ታዋቂው ጋዜጠኛ ንጉሴ ጋማ አረፈ – ኢሳት
ኢሳት ዜና:- ጋዜጠኛ ንጉሴ ጋማ በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን በጋዜጠኝነት ያገለግሉ ነበሩ:: በደረሰባቸው ድንገተኛ ህመም ለጥቂት ጊዜ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ግንቦት 16 ቀን 2004 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል::
ጋዜጠኛ ጋዜጠኛ ንጉሴ ጋማ ባለትዳርና የ4 ልጆ ች አባት እንዲሁም የሁለት ልጆች አያት ነበሩ::
በጋዜጠኛ ንጉሤ ጋማ የህይወት ታሪክ ዙሪያ የተዘጋጀ ዘጋቢ ፊልም በቅርቡ ይዘን እንቀርባለን።
በዚህ አጋጣሚ ለጋዜጠኛ ንጉሴ ጋማ ቤተሰቦች፣ዘመድ አዝማዶች ጓዸኞች፣ የሥራ ባልደረቦች እና ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት በአገራችን እንዲረጋገጥ ያለመታከት በጽናት ሢሰራ የቆየው የነፃነቱ ዘብ ንጉሴ ጋማ በማረፉ ሀዘን ለተሰማችሁ በሙሉ፤ የኢሳት ዝግጅት ክፍል መጽናናት እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞቱን ይገልፃል።



በጣም አሳዛኝ ድንገተኛ ዜና…ይቺ ዓለም ኢትዮጵያ የቅን ሀሳቢ,ታታሪ,ተሟጋች,ዕድገት ሰላምና ብልፅግናዋን የሚሹ ልጆቿ ከቀዬአችው ወጥተው ሲባክኑ, ሲያዝኑ, ሲደክሙ,በአቅማቸው የተቻላቸውንም እያደረጉ የልፋታቸውን ውጤት እና ግብ ካሰቡበት ሳይደርስ እንዲሁ በእንጥልጥል እንዳለ ቀድመው ማለፋቸው በጣም ያሳዝናል::ሆኖም አኩሪ ሥራቸው በሥራ ባልደረቦቻቸው በትግል አጋሮቻቸው በቤተሰቦቻቸው በጓድኞቻቸው እና ሥራቸውን በተመለከቱ ኢትዮጵያውያን ልብ እና አዕምሮ ሁሉ ዘላለም ተቀርፆ ይኖራል::ተተኪውም ትውልድ አርዓያነታቸውን ተከትሎ ወደፊት መቀጠል አለበት::
ለባለቤታቸው ለልጆቻቸው ለልጅ ልጆቻቸው እንዲሁም ኢትዮጵያን ለሚወዱ ሁሉ እግዝሐብሔር ያበርታችሁ !!!!
የወንድማችንን የክቡር ንጉሴ ጋማን ነፍስ ይማር ጌታ በቀኙ ያኑርልን የሐዘንም መጨረሻ ያድርግልን::አሜን!
*******************************************
ጽፏል አንብበናል ጠየቀም ተረዳን
ዘገበ አቀረበ ሁሉንም አሳየን
ተናገሩ ጠይቁ መብታችሁ ነው አለን
ተረከልን አንድነት እኩልነት ነጻነትን
ምነው ዛሬ ዝም አለ ድምፁ አልተሰማ?
ደከመው አረፈ አሉ ያ.. ንጉሴ ጋማ ::
**********************
ከሀገረ ካናዳ~~~~~~
We will miss our dear country man and brave journalist Neggusie Gamma. His contribution to ESAT and to the freedom movement has been so inspiring and an encouragement to many Ethiopians.
My condolensences to his family.
God bless his soul
I am deeply so sad with this bad news. I have known Neguse Gamma since 2007. He is a man with a head and dedicated himself for the betterment of his nation in his level best.
Let his soul rest in peace.
R.I.P
ነፍስ ይማር! ለወገን ለህገር የሚያስቡ: እጅግ ጥሩ ኢትዮጵያዊ ነበሩ::
I remember him , he was very experienced journalist , all the time i’m watching his program and i’m never ever forgetting him .
we lost our HERO.
በጋዜጠኝ ንጉሴ ጋማ ህልፈት የተስማኝን ልባዌ ሃዘኔን እየገለጽኩ
ለቤተስቡ ጽናትን እየተመኝሁ : ስላማዊ ሥራዎቹና የሃገር ተቆርቋሪነቱ
ለዘለዓለም ከኛ ጋር ይኖራሉ !
ክቤልጄም
በዉድ ጋሼ ንጉሴ ጋማ ድንገተኛ እረፍት የተሰማን ሃዘን እጅግ በጣም መሪር ነዉ::
ከወራት በፊት በቤልጄም ከሚኖረዉ ኢትዮጵያዊ ጀግና የጀግና ልጅ ሁሴን ጋራ የመጀመሪያ ቃለ መጠይቅ አቅርቦልን ሁለተኛዉን ቀጣይ ዝግጅትም እንደሚያቀርብ ተስፋ ስጥቶን ለመስማት በታላቅ ጉጉት ስንጠባበቀዉ ድንገት በሞት በመለየቱ የተሰማን ሃዘን ከፍተኛ ነዉ::
እግዚአብሔር ነፍሱን ይማርልን::
ለመላዉ ቤተሰብና ቤተ ዘመድ መጽናናትንና ብርታትን እንመኛለን::
እነ
ደርብ ቀጀላ
ገለበዉ ሰንጎጎ
አልማዝ ባልቻ
በጋዜተኛ ንጉሴ ጋማ ከዚህ አለም በመለየታቸው የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን ስገልጽ እንዲሁም ለቤተሰኦቻቸው ለስራና ለቅርብ ጓደኞቻቸው በሙሉ እንዲሁም ለአድማጮቻቸው እግዚአብሀር መጽናናት እንዲያድላቸው:ነብስ ይማር መንግስተሰማይ ያዋርሳቸው
Mahlet bekay