በቴዲ አፍሮ “ጥቁር ሰው” ውስጥ የተዛባ የታሪክ ግድፈት የለም (በከፍያለው ፈንቴ)
ማንኛውም የኪነጥበብ ስራ ለህዝብ ሲቀርብ ከባለሙያም ሂስ ፣ ከታዳሚ ደግሞ አስተያየት መሰጠቱ የሚጠበቅ ነው። ሆኖም ግን የግለሰቦች አስተያየት ፣ ከአስተያየትነት አልፎ ሄዶ ፣ ተጠባቢውን በመናቅ የጥበብ ስራውን አፍርሶ እንዲሰራ ለመጠቆም መሞከር ፣ እጅግ ከጥበብ አለም ከራቀ ሰው ብቻ የሚደረግ ድፈረት ይመሰለኛል። “የቴዲ አፍሮ “ጥቁር ሰው” እና ጥቂት የተዛቡ የታሪክ እውነቶች” በሚል አርዕስት ስር የቀረበውን መጣጥፍ አንብቤ እንደጨረስሁም የደረስሁበት ድምዳሜ ፣ ከአስተያየቱ ገንቢነት ይልቅ ፣ አስተያየቱን የሰነዘሩትን ግለሰብ ፣ ግላዊ ጀብደኝነትን የሚያጎላ ሆኖ ነው ያገኘሁት።
ተችው ያቀረቡትን ነጥብ በማንሳት ፣ በግሌ የሚታየኝን የማልስማማበትን ሃሳብ ከመሰንዘሬ በፊት ግን ፣ በመግቢያየ ላይ የሰነዝርሁትን ሃሳብ ፣ ከስነ-ግጥም ወጣ ባለ መልኩ ፣ የግለሰቡን ትችት በሌላ የስነ-ጥበብ ክፍል እንዲመለከት እንባቢየን ልጋብዝ። “ጥቁር ሰው” የሚለው ሃሳብ ፡ በዜማ ስጋ እና አጥንት ጠንክሮ ፣ በተዋቡ የግጥም ቃላቶች የደም ዝውውር ስላለውና ፤ ቃላትን ደግሞ አማርኛን ለመግባቢያነት የምንጠቀም ሁሉ ፣ በቁሙ ከመተርጎም ጀምረን እንደፈለግን እከመተንተን ሃቅሙ ብቻ ስላለን ፣ ያሻንን ልንል ቻልን እንጅ ፤ ይህ ግዙፍ የሆነ ሃሳብ ፣ ሌላ የጥበብ ዘርፍ በሆነው በስነ-ስዕል ቢገለጽ ምን እንል ነበር። ሎሬት አፈወርቅ ተክሌ ፣ በአረንጓዴ ቀለም የሳሉትን የሰው ምስል “ጥቁር ሰው” ብለው ቢሰይሙት የምንሰጣቸው እርምት ምን ይሆን ነበር? ምናልባት ይህን ሃሳብ የሰነዘርሁት እንዲሁ ለልብ አድርቅ ክርክር ሳይሆን ፣ እንዴውም በዚሁ በ “ጥቁር ሰው” አልበም ከተካተቱት ውስጥ ፣ በግሌ የአንደኝነት ደረጃ በምሰጠው “ ስለ ፍቅር” በተሰኘው ዜማ ውስጥ …
“አፈር ይዞ ውስጡ አረንጓዴ
ለምን ይሆን የራበው ሆዴ።”
የሚል ስንኝ ተቋጥሮ እናገኛለን። ለመሆኑ ግን ፣ የት አገር ነው አረንጓዴ አፈር ታይቶ የሚታወቅ?! መልሱ አንድ እና አንድ ነው ፣ ኪናዊ ገለጻ በህግጋት የታጠረ አይደለም። የልቁንስ ተጠባቢው በህይወቱ በሚያካብተው የህይወት ነጸብራቅ ውስጥ እየተመራ ፣ የራሱን ፍልስፍና ተንፍሶ እፎይ የሚልበት ነው።
እናም ፣ ቴዲ አፍሮ በዚህ አልበሙ ውስጥ “በጥቁር ሰው” ዜማ ውስጥ የተካተቱት ታሪካዊ ጀግኖቻችን ፣ በነጸብራቅነት የተጠቀሱበት እንጅ ፣ የታሪክ ገድላቸው በዝርዝር የተዘከረበት አይደለም። ሊሆንም አይችልም። ሊሆንም አይጠበቅበትም። ምክንያቱም ስነ-ግጥም በትንታኔ መተረክ ስራው አይደለም። የከያኒውን ጥበባዊ ግዝፈት ወደ የቃላት ለቀማ ማውረድም ተገቢ አይደለም።
