ገላው ልጅ ወለደ በእንግዳ ታደሰ
ጀግና አምጣ ጀግና ወልዳ አቁማለች፣
እናት ምድር ልጅ ለመውለድ አርጣለች፣
አርባ ዓመታት አልፏት መክና ተክዛለች፣
ብለን አዝነን ቱቢት ለብሰን ባዘንበት፣
ጀግና ወጣ ! ዘራፍ ብሎ ! ከኢሳት ቤት፡፡
የኛ ! ቧዚዝ! የኛ ጀግና ! የቴዎድሮስ ልጅ፣
ጃሎ ! ብሎ በአዳራሹ አዋጅ ቢያውጅ፣
የት ይደበቅ ? የት ይሸገግ የሹምባሽ ልጅ ?
አይኑ ብልጥጥ ! ፊቱ ድንግጥ ፣
እስኪመስል ያችን ድንቢጥ ፣
አሸበረው የገላው ልጅ ያንን አይጥ፡፡
እንግዳ ታደሰ / ኦስሎ ኖርዌይ – ለጀግናው አበበ ገላው መታሰቢያ ትሁንልኝ ፡፡



May almighty God bless ABEBE GELAWU? Yes ofcourse why not; I am overwhelmed with your courage to expose this pathetic lair in front of the deligates from the entire world. Abebe Gelawu and others like Tamaggne, Dr Birhanu Nega, Prof Al Mariam, Dr Nuru Dedefo and others are heroes of our generation. Am proud of you guys. This is a wake up call to replicate such a courage by the youths.
ይህ እንቅስቃሴ በመላው ኢትዮጵያም በተለያዪ ቦታወችም መጀመር ያስፈለጋል አሁን ግዚው በአንድነት ሆነን ይህንን ሰጋ ለበስ አጋንንት ሰው በላ የወያኔ ሥራት ለአንዴና ለመጬረሻ ማስወገድ ይኖርብናል ኢትዪጵያን እግዚአብሔር ያድናት ከዚህ በሁአላ ሺ አበበ ተፈጥሮአል በጎንደር በጋአምቤላ በተለያዮ የሃገሪቱ ክፍልም እንቅስቃሴወችን እየሰማን ንው ይህ ሁሉ የተመዘገበው ውጤት በአንድነት በመቆምችን ነው;;
አቶ መለስ ዋሽግተን ባይመጡ ይሻልቸው ነበር በ21 አመታችው በአለቆቻቸው ፈት ነብር አያቸው አልልልልልልልልልል ብያለው በትናትናው ቀን ለተወለድው ጀግና አልልልልልልልልል
ወንድ ልጅ ተወልዶ ካልተባለ አጅሬ
ልቀቁት ክሜዳ ሳር ይብላ እንደበሬ::
እንዲህ ነው ጀግንነት አበበ ገላው የኢትዮጵያ ጀግና እናት ወለደች አንተን
እስቲ አሁን እንኳን ፍርሃታችን ይልቀቀን ጎበዝ
በዚያ ባዳራሽ ውስጥ የኛይቱን ጦጢትን ድፍረትዋን አየነው
መግቢያ መውጫ አጥታ አይንዋ ሲጉረጠረጥ ለሃጭዋን ስትዘራው
እንዲያ የምታገሳው ወራዳ ምናምን ስትል ምትፎክረው
ለካስ አጋአዚዋን ጨፍጫፊ ማሽንዋን በርግጥ ተማምና ነው
ባዶ እጅዋን ብትገኝ በነጮቹ ሃገር በነጮች ከተማ
የጀግና ድምጽ ሰምታ ምንም ሳታቅማማ
ድፍት አደረገች ቅሌታም አንገትዋን
በሱሪዋ ላይም ለቀቀችው ሽንትዋን
ልትለው ያሰበችው ንግግርዋ ሁሉ
ምላስዋ ቢታሰር ቢጠፋባት ውሉ
ሄደች ወደሆቴል በንዴት በቁጭት
ቁጭ ብላ አደረች ህይወትዋ አሳስባት
ፈሪ ሰው መሆንዋን ትናንት አወቀዋለች
በፍርሃትም ብርክ ነፍስዋ ርዳለች
ሰማንያ ሚሊዮን የናቀችው ጦጣ
የምትይዘው ጠፋት በአንድ ጀግና ቁጣ
በውጭ ያለው እንቅስቃሰ በሀገር ውስጥም እንዲቀጥል በጋራ እንስራ
አዎ እንደዚያ ነው ተባረክ:: እኛስ ምን እያደረግን ነው?
