ምን ጉድ ዉስጥ ገባን ! – ከኮቾናው, ቫንኩቨር
በዚህች ባገኘናት እድሜ ታሪክ አየን። መችም ለጉድ ነው ያቆየን ጉድም እያየን ነው። ግፍን የሚሰራና የሚዋሽ ሁሌ ነፃነት የለዉም።ወንጀለኛ ሲመረመር ይንተባተባል ወይንም ይቀባጥራል መርማሪዉም ግምት ይወስዳል። የቀድሞው የአሜሪካን መሪ ከጋዜጠኞች ጋር በጥያቄና መልስ ወቅት አንገታቸዉን እንዲደፉ የሚያስገድዳቸው ዉሸት ነበር። ጋዘጠኞችም ጠንቅቀዉ ይገነዘቡት ነበር።አንዳንዱ ደግሞ የዋሽዉን ዉሸት ስለሚዘነጋው እንዲህ ብለህ ያልከው ተብሎ ከተጠየቀ ሽምጥጥ አድርጎ ከመካዱም ሌላ ጠያቂዉን ሲያሳድደው ይታያል። ልምድ ሲቆይ ባህል ይሆንልና አንዳንዱ ደግሞ ዉሸት ልምዱ ስለሆነ እንዲሁ እንደሸመጠጠ ይኖራል ።ይሀኛው መቸም ቢሆን ከዚህ አዙሪት አይወጣም ከጥላው ጋር ዘላለም እንደተጣላ ይኖራል።እመራዋለሁ ከሚለው ህዝብ ፊት ከሚዋሽ መሪ እግዜብሔር ይጠብቀን። ዉሸታም ነፃነት የለዉም ያልኩት ለዚህ ነበር። አዲሱ የአሜሪካን መሪ አንቱ ያሰኛቸው የሃገራቸዉን ብቻ ሳይሆን የአለምን ፍቅር ያገኙት ሃገራቸዉን መዉደዳቸው ለህዝባቸው ስለማይውሹና በልባቸዉም በአካላቸዉም ፍፁም አሜሪካዊ መሆናቸዉና ከሁሉም በላይ ሃገር ይቅደም የሚል ራእይ ይዘው መነሳታቸው ነበር። በተለይም ጥቁር አሜሪካ ነጭ አሜሪካ ሰማያዊ አሜሪካ ሳንል ሁላችንም የተባበርን አሜሪካውያን ነን ያሉት የአሜሪካውያንን አንድነትና የወደፊት ተስፋን የሚያመላክት ብሩህና ቅንነት የተሞላው አረአያዊ ራእይ በመሆኑ ባላንጣዎቻቸዉን ሳይቀር ከጎናቸው ያሰለፈ ነበር። በተለይም አንዲት እዉቅ ሪፓብሊካን ሲናገሩ የኦባማ ቅንነትና ለዚህች ሃገር ያለው ብሩህ እይታ ልቆጣጠረው በማልችለው መልኩ ድጋፌን እንድቸራቸው አስገደደኝ ያሉት ይበቃል። ሁላችንም እንደታዘብነው በርካታ ሪፓብሊካን የሳቸዉን መመረጥ ደግፈዋል። ይህ ሁሉ የሆነው እኝህ መሪ ለህዝባቸው ግልፅ ሆነው በመቅረባቸው የህዝባቸዉን አመኔታ በማግኘታቸው ፍቅርንና ተስፋን በመለገሳቸው ነው ተቃዋሚዎቻቸዉን ዽል ያደረጉት። በተለይም ተቃዋሚዎቻቸው በሆነ ባልሆነ ስማቸዉን ሲያጠፉ እሳቸው ግን በበጎ መቅረባቸው ጥላቻን ሲያሳይዋቸዉ ነገርግን ፍቅርን ማሳየታቸው እጅግ እዉቅናን እያስገኘላቸው መጣ። ታዲያ ከዚህ በላይ ነብይነት ምን አለ! እኝህ ታዋቂ ሰው አሁን ሃገራቸው ካለችበት የምጣኔ ሃብት ዉድቀት ለማውጣት የሚያደርጉት ትግል ቢሳካላቸዉም ባይሳካላቸውም ህዝቡ እምብዛም ሊፈርድባቸው አይደፍርም ምክንያቱም በህዝባቸው ደም ዉስጥ ገብተዋልና ህዝባቸዉም እንደነብይ ቆጥርዋቸዋልና ነው። ዉሸት እጅግ እጅግ አፍራሽ ዉጤት አለው። ለምሳሌ ያህል በትዳር በተሳሰሩ ጥንዶች መሃል መተማመንና ሃቅ ይጠበቃል። ማንም ሊገምት እንደሚችለው ሚስት ባልዋን ባል ሚስቱን ከተዎሻሹ ነገር አበቃ ማለት ነው። የትዳርን መፍረስን ማስከተሉ አይቀርም። ታዲያ አንድ መሪ ህዝቡን ከዋሸ ምኑን ተዋሃደ ይባላል። ከሁሉ የሚያስፈራው ጉዳይኮ የገዛ ቤተሰቡን ዋሾ ከማድረግ አልፎ ትውልዱን በሙሉ በክሎ ማለፉ ግንዛቤ ዉስጥ መግባት ያለበት ነው። አንድ መሪ በአደባባይ የሚያሳይቸው ባህሪዎቹ ብቻ ሳይሆኑ በግል የሚያደርጋቸው የግል ድርጊቶቹ ሁሉ ተጽእኖ አላቸው። መቸም እኝህን ድንቅ መሪ አሁንም እንደነብይ መጥቀስ ሊኖርብኝ ነውና አንድ ሁነታን ልጥቀስ።