አሁን ካልተነሳን መቼ ? የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ! – አወደ እትም 24

February 26th, 2009 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

እኛ ካልተነሳን ማን ? አሁን ካልተነሳን መቼ ?

በሚሊዮን የምንቆጠር ኢትዮጵያዉያን የምንወዳትን አገራችን እየተውን በስደቱ አለም እየኖርን ስንገኝ አብዛኞቻችን ለስደት የተዳረግነዉ በመልካም አስተዳደር ጉድለትና በኢኮኖሚ ችግር ነዉ።

ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ በአገሩ ሰላምና ዲሞክራሲ ቢኖር ኖሮ መሰደድን አይመርጥም ነበር። የሰላምና የዲሞክራሲ አበባ ፈክቶ ኢትዮጵያ በፍቅርና በአንድነት የታነጸች አገር እንድትሆን የማይናፍቅና የማይመኝ ማንም ኢትዮጵያዊ የለም። የሁላችንም አላማና ግብ በዘር በኃይማኖት በጾታና በመደብ ያልተከፋፈለች፣ ሕግ የበላይ የሆነባትና የሰዉ ልጅ እንደስዕብናዉ የሚከበርባት አንዲት ኢትዮጵያን ማየት ነዉ።

ይች ሁላችንም የምንመኛት ኢትዮጵያ በቀላሉ፣ በጥቂቶች ጥረት ብቻ፣ ወይም በዝምታና በምኞችት አትገኝም። ይች ኢትዮጵያ የመለስ ዜናዊም ስጦታ አይደለችም።

ይችን ኢትዮጵያ ለማግኘት መስዋዕትነት መከፈል አለበት ። ይች ኢትዮጵያ እንድትኖር የማይፈልጉና ጥቅማቸዉ የሚነካባቸዉ ጥቂቶች፣ እኛ እንዳንቀሰቃሰ ተስፋ እንድቆርጥና እንድንከፋፈል ለማድርግ ሌትህና ቀን መስራታቸዉ አይቀሬ ስለሆነ የምንፈልጋትን ኢትዮጵያ ለማየት የነዚህን እኩይ ኃይላት ደባ ማክሸፍን ይጠይቃል።

ስለዚህ እያንዳንዳች ካቀረቀርንበት ቀና ብለን፣ የድርሻችንን ለማበርከት መዘጋጀት ይኖርብናል። እህታችን ሽብሬ ደሳለኝ እንዲሁም በሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን በየክልሉ ከአጋዚ ጦር በተተኮሰ ጥይት ወድቀዋል። እህታችን ብርቱካን ሚደቅሳ እኛ ሁላችንም ልናያት የምንፈልጋትን ኢትዮጵያ ለማየት በመታገሏና «እምቢ ለባርነት» በማለቷ ከአምሳ ቀናት በላይ በግፍ በጨለማ ቤት ዉስጥ ከጠበቃዋ ጋር ሁሉ ሳይቀር እንዳትገናኝ ተከልክላ፣ ቶርቸር እየተደረገች ነዉ። ብዙ ኢትዮጵያዉያን ሕይወታቸው እየጠፋ፣ እየታሰሩ እየተደበደቡ ትዕግስት አስጨራሽ ትግል እያደረጉ ባሉበት ሁኔታ እኛ እጆቻችንን አጣምረን የምንቀመጥበት ጊዜ አይደለም።

በዉጭ አገር የምንኖር ኢትዮጵያዉያን በጥቃቅን ነገራት እግሮቻችን ተይዘዉ መጓዝ የነበረብንን ያህል አለመጓዛችን የታወቀ ቢሆንም ካለፉት ስህተቶች ተምረን በጋራ ከሰራን በወያኔ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማምጣት እንደምንችል አስረግጠን ማወቅ አለብን። በዉጭ አገር የምንኖር ኢትዮጵያ ትልቅ ኃያል አለን።

ሰላሳ በመቶ የዉጭ ምንዛሪ ወያኔ የሚያገኘዉ እኛ ዉጭ አገር የምንኖር ኢትዮጵያዉያን ከዉጭ ከምንልከዉ ዶላር ሲሆን አርባ በመቶ ደግሞ በልመና ከምዕራባዉያን አገራት የሚገኝ ነዉ። ስለዚህ ወያኔ ለግፍ አገዛዙ ከሚጠቀምበት ሰባ በመቶዉ የዉጭ ምንዛሪ ላይ እኛ በውጭ አገር የምንኖር ኢትዮጵያን ትልቅ ጫና ማድረግ እንደምንችል በግልጽ የሚያሳይ ነዉ።

እንግዲህ ይህን ያህል ኃይል እንዳለን ካወቅን ትንሽም ትሁን ትልቅ የድርሻችንን ከማበርከት ወደኋላ ማለት የለብንም። ከአቅማችን በላይ አይደለም። የአቅማችንንና የቻልነዉ በታማኝነትና ሳንጠይቅ ለአገራችን ለማበርከት መዘጋጀት ይኖርብናል። ስለምንስ አገራችን በተመለከተ እንለመናለን ? ስለምንስ እኛ ተኝተን ሌሎች እንዲሰሩ እንፈልጋለን ?

