Recent Posts
- ወይ መላ ነሽ አሉ ወይ መላ አባ መላ! ከሎሚ ተራተራ፦ ከሎሚ ተራተራ፦
- ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ 2ኛ ዓመት ቅጽ 2 ቁ 76
- በላተኛው አባ-መላ ከያሬድ አይቼህ
- የሰማይ ላይ ግንብ የመጽሃፍ ግምገማ ሰለሞን ሃይለ ማሪያም
- የኛ ነገር፡ የኔም ነገር፤ አንድ እንደመግቢያ፤ አሸዋና አለት በልጅ ተክሌ
- ኢትዮጵያዊነት እያበበ ነው ወይስ እየጠወለገ? የኢሮብ መብት ተማጓች ማኅበር
- የበረከትና አላሙዲ ልሳን (ከኢየሩሳሌም አርአያ)
- የመለስ ዜናዊ ሌጋሲ ስቶኮልም ስንድሮም በታሪኩ አባዳማ
- የመለስ መታሰቢያ ተቋም (Foundation) – ክፍል 3 ከ 3 ግርማ ሞገስ
- አሸባሪው ማን ነው? ከተስፋዬ ዘነበ
Recent Comments
- Tolla on በላተኛው አባ-መላ ከያሬድ አይቼህ
- አበራ ለማ on የሰማይ ላይ ግንብ የመጽሃፍ ግምገማ ሰለሞን ሃይለ ማሪያም
- አስማረ on የኛ ነገር፡ የኔም ነገር፤ አንድ እንደመግቢያ፤ አሸዋና አለት በልጅ ተክሌ
- በላይነሽ on የኛ ነገር፡ የኔም ነገር፤ አንድ እንደመግቢያ፤ አሸዋና አለት በልጅ ተክሌ
- Gerum Tessfa on የኛ ነገር፡ የኔም ነገር፤ አንድ እንደመግቢያ፤ አሸዋና አለት በልጅ ተክሌ
- በለው ! on የመለስ መታሰቢያ ተቋም (Foundation) – ክፍል 3 ከ 3 ግርማ ሞገስ
- ይብሳ on ሁለ ገብ ትግሉና ህዝባዊ አመጽ። ዛሬስ። ከዳኮታ የጥናት ማእከል።
- Gethann on ኢትዮጵያዊነት እያበበ ነው ወይስ እየጠወለገ? የኢሮብ መብት ተማጓች ማኅበር
- ጥሩወርቅ(ጥሩዬ) on ሁለ ገብ ትግሉና ህዝባዊ አመጽ። ዛሬስ። ከዳኮታ የጥናት ማእከል።
- በላይነሽ on የመለስ መታሰቢያ ተቋም (Foundation) – ክፍል 3 ከ 3 ግርማ ሞገስ

Categories
Archives
- May 2013
- April 2013
- March 2013
- February 2013
- January 2013
- December 2012
- November 2012
- October 2012
- September 2012
- August 2012
- July 2012
- June 2012
- May 2012
- April 2012
- March 2012
- February 2012
- January 2012
- December 2011
- November 2011
- October 2011
- September 2011
- August 2011
- July 2011
- June 2011
- May 2011
- April 2011
- March 2011
- February 2011
- January 2011
- December 2010
- November 2010
- October 2010
- September 2010
- August 2010
- July 2010
- June 2010
- May 2010
- April 2010
- March 2010
- February 2010
- January 2010
- December 2009
- November 2009
- October 2009
- September 2009
- August 2009
- July 2009
- June 2009
- May 2009
- April 2009
- March 2009
- February 2009
- January 2009
- December 2008
- November 2008
- October 2008


How many Jews are there in Ethiopia? Is it not bending backward for a non-existent religion?
THE ETHNO-FASCIST WOYANE JUNTA IS meticulously and deligentlt carrying out its task of dismantling Ethiopia without taking any breaks. Day and night we hear and see different crimes of the woyane.
The attack on relegion and the incitement of hate and violence between relegious groups is one of woyane’s strategy to create chaos and blood shed in Ethiopia.
where is the woyane going to stop? we seem to be bearing every hardship the woyane is throwing at us any other group of people would have not tolerated for such a long time.
It is time to rise up and say enough is enough.
ለአኢጋን
በአስቸኳይ መግለጫ ላይ ያሰፈራችሁት መልእክት ጊዜያዊና አስፈላጊም ነው፡፡ እርግጥ ነው እኛ ኢትዮጵያውያን አብረን መስራት፤ ለአገራችን አስቸኳይና መሰረታዊ ችግሮች አብረን መቆምና መታገል ይገባናል፡፡ በዚህ የጋራ ጉዳይ ላይ የሃይማኖትም ሆነ የመደብ ልዩነት ማድረግ አይገባንም፡፡ ድሮ ልጆች ሆነን ሲጠቀስ እንደሰማነው ቀዳማዊ ኃይለስላሴ “አገር የጋራ ነው ሃይማኖት የግል ነው” ያሉት ለጥቅስ የበቃ አባባል መርሆ ሊሆነን ይገባል፡፡
እናንተ አሁን ካወጣችሁት መግለጫ ጋር አብሮ የሚሄደው ትልቁ ጥያቄ ግን፡ ይህንን መግለጫ በአስቸኳይ ያወጣችሁላቸው የእምነት ተከታዮች ማለትም ሙስሊሞችና እምነታቸው እስልምና ይህንን እናንተ እና እኔ የምንለውን ነገር በእርግጥ ያምናሉ ወይ? እናንተ እና እኔ አሁን ለምንለው ዓላማ ይቆማሉ ወይ? በእምነታቸው ውስጥስ እውነተኛ የሰው ልጆች በሰላም አብሮ መኖርና መከባበር ይታወቃሉ ወይ? እንደ እኔ፤ እንደ አኔ፤ እነዚህንና የመሳሰሉትን ጥያቄዎችን በአግባቡ ያያችኋቸው አይመስለኝም፡፡
እኔ የኢህአዴግ መንግስት የሚያራምደውን ፖሊሲ አልደግፍም በእስልምናና በአንዳንድ አክራሪዎች ላይ ያለውን አቋም ግን አደንቃለሁ፡፡ መብታችን ተነካብን ላሉትና ለእናንተ አቤቱታ ላቀረቡት አሁን እናንት የምትጮሁላቸው ቤተክርስትያን ሲጨፈጭፉ፣ አማኞችን ሲያሰቃዩ፣ እዚህ አካባቢ ክርስትያን ሊኖር አይችልም ለቃችሁ ውጡ ሲሉ ምን ተናግራችሁ ነበር?
