የሙስሊሞች ጉዳይ የኢትዮጵያ ጉዳይ! Jafar Hasen

May 15th, 2012 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

ይህቺን አጭር ጽሑፍ ለመጻፍ ያነሳሳኝ ሚያዝያ 30 ቀን 2004 በፍኖተ ነፃነት ቁጥር 41 ላይ በቅርቡ የወጣው የሰለሞን ስዩም ጽሑፍና አያይዞም ለማጠናከሪያ ያቀረበው የቃለ መጠይቅ ድጋፍ ናቸው፡፡ ፍኖተ ነፃነቶች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚያቀርቧቸው መረጃዎች ጥሩም አግባብም ያላቸው ናቸው፡፡ በብዛትም ሚዛን የያዙና ብዙዎችን የሚወክሉ ለአገርም ጥቅም የቆሙ ናቸው ለማለት ቅር አያሰኝም፡፡

ይሁን እንጂ የአሁኑ የሰለሞን ስዩም ጽሑፍና የቃለ መጠይቁ አካሄድ አላማረኝም፣ በአጠቃላይ ኢትዮጵያውያንን ለመጥቀም የሚችል አይደለም፡፡ አቶ ሰለሞን በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ የለም ወይንም ስለኢትዮጵያም ሆነ ስለዓለም አቀፍ ሁኔታ ምንም አያውቅም ማለት አልችልም፡፡ ለማለት የምችላቸው ነገሮች፣

• በመጀመሪያ ደረጃ፤ የሰለሞን ጽሑፍ ሚዛናዊ አይደለም፡፡
• በሁለተኛ ደረጃ፤ ታሪክንና እውነትን በሚዛናዊነት የወከለ አይደለም፡፡
• በሦስተኛ ደረጃ፣ የተጻፈበት ዓላማ በትክክል ግልፅ አይደለም ወይንም መልካምን ለምንመኝለት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ምንም ጠቀሜታ የለውም ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊንና የሚከተለውን የፖለቲካ መስመር ማናናቅና መተቸት ይቻላል፣ በእርግጥ ይህንንም ለማድረግ ሚዛናዊነት ያስፈልጋል፣ አሁን ላለንበት ሁኔታ የጥላቻ ጋዜጠኝነትና ፖለቲከኛነት የትም አያደርሰንም፡፡ ቀጥሎም ማንንም ደግሞም ለማንም አይጠቅምም፡፡ አቶ መለስ ዜናዊ ጠቅላይ ሚኒስቴርነቱን እስከያዘ ድረስ የመለስ ዜናዊ ጉዳይ የራሱ ጉዳይ ነው ማለት ግን እንደ እኔ ስህተት ነው፡፡

የአቶ ሰለሞን ጽሑፍ “የሙስሊሞች ጉዳይ የኢትዮጵያ ጉዳይ ነው” ይላል፡፡ በጣም ጥሩ ርዕስና ትኩረትን የሚስብ ነው፣ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ የአንድ ሙስሊም ጉዳይ የኢትዮጵያ ጉዳይ መሆኑ አገርንና የሰው ዘር ወዳጅ ኢትዮጵያዊን ሁሉ ያስማማል፡፡ ነገር ግን የሙስሊሞች ጉዳይ በጅምላ የኢትዮጵያ ጉዳይ የሚሆነው መቼ ነው? ደግሞስ እንዴት ነው? ይህንን ስንል ምን ማለታችን ነው? ይህንንስ ለማለት ያስፈለገው ለምንድነው? የሚሉትን ነገሮች የአቶ ሰለሞን ጽሑፍም ሆነ ይህንን አባባል እንዲደግፍ የተቀናበረው ቃለ መጠይቅም አላሳዩንም፡፡

ለአገርና ለወገን የሚያስቡና በትክክለኛ ጋዜጠኝነት ሙያ ላይ የተሰማሩ ማቅረብ የሚገባቸው ነገር የኢትዮጵያውያንን ሁሉ ጉዳይ፤ የእናት ኢትዮጵያ ጉዳይ ነው በማለት እንጂ የአንድን ሃይማኖት ወይንም ቡድን ነጥለው ለብቻ በማቅረብ መሆን አይገባውም፡፡

ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ኢትዮጵያዊ መሆኑን እስካመነና፤ አገሩን ከሃይማኖቱ ነጥሎ በመመልከት ለአገር ሰላምና አንድነት እስከቆመ ድረስ የእርሱ ጉዳይ የኢትዮጵያ ጉዳይ ነው፡፡ አንድ የአገር ዜጋ በሃይማኖቱ ሳይሆን በአገር ዜግነቱ ብቻ የእርሱ ጉዳይ የአገር ጉዳይ ነው፡፡ ከምዕራባውያኑ የዜግነትና የዜጎች ጉዳይ መርሆ መማር የምንችለውም ይህንን ነው፡፡ እነርሱ “ሃይማኖትን ከዜግነት – ዜግነትን ከሃይማኖት” በመለየታቸውና ማንም ሰው በሃይማኖቱ፣ በዘሩ፣ በጽሑፉ፣ በንግግሩ፣ ወይንም በማንኛውም ሰብዓዊ አመለካከቱ የተነሳ የዜግነት መብቱና ክብሩ እንዳይወሰድና እንዳይነካ አድርገዋል፡፡ ማንኛውም ዜጋቸው በአገራቸው ውስጥ ቀርቶ በሌላ አገር ውስጥ እንኳን እያለ መብቱ እንዲከበር ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ፡፡ መብቱ ሲጎዳም ግለሰቡ እስካለበት አገር ድረስ ወኪሎቻቸውን ልከው ይከራከራሉ፣ ጋዜጦቻቸውም ተገቢውን ርብርብ ያደርጋሉ፣ አንድ ዜጋ ክቡር ነው፣ ክቡር ያደረገው ደግሞ ሰው መሆኑ እንጂ በሃይማኖቱ ለብቻው ተነጥሎ አይደለም፡፡

አቶ ሰለሞን የሙስሊሞችን ጉዳይ ገሃድ ለማውጣትና ወደ አንድ ጎን ያዘመመ ሙግቱን ለማሰማት ጥሩ ጥረቶችን አድርጓል፡፡ በዚህም የአገሪቱን ታሪካዊ አካሄድ፣ ሙስሊሞች ኢትዮጵያን ከረገጡ በኋላ እስከ ቅርብ ድረስ ይከተሉ የነበረውን እርሱ እንዳስቀመጠው የዝቅተኝነት መርሆ ማለትም “በዚህም የተነሳ የኢትዮጵያ እስልምና ከሃይማኖታዊ ስነ መለኮቱ ውጭ ማህበረ ኢኮኖሚና ፓለቲካዊ ትውፊቱን ኢትዮጵያ ውስጥ ለመስራት ተገዷል” ብሎናል፡፡ እዚህ ላይ አቶ ሰለሞን እስልምና አገሪቱን ከረገጠ ጀምሮ ይመኘው የነበረ ነገር እንደነበረ ቢጠቁምም በግልጥ ሊነግረን አልቻለም፡፡ ቀጥሎም የገዢውን መደብ ያስደነገጠ ነው ያለውን ንቃተ እስልምና ሃይማኖት እንደ አዲስ ነገር አሳይቶን፣ የአገሪቱ ንግድ እንቅስቃሴ የሙስሊሞች መብት እንደነበረ ዓይነት አድርጎ በማስቀመጥ በኢህአዴግ እንደተነጠቁ አስመስሎ አቅርቦታል፡፡

ሙስሊሙ ንግድ ላይ መሰማራቱን ስለተቀማ በትምህርት ላይ ተሰማርቶ ስራ ሊያገኝ እንዳልቻለ ይህ ሁሉ ተደማምሮ ሙስሊሞች የመብት ጥያቄን እንዲያነሱ እንደቀሰቀሳቸው አንስቷል፡፡ ነገር ግን ተምሮ ስራ ማጣት በሙስሊሙ ላይ ብቻ የመጣ ችግር ነውን? በንግድ ላይ የመሰማራት መብትንስ ማጣት የሙስሊሙ ቡድን ብቻ ችግር ነውን? ከትልልቅ ተቋመት ተመርቀው የኢህአዴግ አባላት ባለመሆናቸው ስራ ሳያገኙ የተቀመጡ ብዙ ክርስትያኖችና የሌላው እምነት ተከታዮች የሉምን? አቶ ሰለሞን እነርሱን ቢያንስ ከሙስሊሞች ጋር ለምን አልጠቀሳቸውም?

ከጽሑፉ በመነሳት አቶ ሰለሞን ለምንና ለማን እንደቆመ ለማወቅ ያስቸግራል፤ ቢያንስ ለወደፊቷ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊነትና የሰው ልጅ አብሮ መኖሪያነት ለመቆሙ ያጠራጥራል፡፡ ለዚህ በቂ ምክንያት አለኝ፣ ምክንያቴ እንደሚከተለው ያሰፈረው ሃሳብ ነው “ኢህአዴግ ሀይማኖትን ፖለቲካዊ ማድረግ (politici-zation of religion) የሚለው ሀሳብ ካለገደብ የፈራው ይመስላል፡፡” በማለት ጽፎ በመቀጠልም፤ “በመሆኑም ትንሽ ኮሽ ላለ ሀይማኖታዊ ጥያቄ ስሱ በመሆን ያልተመጣጠነ መልስ ወደ መስጠት ለመሄድ ጊዜ አልወሰደበትም፡፡ ሀይማኖታዊ ዋጋ ለመክፈል ለተዘጋጀ ሰው ይህ የማይገኝ አጋጣሚ በመሆኑ ጥያቄውን የባሰውኑ ያጠናክረዋል፡፡” በማለት ያስቀመጠው ሃሳብ ነው፡፡ ከእነዚህ ዓረፍተ ነገሮች በመነሳት አንድ ሰው የሰለሞን ጽሑፍ የሚያቀነቅነው “ለሃይማኖት ፖለቲከኝነት ነው” በማለት ቢናገር የሚሳሳት አይመስለኝም በተለይም ለሙስሊም ሃይማኖታዊ ፖለቲከኛነት እያቀነቀነ ነውና፡፡

በአጠቃላይ የሃይማኖት ፓለቲከኛነት በተለይም የሙስሊም ሃይማኖት ፖለቲከኛነት ኢህአዴግ፤ ቀርቶ የሰው ዘር በሙሉ ሊፈራውና ሊጠላው ሊዋጋውም የሚገባው ነገር ነው፡፡ በተለይ ለአገራችን ለኢትዮጵያ አጠቃላይ ሁኔታ ተቀባይነት የሌለው ነው፡፡ ይህንን ለመረዳት የሚፈልግ ማንም ቢኖር የሙስሊሞችን መጽሐፍ ቁርአንንና ሕጋቸውን ሸሪያን ማገላበጥ ይችላል፡፡ ከዚህም በላይ የሙስሊም ሃይማኖታዊ ፖለቲከኛነት ከመጀመሪያው ጀምሮ የተተገበረባቸውን አሁንም ያሉትን አገሮች እናውቃለን፣ የሰው ልጅ ሰቆቃና ሮሮ በየዕለቱ ሞትና እልቂት ታሪካቸው አይደለምን?