ለምሳሌ ትችቱን ያቀረቡት ግለሰብ “አባ ነፍሶ” የደጃዝማች ባልቻ የፈረስ ስም እንጅ የአባታቸው ስም አለመሆኑን መጥቀሳቸው ፣ እንኳንስ የከያኒውን ይቅርና ፣ የተደራሲውንም የግንዛቤ ደረጃ ያልተረዱ አስመስሎባቸዋል። ይህን አስተያየታቸውን ሳነብ ፣ ቴዲ አፍሮ በ “ያስተሰርያል “አልበሙ ላይ “ሸመንደፈር” ዘፈኑን የሰማ አንድ ጓደኛየ የተሰማውን ቁጣ አስታወሰኝ። ይህ ጓደኛየ በዚህ ዘፈን ላይ ያለው ትችት ፣ ቴዲ አፍሮ “ሙስሊም እና ክርስቲያን ቢጋባ” ብሎ የመከረ ያህል አድርጎ እንጅ የተረዳው ፣ ስለኢትዮጵያዊነት በሃይማኖት የመቻቻል ፣ ታላቅ እሴት ገለጻ አድርጎ አልነበረም የተረዳው። ልክ እንደዚያው ሁሉ ፣ “ባልቻ አባቱ ነፍሶ” የሚለውን ሃረግ ፣ ሙሉ በሙሉ በቁሙ ከመተርጎም ይልቅ ፣ ቴወድሮስ ለማለት የፈለገው “ምን ይሆን?” ብሎ ጥበብን መመርመር ተገቢ ነው። ጥበብ ሲመረመር ግን ፣ በቁጥብ ቃላት የተገለጸን ሃሳብ ዝርዝር ወደ ሆነ ተረት ተረት መቀየር ማለት አይደለም። ስለዚህ ፣ የዚህን ሃሳብ ምንነት መተቸቱን የምቃወመውን ያህል ፣ የተቃና ትርጉም ለመስጠት ብሞክር ግን የአስተያየቴን አቅጣጫ ያስተዋል ብየ አምናለሁ። እኔ ከምለው የተሻለ ግን ፡ አቶ ዳዊት በራሱ የብዕር ሰይፍ የራሱን ሃሳብ ቀንጥሶ ሲጥል ፣ “ፊአውራሪ ገበየሁን አርበኛው ሲያወድሳቸው ፣ በረፈረሳቸው ስም “እረ ጎራው” ይላቸዋል” ይላል። ታዲያ የዛን ዘመን ገጣሚ ጀግናን በፈረሱ ስም ከጠራው የዚህ ዘመኑ ቴዲ አፍሮ ደግሞ የጀግናውን ባልቻ አባት በጥበባዊ ገለጻ የፈረሱን ስም ቢሰጠው ምኑ ላይ ነው የታሪክ ግድፈቱ?!
ከዚህም በተጨማሪ፣ ትችት ሰንዛሪው ያቀረቡትን ሁለተኛ ነጥብ ቃል በቃል ለመተቸት እወዳለሁ። “ መድፉን ጣለው ተኩሶ” የሚለው የሙገሳ ስንኝ ከደጃዝማች ባልቻ ይልቅ ፣ ለሊቀ መኳስ አባተ የሚገባ አድርገው ትችት ሰንዝረዋል። ለመሆኑ በግጥም ስንኝ ውስጥ የሚሰነዘሩ ሃሳቦች ፣ በቁጥብ ቃላት በርካታ ሃሳቦች መሆኑን ተረድተውት ይሆን ግለሰቡ?! ደጃዛማች ባልቻ መድፈኛ ለመሆናቸው እና የመድፈኝነት ጀግንነታቸውንም እንኳንስ ሊቀመኳስ አባተ ቀርቶ ፣ ፊታውራሪ ገበየሁ እንደሚቀድሟቸው ተከታዩ የወቅቱ ግጥም ይገልጻቸዋል፦
“ገበየሁ ቢሞት ተተካ ባልቻ
መድፍ አገላባጭ ብቻ ለብቻ።”
ታዲያ የቴዲ ግጥም የደጃዝማች ባልቻን መድፈኝነት ከአድዋ ጋር ከማቆራኘት ያለፈ ምን የታሪክ ዝንፈት አስገባ?! የልቁንስ የከያኒው ቁጥብ ገለጻ ፣ እንደዚህ የተለያዩ ሃሳቦችን እያነሱ ለመወያየት ይረዳ እንደሆነ እንጅ?!