ዉድ ኢትዮጵያዉያን ልናበረክተዉ ከምንችላቸዉ በርካታ ነገራት አንዱና እጅግ በጣም ቀላሉ በሰላማዊ ስለፍ ተቃዉሞ ማሰማት ነዉ። ሰላማዊ ሰልፍ በርካታ ጥቅሞች አሉት። ከነዚህም መካከል በዋናነት የሚጠቀሱ ሁለቱ የሚከተሉት ናቸዉ፡

• በዉጭ አገር የምንኖር ኢትዮጵያዊያን በአገራችን ላለው ሕዝብ ድምጽ ሆነን፣ ሲደማዉ ደምቶን፣ ሲያመዉ አሞን ተቃዉሞ ስናሰማ በኢትዮጵያ ላለዉ ወገናችን ትልቅ የሞራል ድጋፍ እንሆነዋለን። ሕዝባችንን ለማበረታት ሲባል ብቻ ሌላዉ ቢቀር እንኳን ሰልፍ መዉጣት ያስፈልጋል።

• በሁለተኛነት የሚጠቀሰዉ የሰላምዊ ሰልፍ ጥቅም ወያኔ የምዕራባዉያንን ድጋፍ እንዲያጣ ስለሚረዳ ነዉ። ወያኔ ገንዘብ ለማግኘተ ራሱን እንደዲሞክራትና ሕግ አክባሪ አደርጎ የሚያቀርበዉን ማጭበርበር በማጋለጥ የበለጠ እርቃኑ እንዲወጣ ማድረግ ያስፈልጋል።

በተለይም ሰልፎች በተደጋጋሚ ከተደረጉና በርካታ ሕዝብ ከተገኘ መንግስታት የሚያራምዱትን ፖሊሲዎች እንዲመረምሩ የማድረግ ትልቅ አቅም አላቸዉ።

በአሜሪካን በቅርብ ስልጣን የጨበጡት ፕሮዜዳንት ባራክ ኦባማ የሰብዓዊ መብትን ከሚጥሱ፣ ሕግን ከሚረግጡና በሙስና ከተዘፈቁ ጋር አሜሪካ ዉል እንደማይኖራት በአዳባባይ ተናግረዋል። ወያኔ እንደለመደዉ መልኩን ቀይሮ እራሱን በኦባማ ፊት እንደ መልዓክ ለማቅረብ እየተፍጨረጨረ ባለበት ጊዜ እኛ ዝም ብለን ከተቀመጥን በቀላሉ የኦባማ አስተዳደር ባለሥልጣናትን ወደ እነርሱ ሊያመጡ እንደሚችሉ መዘንጋት የለብንም። ስለዚህ እኛ ኢትዮጵያዉያን የኦባማ አስተዳደር የሕዝባችንን ብሶት እንዲያዉቅ የማድረግ አገራዊ ግዴታ አለብን።

በዚህ ምክንያት ከማርች 2 እስከ ማርች 9 2009 ባለዉ ሳምንት ዉስጥ በተለያዩ የአለም አቀፍ ከተሞች የአንድነት ድጋፍ ማህበራት ከኢሕአፓ ዲሞክራሲያዊ፣ ከሕብረት፣ ከኢትዮጵያ አገራዊ ጉባዔ፣ ከአዲሲቷ ኢትዮጵያ ሶሊዳሪቲ ንቅናቄ፣ ከኦሮሞ ተማሪዎች ሕብረትና ከጋሻ ኢትዮጵያ እንዲሁም ሌሌሎች የሲቪክና የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር በመሆን ሰላማዊ ሰልፍ ጠርተዋል።

በነዚህ ሰልፎች ኢትዮጵያዊያን የሆንን ሁሉ ተገኝተን የዜግነት ግዴታችንን እንድንወጣ ያስፈልጋል። ጊዜዉ የሥራ ጊዜ ነዉ። ጊዜዉ ከኢትዮጱያ ህዝብ ቆን ለኢትዮጵያ ደህንነት የምንቆምበት ጊዜ ነዉ። እኛ ካልተነሳን ማን ? አሁን ካልተነሳን መቼ ?

 1. .ሊሊ
  | #1

  ልክ ነው ለውጥ ሌያመጣ ይችላል

 2. ሞላ ነኝ
  | #2

  ሰላማዊ ሰልፍ ወይስ አመጽ ሰልፍ? አይመስለኝም፡፡

 3. Anonymous
  | #3

  ለመብታችን መታገል አለብን!!!!!!!!!!!

 4. እንግዳ
  | #4

  ትክክል ነው:: በውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያን ማድረግ የሚችሉትን ሁሉ ማድረግ ይገባቸዋል:: ወያኔ ጸረ ዲሞክራሲ ነው:አምባገነን : ጨፍጫፊ ነው ብሎ ለመጮህ ደግሞ ምንም ዓይነት: ድርድርና ውህደት አይፈልግም: ማንኛውም ኢትዮጵያው ውስጥ ወገን አለኝ የሚል አካል ሊሳተፍበት የሚገባው ነገር ነው::የምንም ድርጅት ወይም ዘር አባል ይሁን: ይህ ጉዳይ ይመለከተዋል::

 5. Docile
  | #5

  ደደብ ወያነና መሪዎቹ አንድም ቀን ህዝብ ውስጥ ስሜት ሳይፈጥሩ 17 ዓመት? ጠቅላላ ህዝብ ጠልቶታል:: ጉድ ነው:: እኛማ ታስረናል:: በትግሉ እንድንሳተፍ ከፈለጋቹ ከዚህ ሃገር አውጡን::

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።