የዚህ ድረ ግጽ አዘጋጃች ስላም ለአናንተ ይሁን ለመሆኑ ስንት ቀን ይፈጃል አስተያቶችን ሳንሱር አድርጋቹ ለመለጠፍ, ይህንን ልጠይቃቹው የተገደድኩትም አስተያየት በጻፍ ቁጥር ለ3 ቀን አና ከዚያም በላይ ሲቀመጥ ስለማይ ነው ከወያኔ አና ከሻቢያ የሚመጡትን ጽሁፍች ለመለየት ይህንን ያህል ቀን ይወሳዳል ባንጻሩም ደግሞ የምትፈልጉት አስተያየት ባአፍጣኝ ስትለጥፉት ተመልክቻለው አስራራችሁን ግልጽ አድርጉት ሁሉንም በአኩል ለማየት ሞክሩ አመሰግናለው
Awe and shock to the fascist and racist Meles Zenawi. Journalist Abebe Gellaw is a hero to be celerbrated by Ethiopians. The fascist Meles Zenawi pissed and shit in his pants.
በመጀመሪያ በኢሳት ዜና አበበ „መለስ ነፍሰ ገዳይ ነዉ“ ማለቱና
በፀጥታ ሀ ይሎች ታጅቦ መዉጣቱን ሳነብ „የፀጥታ ህይሎች ለምን
አስወጡት?“ ከሚለዉ ጥዬቄ ጋር ብቻ ስሙዋገት ነበር ሲሳይ አገና
አበበን ቃለምልስ ይዞ የቀረበዉ::
የኢትዮጰያ መወያያዎች መድረክ ቀድሞ የአበበን ቢዲዮ ለመለጠፍ
በመቻሉ የተናገረዉን የጀግና ድምፅ ስቃጭል አደመጥኩ!
ጀግናም ከሀዲም ለመዉለድ ያለመከነች አገር እንደ ትላንቱ ዛሬም
በጅንጉርጉር ሆድዋ ጀግናም ከሀዲም መዉለድዋን መፈላሰፍ ሰለቸኝ!
ወደር የሌለዉ ብልሃትና ጀግንነት!
ዘራይ ደረስ የአገሩን የሽለላ ትዓትር እንዲያሳይ ነበር የሮም ሜዳ
የታጨዉ:: ግለያዲያቶሬዎችን ደጋግማ ያስተናገደቸዉ ሮም
ኢትዮጲያዊዉን ዘራይደረስ በተራ አላስተናገደችም::
በወስጡ ማዕበል ያረገዘዉን ኢትዮጰያዊዉን አቤ የዘመናችንን ዓለም
ለማንቀጥቀጥ የታደሉቱ ነገስታት ንቀዉ የሚያልፉት አልሆነም::
ድምጾቹ ማዕበል መቀመር ይችላሉ::
በዘያ አዳራሽ የአንድ ታመኝን ድምፅ ያረገዘ የአቤን ድምፅ መቀበል
የሚችል መገኝት ቢችል ኖሮ ዓለምን የሚያንቀጠቅጡት ስንቀጠቀጡ
ማዬት እንችል ነበር::
በገዛ አዳራሻቸዉ የዉሻቸዉን በህሪ: የመናከስና የገዛ እናቱን ማዕጸን
ለመብላት ነዉር የማያዉቀዉን ቡችላ እፍታቸዉ እንዲያቀረቅር አደረገዉ::
እንኩዋን ከአደራሽ ማስወጣት እንኩዋን ማሰር መግደልም ይችላሉ::
ዲረጊቱን ግን መግደል አይችሉም::
ለእስክንድር: ለርዕዮትና ለአነዱዓለም ከተመንበረከክንበት ሳንነሳ
ከዓለማችንን ማዕዘናት አዳደስ እስክንድችሮች አዳድስ የኔ ሰዎች
ችቦ እየተንቦገቦገ ነዉ::
አላሁ አክበር ከዋልደባ: እግዚዓብሄር የተከበረወ ነዉ የሚለዉ ድመፅ
ማስተጋባት እየቻለ ነዉ::
የኢትዮጰያ ጋዜጠኞች በዚህ ታርካዊ ወቅት የግንባር ሥጋ ሆነዉ
ለከፈሉት መስዋዕትነት: በመክፍል ላይ ላሉትና ለሚከፍሉት መሰዋዕትነት
ታርክ ትልቅ ቦታ ትሰጣቸዋለች::
ኢትዮጰያዊያን ሴቶችና ኢትዮጲያዊያን ጋዜጠኞች ፉሺስታዊዉን
የመለስ አገዘዛ የተጋፈጡትን ጠብታ ሌሎች መጋራት ቢችሉ ምን
ያክል ሁነታዎችን መቀየር በተቻለ!