የአቶ ሰለሞን ጽሑፍ ሙስሊሞች ንግዱን በኢህአዴግ በመነጠቃቸው ትምህርትም ተምረው ስራ በማጣታቸው ሕገ መንግስታዊ የመብት ጥያቄ አነሱ ለማለት ያቀነቅናል፣ ነገር ግን እውነተኛ ጭብጥ የሌለው ነው፡፡ መርካቶንና በአገሪቱ ውስጥ ያሉትን የንግድ ቤቶች የግብርናና የልማት ኢንቨስትመንቶች የሆቴሎችን ግንባታዎች ሳይቀሩ በእነማን እንደተያዙ አቶ ሰለሞን መረጃ የለውም ማለት ነውን? የአገሪቱ ሙስሊሞች ሳይቀሩ የቱርክና የሳውዲ አረቢያ የግብፅ ሙስሊም ቱጃሮች አገሪቱን እንደመቆራኘት ያህል በተለያየ ዘርፍ አልዘመቱባትምን? ይህ ደግሞ የሆነው ከመቼውም ይልቅ በኢህአዴግ መንግስት ብቻ ለመሆኑ አቶ ሰለሞን እንግዳ ነውን? ኢህአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ ጀምሮ በአዲስ አበባ ብቻ የተሰሩ መስጊዶችን ቁጥር አቶ ሰለሞን አያውቅምን? በታሪክ ውስጥ ስልጣን ከያዙት መሪዎች ውስጥ እንደ ኢህአዴግ ለሙስሊሞች የተመቸና አገሪቱን ለሙሽሊሞች የሸጠ ማንም የለም፡፡ በዚህ መልኩ ኢህአዴግ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላት ተደርጎ ሊቆጠር ይገባዋል፡፡

ሰለሞን ከተናገረው አንድ እውነታ ገዢው ፓርቲ የሙስሊሞችን አካሄድ አያውቅም የሚለው ይደነቃል፡፡ ምክንያቱም የመስጊድ ግንባታ ፈቃድ በመስጠትና በማስገንባት፣ ለሙስሊሞች ብቻ በልዩ ሁኔታ በሚሰጥ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ሙስሊሞችን ለማርካት ጥያቄያቸውንም ለመመለስ አልቻለም፡፡ ምክንያቱም ሰለሞን እንደጠቆመው የእነርሱ ጥያቄ መስጊድ መገንባት ትምህርት ቤት መክፈት ትልልቅ ኢንቨስትመንት ማካሄድ ብቻ ሳይሆን ፓርላማውን መቆጣጠርና ኢትዮጵያን ከእስላም አገሮች አንዷ አድርጎ ክርስትያን ኢትዮጵያን ባገኙት ሁሉ መንገድ መበቀል ነው፡፡

ኢህአዴግ በእስልምና ላይ ያልተደሰተበት ወይንም እስልምናን በጥርጥር ዓይን እንዲያይ ያደረገው ይህ ውስጣዊ ጥያቄያቸው እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ለዚህ ነው የአቶ ሰለሞን ጽሑፍ ሚዛን ያጣው፣ ለዚህ ነው ኢሕአዴግንና መለስ ዜናዊን ለመስደብ ብቻ ሲባል ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ መሳትና አንባቢንና ሕዝብን ማሳሳት ትክክል አይደለም የምለው፡፡

እኔ እንደማምነው ከሆነ የሙስሊሞች ጉዳይ የኢትዮጵያ ጉዳይ አይደለም ወይንም ሊሆንም አይችልም የሚል የፖለቲካ መሪ እና ድርጅት ሊኖር አይችልም፡፡ ትልቁ ጥያቄ ግን ሙስሊሞች፣ ቃለ መጠይቅ የተደረገለትን ጋዜጠኛ ጨምሮ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያውያን ነገር የእኛ ነገር ነው፣ የእኛ ጉዳይ ነው ይላሉ ወይ? የሚለው ነው፡፡

እኔ እንደማውቀው ሁሉ የክርስትያኑ እምነት መመሪያ የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ፣ ለሰው ዘር በሙሉ የሕሊናና ተፈጥሮአዊ የሆነው የሰብዓዊ እርህራሄ እንዲደረግለት ያበረታታል፡፡ ክርስትያን አማኞች ሙስሊሞችን ብቻ ሳይሆን ማንኛውንም የእምነት ተከታይ ጠላቶቻቸውንም ጭምር እንዲወዷቸው፣ እንዲፀልዩላቸው፣ እንዲያከብሩዋቸው አብረዋቸው የነፃነትን ደስታ እንዲቋደሱ፣ አብረዋቸው በሰላም እንዲኖሩ ይናገራል፡፡

አሁንም እኔ እንደማውቀው ሁሉና በትክክል ጠቅሼም ለማስረዳት እንደምችለው የሙስሊሞች የእምነት መመሪያ ግን ተከታዮቹ ሌላውን የሰውን ዘር የሚወዱበት ከሌላው የሃይማኖት ቡድን ጋር አብሮ በሰላም መኖር እንዲችሉ የሚሰጠው መመሪያም ሆነ ሰዋዊ ሰብዓዊ ርህራሄ በጭራሽ የለውም፡፡

ሌላው ዜጋ ለሙስሊሞች መልካም የሆነ አመለካከት ሊኖረውና እንደሰው ሊወዳቸው ይችላል በማለት መናገር እንችላለን፣ የሙስሊሞቹን ግን መናገር ማንም አይችልም፣ ጽሑፉን የጻፈው ሰለሞንም ሆነ ቃለ መጠይቅ ያደረገለት ሰውም መናገር አይችሉም፡፡ ምክንያቱም የሃይማኖታቸው መጽሐፍ የቁርአንና የሕጋቸው የሻሪያ መርሆ በፍፁም አይፈቅድላቸውም፡፡ ደህና ሰለሞንም ሆነ ቃለ መጠይቅ የተደረገለት ሰው ወይንም የሙስሊም ሊቃውንት ከዚህ ውጪ መሆናቸውን ከሃይማኖታቸው መጽሐፍ በመጥቀስ በተግባርም ከታሪክም ሊያሳዩን ከቻሉ ወደፊት እንጠብቃለን፡፡ ይህንን ማድረግ የሚችሉት መጽሐፋቸውን ሲጥሉና ልዩ የሆነ ተሐድሶ ሲያደርጉ ብቻ ወይንም እምነቱን ለቀው እንደ እኔና እንደመሰሎቼ ሲያደርጉ ብቻ ነው፡፡

ለዚህ ነው እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን ልናያቸው የምንችለው እንዴት ነው የሚለው ጥያቄ ዞሮ ዞሮ የሚነሳብንና የሚያሳስበን፡፡ ሙስሊሞችን የምናያቸው ከሃይማኖታቸው መርሆ አኳያ ነው ወይንስ እንደማንኛውም ሰብዓዊ ፍጡር ነው? የሌላው እምነት ተከታይ ግን ክርስትያኑንም፣ ሃይማኖት የሌለውንም፣ ወይንም እንጨትና ድንጋይንም የሚያመልከውንም፣ የፈለገውን እምነት ለመከተል የሚችል ሰብዓዊ መብት እንዳለው የሰው ዘር መመልከት ይችላል፣ የእስልምና ተከታዮችና እምነታቸው ግን እንደዚህ ዓይነት አመለካከት የላቸውም፣ ይህ ሰብዓዊነት በታሪካቸው አልታየም አሁንም አይሆንም ለመጪውም ጊዜ አይሆንም፡፡ የሰለሞን ጽሑፍ ይህንን ስላላሳየን በጣም አስቸጋሪ ጽሑፍ ነው ተገቢም አይደለም፡፡

ቃለ ምልልሱ፡

ሰለሞን ስዩም ለማለት የፈለገውን ለማስደገፍ ጸሐፊውንና የሙስሊም ጋዜጠኛውን ሙስሊማዊ አመለካከት በቃለ ጥያቄ አቅርቦልናል፡፡ መልካም ጥረት ነው፣ ፈረሱም ሜዳውም የሰለሞን ስለሆነ የፈለገውን ሁሉ ቃለ መጠይቅ ማቅረብና የሚፈልገውን ሐሳብ ማስተላለፍ ችሏል፡፡ ቃለ መጠይቁ ዞሮ ተጠማዞ የሚያሳየው ነገር የኢትዮጵያዊነትን ሐሳብና መርሆ በአንድ ላይ ስለማራመድ ሳይሆን ያው ሙስሊሞች ለዘመናት ሲሉ የነበሩትን “መብታችን ተነፈገ ነፃነታችንን ተቀማን” የሚለውን ጩኸት የሚያስረዳ ነው፡፡

ሙስሊሞች በኢህአዴግ ዘመን ከፍተኛ እገዛ እንደተደረገላቸው ሳይጠቅሱ፣ ሳያመሰግኑም አሁንም የሚጮኹት የድሮውን ጩኸት ነው፡፡ አቶ ኢስሐቅ ያስቀመጠው ዞሮ ዞሮ ተበድለናል የሚለውን ያንኑ ጩኸት ነው፡፡ ክርስትያኑና የሌላው እምነት ተከታይ በገዢው መደብ አልተበደለም ያለው ማነው? አቶ ኢስሐቅ ሙስሊሙ እንዳይማር መብት ተከልክሎ ነበር በሊቅነት መንገዶች ላይ አላተኮረም ነበር ብሏል፡፡ በየትኛው ዘመን ነበር ሙስሊም ትምህርት ቤት አይገባም ተብሎ የነበረው? ለመሆኑ መቼ ነበር የተከለከለው? እነማን ከልክለውት ነበር? አልጠቀሰልንም፡፡ እኛ ግን ሙስሊሞች ከክርስትያኖች ጋር እኩል ተምረን ነበር እኩል ተጫውተናል፣ እኩል አፈር ፈጭተናል ሙስሊም ትምህርት ቤት ሲከለከል አላየንም፣ ምናልባት የሃይማኖቱ መመሪያና ኢማሞቹ ክልክለው ከነበረ ወቅትና ዘመን ጠቅሶ ሊነግረን ይችላል፡፡ በመለስ ዜናዊም ግዛት ውስጥ ሚኒስትሮች የሆኑት ሁሉ ከየት ነው የመጡት እዚሁ አገር ውስጥ በነበረው ስርዓት በእኩል መብት ተምረው አልነበረምን? እዚህ ነጥብ ላይ ለአቶ ይስሐቅ አንድ ጥያቄ መወርወር ያስፈልጋል፡ በእስላም አገሮች ውስጥ ካሉት የታወቁት ሊቆችና ሳይንቲስት ስንቶቹ ሙስሊሞች ናቸው? በእስላም አገሮች ውስጥ ሙስሊሞች ሊቆችና ሳይንቲስት እንዳይሆኑ የከለከላቸው ማነው?