በአሜሪካን የግብረገብነት(ethics) ተምዋጋች የነበሩ አንዲት ወይዘሮ የፕሬዘደንት ኦባማ የትምባሆ ጉዳይ አረአያነቱ አስከፊ ስለሚሆን ትንባሆ ማቆም እንዳለባቸው አበክረው የሚያስገነዝቡት ለወደፊቱና አሁን ላለው ለጋ ትዉልድ ሊኖረው የሚችለዉን አስከፊነት ግምት ዉስጥ በመክተት ነው። ሰዎች ነፃነት ማጣት መታሰር ወይንም መታገት ብቻ ይመስላቸውል። መታገት እንድያዉም የአካልን ነፃነት ብቻ ማሳጣቱ እንጅ ህሊናን አይረብሽም። ትልቁ የነጻነት ማጣት ግን ሳይታገቱ የሂሊና እስረኛ መሆን ይመስለኛል ታዲያ መሪዎቻችን ስለሚዋሹ አንደበታቸው ይተሳሰራል ይንተባተባሉ ሰዉነታቸው ይተሳሰራል በመጨረሻም የዋሹትን ህዝብ እንደጠላት ያዩታል። ንግግራቸው ሁሉ በቀልና ጥላቻ ቁጭትን ያዘለ ይሆናል። የተቀመጡበት የቆሙበት የተኙበት ያዩት ሁሉ ጠላት ይመስላቸዋል። በቁም ይባንናሉ ራእይ ያጣሉ ተስፋ ያሳጣሉ።
መቸም ነገርን ነገር ያነሳዋል በሚል በዚህች አምላክ በሰጠኝ እድሜ እኔ የታዘብኩትን ታዝባችሁ ከሆነ በሚል ነዉና እስቲ ወደመጣሁበት ታሪክ ልለፍ። የእናት ሆድ ዥንጉርጉር ነው ይባላልና እስቲ ይህች ምድር የወለደቻችዉን ሌሎችን በሃገራችን የተፈጠሩ መሪዎቻችንን እንመልከት ( ከዚህ ቀጥሎ የምጠቅሳቸው ስሞች አእምሮን ስለሚረብሹ አንባቢ ጥንቃቄ/readers discretion/እንዲያደርግ እመክራለሁ)። ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ መቸም እንደ ሂትለር ለወደፊት ስማቸው ትውልድ እንዳይጠቀመው ቢከለከል በታሪክ ባይነሳ እኛ የባነነዉን ያህል ትውልድ እንዳይረበሽ ይረዳል የሚል አምነት አለኝ። በሰለጠነው ሃገር መስፈርት ቢሆንማ ከዱር አራዊት ጋር በጥበቃ መቀመጥ የሚገባቸው ነበሩ ያዉም አራዊቱንም እንዳያዉኩ በልዩ ጥበቃ!!። እንደሰው ተፈጥሮ ነገርግን የሰዉነት ባህርይን ያጣ ከአዉሬ የሚለየው ምን አለ በሚል ነዉና። እንዲያውም ዛሬ ክፉ የተባለዉን አዉሬ ሰዎች አግባብተውት የአውሬነት ባህሪዉን ሲያላቅቁት እያየን ነው እንዲያዉም ሰልጥነው ሰዎች የሚያከናዉንዋቸዉን ሲፈፅሙ አይተናል። ዛሬ ሁላችን እንደምናየው ታሪክም በክፉ የጠቀሳቸው ጨካኞች ከፈፀምዋቸው ጭካኔዎች ዉስጥ እሳቸው ያላከናወንዋቸው ወይንም ያጎደልዋቸው አለ የሚለኝ ካለ ለኔም ለሌላውም ዜጋ ትልቅ ትምህርት ይሆናል። ወያኔ ከመግባቱ ቀደም አብረዋቸው ከነበሩት ከነ አብረሃም ያየህ ስለ ጭካኒያቸው ጥልቀት ሲባል የነበረዉን በጥንቃቄ አጢነነው ቢሆን ኖሮ! ደርግ እለት በእለት ከኔ የባሰ ጨካኝ ሊመጣ ነው እያለ ሲወተዉት ግንዛቤ የወሰድን ቢሆን ኖሮ ለዚህ ባልበቃን ነበር እንዲያው ለነገሩኮ ደርግ የገደለው አስከሬን አደባባይ ላይ ይገኝ ነበር። የነኝህ የሚደንቀው አስከሬኑን ይብሉት የት ያድርጉት ደብዛው ነው የሚጠፋው። የሚደንቀው ደግሞ ወያኔ እራሱ ገሎ አብሮ አዛኝ መስሎ አጣሪ ኮሚቴ መሰየሙ ነው። በተለይ በተለይ በጫካ ዉልዋቸው በሃሳብ ያልተግባባቸዉን ነፍሱ ሳታልፍ በህይዎት እንዳለ በመጥበሻ ጠብሰው ለሌላው መቀጣጫነት ያደርጉት ነበር የተባለው ሲገርመን ዛሬ ደግሞ ለጉድ ያስቀመጠን የነሱ ግፍ ሰለባ የነበሩ አዛውንት ልብሴን አስወልቀው እንደዶሮ በእሳት ለበለቡኝ ብለው አረፉት። አስቲ ጊዜ ጥሩ ነውና ገና ብዙ ያሰማናል! በተለይ እጅግ ቱባ የነበሩ ዛሬ እነሱም የወያኔ ሰለባ ከሆኑት አይንህን ለአፈር ብለው ካሉ ከእነ አቶ ስዬ አብረሃምና ከእነ አቶ ገብሩ አስራት አንዲሁም ዳግም የመወልድ እድል ከገጠማቸዉና ብዙም ካላሉን ከአቶ ታምራት ለአይኔ ከጫካ ዉልዎቸውና ሃገር ቤት ከገቡ በህዋላ ከተፈፀሙ የግፍ ማህደሮች ትንሽ ካካፈሉን በሚል ነው።
በተለይ እጅግ ከሚደንቀኝ ነገር መቸም ዉሽትን በተመለከተ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አእምሮ እየሆነ ያለውን ነገርና ጭንቀት ሊገባኝ ቢችልም እንደሳቸው አያርገኝና ከውሸታቸው ብዛት በአካል ካገትዋት ነገርግን ህሊናዋ ሃቅን በመፈፀምዋ ነፃነትዋን ይዛ በወህኒ የእድሜ ልክ ከተፈረደባት ዉድ እህታችን ይልቅ እሳቸው ነፃነት አተው መኖራቸውን ያለመገንዘባቸው ነው። አንዳንዴ ከሚደንቀኝ ነገር እንዴ! እኝህ ሰው ልጆች ወልደዋል፡አይደል እንዴ!። ለልጆቻቸው የወደፊት እጣ ፈንታ ምንም ደንታ የላቸዉም እንዴ እያልኩ እንደሞኝ አስብና አይ ስግብግብ ፍቅርን አያዉቅም ለቤተሰቡ ደንታ የለዉም በሚል መለስ እላለሁ። በእውነት ለመናገር አትታዘቡኝና የልጆቻቸው ጉዳይ እጅግ ያስጨንቀኛል። ክፉና ደግ ጊዜ ይመጣል ታድያ ልጆቻቸውን ከዚሁ ካሰቃዩት ህዝብ ጋር ሊያኖርዋቸው እንደማያስቡ ግን ትንሽ እገነዘባለሁ። ደግሞ በስደትም ያስቸግራል። ዛሬ በዉጭው አለም የተበተነው ወገን ሁሉ የሳቸው ግፍ ሰለባ ነው። ለሳቸውም ሆነ ለቤተሰባቸው ፈገግታ እንደማይቸራቸው መገመት አያስቸግርም። ግን ታሪክ ደጋግሞ ያሳየን ሁኔታ ደግሞ አምባገነኖች በቀይ ምንጣፍ በክብር ስለማይንግሱ እንደዉሻ ተቀጥቅጠውና ተዋርደው እንደሚወርዱ ነዉና ይሀንን መርጠው ሊሆን ይችላል። ግራ የገባ ነገር! ህሊና የቸረው ሰው ይቅርና እንሰሳም ቢሆን ማረፊያውን ያስባል። እንዴ! እኝህ ሰው ምን እያሰቡ ነው ያንን ሁሉ ደም ሲያፈሱ ያ ሁሉ ደም እየጮሀ እንዴት ነው እንቅልፍ የሚወስዳቸው። የፈጸሙት ግፍና የሚዋሹት ዉሸት ብዛት ጸጉራቸውን አረገፈው። የገደሉትን ገለው የቀረውን በረሃብ እየቀጡት ነው።