እናንተ አሁን የምትጮሁላቸው ሙስሊሞች ዓላማቸው ምንድነው? ከሳውዲ አረቢያና ከመሰል የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላቶች ጋር በመሆን ኢትዮጵያን እስላም ለማድረግ የሚሰሩትን የምስጢርና የድብቅ እንቅስቃሴ አታውቁትምን? ካላወቃችሁ እንደዚህ ዓይነቱን ስራቸውን እንድታስቡበ ልንጠቁማችሁ እንወዳለን፡፡
ብዙ የፖለቲካ መሪዎች እና የፖለቲካ ድርጅቶች ተቀባይነትን ለማግኘት ሲሉ ብቻ ወይንም ለድምፅ ወይንም ለድጋፍ አገርን እና ሕዝብን በሚጎዱ ነገሮች ላይ መሰማራታቸው የተጀመረው በእናንተ አይደለም፡፡ ለምትሏቸው ቡድኖች መቆማችሁና አስቸኳይ መግለጫ ማውጣታችሁ ግን ይች የድሃዎች አገር ነገ የሰው ዘር መኖሪያ እንዳትሆን እያደረጋችሁ ነው፡፡
የእነርሱን ድጋፍ ለማግኘት የምታደርጉት ጥረት ጥናት አያስፈልገውም በመግለጫችሁ ላይ ያወጣችሁትና ክርስትያን በበዛባት አገር ውስጥ የመጀመሪያ አረፍተ ነገር አድርጋችሁ ያስቀመጣችሁት ቃል “ቢስሚላሂ” እራሱ ይመሰከርባችኋል፡፡
ያለውን መንግስት ለመቃወምና ለድጋፍ ብቻ ስትሉ ውስጣዊ ዓላማቸውን በግልፅ ለማታውቁት ወይንም በሌላ አነጋገር ተገዝታችሁ አገሪቱን ከፍተኛ አደጋ ላይ ለመጣል መነሳታችሁ ያስገርማል ነገር ግን አይሰካችሁም፡፡
በሳውዲ አረቢያ እና በመሳሰሉት አገሮች ድጋፍ የሚንቀሳቀሱትን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ችግር ምንም ደንታ የሌላቸውን የሰብዓዊ መብት ረጋጮችን መደገፋችሁ ያስገርማል፡፡
ክርስትና ግን እምነቱንም ሆነ አመለካከቱን በማንም ላይ አይጭንም እስልምና ግን የተለየ ነው፡፡ በእስልምና ስር ሆነህ እስላም ካልሆንህ የመኖርም የመስራትም መብት አይኖርህም፡፡ ይህን እውነታ ደግሞ ከታሪክ መረዳት የሚቻል ሲሆን የእኛ አገር እስላሞች ተሳክቶላቸው የመሪነት ቦታ ቢይዙ የተለየ እምነትና አቋም ይኖራቸዋል ብሎ ማሰብ ግን ለታሪክ እና ለእውነት እውር መሆን ትውልድንና አገርን መሸጥ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላምና እረፍት ተጠምቷል፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ የግል ጥቅም ያሰከራቸው ሰዎች መጠቀሚያ መሆን መሮታል፣ ችግሩ የሚቋጭበት ጊዜ እንዲመጣለት በጉጉት በሚጠብቅበት በዚህ ሰዓት እስልምና በበኩሉ የደገሰለትንና የሚጠብቀውን ፍዳ መደገፋችሁ የሚገርም ብቻ ሳይሆን ስህተት ነው፡፡ ስለዚህም ሕዝቡን ይቅርታ መጠየቅና ከእንደዚህ ዓይነት የሕዝብ ጠላትነት ብትታረሙ ይበጃችኋል፡፡
አዲስቱ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ለሰጣችሁት መግላጫ በጅጉም በሀገራችንና በሕዝባችን በእምነቱና በመብተኡ በክቡር ነጻነቱ ላይ እየተደረገ ያለውን አሳፍሪና የታሪክ አጥፊነት ውንብድና ላለፉት 21 ዓመመታት በማን አለብኝ እንዲሁም ለሆድና አደሩ የወገን ጠላቶች እየተፈጸመ ያለው የሃገር ክህደት የሕዝብ ውርደት በያለንበት በጽሑፍ በሰላማዊ ሰልፍ ተቋውሞ ስናካሄድ ምንም እንኳን በመጠኑ የሕዝቡን ስነ ልቦና የአይምሮ ጉልብትና የመንፈስ ብርታት ብናደርግም ያለውን ስራአት ከሚያደርገው የሃገርና የወገን ጥፋት ለማቆም አልቻልንም: በወቅቱ የነበረው የሁሉም ሃገራውያን የሆን ችግር በተናጠል በማየት በሃይማኖትም በኩል እምብዛም ትኩረት ሳይሰጠው በተለያዩ ወቅቶች በጅማ በአቦምሳ በሃረር በወሎ በስልጤ የሕዝብ ጭፍጨፋ የቤተክርስቲያን ቃጠሎ ያለው ጨቋኝ እምባገነን መንግስት በካድሬዎቹ(ሎሌዎቹ) አማካኝነት ሲፈጽም እንድነበር ዛሬም በገሀድ ገዳማትና የታሪክ ቅርሶችን ማውደም ሕዝቦችን ማፈናቀል ተያይዞት እናያለን: ይህ ስራዓት በጸሎትና በእርግማን በወረቀት ጽሑፍ ለማሸነፍ የምንሞክረው ሁሉ የዋህነት ከመሆኑ ባሻገር ከሚያደርጉት እኩይ ተግባራቸው ለመግታት አልተቻለም ስለዚህ ይህን አስከፊና የሀገር የወገን አሸባሪ ስራአት ለማብቃት ሁሉም ወገን አላንዳች ማመንታት በአንድ ወጥ ለሀገር ድሕነት ነፍጥ አንግቶ ጋሻ መክቶ ጦር ሰብቆ እምቢ ለዘረኞች በቃኝ በማለት መነሳት ይኖርብበታል::
እንዲሁም ዛሬ በኩራትና በትባት መብታችን ይከበር መሪዎቻችን እኛው እንምረጥ ብለው የተነሰት የኢትዮጵያ ሙስሊም ወንድሞቻችን ለአመታት የተከለከለውን የሰልፍ በመጣስድ ያላንዳች ፍራቻና አልበገር ባይነት በተከታታይ ላለፉት 14 ሳምንታት የወያነን አፈና በማጋለጥ ለክርስቲያን ወገኖቻቸው አራያ በመሆን የተነሱበትን አላማ አጋር በመሆን እንድነሱ ያላፍራቻ በጽናትና በትባት ለመነሳት ሁሉንም የክርስትና ተከታዮች የሆን በሙሉ ለዚህ በጎ ተግባር በመሳተፍ የሀገራችንን የሕዝባችንን ድሕነት ላማድረግ ይህን አረመኔ የሕዝብ ጠላት አይቀጡ ቅጣት ለመቅጣት በሓብረት እንነሳ::
ሁላችንም አንድልብ ከሆናችሁ በምቀኝነት እርስ በርስ ተዋግታችሁ: ካላለቃችሁ በቀር: ኢትዮጵያ ሀገራችሁን ለሌላ ለባእድ አትሰጧትም: ክፉ ነገር አገራችን አይነካትም ነፋስ አይግባባችሁ አገራችሁን በያላችሁበት በርትታችሁ ጠብቋት:
ወንድሜ ወንድሜ እየተባባላችሁ ተደጋገፉ:
የኢትዮጵያን ጠላት ተጋግዛችሁ ከድምበር መልሱ: የኢትዮጵያን ጠላት አንዱ ወገን አጥቅቶ ላንደኛው ወገን ተመሳሳይ እንድሚያደርግ አትሳቱ ጥቃትም ሲያደርስ በኔ ወገን ካልመጣ ምንቸውገረኝ ብላችሁ ዝም አትበሉ: ጠላት በመጣበት በኩል ኁላችሁም ሄዳችሁ በአንድነት ተጋግዛችሁ ጠላታችሁን መልሱ እስከ የቤታችሁ እስኪመጣ ዝም ብላችሁ አትጠብቁ: በማለት ታላቁ የኢትዮጵያ መሪ ዳግማዊ አፄ ምንሊክ የዛሬ 106 ዓመት የተናገሩት ቃል ለዚህ ወቅት እውነተኛ ምልክትና ሁሉንም የሚነካ በመሆኑ ለአንድነቱ ለሀገሩ ኩሩና ጀግና ሕዝብ ዛሬም እንደቀደምት አባቶቹ ታሪኩን ማንነቱን ጠብቆ ለተካታዩ ትውልድ የማስተላለፍ ኃላፊነት በጫንቃው ያለ በመሆኑ ከተወቃሽነትና ከተጠያቂነት ለመዳን ግዼታውን መወጣት ይጠበቅበታል
ሞት የተሰጠ የሰው ልጆች ጸጋ በመሆኑ በረሃብ በጠኔ በነፃነት እጦት በቁም ከሞሞት ክብርን ተጎናጽፎ ለዓላማ መሞት የታሪክ ሃወልት ሰማእትነት ነው:: ፍርሃት ለተገዥነት ያመቻል:
ድል ለመላው ኢትዮጵያ ሕዝቦች እንቅስቃሴ
ድል ለመላው የክርስትናና የእስልምና ተከታዮች
ውድቀት ለዘረኞች ለሆድ አደሮች መብት ላማይገባቸው
ኢትዮጵያ በነፅአነቷ ለዘላለም ትኑር
ዋልድባ ተደባ (ተፃፈ በወፉ)
ማድባት የሚለውን ቃል ርቢ ሳስብ ይገርመኛል አንዳዴም ያስቀኛል ሌላ ጊዜ ደግሞ ያስፈራኛል፡፡ … የቃሉን ፍችና የዘር ርቢ ትንታኔ ለቋንቋ ባለሙያዎች ልተወውና በተራ ሰው አስታሳሰብ ቃሉን ላዋልደው፡፡ ከተቻለም ላድባው፡፡ ማድባት፤አደባ፤ተደባ፤ ተደባባ፤ ተዳባቢ (የሚባል ካለው ተዳቡ፤ ተዳቢ፤ ተደባቡ፤ ድባታም (የእኔ ብቻ ነው ሊሆን ይችላል) ፡፡ የአድቢ፤ አዳቢ፤ መደባባት …ግርድፉ ትርጉም በአዕምሮ በልብና በመንፈስ ሲፈልግ የነበረውን ጉዳይ አሣቻ ጊዜ ተጠብቆ ማጥቃት፤ መደብደብ፤ ማራቆት ፤ማውደም …ሊሆን ይችላል፡፡ አሊያም ይፈልጉት የነበረውን ነገር ተፈላጊው ሲዳከም፤ ሲቀዘቅዝ ወይንም አቅም ሲያጣ ማጥቃት ማለት ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ግርድፍ የጨዋ ትርጓሜ ነው፡፡ የቋንቋው ሊህቃን ሊተቹበት ይችላሉ፡፡ ይህ ጥሬ ትርጉም ሳይሆን ከዚህ መጣጥፍ ጋር የሚያገናኘው መንፈሳዊ ፤ሃሳባዊና ይዘታዊ ትርጉሙ ግን ይኽ ነው፡፡ ከትርጉሙ ተነስተን ተደባ በሚለው ቃል ውስጥ ቢያንስ ሁለት አካላት አሉ፡፡ አንዱ አዳቢ ሲሆን ሌላው ተደቢ ነው፡፡ አድቢው ቂመኛ ከሆን ወይንም የህልውናው መሠረት ከተዳቢ ጋር የተገናኘ ሆኖ ሲገኝ አደባ የሚለው ግስ ህይወትና ነፍስ ዘርቶ በግዝፈተ አካል ውስጥ እናየዋለን፡፡
ስለማድባት እና አድብቶ ስለመያዝ ብሎም ሥለማጥቃት ሳስብ ከሰው ልጆች ይልቅ የእንስሳው አለም መሣጭ ነው፡፡ በጣም ይስባል፡፡ አድብቶ ከመያዝ ጋር የተገናኘ ድንቅየ ታሪክ በአብዛኛው የድመት ዘር ያላቸው ፤ሰማይ ጠቀስ የስም ፎቅ የተሰራላቸው ናቸው፡፡ ለምሳሌ አህያ በማድባት አትታማም ምክንያቱም የምትመገበው ሣር ተደቢ ሣይሆን የማይንቀሳቀስ በመሆኑ የማድባት ክህሎት አልተሰጣትም ወይም አላዳበርችም፡፡ ፈረስም ያው ነው፡፡ ላምም ብትሆን የማጥቃት ሳይሆን የመጠቃት አሊያም የመመገብ ባህሪ ነው ያላት ስለዚህም የማድባት ዝናዋ የፈረሰ ሳር ቤት ይመስላል፡፡ ላም ምናልባት እንደ ጎሽ በመሸሽ መከላከል ላይ ያዘነበለች እንስሳ ናት፡፡ ለነገሩ እነ ፍየል እነ በግ እነ ዶሮ እነ ዝሆን ጥንቸል…የመሳሰሉት በዚሁ ይመዳባሉ፡፡
ቅድም ያነሣሣኋቸው የድመት ዝርያዎች ግን ለመከላከል ብቻ ሣይሆን ለማድባትም የተፈጠሩ ናቸው፡፡ ያደባሉ ፤ያጠቃሉ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ ይሸፍታሉ፡፡…ከአድቢ የድመት ዝርያቸው መካከል ጥቂቱን ልጥቀስና አንበሳ፤ ነብር፤ አነር፤ አቦሸማኔ፤ ድብ እና ድመት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ የሚገርማችሁ በአገር አሜሪካ በአንደኛው ግዛት ውስጥ እነዚህን ሁሉ አይቻቸዋለሁ፡፡የዋልድባ መነኮሳት ግን በዋልድባ አይተዋቸው ያውቁ ይሆናል፡፡ ቢያንስ በጻድቃን ሰማዕታት የሥነ ሥዕል ጥበብ ውስጥ ስለሚገኝ ሃሳቤ ሃሳባዊ ፍሰት ብቻ አይደለም በመረጃ የተደገፈ እንጂ፡፡ ከድመት ውጭ ሌሎች እንዴት እንደሚያደቡ፤ እንደሚደባቡ በቴሌቪዥን መስኮት አይቻለሁ፡፡ እውነቱን ልናገርና አንድም ቀን በአካል በእነዚህ እንስሳት ተደብቼ አላውቅም፡፡ የዋልድባ መነኮሳት ግን ሳይደቡ አይቀሩም ኑሮአቸው ከእነሱው ጋርም አይደል፡፡
ወደ ዋናው ነጥብ ከመሄዳችን በፊት እኛ ቤት አጠገብ ይኖር የነበረ አንድ ቀለሙ በውን ተለይቶ ይህ ነው የማይባል ድመት ነበር፡፡ በርግጥ ግነት በሌለበት ሁኔታ ድመቱ የጋሼ ሃጎስየ ድመት ነበር፡፡ ሃጎስየ የተዋጣለት ቀለም ቀቢ ነው፡፡ ብዙ ልጆች ቢኖሩትም ሁለቱን የሃጎስየ ልጆች ቹቹና ፋኑኤልን አስተውሳለሁ፡፡ ባለቤቱ ደስታየ የምትባል ጎጃሜ ነበረች፡፡ ቹቹየን የምናስታውሳት የመጀመሪያዋ የሃጎስየ ልጅ በመሆኗና ቹቻሬ ቸርቻሬ እያልን በልጅነታችን እንቀልድባት ሥለነበር ነው፡፡ ፋኑኤልን የማንረሳው ደቢዞ ከሚባለው ድመታቸው ጋር ናጫ ግራጫ በመሆኑ ነው፡፡ ደቢዞ የተባለው በቀለሙ ጥቁር አይሉት ግራጫ ቀለም ሥለነበረው ነው፡፡ ሃጎስየ ጨዋ እግዚአብሔርን የሚፈራ በዚያውም ልክ ታምራት ገለታን የሚያስከነዳ ጠንቋይ ተከታይም ነው፡፡ ይህ ጠንቋይ የሚስቱ አጎት ሲሆን ባልሣሣት የጁቤ የሚባል አገር በርሃ የታወቀ አመላካች ነው፡፡ አንድ ጊዜ ፋኑኤል እንደነገረኝ ሃጎስየ በጠና ታሞ የየጁቤው ጠንቋይ ነፍስህን የያዝኋትን እኔ ነኝ፡፡ አባይን ስትሻገር ቀልብህ ካንተ ጋር አልነበረችም፡፡ በጨርቅ ጠቅልየ እኔ ነኝ አባይን ያሻገርኳት ብሎት እኔ ነኝ ያለ ዕጅ መንሻ (ሥጦታ ) ጠንቋዩ ከሃጎስየ እንደተቀበለ አጫውቶኛል፡፡ ፋኑኤል የሚያጫውተኝን ነገር ምንም እንኳ በዕድሜ ታናሼ ቢሆንም ለመረዳት እጅግ ጠሊቅ ነበርና አሁን ድረስ ትዝ አይለኝም፡፡ ይች በጨርቅ ጠቅልሎ ነፍስን የማሻገር ነገር ግን ገብታኝም አስቃኝም አልፋለች፡፡
ወደ ደቢዞ ልምጣና ደቢዞ ከፋኑኤል በፊት ቤት ውስጥ የመጡ ሴትና ወንድ ድመቶች የልጅ ልጅ ነው፡፡ ሥለዚህ ደቢዞ የሃጎስየን ቤት ከቹቻሬና ከፈኑኤል ጋር ባለርስት ነው ማለት ነው፡፡ የመልኩ ጥቁረትና ቀለማ ቀለምነት የመጣው ከእርስቱ ለማፈናቀል በሚሞክረው በአዲሱ ይገባኛል ባይ ተወላጅና በአውራሹ ሃጎስ ምክንያት ነው፡፡ ፋኑኤል ጭራውን ቆርጦታል እግሩንም ሰብሮታል ደቢዞም የፋኑኤልን እጆች ካርታ ስሎባቸዋል፡፡ እንዲያውም አይነ ስሩ (የአይኑ ስቡ ላይ) ረጅም ቦይ የወጣው በደቢዞ ንድፍ ሥራ ነው፡፡ የሁለቱ ወራሾች የፋኑኤልና የደቢዞ ፉክክር የይሳቅና የእስማኤል ትግል ያዕቆብና የኤሳው በሆድ ውስጥ ያደረጉትን ትግል አስመስሎታል፡፡ የይሳቅና የእስማኤልን ትግል ቅዱስ መጽሐፍ እንዲህ ብሎ ያስቀምጠዋል፡፡ አብርሃም ከቤተሰቦች ጋር ከሚኖርበት አገር እግዚአብሔር ጠርቶ ዘርህን እንደ ምድር አሽዋ እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛዋለሁ ብሎ መካኖችን