ያንዣበበ አደጋ የለም!?

የቃለ መጠይቁ ዋና ርዕስ በሕዝበ ክርስትያኑ ላይ ምንም ያንዣበበ አደጋ የለም የሚል ፕሮፓጋንዳን ያስቀመጠ ነው፣ ይህም የቃለ መጠይቁ አቅራቢ ትኩረት ሳቢ ቅንብር ነው፡፡ አቶ ኢስሃቅ እንደሚለው ቢሆን ኖሮ መልካም ነበር፡፡ በሌሎች አካባቢዎች የተደረጉትን ትቼ በጅማ አካባቢ ብቻ በተከታታይ ዓመታት በክርስትያኖች ላይ እንዲሁም በቤተክርስትያን ላይ የደረሰውን ጥቃትና እልቂት አቶ ኢስሐቅ አያውቅም ነበር እንዴ? ወይንስ በጋዜጠኛ ሙያ ላይ ተሰማርቶ እያለ አልሰማም ነበር ማለት ነው? ወይንስ አቶ ኢስሃቅ አደጋን የሚተረጉመው እንዴት ነው? አቶ ኢስሐቅ ለዘብተኛ ሙስሊም ነው፣ ወይንም ሰላም ወዳድ ነው፤ በማለት እየከበደን ብንውሰደው እንኳን፣ አቶ ኢስሐቅ ሙስሊሞችንና የሚከተሉትን እምነትና መርሆ ወክሎ መናገር ይችላል ለማለት አንደፍርም፡፡

ሙስሊሞችም ሆኑ ሌሎች “የሃይማኖት ፓለቲካ” እስካካሄዱ ድረስ በሌላው ሕዝብ ላይ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ከፍተኛ አደጋ እያንዣበበ መሆኑን ማየት ለማንም የተሳነ አይሆንም፡፡ ምክንያቱም ከዚህ በፊት የደረሱት ጥቃቶች ሁሉ የዚያ ውሽንፍሮችና ቀዳሚ ምልክቶች ናቸውና፡፡

አቶ ኢስሃቅና የሃይማኖት ፖለቲካ አቀንቃኙ ሰለሞን፣ ሌሎችም እንዲያስቡበት የምፈልገው “የሃይማኖት ፓለቲካ” በለተይም “የሙስሊም ሃይማኖት ፖለቲካ” አደጋውና መዘዙ በቀላሉ የሚታይ ሊሆን እንደማይችል ነው፡፡ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ልማትም ሰላምም በፍፁም የሚበጅና የሚጠቅም አይደለም፡፡

የሙስሊም የሃይማኖት ፖለቲካ ተሳክቶለት ሙስሊሞች ኢትዮጵያ ውስጥ ስልጣን ቢይዙ ምን ይሆናል ብለን ወደ ማሰብ ብንመጣ የሚሆነውን ነገር በጥቂቱ ልናይ የምንችለው ከጎረቤታችን ከግብፅ ታሪክ ውስጥ ነው፡፡ በግብፅ ውስጥ የክርስትያኑ ቁጥር በመቶ አስር እጅና ወደ 8.3 ሚሊየን የሚደርስ ነው፡፡ በአብዛኛውም የጥንት የኦርቶዶክስ አማኝ ክርስትያኖች ናቸው፡፡ የሆነው ሆኖ በግብፅ ውስጥ የኦርቶዶክስ ክርስትያን አማኞች የሚኖሩት ኑሮ እንዴት ነው? ሰብዓዊ መብት አላቸውን? እንደሰውና እንደ አንድ ዜጋ ይቆጠራሉን? ግብፃውያን ክርስትያኖች በግብፅ ሙስሊሞችና የሙስሊም ሃይማኖት ፖለቲከኞች ዘንድ በየዕለቱ የሚያጋጥማቸው ነገር ምንድነው?

የዓለም ዜናዎችን ብንከታተል፣ በግብፅ ብቻ ሳይሆን በኢራን፣ በኢራቅ፣ በሳውዲ አረቢያ፣ በፓኪስታን ወ.ዘ.ተ የሌሎች እምነት ተከታዮችና ክርስትያኖች ላይ የሚደርሰውን ግፍና ሰቆቃ በቃላት ማስቀመጥና በጽሑፍም መግለጥ ይከብዳል፡፡ ሙስሊሞች ስልጣንን ሲይዙ የኢትዮጵያንም ሕዝብ የሚያጋጥመው ከዚህ ያነሰ ነገር ሊሆን አይችልም፡፡ አሁን ስራ የሌላቸው ሙስሊሞችም ክርስትያኖችም ሊሆኑ ይችላሉ፤ ያኔ ግን ሙስሊም ያልሆነ ስራ አይዝም፣ ያኔ ግን ሙስሊም ያልሆነ ትምህርት አይማርም፣ ያኔ ግን ሙስሊም ያልሆነ ለምኖም እንኳን ለመብላት ይከለከላል፡፡

የሃይማኖት ፖለቲካ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሊሆን አይችልም፣ የሃይማኖት ፖለቲካ የሚሰራው ለቫቲካን ብቻ ነው ከዚያ ውጭ በተለይም የሙስሊም ሃይማኖት ፖለቲካ አደገኛ ነው ብለን ከምንለው ሁሉ በላይ አደገኛ ነው፡፡

ወደ ጽሑፌ ማጠቃለያ ስመጣ አቶ ሰለሞን በጽሑፉ ላይ ስለውሸት የተናገረውን ነገር በመጥቀስ ነው፡፡ ሰለሞን ጓደኞቼ እና አብሮ አደጎቼ ያላቸውን ጠቅሶ፡ “ታዲያ ከመለስ ዜናዊ መንግስትና ከነሰሚራና ሱልጣን ማንን አምናለሁ? እነ ሱልጣን እንደመንግስት ዋሽተዉኝ አያዉቁም፡፡” በማለት ነው፡፡ ሰለሞን እውነቱን ነው የመንግስት ባለስልጣኖች ይዋሻሉ፡፡ ነገር ግን እነ ሱልጣን ብሎ የጠቀሳቸው አይዋሹም በማለት ለሰለሞን የነገረው ማነው? የመንግስት ባለስልጣናቱ ለስልጣን ብለው ዋሽተው ይሆናል ይህንን መገመት አይከብድም እንደሚታወቀውም የኢህአዴግ መንግስት በውሸት መተጣጠፉን ያውቅበታል፡፡ ነገር ግን የሰለሞን ጽሑፍ በእርግጥ የሚገርም ነው፣ የእስልምና ተከታዮች ሁሉ ስለ ውሸት የሚናገሩትን አያውቅም ማለት ነውን? በሙስሊሞች እምነት መሰረት ማንኛውም ሙስሊም በአራት ነገሮች ላይ መዋሸት ይፈቀድለታል፡፡ እነዚህም፡ አንደኛ ሕይወቱን ለማዳን ሲል፣ ሁለተኛ ደግሞ ሰላምንና እርቅን ለማምጣት፤ ሦስተኛ ሴትን ለማባበል፣ አራተኛ በጉዞና ወይንም በጦርነት ወቅት ናቸው፡፡ ከዚህ የተነሳ በአንድ አገር የፖለቲካ ስልጣንን ለማግኘት ውሸትን መዋሸት፣ የፈጠራ ታሪኮችን ማቀናበር እስከምናውቀውና በእኛ አገር ላይ እንኳን እስከተሰራው የውሸት ፊልም ማቀናበር ድረስ በሙስሊሞች ቢሰራ ምንም ችግር የለበትም፣ በቃ ለሃይማኖቱ ማስፋፋት ሲባል ወይንም ለጦርነት ይፈቀዳል፡፡

እንዲያው ለሰለሞን እንዲገርመው ያህል “ውሸት በአሁኑ ጊዜ” በተባለ ርዕስ ስር ስለ ሙስሊማዊ ውሸት የተጻፈ ትንሽ አረፍተ ነገር ላይ ያገኘሁትን ከዚህ በታች አስፍሬለታለሁ “ንግግር አንድ ዓላማን ለማስገኘት ነው፡፡ አንድን መልካም ነገር በመዋሸትም በእውነትም (ማለትም በሁለቱም) መንገድ ማግኘት የሚቻል ከሆነ በእውነት መንገድ ማግኘት ይገባል መዋሸት ስለዚህም ትክክል አይደለም አስፈላጊ አይደለምና፡፡ ነገር ግን ይህንን ዓላማ እውነትን በመናገር የማይገኝ ሆኖ ሲቻል እና በውሸት ማግኘት ከተቻለ መዋሸት ይፈቀዳል ይላል” በImam Abu Hammid Ghazali (Ahmad ibn Naqib al-Misri, The Reliance of the Traveller, translated by Nuh Ha Mim Keller, amana publications, 1997, section r8.2, page 745) እንግዲህ ሰለሞን ከሁለት ውሸታሞች ማለትም “ከሃይማኖት ውሸተኛ እና ከፖለቲካ ውሸተኛ” መካከል የሚያምነውን አሁን ይምረጥ፡፡