ለመሆኑ ይህ ህዝብ ምን አጥፍቶ ነው ለዚህ መከራ የተዳረገው! የሃገሪቱን ሃብትና ሌሎችንም ለምእራባውያን ተላልከው ያገኙት እርጥባን ሳይቀር መዘበሩት። ነገር ግን አንድ ያልተገነዘቡት ነገር አለ ስግብግብነት ነው እንጂ በርካታ መሪዎች የዘረፉትን ገንዘብ አንዲት ሳንቲም እንኩዋን ለመቅመስ እድል ሳያገኙ ነው የጠፉት። ሞቡቱ ሴሴሴኮር ሲሞቱ በስማቸው $220.000.000,00 ዶልላር ነበራቸው ሳንቲም ሳይጠቀሙ ነው ጥለዉት ያለፉት ይህንን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሊያስተዉሉ ይገባ ነበር። በሳቸው እድሜ የሆነ ታሪክ ነው በሚስታቸዉና በዘምዶቻቸው ስም በዉጭ ባንክ ያካበቱትን ገንዘብ የዚያ የደሃ ህዝብ ንብረት ነበር። ዛሬ ህዝቡ እሳቸው በህይወት እያሉ ቢጠቀምበት በሚል ነው።ምክንያቱም ገንዘቡን በአደራ ያስቀመጡባቸው የውጭ ባንኮች አንድም የአፍሪካ መሪ በህይወት መጥቶ ገንዘቡን ለመጠየቅ እድል እንደማያገኝ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ደንበኞቻቸው ሁሉ በአብዛኛው የአፍሪቃ መሪዎች ናቸው። ገንዘቡም ጠያቂ አጥቶ ባክኖ ይቀራል ።ይህንን ገንዘብ እሳቸዉም ቢሆኑ አይጠቀሙበትም። ሳይጠቀሙ እንደሚቀሩ ይታዘቡት እንዳልል ለመታዘብ የሚያስችላቸውን እድል የሚያገኙ አልመሰለኝም። ምን ጉድ በኛ ላይ እንደወደቀ አላውቅም። አንድ ቀን በሚገዙት ህዝብ ፊት ወጥተው አጃቸውን ሳያውለበልቡ፡ አንድ ቀን በአደባባይ ወጥተው ተስፋ የሚሰጥ ንግግር ሳይቸሩ፡ ከሁሉም ከሁሉም አንድ ቀን እንኩዋን ስለዚያች ሃገር ታሪክ ስለ ጀግኖች አባቶቻችን ገድል በአደባባይ ወጥተው ሳይመሰክሩ፡ አንድ ቀን እንኩዋን በየጦር ግንባሩ የማገዱትን ሰራዊት ቤተሰብ ሳያጽናኑ፡ አንድ ቀን እንክዋን በከንቱ የማገዱትን ሰራዊት አስከሬን አስልቅመው በክብር ሳያስቀብሩ፡ አንድ ቀን እንኩዋን በህዝብ በአል ተካፍለው ከሚገዙት ህዝብ ጋር የእጅ ሰላምታ ሳይለዋወጡ፡ አንዲት ቀን እንኩዋን እውነት ሳይናገሩ፡ በተመላለሱባቸው ጎዳናዎች ሁሉ አንድ ቀን እንኩዋን እልል ሳይባልላቸው ይሀ ግፈኛ እንደተባሉ፡ አንድ ቀን የመታሰብያ ፊርማ (Autograph) ለህጻናትና ሆነ ለአዋቂ ሳያኖሩ፡ አንድ ቀን እንኩዋን ፈገግታ ሳናይባቸው፡ አንድ ቀን እንኩዋን በፍቅር ሳይናገሩ፡ አንድ ቀን እንኩዋን ህዝብ ወጥቶ በደስታ ሸኝቶ በሰላም ይመልሶት ሳይል፡ አንድ ቀን እንኩዋን ይህ ስህተት ነበር ሳይሉ፡ አንድ ቀን እንኩዋን ወደ ውጭ ሃገር ለስራም ሆነ ለልመና መጥተው በፊትለፊት ገብተው በፊትለፊት ሳይወጡ በጉዋሮ በር በጸጥታ አስከባሪዎች ተገንዘው እንደተጫኑ፡ አንድ ቀን እንኩዋን ዉጭ ያለ ኢትዮጵያዊ ተቀብልዎ ሳይሸኞ!!!የሃገሪቱን ገንዘብ ሲመዘብሩና ደም እንዳፈሰሱ በፓርላማዎ በከብት ርቢ ብቻ ተዎጥረው የሚፈይድ ስራ ሳይፈጽሙ ግዜዎ አለቀ።