አብርሃምንና ሣራን ተስፋ በተስፋ አምበሸባሻቸው፡፡ ድንቅ ተስፋ ተመገቡ፡፡ይሁን እንጂ ይህ ተስፋ ዘገየ አብራሃምም አረጀ ሚስቱም ሣራ ደከመች በመሆኑም ሰወኛ ዘዴ ዘየዱ፡፡ ሃሳቡን ያመጣቸው የአብርሃም ባለቤት ወ/ሮ ሣራ ናት፡፡ ወይዘሮ ሣራ መካንነቷን አምና ስለተቀበለችው መካን ያልሆነች ኮረዳ ስትፈልግ አጋር የምትባል ሰራተኛዋ ጡቶቿ ያጎጠጎጡ ውብ ተክለ ሰውነት እንዳለት የተመለከትችው አሮጊቷ ለባለቤቷ ተመኘቻት፡፡ ደግ ዘመን ነበር ያስብላል፡፡ ባህላዊውም የብዙሃን ጋብቻ (ፖሊጋሚ) ይፈቅድ ስለነበረ ሊሆንም ይችላል የሳራ ልስላሴ፡፡ የሣራ የሚስት አማጭነት ወይንም አደራዳሪነት የተሳካ የድለላ ስራ ነው ብንለው ያስኬደናል፡፡ ኪራይም ሊሆን ይችላል፡፡ ኪራይ ሰብሳቢ ብትሏትም ያዋጣል፡፡ በኪራይ ሰብሳቢነት መክሰስ ብቻ ነው የማይቻለው፡፡ ኦኦ ለካነስ በሌለችበትም ቢሆን መክሰስ ይቻላል፡፡ ለማንኛውም አጋር ይግባትም አይግባትም አብርሃም በሣራ ጠቋሚና ፈቃጅነት የገባው ልጅ ለመውለድና ለዚህ አላማ ብቻ ነው፡፡ ለመሰንበት አይደለም፡፡
ይገርማል የተባለው አልቀረም እግዚአብሔር ዘገየ እኔው ራሴ የራሴን ቤት ልስራ ብሎ ከአጋር ጋር እስከሚገባው ድረስ ዘሎ ዘሎ ወንድ ልጅ ከእነ ቃጭሉ ዱብ አደረገ፡፡ ዱብ አለ የሚለው ስም ከዚሁ ጋር ይገናኝ አይገናኝ አላውቀም ዱባለችም ብትሆን ከዚያው ዱብ አለ ከማለቱ ጋር ሊገናኝ ይችላል፡፡
ህጻኑ ልጅ እስከ አስራ አራት አመቱ ድረስ እንደ ወራሽና ጀግና ወተቱንም እየጠጣ ማሩንም እየላሰ ከብትም ጥጃም እየጠበቀና እያለበ አደገ፡፡ አቤት የእስማኤል ደስታ ብዙ ነበር፡፡ እስማኤል ሳቂታ ልጅ ነበር፡፡ እስማኤል ፈገግተኛ እንዲያውም ጥርሱ ገዳይ የሚሉት አይነት እንደ ነበር እገምታለሁ፡፡ በጣም ተንተክታኪ ነበር፡፡ ምንም ጥያቄ የለውም ለዚህ ሁሉ ማስረጃ ዓለ፡፡ የሚገርማችሁ ቀና ያለ ፍጡር ነበር፡፡ ተወዳጅ፤ ጠላት የሌለበት፤ ሴራ ያልተሰራበት እና ተፈልጎ የመጣ ነበር፡፡ እነ አብርሃም ጎጃሜዎች ቢሆኑ ኑሮ የእስማኤልን ስም ግጥም የሚገጥም አድርገው ያወጡለት ነበር፡፡ ትዝ አይላችሁም ሙሉቀን ዘነበ ፤እያደር አዲስ፤ አዲስ አለማየሁ ፤ታመነ እንዳላመው እንደሚለው ለእስማኤልም ጎጄዎቹ ጨለማ ተገኑ፤ ለጊዜው ጠብቀን፤ ስፈልግህ መጣህ ፤መሻቴ ወይንም ምኞቴ ሊሉት ይችሉ ነበር፡፡ ለማንኛውም እስማኤል እስማኤል ተብሏል፡፡
ማን ነበር የሰው ሥራ ሲያቆም የእግዚአብሔር ይቀጥላል ያለው፡፡ ሰው ሲጨርስ እግዚአብሔር ይጀምራል ያለ ሰባኪም ነበር፡፡ እኔ ማንም ይበለው ማን ዋናው የእኔ ንግግር አለመሆኑን ለማሳየት ብቻ ስለሆነ ተግባሬ ምንጩ ውል ባይልልኝም ችግር የለም፡፡ በአብራሃምና በሳራ ሕይወት የሆነው ይኼ ነው፡፡ አብርሃምና ሳራ ለረጅም አመት ጠብቀው ፍትዎተ ስጋ ለመፈፀም እንኳን በማይችሉበት ጊዜ እግዚአብሔር መጣ፡፡ እዚሁ ጋር አንድ ጊዜ ቆም እንበልና ፍትወተ ስጋ ያለው ማነው? ይህ አባባል ፍትዎተ መንፈስ አለ ማለት ነው የሚለውን ሃሳብ ይወልዳል፡፡ የወንድና የሴት የፍቅር ግንኙነት በጋብቻ የተቀደሰ ከሆነ መንፈሳዊ ነው፡፡ ስለዚህ የስጋ ስራ ሳይሆን ሁለንተናዊ የሰው ልጅ ተራክቦ ነው፡፡ እንቀጥልና ለማንኛውም ሳራም ሆነች አብራሃም ለአልጋ (ለመደብ) ጨወታ ባልበቁና በማይችሉበት ጊዜ ሁሉን እችላለሁ ያለው አምላክ ጨዋታውንም፤መፀነሱንም፤ መውለዱንም ፈጽሞ ሌላ ባለቃጭል ከሳራ ማህፀን ዱብ አለ፡፡ ሰው ሁሉ እማማ ሳራ ወለደች እያለ ሳቀ ፤ተንከተከተ፤ ተፍነከነከ …የፍንክንክ ቤት ሆነ ሣቅ በሣቅ …፡፡ እኔ እምለው እዚያ ቤት ውስጥ ከአጋርና ከእስማኤል በስተቀር በጥርስ የተሳቀ አይመስለኝም፡፡ በድድ እንጂ፡፡ ምክንያቱሳ? አብርሃምና ሳራ እጅግ አርጅተው ስለነበር እና ይስሀቅ ጥርስ ሲኖረው በጥርሱ ይስቃል እንጂ እርሱም ስላላወጣ በድድ ነበር የሚንከተከተው፡፡ ይህ ነገር አንድ ግጥም አስታወሰኝ ፈገግታ ትላለች፡፡
ፈገግታ
የሁለት አለም መገለጫ
ተሸካሚ እውነት ውሸት ሞላጫ
ሰው ሲታለል በውጫዊው መገለጫ
ጉድ በኖርስ በደንብ ላየው ፤ከኋላዋ መቀመጫ
…
ማን ያውቃታል ለመተረክ
ገላጭ ብትሆን የመፍነክነክ
ሸፋኝ ብትሆን የመብረክረክ ፤
ውልድይኖራት ከሁለቱ
አንድ በደስታ!
አንድ በዋይታ! (ቡቃያ ገጽ 15)
ለማንኛውም ሁሉም ሲስቅ ሳቅ በሳቅ ሲሆን አዳሜ ሆዱ እስከሚፈርስ ሲንከተከት ምንም ያላለችው ሳራ የሰው ነገር ነውና ውለታዋን ረስታ እስማኤል በይስሐቅ ላይ ሲስቅ ፈገግ ሲል አይታውም ሊሆን ይችላል እስማኤልንና እናቱን አጋር አይናችሁን ላፈር አለቻቸው፡፡ እንዲያውም ከቤቴ ካልወጡ ብላ አበርሃምን አስቸገረችው፡፡ አብርሃምም ቸገረው፡፡ አወጣ አወረደ ፀለየም እግዚአብሔርም ሳራን ተባበራት፡፡ የእግዚአብሔር ከሳራ ጋር መተባባር በስነ አመክንዮ ትክከል ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም እስማኤልን ለመውለድ እነ አብርሃም ሲመካከሩ አብሮ አልመክርም ችግር ሲመጣ ነው ያማከሩት፡፡ በሌላው ጎኑ እግዚአብሔር ከጠብ ይልቅ ለሁለቱም ሰላም ለማምጣትና ያሰበውን በረከት ለመስጠት ነው፡፡ የሳራ ግን ውለታ ቢስነት ነው፡፡ እስማኤል ወጣት አይደል ይሄኔ እኮ የሳቀው ምናልባት የይስሐቅን ቀሚስ ያልበሱ ቃጭል አይቶ ይሆናል፡፡ አብራሃም ባለ ሁለት ቃጭል ልጅ ሆኖ በደስታ ሲፍነከነክ ግን ሳራ አልተበሳጨችም፡፡ ይገርማል፡፡ ለማንኛውም የእስማኤል ፈገግታ ሳራን አብከነከናት፡፡ የአንዳንዱ ፈገግታ ገንዘብ ያመጣል፡፡ የአንዳንዱ ፈገግታ ደግሞ ከርስት ይነቅላል፡፡ በሳቅህ ምክንያት አብረህ ከልጄ ጋር አትወርስም ነው የተባለው፡፡ ከቤትም የወጣበት ምክንያት ፈገግታ አብዝቶ ነው፡፡ ኮስተር ማለት አቅቶት፡፡