እንዴውም ከታሪክ አንጻር እንነጋገር ከተባለማ ፀሃፊው፦
“የአድዋ ስላሴን፣ ጠላት አረከሰው፤
ገበየሁ በሞቴ፣ ግባና ቀድሰው።”
የሚለውን ግጥም አስታክከው ፣ ጸሃፊው አዛብተው እንዳቀረቡት ፣ “ሰራዊቱ ጦርነቱ የሚጀመርበትን ቀን መናፈቅ ጀምሮ ፊታውራሪ ገበየሁን በግጥም ሸነጥ” ለማድረግ ሳይሆን ፤ ግጥሙ የተገጠመው ከጦርነቱ በኋላ ሲሆን ፤ የግጥሙ ታሪካዊ ምንጭም እንደሚከተለው ነው።
ጣሊያኖች እንዳ ስላሴ ብቻ ሳይሆን ፣ በሁሉም የጦር አቅጣጫቸው ከትመው ጦርነት ማድረግ አይፈልጉ የነበረበት ምክንያት ፣ በበርካታ ሽህ ህዝብ የሚቆጠረው ኢትዮጵያዊ ሰራዊት ፣ በእግሩ እና በፈረስ ብቻ ሩቅ ተጉዞ የመጣ በመሆኑና ፣ ጦርነቱ ሳይደረግ ትንሽ ቀናት ከቆየ ፣ ይዞት የመጣውን ስንቅ በልቶ ይጨርሰውና ፣ ጣሊያኖች ብዙም መቋቋም ሳይገጥማቸው በቀላሉ ለማሸነፍ የወጠኑትን የጦርነት ስልት ነበር። ይህንም ስልት ለማክሸፍ ነው ፊታውራሪ ገበየሁ ጦርነቱን የቀደሰው እንጅ ፣ ሰዎች በግጥም ገፋፍተውት አይደለም። ይህም በንጉስ ምኒሊክ ዘንድ ከበሬታ ያስቸረውን ያህል ፣ አደገኛ የተናጠል ድርጊት ተደርጎ ተወስዶበት በወቅቱ በንጉስ ምኒሊክ እንዳስተቸው በታሪክ ተጽፏል። እናም ግጥሙ የተገጠመው ከእንዳ ስላሴው ጦርነት በኋላ እንጅ በፊት አይደለም። ይህንም ያነሳሁት ፣ እንድትልቅ ልዩነት ለማሳየት ሳይሆን ፤ እንኳንስ ለዘፈን በሚደረስ ምጥን ስነ-ግጥም ውስጥ ቀርቶ ፣ ያሻን ያህል ቃላት ተጠቅሞ በሚቀርብ መጣጥፍም ፣ ሃሳብ ምን ያህል ሊመዛበር እንደሚችል ለመግለጽ ብቻ ነው።
የፊታውራሪ ሃብተጊዮርጊስም ጉዳይ ፣ እንዲሁ የቃላት እሰጥ አገባ ካልሆነ በቀር ፣ ትችቱን የሰነዘሩት ግለሰብ የመነሻም ሆነ የመድረሻ ሃሳባቸው መሆን የነበረበት ፣ ሌላው እንኳን ቢቀር “የሃብተጊዮርርጊስ የማዕረግ ስማቸው ማን ነበር?” የሚለው ነው። መልሱም “ፊታውራሪ” ነው። ከዚህ በኋላ ያለው ትንታኔ ለታሪክ አስተምሮት የሚጥቀም እንጅ ፣ ኪነትን ለመሞገት ሃቅም ያለው የመከራከሪያ ሃሳብ አይደለም።
እንዴውም ትችት አቅራቢውን ሊገርማቸው በሚችል መልኩ ፣ ቴዲ አፍሮን በዚህ አልበሙ “ጥቁር ሰው” እያለ ያሞካሻቸው እምዬ ምኒሊክ ፣ በታሪክ አጋጣሚ በአንድ ወቅት እራሳቸውንና ኢትዮጵያውያንን “ኒግሮ ወይም ጥቁር አይደለንም” እንዳሉ ታሪክ ዘግቦታል። ይህ ግን በወቅቱ የነበረውን አመለካከት ብቻ ሳይሆን ፣ እስከአሁንም ድረስ እራሱን ከሌሎች አፍሪካውያን ልዩ አድርጎ የሚቆጥር ኢትዮጵያዊን የሚገልጽ ቢሆንም ፤ ዘመን ተሻጋሪ የጥበብ ስራዎችን እያቀረበ ያለው ቴዲ አፍሮ የሰጣቸው ስያሜ ግን ፣ እምዬ ምኒሊክ ከአደዋ ድል ማግስት ድላቸው የሁሉም ጥቁር ህዝብ መሆኑ እና እኛም ጥቁርነታችን ምድር ላይ የሚስተዋል ሃቅ መሆኑ ነው። አጼ ምኒሊክን “ጥቁር አይደለሁም” ብለው ነበር ብሎ የሚተች ትውልድ ቢኖር ፣ አቶ ይድነቃቸው ተሰማ “ለአውሮፓ አገር በፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋችነት ፣ በሚሊዮን ዶላር መሸጥ ባርነት ነው” ማለታቸውንም በዘመን ሚዛን ሊለካ ይገባል።
በመጨረሻም ፣ ታላላቅ የኪነጥበብ ስራዎች አይነተኛ መለያቸው ህበረተሰብን ለውይይት የማነሳሳት ሃቅማቸው ቢሆንም ፤ ህብረተሰቡ የሚያነሳቸው ሃሳቦች ግን ከውይይት አልፈው ከያኒውን የመጠምዘዝ ሃይል ይኖራቸዋል ማለት አይደለም። ውስጣዊ ፍልስፍናውን በሰዎች አስተያየት የሚቃኝ ከያኒ ቢኖር ፣ ፍጹም የኪነት ሰው ሳይሆን ፤ አሁን አሁን እንደምናያቸው ያሉ ለጥቅም የተሰማሩ ፣ ልማታዊ አርቲስቶች እና የገንዘብ ሰራዊቶችን ይመሰላል።
kefyalewf@yahoo.ca



ሰላም ከፍያለው::
እርስዎ ያነሱት ሀሳብ በልቤ ውስጥ ያለውንና ልጽፈው በዝግጅት ላይ የነበረውን ነው:: አቶ ዳዊትን በሁሉም ቦታ ቦታ አለው አለው ማለትና አውቃለው የማለት ባዶ አባዜ እንዳላቸው ከሀገር ቤት ጀምሮ እስከ አትላንታ ከዛም በፓልቶክ የምናቃቸው የትልቅ አጥረ ቀላል: ባዶ ጉረኛ ሰው ናቸው:: ቴዲንም ሆነ ተደራሲውን ለመዝለፍ የሞራሉን የአቅሙም የችሎታውም የዕምነቱ የሰውነቱንም ብቃት የላቸውም አቶ ዳዊት::
አንድን ስው ከወደድን ሌላው መተችት የማይቻልበት ዘመን
Ethiopiawinet is alive and kicking.
What does Teddy Afro’s song and the huge reaction it has provoked tell us?
