ያለ ጨረታ ! ለነ ሌንጮ ለታ ? እንግዳ/ ከኦስሎ
’’የመለስና የሌንጮ የመግባባትና የስምምነታቸው መሰረት ከቶ ምን ሊሆን ይችላል? የድርድራቸው ማእከልና ያግባባቸው የጋራ ፍላጎት ምንድነው? አልገባኝም። መረጃም የለኝም። ማለት የሚቻል ነገር ግን ይኖራል። ሌንጮና ዲማ የዋህ ፖለቲከኞች አይደሉም። ’’የአበሻን ተንኮል አሳምረው የሚረዱ ናቸው ’’። ያግባባቸው አንድ የጋራ የሆነ ማእከላዊ ነጥብ ግን የግድ ይኖራል። ’’ተስፋዬ ገ/ አብ
መቸም ! ተስፋየ በጥሩ ብዕሩ እያዋዛ በሚለቃቸው መጣጥፎቹ ውስጥ በየመስመሮቹ መሃል ወሸቅ የሚያደርጋቸው አፋጀሽኝ ቃላቶቹ አሁንም አልለቀቁትም ፡፡ ’’ ያደቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም ’’ ሆነና አድባር ስትከፍትለ’ት በሚለቃቸው መጣጥፎቹ መስመሮች ውስጥ – በአብዛኛው በአማራና – ኦሮሞ ህዝብ ውስጥ ንትርክ እንዲቀጥል ሲፈልግ ፣ ዛሬ ደግሞ ሴሜቲኮችና ኩሺትኮች በሚላቸው ኢትዮጵያውያን መሃል ሽኩቻው እንዳያባራ – የአበሻን – ተንኮል አሳምረው ሌንጮና ዲማ ያውቁታል በሚል ጥርጣሬው እንዲጠጥር በር ይከፍታል፡፡ ይህች አንጓ አስታራቂ ናት ወይስ ቀጣይ ጥርጣሬን ጫሪ ? ደራሲ ተስፋዬ ?
ካልተሳሳትኩ ተስፋዬ በአንድ ጽሁፉ ላይ ከኦቦ ሌንጮ ለታ ጋር ጥብቅ የሆነ ወዳጅነት እንደነበረው ፣ ኔዘርላንድ በአንድ ወቅት አብረው እንደከረሙና ፣ በቀጣይነትም ኦቦ ሌንጮ ከሚገኙበት ስካንዲኔቪያዋ አገር ኦስሎ መጥቶ እንደሚጎበኛቸው በጽሁፉ አስነብቦን ነበር ፡፡ ይህ የሚያሳየው የወዳጅነታቸውን ጥብቅ ትሥሥር ሲሆን ፣ የቤተ መንግሥቷን ሹክሹክታ እንዳለ ሙሉ በሙሉ ባይነግሩትም በገደምዳሜ ግን ቅርፊት ቅርፊቷን እንዴት እንዳልነገሩት አልገባኝም፡፡ የድርድራቸው ማዕከልና ያግባባቸው የጋራ ፍላጎት ምንድነው ? አልገባኝም ፡፡ መረጃም የለኝም ላልከው ግርታ ለፈጠረብህ ድርድር ፣ ቅርበት አለኝ እስካልከን ድረስ ኦስሎና አምስተርዳም ፍላጎቱ እስካለኽ ድረስ ብዙም ስለማይራራቁ ዉነቱን አውጥተኽ ታሳየን ነበር ፡፡ ኦቦ ሌንጮ ለታ ደግሞ ለቡርቃ ዝምታህ ውለታ ሲሉ እጀ- ንፉግ የሚሆኑብህም አይመስለኝም፡፡