ይህን ወግ ያመጣሁበት የደቢዞ ጉዳይ እየከነከነኝ ነው፡፡ የደቢዞ አያቶች የመጡት ቅድም እንዳልኳችሁ መጀመሪያ እነ ሃጎስየ ልጅ ሳይወልዱ በመቆየታቸው ወደ የጁቤ የበርሃ ጠንቋይ ሂደው አስጠነቆሉ አሉ፡፡ ጠንቋዩም ወንድ ልጅ በዓመቱ ትወልዳለችሁ አላቸው፡፡ እንደተባለውም ልጅ ተፀነሰ፡፡ የጠንቋዩ ጥንቆላ ሠራ፡፡ የሠራው ግን ለዘጠኝ ወር ብቻ ነው፡፡ ወንዱ ልጅ ሲጠብቅ ቹቻሬ ተወለደች፡፡ እስማኤል መጣ ማለት አይደለም? ወንድ ልጅ በጥንት ዘመን ምን ያህል ተፈላጊ እንደነበር ማስታዎስ ይችላል፡፡ ሃጎስየም ይህንን ሲያይ እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ ሚስቱን ደሰታየን ከአዲሷ ልጃቸው ቹቻሬ ጋር የእቃ ያክል አንጠልጥሎ በወሩ ጠንቋዩ ቤት ከተፍ አለ፡፡ መጀመሪያ ላይ የሃጎስየ ብስጭት ከመጣበት ከወንዙ በመሆኑ ወዲያው የሚበርድ ነው ብላ ሚስቱ ደስታየ አለተገረመችም እንዲያውም ሃጎስየ “ቧ” ሲል በልቧ “ቡ” ትል የነበረችው ደሰታየ የዛሬው የተለየ በመሆኑ ከጠንቋዩ አጎቷ ጋር ተጣልቶ እንዳይቀሰፍ ሳትሰጋ አልቀረችም፡፡ “እኛ አንፈልግም አቡነ አረጋዊ ነው የምልሽ ልጃችንን ያምጣ አለበዚያ ምናምን አድረጌ በቴስታ ወይንም በቴስታታ ይህን አጎትሽን ተርትሬው ነው የምሄደው አቡነ አረጋዊን” አለሃጎስየ፡፡ ደስታየ ደንግጣለች፡፡
በዚህ ወኔ ነበር ሃጎስየ ወደ ጠንቋዩ ቤት የደረሱት፡፡ ወደ ውስጥ ሲገቡ ገና የዕጣኑን፤ የጋያ ጪሱን፤ የጫቱንና እና የቡናው ሽታ ሃጎስየ በአፍንጫው ሲስበው አምልክ አምልክ አሰኘው፡፡ ወዲያው ሃጎስየ ወኔው በጭስ መልክ በላብ ወጣለት መሰለኝ ቀለሙ ቀላ ያለው ሃጎስየ በግንባሩ እየሰገደ ወለሉ ላይ ሲነጠፍ ላየ ሰው በቄጤማው ላይ የተነጠፈ ቀይ ስጋጃ ይመስል ነበር፡፡ ሃጎስየ ምን አላፋቸሁ ሌላ አጥንትና ደም የሌለው ቄጤማ ሁኖአል፡፡ ግን የሚናገር ቄጤማ “ይቅር በለኝ ጌታየ ይቅር በለኝ ጌታየ” እያለ ሲለፈልፍ ደስትሽ ጎጃሜዋ “ቦቅቧቃ ለዚህ ነው…ትል የነበረው” ሳትል አትቀርም፡፡ ጤንሽ ጎጃሜ አይደለችም ወሬ የማያበዛ ጀግና ሳትማልል አይቀርም፡፡ እንዲያውም ትታማለች ይባላል፡፡ ቀብረር ያለ ሰው ትወዳለች፡፡ ቀብራራው ጎጃሜ የሚለውን ዘፈን እየሰማች አይደለም ያደገችው፡፡
ጠንቋዩም ለመሆኑ ምን እየተናገርክ እንደመጣህ ሰምተናል በፈረሴ ላይ ምን እንደተናገርክ አውቀናል በፊቴ መውደቅህ አዳነህ፡፡ ለመሆኑ ምን አመጣህ አለ፡፡ ሃጎስየም የሰጠኸን ሴት ልጅ ስላስደሰተችኝ ላመሰግንህና ወንድ ልጅ እንድትመርቀኝ ነው አለው፡፡ የሰጠሁህ መጀመሪያ ወንድ ልጅ ነበር ግና የአየሩ ጋኔል ሴት አድርጎብህ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ሦስት ወንድ ወንድ በላይ በላይ ትወልዳላችሁ አላቸው፡፡ ነገር ግነ እኔ የማዝህን መፈጸም አለብህ አለው፡፡ ሃጎስየም እሺ እሺ አለ በፍረሃት እየራደ፡፡ ደስታየም ሳቋ መጥቷል፡፡ ጠንቋዩ ቤት እየከደመች ስላደገች ቦታውን ትንሽ ደፈር አድርጋዋለች፡፡ ሥርዐቱንና አምልኮውን ዘና ብላ የምታየው፡፡ በልቧም በድጋሚ “ቦቅቧቃ” አለች፡፡ወደ ሌላ ሴት እማግጣለሁ ብትል ግን እዚህ አምጥቼ አንቀጠቅጥሃለሁ አለች በልቧ ፡፡ “ቡኮ” አለች ድምፀን አውጥታ፡፡ ጠንቋዩም ምን ተናገረሽ ደስቱ አለ፡፡ ለካንስ ድምፅ ተሰምቶ ኑሯል ፡፡ አይ እኔ እንኳን ቡኮየን እንድተባርክልኝ ነው አለች፡፡ ጠንቋዩ አጎቷም የልጅ ነገር ሁሉ በአንድ ጊዜ መቼ ይሆናል፡፡ እንደተሸወደ አላወቀም፡፡ የልጅ ጉዳዩን መጀመሪያ እንጨርስ አለ ጠንቋዩ አጎቷ ፡፡
በመቀጠል ጠንቋዩ ትዛዝ ሰጠ፡፡ ትዛዙም በግቢው ውስጥ የተቀመጡ ሁለት ጥቋቁር ድመቶች ነበሩና እነ ሃጎስየ ወደቤታቸው ይዘዋቸው እንዲሄዱና እዚያም ወንድ ልጅ መውለድ እንዲችሉ የሚያደርጉና ጋኔን ፆታ እንዳይቀር የሚከላከሉ ናቸው፡፡ በሌላ አነጋገር መብረቅ መከላካያ ቤታቸው አስገቡ ማለት ነው፡፡ ወይንም የተረገዘው ወንድ ከሆነ በኋላ ሴት ከሆነ፤ የተረገዘችው ሴት ከሆነች ወንድ አድርጎ የሚቀይር ጋኔልን የሚያንበረክክ ሃይልን ተቀብተው የሚንቀሳቀሱ አማልክት ናቸው ማለት ነው፡፡ ለማንኛውም ሃጎስየ የድመት አማልክት ቤቱ ውስጥ አስገብቷል፡፡ ዛሬ የፆታ ቅየራ በሽበሽ በሆነበት ጊዜ ቢኖሩ ኖሮ በያገሩ እንደ አንዳንድ የማህበራዊ ሳይኮሎጂ ጠበብት ተደርገው ምክር ለመለገስ አለምን በሃዋርያዊ ጉዞ በዞሯት ነበር፡፡
እውነትም በመጀመሪያው ባይሰራለት በሁለተኛው ሰርቶለት የየጁቤው ጠንቋይ እነዚያ ጥቋቁር ድመቶች ብዙ ወንድና ሴት ልጆች በወለዱ በወሩ ሃጎስየና ደስታየ ቀይ ቃጭላም ወንድ ልጅ ዱብ አደረጉ፡፡ ፋኑኤል እንግዲህ በዚህ ምክንያት ነው የተወለደው ማለት ነው፡፡ በሣይንሱ ከሆነ ሃጎስየ ከደስታየ ቹቻሬንና ፋኑኤልን አንድ ሴት አንድ ወንድ ወልዷል ማለት ነው፡፡ በጠንቋዩ ስሌት ሃጎስየና ደሰታየ ሁለት ወንድ ልጆች ወልደዋል ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ቹቻሬ ወንድ ሆና ሳለ የአየሩ ጋኔኤል ወደ ሴትነት ቀይሯት ነው፡፡ ቹቻሬ ግን እስካሁን ወንድ የመሆን ስሜት (ሆርሞን) አለብኝ ስትል አልተሰማችም አግብታ ወልዳ ሊሆንም ይችላል፡፡ የፋኑኤል መወለድ እንግዲህ ከድመት ስነ ልቦና ይገናኛል ማለት ነው፡፡ እነዚያ ድመቶች የደቢዞ አያቶች ናቸው፡፡ በሌላ አነጋገር ፋኑኤል የሃጎስየ ልጅ ብቻ ሳሆይን የድመት ውጤትም ነው ማለት ነው፡፡ የጡቋቁር ድመቶች የመንፈስ ልጅ ነው ብንል ያስኬደናል፡፡ ደቢዞም ቢሆን የ እነ ሃጎሰየ የስጋ ልጅ ባይሆን የጉዲፊቻ ልጅ ነው፡፡ ደቢዞና ፋኑኤል ወንድማማች ናቸው ማላት ነው፡፡
ከዕለታት አንድ ቀን ደቢዞ በፋኑኤል ላይ ሚያው ሚያው ሲልበት ደስታየ ተመለከተች፡፡ ደሳተም ሃጎስየን ይህ ድመት ከቤቴ ካልወጣ በማለት አንቃ ያዘችው፡፡ ሃጎስየም አይ ይህ አይሆንም ባለውለታችን ነው፡፡ ወዲያውም ደግሞ አብረን ለብዙ ዘመን ኖረናል በማለት ይመልሳል፡፡ በዚህ ምክንያት በባልና ሚስቱ መካከል ትልቅ አምባጓሮ ይነሳል፡፡ይባስ ብሎ ደቢዞ አንድ ቀን ምክንያቱ ባልታወቀ ጉዳይ ይበሳጭና በፋኑኤል አይነ ስብ ላይ የየጁቤ ከተማን ስሎ ጠበቃቸው፡፡ እናትና አባት አበዱ፤ ተጣሉ፤ ቄጤማው ሃጎስየ መጨከን አቃተው፡፡ በዘህ ምክንያት ተያይዘው ወደ ጠንቋዮ ቤት ወረዱ፡፡ ጠንቋዩም በምን ምክንያት እንደመጡ ጠየቃቸው እነሱም ችግራቸው ደቢዞ እንደሆነ ነገሩት፡፡ ጠንቋዩም ማነው ደቢዞ ብሎ ጠየቃቸው፡፡ ሃጎስየም የተረሱትን የጥቋቁር ድመቶች ታሪክ አንስቶ በማብራራት ዝርያው ያው አንዱ የጥቋቁር ድመቶች የልጅ ልጅ መሆኑን አስረዳ፡፡ ጠንቋዩም ደቢዞን ማን አስቀምጡ አላችሁ እኔ አያቶቹን እንጂ ስለ አሁኑ የልጅ ልጆች ታሪክ የማውቀው ነገር የለኝም አለ፡፡ አያቶቹን እንኳን ተንከባክባችሁ በሰላም እንዲያነቀላፉ አደረጋችሁ በማለት ሳያመሰግናቸው አላለፈም ፡፡