For the last three decades or so,there has been a very dogmatic,stifling and a virulent form of elite inspired and officially dictated politics of ethnicity that has threatened the viability of our historic nation while entrenching a corrupt Tigrayan minority rule that has stayed in power through divide and rule while at the same time serving the interest of foreign powers who in turn prop it up by various means.
As result of the many fanatic assaults that it received from various directions for so long,Ethiopiawinet,at the face of it,seemed to have had a hard time.In particular,the sustained work done to make particularly the young forgetful of their proud common heritage and the great achievements of their ancestors appeared to have made much headway.In tandem with the dismantling of the glorious past,a lot has been done to uncouple the vital link of the young from its ancestral identity and heroic heritage through a massive inculcation neocolonial culture.This has been propagated with the hope of taking away the pride of the youth while corrupting and belittling it in its own eyes.But naturally and all along, the counter current of Ethiopiawinet has flown below the surface.The wave of that flow has grown particularly stronger when it has been impeded from its natural course by the arbitrary and dictatorial forces of ethnicity and insidious cultural imperialism.
They say for ever action,there is an equal and opposite reaction.
Teddy Afro’s exciting song tap into and rhymes with the defensive reaction of our people who are subjected to the barrage of the politics of Ethnicity through the dismantling of our common Ethiopiawinet.The song is giving voice to the people who are saying no the dispparragment of the independent spirit and great heroic deeds scored by our Ethiopian ancestors.
Thanks to that song,the young,once again,are reconnecting with their vital past.Historic Amnesia is going out of the window while revitalized sense of identity and pride are coming through the door.
The arrogant and suffocating Marxsim,was there for a while.But later, it died leaving its place for an equally arrogant and suffocationg politics of Ethnicity.The latter has been here for a while but it too will surely go in its time. Empires too come and go.While the
Persian,Egyptian,Roman,Arab,Turkish,Spanish,Portugese,British etc Empires came and went,the little free and proud nation,Ethiopia survived.The all embracing,historic and righteous Ethiopiawinet will eventually replace ethnicity and neocolial subjugation ensuring the survival and independence of Ethiopia.Ethiopiawinet is alive and kicking.
geta yibarkh wondme, lela qal yelegnim.
