አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።
Recent Posts
- የአባይ ጉዳይ የዛፍ ላይ እንቅልፍ የሆነባት ግብጽ እና ለስልጣን ጸብ ጫሪው ህውሃት! ግርማ ሞገስ
- “ሕልምና ቅዥት” ክፍል ፪. የጐንቻው!
- ከፍተኛ የደህንነት ሹም ከስልጣን ተነሱ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)
- አባ ማትያስ : “እንዲህ ያለ ፓትርያርክ አይተን አናውቅም” – በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ
- የአባይ ወንዝ ህዳሴ ግድብ ትርፎች፤ ቦንድ፣ ዕዳ፣ አፈር መዛቅ፣ የጦር ዛቻ በዘውገ ፋንታ
- ኢትዮጲያ የማን ናት? ከኤደን መስፍን(ኖረዌይ)
- ወያኔን ማስወገድ አይደለም የሚያስቸግረው፤ አስቸጋሪው ነገር አገርን መገንባት ነው !!በፈቃዱ በቀለ
- የሰባአዊ መብት ድርጅቶች፡ የሃይማኖት አባቶች፡ ምሁራን እና የካናዳ ፓርላማ አባላት የተሳተፉበት ውይይት ለሃገራችን ችግሮች የፖልሲ አማራጮች አቀረበ (ሽንጎ)
- ስደት ድህነት ነው ድህነት የብልሹ ፖለቲካ ስርዓት ውጤት ነው በግሩም ተ/ሀይማኖት
- ትውልድ ያናወጠ ጦርነት የመጸሃፍ ግምገማ በአቶ አበራ ለማ
Recent Comments
- Anonymous on ወያኔን ማስወገድ አይደለም የሚያስቸግረው፤ አስቸጋሪው ነገር አገርን መገንባት ነው !!በፈቃዱ በቀለ
- ገብረ on የአባይ ወንዝ ህዳሴ ግድብ ትርፎች፤ ቦንድ፣ ዕዳ፣ አፈር መዛቅ፣ የጦር ዛቻ በዘውገ ፋንታ
- ሳልሳዊት on የሰባአዊ መብት ድርጅቶች፡ የሃይማኖት አባቶች፡ ምሁራን እና የካናዳ ፓርላማ አባላት የተሳተፉበት ውይይት ለሃገራችን ችግሮች የፖልሲ አማራጮች አቀረበ (ሽንጎ)
- Oda Tulu on ወያኔን ማስወገድ አይደለም የሚያስቸግረው፤ አስቸጋሪው ነገር አገርን መገንባት ነው !!በፈቃዱ በቀለ
- Oda Tulu on ኢትዮጲያ የማን ናት? ከኤደን መስፍን(ኖረዌይ)
- ፈቃዱ on ወያኔን ማስወገድ አይደለም የሚያስቸግረው፤ አስቸጋሪው ነገር አገርን መገንባት ነው !!በፈቃዱ በቀለ
- Zerayakob Yared on ከፍተኛ የደህንነት ሹም ከስልጣን ተነሱ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)
- አቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ-ወመንፈሳዊ on ወያኔን ማስወገድ አይደለም የሚያስቸግረው፤ አስቸጋሪው ነገር አገርን መገንባት ነው !!በፈቃዱ በቀለ
- Anonymous on የአባይ ወንዝ ህዳሴ ግድብ ትርፎች፤ ቦንድ፣ ዕዳ፣ አፈር መዛቅ፣ የጦር ዛቻ በዘውገ ፋንታ