የሆነው ሆኖ እኛ አገራችንን የምንወድ ኢትዮጵያውያን የሰለሞንን የፖለቲካ ሃይማኖት አቀንቃኝነት አንፈልገውም፡፡ የሃይማኖት ፖለቲካ ለሌሎች መከራ እና የሰብዓዊ መብት መገፈፊያ መሆኑን እያወቅን ወደ አገራችን ልንጋብዘው አንፈልግም፡፡ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጉዳይ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ጉዳይ የኢትዮጵያ ጉዳይ ነው፣ አዎ እኛ ሙስሊሞችን እንፈልጋቸዋለን፣ እንወዳቸዋለን፣ እኛ ተቻችሎ መኖርን እናውቃለን እንቀበለዋለንም፡፡ ያለ ሃይማኖት ልዩነት ሁላችንንም በምትችለው አገር፣ በሰላም በአገራችን፣ በሰላም አብረን እንኑርበት፡፡ ስለዚህም ልናነግበው የሚገባንና መሆን ያለበት መርሆ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ጉዳይ የእናት ኢትዮጵያ ጉዳይ መሆን ይገባዋል የሚለው ነው፣ በጋራ የሚጠቅመንና የሚያሳድገን ይህ ብቻ ነውና፡፡

  1. ቤኛ ጦኔ
    | #1

    ትክክለኛና ወቅታዊ ጽሁፍ ነው ለምሳሌ (ካፊር) የሚለውን አጠራር ብንመለከት የማያምን የሚለውን ስያሜ እንደያዘ እንረዳለን የማያምን ማለት ደግሞ የ ( መሃመድ ነብይነትን )የማይቀበል ማለት ነው ስያሜው የብዙ ህዝባችን ማንነት ይነካል ስለዚህ ስለ ካፊር የተጻፉ የቂርኣን አስተምሮቶች መስተካከል አለባቸው ::
    እስልምና ከኅይማኖታዊ ትውፊቱ ይልቅ አረባዊ ባህላዊ ህሴትን በማጉላት ላይ ያተኩራል :: ለምሳለ ኣንድ አረባዊ ዜግነት የሌላው ሰው እስልምናን ሲቀበል የዘወትር ጸሎቱን በአረብኛ ያደርጋል የአረብ ሃገር ባህላዊ ህሰቶችን እንዲከተልና ሲጸልይ ፊቱን ወደ አረብ ሃገር አቅጥጫ ዞሮ እንዲጸልይ ይነገረዋል …. ወዘተ ::

  2. Anonymous
    | #2

    I like this woyane apologist. He comes out at a time when peope are coming together to challenge the Woyane regime. So it is hurting where it hurts more, Woyanes and Woyane cadres. Get out of Ethiopian politics now. You are too compromised about anything Ethiopian because of your desire to seed hatred among Ethiopians and religious beliefs. We know that a non troubled Ethiopia is not conducive for your looting.

  3. Mamo
    | #3

    I like this woyane apologist. He comes out at a time when peope are coming together to challenge the Woyane regime. So it is hurting where it hurts more, Woyanes and Woyane cadres. Get out of Ethiopian politics now. You are too compromised about anything Ethiopian because of your desire to seed hatred among Ethiopians and religious beliefs. We know that a non troubled Ethiopia is not conducive for your looting.

  4. Michael
    | #4

    It’s believed that in the future Muslim fanatics will be the core problem of the country. As the writer mentions, many Christian churches has been burnt by existing Muslim fanatics in the country. In the South we see that Muslim school students and their communities let down burnt “Selties Christians Churches”. They were chanting as Alah-Akber, god is great. Their chanting is the same with the Terrorist Muslim Al-Qaida. I had a great friendship with my Ethiopian Muslims but still I am ok. But now after I see the burning of many churches by chanting Al-Qaida’s slogan, it forced me to ask why? As we have at this moment entrusted government, Muslims are doing whatever they like through monster Alamudi and Ali-Abdo (who was mayor of Addis Ababa). These two monsters build hundreds of Muslim temples in different part of the country. When all these happen, agents of the Orthodox Church don’t show up. In case of the rule the Muslim sharia doesn’t or can’t bring peace in every country or the world. Because sharia rule can’t live in harmony with other religions. Sharia is simply the domination of Islam over anything or religion. We can see what the consequence of the rule or law Sharia is in Sudan. It divides the country in to two, South and North Sudan. Because the north Sharia law of the Muslims can’t coexist with the south Christians in harmony. The two countries are now in terrific war. God Bless Ethiopia.

  5. Anonymous
    | #5

    @Mamo
    I wouldn’t agree more bro.,looting Ethiopia is their primary goal.
    All Ethiopians Watch out for these wolfs in sheep’s skin.

  6. ኢትዮጵያ
    | #6

    Ato Jafar Hasen, you are not Jafar but rather Meles Zenawi because each and every word in the article are that of Melese’s words. We Ethiopians(Christians as well as Muslims) love each other. Our history is not the history of Egypt and other countries, we are unique. Therefore, don’t try to interfer between christians and muslims.

  7. Check it
    | #7

    Please check on the internet: write this and google – ‘False religions’. And ‘the criteria of true religions’.

  8. በሺር
    | #8

    የጃፋር ጽሑፍ ወቅታዊ ነው፡፡ በሙስሊሞች የሃይማኖት ፖለቲካ እንቅስቃሴ የተነሳ አገሪቱ ልትገባበት ያለውን ስቃይና ፈተና የሚጠቁም ነው፡፡ መለስ ዜናዊንና የፖለቲካ ፓርቲውን ኢህአዴግን ለመንቀፍ ብቻ ሲባል የአገር ብቻ ሳይሆን የሰው ዘር፣ ማለትም የማንኛውም የሰው ልጅ ጠላት የሆነውን “የሙስሊም ሃይማኖት ፓለቲካ” ለመደገፍ መነሳት እብድነት ነው፡፡
    ከዚህም በፊት አኢጋን “ጥሪ ለመላው የሃይማኖት ነጻነት አፍቃሪ ኢትዮጲያዊያን በሙሉ” በሚል ርዕስ የሰጠው የሙስሊማዊ ድጋፍ መግለጫ፣ የአሁኑ በፍኖተ ሰላም ላይ የወጣው ጽሑፍ አቶ ጃፋር ሃሰን እንዳለው “ሚዛናዊ እና የእውነት ጭብጥ የሌለባቸው ጽሑፎች” ሲሆኑ የሚጠቁሙትና ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የሚጮኹት ብዙዎች ስለ “የሙስሊም ሃይማኖት ፖለቲካ” ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ነው፡፡
    የጃፋር ጽሑፍ አንጀቴን አርሶታል እባክህ ደጋግመህ ጻፍልን፣ እንደ ሰለሞን ስዩም ዓይነት “ግራ የተጋቡ” ወይንም “በሙስሊም ፔትሮ ዶላር” የተገዙ ጋዜጠኞችን ልክ እንዲገቡ አድርግልን፡፡ ከሰለሞን ስዩም ዓይነት ጋዜጠኞች እኛ የምንጠብቀው ለአገራቸው መስዋዕትነት እየከፈሉ እንዳሉት እንደ እነ እስክንድር ነጋ በእውነት እና ለእውነት መቆም ነውና፡፡

    ማንኛውም ኢትዮጵያን የሚወድ፣ ለአገሪቱ ሰላምና የወደፊት ደህንነት የሚቆረቆር ፖለቲከኛ ሁሉ ሙስሊሞችን መጥላት የለበትም ነገር ግን ውስጥ ውስጡን በሳውዲ አረቢያና በሌሎች የሙስሊም አገሮች እገዛ የሚያደርጉትን ፀረ ኢትዮጵያ እንቅስቃሴ ማወቅ አለበት፡፡ ስለዚህም ጃፋር እንዳለው “የሙስሊም ሃይማኖት ፖለቲካ” የአገሪቱ ጠላት እንደሆነ መታወቅ አለበት፡፡

    የጋራ ጠላታችንን ኢህአዴግን ለመቃወም ሲባል ሌላ የከፋ፤ እጅግ፣ እጅግ በጣም በቃላት ሊገለጥ በማይቻል መንገድ በጣም የከፋ የአገር ጠላትን መደገፍና መቀበል አይኖርብንም፡፡

    ይሁን እንጂ አቶ ጃፋር ሃሰን እራሱ የወያኔ ደጋፊ መሆኑ ለእኔ በጭራሽ አይታየኝም፡፡ የወቅቱን ሁኔታ በእውነት የሚያሳየንን፣ ምናልባትም ደስ የማይለንን ነገር የነገረንን ሁሉ ወያኔ ነው ለማለት እንችላለን እንዴ? ደግሞስ እንደዚህ ማለት ይገባል እንዴ? መልሱን ከዚህ በላይ አስተያየት ለተውልን ለእነ አኖኒመስ ልተወው!

  9. kemal
    | #9

    ሁለቱም ማለትም የሃይማኖት ፖለቲካም የጎሳ ፖለቲካም /በወያኔ እንደታየው/ ለሃጋራችን ጸር ከመሆናቸውም በላይ በአፋጣኝ መፍትሄ
    ካልተበጀለት ኢትዮጲያችን ለማንኛችንም እንደማትሆን ማወቅ መቻል አለብን!

  10. the observer
    | #10

    Jaffer…i don,t think you understand or read solomon’s article well..this is not an intelectual debate..it is a pure personnal feelingsfor this i side with solomon..and lpz if u can write better then write ur op..and lets learn something…

  11. እግዜር ይርዳን
    | #11

    አደገኛ ማለት አንተ ነህ

    ‘…የሙስሊም የሃይማኖት ፖለቲካ ተሳክቶለት ሙስሊሞች ኢትዮጵያ ውስጥ ስልጣን ቢይዙ ምን ይሆናል ብለን ወደ ማሰብ ብንመጣ የሚሆነውን ነገር በጥቂቱ ልናይ የምንችለው ከጎረቤታችን ከግብፅ ታሪክ ውስጥ ነው፡፡…’

    ‘…እኔ እንደማውቀው ሁሉ የክርስትያኑ እምነት መመሪያ የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ፣ ለሰው ዘር በሙሉ የሕሊናና ተፈጥሮአዊ የሆነው የሰብዓዊ እርህራሄ እንዲደረግለት ያበረታታል፡፡ ክርስትያን አማኞች ሙስሊሞችን ብቻ ሳይሆን ማንኛውንም የእምነት ተከታይ ጠላቶቻቸውንም ጭምር እንዲወዷቸው፣ እንዲፀልዩላቸው፣ እንዲያከብሩዋቸው አብረዋቸው የነፃነትን ደስታ እንዲቋደሱ፣ አብረዋቸው በሰላም እንዲኖሩ ይናገራል፡፡…’

    1. ሙስሊሙ ስልጣን ቢይዙ ምን ያመጣል ብሎ ማለት እነሱን እናግልል ማለት ነው ስለዚህም ታረም
    ሁለተኛ
    2. ወያኔ የክርስትያን ልጆች አይደሉም ልትል ነው? ወይስ አንደኛውም ሆነ ሁለተኛው ዓለም ጦርነትን ክርስቲያኖች አላስነሱትም? ለመሆኑ አፓርታይድን ያቀነባበሩት የመሩት ከርስትያን አይደሉም?