ቴዲ የተባለው ሰው ሻእቢያ ነው ይባላል በዛ ላይ እየሰራ ያለው ከወያኔ ጋራ ነው ጎበዝ ምነው እንደዚህ ከፍ ባናደርገው::
Well said Kefyalew, Tedy Tarik alazabam, endewim tarikachinin agolalin.
ere Yetedy aynet 1000 yiweled, He is a hero. We are blessed we have Tedy.
@አቶ ከፍያለዉ ፈንቲ
የተምታትብህ ትመስላለህ::
ኣጤ ምንሊክ ኔግሮ አይደለሁም ብለዋል አልክ:: ትክክል ነዉ ያሉት::
እኛ ኢትዩጵያዉያን ጥቁር አፍሪቃዊ እንጂ ” ኔግሮ” አልነበርንም: አይደለንም::
እረ ለመሆኑ የአሜሪካ ጥቁሮች ላምን ታዲያ ኔግሮ አትበሉን አፍሪቃዊ አሜሪካዉያን ብሉን በለዉ እነ ማልኮልም ኢክስ በጀመሩት ጸረ ዘረኝነት ተጋድሎ አይደለም እንዴ ኔግሮ የተባለዉን መጠሪያ ያስቀየሩት?
ኣርበኛዉና የመጀመሪያዉ ሃኪም መላኩ በያን ኔግሮ የተባለ የዘረኞች ስያሜን በቅድሚያ የተቃወመዉ:: ጥቁር ኣሜሪካዊ ተብለዉ መጠራት እንጂ “ኔግሮ” መባል እንደሌለባቸዉ ከሁሉ አስቀድሞ ያሳሰበዉ::
የነጭ ዘር የበላይነትና አስልጣኝነት ሃሳብ አናፋሾች የጥቁርን የዘር በዝቅተኛ ደረጃ
መድበዉ መጠሪያዉንም “ኔግሮ” ብለዉ ከአፍሪቃ ትዉልድ ቀየዉ በባሪያ ፍንገላ አትላንቲክ ዉቅያኖስ ማዶ ሲያሻግሩ ያለቀዉ ቁጥር በጣም ከፍተኛ ነዉ:: የተረፈዉ በጣም ጥቂቱ ነዉ::
ዘረኞች “ኔግሮ” ማለት ጥቁር ነዉ ካሉ ለምን በአለም ላይ ያሉ ጥቁር ዘርያዎች ሁሉ “ኔግሮ” አልተባሉም? “ኔግሮ” የሚለዉን ቃል ምድረ ዘረኛ ሁሉ የሚጠቀሙት ከአፍሪቃ ለፈነገሉት ባሮች መጥሪያ ብቻ ነዉ::
ለምን የሕንድን: የፓፑዋን: የፍሊፕንን: የታስማኒያን: የኒዉዪላንድን ወዘተረፈ ጥቁር ዘርያዎች ግን ኔግሮ ተብለዉ አይጠሩም? እንዲያዉም የአዉስትራሊያ ጥቁር ነባር ሕዝቦችን “ኣቦሪጅን” እንጂ ኔግሮ አይሉዋቸዉም:: የአዉስትራሊያ ጥቁር ሕዝብም ብለዉ አይጠሩም:: ለምን?
ጸረ ኢትዮጵያዉያን ዘረኞች ይነዙ የነበረዉን ፕሮፓጋንዳ ታናፍሳለህ::
ጥቁሮች በአሜሪካና ካሬቢክ በአፍሪቃና እሲያ የኢትዮጵያን መወረር በመቃወም ለመርዳት ሲነሱ ፋሽስቶችና ተባባሪዎቻቸዉ ሁሉ ሲነዙ የነበረዉ ይህንኑ ዉሸት ነዉ::
ቸር ይግጠመን
ድርብ ቀጀላ
ጆሌ ወበራ
እንደዚህ ስለጥበብም ስለታሪክም የሚያውቅ ሰው ሲናገር የልብ ያደርሳል:: አቶ ዳዊት የቴዲ አፍሮን ሙዚቃ እንደሰሙ ወዲያው ከመጸሃፍ ጋር ማስተያየት የጀመሩ ይመስላል:: የታሪክ መጽሃፍና የዘፈን ግጥም ልዩነቱን ግን አቶ ከፍያለው በደምብ አስረዷቸው::
ሰዎች የደከሙበትን ለማፍረስ ከመሯሯጥ ይልቅ ; በጥሩ መንፈስ ይህን የዘመናችን ብርቅ ሰው ማበረታት ይገባል:: የቴዲ አፍሮን ስራ እንደ አቶ ዳዊት አፍራሽ እንዳሉ እንደ ከፋያለውም አገናዛቢ መኑሩ ያች ኢትዮጵያ ሁሉም አይነት ሰው እንዳለባት ያሳያል::