- Anonymous on ወያኔን ማስወገድ አይደለም የሚያስቸግረው፤ አስቸጋሪው ነገር አገርን መገንባት ነው !!በፈቃዱ በቀለ

Categories
Archives
- June 2013
- May 2013
- April 2013
- March 2013
- February 2013
- January 2013
- December 2012
- November 2012
- October 2012
- September 2012
- August 2012
- July 2012
- June 2012
- May 2012
- April 2012
- March 2012
- February 2012
- January 2012
- December 2011
- November 2011
- October 2011
- September 2011
- August 2011
- July 2011
- June 2011
- May 2011
- April 2011
- March 2011
- February 2011
- January 2011
- December 2010
- November 2010
- October 2010
- September 2010
- August 2010
- July 2010
- June 2010
- May 2010
- April 2010
- March 2010
- February 2010
- January 2010
- December 2009
- November 2009
- October 2009
- September 2009
- August 2009
- July 2009
- June 2009
- May 2009
- April 2009
- March 2009
- February 2009
- January 2009
- December 2008
- November 2008
- October 2008


ገታ እጅሽን ይባርከው…ለምለም
“ሀገር ሲያረጅ ጃርት ያፈራል”ይህን ያለው ሰው ነቢይ ነው መለስን የመሰለ ከጃርትም ጃርት ኢትዮጵያን ሲመራ ማየት ከውርደትም ውርደት
መለስ ሲስቅ ያናድዳል፤ ሲናደድ ያስቃል! (ተፃፈ በወፉ)
መለስ ሲስቅ ያናድዳል፤ ሲናደድ ያስቃል የሚለውን ርዕሰ ጉዳይ ሳስብ ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለተደራሲያን ሁሉ ግልንቢጥ ነው፡፡ በዘመነ ግልንቢጥ ዝናብ ሽቅብ ይዘንባል እንደሚባለው ፡፡ እስኪ ተመልከቱ ሲስቅ የሚያናድድ፤ ሲናደድ የሚያስቅ ፍጡር መኖሩ በራሱ አይገርማችሁም፡፡ አያ ፈንተሌና ጤንዜሌ ለቅሶ ቤት ይስቃሉ፤ ሰርግ ቤት ያለቅሳሉ ቢባል ወደ ሃኪም ቤት አንጠልጥላችሁ ትወስዷቸው ነበር፡፡ ምክንያቱም በዕውነተኛው ዓለም ለቅሶ ለቅሶ ፤ደስታ ደስታ ስለሆነ ብቻ ነው፡፡ በመለስ ሳቅ መናደድ፤ በንዴቱ መሳቅ ግን እንደ አያ ፈንቴሌና እንደ እቴቱ ጤንዙሌ ወደ ሃኪም ቤት ልውሰዳችሁ አያስብልም፡፡ የዚህ ምክንያት ደግሞ የመለስ ስብዕና በእውነተኛው ማንነት ላይ ያልተገነባ በመሆኑ ነው፡፡ በመሆኑም የመለስ ሳቅ የሚያናድደው ሳቁ ውሸት ስለሆነ ሲሆን ንዴቱ የሚያስቀው ንዴቱ እውነት ስለሆነ ነው፡፡ መለስ የለም ካለ፤ አለ አለ ካለ የለም ነው፡፡ መለስ በቴሌቪዥን እየሳቀ ከተናገረ ለምሳሌ የሚናገረው ስለ ዕድገት ከሆነ የዕድገት ዘር ጠፍቷል ማለት ነው፡፡ እየተበሳጨ ይሄ የነፍጠኛ ወሬ ነው ካለ ነገሩ ሆኗል ማለት ስለሆነ ብስጭቱ የትግላችንን ሃይል ይገልጥልናልና ያስቀናል፡፡ መለስ ከሳቀ ሸፍጥ አለ ማለት ነው፡፡ መለስ የማያውቀው እኛ እንደዚህ በግልንቢጥ ንግግሩን እንደምናነበው ብቻ ይመስለኛል፡፡ ለዚህ መሰለኝ ሁልጊዜ ሊዋሸን የሚሻው፡፡
አንድ የልጅነት ወዳጄ ጋር ተገናኝተን የልጅነት ወግ ስንጠርቅ ጓደኞቻችንን እና ወዳጆቻችንን አንስተን ትምህርት ቤት ምግብ ቤት አደራርሰን አንድ ኪዮስክ ጋር በሃሳብ ስንደርስ ወዳጄ “ዳፍንቴ” ትዝ ይልሃል አለኝ፡፡ እኔም ዳፍንቴ የሚባለው ሰው ተግባሩ ግራ (ግልንቢጥ) ነበርና ለማስተዎስ ጊዜ አልወስደብኝም፡፡ዳፍንቴ በኪዮስኳ አጠገብ የሚቀመጥ እውነተኛ እብድ ነበር፡፡እፀድቅ ባይ የሚጎበኘው፤ የሚያበላው፤ የሚያጠጣው፤ የእግዜሩ እንግዳ ነበር ብል እውነትነት አለው፡፡ የዳፍንቴ አንዱንም ዘመድ አላስታውስም፡፡ የየት አካባቢ ሰው እንደሆነም አላውቅም፡፡ ዳፍንቴ የሚራራ አንጀት ያለው ሁሉ ዘመዱ ነው፡፡ አንድ የማልረሳው ቻጋ ችፍርግ ( ቻቻ ችፍርግ እየደጋገመ ስለሚል መሰለኝ ይህ ስም የወጣለት ) ብቻ ዳፍንቴን በጣም የሚቀርበው እሱው ነው፡፡ ቻጋ ችፍርግ ወፈፌ ነው፡፡ እንደ ዳፍንቴ ባይሆንም እሱም ነካ ያደርገዋል፡፡ ታዲያ ቻጋ ችፍርግና ዳፍንቴ ያወጋሉ፤ ይስቃሉ፤ ምን እንደሚባባሉ፤ ምን እንደሚያወጉ፤ ምን እንደሚያስቃቸው ግን እግዚአብሔር ይወቀው፡፡
ዳፍንቴ ዳፍንቴ የተባለው ፀጉሩና ጺሙ ፤የእጅና የእግሩ ጥፍር አድጎ ፤የፊቱ ገፅታ ገርጥቶ፤ ያልታጠበ ቆዳ ለጥፎ የሚኖር የዛገ አሮጌ ጥቁር በርሜል ስለሚመስል ነው ብሎኛል አንዱ ወዳጄ፡፡ ዳፍንቴ አያስብ፤ አይታጠብ፤ አይፀዳ ፤ከማውራት አያባራ ምን አለፋችሁ አንገት ደፊ እብድ አልነበረም፡፡ ሲለፈልፍ ከፂሙ ከተሸፈኑ መጣጣ ከሰልማ ከንፈሩ አፈትልከው የሚወጡት ሁለት ቃላት አይረሱኝም፡፡ ተኩስ ነው ፤ተኩስ ነው፤ ቁም ቁም፤ ሰላም ነው፤ ሰላም ነው የሚሉ ነበሩ፡፡
ታዲያ የሰፈሩ አሮጊቶች አንድ የማይሆን፤ የማይገጥም፤ የማይከናወን፤ ተስፋ ወይም ንግግር ከማንም ይስሙ ከማን እንደማይሆን ከገባቸው የዳፍንቴ ሰላም፤ የዳፍንቴ ተክሱ እያሉ ይዘባበታሉ፡፡ ቡና ጠጡ ተብለው የተጠሩ ጎረቤት ከዘገዩ ወይንም አልሞላላቸው ብሎ ከቀሩ ምነው የዳፍንቴን ወሬ አደረግሽው ይባላል፡፡
