦነግ ብለው ገደሉት’ አለችኝ። ‘እናቴ ደግሞ ነፍጠኛ ተብላ እንዳትገደል ፈርታ ወደአዲሳባ ሸሸች’ እያለች ታጫውተኛለች።ከትናንት ወዲያ ደግሞ ግንባሯ ላይ የመስቀል ንቅሳት ያለባት አንዲት ቆንጆ፣ ‘ትግሬ ስለሆንኩ ጠሉኝ’ብላ እኔ ፊት ተንሰቅስቃ አለቀሰች።እኔ ደግሞ ይህንን ሁሉ ሮሮና ሰቆቃ የሚፈጽመው ቡድን ካድሬ ነበርኩ።” እርግጥ ነው ዱባይ ላይና በየተሰደዱበት ሁሉ በዚህ ስም አይጠሩ ሙያ ላይ የተሰማሩ በርካታ ኤርትራውያንን ለምናውቅ፤ በተለይም ነውር በሚሰኝ ማናቸውም ስራ ሲሰማሩ ኢትዮጲያዊ ነኝ ብለው የመቅረባቸውን የአደባባይ ምስጢር ሁሉ ለሰማን የተስፋዬን የንቅሳታሟን ልጅ አሳሳል እንደአንድ ሌላ ድብቅ አጀንዳ ልንወስደው እንችላለን።መጠርጠርን፣ ዝም ብሎ አለማመንን እሱንም ጨምሮ ተስፋዬ በአሁኑ ወቅት የሚፈራ አይመስለኝም። ለማንኛውም በሌሎችም ምንጮች የተረጋገጠውና የማይካደው ነገር እነመለስ በየጊዜው የሚያስመዘግቡት “ልማት” በዚህ ስም አይጠሩ ስራ በአገሩ ውስጥም ሆነ በውጭ አገር የተሰማሩትን ኢትዮጲያውያን እህቶቻችንን ቁጥር በአያሌው ከፍ እንዳደረገው ነው።እንዲያውም አዲሳባ በቅርቡ ደርሶ የተመለሰ በዩጋንዳ የሚኖር “ልማታዊ ባለሃብት”እንዳጫወተኝ በአዲሳባ የሚኖሩት አንዳንድ ልማታዊ ባለሃብት አጋሮቹ “ልማቱን”ለማፋጠን አንድ እርምጃ ወደፊት በመሄድ ሚስቶቻቸውን በእጅጉ በሚያማልል መልክ እንዲለብሱ በማድረግ የላቁ የእነመለስ የልማት አጋሮች በሚመሽቱባቸው የዘመኑ መሸታዎች ወስደው ፍንድቅድቅ እያሉ እንደሚያስረክቧቸው መታዘቡን ነግሮኛል።

“ወንዱም የሚሸጥ ነው ሴቱም የሚሸጥ ነው ገንዘብ ያለው ይግዛ ይገዛ የሌለው” ሲሉ በስድሳዎቹ መጀመሪያ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም የተነበዩበት ዘመን ላይ በሙሉ አቅማችን ደርሰናል።

ወደተስፋዬ ኤርትራ ላይና ኤርትራ ራሷ አምጣ በወለደችው አምባገነን ራሷን ለመደፍጠጥ ስለመረጠችው ኢሳያስ አፈወርቂ ላይ ስለመጻፉ አለመጻፉ ጉዳይ እንመለስ።እኔ ተስፋዬ ነጻ መንፈስ ይዞ በአሁኑ ጊዜ በቀድሞ ጌቶቹ ወያኔዎችና ኢትዮጲያ ላይ እንደሚጽፈው ባይሆንም ፈራ ተባ እያለም ቢሆን በኢሳያስና ሻእቢያ ላይም ከላይ ባሳየሁት ሁኔታ ጽፏል እላለሁ።በወያኔ ላይ እንደሚጽፈው በሻእቢያ ላይ እንዳይጽፍ ደብረዘይት አደግ ከመሆኑም ባሻገር በምርኮኝነት ተቀላቅሎ አዲሳባ የገባው የወያኔ ባለሟል ሆኖ እንጂ እንደትውልድ ሀረጉ ለሻእቢያ ተሰጥቶ አስመራ ላይ በመክተም የወያኔን ምስጢር ያወቀበትን እድል በሻእቢያ ላይ አላገኘም።እንዲህ ያለ እድል በሻእቢያ በኩል ስለማግኘት አለማግኘቱ በሌላ ወገንም አልተነገረንም።ወያኔና ሻእቢያ ፍልስልሳቸው በወጣ ማግስት በሻእቢያ ሰላይነት ተጠርጥሮ ከተሰደደ በኋላ አስመራ ሄዶ ያየውንና ሌሎች የመገናኛ ብዙሃን በተለይም በሶማሊያ ጉዳይ ከመለስ የተለየ ለአሜሪካና አጋሮቿ ያላጎበደደ አቋም ኢሳያስ በመያዙ ቀድሞ የአርነት ታጋይና ጀግና ብለው ሲያሞካሹት በነበረበት አፋቸው ዛሬ ብቸኛ የአፍሪቃ ቀንድ አምባገነን እያሉ እንደሚስሉትና አዲሳባ ወያኔ የሚያፈነዳውን ቦምብ ሁሉ ሳይቀር በኢሳያስ እንደሚያላክኩበት አይነት ፕሮፓጋንዳ ተስፋዬ እንዲያስተጋባ መጠበቅ የለብንም።ለነገሩ ኢሳያስን ተጠግቶ መለስን ማስወገድ ይቻላል የሚል አቋም አንዳንድ ተቃዋሚ ድርጅቶቻችን ከያዙ በኋላ ይህንኑ የሚጋሩ ድህረገጾቻችን ሁሉ በኢሳያስ ላይ ትችት የሚሰነዝሩ ጽሁፎችን ስለነጻ ፕሬስ አስፈላጊነት በሚለፍፉበት ልሳናቸው አፍነዋል።እዚህ ላይ ኢትዮጲያን ሪቪው ብቻ ከሆነ በአእምሯቹህ የሚመጣው ተሳስታችኋል።ሌሎች ደግሞ አፍቃሪ ስዬዎች ጥንት በወያኔነቱ የነበረውን ጽንፈኝነት በማንሳት በአሁኑ አዲስ ማንነቱ ላይ ጥያቄ የሚያነሱትን ቀድሞ ጽሁፋቸውን ሲያትሙ ከርመው “የአሁኑ ጽሁፍህ ከሙያው ስነምግባር ርቋል”እያሉ “ከፍ ባለ ሃሳብን በነጻነት መግለጽን በሚያበረታታ መንፈስ”ያፍናሉ።ስለዚህ በዚህና በሌሎችም ተዘርዝረው በማያልቁ ምክንያቶች ተስፋዬ እኛ በምንፈልገው መንገድ በኢሳያስ ላይ እንዲጽፍልን ወይም ስለኢሳያስ ካልጻፍክ ስለመለስ አትጻፍ ልንለው አንችልም።