በቴዲ አፍሮ “ጥቁር ሰው”በተሰኘው የሙዚቃ(ዘፈን)ውስጥ የተዛባ የታሪክ ግድፈት የለም::የታሪክ እውነቶችም አልተዛቡም! መጣም ጥቂት ሲበዛ ጥቂት ያለው ስሕተት ግን በታሪኩ ላይ የተሳተፉት ግለሰቦች ትክክለኛ ቦታቸውን አልያዙም! የሚል አቶ ዳዊት ከበደ የሚባሉ ግለሰብ እጅግ በሚያስደንቅ ገንቢ እና የማሻሻያ ሀሳባቸውን መስጠታቸውን አንብቤአለሁ::ይህም ስሕተት በጣም በቀላል ከእያንዳንዱ ግጥም አንዳንድ ቃል ቢስተካከል ሥራው እንደዚህ ከታሪክ ማስታወሻነት አልፎ መወቃቀሻ ባልሆነ የሚገርመው ግን በዚህ ጽሁፍ የታሪክ እውነታው ተጠናብሯል::የጥቁር ነገር ሲነሳ በአሜሪካ ከተማ የተለበሰ የካኒቴራ ላይ ጽሑፍ ዛሬ ድረስ ያስቀኛል (burn face) ኢትዮጵያ ማለት በጸሐይ የተቃጠለ(የተለበለበ) ማለት ነው ይላሉ ቃሉ የተገኘው ከግሪክ ቃል በለንደን ዩኒቨርሲቲ የተገኘ መጽሐፍ ይሉታል የእኛ ቤት ምሁራን ድንቄም!!!በግሪክኛ “ማቭሮ”ጥቁር ማለት ነው ለመሆኑ ‘አራቢ’ወይንም ‘እስክላቭ’ማለት ማን ማለት እንደሆነ ያውቃሉን??እምዬ ምንይልክ እንኳንም አበጀ “ኔግሮ” ከመባል ጥቁር መባልን መምረጡ አንዳንድ ወጥላቆች ግን ሁለቱንም አደለንም አለ ብለው መዘገባቸውን አይቼዋለሁ ለመሆኑ ጸሓፊዎቹ እና አቀንቃኞቹ እነማን ናቸው??????!
እዚህ ጸሓፊው አንዳንድ የተደናበረ ምሳሌ አምጥተዋል::
1)ሎሬት አፈወርቅ ተክሌ በአረንጓዴ ቀለም የሳሉትን የሰው ምስል “ጥቁር ሰው”ቢሉት ወይ ጠጥተው ነበር:: ወይ ቀለምን አያውቁም:: አረንጓዴ የብር ኖቶች ላይ ኢትዮጵያዊ ስላለበት ቀለሙ የብር ኖቱ እንጂ የግለሰቡ አደለም::!
2)”አፈር ይዞ ውስጡ አረንጓዴ
ለምን ይሆን የራበው ሆዴ?” እዚህ ጋ ግጥሙ በጭራሽ ስለ አረንጓዴ አፈር አያወራም::የተዘራበትን ሁሉ የማብቀል
የማፍራት የሚያስችለን ምድር ይዘን ለምን ተራብን ይላል::አፈር ውስጥ ተዘርቶ የሚበቅል ሁሉ አረንጓዴ ነው!!!
3)”የአድዋ ስላሴን ጠላት አረከሰው
ገበየሁ በሞቴ ግባና ቀድሰው!” እዚህ ጋ ግጥሙ የተገጠመው ከጦርነቱ በኋላ ወይስ በፊት?”ገባ እና ቀደሰው”ጦርነቱ ካለፈ በኋላ ቢገጠም ኖሮ::ግን ወደ ጦርነቱ እንዲገባ ገበየሁ በግጥም ሲሸነጥ “ግባ እና ቀድሰው” ቅደም እና ጀምረው ተባለ::የዚህ የዘፈን ጉዳይ ይህን ያህልም አወዛጋቢ ነገር ያለው ሆኖ ሳይሆን በአጋጣሚው ሁሉም የራሱን ጥበብ የተወነበት አጋጣሚ ፈጥሯል ከአስተማሪነቱ ይልቅ አስቂኝነቱ ተወዳጅ አድርጎታል::አቶ ቲዎድሮስ ካሳሁንም በርቱ ሌሎችም እንዲሁ
ጆሌ ወበራ መልካም አስተያየት ነው በርቱ!እንዲህ አደል እንዴ ሀገር የምትፈርሰውም የምትጠበቀውም ሁላችሁንም በማድነቅ
በቸር ይግጠመን በለው!<<<<<<<<<<<<
I think Teddy`s ጥቁር ሰው has far-reaching political implications on our current political discourse-The pariotism of Adwa heroes was under attack by some thugs of the regime recently- Firstly, Teddy has hard hit back to this distructive move, and with the recent displacement of our people, the legitimacy and viability of ethnic federalism is undoubtably beated, I believe!!