ዳፍንቴን ከዚህ ሁሉ በላይ ልጅ ሆነን የማንረሳው ንግግሩ ከተግባሩ ጋር ያለው ተቃርኖ ነው፡፡ ዳፍንቴ ምግብ ትፈልጋለህ ተብሎ ከተጠየቀ አልፈልግም ይላል፡፡ አትፈልግም ማለት ነው? ከተባለ እፈልጋለሁ ይላል፡፡ ምሳ በልተሃል ወይ ተብሎ ቢጠየቅ ከበላ አልበላሁም ይላል ካልበላ በልቻለሁ ይላል፡፡ መጀመሪያ አካባቢ ዳፍንቴ በዚሁ ንግግሩ ምክንያት ተጎድቶ ነበር፡፡ በኋላ ላይ ግን ሁሉም ይህን የግልንቢጥነት ባህሪውን እያወቀ ሲመጣ በተቃራኒው ማለትም በልቻለሁ ካለ አልባለም፤ አልበላሁም ካለ በልቷል ማለት ነው በማለት ዳፍንቴና እጸድቅ ባይ ዘመዶቹ ተግባቡ፡፡
ከዳፍንቴ የሚገርመኝ ነገር ሲስቅ ያስፈራል፤ ያናድዳል፤ ድንጋይ ይወረውራል፤ ምራቅ ከአፉ ይፈልቃል፡፡ ለማንኛውም ሳቁ አጥፊ ነው፡፡ ሲስቅ ያለቅሳል፡፡ ዳፍንቴ ሲበሳጭ ደግሞ ድድማስጫ የምትባለው ድልድይ ውስጥ ይወሸቃል፡፡ ድልድይ ስር ውስጥ ቁጭ ብሎ መሬቱን እየጫረ ይስቃል፤ ልቡ እስኪፈርስ ድረስ ይንከተከታል፡፡ ፍፁም ሰላማዊ ይሆናል፡፡ ዳፍንቴ ከተናደደ እንደ ህጻን ልጅ ይስቃል፤ ይቦረቃል፡፡
ታዲያ ያ ልጅ ሆነን የምናየውን የዳፍንቴ ባህሪ አድጎ በአገር መሪ ደረጃ በተቀመጡ ቅቡዓን (ሉዑላን) ስነ ልቦና ውስጥ በስፋት የመንደር ያክል ተንሰራፍቶ ሳየው ገረመኝ፡፡ የዳፍንቴ ባህሪ ካየሁባቸው ሰዎች መካካል ክብሩን ለመንካት ሳይሆን የባህሪው ተምሳሌት በላዩ ላይ በስፋት ስለሰፈረበት ብቻ መለስን ላንሳ ( በነገራችን ላይ ሌሎችም መሪዎችን የሚያጠና ይህን ባህሪያቸውን ሊያገኘው ይችላል)፡፡ የወያኔውን ቁንጮ መለስ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ነው፡፡ ባጭሩ መለስ ሲስቅ ያበሳጫል ከተበሳጨ ደግሞ ያስቃል ነገሩ ሰምሯል (ሆኖል) ማለት ስለሆነ ነው፡፡ ይህ እንግዲህ ወይም ሰሚው አብዷል አሊያም ተናጋሪው ተደናግሯል ሊያስባል ይችላል፡፡ ለምሳሌ መለስ ተበሳጭቶ በቴሌቪዥን መስኮት ተናግሯቸው ያሳቁንን አምስቱን ብቻ እናንሳ
1. የመለስ ንዴት የእኛ ሳቅ( አንድ)፡- አንድ ጋዜጠኛ ከዛሬ 10-12 ዓመት በፊት በኢትዮጲያ እና በኤርትራ መካከል ጦርነት አለ ይባላል እንዴት ያዩታል ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ የነፍጠኞች ወሬ ነው አለ፡፡ እኛን ግን አሳቅን፡፡ እውነት ስለሆነና ጦርነቱ ያለማጋነን በማግስቱ በመጀመሩ ነው የሳቅነው፡፡ ሌላው የሳቃችን ምክንያት ኢትዮጲያ ለኢትዮጲያውያን ልትሆን ነው ብለን ነበር፡፡
2. የመለስ ንዴት የእኛ ሳቅ( ሁለት)፡- የአማራ ህዝብ ከደቡብ ክልል ተፈናቀለ እንዴት ያዩታል ለሚለው ጥያቄ መለስ በንዴት ሲመልስ አልተፈናቀሉም ደን ያቃጠሉት ( ጎጃሜዎች) ብቻ ላይ ነው እርምጃ የተወሰደባቸው (የዋልድባ ገዳምንም ያጠቃልላል) አለ፡፡ እኛን ግን አሳቅን፡፡ በዚህ ንግግር አሃ ለካንስ እነ መለስ የተሳተፉባት ጨዋታ ነው አስባለን፡፡ ከላይ የተወጠነ የጥፋት ተልኮ እንዳለበት ስላወቅን ነው የሳቅነው፡፡ ይህ ደግሞ ለመጠናከራችን ጉልበት ይሆነናልና አስደሰተን፡፡