ታሪክ ነው! ለመሆኑ እኝህ ሰው ህዝቡን ሲዋሹት እንደናቁት አላወቁት ይሆን፡ ህዝቡ ላይ ሲያሾፉ ህዝቡም እያሾባቸው እንደሆን አልተገነዘቡት ይሆን።እንዲያው ህዝቡ እንዴት እንደጠላቸው አላወቁት ይሆን። በጣም የሚገርመው ነገር የትግራይን ህዝብ እንደዛሬው ሌላውን የሃገሪቱን ክፍል ከመውረራቸው በፊት ሲያሰቃዩት እንዳልነበር ሁሉ ዛሬ ያንኑ ህዝብ እኔ ከጠፋሁ ትጠፋለህ እያሉ መሳሪያ ሊያደርጉት መሞከራቸዉና ከሌላው ወገኑ ሊለዩት መጣራቸው ነው። የትግራይ ህዝብ ግን አስተዋይና አርቆ አሳቢ እንደለሎቹ ወገንቹ ፍዳውን እየቆጠረ እንደሆነ ሌላው ወገኑ ተረድቶታል እንዲያዉም እንደሆነው ከሆነ ወያኔ ሃገሪቱን ከመቆጣጠሩ በፊት የትግራይን ህዝብ በአስከፊ ሲያሰቃየው እንደነበር የግፉ ሰለባ የነበሩ እያጫወቱን ነው። ወያኔ ለትግራይ ህዝብ ምኑም አይደለም።
ዛሬ አለም እየተለወጠች እነኚህን የመሳሰሉ መሪዎች የአፍሪቃ የመጨረሻዎቹ አምባገነኖች ከሚባለው ዘርፍ ገብተዋል። በዚህች ተመዝብራ በማታልቅና ተገፍቶ ባልጠፋዉና ፍዳውን በሚያየው ህዝብ ስቃይና በሃገራችን ጉዳይ ድርሻ አለን የምንል ድምፃችንን አንዴ ጎላ አንዴ ደግሞ አለዝበን በየአቅጣጫው የምናሰማ፡ ሁላችንም አነሰም በዛም አጠገበም አላጠገበም የምናደርገዉን ሁሉ አድርገናል።የትግላችንን ዉጤት ሁላችንም ስለምናውቀው ብዙም የምለው የለኝም።በሃገራችን በህዝባችን ላይ እየተፈጸመ ባለው ግፍ የቀትታ ሰለባዎች ባለምሆናችንና ርቀን በመኖራችን ስንቶቻችን ወላፈኑ እየተሰማን እንደሆነ ለመገመት ያስቸግረኛል። ዛሬ የጠላቶቻችን ተጽእኖ ሳይኖርብን ግን እኛው በፈጠርነው ዉስጣዊና መሰረተቢስ ችግሮች ተቆላልፈናል። ዛሬ በያለንበት ከተማ ትናንሽ አጅንዳዎች ቀስፈውን ከዚህ አዙሪት የሚያወጣንን ነብይ ፍለጋ እየባዘንን ነው።ስንቶቻችን ግፍና መከራ የህዝባችን የእለት እለት ህይዎቱ ሆኖ እንዳለ ምን ያህል የተገነዘብን ስለመሆናችን ለመናገር ብዙም ማስረጃ ያንሰኛል።ዛሬ ህዝባችን በቁስሉና በጉሮሮው እንጨት እየሸነቆሩበት እያሰቃዩት ነው። በቀን ሶስት ጊዜ እንደሚበላ ከገዢዉቹ የተሰጠዉን ተስፋ ቀርቶበት ግን በሰላም አደባባይ ወጥቶ ወደስራ ሳይሆን ግን ቤተሰቡን አቅምሶ የሚያሳድር ፍርፋሪ ለቃቅሞ የመግባት እድል ለማግኘት የወያኔ አባልነት መታወቂያ
እንደ መስፈርት ቀርቦለታል። ትንሽ ኖሮት ቀጥሮ ለወገኑ የስራመስክ ሊከፍት አቅም ያለው ባለሃብት ቢኖር እሱንም ተወርዋሪና ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሆነ ከመንግስት መዋቅር ዉጭ የሆነ የገዳይ ቡድን እንደዶሮ በጠራራ ፀሓይ እያነቀ መጣል የእለት እለት ክንዉን ሆንዋል። እራሳቸዉን ገደሉ፡ ሞተው ተገኙ የተባሉ በወያኔ ግፈኞች የተገደሉ መኖራቸው የምናየዉና የምንሰማው ነው ይህንን የመሰለ ግፍ እያየን ግን መላ ለመሻት እንዳንችል የሚያግባባንና፡ ተብትቦ ከያዘን ጥቃቅን አጀንዳ የሚያላቅቀን ጀግና አጣን።
ምን ነካን!