ተስፋዬ ራሱም ግን ስለወያኔይቱ ኢትዮጲያ ጥግ ድረስ እየጻፈ ስለሻእቢያ ኤርትራ በመሰላቸው መንገድ ሃሳብ የሚሰነዝሩትን ኢትዮጲያውያኖች “የጨረቃ ፖለቲከኛ”ማለቱ ያደገበት ወያኔ ማለት እንደሚያዘወትረው “ፍትሃዊ”አይሆንም።በተረፈ በአብዛኛው ትግሪኛ ቋንቋ ተናጋሪ ልሂቃኖች ላይ በተደጋጋሚ የምናየው ዘር ከልጓም የሚስበው በሽታ ተንጸባርቆበት ካልሆነ ፕሮፌሰር መስፍን እንዳሉት “ኢትዮጲያ ከኤርትራ ተገነጠለች”ወይም ኤርትራ ከኢትዮጲያ ተገነጠለች መገንጠሉ የባሳት ለኤርትራ መሆኑ፣ኢትዮጲያ ባንጻሩ ብሄራዊ ጥቅሟን እንኳ የሚያስጠብቅ መንግስት ሳይኖራት ያለኤርትራ በሚገባ መቆም እንደምትችል በገሃድ የታየበት ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው።ከዚህም በላይ አብዛኛው ኢትዮጲያዊ ኤርትራን ከሻእቢያ እጅ ለማስጣል ያደረገውን ከንቱ ጦርነት ባስታወሰ ቁጥር የሚቆጨው የወታደራዊ የበላይነቱ የኢትዮጲያ በነበረ ጊዜ የኢትዮጲያን ጥቅም ባረጋገጠ መልኩ ጉዳዩን ሁሉ ለዛሬዎቹ ኤርትራዊያን ጥሎ መውጣት ብልህ ውሳኔ መሆኑን አውቆ የሚያሳውቅ አመራር ቢኖረው ስንት ህይወት፤ስንት ንብረት ማዳን በተቻለ ነበር እያለ እንጂ ተስፋዬ እንደሚነግረን ኤርትራ ያለችበትን የጥንት የኢትዮጲያን ካርታ ሰቅሎ በሰመመን ጊዜውን የሚያጠፋ የለም።ተስፋዬ ራሱ የሚወደው በአሉ ግርማ በኦሮማይ ላይ በወዶ ገባው ስዕላይ በረኺ አማካይነት “ዝም ብላችሁ እኮ ጎንደር ላይ ቆማችሁ ብታዩን እርስ በራሳችን በካራ ስንተራረድ ታዩን ነበር”ያለውን ያላጤን ብቻ ሳይሆን በአሉንም ያስበላን ትውልድ አባል በመሆናችን ራሳችንን ዝንተአለም ስንወቅስ እንገኛለን።በተቀር “ኤርትራ ጣጣ የበዛባት አገር ናት” ያለው ተስፋዬ ልክ ሲሆን ጣጣዋ ግን የበዛው አሪስቶትል እንዳለው ባንዳንድ ነገር እኩል ያልሆኑ ልጆቿ በሁሉም ነገር እኩል ለመሆን እንደመታገል ባንዳንድ ነገር እኩል ስላልሆኑ በሁሉም ነገር እኩል ላለመሆን ስለታገሉ ነው።የተመኙትን የማይነሳው– – እንዳስተዋልኩት በቅሎ ጠግባ ሰማይን ከረገጠች ወዲህ ያለው ድህረ እርግጫ አምላክ ክፉ ሲመኙ ቶሎ ምላሽ ይሰጣል– ለቀድሞ ኢትዮጲያውያን ወገኖቻችን የተመኙትን በመስጠት “ናጽነት” ያገኙባት ኤርትራቸውን በገፍ ጥለዋት የሚሰደዱባት፣ናጽነት ያጎናጸፋቸው መሪ ከመለስም በታች ተንቆና የማሪያም ጠላት ተደርጎ እልፍ አእላፍ ጊዜ ማእቅብ የሚጠራበት ግለሰብ ተገዢ ለመሆን በቅተዋል።

በመጨረሻም ተስፍሽን እለዋለሁ።ጽሁፍህ ያመረቃኛል።በመረጥከው ርእስ ጻፍ እያሳደድኩ አነባለሁ።በኤርትራ በቅምብቢት ወዘተ ለምን አልተጻፈም የሚል ራሱ ይጻፍ።