ደስታየ ወዲያውኑ ውለታዋን እንደ ሳራ ረስታ ይውጣብያለሁ አለች፡፡ ጠንቋዩ ግን አይፈረድበትም ደቢዞን አያውቀውም፡፡ ያም ሆነ ይህ ጠንቋዩ ደቢዞን አዳክመው፤ ነጭተው፤ አናጭተው፤ ቆራርጠው እና አቆራርጠው ማስወጣት እንጂ እንዲሁ ቢያስወጡት ፋኑኤል የመጣው ከድመት ጋር በተገናኘ ሁኔታ ስለሆነ ይሞታል አላቸው፡፡ ደቢዞ ሳይፈለግ ተፈላጊ ሆነ ማለት ነው፡፡ ይህ ግን ለጊዜው ነው፡፡ በመሆኑም ደቢዞ ከቤት ከመውጣቱ በፊት እንዴት መዳከም እንዳለበት በጠንቋዩ ነገራቸው፡፡ መጀመሪያ አዳክሙት ከዚም ውጣ አትበሉት እንዲወጣ አድርጉት እንጂ፡፡ ውጣ አትበሉት እንዲወጣ አድርጉት የምትለዋን ቃል ጎጃሜዎች ለመጀመሪያ ጊዜ የሰሙት በጠንቋዩ ምክር ሃጎስየ ሲያወራት ነው ይባላል፡፡
ጠንቋዩ የሰጠው ትዕዛዝ የሚከተለው ነው
1ኛ ፋኑኤል የደቢዞን ጅራት በመጥረቢያ እንዲቆርጥ ይደረግ፡፡ምከያቱም የፋኑኤል ታሪክ ከድመት ጋር የተያያዘ በመሆኑ፡፡ የታሪክ ብጣሴ ከሌለ ሁልጊዜ ከድመት ጋር የተያያዘ ታሪክ ሊኖረው ነው ማለት ነው፡፡ ደቢዞ ካለ ፋኑኤልም በጥንቆላ የመጣ መሆኑ ሁልጊዜ ሊታወስ ነው ማለት ነው፡፡ ይህ ለፋኑኤል አደገኛ ነው፡፡ ጅራት ታሪክ ነውና፡፡
2ኛ ፋኑኤል የደቢዞን ሁለት የፊት እግሮቹን እንዳይሰሩ አድርጎ ይስበር፡፡ ርቆ ወደሌላ ቦታ እንዳይሄድና ከሌላ ድመት ጋር እንዳይዋለድ ከዚያም እንዳይጠናከር፡፡ ዝርያው ከቀጠለ የሃጎስየ ልጅ የፋኑኤል የምግብ ዋስትና ተበጠሰ ማለት ነው፡፡
3ኛ ደስታየ ለደቢዞ ምግብ ሙሉ በሙሉ ሳትከለክይው አስረበሽ ግደይው የሚል ነው፡፡ ሙሉ በሙሉ ከከለከልሽው ወደ ሌላ ቤት ሂዶ ይቀላውጥና ይወፍራል አሊያም የነብር ዘር ስለሆነ ይሸፍታል፡፡ ከሸፈተ ደግሞ ይሰነብታል፡፡ከሰነበተ ደግሞ ለፋኑኤል…
4ኛ ሃጎስ ቀለም ከምትቀባው አዳዲስ ቤት የሚተራርፈውን ልቅላቂ እየወሰድክ ባገኘኸው አጋጣሚ ሁሉ በላዩ ላይ ድፋበት መልክ እንዳይኖረውና ሰው እንዳያውቀው፡፡ በዚያውም በእንስሳው ላይ የምታደረሱትን ሰው እናዳያውቅ ያደርጋችኋል ፡፡ ባለውለታው ደቢዞ ላይ ይህ ተዶለተበት፡፡ የርስት ጉዳይ ለችጋራሙ ሃጎስየ ዋና ነገር ነበርና ለውሳኔ ተቸኮለ፡፡
የፋኑኤልና የደቢዞ ጠብ እንግዲህ ጭንቅላቱ ከጥንቆላ ጋር የተያያዘ ነው የምለው ለዚህ ነው፡፡ አንድ ቀን ረፋዱ ላይ ሃጎስየ አገር የሚያክል ሙክት ቤቱ ውስጥ ይጥላል ( ያርዳል) ሁሉም ደስ አለው፡፡ ደቢዞም ማጨብጨብ ባይችል በምላሱና በመዳፉ አፉን አሟሸ፡፡ ደቢዞም እንደገና በበጉም በፋኑኤልም ከት ብሎ ሳቀባቸው፡፡ ደስታው ትልቅ ነበርና፡፡ ቹቻሬ በነገራችን ላይ ሁሉን ነገር ተመልካች ናት የስነልቦና ቀውስ ከልጅነቷ ደርሶባታልና፡፡ የቤቱ ውስጥ ትግል እንዳነበባችሁት የሁለቱ ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜ ፋኑኤል ደቢዞን ከቹቻሬ ጋር ለማጋጨት ሞክሯል፡፡ ድንገት ደቢዞ አንገት ላይ ዳዋ የሚባል ውሻ የሚታሰርበት ሰንሰለት ሲጠልቅ ግራ ገባው፡፡ወዲያውኑ ፋኑኤል በአባቱ እርዳታ ትልቅ መጥረቢያ አምጥቶ የደቢዞን ጅራት ከተፈው፡፡ የደቢዞ ደም ከታረደው ሙክት በላይ እንደወንዝ ጎረፈ፡፡ ደቢዞ እጅግ አለቀሰ የቤት ውስጥ ልጆች ቀላል ንትርክ ወደ መረረ ቂም በቀል ተሻገረ፡፡ እንደዚያ አይነት ክፋት ገጥሞት አያውቅም፡፡ ሸሽቶ ከቤት እንዳይወጣ ያንን ሙክት ለአንድ ቀን ካበሉት በኋላ ፋኑኤል በእናቱ እርዳታ ትልቅ የብረት ዲጅኖ አምጥቶ እገሩ ላይ ጣለበት፡፡ አወይ ድግስ ያስብላል፡፡ ሁለቱም የፊት እግሮቹ ተሰባበሩ፡፡ ደቢዞም አለቀሰ፡፡ ለምን ግን አለ… እንዲህ ተጨከነ አለ፡፡ ሊገሉት እንደፈለጉ አልገባውም፡፡ እንዳይሸሽ ምግቡን አስረው ያበሉት ጀመር፡፡ ደቢዞ ሁለት ቀን በማይሞላው ቀን ጅራተ ጎራዳ እግረ ሰባራ ሆነ፡፡ ደቢዞ ላይ የሆነው ነገር በአጭር ጊዜ ይሁን እንጂ ዱለታው የሰነበተ ነው፡፡ ካሳምንታት ጊዜ በኋላ ደቢዞ ተፈታ፡፡ ለደስታየ በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ለደቢዞ ምግብ መከልከል ተጀመረ፡፡ለም የሆነ ስጋ ተነፈገው፡፡ አጥንት ብቻ ይጣልለት ጀመር፡፡ ሃጎስየም ያገኘውን የቀለም ልቅላቂ ሁሉ ይደፉበት ጀመር፡፡ የሰፈሩ ሰው ሁሉ ጎምላላውን፤ ቀብራራውን፤ ደቢዞን ረሳው፡፡ ደቢዞ ግን ደቢዞ ነው፡፡ ደቢዞ ሩጦ የሚደርስበት፤ አባሮ የሚገድለው ፤የሚያሸንፈው አንድም አልነበረም ቤተሰቦቹ በሸር፤በተንኮል አጠቁት እንጂ፡፡ ዛሬ ደቢዞን ማንም አያውቀውም፡፡ አንዳንዱ ቤት አጥፊ የጫካ ድመት ይመስለዋል፡፡ ደቢዞ ግን የቤት ማገር፤ አያቶቹ የሃጎስየ ልጅ የፋኑኤል መገኘትም ፤መምጣትም ምክንያት ነበሩ፡፡
“ማነው ወርቁ ደበዘ ያለው…” እኔ የምለው ይህ ሁሉ በደቢዞ ላይ ግፍ ሲሰራበት የድመት መንጋ የት ነበር? የአይጥ መንጋማ በደስታ ድግስ ላይ ነበር፡፡ ደቢዞ ቢጠፋ አይጦች በሰላም የሚኖሩ ይመስላቸዋል፡፡ ድመት ቢጠፋ እኮ የአይጥ ቅልብ ይመጣና ሰውንም እህሉንም አይጡንም ማስቸገራቸው አይቀርም፡፡ እኔ የምለው የአይጥ ጠላት እኮ ድመት ብቻ አይደለም ለነገሩ አይጥ አያስብ የት ይገባውና፡፡
ደቢዞ ስሞ ተለውጦ ነው ደቢዞ የተባለው፡፡ አንዲት በልጅነታቸው ቀለም ወዘና የነበራቸው ሴት ወይዘሮ፤ውበት እንደነበራቸው የሚያስታውቅ ተክለ ሰውነት ያለቸው ሴት ሃጎስየ ከሚያከራያቸው ቤቶች ውስጥ ተከራይተው የሚኖሩ ናቸው የቀለም ልቅላቂ በላዩ ላይ ስለደፋበት ቀለሙ ለቆ እግሩ ተሰባብሮ ጅራቱ ተቆራርጦ ባገኙት ጊዜ ነው አሉ “የማነው ይኼ ደቢዞ ምን ይመስላል ያሉት፡፡” እሳቸውም ወዘናቸው ጠፍቶ መለስተኛ ደቢዞ ሆነው ሳለ በአይንህ ላይ ግመል ተቀምጦ ትንኝ ታጠራለህ እንዳለው ሆነው ለደቢዞ ስም አወጡለት፡፡ ደቢዞዋ ደቢዞ ብለው ስም አወጡ፡፡ ደቢዞ ቃል የለውም እንጂ ጩኸቴን ቀሙኝ ይል ነበር፡፡