ወደድንም ጠላንም በህዝባችን ላይ ለሚደርሰው ሰቆቃ የኛ አሻራ ያለመኖሩን ለመመስከር ቃል ያንሰኛል። መቻቻልና ትእግስት፡ ጎደለን። መደማምጥ አቃተን በጠላቶቻችን ላይ የጠላናቸው ጉድፎች በኛ ላይ እየታዩ ነው።በገዛ ሃገራችን መብት አጣን፡ የመሰባሰብና ፈቃዳችችንን የመግልፅ ነፃነት ተነፈግን ብለን ዉቅያኖስ ዘልቀን ነፃነት ተሰፍሮ በማያልቅበት ቦታ ከደረስን በህዋላ፡ ለዚህ መከራ የዳረጉንን ነቀርሳዎች ለመንቀል መላ ማፈላለግ ሲጠበቅብን በሌላ አጀንዳ ተወጠርን። ዛሬ ባለንበት የዉጭ አለም ኢትዮጵያውያን በሚያመልኩባቸው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናት ያለው ትርምስና ከዚሁ አተካራ ጋር በተያያዘ ዉሎዋቸውን በየፍርድ ቤቱ ያደረጉ ወገኖቻችንን ቁጥርና ለጠበቃ የባከነዉን ገንዘብ ሁላችንም በያለንበት እየታዘብን ነው። ይህ ችግር በአንድና በሁለት ቦታ ቢሆን የአጋጣሚ ነው ቢባል ሊያግባባን ይችላል። ግን ችግሩ በመላው አለም እንደወረርሽኝ ተዛምትዋል። እንደ ገማቾች ከሆነ በአንድ ከተማ ቢቻ ለሚነሳ ጭቕጭቅ እስከ ሁለት መቶ ሺህ ያህል ብር የምጽዋት ገንዘብ ለጠበቃ ይከፈላል።ታዲያ ይህ ክርስትና ሃይማኖትን ከግራኝ መሃመድ ወረራ ለመከላከል ይሆን ወይንስ ዩዲት ጉዲት መጣች ነው የሚባለው። በዚህ አተካራ ተተብትበው የሚናቆሩ ወገኖቻችን ወደ ዋናዉና ከሃገር ባወጣን ጉዳይ ላይ አተኩረው የዚህን ያህል ጥረት ቢያደርጉ ምንኛ የተባበረ ሃይል ፈጥረን ህዝባችንን የማዳን መስዋትነት በከፈልን ነበር። ከሁሉ የሚደንቀው ግን ለዚህም ተከሳሽ ወያኔ መሆኑ ነው። ጎበዝ በንድ ነገር ብንግባባ ደስ ይለኛል። በዚህ አይነቱ ሰይጣናዊ ስራ የወያኔ አሻራ አይጠፋበትም ምናልባት ከሆነ አንድ ነገር ነው። የለም በእርግጥ የወያኔ እጅ ነው ደግሞ ሌላ ነገር ነው። አንድም እንኩዋን ጥርት ያለ መረጃ ሊያቀርብ የቻለ የለም። ወያኔን ባህር አሻግረን ያመጣነው እኛው ነን ወያኔ ከሃገርቤት ዉጭ አማትሮ ሊይይ የሚችል እይታም አልነበረዉም።በየትኛውም ቤተክርስትያን የአልባንያ ህወሃታዊ ኮሚኒዝም ሲሰበክ አልሰማንም። በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ ብፁአን አባቶች እነኝህን ወገኖች ህሽ ሊልዋቸዉና ወደ ዋናው አጀንዳችን ልንመለስ ይገባል። አፄ ሚኒሊክ ከእምነታቸው ፅናት የተነሳ ጠላትን ድል ነሱ። የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን በዚያን ወቅት የነበራትን ሚና ማስታወስ ይበቃል።ጦርነቱ የነፃነት የወገን ማዳን ጦርነት እንጅ የህይማኖት አልነበረም። አቅጣችንን ስተን የሌላውንም አቅጣቻ እንዳናስት ያስፈራኛል።የዚህ ማለቂያ ለሌለው አተካራ አሁንም ተጠቃሚው ያው ጠላት መሆኑን መገንዘብ ይኖርብናል። ምንም ይሁን ምን የትግላችንን አቅጣጫ ልንስት አይገባንም። የጠላትም እጅ አለበት እንኩዋን ቢባል ወያኔን ከተንሰራፋበትና ከዚያች ምድር ከስሩ መንግሎ መጣል ሊኖርብን ነው ይህም የተባበረና የተቀናጀ አንድነታችንን ይጠይቃል።