ደራሲና ጋዜጠኛ ተስፋዬ ! መቸም እንደቅርበትህም ሆነ እንደጋዜጠኝነትህ ፥ ኦቦ ሌንጮም ሆኑ ፣ ዶክተር ዲማ ነገዎ ኦነግ ውስጥ እንደሌሉ ሳትሰማ የቀረኽ አይመስለኝም ፡፡ ቢያንስ ፊርማና ወረቀቱን አይተናል ብለን ባንመሰክርም – ከኦነግ ተባረዋል ከተባለ ዘመን ባጅቷል፡፡ የቤተ መንግስቱ ሹክሹክታ ውነት ከሆነ ፣ አቶ መለስ ኦህዴድን የሚሸጡት ለቀድሞዎቹ የኦነግ አባሎች እንጂ አስመራ ለሚገኘው ኦነግ አይደለም ማለት ነው ፡፡ እሱም ላይ ቢሆን ገና ኦነግ በሁለት ሰዎች መሪነት የሚነቃነቅ እስከሆነ ድረስ ኦቦ ሌንጮ ለታ እስከአሁንም ድረስ ከነኝህ ሁለት የኦነግ ድርጅቶች ጋር የትሥስር አንጓ እንደሌላቸው ነው የሚነገረው፡፡
የፍትህ ጋዜጣ ባለቤት ተመስገን ደሳለኝ – ’’ህዝብና የተቃዋሚዎች ፓርቲዎች መንታ መንገድ ’’ በሚል ርዕስ በጻፋው መጣጥፍ ላይ እስከዛሬ አገሪቱ በተቃዋሚ ድርጅቶች ፥ ወይም የድርጅቶች መሪዎች ድክመት ላይ ፣ ነቅሶ ያወጣቸውን ነጥቦች ፣በፕሮፌሰር መስፍን ቀጣይነት አስተያየት ቢታከልባትም ፣ አዎ ልክ ነው ወይም የለም ሃሰት ነው የሚል ቀጣይ አስተያየት እስከአሁን በሌሎች ጸሃፊዎች ዙርያም ሆነ የድርጅት ደጋፊዎች ዙርያ አላነበብኩም፡፡ ተመስገን እንዲህ ይለናል ፡፡
’’በነገራችን ላይ ደጋግሜ እንደፃፍኩት ምክንያታቸው ምንም ይሁን ምን የተቃውሞውን ጎራ ለመምራት ወደ አደባባይ የወጡት ፖለቲከኞች በዛጎላቸው ከተሸሸጉት ‹‹ሌሎች ኢትዮጵያውያን›› የበለጠ ‹‹አክብሮት›› ይገባቸዋል። (ይሁንና ግን ሌሎች ኢትዮጵያውያኖች ማለት ምን ማለት ይሆን ? እዚህ ውስጥ የሚመደቡትስ እነማን ይሆኑ ? ከኢትዮጵያ ሌላ ትርፍ አገር ያላቸው ናቸው ወይስ የስርአቱ ምንደኞች ?) ብቻ ከዚህ ባለፈ ክንብንባቸውን ገልጠው ፊታቸውን ያስመቱ ፖለቲከኞቻችን ለእስከአሁኑ አበርክቶታቸው ዋጋ ሊያገኙ ይገባል። በዚህ በኩል ችግር የለም፡፡ ችግር የሚኖረው ያ የአክብሮት ዋጋ በየአመቱ እየተመነዘረ ‹‹መሪ›› በሚል ስም ዛሬም በስልጣናችን እንደተቀመጥን መቀጠል አለብን ሲሉ ነው። ይሄ ወደድናቸውም ጠላናቸውም ትልቅ ችግር ፈጣሪ ነው፡፡ ምክንያቱም አሁን ኢትዮጵያ ያለችበት አጣብቂኝ ከጥቆማና ከአጋላጭ ባለፈ ‹‹አንቂና አደራጅ›› መሪ የሚፈልግበት ወሳኝ ጊዜ ላይ ነውና።’’ ሰረዝ የኔ፡፡
በርግጥ እንደጋዜጠኝነትህ – ኦስሎ በነ – ኤፍሬም ይስሃቅ እንደተጎበኘች ያሰፈርከው ጽሁፍ ትክክል ነው ፡፡ ኤፍሬም ይስሃቅ ኦስሎን ከግር እስከራሷ እያሉ ከርመውባታል፡፡ በቅርቡም እንዳልከው ዶክተር ዲማም ጎብኝተዋታል፡፡ ከኦቦ ሌንጮም ጋር መክረዋል ፡፡ የቤተ መንግሥቱ ሹክሹክታ ለአቶ መለስ ሊሠራ የሚችለው ፣ ኦቦ ሌንጮ ከነሙሉ ክብራቸውና ዝናቸው የታገሉበትን ኦነግ የተባለውን የቀድሞ ድርጅታቸውን ከአስመራ አስነቅለው እንደ ሰባ ሰገል ሰዎች ፊንፊኔ ላይ ለአቶ መለስ ቢያስረክቡ እንጂ እሳቸው ዘወትር ኦስሎ ላይ በጀርባቸው አዝለዋት የሚሄዷትን ቦርሳቸውን ለመለስ ቢያስረክቡት ደስተኛ አይሆንም ፡፡