3. የመለስ ንዴት የእኛ ሳቅ( ሦስት)፡- የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄ ከየት የመጣ ነው ተብሎ ሲጠየቅ መለስ በንዴት ሲመልስ የአልቃይዳ ህዋስ እና የፖለቲካ አጀንዳ ያላቸው ስራ ነው፤ ቁጥራቸውም ጥቂቶች ናቸው አለ፡፡ ጥቂት ነውጠኞች ናቸው የሚለው ንግግሩን በእጁ እየተወራጨ እና በምላሱ እየተናገረ በንዴት ሲጦፍ እኛን ግን አሳቀን፡፡ ምክንያቱም ሙስሊሞች በክርስቲያኑ ችግር ለመፍጠር ያልሞከሩ፤ የማይፈጥሩ እና ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ብቻ እያቀረቡ መሆኑን ስላወቅን ነው፡፡ እናም እንደሳቅነው የጥቂቶች ጥያቄ የተባለው በማግስቱ የሚሊዮኖች ሆነው ታየ፡፡ ታዲያ አያስቅም፡፡
4. የመለስ ንዴት የእኛ ሳቅ( አራት)፡- የኢትዮጲያ ወታደሮች ጅራታቸውን ቆልፈው እንደውሻ ከሶማሌ ባለፈው በሽንፈት ለቀው ነው የወጡት ተብሎ በአንዲት የውጭ አገር ጋዜጠኛ ሲጠየቅ በንዴት መለስ ይህ የአንች አመለካከት ነው አላት፡፡ ይህን ተናግሮ “ቧ” ብሎ ጦፈ እኛን ግን አሳቀን፡፡ ምክንያቱም ይህ ሽንፈት ያለምንም ምክንያት ደማቸው የሚፈሰው የወያኔ ሰለባ የሆኑ ወታደሮችን መለስ መልሶ ሶማሊያ እንደማያስገባቸው ተግባባን ባንነጋገርም፡፡ የነገሩን እውነትነት ቢያንስ በቴሌቪዥን መሰኮት የሶማሌ ወታደሮች ብቻ ሳይሆን የመንደር ሴቶች የኢትዮጲያ ወታደሮችን እየጎተቱ አሳዩን፡፡ ከዚሁ ጋር ስንት ወታደር በሶማሊያ ሞተ ተብሎ በፓርላማ ሲጠየቅ በንዴት ጦፈ፤ ተወራጭቶ፤ በዚህ ደረጃ ወርጄ ይህን ያህል አሃዝ ማቅረብ አይገባኝም አይነት መልስ በንዴት ሰጠ፡፡ እኛን ግን አሳቀን ምክንያቱም በሀይለኛ ሁኔታ የወያኔ አከርካሪ እንደተሰበረ የሳያልና፡፡
5. የመለስ ንዴት የእኛ ሳቅ( አምስት)፡- መለስ የመምህራን ጥያቄ የምን ጥያቄ ነው ለተባለው ጥያቄ በንዴት ሲመልስ ጥቂት የደሞዝ እርከንና ጭማሪ የተምታታበቸው( ተመልከቱ አሰተማሪው የማይገባው ነው ሲባል፡፡ መምህሩ የቀለም አባቱ ዶሞዝ እና እርከንን መለየት ሲያቅተው) እና የውጭ ሃይል ግፊት ያለባቸው በዚያ ላይ የማስተማሩ ሂደት ላይ ያልተሳካላቸው ናቸው ሲል በለመደው ሃይል ተናዶ ተናገረ፡፡ እኛን ግን አሳቅን ምክንያቱም ያመፁት የተዋጣለቸው፤ አንቱ ተብለው በወያኔ በራሱ የተሸለሙ፤ ነገር የሚገባቸው እና ቁጥራቸው ብዙ መሆኑን ስላሰወቀን ተደሰትን፡፡ በነገራችን ላይ በጉርዳ ፈርዳ ወረዳ ደን የጨፈጨፉ ናቸው የተባሉትም ቢሆኑ እንኳ በልማታዊ አርሶ አደርነት የተሸለሙ ናቸው ሲባል ሰምተናል፡፡ በአጭሩ እርሶዎም መለስ በንዴት ሲጦፍ በሳቅ ፍርስ ሊሉ ይችላሉ ጥቅሙ ከገባዎትና የመለስ ትወና ከተከሰተለዎት፡፡