ገና ያቀረቅራል ጨዋታ ስጀመር
ጨዋታዉ የሰሜን የጋዳፊ ጀምበር
መጥለቅ እንጂ መዉጣትዋ የማያምር
በቤናሊ ታጅባ በሞባረካማ የሚትከር
ወንዱን አፋላልገሽዉ አንቺም ከመቅደላ
በወንዶች አገር ነዪ እንጫወት ከጋምቤላ
ወርቅ እያቀለጥን በጉረፈርዳዉን ካዶላ
የደሰዋ ልጅ ዲሲ ወንድ ወልደሽ
ትልቁን የኦባማ አፍ አዘግተሽ
ያለ ነፃነት በመኖ እነዳይሳለቅብሽ
የጎጀብም የሸታ የጣና ዋናተኛ ሆነሽ
በደቻቱን መቀነት ባሮዉምን ዙሬሽ
ካባ ጂፋሩን መንደር ቡናን እያፈላሽ
ከዋልድባዉ ገዳም አላሁ አክበር ብለሽ
እልልታሽንም ያሰማኛል መለስን ሰቅለሽ
ኣበበ ትሩ ምሳሊ ነው የሆንከን ሁላችሂንም መነሳት አለብን እሂን ሰይታን ከፋፋይ ገነ እርካኑን እናስከረዋለን አንተ ቲዎድሮስ ነህ…..
aba teru menkakate fetrhelenale enamesegenehalen
ጀግና እንደዚህ ከረከሰ የኢትዮጵያ እናት ገና መካን ናት ማለት ነው:: አበበን ማንኳሰሴ እንዳልሆነ ይታወቅልኝ:: ነገር ግን የጀግንነት መስፈርት እየወረደ እንደሆነ ይሰማኛል:: እነ አብዲሳ አጋን: በላይ ዘለቀን: ዘርዓይ ደረስን: አቡነ ጴጥሮስን: ባልቻ አባ ነፍሶን: አሉላ አባ ነጋን: መይሳው ካሳን ወዘተርፈ የመሳሰሉ እጹብ ድንቅ ጀግኖችን ያበቀለች ሀገር አንድ መጻጉዕ ወያኔን ዴሞክራሲ በሰፈነበት ሀገር አምባ ገነን ነህ ብሎ መናገር እንደ ጀብድ ከተቆጠረ እውነትም ወርደናል ማለት ነው:: ምን ይደረግ? ልዩ ጥበቃ የሚደረግላቸውን አረመኔወቹን መንግስቱ ሀይለማርያምንና መላኩ ተፈራን በጠራራ ጸሀይ በጨበጣ የገጠሟቸውን አንድ ፍሬ ህጻናት እንኳን የጀግንነት ስም ሳንሰጣቸው በመቅረጸ ድምጽ መብቱ ተከብሮ አምስት አረፍተነገሮችን በመደርደሩ ጀግና ብለን የምንመጻደቅ ከሆነ የጀግንነት ትርጉሙ አልገባንም ማለት ነው:: የመትረየስ እሩምታ ፊቱ ላይ እየተርከፈከፈ ምሽግ ሰብሮ የሚገባው በሚሊዮን የሚቆጠረው ኢትዮጵያዊ ጀግናስ ምን ስም ልንሰጠው ነው? አረ ጎበዝ የጀግናን ስም ቀማኞች እየሆንን ነው እኮ! አበበ ገላው የሚጠበቅበትን ኢትዮጵያዊ ግዴታውን በሚገባ ተወጥቷል:: አጋጣሚውን ተጠቅሞ ለመለስ የሚጎመዝዘውን ስም ሰጥቶታል:: ይሁን እንጅ በምንም መለኪያ ለጀግንነት የሚያበቃ ነገር አይደለም ሊሆንም አይችልም:: አባይን ላላወቀ ምንጩ ሁሉ አባይ ቢመስለው አያስደንቅም:: ይሁንና በባህላችን ጀግና በፈረንጆቹ “ሂሮ” የሚባለው ስም እንደፈለግነው እየቆነጠርን የምናድለው ገጸ በረከት አይደለም:: የጀግንነት ትርጉም በዘመናት በጣም አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ሰብዕናቸው በሞትና በህይዎት አጣብቂኝ ላይ ሆና እያለ ከተጋረጠባቸው ሞት ይልቅ የቆሙለት መርህ ክብደቱ ተሰምቷቸው በሞት ወረዳ ውስጥ ልዩ (extraordinary) የሆነ ተግባር ላይ ሲሰማሩ ይህ ስራቸውም መየትኛውም ፍጡር የማይሞከር ቢሞከርም በክፍለዘመን አንዴ የሚፈጸም አይነት ሲሆን ‘ጀግና’ የሚለውን ልዩ ክብር ይቀዳጃሉ:: አበበ በዚህ ሁኔታ ላይ ነበር? መልሱን ከናንተ…