የደቢዞ የጥንት ስሙ “በለው” ነበር አሉ፡፡ ለነገሩ “በለው” እየተባለ ሲጠራ እኛም በመጠኑ ደርሰንበታል፡፡ አዲስ ስም ይጣፍጥ የለ ደቢዞን ሃጎስየም ለምዶት አይጥ ሲያስቸግረው ደቢዞ የት አለ? የለም እንዴ ማላቱ አልቀረም፡፡ ማስፈራሪያ አድርጎታል፡፡ አቤት የደቢዞ ግፍ! ወደዋናው ነገረ ጉዳይ ልመለስና ለጥቂት ጊዜ አንገቱን ከደፋ በኋላ የእነ በለው ዘር አይደል ምግብ ሲያጣ አደን ጀመረ፡፡ ሸፈተ፡፡ ወይንም ፋኖ ሆነ፡፡ አንድ ገጣሚ እንዲህ እንዳለው
ፋኖ ፋነነ
ከውርደት መነነ
ጅላጅል በመሆን እንዲያው ተጀነነ
ከውርደት ይሻላል በጫከው የዋለ
ከመዳጥ አምልጦ በዱር ነሆለለ
ሲታይ አልገባውም ለብልጣብልጦቹ
ለሚሞዳሞዱ ለሚመቻመቹ
ዳሩ ነቅቶ ዘርቶ
አረምን ኮትኩቶ
ትዳርን ያውቀዋል ነፃነት ጨምሮ
ለዚህ ነው ምናኔው ነቅቶ ገና ድሮ (1999)
ለማንኛውም ደቢዞ ከእኛ ቤት ፊት ለፊት ባለችው ጫካ ውስጥ ሸመቀ፡፡ ደቢዞ የጥንቱን ስም በለውን ይዞ አደን ሲጀምር አርጅቶ ነበርና ከበድ አለው፡፡ ነገር ግን ዝርያው በውስጡ ነበርና እንደ አንበሳ በድፍረት፤ እንደ አቦሸማኔ በፍጥነት፤ እንደ ነብር ማንቁርት በማነቅ የተዋጣለት አዳኝ ሆነ፡፡ ልጅ እያለሁ ማድባት፤አደባ፤ የሚለውን ቃል ተጠቅሜ የአማረኛ ትምህርት የቤት ሥራ አረፍተ ነገር ስራ ስባል ትዝ ይለኛል ከዚህ ጋር የተገናኘ ነበር፡፡ ሦስተኛ ክፈል ተማሪ ነበርኩና የሰራሁት አረፍተ ነገር ደቢዞ ቀማ፤ ደቢዞ አደባ፤ደቢዞ አደነ፤ ደቢዞ ሮጠ የሚል ይበዛው ነበር፡፡ የአማረኛ አስተማሪየ አለማየሁ ዳቃ ይባሉ ነበር፡፡ አንዳንድ ጓደኞቻቸው አለማየሁ ዳቃ እንጫወት ዶቃ እያሉ ይጠሯቸው ነበር፡፡ አይ ዘመን በግጥም መጠራራት፤ በግጥም መጫዎት፤ መተራረብ ደስ ይል ነበር፡፡ ታዲያ እኒህ አስተማሪየ በሁሉ አረፈተ ነገር ላይ ደቢዞ የሚለውን ቃል ስለሚያገኙት ማነው ደቢዞ ብለው እንደጠየቁኝ አስታውሳለሁ፡፡እኔም አሁን ያወጋኋችሁን የደቢዞን ታሪክ (ወግ) አወጋኋቸው፡፡ መጀመሪያ እንደማዘን አሉ በኋላ ላይ ግን መሸፈቱን ሲያስቡ ደስ አላቸው፡፡ እንዲያውም ምን ድመት ሆነ ትለኛለህ አነር ሆነ እንጂ ጎሽ የእኔ አንበሳ ሲሉኝ ፤ አነር ደግሞምንድነው አልሁ የኔ አንበሳ የምትለው ቃል ለኔ መስሎኝ ልቤን ሞቅ ብሎት ነበረና ለአባቴ መምህሩ ያሉኝን አጫወትኩት፡፡አንትን አይደለም በለውን ነው የእኔ አንባሳ ያሉት አለኝ፡፡ እኔም እንደገና ከፋኝ የተሰጠኝ አዲሱ ስሜ ስለተወሰደብኝ፡፡ በኋላ እንደ አንበሳ ሆኜ ሞቅ ብሎኝ እነዳለሸፍት ነበር ሲገባኝ ምናለ አንበሳውን ባይወስድብኝ፡፡ ግና ደቢዞ ስሙን ይወደው ይሆን፡፡ በነገራችን ላይ በደቢዞ ላይ ይህ ሁሉ ለምን እንደደረሰበት የቤተሰብ ምስጢር ነው ብሎ ፋኑኤል ያጫወተኝ አስረኛ ክፍል እያለሁ ከሰባት አመት በኋላ ነበር፡፡
ወደ አደኑ ልመለስና ብዙ ጊዜ እንዳየሁት ከሆነ ደቢዞ ሲያድን የሚጠቀምባቸው ስልቶች ነበሩት
1. ወደ ኋላ ይሳበል
2. ጅራቱን ያነቃንቃል
3. እንደመተኛት ይላል
4. ትንፋሹን ይስባል
5. ትኩረት ይሰጣል
6. አደኑ በዕጁ እንደሚገባ ሲያረጋግጥ በፍጥነት ታደኙ ላይ እምር ብሎ ጉብ ይላል፡፡
ደቢዞ የሚታደነውን ከማይታደነው መለየት ወይንም ለይቶ መውሰድ ይችላል፡፡ ደቢዞን ደቢዞ ካሉት አሮጊት እጅ ላይ ቀይ ሙዳ ሥጋ አድኖ ሲበላ አይቻለሁ፡፡ ተሳክቶለታል፡፡ ዘሩ ነው፡፡ የእባብ ጭንቅላት ላይ ጉብ ብሎ መርዝ ሲያስተፋ ተመልክቻለሁ፡፡ ውጤታማ ነበር፡፡ ደቢዞ ከህጻን ልጅ አናት ላይ ያለውን ቅቤ ለመላስ ቅቤ በተቀባው ህጻን ትክሻ ላይ ቁጭ ብሎ ሲዝናና ተመልክቻለሁ፡፡ ግነት የለውም ወፍ ሲይዝ፤ አይጥ ላይ ሲጫዎት፤ ከውሻ ሲያስተፋ ተመልክቻለሁ፡፡ የማድባት ትርጉም ለእኔ ይሄ ነው፡፡ ተደባ ፤አደባ ስል ከዚህ የታሪክ ጭብጥ የሚቀዳ የወንዝ ጅረት እንጂ ደረቅ ቃል አይደለም፡፡
እኔም ወደ ርዕሰ ጉዳዩ ልምጣና በዋልድባ ሁለት ገዳማት መነኮሳት መካካል የተፈጠረው ችግር ገዢው ስሁት ጠንቋይ በሁለቱ ገዳማት የሰነበተውን የቤት ውስጥ የመደባባት ጨዋታ አግዝፎ፤ የተቋጠረ ቂም የዘረገፈበት፤ ውለታውን ረስተው ደሰታየና ሃጎስን የመሆን ምልክት ያሳዩትን ገዥ ዘመም መነኮሳትን የማነሳሳት ዘመቻ ይመስላኛል፡፡ ጎንደሬ ተደብቷል፤ አማራ ተደብቷል፤ ወያኔ አድብቷል ልላችሁ አልነበረም የፅሁፌ አላማ፡፡ ፀጋየ ገ/መድህን (ሎሬት)የክፍልፋይ ቡልደዘሮች፤ ደናቁርት ምሁራን፤ የልዩነት አብሳሪዎች የምትለው ንግግሩ ሁልጊዜ በህሊናየ ትኖር ነበርና፡፡ ዳሩ ምን ያደርጋል ፋኑኤል የደቢዞን ታሪክ ከብዙ አመት በኋላ ምስጢር አድርጎ እንደነገረኝ ሁሉ ገ/መድሕን አርያ የተባሉት የጥንቱ የወየኑት ሹም አማራን ተደብቷል፤ አማራን ማዳከም፤ ማጥፋት አለብን ስንል ነበር የሚለውን ሀቀኛ ድምጻቸውን ስሰማ…እንጂ
ጅራትና እግር የመቁረጥ ሴራቸው በዋልድባ ገዳም ሴራ ውስጥ የለም አልላችሁም፡፡ ወደዳችሁም ጠላችሁም ዋልድባ የሃይማኖት ገዳምን ከመድፈር ባለፈ ደቢዞ እያለ ፋኑኤል ሃጎስ በሕይወት አይኖርም ስለዚህ ደቢዞን እናዳክመው የተባለ የባህረ ነጋሽ የጥንት ዘመን ጠንቋይ ምክር አለበት ነው የምላችሁ፡፡ ነብዩ ኢሳይያስ በስሙ ትንቢት የሚናገሩትን ከባበሎን መለስ የተላኩትን የጥፋት አስማተኞች “ቤል ተዋረደ ናበው ተሰባበረ ጣዖቶቻቸው በእንስሳና በከብት ተጭነዋል ሸክሞቻችሁ ለደካማ እንስሳ ከባድ ጭነት ሆነዋል” ብሏልና ሥጋት የለም አደን እንጂ ( ኢሳይያስ 46፡1)፡፡ አስተውሉ በለውን ወደ አደን የሚጠራ የመጨረሻ ግፍ ነው፡፡ የመጨረሻው ደወል፡፡ በለው ከማድባቱ በፊት የአደን ስልቱን ከደቢዞ ይማር፡፡ ከዚያም…
በዳባት፤ ዋልድባም ተደባ
ቋራ ብለህ ጥራ፤ ውስጡ ቋጥሯል ደባ
ደጄ አጋንንት ሆኖል፤ መነኩሴ ተሰዷል፤ የለበትም አባ
በጎ እንደር እንጂ እንዲሁ አይጠባ
በጥዋት ተነስተህ፤ ቋርፍ ምናምን ሰብስብ፤ ወደ አደነህ ግባ
አዳኝህን እወቅ እንዲሁ አትባባ ፡፡
በማለት ልሰናበታችሁ፡፡
please lets strength our struggel. We are one as Ethiopians. no religious,ethnical and other bounderies.