መለስ ሲስቅ እኛ የተናደድንበትን ላንሳና ሃሰቤን ልጠቅልል…
1. የመለስ ሳቅ የኛ ንዴት (አንድ)፡- በምርጫ 97 (2205) ወቅት ሚያዚያ 28 ይመስለኛል ወያኔ በጠራው ስብሰባ መለስ ወደ አደባባይ ወጥቶ በደስታ እየፈነደቀ፤ በስካር አንድ ነገር ተናገረ፡፡ ኢህአዴግ ምርጫ ለማሸነፍ ማጭበርበር አያስፈልገውም አለ፡፡ ፍንክንክ ብሎ ሲናገር እኛ ግን ተናደድን፡፡ ምርጫውን ለማጭበርበር መሰናዶውን ጨርሶ ህዝቡን ሲያይ ብዙ ደጋፊ ያለው መስሎት ይህ ሁሉ ከደገፈን ማጭበርበር የለብንም እያለን ነበር፡፡ ዳሩ እኛ እሱን የሚደግፉት ጥቀቶች መሆናቸውን ስለምናውቅ ምርጫውን እንደተናደድነው አጭበረበረ፡፡ ሰውም ገደለ፡፡
2. የመለስ ሳቅ የኛ ንዴት (ሁለት)፡- በቅርቡ በተካሄደው ምርጫ ላይ በደስታ ሲናገር ተናደድን፡፡ አስቀድሞ የሚያውቀውንና የወሰነውን ምርጫ በደስታ ወደ አደባባይ ወጥቶ 96.9 በላይ አሸነፍኩ ሲል ሳቀ እኛ ግን ተናደድን፡፡ የለየለት አምባገነን መሆኑን ስለገባንና መጻኢው ዘመን የህዝብ እልቂት፤ የአፈና እንደሚሆን አውቀናልና፡፡
3. የመለስ ሳቅ የኛ ንዴት (ሦስት)፡- ዲሞክራቲክ መሪ ተብሎ በቶኒ ቢለየር ተመርጦ ሲፍነከነክ እኛ ግን ተናደድን፡፡ ምክንያቱም አስቀድመን ዲሞክራቲክ ሳይሆን የአምባ ገነን ዛር ተጭኖት አይተናልና ለዚሁ ምስክር የሚሆነን ግርድፍ እውነት ድፍን ሃያ ዓመት ስልጣን ላይ ፊጥ ብሏል፡፡
4. የመለስ ሳቅ የኛ ንዴት (አራት )፡- ኢኮኖሚያችን ምን ያህል አድጎል ሲባል መለስ በፈገግታ 11 በመቶ አድጎል አለን፡፡ በሳቅ፤ በደስታ በመቀጠልም ልማታዊ መንግስት ነን አለን፡፡ ልማታዊ መንግስት ነን፤ልማታዊ መንገድን መርጠናል አለ አፉን ሞልቶ እኛ ግን ተናደድን፡፡ ምክንያቱም ልማታዊ ሳይሆን ስር ነቀል ጥፋታዊ መሆኑን አውቀን ነበርና ነው፡፡ ዕድገት የለም የቁልቁለት መንገድ ላይ ነን ብለን ተናገርን አልሰማንም እኛም ተናደድን፡፡ ኑሮ ጦዘ፤ ርሃብ መጣ ፤አገር በኑሮ ውድነት ቀውጢ ሆነች፡፡ መለስ ምሰጋና ይግባውና ሰሞኑን ቁልቁለቱን ዘልቀን መግባታችንን አረዳን ቢሆንም ይህንንም አናምንም የራሰችንን መረጃ እንጂ፡፡