ሊመይሉልኝ ቢሹ kiflukam@yahoo.com

  1. በላይነሽ
    | #1

    አወቅሽ አወቅሽ ቢሏት ፌቷን ቆሻሻ ተለቅልቃ መጣች ማለት አነተነህ::በአለፈው በጻፍከው አርቲክል ጎበዝ ጎበዝ ቢሉህ ወርደህ መቦጫረቅ ጀመርክ::
    በመጀመሪያ ተስፋየን በኢትዮጵያ ጉዳይ አትጻፍ ያለው አልነበረም::ጸሃፌም ደንበር የለውም በሚል ሁሉም ሰው ተቀብሎት አክብሮትም አድንቆትም ነበር::አቶ ተስፋየ የተወገዘውም ሆነ የተሰደበው በመጻፉም አልነበረም::ታሪክ አውቃለሁ በማለት የማንም መንገደኛ የጻፈውን የውሽት ታሪክ ለማቅረብ መሞከሩ ነው::ይህ የታሪክ ሁኔታ ተመልክቶ ስውን ንትርክ ውስጥ ለማስገባት ሆነ ተብሎ የተጻፈም ይመስላል::የጊዜውን ትኩሳት ተጠቅሞ አንዲት ቃላት አገርም ልታፈርስ ትችላለች::የተስፋየ አጻጻፍ የአጼ ቲዎድሮስና የቲጌ ታይጡ ደጋፌዎችና አድናቂዎች ብሎም አጼ ሚኒልክን የሚደግፉትንና የሚያደንቁትን ለማባላትና አንገት ለማስደፋት አደገኛ አካሂድ ስለሆነ ነው::
    መርጃ/ምንጭ ጠቅሶል የሚባለው ስንመጣ አንድ ተመራማሪ ምርምሩን ሲጽፍ ምንጭ የሚጠቅስበት የራሱ አለመሆኑንና ለጻፉትም ሰዎች ክብር ሲባል ነው::ስህተት ቢሆን መረጃ ስለጠቀሰ ከስህተት ነጻ አይወጣም::የተረጋገጠ ምንጭ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት::ተሰፋየ ከአቅም ማነስ ሊሆን ይችላል ይህን አለደረገም::አቶ/ጋዜጠኛ ፓውሎስ እኞኞ አሳሳትም ማለት ስህተት ነው::የማይሳሳት ከአለ እግዜአብሔር ነው ማለት ነው::ሰው በመሆኑ ተሳስቷል መታረም አለበት::
    አቶ ተስፋየ ገ/አብ ተሳስቶ ከሆነና ምናልባት ስህተቱ በቅንነት ከሆነ ከዚህ ትምህርት ወስዶ መጽፍ መብቱ ነው::
    የትኛውም አገር ጸሃፌም ሆነ ደራሴ እውነት በመናገሩ ከመጥፋት አያድነውም::የሚኖርባትን አገር ሚስጥር አሳልፎ ቢሰጥ/ህብረተስብን ከህብረተስብ ሊያጋጭ የሚችል ከሆነ የትኛውም አገር መንግስት መብቱ ነው ብሎ ዝም አይለውም::
    መብትም በህግ የሚገደብበት ጊዜ አለ::ነጻነት ማለት ሰርዓት አልበኝነት ማለት አይደልም::
    ስለዚህ አቶ ክፍሉ አቶ ተስፋየን ማድነቅ ያነተ ሙሉ መብትህ ነው::ኦደየንስ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ትንሽ አሰላስል::
    ኦዲየንስን የሚያስቀይም ጸሃፌም ሆነ ተናጋሪ ለራሱ መርዝ ነው የሚጠጣው ያውም የሚያሳብድ::
    አንተም ሆንክ ተስፋየገ/አብ ለወዲየንስ ክበር ስጡ ከአላወቃችሁም አንብቡ::

  2. ALEMAYEHU
    | #2

    KIFLU! KIKIKIIIIIIIIIIII WHY YOU AFRIED WEYANE AND STARTED TO TALK ABOUT ERITREA? WE DO NOT CARE ABOUT ERITREA. TALK CAN NOT BRING SOLIUTION IN ETHIOPIA BUT FIGHTING. BECOUSE USA ARE HELPING WEYANE TO STAY LONG.IF YOU ARE A FREEDOM FIGHTER YOU MUST BE INSIDE ETHIOPIA NOT IN UGANDA. I AM NOT TIGRIAN BUT PEUR ETHIOPIAN. BUT OLSO I HEAT WEYANE REGIM. WEYANE MUST LEAVE ETHIOPIA. GOD BLESS MAMA ETHIOPIA

  3. Tekle
    | #3

    First- your writing follows no rules – no full stop no coma no begining and no closing. This is one of the major problems facing our generation – we write without knowing how to, we comment without any knowledge about the issue, we judge without the ability to evaluate, we condemn without substantial proof… etc. You lack good knowledge about the issue you raised and coting Sibahat here Tesfaye there Mesfin here… what is your point? This is a good example of the general status of our intelectual maturity. We are not admiting our ignorance, and because of that we never learn.