አሁንም እጅግ የጎዳን እጅግ በከፋ ያቆሳሰለን የሰዎችን ስም ማጥፋት ነው። በሃሳብ ያልጣመንን ሁሉ ወደ ጠላት ጎራ እየገፋነው ነው። ይህ አይነቱ ተግባር ደግሞ እጅግ ጎጂ ነው። ወያኔ ሃገርቤት ግራ ሲገባው ሰዎችን ከአንዱ ጎራ በመመደብ የሚያዋክብብበት አንዱ መሳርያ ነው። ትግላችንኮ የሃስብ ነፃነትን ማጎልበት ነው። ትግላችንኮ ሰዎች በነፃነት የመሰላቸውን ሃስብ እንዲሰጡ ነበር። የሰዎች ሃሳብ ላይጥመን ሊጥመን ይችላል ይህ ሌላ ታሪክ ነው ነገር ግን ከወያነ ጎራ ሊያስመድባቸው የሚያስችል መስፈርትም አይደለም። በዚሁ ሰለባ ሆነው ከትግሉ ጎራ የተለዩንና በየቤታቸው የተከተቱ ወግኖቻችንን ብዛት ቤት ይቁጠረው። ትንሽ ማሰላሰል ሊኖርብን ነው። ሰዎችን ከጠላት ጎራ ስንመድብ እጅግ በርካታ ማስረጃዎችን ልንሰበስብ ይገባል። ሰዉን ሁሉ ከትግል ሜዳ አባረን ማንን ይዘን ልንፋለም እንዳሰብን አልገባኝም። ያለንበት ጊዜ እጅግ የከፋ ነው። ዛሬ ከመቸዉም በበለጠ ልንተባበር የሚሻን ወቅት። የህዝባችንን መከራ የምናበዛዉም የምናሳጥረዉም እኛው ነን። ለወያኔም እድሜ የጨመርንለት እኛው ነን እንጅ ወያኔ ልዩ ጥበብ ኖሮት አይደለም። አንዳችን በአንዳችን መተላለፊያ ላይ የቀበርነውን ፈንጂ ማክሽፍ ሊኖርብን ነው። እያንዳዳችን ከዚህ በፊት ያለፍንባቸውን የፖለቲካ ክንዎኖች እያነሳን አንነታረክ ለወደፊቱ ጉዝዋችን የሚፈይደው አንዳችም ጥቅም እንደሌለው ማስተዋል ይጠበቅብናል። ያለፈን ታሪክ ለማውራት ጊዜው ረፍድዋል ወይንም ጊዘዉም ያለን አልመሰለኝም። አጀንዳዎቻችንና ኢላማዎቻችንን አየቀነስን መምጣት ግድ ሊሆን ነው። ጠላቶቻችን ጊዚያችንን ለመጋራት የሚያጠምዱት ወጥመድ ነው። ከዚህ ቀደም በትግል ያለፉ ሰማእታት አስክሬን በሰላም ካረፈበት እያወጡ ደጋግመን እንድናለቅስ ሲኮረኩሩን እንደነበር አንዘነጋም። ዳሩ ግን ወያኔ የቀበራቸውን ሰማእታት አስከሬን አላሳየንም። ያለፈን ለታሪክ ፀሃፊ እንተወው። ለክንዉኖቻችን ቅደም ተከተል ብንሰጥ ጥበብ ነው።ትኩረታችንና ትግላችን ዛሬ ለህዝባችን ተስፋ ልንሆነው እንችላለን ወይንስ አንችልም ነው። ሁለት ነገሮች እናስተውል፡ ትግሉን ተጋግዘን በምክክር ልናራምድ የምንፈልግ ካለንና ቃል ልንገባባ ከቻልን እሰየው ነው። የለም የተለየ አላማና የሚፈይድ መላ ሳንይዝ የሰዎችን ጥረት እያረከስንና ስም እያጠፉ መኖር ሌላ ነገር ነው። የጎዳንም የበታተነንም ይሀው ችግር ነው። ትግሉን ማገዝ ካልቻንና ልንተባበር ካልፈቀድን ለሌሎች ደንቃራ ባንሆን ጥሩ ነው። ከኛ ይሻልም ኣይሻልም እየተነቃነቁ ነውና ገለል ብንልላቸውና አፋችንን ሰብስበን ብንቀመጥ ይህም ከትልቅ እርዳታ ይቆጠራል።ማንም ይሁን ማን ይነስም ይብዛም ትግሉ ወያኔን ለመጣል እስከሆነ ድረስ የተቀደሰ ነው።በአንድነት ልንሰባሰብና የተቀናጀ ግፊት ማድረግ ካልቻልን ያለው አማርጭ ይሀው ብቻ ነው። ያሰብነውን አላማ በጥናትና በብልህነት ሳናከናዉን ቀርተን ሳይሳካልን ሲቀር በሌላው አናመካኝ የኛ ድክመት የኛው ነው። ሁላችንም ለሰራነው ስህተት ሃላፊነት መውሰድ ሊኖርብን ነው።አንዳችን በአንዳችን ማላከኩ ያብቃ ስለኛ ብቃት ማረጋገጫ የለንምና ነው። ፖለቲካ ጥበብን ብልህነትንና ልምድን ይጠይቃል። አንዳችን የሌለን ሌሎቻችን ሊኖረን ስለሚችል ከመወቃቀሱ መመካከሩ ይበጃል። አኔ ያልኩት ብቻ የኔ ብቻ ማለትን የመሰለ ስግብግብነት የለም። በጠላቶቻችን ላይ የጠላነው ነገር በእኛ አንዲታይ መፍቀድ አይኖርብንም። መደማመጥና የተሻለ ዘዴ ካለ ያንን ለመዋሃድ እራስን ፈጥነን ማዘጋጀትያስፈልጋል።