    ፓለቲካ ጥፋትን በዘር ይሁን በሃይማኖት ማሳበብ አግባብ አይደለም አደገኛ ነው

    እዛው የመጣህበት ሒድና አታል!!!

  12. ሁስይን
    | #12

    ato jafar metilwn yemitawk aymsleghnm ahun sele eslmena aweku beleh new meathun yemitawrdew eslemine ante kemitlew hulu yetera new lente mels mestet gize mebaken behunem eslam endenebrk new enkawn wede kirestenegn kerto gedel betgeba eslimina kintat yekil aygodam bealem betam bemsfafat ley yele heymanot eslimine mehonun kelawek kahun behale lemawek moker

  13. በሺር
    | #13

    እስካሁን ድረስ ካየናቸው አስተያየቶች የቤኛ ጦኔ፣ የሚካኤልና የከማል አስተያየቶች ከጃፋር ሃሰን ጋር ይስማማሉ፡፡ እንደምገምተውም አገሪቱ በሃይማኖት ፓለቲካ በተለይም በሙስሊሙ የሃይማኖት ፖለቲካ ውስጥ ብትነከር ኢትዮጵያውያን መውጫ የሌለው ማጥ እንደሚዘፈቁ ገብቷቸዋል፡፡
    ይህ እውነታ ለብዙዎች አልገባቸውም፣ ብዙዎች የሚመስላቸው አብረው እንደኖርን – አብረን እኖራለን የሚለው ዘፈን እንደሚቀጥል ነው፡፡ የሙስሊም የሃይማኖት ፖለቲካ ይህንን ዘፈን የሚዘፍነው ስር እስኪሰድና በእግሩ እስኪቆም ድረስ ብቻ ነው፡፡
    የሙስሊም የሃይማኖት ፖለቲካ ከሌላው የሃይማኖት ፖለቲካም ሆነ ግለሰብ ጋር ወንድማማች ነን የሚልበት ጊዜ በፍፁም አይኖርም፡፡ ይህንን ይላል ብለን የምናስብ ከሆነ ትልቅ ስህተት ውስጥ መኖራችን ነው፤ በዓለም ውስጥ ከተፈፀሙት ታሪኮች ምነው ብንማር?
    ብዙ ኢትዮጵያውያን ያንዣበበውን አደጋ ላለማወቃቸው ሌላው ማስረጃ በቅርብ በወጣው በፍኖተ ነፃነት ቁጥር 42 ላይ የአሜሪካ የኦርቶዶክስ ሲኖዶስም ከሙስሊም ወገኖቻችን ጋር አብረን እንቆማለን የሚለው መግለጫ ነው፡፡
    ከሙስሊሞች ጋር አብረን ልንቆም ወንድሞቻችን ልንላቸው ልንደግፋቸውም እንችላለን፣ በሙስሊም የሃይማኖት ፖለቲካ መርሆ መሰረት ግን ሌላው ሲጠቃ ሌላው ላይ ግፍ ሲደርስ አብሮ ወንድሜ ብሎ መቆም አይኖርም፡፡ የሙስሊም የሃይማኖት ፖለቲካ ውለታ አያውቅም ይህ ሕዝባችን የድጋፍ አካሄድ ለአገሪቱ በፍፁም አይበጅም፡፡ አብረናቸው ቆመን ደግፈናቸው የሃይማኖት ፖለቲካቸው ሲሳካ የመጀመሪያ ጥቃታቸው የሚያነጣጥረው በቤተክርስትያን፣ በገዳማቱ እና በካህናቱ ላይ እንደሆነ አለመታወቁ ይገርማል፡፡ ለዚህ ማስረጃ ይኖር ይሆንን እስኪ ከሚከተለው ሊንክ ላይ ያነበብኩትን ተመልከቱ! ትገረማላችሁ http://www.answering-islam.org/amargna/news_digest/01_04_2012.html እግዚአብሔር ይችን አገር ከሚመጣው ክፉ አዘቅት ይጠብቃት፡፡

  14. Anonymous
    | #14

    mengistn lemekawem sibal bcha mengst yemiwesdachewn ermjawech hulu bemetfo mewsed tiru aydelem. be ethiopia yalew yemuslimu enkiskase betilket litay yigebal. bekelalu mayet tegebi aydelem. yegizewn yemengist askefi dirgit bemayet mengistin kemikawem wegen hulu maber yebefitun sihte medgem endaihon. Dergn lemetal kewoyane gar tebabren keditu wedematu werdenal- yih sihtetachin endaidegem lindegfewna linikawemew yemigebanin meleyet yasfelgal. weyane ketewegede lelaw ayaschegrim blo maseb yewahnet new. yetim ayders teblo yetenakew woyane new ahun mekerachini eyasayen yalew. silezih eyandandun enkiskasiachinin betinikake meramed yasfelgal. zim bilo mawej ayawatam

  15. Sirak
    | #15

    That is the pen of Militia Meles Zenawiwith the name of Muslim name Jafar Hasen. Zenawi, we know who you are and you are the cancer cell of our beloved country.
    Arrogant militia

  16. tofik
    | #16

    we need our monarchy for our future peace.
    aslong as you are not unhappy if the king convert to islam in the future like nagashi.

    i want my old muslim culture i don’t need the new alhabshi or wehabiy.
    the govermet has to protect the nation from any new religion intering to the country.under cover chjristians they going to exterim,those are pushing the normal muslim to extrimisum.

    if you are in addis the new generation christians to make angery the muslim they open mezmur to extrim,that has to stop its market place ,from every corner,you are happy to hear if you are christian but the message is to the muslim it is to shut up.thats whewre the problem is.

    for the guy who talk about why the is no muslim scintist there are butif you talk about arab we are not arab,if you talk about muslim.
    astronaout armstrong he converted to islam i can tale you one geneuse look michel jackson,chris tacker,the rush hour star,mick tyson,
    you go to google 38 famouse and scintist convert to islam ,there are muslim scintist,now youy get the point ,

    if you ask me arab,the pyramid,the number you are using now the first mathematics,the babilon,go and search you will get the answer.

    as an ethiopian muslim u can ask me do not ask me about islam you can be amuslim tomorrow so when you become no one is gone take away from you your tiltle.DR or profesor,so you are amuslim profesor,

    if you asking nation scintist you labling people so you gone disable your self.

  17. elias55
    | #17

    yemcheresha bokbuaka neh! anten bilo tsehafi tsifeh motehal bezih tsufieh min endantsebarekh gilts new. Demo yeferahew ayikerim!

  18. ታዛቢው
    | #18

    ውውውው እየተስተዋለ ይሁን እንጂ እንዴ ምነው በሰው ቁስል እንጨት ስደድበት ማለት ይህ ነው:: ብዙ ነገሮች ሊዘበራርቅብን አይገባም :: የኢትዮጵያ ጉዳይ እንደሃገር የሁሉም ዜጋ ጉዳይ ነው:: በተለያየ መልኩ የግለሰብና የማህበረሰብ ጉዳይ ተነጥሎ ባግባቡሊታይ ይችላል:: አሁንም ቢሆን ሙስሊሙ በጣም አደገኛ የሆነ መከራ ደርሶበታል በዚህን ጊዜ ከላይ የቀረበው አይነት አሳፋሪ ፁሁፍ መቅረቡ በጣም ቢያሳዝንም ምናልባት ፀሃፊው የወያኔ አገልጋይና በፍም ላይ ነዳጅ አርከፍካፊ ናቸው::
    እስልምና ላይ ምንም ለሰው ልጆች ሰብአዊነት ያሚያዝ መልክት የለም ማለታቸው ፍፁም ቅጥፈት ለመሆኑ ሙስሊም ጎረቤት ያለው እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ መመስከር ይችላል::

    ስለኢስላም ሰብአዊነት መረጃ ከተፈለገ ታላቁ የመጨረሻው ነብይ ነብዩ መሃመድ ሰላም ለሳቸው ይሁንና መልክታቸውን እንዳስተላለፉ አንድን ሙስሊም ያልሆነ በሙስሊም ሃገር ተዋውሎ የሚኖርን ሰው መግደል ወደ ጀሃነም አዘቅት እንደሚያስወረውር ሙስሊሞችን አስጠንቅቀዋል:: በሌላ መልክታቸው እንኩዋንስ የሰውን ልጅ አይደለም አንዲትን ድመት አስራ የምታሰቃይ ሴት በገሃነም እንደምትሰቃይ ገልፅእዋል:: ከዚህ የበለጠ ለፍጡራን ማዘን ከማንም ቀድሞ ሲሰበክ አልሰማንም ከኚህ የፍቅር የሰላምና የብሩህ ተስፋ ገላጭ ነብይ በስተቀር::
    ስለዚህ ከላይ የሚነበበውን መርዛማ ፁሁፍ አቅራቢ በዚህ መልቅቴ ሊማሩበት ብቻ ሳይሆን ጤነኛ የሆነ ህሊና ካላቸው ህሊናቸውን ሊያክሙበት ይገባል:: በይበልጥ ለመረዳት ከታች ያለውን ፁሁፍ በጥሞና ማንበብ በቂና ከበቂ በላይ ነው::::

    መቻቻል በኢስላም

    ፈጣሪያችን አላህ መሬትንና በዙርያዋ ያሉትን ሁሉ ከፈጠረበት ጊዜ አንስቶ ለሰዎች ትክክለኛውን የሕይወት ጎዳና እያመላከቱ በደሐቅ የሚመሩ፤ መጥፎን ተግባር እያጋለጡ የሚያስጠነቅቁ መልእክተኞችን ልኳል።
    ለዘመናት የተላኩት ነብያት ቁጥራቸው ቢበዛም፤ ሃይማኖታቸው ለየግል ሆኖ ሕጋቸው ቢለያይም፤ ሁሉም የሚጣሩት የሃያሉን አላህ አንድነት በማስተጋባትና ብቸኛ ተመላኪነቱን በማረጋገጥ ነው። ከአላህ ሌላ ለፍጡር ያለመገዛት፤ በአላህ ያለማሻረክንና አላህ አንድና ብቸኛ ጌታ መሆኑን፤ የሁሉም መጠጊያና ከዚህ በፊት ያልወለደም ያልተወለደም ሆኖ፤ በባህሪው አንድም ቢጤ እንደሌለው ጥሪ አድርገዋል።
    ከብዙ መቶዎች አመታተ በኋላ… መልእክተኞች ወደ አላህ መንገድ ያደረጉት ጥሪ ተረሳና፤ ከሰማይ የወረዱ ወደ ሐቅ የሚጣሩ መፅሐፍቶች የሰው እጅ ገብቶባቸው ተበርዘው፤ ጥመትና በአላህ አምልኮ ማጋራት ሲስፋፋ፤ አላህ እስልምናን የሐይማኖቶች መደምደሚያ እንዲሆን፤ አለምን ሁሉ በሐይማኖት አንድ ለማድረግ ፤ባለፉት ሃይማኖቶች ተከስቶ የነበረውን ጥመት በማጋለጥ፤ ከአላህ በስተቀር በሐቅ ሊመለክ የሚገባው አምላክ እንደሌለ ለማመላከት፤ አላህ ነብዩ መሐመድን (ሰ አ ወ) (በረከትና ሰላም ለርሳቸ ይሁንና) በነብይነት መርጦ ወደ ጠቅላላ የአለም ሕዝቦች ላካቸው።
    በተጨማሪም ለሰዎች እውነታዎችን ለማመላከት፤የሐይማኖታቸውንም ሆነ የሕይወታቸውን ጎዳና ግልፅ የሚያደርግ ብቸኛና ትክክለኛ የሆነ የመተዳደሪያ ሕግ የያዘ ቁርአን በነብዩ መሐመድ አማካኝነት ከሰማይ አውርዷል። ይህም ቁርአን ከሰማይ ከወረዱ መፅሐፍቶች የመጨረሻው ሲሆን እስከ አለም ፍፃሜ ድረስ ለሰዎች መመርያ ሆኖ እንዲቆይ አላህ ወስኖታል። በተጨማሪ በቁርአን መልእክት ላይ የሰው እጅ ገብቶበት እንዳይበረዝና እንዳይደለዝ አላህ እራሱ እንደሚጠብቀው ቃል ገብቷል።
    በእርግጥ አላህ የእስልምና ሐይማኖትን ኢስላም ብሎ ነው የሰየመው፤ ትርጉሙም መማረክ (ኢስቲስላም) ማለት ሲሆን፤ ይህም ማለት አላህ ያዘዘውን በመታዘዝና የከለከለው በመከልከል ለአላህ መተናነስ ማለት ነው።
    ሙስሊሞችም ሆኑ ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች በጠቅላላ የእስልምናንም ሆነ የትምህርቱን ገርነት፤ሙስሊም ካልሆኑ ከሌሎች ሰዎች ጋር የሚያዘው መግባባትና መቻቻል፤ በጣም ምቹ መሆኑን ጠንቅቀው ያውቁታል፤ በተጨማሪም ሙስሊም ያልሆኑ አስተዋዮች፤አዋቂዎችና ምሁራን ይመሰክራሉ።
    የሐይማኖቶችን ታሪክ ያጠኑ ፁሑፎችን ስናመሳክር እስልምና ጠላቶቹ እየቀጠፉ እንደሚያስወሩት አንድም ቀን በአክራሪነትና በአመፀኛነት የተፈረጀበት ጊዜ እንደሌለ እናረጋግጣለን። እንዲያውም በተቃራኒው እስልምና ለሰው ልጆች ነፃነትና ስልጣኔ አጋዥ እንደሆነ ይታወቃል። እስልምና የእውቀትንና የምርምርን ችቦ የለኮሰ፤ለእውቀት ምንጭ እንዳበረከተ፤ለሰው ልጆች ነፃነት እኩልነትና ፍትህ የሚሆን አስተማማኝና ሐቀኛ የሆነ መመርያ እንዳስጨበጠ ይታወቃል።
    እስልምና ለሰው ልጆች የመዋደድን፤የወንድማማችነትንና የመቻቻልን ትልቅነት ሲያስተምር ቆይቷል። ሙስሊሞች የሌሎች ሐይማኖትን እንዳያንቋሽሹ ያዘዛቸው ሌላ ሳይሆን ቁርአን ነው፤በሌሎችም ሐይማኖት፤ ባህልና በተለያዩ ስርዓቶች ጣልቃ ሳይገቡ ተከባብሮ መኖር፤ ከኢስላም መሠረታዊ መርሆዎች (አቂዳ) አንዱ ነው።
    የቁርአንም ሆነ የነብያዊ ፈለግ መልእክት ትክክለኛውን መቻቻል ለሙስሊሞች በሰፊው ያስተምራሉ። ለዚሁም መረጃ ለዘመናት ኢስላም የስመዘገበው ታሪክ በቂ ምስክር ነው።
    የኢስላም ሐይማኖት ገር መሆኑንና ተቻችሎ መኖርን እንደሚያስተምር የሚያመላክቱ የተወሰኑ ነጥቦች በሚከተለው መልኩ ይቀርባሉ።

    የኢስላም የትእዛዙ መጠነ ልከኛነት :- (وسطية الإسلام) 1) -
    ከኢስላም ዋና ዋና መመርያዎች አንዱ ሁሉም ነገር በመጠኑ መከናወን እንዳለበት ማመን ነው ፤ አላህም የኢስላምን ሐይማኖት ልዩ ያደረገበት ነጥብ ሁሉም ነገር በመጠኑ መከናወን እንዳለበት ስለሚያዝ ነው።
    በፈጣሪ አምላካችን አላህ ብቸኛ አምላክነት እንዴት ማመን እንዳለብን፤ያለአንዳች ቅጥፈት፤ ስሜታዊነትና ነፍስን ሳያሰቃዩ አላህን እንዴት ማምለክ እንዳለብን፤እንዲያውም ሰውነትን እየጠበቁና እየተንከባከቡ፤ በፀባይም ቢሆን በጥሩ ሥነ- ምግባር በመታነፅ፤ ባጠቃላይ የኢስላም ሸሪአ በሁሉም የሕይወት ጎዳና ለሰው ልጆች አቅም በሚመጥን መልኩ ትእዛዝ ያስተላለፈ መሆኑን የመጨረሻው መልእክተኛ ነብዩ መሐመድ (ሰ አ ወ) በሰፊው አስተምረዋል።

    ፍትህ እና እኩልነት በኢስላም:- (العدل والمساواة) 2) -

    በመሠረቱ የኢስላም ሃይማኖት ከመጣበት አላማ አንዱ የሰው ልጆች ለአላህ ያላቸው ፍራቻ ካላበላለጣቸው በስተቀር በመካከላቸው ምንም ልዩነት እንደሌለ በማስመር፤ የዘረኝነትንና ጎጠኝነትን በመሰረዝ፤ የአለም ሕዝብ ሁሉም የሰው ልጆች በመሆናቸው ብቻ አንድ የሆኑና ምንም ልዩነት እንደሌላቸው ለማረጋገጥ ነው።
    የሰው ልጆች ሁሉም የአንድ አባትና እናት ልጆች በመሆናቸው በጥቁርና በቀይ መካከል የቀለም ልዩነት፤ በአዛዥና በታዛዥ፤ በሃብታምና በድሃ መካከል ሰብአዊ ልዩነት እንደሌለ እስልምና በጥብቅ ያሳስባል። እንዲያውም ሐብታም ድሃን መርዳት ግዴታው ሲሆን ያለበለዚያ የቂያማ ቀን ያስጠይቀዋል። ጠንካራው ደካማውን ካረዳና በጥንካሬው ሰበብ ምንዳ ካላገኘበት ጥንካሬው ትርጉመ ቢስ ይሆንበታል። እውቀት ያለው እውቀት የሌለውን ካላስተማረ አላህ ዘንድ ስለሚያስጠይቀው እውቀቱ ኪሳራ ይሆንበታል።
    ነብዩ መሐመድ (ሰ አ ወ) ለሙስሊሞች ይፈፅሙት የነበረው ፍትሃዊነት ታሪካቸው ይመሰክራል።
    በአንድ ወቅት ነብዩ መሐመድ (ሰ አ ወ) የሙስሊሞችን ሰራዊት ሲያሰልፉ አንድ ባልደረባቸው (ሰሃባ) ከሰልፉ ወጣ ብሎ ሲያዩት፤ በመፋቂያቸው ሆዱን ገፋ አድርገው ሰልፉን እንዲያስተካክል አዘዙት፤ በዚህን ጊዜ ሰሃባው “አንቱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ ሆዴን አሳመሙኝ ” አላቸው፤ በዚህን ጊዜ ነብዩ መሐመድ (ሰ አ ወ) ውድያውኑ ሆዳቸውን ገልፀው {ፍርድህን ውሰድ (እንዳሳመምኩህ አሳምመኝ)} አሉት፤ ሰሃባውም ከመቅስፈት ፊቱን በነብዩ (ሰ አ ወ) ሆድ ላይ ለጥፎ ፍትሃዊነታቸው ገርሞት አለቀሰ።

    መተዛዘን በኢስላም:- (الرحمة) 3) -
    ከሙስሊም ባሕሪያቶች አንዱ ልቡ በአዛኝነቱና በርኀሩኀነቱ ልዩ መሆን አለበት። ይኸውም ለደካማና ለተጎዳ በማዘን፤ ለድሃ በመራራት፤ ለተረጂ እጆቹን በመዘርጋት፤ ከጭካኔና ከወንጀል ሲርቅ ልቡ ፍፁም ቅን ሆኖ በዙርያው ላሉ ፍጡራን የሰላምና የበጎ ተግባር አፍላቂ ይሆናል።
    ሌላው ምሳሌ ለአማኙም ሆነ ለከሃዲውም፤ ለበጎ አድራጊውም ሆነ ለወንበዴው፤በዚህኛውም ሆነ በመጪው አለም፤ ፍጥረታት የሚጠቃቀሙበት የአላህ እዝነት ነው። ይህም አረሕማን (አዛኙ) ከሚለው ከታወቀው ከአላህ ሥም ጋር ተመሳሳይነት ያለው የአዛኝነት ፀባይ ሙስሊም ስለተላበሰ፤ ሙስሊም የግድ ልበ አዛኝ ሰው መሆን አለበት። በአንድ ወቅት ነብዩ (ሰ አ ወ) አዛኙ የተባለውን የአላህ ባሕርይ ትርጉሙን ለሙስሊሞች ሲያስረዱ፤ በአንድ ወቅት አንድ ሕፃን ከእናቱ ጠፍቶ ሳለ እናቱ እየተሯሯጠች ልጇን ፈልጋ እንዳገኘችው ከሆዷ ጋር ልጥፍ አድርጋ አቅፋው እያጠባችው ታለቅሳለች፤ በዚህን ጊዜ ነብዩ (ሰ አ ወ) ለሰሃባዎቻቸው “ይህችህ ሴት ልጇን ጨክና እሳት ውስጥ ትወረውረዋለችን?” አሉ፤ ሰሃባዎችም “ፈፅሞ አትወረውረውም” አሉ። መልእክተኛውም “አላህ ለባርያው ይቺህ እናት ለልጇ ከምታዝነው የበለጠ አዛኝ ነው” አሉ።