  4. yeteregema tiwilid
    | #4

    are mela belut bilen neber diro ahun new inda yetyachu midire maferya degi aderegen gena angetachinin yasarirenali!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  5. አምባራስ
    | #5

    ተስፋዬ:
    ትላንት የዎያኔ አሽከር እያለህ የዘባረቅከዉ አፍራሽ ፕሮፓጋንዳና ስድብ ሁሉም እዉነትነት ስላለው እስካሁን ድረስ ተነባቢ ነዉ እያልክ ነው:: ራስህንም ለእውነት ብቻ የቆምክ ትልቅ አዋቂ አድርገሃል:: የዎያኔን ዳረንጎት ለማግኜት የደረስከው የቡርቃ ዝምታ ልቦለድህም ፍጹም እዉነት መሆኑን ዛሬ ድረስ ትተርክልናለህ:: መጻፍ ስለቻለክ ብቻ ዎይም ደግሞ የተጻፈ ነገር ሁሉ እዉነት ይመስልሃል? ይልቅስ የዎያኔ ድምጽ እያለህ ላደረግከዉ መርዘኛና አፋጅ ፕሮፓጋንዳ ሁሉ ይቅርታ ጠይቀህ ለእውእነት ብትጽፍ ይበልጥ ተዎዳጅነትን ታተርፋለህ:: ችሎታህን ሲያዩት ደስ እንደሚል ነግር ግን ዉስጡ በመርዝ እንደታጨቀ የመርዝ ብልቃጥ አታድርገው::

  6. አሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወይስ አገር ተቆርቃሪነት?
    | #6

    ‘…ስለዚህ በዚህና በሌሎችም ተዘርዝረው በማያልቁ ምክንያቶች ተስፋዬ እኛ በምንፈልገው መንገድ በኢሳያስ ላይ እንዲጽፍልን ወይም ስለኢሳያስ ካልጻፍክ ስለመለስ አትጻፍ ልንለው አንችልም።…’

    ማን ይከለክለናል? ያንተ ብዕር? አንተም ትጠረዛለህ!!! እንችላለን!!!!!!!!

  7. United Horn of Africa (U.H.E)
    | #7

    @በላይነሽ
    በጣም የምደግፍ አሰተያየት !!!

  8. United Horn of Africa (U.H.E)
    | #8

    @በላይነሽ
    I find it hard to type in Geez Font. What I was trying to tell you is your comment is a comment that comes from a seasoned politician. About Tesfaye, the only thing I can say about him is he is talented novelist hoe ever his inability to weigh up the consequences of his articles proves he the worst politician ever. as for freedom of speech and expression and the human right issues, people must not take them as the holy bible, and see it as infallible and non defective legal theory. Laws are made in consideration of certain societies social, economical, and political cultural conditions. Just because certain legal concepts are work for the west and are pushed to enter on universal declarations dose not necessarily mean it is effective in Africa.
    I do agree that everyone is entitled to comment on the political situation of any country. Comment is not active participation. I am Eritrean and I am commenting here. and I am glad that I find some one who is broad minded.

  9. አቡ
    | #9

    ተሰፋዬ ኢትዮጵያዊ ተሰፋዬ ኤርትራዊ – ምነዉ መነጋገሪያ ጠፋ እንዴ? እኔም ተስፋዬም የተወለድነዉም ያደግነዉም ደብረ ዘይት ነዉ- ማነዉ ኢትዮጵያዊ ናችሁ አይደላችሁም ብሎ የሚነግረን? ተስፋዬ ኢትዮጵያን ስለበደለ ነዉ እሱ ነኘ የሚለዉን ኢትዮጵያዊነት የምንከለክለዉ? ስንት ኢትዮጵያዊ አለ ከተስፋዬ በላይ ኢትዮጵያን የበደለ? እስከዛሬስ ሲበድሉንና ሲረግጡን የኖሩት ኢትዮጵያውያን አይደሉም እንዴ ታዲያ ለምንድነዉ ኤርትራዉያን የማንላቸዉ? ኢትዮጵያዊነት የምሰጠዉም ሆነ የምንቀማው ነገር አይደለም!

  10. Tulu Oda
    | #10

    Ugandans have tolerated your shameful rudness over the years. You as a refugee have no right to interfere with their internal politics often siding with the opposition.

    No matter how much you try to protect him, Tesfaye G/A is a loyal servant of Isaias Afeworki.

    In any case your writing has no relevance to the critical issues currently facing Ethiopia.

  11. መሃመድ የሽሆቹ ልጅ
    | #11

    ክፍሉ ውሴን ጽፈህ ሙተል ልብህ ውልቅ ብሏል::ይህን የሞተ ሻቢያ የሚጽፈውን የምታደንቅ ከሆነ አንተም ከእጅ አይሻል ዶማ ነህ::ተሰድስህ ሙተሃል ከቤተስቧ ጋር እንደተጣላች ዝንጀሮ ከዚሁ እልፍ ብለህ ተቀምጠህ ወግ አደርሶህ ከአገሬ ወጥቸ ተስድጄ ትላለህ::አገር ሙሉ ከምትጽፍ ሃሳብህን አጠር አጠር አድርገህ በጎበዝ አጣጣፍ ዘዴ አስቀምጠው::የሻቢያውንም የሞኝ ስልት እወቅበት::ሞኝ ሁኖ እንድያሞኝህ::
    የጻፍከው ምንም የምተቸው ፍሬ ነገር አጥቸበት ተማር ይቀርሃል ገና ይቀርሃል ብየ መካክሬ አልፌሃለሁ::