የድርጅት ፍቅርና የግል ዝና ሊገለን ነው። ማንኛችንም ብንሆን ተለያይተን በግል የምንፈጥረው ተአምር እንደሌሌ መገንዘብ ሊኖርብን ነው። ከራስ ዝና ፍለጋና ከድርጅት ፍቅር ተላቀን ለሚመጣ አዲስ ሃስብና መላን ለመቀበል መፍጠን አለብን እያንዳንድዋን ሰአት በአግባቡ በመካከርና በመደማመጥ ብናባክናት ለህዝባችን ትልቅ ተስፋ ነው። ባለማስተዋል ወይንም በእይታ ማነስ ምክኒያት ትግሉን የረዱን መስለን አጋር ሊሆኑን የሚችሉ ሃይሎችን ስም የምንበክል ወይንም በወያኔነት የምንፈርጅ ካለን መለያውን ዜዴ እናፈላልግ። ወያኔ ማነው ወያኔ ምን ይመስላል መሰረታዊ አውቀት ነው። እንዲያው ዝም ብለን በየመሸታ ቤቱ በተፈጠረ ግጭት ምክንያት ከጎናችን ሊቆም የሚችል ሃይል ለማሰባሰብ በሚል ስግብግብና ሃላፊነት በጎደለው መንገድ የሰዎችን ስም ማጥፋት ከባድ ወንጀል ነው።
ብዙ ተባባልን እኔም ከዚህ ጉድፍ የፀዳሁ ነኝ ለማለት ይችግረኛል እንዲያው እንተራረም በሚል እንጂ። በዚህ ፅሁፍ በተለይ ያነጣጠርኩበት ግለሰብ ወይንም ቡድን የለም። ስህተት ካለብኝ በማንኛውም መንገድ ልታረም ተዘጋጅቻለሁ። በመጨረሻም ታሪክ ጸሃፊ ይኖራል ይህንንም በህዝባችን ላይ ያለውን ሰቆቃ መጥቀሱ አይቀርም። ለኔ የጨነቀኝ ግን ስለነዚህ ጉዶች ምኑ ተብሎ ምኑ እንደሚቀር ለማወቅ ያስቸግረኛል። ዛሬ የኛ ዉሳኔና ቃል ኪዳን ከመቸዉም በበለጠ ይጠበቃል። ዛሬ የኛ ፈጥነን መዋሃድና መተባበር በህዝባችን ያለውን መከራና ፍዳ በፍጥነት ለማስወገድ ይረዳናል። አንዳችን በአንዳችን ላይ ወጥመድ አናጥምድ። ኢትዮጵያ እናታችን ከሁሉም በላይ ናትና እስዋን እናስቀድም ሃገር ይቅደም የሚል አስተሳሰብ የወቅቱ መፈክር ይመስለኛል። ውድ ወገናችንንም አምላክ ይጠብቀው።



ጸሀፊው ለማስተላለፍ የፈለጉት ሃሳብ ወቅታዊና ሁሉም ካለፈው ስህተቱ በመማር ለዲሞክራሲ ለህግ የበላይነትና ሁሉም እኩል የሆነባት ኢትዮዽያን ለመገንባት በጋራ እንቁም::ከዚህ በተጨማሪ ጸሃፊው እንደጠቀሱት የወያኔ ዘመን ልክ እንደዘመነ ግራኝ የጨለማው ዘመን ተብሎ እንዲዘለል ማድረግና ትውልድ ሁሉ ለመጥራት እንዲጠየፈው ማድረግ ይኖርብናል እላለው::
እግዛብህር ይስትህ ይህንኑ መስማት ተስኖናል. በዚህ በምኖርብት washington DC አካባቢ የራዲዮ ታቢአይዎች እንዲሁ የነሱን ሃሳብ የማይደእግፈወን ሲሳደቡ መልስው ደሞ ስው ለምን አይሰማንም እያሉ ሲበሳች ይሰማሉ. ስድብ አኩሙና ተባበሩ. ታስተላላችህ ብዙ እውከት አላችህ ግን ምን ዋጋ አለው. ስድብ እና መናኮር ሰለችህን ብካና
የደም- ዕዳ
ትናንት፡ሳይሆን፡ከጥንቱ፤
ለኦሮሞ፡ነጻ-መብቱ፤
ግንባራቸውን፡ሳይፈቱ፤
ሲታገሉ፡ሲሟገቱ፤
ውድ፡ልጆቹ፡ሲሞቱ፤
ለስልጣን፡ለደሞዝ፣
ኦሮሞን፡የከዳ፤
ባንዳ፡ሆኖ፡ይሞታል፣
በሙታን፡ደም-ዕዳ።
ዛሬም፡በቀን-ጥላ፣
ከርሱን፡እየሞላ።
ልቡን፡ያሳበጠ፤
የግፍ-ደም፡ያማጠ።
ሕጉን፡እየጣሰ፣
ደም፡እያፋሰሰ፤
ባንዳ፡ሆኖ፡ዛሬም፣
ሕዝብን፡የሚከዳ፤
ነገ፡ይፋረደዋል፣
የሙታን፡ደም-ዕዳ።
ባንዳ፡እስኪ፡ቁጠሩ፤
ከሹሞች፡ጀምሩ።
ቀበሌና፡ፖሊስ፣
በቀደም፡ሲሰሩ፤
“ኦሮሞ፡ጠባብ፡ነው”፤
ብለው፡ያስተማሩ።
ወያኔ፡የጠላውን፣
ሌሊት፡እያስጠሩ፤
ያንን፡አስገድለው፣
ይሄን፡ያሳሰሩ፤
ዛሬ፡ግን፡ተባረው፣
በረንዳ፡የሚያድሩ፤
አስተውሏቸው፡አሉ፣
እነማን፡ነበሩ?
ለሥልጣን፡ለደሞዝ፣
ሕዝብን፡የሚከዳ፤
በገዛ-እጁ፡እንዲሞት፣
ደሙ፡እየተቀዳ፤
ባንዳነቱ፡ይጋለጥ፣
በሙታን፡ደም-እዳ።
“ቢኑንሲ፡ነመኛቱ፡ሰገዳን፡ነመሂንዲሱ።”