ችግሩ ምን ላይ መሰለኽ ! ደራሲና ጋዜጠኛ ተስፋዬ ! የፍትሁ ተመስገን እንዳለው ! ችግር የሚኖረው ያ! የአክብሮት ዋጋ በየአመቱ ተመንዝሮ ‹‹መሪ›› የሚለው ቃል ወርዶ ፥ ወርዶ በወጣቱ የኦነግ ደጋፊዎች ዘንድ አልቋልና ነው፡፡ ከዚህ በላይ ምንም የሚጨመር ነገር የለውም ፡፡ የችግሩ ምንጮችን ፣ የፈለግኽውን ሊፕስቲክ ቀባብተህ ፣ የጸጉር ስታይላቸውን ለውጠኽ ፣ አርተፊሻል ጸጉር ጭነኽ ምንይልክ ቤተ መንግሥት ብታቀርባቸው ፣ የችግሩ መፍትሄ አይሆኑም፡፡
በርግጥ ኦቦ ሌንጮ በርዮተ ዓለም ቅርበትና የአማራን ህዝብ በመጥላት ለአቶ መለስ ይቀርቧቸዋል ፡፡ የኢትዮጵያን አንድነት እያለ እስከአሁን የሚዘምረው ኃይል ዘወትር ለኦቦ ሌንጮ ራስ ምታታቸው ነው ፡፡ የሚሰማ’ቸው የሙዚቃ ቃና ’’ የአማራ በላይነት ነው ’’ ፡፡ በዚህ ችግር የተተበተበን ሰው አቶ መለስ ቤተ መንግሥት ወስዶ ቢያስጠጋቸውና ሁለቱንም የሚያስደስታቸውን የሰባራ ሸክላ ሙዚቃ አብሮ ከማድመጥ ሌላ የሚወጣ ምንም አዲስ ነገር የለም፡፡ ከንግዲህ ኦቦ ሌንጮ የኦሮሞን ህዝብ ከወያኔ ጋር ያስታርቃሉ ብሎ መገመት የዋህነት ነው ፡፡
እድሚያቸው ከጡረታ ስላለፈ ፣ የስካንዲኔቪያዋ ክረምትም ብርቱ ስለሆነች አጥንታቸው ድረስ ዘልቃ ስላንዘፈዘፈቻቸው ጸሃይቱን ፍለጋ ፊንፊኔ ቤተመንግሥት ቢያቀኑ አይፈረድባቸውም ፡፡ እንደ ሹክሹክታህ መሠረት ከሆነ ፡፡ ከዚህ በተረፈ ግን! የአቶ ሌንጮ መስራች መሪ የሚለው ቃል በየአመቱ እየተመነዘረ ፣ቁልቁል ስለወረደ ከኦሮሞ ወገኖቻቸው ክብሩ ዝቅ እንዳለባቸው ነው እየታየ ያለው፡፡ ኦነግን ይዞ ገብቶ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴርነትን ብለህ የተመኘኽላቸውን በጎ ምኞት እንዲህ በቀላሉ ይሳካላቸዋል ብዬ አላምንም፡፡ ህልም ከአለምን ምናልባት ለኦቦ ሌንጮ ጥሩ ብንመኝላቸው ፣ ለኦሮሞ ህዝብ ’’ መያድ ’’ Ngo ላቋቁምለት ብለው ቢያቀኑ ነው የሚበጀው ፡፡ እሱም ቢሆን ከወያኔ የስለላ መረብ ውስጥ ነጻ አይሆንም፡፡