  12. በላይነሽ
    | #12

    United Horn of Africa (U.H.E)ልተረዳልኝ የሚገባህ ማንኛውም ነገር ተለዋዋጭ ነው::ይወለዳል: ያድጋል :ይሞታል::ይህ ህይወት በለው ላይ የሚታይ ነው::ሕይወት የሌለው ነገር ብቻ ሕያው ሁኖ ይኖራል::ለትውልድም ቅርስና መልካም/መጥፎ ምሳሌ ሆኖ ይኖራል::ተፋየ ገ/አብ በማወቅም ሆነ በአለማወቅ ጥሩውን ገጽታ ወደ መጥፎ ቀይሮ ሊያስቀምጥልን ነው የሞከረው::ይህ ደግሞ ትውልዳችነን ይጎዳዋል::
    ወቅታዊ ሁኔታ ትውልድንና አገርን ሊያጠፋ ይችላል::ያ ወቅታዊ ሁኔታ ጠባሳው ለኩሶት የሚያልፈው እሳት አደገኛ ነው::
    የኔም ትችት የመጣው ስለህብረተስብም ሆነ ስለታሪክ አንድ ሰው ሲጽፍ በጥንቃቂ መጽፋ አለበት::ትውልድ አልፎ ትውልድ ሲተካ የታሪክ ምንጭ ውሽቱ እንደውነት ሆኖ ግጭት ሊያስነሳ ይችላል::በአገራችንም ያለው ችግር ይህ ነው::
    አቶ ተስፋየ ገ/አብ የጠቀሳቸው ምንጮች በጣም የተዛቡ ከመሆናቸውም ባሻገር ሊያመጣ የሚችለው አድምታ ጥሩ አይደለም ነው::
    ተሰጦ/ታለንት ምንድን ነው?የታለንት/የተሰጦ መለኪያው ምንዲን ነው? የራሳቸው መልኪያ አላቸው::ጥያቂውን ለአንተው ልተወውና ልለፈው::
    ስለህግ የጠቃቀስካቸው ከሞላ ጎደል ትክክል ናቸው::ሕግ ማለት ስምምነት ነው::የማነው ስምምነቱ?ሌላ ጥያቄ ነው::
    ሕግ ሳይንስ አይደለም ማህበራዊ ኑሮ ውስጥ የሚካተት የማህበርዊ ስይንስ ነው::ማህበራዊ ሳይንስ የሚገለገልበትን መሳርያ ሲጨምር ነው::ህግም ዳይናሚክ ይሆናል::
    ቁም ነገሩ እውነትና ውሽት ሁሉም የራሳቸው ጊዜና ቦታ አላቸው::ሁሉቱም የየራስቸው ጠቀሜታ አላቸው::ውሽት በፖለቲካል ሳይንስ ከፍተኛ ቦታ አለው በንግድም ጭምር::
    ለአነተም ሆነ ተስፋየ የምለግሰው ውሽትንም ሆነ እውነት በጊዜውና በቦታ አስቀምጣቸው ይጠቅማሉና::
    አመስገናለሁ ለሃስብህ::

  13. በለው!
    | #13

    “ስደት ለወሬ ያመቻል” በዩጋንዳ ዓምስት ዓመት ቆይታዎ” ሃሳብን በነጻነትና በጨዋ ደንብ መለወጥ ባሕል በሆነበት ዩጋንዳ በሴቩኒ ላይ የትችች ናዳ በማውረድ አድናቆትን አትርፈዋል እርስዎም ፈንድቀዋል ይህንን አጋጣሚ ኢትዮጵያ ዕድሉ ቢኖራት ከእርስዎም ከተስፋዬም በተሻለ መልኩ ክህሎቱ ያላቸው ዜጎች አሉን ወጣሁ ብለው አይዘኑ እንኳንም በጊዜ ተነቀሉ::
    አንቀጽ 19 የሰብዓዊ መብቶች አዋጅ ትርጓሜ እዳሰፈሩት”ማናቸውም ሰው በነጻነት ማሰብ እራሱን በነጻነት መግለጽ” የሚለው በዩጋንዳ ቋንቋ ሲተረጎም ካልሆነ በቀር ከእኔ በተሻለ መልኩ ሊ/ ጠበብት አለማየሁ ገ/ማርያም የተባሉ ኢትዮጵያዊ ቢያስረድዎ እመርጣለሁ::እኔን ፈገግ አድርጎኛል እሳቸውስ?
    የዩጋንዳ መንግስት በ 2009 ያወጣው ሕግ” ማናቸውም ስደተኛ የገዛ ሀገሩን በሚመለከት ሆነ በሌላ ማናቸውም አገር ጉዳይ ላይ ምንም ዓይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማድረግ አይችልም” የሚለው አሁንም ትርጓሜው ተሳስቷል ያንቡት! እንደ ራስዎ ጽሑፍ ግን ኢትዮጵያውዊው በዩጋንዳ ጉዳይ አይፈትፍት;ኢርትራዊውም በኢትዮጵያ ጉዳይ አይዳክር ማለት ነው::ሕጉ መልካም ነው ማለት ነው!
    ኢትዮ-ኡጋንዳዊነትና,ኢትዮ-ኤርትራዊነት የተለያዩ በስደትና በትግል የተገኙ ናቸው::
    እንደ ተስፋዬ ያለ ብዕረኛ “ዕንቁ ተሰጥዎ” ብዕር እና ውቃቢ ዝምድናቸው አልገባኝም? ውቃቢ..
    ዛር,ጥንቆላ,ማጓራት,አዶ-ከብሬ;ዕጣን ጫት ማመንዥክ ሲበዛ አቶ ክፍሉ ሁሴን መረቀኑ !!!!
    “የቡርቃ ዝምታ” ተጻፈ ሰውን አነጋገረው አነቃነቀው ስላላነበብኩት አስተያየት አልሰጥም በጃፓን የሚኖሩ ጥሩ አስተያየት ሰጪ አቶ ዋቆ ሀሳባቸውን ቢሰጡ እመርጣለሁ:: “የጋዜጠኛው ማስታወሻን”
    በኤርትራ ሬዲዮ የተረከው ጋዜጠኛ ኢትዮጵያ ጥገኝነት አገኘ ሕዝብ ታሪኩን ወደደው እሱ ያውጋው
    ከወያኔ ጋር ያሳለፋቸውን የአድርባይነት ግዜያት “እንደሱፍ አበባ ፀሐይ እያዩ መገላበጥ” “ከእንቅልፌ ስነቃ እራሴን ወያኔ ሆኜ አገኘሁት” ድሮስ በቁሙ የተኛና የሚዳክር ምን ይበል??
    “ለመሆኑ በዘመነ ግሎባላይዜሽን የማይመለከተን ጉዳይ አለ እንዴ?ያሉት “አሁን ሳቄ መጣ !!
    አሁንም ብዙ ከመፈትፈትዎ በፊት የዶ/ር ፍቃዱ በቀለን ጽሑፎች ያንብቡ አደራ!!በአንድ ወቅት ሊ/ጠበብት መስፍን ወ/ማርያም “ግሎባል ኢኮኖሚን”የሚለውን “የሙሉ ዓለም ኢኮኖሚ” ብለውታል
    ግሎባላይዘሽን :ግልቤያዜሽን መሆኑ ነው (መጋለብ) የራስን ሀገር ጥሎ በድሃ ሀገሮች መሬትና ጥሬ ሀብት መናኘት መበልጸግ ማጭበርበር መዝረፍ መውረስን ያካትታል(የ99 ዓመት የመሬት ሊዝ)
    ሌላው (መግለብ)አቅመ ደካማ ሀገሮችን ባሕል;ቋንቋ,ሃይማኖት,ሉዓላዊነት መናድ,እርስ በርስ ማናቆር,ትውልድን መበረዝ,ነባር ታሪክን ማጥፋት አዲስ ታሪክ መፍጠር,ወ.ዘ.ተ ያካትታል::
    እዚህ ላይ አቶ መልካሙ የተባሉ አስተያየት ሰጪ ያብራሩልዎት::እንደ እኔ እምነት ከሙሉ ዓለም ኢኮኖሚ በባዶ ሆድ የሙሉ ቀን መለሰን ሙዚቃ ማዳመጥ ብቻ ነው:: ” ስብሃት ገ/እግዝሐብሔር ለተስፋዬ ገ/አብ የመከረው”በጻፍከው ነገር ለሚደርስህ ትችት በምንም ዓይነት መልስ አትስጥ” አሁን ኩርፊያዬም ፈገግታና ሳቄ አልቆ እንቅልፌ መጣ ይህ የሚያረጋግጠው ዲሞክራሲን,መሰልጠንን ሳይሆን ትምክተኝነትን ነው:: የብሔር ብሔረሰብ ሊ/መንበር በፓርላማ የሚያደርጉት ከዚህ መርሆ ተነስቶ ነው::ስብሰባ ይጠራሉ:ያነባሉ:የተቃዋሚ ጥያቄን እንደፈለጋቸው ተርጉመው: ሕዝቦቻቸውን “በሲቲንግ ዳውን ኮመዲ” አስፈንድቀው አስጨብጭበው ይሄዳሉ::ከጽሁፍዎ ይቺን ብቻ ተረዳን!
    ክቡር ክፍሉ ሀሰን ሲፈተፍቱ አጥንትም አለ ተጠንቀቁ! አቶ ተስፋዬም ሲዳክሩ ጠጠርና እሾህ አለ ተጠንቀቁ በለው ! ከሀገረ ካናዳ በቸር ይግጠመን>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>