5. የመለስ ሳቅ የኛ ንዴት (አምስት)፡- ውጭ የተቀመጠ ገንዘብ አለዎት ይባላል ምን ይላሉ ተብሎ ሲጠየቅ አይ የለኝም አለ፡፡ አየሳቀ ከወርቅ ህዝብ ብወለድም ያለኝ ጨርቅ ብቻ ነው አለን፡፡ አንድ ፀሃፊ መለስ የጨርቅ ሥነ ልቦና አለው ያለው ትዝ አለኝ፡፡ ባንዲራ ጨርቅ ነው፤ መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ፤ ጨርቅ ህዝብ አይደለም፤ ያለኝ ጨርቅ ነው እያለ ይቀጥላል፡፡ ወደፊትም የበለጠ ወፈፍ ካደረገው ጨርቃም ልማት፤ የጨርቅ ግድብ፤ የጨርቅ ዲሞክራሲ ፤እያለ ይቀጥላል፡፡ እናም ጨርቅ ብቻ ነው ያለኝ ያለው አነጋገሩ ያበሳጫል፡፡ ጨርቅም ቢሆን ሃብት ነው፡፡ የጨርቃጨርቅ ልብስ መደብር እኮ ያለቸው ባለ ሃብት አሉ መለስ ያለውን የጨርቃጨርቅ ክምር በሁለንተናዊ ሚዛን ከእንድ የጨርቅ ነጋዴ የበለጠ ከሆነስ፡፡ ለማንኛውም ይህን ሲነገር ቢያንስ ቢያንስ መለስ እነዚህ ነገሮች አሉት 1) ወርቅ ህዝብ አለው 2)ሙሰኛ ባለስልጣናት ከጎኑ ሆነው የሚያጎርሱት አሉት 3) ነጋዴ ሚስት ወ/ሮ አዜብ አሉት( ቡና የሚቆሉለት) 4) ኤፈርት አለው 5) የተጠራቀመ የማይታወቅ ሃብት አለው( ግምት) 5)የምትጠብቀው የዘር ማጥፋት ክስና ከርቼሌ እንዲሁም የማይቀረው የሞት እዳና የታሪክ ተጠያቂነት ሃብቱ ነው፡፡ ታዲያ መለስ ጨርቅ ብቻ ነው ያለኝ ሲል ማን ያምናል፤ ማን እሰየው ይላል ይበሳጫል እንጂ፡፡
ጥያቄው የመለስ ተለዋዋጭ ባህሪና ተገለባባጭ ማንነት የተገነባው ከምንድን ነው ያስብላል፡፡ ይህን የስነልቦና ባለሙያዎች ሊያጠኑ ይችላሉ፡፡ መለስ እምየ ምኒልክ ቤተመንግስት ሳይገባ በፊት ያዳበረው ባህሪው እንደሆነ እምየ ምኒልክን የዘረጠጠው፤ አማራን በስድቡ ተውቦ ያዋረደው የጋሜ መለስ ተላላኪ የሆነ ፀሃፊ አንድ ወቅት መለስ ጋር ተኮራርፈው እያለ የተናገረውን ማየት ተገቢ ነው እንዲህ ይላል “የመለስ ፖለቲካ ከጓደኝነት ጋር ተሳስሮና ተመሳጥሮ ይቆይና በመጨረሻ አንድ ደረጃ ላይ ሲደርስ ደምበኛ ታማኝነቱን እና ጓደኞቹን ወደ ደንበኛ ጠላትነት የመቀየር ባህሪ ከደሙ ጋር የተዋሃደ አሰራርና ልምድ የሚከተል ሰው እንደሆነ ግልፅ እየሆነና እየጠራ ሂዷል፡፡” እኛም እነዲህ እንላለን መለስ ሆይ አንተማመንም፡፡ ሳቅህ ያበሳጨናል፤ ብስጭትህ ያስቀናል፡፡ ደህና ዋል፡፡ አንተም ቀና ንግግር መስሎህ ደህና ዋል የምትለዋን ቃል አትመናት ፡፡
ንዲት የሚብስበት ከዚህ በላይ የጣፈው ግለሰብ የሀሥአቡ ድርሰት ከሳአቅ ወደ ሀኪም ደርሱዋን ድክመቱ በስድብ ጨርሶታል የቀረው ን ሰሚ ና የሚረዳው ባለማግኝቱ ኦ ኦ ብሎ ጨረሰው ይሁን እንጅ እውቀቱ ጎደሎ በመሆኑ ነው መልስ የሚገባው ጥያቂ ባለማቅረቡ መሳቂያ መሳለቂያ ስራ ስለለው የአማሪካን ቢራ ጠጥቶ ስለረካ ጽፈቱ እንቆቅልሽ ምናውቅልሽ በዎጥመድ ያለሽ ማነሽ ታውቂያልሽ ብሎ እንደጠቀ ነው የተረዳሁት ስለዚህ መልሱ ግዚሽን ጠብቀሽ አልካይዳ አጥፍቶ አጥፊ ሁነሽ በአምሳው እስቲት በመጨረሻ አንድ ደረጃ ሁኖ ይቆጠርብሀን ይቆጠርብሻን ከመጻፍ መናገር በልጦ በሩን ያንኩዋውንን