    ሰላም በኢስላም:- (السلام) 4) -
    አላህ ነብዩ መሐመድን (ሰ አ ወ) ትልቁን ሃይማኖት እስልምናን ሊያስፋፉ ሲላኩ፤ዋና አላማው ሰዎች አላህ በመረጠላቸው በሸሪዓ ሕግ ጥላ-ሥር ሆነው ሕይወታቸው፤ ክብራቸው፤ ንብረታቸው፤ ተጠብቆ በሰላምና በደሕንነት እንዲኖሩ ታቅዶ ነው። ሙስሊሞች እርስ በርስ ሲገናኙና በሰላታቸውም መጨረሻ ላይ ሰላም የሚሉት፤ ሰላም ዋና መመርያቸው በመሆኑ ነው፤ ሙስሊሞች ሰላምን ፍለጋ ያጠፋውን ይቅር በማለት፤የተሳሳተውን በመመለስ፤ ከተበዳይ ጎን በመቆም፤ በተግባርም ሆነ በቃላት ሰዎችን ሳያስቀይሙ መኖር የየእለቱ የኑሮዋቸው መመርያ ሆኖዋል።
    ታሪክ እንደሚመሰክረው በዚች በምንኖርባት ምድር እንደ እስልምና በአጭር ጊዜ ውስጥ ከሚገመተው በላይ በፍጥነት የተስፋፋ ሃይማኖት የለም። ይህም የሆነበት ዋና ምክንያት የሰው ልጆች የሚፈልጉትና ሊኖሩበት የሚመኙት ሰላም በእስልምና ውስጥ ስለሚገኝ ነው።
    ሰላም የኢስላም በታወቂያው በመሆኑ፤ አላህ በሙስሊሞች ላይ ከማንኛውም ሰው ጋር በጉርብትና፤ በንግድ ግንኙነት፤የሌሎችን ሕይወታቸውንና ክብራቸውን በመጠበቅ፤ በሰላምና በደህንነት እንዲኖሩ ግዴታ አድርጎባቸዋል።

    በጎአድራጊነት በኢስላም:- (الإحسان) 4
    በጎ ሥራ በኢስላም ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው ይኸውም መልካም ፀባይ ማሳየት፤ ቸር መሆን፤ ይቅር መባባል፤ ትሁትና ሰው አክባሪ መሆን፤ ከሰዎች ጋር መሰላም አብሮ መኖር በኢስላም ትልቅ ቦታ ይሰጠዋል።
    ኢስላማ በተለይ ወላጆችን መንከባከብ፤ ማገልገል፤ እድሜ ሲጫናቸው መርዳትና መልካም ቃላት መናገር፤ግዴታ ያደረገው ሲሆን፤ ከዚህ ውጪ ወላጆችን መበደል ማሰቃየት ወይንም ችላ ብሎ መተው፤ ጥብቅ ቅጣት እንደሚያስከትል አላህ አስጠንቅቋል። በቁርአን ውስጥ አላህን ብቻ መገዛትና ያለማሻረክን ማስጠንቀቂያ ለወላጆች ከመታዘዝ መመርያ ጋር ተቆራኝቶ ይገኛል፤ በተጨማሪም ወላጆቹን ያገለገለ ትልቅ ምንዳ ሲያገኝ ወላጆችን የበደለ ክፉ ቅጣት እንደሚጠብቀው ተገልጿል። ከበጎ ሥራዎች በተጨማሪ ሙስሊሞች ከዘመድ ጋር በመቀራረብ ሃዘናቸውንና ደስታቸውን በመካፈል፤ በቸገራቸው ጊዜ ከጎናቸው በመቆም፤ዘውትር በመጠያየቅ ዝምድናን ማጠናከር በኢስላም ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ተግባር ነው።
    ይህ ሁሉ በጎ ተግባር በኢስላም የታዘዘው በሕብረተሰቡ መሐል ትብብርና ፍቅር አብቦ አንድነት ፈጥሮ በሰላም የመኖር ዋስትና እንዲጎናፀፉ ነው።

    ባጠቃላይ መቻቻል በኢስላም በሚል ርእስ የተላለፉት መልእክት የሚጠቁሙት አንድ ትልቅ ጉዳይ አለ፤ ይኸውም አምልኮ የሚገባው ከአላህ በስተቀር ምንም አምላክ እንደሌለና; ኢስላም ከታወጀ በሁዋላ ከኢስላምም በስተቀር ፈጣሪ አላህ ዘንድ ሌላ ተቀባይነት ያለው ሃይማኖት እንደሌለ ነው።

  19. አብ
    | #19

    ሙስሊም ተቻችሎ መኖርን ነው የሚያስተምረው የትኛውም ሀይማኖት ከሌላ ሀገር ነው የገባው

  20. እግዜር ይርዳን
    | #20

    የአገራችንን ሙስሊሙን ክፍል መዝለፍ ይቁም!!! ማንነታችሁም እንዲጋለጥ ሕጋው እርምጃ እንደሚወሰድ ለአንዴም አትዘንጉ
    የኦርቶዶክስ ክርስቲያኑን መሬት የሚያስነጥቀው ክርስትያኑ ልጅ የሆነው ወያኔ ነው
    በዓለም ላይ ከፍተኛው ጦር መሳሪያ አምራቹ ክርስትያኑ ነው ይህ ማለት ክርስትያኑ ሁሉ ጦረኛ ነው ማለት አይደለም
    ዓረቦች አገርም ከፍተኛው ጦር የሰፈር ያላቸው ክርስቲያኖች ናቸው
    በዓለም ላይ ኢኮኖሚክ ቀውስ እየፈጠሩ ያሉት የክርስትያን አገር ባንኪች ናቸው ይህ ማለት እስላሙ አገሮች ባንኮች ነጻ ናቸው ማለት አይደለም
    ስለዚህ ፖለቲካ ቀውሱም ሆነ ኢኮኖሚክ ቀውሱን ከዘርና ከሃይማኖት ውጭ ማየት ግዴታ አለብን
    ማንም ዘር ሆነ ሃይማኖት ከሌላው በልጦ በጥፋቱ ተጠያቂ ሆኖ እንዲታይ ለማድረግ መሞከር የለብንም
    ፓለቲካ ወንጀልና የአንድ ሰው ዘሩ ወይም ሃማኖቱ ምንም ግንኙነት የላቸውም

    አቡጊዳ በሙስሊሙ ወጎናችን ላይ ይህን ስድብና መስረት የሌላቸውን ወሬዎች ማስቆም ግዴታ አለበት

  21. በሺር
    | #21

    @tofik
    Tofik
    You have got every thing wrong, one thing is good about you, you are willing to read. But you need to read why things are said and written as well.

    If you really know the truth about the so called, and the falsely fabricated conversions of famous people to Islam, you will be ashamed of your religion, I mean if you are a Muslim.

    Any way please visit the following link, http://www.answering-islam.org/amargna/quranandscience/hoaxes_neil.html
    and please read about Neil Armstrong.

    And you also mentioned about Negashi, don’t you know how falsely fabricated legend and story it is? You don’t need to fabricate stories to make your case!
    As for me the point Jafar made is true and we must all think about it.

    You don’t need to be Muslim to be doctor or a scientist, but being a Muslim is a great hindrance for personal intellectual as well as national development. Think about it don’t believe false ideas fabricated to promote false ideology.

  22. yezid
    | #22

    please my dear muslim &peace loving chrstian brotheres ignore this abnormal person & his article.on his fake name before a year he was sprayng woyanizem poison,to divide us.he like or no all Ethiopians will live together.muslims,chrstians…

  23. አቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ-ወመንፈሳዊ
    | #23

    መቼም የገፅታ-መረብ(ፌስ-ቡክ)ጓደኛ የቅርብ አይደለምና ቅንነት ደግ ቢሆንም ተላላነት ወደ አልተጠበቀ አቅጣጫ ይወስዳልና አንገትን ዞር አድርጎ በማየት መጠንቀቁ ተገቢ ነው::
    የዚህ ፅሁፍ መነሻዬም ከወዳጅህ እዮብ ብርሃነ የተላከልህ አሳዛኝ ሁኔታ የሁላችንም ጉዳይ ቢሆንም ወደአንተ የተላከበት በቂ ምክንያት አልታየኝም:-ውጤቱም በአንፃራዊነት እንደሚነበበው የብዕር ሙያህን ከጥራቱም ሆነ ከውበቱ ተፈታትኖታል::
    የእህታችን ጉዳይ እጅግ አሳዛኝና ምክንያቱ እና ሰበቡ ተለይቶ ያልታየበት ፍትሕ የሌለው ቢሆንም ስንቶቹ ውስጥ ውስጡን የሚታረዱትን ቤቱ ይቁጠረው::
    በመጨረሻም መቼ ነው የሚቆመው ለሚለው አንድ በኦሮምኛ የሚነገር ምሳሌ ልበልህና ላብቃ:-ውሃን የማያውቅ ሰው ውሃ አጠገብ ቆሞ ውሃ ይጠማዋል ይባላል::ለዚህ መራራ ግፍ ማብቂያው መራራ ትግል ብቻ ነው:-ምክንያቱም የእህቶቻችንን እና የሁሉንም ኢትዮጵያውያንን ደም እየጠጣ በሥልጣን ላይ የተሸነቀረው ጉጅሌ ካልተወገደ ምንም መፍትሄ አይኖርምና ይህንን በጥልቀት እንደምታውቅ ማሳወቅ ይኖርብሃል::አንተም ራስህ ከእንግዲህ አገር የሌለህ ድንገተኛ መጥፎ ነገር ቢመጣ መኩሪያም ሆነ መከታ የለህምና እያወቅከው ያልተገነዘብከው ከሆነ ተላላነት ይዞ ትግል የለምና ብርታቱን ይስጥህ::

  24. Anonymous
    | #24

    kemal :
    ሁለቱም ማለትም የሃይማኖት ፖለቲካም የጎሳ ፖለቲካም /በወያኔ እንደታየው/ ለሃጋራችን ጸር ከመሆናቸውም በላይ በአፋጣኝ መፍትሄ
    ካልተበጀለት ኢትዮጲያችን ለማንኛችንም እንደማትሆን ማወቅ መቻል አለብን!