  14. እልፍነሽ አብዲሳ
    | #14

    የበላይነሽን አባብል እኔም የምጋራው ነው::ተስፋየ ገ/አብ የጻፈቸው ሁለቱም ስህተት መሆናቸው ታውቆ የተተቸና ያለፈ ነገር ነው::
    አንዳንድ ሰዎች ነገሮችን ጠለቅ ብሎ በአለማየት አሁንም የተስፋየን አስተሳሰብ የሚያራምዱ አሉ::አውቆ የተኛን ሰው ቢቀስቅሱት አይሰማም ዓይነት ነገር ነው::ተስፋየ ገ/አብ ብዙ ጊዜ ችግር ያለበት ይመስላል::የቡርቃ ዝምታን መጽሃፍ ሲጽፍ ምን ያህል አደጋን ጠንቅቆ የማያውቅ ሰው መሆኑን ነው የሚስረዳው::ሰውን ከሰው ማፋጀት ተስጦ ብሎ ማስብ የወንጀሉ ተባባሪ ነው::
    አቶ ክፍሉ ውሴን ይህን መረዳት ያቃተው ከሆነ ስደተኛ ነው ብሎ ማስብ ያቅተኛል::ሰድተኛ የሆነ ሰው ቢያንስ ይህን መረዳት አይቸግረውም:: ኮሚንቱ የጊዜውን ወቅታዊ ፖለቲካ ጋር ማያያዝ ነው የሚለው ከዚህ የበለጠ ምን የባሰ ነገር አለ::

  15. በላይነሽ
    | #15

    United Horn of Africa (U.H.E)አመስግናለህ ብየ ለመጻፍ ነው ብዙ ያተትኩት::አባባሌ ትክክል ከአልሆነ ይቅርታ::
    ወድ ስራ ልገባ እየተጣደፍኩኝ በድብ አላነበብኩትም ነበር::
    United Horn of Africa (U.H.E)በድብ በድጋሜ አመስግናለሁ::

  16. United Horn of Africa
    | #16

    @በላይነሽ
    Dear Belaynesh once again I couldn’t agree more . I strongly support what you said. I would like to put you on notice and to congratulate you that I can confidently say our nationalist elite ideas are taking shape and Is travelling beyond our boundaries. History distortion or sensationalized reports are not as effective as they were before 10 years. This new awareness preserve the current generation from demoralization. We have reached half the battle. By God’s Grace we shall win. Peace and love to the Horn of Africa. Forming different flags under one roof is a dream that can become a reality. U.H.O.A
    Thank you Melkam Yesera Ken.