ዳዊት ከበደ ያቀረቡት የማስተካከያ ሃሳብ፡ ቴዎድሮስ ካሳሁንን የመተናኮል ዓይነት አድርጋችሁ የወያኔ ባሕርይ በማታውቁት መንገድ የተጠናወታችሁ ኔጋቲቭ አእምሮ የተሸከማችሁ ግለሰቦች፡ አመል ሆኖባችሁ በጥሩ ግብረገብ የቀረበውን ማስተካከያ ለሻቢያዎችና ለወያኔዎች መፈንጫ አደረጋችሁት።
ቴዲ ጥሩ እንደሠራ ሁላችሁም ተስማምቷችኋል። በቃ አባቱ ነፍሶ የሚለውን፡ ፈረሱ ነፍሶ ብሎ እንደሚያስተካክል እርግጠኞች ነን።
@እሽቴ
ቱሪናፋ… ድድብናህ ጣራ የነካ ነው ባክህ! በዚሁ ቀጥል, ለ Genius book of record ትበቃልህ ባዶ.
እኔ የሚገርመኝ ቀናውን ቀናውን ማሰብ ተውን መሰለኝ:: አቶ ዳዊት ያቀረቡት ሀሳብ ታሪክን የሚመለከት ነገር በዘፈቀደ የምንቀይረው ነገር አይደለም ነው ስለዚህ አንዳንድ የተዛቡ ነገሮች ይስተካከሉ ነው:: አቶ ዳዊት ያቀረቡት የታሪክ ውነቶች ልክ አይደሉም ካልን ይህንን በማስረጃ አቅርበን ሥራው ሙሉ መሆኑን ማረጋገጥ:: በእርግጥ ቴዎድሮስ ካሳሁን ያወጣው ዘፈን ከግጥሞቹ ከቅንብሩና ኢትዮጵያዊነትን ከመዘከር አንጻር ካለው ጉልበት አንጻር የተዋጣለት ነው:: አርቲስቱን በጣም ልናደንቀው ይገባናል ይበጅም ሊባል ይገባዋል:: የተሳሳተ ነገር እንዲታረም መጠየቅ ግን ነውር አይደለም:: በየእለቱ የምንጮህበት ነገር እኮ በማወቅም ባለማወቅም የታሪካችን መሰረት እየተነካ አይደለም እንዴ? አርቲስቱ ደግሞ የታሪክ ምሁር አይደለም ጠይቆ መረዳት አለበት:: ማንም ከኢትዮጵያና ከታሪኳ በላይ ሊውል አይችልም::
mastewal well done i agree.
every time they trying to keep every one to shut up.
i will say shut the f…k up…
tedy say that say this do you realy rember 2001 when osama biladen terore group bomb twin tower in america.in that sensetive time the group called BLACK EYE PEAS,they sing where is the love when america start bombing afgan and iraq,can you comapare tedy afro with that..
let him say you people you need 10 like teddy to keep your mouth shut!!!
where have been my who ever we alwayes heard balcha abnbeso yehe new dekama shemagle new it was in teater long time ago why you did not complaine then.
tedy can and will sing til you furestret he is not against any one but the TRUTH,you have problem with TRUTH, so sort out your problem.
@ምንትዋብ: አቶ ከፍያለው በማስረጃ አስደግፈው የአቶ ዳዊት ከበደን ስም ማጥፋትና በእሽቅድድም እኔ አውቃለሁ ማለትን ባዶ አድርገውታል::
አቶ ዳዊት ከበደን ለሚያውቃቸው ሰው አላማቸው እና መላ ነገራቸው ምን እንደሆነ የ 4 ዓመት ህጻን ልጅ ጠንቅቆ ያውቃል:: አቶ ዳዊት ከባዶ ጉራ ውጭና ስማቸውን የፈረንጅ አድርገው “በጹሁፉ ማብቂያ ላይ የተጠተሙበትን -ደቭድ ካርል” ልብ ይሏል – ያው የሁሌ እዩኝ እዩኝ ባይ ቱሪናፋ ነው:: በነገራችን ላይ አቶ ዳዊት ከበደ አትዮጵያ ውስጥ የመጀመሪያውን የወሲብ “ፖርኖ” ጋዜጣ በማሳተም ህዝብ በነቂስ ሰልፍ እሪ ብሎባቸው እንደነበረና ወዘተ ወዘተ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው:: እናም የታሪክ ዕውቀቱም ሆነ ትንሽ ጭላንጭሎም እንደሌላቸው ልብን ሞልቶ መናገር ይቻላል::
ስለ ቴዲ አፍሮ አዲሱ አልበም አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ በቅዳሜ እትም የወጣውን ኦን ላይን እንድታናቢና እጋብዝሻለው ወዳጄ የሀገር ልጅ ምንትዋብ::
Btw, መልካም የዳግማዊ ትንሳኤ በዓል!!