  25. በሺር
    | #25

    @yezid
    Dear Yezid,
    I think you should be reasonable to what you say, Jafar’s article is a warning to all Ethiopians. You might love peace but there is no peace in political Islam! I think you know this, but we Ethiopians want to live in peace we don’t want Secular Dictators as Woyane as well us Religious murderers as Muslim extremists. They don’t have any regard and respect for human life.
    You say Jafar is going to divide us, why do you say that, you hate him because he told you what is your true agenda. You cry out now peace and unity! We all know it is untrue and only done to disguise poor Ethiopians. You know what you plan, and what is your hidden agenda for Ethiopia, you are instrument of Saudi’s and other Arab countries, you are not true Ethipian, simply your agenda it is to kill poor Ethiopian men and make their ladies salves as your founder did and preached.
    Ethiopians could only unite when they disregard what they divide them, Islam never been a peace bringing religion any where in the World, go and study history.

  26. በሺር
    | #26

    @ታዛቢው
    ለአቶ ጃፋር ሃሰን ጽሑፍ ምላሽ እንዲሆን ያረብከውን ጽሑፍ አሁን ነው ያየሁት፡፡ አስተያየት ሳይሰጥህ አስተያየት መስጫው ባለመዘጋቱ ተደስቻለሁ፡፡ ከአጠቃላይ ገለፃህ ባሻገር ስለ እስልምና መልካምነት በስድስት ነጥቦች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተሃል፡፡ እስልምና አንተ እንዳስቀመጥከው ቢሆን ኖሮ በጣም መልካም ነበር፡፡ እኔም እራሴ እንዲሁም እንደነ አቶ ጃፋር የተከበሩ ሰዎችም እምነቱን ጥለውት አይወጡም ነበር፡፡
    አልሰማህም መሰለኝ እንጂ እጅግ ብዙ ሚሊየን ሰዎች በየዕለቱ እምነቱን እየጣሉት ይወጣሉ፣ ሰዎችን በእስልምና ውስጥ ያስቀመጣቸው አንዱና ብቸኛው ነገር ፍርሃት እንደሆነ ይግባህ፡፡ ሰዎች እምነቱን ጥለው የማይወጡት ተደስተውበት እና ተስማምቷቸው ሳይሆን፣ እውነትም ስለ ሆነ ሳይሆን ጥለው ከወጡ ስለምትገድሏቸው ብቻ ነው፡፡ ስለዚህም ሰዎችን በፍርሃት አስሮ የያዘ እምነት ነው ቢባል ስህተት አይሆንም፣ ይህንንም አንተም ታውቀዋለህ፡፡ አንድ ምሳሌ ልስጥህ በእንግሊዝ አገር በሰሙኑ የቢቢሲ ዜና ዋና ትኩረት የ19 ዓመት ልጃቸውን ሻፊሊያ አህመድን በገዛ እጃቸው ስለገደሉ የሙስሊም እናትና አባት ጉዳይ ነው፡፡ ይህ የ’honour killing’ የክብር ግድያ ማለትም የገዛ ልጅን መግደል አሰቃቂና ኢ-ሰብዓዊ ዜና በዓለም ላይ የሚታወቀው በእስልምና ተከታዮች ውስጥ ብቻ ነው፡፡ በሌላ በየትኛውም እምነት ውስጥ እንዲህ ዓይነት ጭከና በፍፁም ተሰምቶ አይታወቅም፡፡
    አንተ ግን እስልምናን የመላእክት እምነት አድርገህ አቅርበኸዋል፣ አሁንም ደግሜ ልበለውና አንተ እንዳልከው ቢኖን እንዴት ጥሩ ነበር! ዉ ዉ ዉ ነገር ግን እውነት አይደለም፡፡ ለመሆኑ በየትኛው የእስላም አገር ውስጥ ነው ሰላም ያለው? ሰላም ላለመኖሩ የችግሩ ምንጭ ምንድነው፣ ለምን ሙስሊሞች በሰላም ከሰው ልጅ ሁሉ ጋር ተቻችለው አይኖሩም? አንተ የመቻቻል እምነት ነው ብለሃል ስለምን ሺያዎች ከሱኒዎች ጋር ይፋጃሉ፣ ስለምን ሰላፊስቶችና ዋሃቢስቶች እርስ በእርስ ይተራረዳሉ?
    እስልምና የተቻችሎ እምነት ነው ብለሃል፣ ቢሆን ኖሮ ጥሩ ነበር ነገር ግን አይደለም፤ ሳወዲ አረቢያ ውስጥ በቤታቸው ሲፀልዩ የተያዙት እና እስካሁን በእስር ላይ የሚማቅቁት ኢትዮጵያውያን ስለምንድነው? የሳውዲ አረቢያው እስላማዊ መንግስት እንዳንተ ያለ አስተማሪ ስለሌላቸው ይሆን?
    እስልምና ለድሃ የሚያስብ ነው ብለሃል፣ በድህነታቸው በባዕድ የእስላም አገር ስራ ሰርተው በአገር ቤት ያሉትን ቤተሰቦቻቸውን ለመርዳት የሄዱትና በቤይሩት በሳውዲ አረቢያ፣ በሊባኖን እየታረዱ የሚመጡት፣ ግፉ በዝቶባቸው እራሳቸውን የሚገድሉት ስንት ድሃዎች ናቸው? በአንተ ደግእስላሞች የሚታረዱት! ይህ የሚሆነው አንተ የምትለውን የመላእክት እምነት ስላልሰሙት ይሆን!
    እኛ ግን ይህንን ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ለማምጣት የማንፈልገው፡፡
    የጠቀስካቸውን ስድስት የእስላማዊ ነጥቦች ውስጥ አንዱንም እንኳን በቁርአን ጥቅስ አላስደገፍክም፡፡ ብታስደግፋቸው ኖሮ ለአንባቢው ጥሩ ነበር፡፡ ነገር ግን ከጠቀስካቸው ውስጥ አንዳቸውም በእስልምና ታሪክ እና እንቅስቃሴ ውስጥ አልታዩም፣ ታይተዋል ካልክ አሁንም ማገናዘቢያ መስጠት ይኖርብሃል፡፡ ቁርአንን አታነብም ይሆናል እንጂ ቁርአን የተሞላው ግደሏቸው፣ ንፁሃንን ሁሉ ሸምቃችሁ ግደሏቸው፣ በመንገድ ላይ ጠብቋቸውና ግደሏቸው በማለት አይደለምን?
    ከሌሎች የእምነት ተከታዮች ጋር ጓደኞች አትሆኑ ከሆናችሁ ቅጣት ይጠብቃችኃል፣ ወ.ዘተ የሚሉትን እየዘለልክ ነው እንዴ የምታነባቸው እስልምና መቻቻል ቀርቶ ያለምንም ምክንያት ሌላውን ሰው ስለማጥቃት አይደለምን የሚናገረው? በዚህ በኩል እስልምና የሰው ዘር ጠላት ተብሎ ሊቆጠር አይገባውምን? እንግዲህ የምናየው ይህንን ነው አንተ የምታወራው በዓለም ላይ ስለሌለው እስልምና ከሆነ ንገረንና በሌላ በአዲስ ቁርአን ወይንም ሌላ መጽሐፍ ስም ሲመጣ እንቀበለው ይሆናል፡፡
    ቁርአንንም ከሰማይ የወረደ ነው የአምላክ ቃል ነው የሚባለውንም ተረት አቅርበኸዋል፣ ቀጥለህም ሌሎች የአምላክ መጽሐፍት ሲለወጡ ቁርአን ምንም እንዳልተለወጠ ጠቀስ አድርገሃል፣ ከዚህም በፊት እንዳልኩት እውነት ቢሆኖ ኖሮ ጥሩ ነበር፡፡ እኔን የሚገርመኝ አንተ ለራስህ እምነት በጣም – እሩቅ – መሆንህ ነው፡፡ ያንተ እምነት ማለትም የምትለው በእምነትህ እውነታ ላይ የተመሰረተ ሳይሆን – በስማ በለው – ላይ ነው፡፡ ስለ ራስህ እምነት ብዙ ስለማታውቅ ስለ ቁርአን አመጣጥ አንብቤ የጠቀመኝንና ወደ አማርኛ የተተረጎመውን እንድታነብ ልጠቁምህ ትምህርት ለመቅሰም አዕምሮህን ከፍት አድርገህ አንብበው ትጠቀማለህ፡፡ ጽሑፉንም በሚከተለው http://www.answering-islam.org/amargna/books/tisdall_sources.htm ሊንክ ውስጥ ታገኘዋለህ፡፡
    አቶ ታዛቢው ያቀረብካቸው ስድስቱም ነጥቦችህ ምንም ፍሬ የሌላቸው መሰረትም ላይ ያልተመሰረቱ “የህልም እንጀራዎች” ናቸው አንተም ብዙዎች ጓደኞችህና የእምነቱ ተከታዮች ሁሉ የተታለሉባቸው “ስማ በለዎች” ናቸው፡፡
    በማጠቃለያህም ላይ የእስልምናን ምንነት ጠቁመኻል፣ እስልምና ከታወጀ በኋላ ሌላ እምነት በዓለም ላይ ሊኖር እንደማይችል ስተገልፅ “መቻቻል” እንደገና “መቻቻል” የእስልምና መሰረት ነው የሚለውን እራስህ እውነቱን በመግለጥ እራስህ ንደኸዋል፡፡
    እኔ ግን ይህን አጋጣሚ ተጠቅሜ ለማጠቃለል የምፈለገው ጃፋር እንዳለው የእስልምና ሃይማኖት ፓለቲካ ከጠቃሚነቱ ይልቅ ጎጂነቱ፣ እንዲያውም የሰው ዘር ጠላትነቱ በጣም ያመዘነ መሆኑን ነው ስለዚህም እንደ ዘር ፖለቲካው ሁሉ ለኢትዮጵያችን አስፈላጊ አይደለም፣ እኛ አንፈልገውም እኛ ኢትዮጵያውያን ከሃይማኖት ፖለቲካ ውጭ አብረን መኖር አለብን አገሪቱ ትበቃናለች፣ መርሆአችን መሆን ያለበት “ሃይማኖት የግል አገር የጋራ ነው” የሚለው ነው፡፡

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።