  17. በላይነሽ
    | #17

    United Horn of Africa
    እጅግ በጣም አመስግናለሁ::
    ባይሆን የመስቀል ወፍ እንዳትሆን አደራ::

  18. አይደረግም እምቢ?
    | #18

    ይሄን ግዛት ማስፋፋት ፍልስፍና አልለቀቃችሁም እንዼ?
    አፍሪካ አንድነት ሕንፃ በቻይና የተ. መንግስታት ወጪ ደግሞ በአሜሪካ
    የናንተን ቀጠና ማን ይሆን ወጪውን የሚችለው?
    ፕሮግራሙን እንድሆን በሕዝብ ፍቃድ አትነድፉት?

    የበላይ ነሽ እያልኩ ሳሞግስሽ ውዬ
    ድንበርና አገር የራስ ታሪክ ታውቂያለሽ ብዬ

    ሃሳቡን የመስቀልፍ ወፍ እንርጋውና እንጣፍው ከቀዬ

    የአባቱን መሬት ያለረሰ ያልኖርበት ያያቱን መሬቱን ጠየቀ እንዳይሉን

  19. አቤው
    | #19

    መልካም አራያ
    ከሁለት ሳምንታት በፈት ከበላይነሽ ጋር ከሙኒክ ሆላንድ ድርስ አብረን ተጉዘናል::ያገናኘንም እሷም ለስራ ሂዳ እኔም ዘመድ ጥየቃ ወደ ሙኒክ ሂጄ ለመመልስ የትራንስፖርት ጉዞ ወኪል በአደርግነው ምዝገባ ነበር::በተደዋወልነው መሰረት በማለዳው ተገናኘን::
    ወደ ሚኪናው እንደ ገባሁ ዓይኔ ያረፈው ከመኪናው ፈት ለፈት ከአለው የፕሮፈሰር አስራትና የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ፎቶግራፍ ከግንቦት7 አርማ ጋር ነበር::አንድም ቃል ስለፖለቲካ ሳናወራ ማህበራዊ ኑሮ እያወራን ወደ ፍራንክፈርት አመራን::ፍራንክ ፈርት የሚጠብቁኝ ሰዎች አሉና ምሳ አብረን እንዲንበላ ፈቃደኝነቴን ጠየቅችኝ::ፈቃደኝነቴን ገለጽኩላት::
    ፍራንክፈርት እንደደረስን ያገኘናቸው አንዲት ሴትና ወንድ አውሮፓዊያን ፕሮፈሰሮች እንድሁም አንድ የጀርመን ባለስልጣን ነበሩ::
    ፍራንክፈርት ስንደርስ ፕሮፌሰሯ መኪናውን ተቀበለችና ጉዞ እንደጀመርን የጀርመናዊ ባለስልጣን አባትሽ የትኛው ናቸው ነበር?ብሎ ለበላይነሽ ጥያቂ አቀረበ::
    በሚገርም ሁኔታ አውሮፓዊት ፕሮፌሰር ነበረች መልስ መስጠት የጅመረችው::
    አይደሉም ይህም የፖለቲካ መሪ ነበሩ ብላ አሟሟታቸውን ዘርዝራ ከአሰረዳች በኋላ ስለዶ/ር ብርሃኑ የፖለቲካ ሕይወትና ስለድርጅታቸው አሁን ያለበትን ሁኔታ በላይነሽም እያገዘች አስረዳች::የኢትዮጵያንም ችግርና የስደተኞችን ችግር እየተጋገዙ አስረዱ::ፕሮፌሰሯ እንደኢትዮጵያዊት ሁና ነበር የምታስረዳው:: ምሳ እስከሚቀርብም ድረስ የኢትዮጵያን ሁኔታ እያነሱ ተወያዩ::በላይነሽም በኩራት እንደተማሪ ሳይሆን እንደስራ ባልደርባ ከዛም በአለፈ እንደእድሜ ጓደኞቿ ነው የምታናግራቸው::ከነሱ ጋር ከተለያየን በኋላ ነበር ስለነሱ መጠየቅ የጅመርኩት::
    ይህች የመመረቂያ ጹህፍ አማካሪ ነች::ይህ አብሮን ምርምር የሚሰራና ዓለም አቀፍ የሃይል ማመንጫ ባለስልጣን ነው:: ይህ እንዲህ ነው ያለችኝ በኋላ ትናት አብረን የምንሰራው ስለበረን አብረን ነብርን::የሷ ጓደኞች ናቸው ::መኪናውም የሷ ነው::እኔ ከያስኩት አመት ሆነኝ እንደምታየው የኢትዮጵያ ባንዲራ ለጣጥፌበት አለችኝ::ቀጥየ ያቀረብኩላት ዶ/ብርሃኑን ታውቂዋለሽ? ነበር::አላውቀውም በቴሌቭዥ አይቸዋለሁ:: ፕሮፌሰሩን አውቃቸው ነበር ወላጂቼን ሰለአስተማሯቸውና እናቴ ጋር የቤተስብ ያህል ነበሩ::ይህን ፎቶ ግራፍ እሷ ነች የስጠችኝ::ለምን ሰጡሽ ብየ ጠይቂያት ነበር አላውቅም ግን ከመኪናሽ ፌትለፈት አድርጊው ብላ ነው የሰጠችኝ::
    የዶ/ር ብርሃኑና ግንቦት7 እኔ ነኝ የሚጠይቀኝና አጋጣሚ ሳገኝ ለማስረዳት ይመቸኛል ብየ ነው አለችኝ::በራሴ እስካን አድርጌ ነው::ዶ/ሩ ያለፍቃዴ ልምን ለጠፍሽ ቢልሽስ ብየ ነበር የጠየኳት:: ወንጄል አለሰራበትግን ለምን ይጠይቀኛል ብለህ ታስባለህ አለችኝ::እንዲህ ያወራን ጉዞ ቀጠልን::
    እነሱ ከዛው ሰቀሩ ሁለታችን ወደ ሆላንድ ደረስ ተጉዘን:; እኔ ሆላንድ ቀረሁ ::እሷ ወደ ት/ቤቷ ጉዞዋን ቀጠለች::
    መልካም ምሳሌ ብየ ያልኩት ብዙዎቻችን ለራሳችን ከተመቸን የሌሎችን ችግር እንዲሁም የአገራችነን ታሪክምና የፖለቲካ ሁኔታ
    ለማስረዳት ሞራሉና ድፍረቱ የለንም::በየደረስንበትና በአገኘነው አጋጣሚ እንደአቅማችን ማስረዳት ብንችል ለትግላችን ሊረዳን ይችላል::ከበላይነሽ የተረዳሁት የግንቦት7 አባል አይደለችም/ዶ/ር ብርሃኑን አታውቃቸውም ነገር ግን ጥሩ ነው ብላ ስለአመነች
    በአገኘችው አጋጣሚ ታስርዳለች::ሰዎችን ስለአወቅናቸውና ስለአላወቅናቸው ሳይሆን መሪዎቻችንን ብናከብራቸውስ የሚል ሃስብ መጣብኝ::የማንበብ ክህሎታችነን ማሳደግም ድፍረት ይሰጠናል:: እኔ ሊቀ አገራት የት እንደሆነ አላውቅም ነበር::
    ስለአብደላሳላህ አንስተው ኢትዮጵያ ቢሂድ የት ይሆናል እያሉ ሲሉ በላይነሽ ለቀአጋራት/አዋሽ አካባቢ የጥንት ቤተ መንግስት አለ:: ከዛም ማረፍ ይችላል በርግጥ አላውቅም::በኋላ ነው ሊቀሃገራትን ያወኩት::ማነበብና ያገራችንን ታሪክም ማወቅ ለድፍረትም ስንቅ ይሆነናል::
    ይህችን ትምህርት ትሆናለችና ብጽፈው ምን ይመስልሻል ብየ በላይነሽን በስልክ ጠይቂያት ያስተምራል ብለህ ከአስብክ ጻፈው እኔን ለማሞገስ ብለህ እንዳትጽፍ አለችኝ::አትፈሪም ብየ ጠይቂያት ነበር:: ለምን እፈራለሁ አልፈራም ፍርሃቱን ተወው ነበር ያለችኝ::እወቅ ያለው 40ቅኑ ያውቃል እንጂ በላይነሽ ገና ወጣት የኔ ልጅ ጓደኛ ብትሆን ነው::
    ችግራችነን ለማስረዳት አንፈር እንበርታ ችግራችነን በማስረዳት የምናገኘው ጥቅም እንጂ ጉዳት የለውም::
    ፍርሃታችነንም አውልቀን መጣል አለብን እላለሁ::