what happening in ethiopia now regarding muslim protest i can give you example if you know in RUSSIA orthodox is the main religion and have the biggest status in kremlin its like white house, even the russia very awere of america involvement priching protestant religion even people againt it,
so can you imagine in RUSSIA with out the orthodox leaders permision
giving some other religion to take in charge of orthodox religon .
you can give any religion to practice their religion but but you can not allow protestant prest to preach in orthodox church!!!!unless you dam wish a death,thats what happening in ethiopia muslim …my religion say dot drink alchol even doctor say so weyane it doesn’t matter its in our constitution you have to drink it this is a crazy centuery we are facing,when one muslim start get killed the christians brothers will get the opportunity to oversrow the goverment this is a time for any party to join watch and see it will happen.i think God saying enough to this goverment.
ethiopia yaferachew yefeterechew andem haimanot yelem we all ethiopians were there for millenium even before you can not tale any one this land belonges to this .bolockes the country if its Gods wish it can be budas or hindus,or jews land you have no power to stope it there is no forigner their you ass hole!!!
ethiopia yaferachew yefeterechew andem haimanot yelem we all ethiopians were there for millenium even before you can not tale any one this land belonges to this .bolockes the country if its Gods wish it can be budas or hindus,or jews land you have no power to stope it there is no forigner their you ass hole!!!
ethiopia yaferachew yefeterechew andem haimanot yelem we all ethiopians were there for millenium even before you can not tale any one this land belonges to this .bolockes the country if its Gods wish it can be budas or hindus,or jews land you have no power to stope it there is no forigner their you ass hole!!!
once i was i london when pakistani origin protesting against the goverment the way they handel muslim extrimst. protesting ok but in regent park mosqe they burn british flag in a day light,,how you bloody compare with that in ethiopia,people of orgine have no right to chose their leader,the number of mosque in london getting closer to that in addis ababa it surprise me,when christians build that big tele medianalem but the muslim keep turn dawn their request the time will come you gone pay the price any way musim number in europe the whites convert to islam you can not stop it it will grow and domonate any way.
we have more freedom outside than in our country you look gazetegna but you abogia hedena atna hau setebesel bege,
በሃይማኖትም ሆነ በስም ዜቤ ልትዛመዱን ለምትፈልጉ ሁሉ ታላቅ ግብዣ እናደርግላችኋለን! በፈለገውም መንገድ ብቻ ዘመዳችንን ያብዛው! አሜን!
አይ ራስ አሉላ፣
ኢትዮጵያም ሆነች የሌላው የሰው ዘር አገር ሁሉ ውስጥ ሰዎች በእኩልነት ያለ ሃይማኖት ልዩነት ሊኖሩባቸው ይገባል፡፡ ራስ አሉላ በሚል ስምህ አስተያየት እንዳጻፍከው ሰው ዘመቻ ከሆነ ግን ከፍተኛ ችግር አገሪቱ ላይ ያጠላ መሆኑን ማየት ይቻላል፡፡ ለዚህም ነው ለአኢጋን እና ለመሰል የፖለቲካ እንቅስቃሴ አራማጆች ማሳሰቢያ መስጠት አስፈላጊ የሚሆነው፡፡
በግልፅ ለመነጋገር አንድ አገር ውስጥ ያለው አመራር በሙስሊም እጅ ከገባ፤ ሙስሊም ያልሆነው እንደሚጨነቅ፣ እንደ ሁለተኛ ዜጋና ከዚያም በታች ስም ካለ እንደሚቆጠር፣ በተወለደበት አገር ማለት በገዛ አገሩ መብቱ እንደሚገፈፍ የታወቀ ነገር ነው፡፡ ይህንን ለመረዳት እሩቅ መሄድ አያስፈልግም ግብፅ ውስጥ ያሉት የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያናትና በክርስትያኖች ላይ የሚደረገው ግፍ በጣም ግልፅ ምሳሌና ትምህርት ነው፡፡
በግብፅ ውስጥ ክርስትያኖች የመናገር መብት የላቸውም ቤተክርስትያን የሚሄዱት በፍርሃት ነው፡፡ ቤተክርትያን ተጨፍጭፎ ሰዎች ሞተው በቁርጥራጭ ሬሳ ላይ ሙስሊሞች እየዘለሉ በደስታ አላህ አኩበር ሲሉ ታይተዋል፡፡ ግብፅ ውስጥ ክርስትያኖች በሙስሊሞች የሚደረግባቸው ግፍ ማን ዘግቦት ይጨርሰዋል፡፡ በሌሎች አገሮችም በታሪክም የታወቀ ነው፡፡ ይህንን ለማወቅ ከፈለጋችሁ በቅርቡ ያነበብኩትን አጭር ዜና በ ተመልከቱ፡፡
ራስ አሉላ እንዳልከው እስልምና ምን ዓይነት እምነት እንደሆነ ሳያውቅ የሚደለልና ወደ እስልምና እምነት የሚቀየር አንዳንድ ሰው ሊኖር ይችል ይሆናል፡፡ በገንዘብም ተደልለው ሙስሊም የሚሆኑ ሰዎች እኛም አገር እየታዩ ነው፡፡ አታውቅ ይሆናል እንጂ ወይንም እልሰማህም ይሆናል እንጂ፣ ሳይደለሉ በየቀኑ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ሙስሊሞች እምነቱን እየጣሉ እየወጡ ነው፡፡
በሙስሊም እምነት ውስጥ ሆነው ነፃነት እኩልነት ሰብዓዊነት የጠማቸው እውነትን ፈላጊዎች ሁሉ እየጣሉት እየወጡ ነው፡፡ ይህ ኢትዮጵያውም ውስጥ በእስላም አገሮችም ውስጥ እየሆነ ነው፡፡ በቅርቡም ኢራን ውስጥ ሁለት የአስራ ስድስት ዓመት እድሜ ያላቸው ወጣት ወንዶች በአደባባይ ቁርአንን አቃጥለው ከእስራቱ መውጣት እንፈልጋለን ብለው ለዓለም ሮሮአቸውን አሰምተዋል፡፡
አሁን አኢጋን ያወጣው መግለጫ ስለሆነ የሚያነጋግረን – እውነተኛ ኢትዮጵያውያን ሁሉ አሁን መንቃት ይገባናል፣ የሳውዲ መንግስት የዋሃቢዝምን እንቅስቃሴ ኢትዮጵያ ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ ከፍተኛ ዘመቻ እያደረገ ነው፣ ዓላማውም ኢትዮጵያን እስላም ለማድረግ ነው፡፡ ምን ታደርጋላችሁ? ኢህአዴግን ለመቃወም ብላችሁ ብቻ አገሪቱ የማትወጣው መዘዝ ውስጥ ባታስገቧት መልካም ነው፡፡ እናንተ ሲከፋችሁ ዮሮፕም አሜሪካም ትሄዳላችሁ ድሃው ወዴት ይሄዳል፣ በእስልምና እንዲረገጥ አሳልፋችሁ ልትስጡት አይደለምን? ሕዝብን የፖለቲካ መጠቀሚያ አድርጎ ለችግር ማጋለጥ በፍፁም ተገቢ አይደለም፡፡
በግብፅ ውስጥ እየሆነ ስላለው ካነበብኩት ብዙ ዜና ባሻገር በአማርኛ ካነበብኩት ውስጥ “ለእስላም መመለስ” ድረገፅ ላይ http://www.answering-islam.org/amargna/news_digest/29_04_2012.html ያለው አስገራሚም አሳሳቢም አስተማሪም አስጠንቃቂም ነው፡፡