ወይ አቶ ዳዊት ከበደ: ኢትዮጵያ ውስጥ የቁጩ ጋዜጠኛ ሆኖ ወደ አሜሪካ ስለወጣ ብቻ , የውነት ጋዜጠኛ የሆነ መሰለውና ; ዛሬ ደግሞ የታሪክ ተመራማሪ ሆነ:: ሎል
ሰዎች ከአዋራምባ ታይምሱ ዳዊት ጋር በስመ ሞክሸነት ሳይሸወዱ የቀሩ አይመስለኝም:: ይህኛው ዳዊት የኛው የአትላንታ ጉድ ነው:: ዳዊት ለመሆኑ አንድ ግጥም ጽፈህ ታውቃለህ እንዴ? እኔ ሳውቅህ ስብሰባ እና እንትን ነው የምትወድ:: ከዚህ በላይ የተጻፈው አንተን የሚደግፍ ጽሁፍ ሁሉ ; ስምህን እየቀያየርህ አንተ የጻፍኸው እንደሆነ ሌላውን ብትሸውድም እኔን ግን አትሸውደኝም::
አንተ ግን ማፈሪያ ነህ:: ቴዲን ያህል ሰው ለመተቸት መሞከርህ በጣም ደፋር መሆንህን ያሳያል::
አቶ ከፍያለው ደግሞ ጥሩ መልስ አዘጋጅተው ; በስመጨረሻ ግን ስለአጼ ሚኒልክ የጻፉትን በተጨባጭ ማስረጃ ቢገልጹት ምንኛ ደግ ነበር:: ደግነቱ ኢሜል አድራሻዎት ስላለ እጠይቅዎታለሁ:: ካልመለሱልኝ ግን ; በዚሁ ቦታ እገልጻለሁ::
ሰሌ ከአትላናታ
I like ato kefylew’s article. It is a well contented response for the distorted fact by mr. Dawit.
I m with Akasi and Mastewal too. Teddy did a great job against our current enemy weyane. However, he is been criticized by unwise so called Ethiopians journalist. If we don’t alleviate his work and respect him, where is our love for our country?
ጉድ ነው መቼስ የሃገራችን ዜጋ የተጠናወተው የምቀኝነት፤ ቅናት ሃሳብ እንደሰንሰለት ተያይዞ፡ ይኸውና ሃገራችን በወንበዴዎች እጅ ላይ ወድቃ ትንገዳገዳለች።
የእነዚያ አርበኞች ታሪክ በቃላት መዛባት ታሪካቸውም እንዳይዛባ የቀረበውን ትህትና አዘል የአቶ ዳዊት ከበደን ጽሁፍ የግል ጥላቻ ማንጸባረቂያና የወያኔዎች ቅጽል ስም መጫወቻ አደረጋችኋቸው። አንድነት ከየትም ሊመጣ አይችልም። ከታሪክ ማህደር መጻሕፍት ብቻ አይደለም፡ ከቀደምት አበው አርበኞችና አረጋውያን የሰማሁትን አቶ ዳዊት ከበደ ለወጣት አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን በማቅረባቸው ከልቤ ከልቤ የምቀበለው ሃቅ ነው። ጊዜያችሁን በጥላቻና ቅናት ስሜት ውስጥ ለወያኔ በር የምትከፍቱ ሁሉ፡ የኢትዮጵያ አምላክ ልቡና ይስጣችሁ።
ስንት አድርባይ ዘፋኝ የማይረባ ግጥም እየሰበሰበ ሲናዘፍን የተቸ አለ? ይህን አንድዪ ብቸኛ የልባችንን የሚዘፍን ብላቴና ምን ዐርግ ነው የምትሉት?
Oh ! Teddy I don’t know how many such beatiful musics you provide us since you are young we have many chances to liston aggin we are lucky!
@ወርቃለማሁ
ትክክል ነው::
@ወርቃለማሁ
እግዚአብሔር ይባርክህ ወንድሜ በጣም ከሚገባው በላይ ገልጠኸዋል::