  20. እልፍነሽ አብዲሳ
    | #20

    በአቤው ላይ ልጨምርበትና ከበላይነሽ ጋር ከ2ዓመታት በላይ አንድ ት/ቤት ተምረናል አበረንም ኑረናል::በዓመት 1ንድ ጊዜ የኢትዮጵያ የቡና ሰርሞንይ በግቢያችን እናዘግጅ ነበር::የተለያዩ ተማሪዎች academic presentation ያደርጋሉ የኢትዮጵያን በተመለከተ እኛ እናደርጋለን::ይህ ደግሞ በግቢ ያለው ህብረተስብ ጋር ለመተዋወቅ እረድቶናል::ትምህርታችንን ሰንጨርስ ራሳቸው ናቸው ከካፓኒ ጋር አስተዋውቀው ስራ የፈለጉልን::
    ሰደተኞችም በሞኖሩበት አካባቢ ኮፌ ሰርሞኒ ወይም በመሰላቸው እያዘጋጁ ጋዜጠኛና የአካባቢውን ህብረተስብ ጋር ቢግባቡ አንዱ የችግራቸው መፍትሂ መፈለጊያ ይሆናቸዋል::በላይነሽ ኮፌሰርሞኒ እናዘጋጅ ስትለን 3 ሰዎች ሁነን እንደገና ከመለማመጥ ጋር አያይዘን ደስ አላለንም ነበር::በኋላ በጣም ደስ ብሎን ብዙ ሰዎችን ተዋወቅን::ማንነትንም ለመግለጽ አለማፈር ለውጤት ያበቃል::
    አቤው ጥሩ ትምህርትና ልምድ ነው ያካፈልከው ትዝ ብሎን አያውቅም ነበር::
    በላይነሽ አሁን ቋሚ መምህር ነች:: ወደ ኢትዮጵያ ቲሰሷን ዲፈንድ ስታደግ ትመለሳለች::ጠንክሮ መስራት ለውጤት ያበቃል::

  21. ገነት
    | #21

    መልካም ምሳሌ ነው::በተገኘው መንገድ ይህን አጥፌ መንግስት ከመጥፋታችን በፌት ማጥፋት አለብን::
    ፕሮፌሰር አስራት ወ/የስ የትግላችን መስረት ናቸው::አሁን ደግሞ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የሳቸውን ዓርማ የተከተሉ የምናከብራቸው መሪ ስለሆነ ይገባቸዋል::ያለሁት ኢትዮጵያ ስለሆነ ከመኪናየ ላይ ባይሆንም የፕሮፌሰሩን ከመኪናየ የዶ/ር ብርሃኑን ከቤቴ አድርገዋለሁ::
    ለትግሉም አስተዋጾ አደርጋለሁ::

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።