ደራሲ ተስፋዬ ይልቅስ በቀልድ እያዋዛህ የምትነግረን ምጸታዊ ጆክህ እንዳለች ሆና ! የጥንት የጠዋቱን ሌንጮ ለታ አሁንም በኦነግ ላይ ኃይል አላቸው ብለህ ማመንህ ትንሽ ከመረጃ ውጭ ያስወጣህ ይመስለኛል፡፡ ኦህዴድ በጨረታ ለሌንጮ ለታ ሊሸጥ ነው ያልከን ቀልድ ግን እጅግ ከምር ነው ያሳቀችኝ ፡፡ ድሮ አጎዛ ሰፈር አካባቢ ’’ ነጻ ከብት ’’ የሚባል ሰፈር ነበር፡፡ የጠፉ ከብቶች የሚገኙበት ፡፡ ዛሬ አቶ መለስ አጋሰሶቻቸውን በጨረታ ነው ? ያለ ጨረታ የሚሸጡት ? የጋማዎቹን መንጋጋ አፍ እያስከፈቱ ጥርሳቸውን መሽረፋቸውንና አለመሽረፋቸውን ሳያዩ መቸም አቶ ሌንጮ አይገዟቸውም፡፡ ለመሆኑ ኦህዴድን አቶ መለስ ስንት ጊዜ ነው ገበያ የሚያወጧቸው ? እያልከን ነው በብዕርህ ? እባክህ ስለዳንሰኛው ባጫ ደበሌ አንድ አስቂኝ ቀልድህን ጻፍልን፡፡ በባጫ ብንላጥ ይሻላል ነው የሚሉት የሸገር ልጆች ፡፡
“Meles has to sell his Horse. Lencho wants to buy it.
¨Lencho: Is this horse faithful ?
Meles: Yes, I have sold it 3 times earlier also. It is so faithful, everytime it returned back to me.



አቦ ይመችህ ወዳጄ እንግዶ! አንዳንዴ እንዲህ የጽሁፍ አድባርና ዛርህ ሲቆም አንጀት አርስ ልብ አረስርስ የሆነ መትቢልህ አዝናንቶ ዕውቀትና ሃቅ ይነቅሳል::
የመጣጥፍ መቸትህን በመድብል መልክ ለማየት ሁሌም እንደጓጓው ነው:: ከነጋሪት እስከ ርካብ: ከኢትዮሚዲያ እስከ አቡጊዳ እና በሌሎችም ሳይበር ሆነ ምድር መነበቢያ ላይ የሰፈሩትን ሁሉ!
ሰላም ጤና እና ክብር ለአንተ አያ እንግዶ!
ቅቅቅቅቅቅ አሪፍ ቅጽል ነው የሰተከው, እንግዶ. ማገዶ. ፋንዶ.ፍንድዶ,,, እያሉ መከተል ይቻላል ይምችህ አቦ!
ልብ አረስ ትንተና ነው, ተስፋየ ገብረአብ ሁሉን አውቃለሁ እያለ ሰላስቸገረ እንኩዋን ነገርከው, በርታ ወዳጀ
Leave the Eritrean alone! He is doing his job.
ምርጥ ጉዳይ ደስ ብሎኘ ኮመኮምኩት, ተባረክ ቀጥልበት
እንግዳ!
የማልስማማበት ብዙ ነገር ቢኖርበትም ትረካህ አሪፍ ነው። ይህን ብእር ይዘህ የት ነው የተደበቅኸው? እስኪ በግል ፃፍልኝና “ሽሙጥ ፍትሃዊ ግንባር” የሚል የሰንበቴ ማህበር መስርተን አብረን እናሽሙዋጥ። እንደምንታዘበው ከሆነ ጀግንነትና ቁምነገር እንደሁ ረክሰዋል። ምንይደረግ?
ታስፋዬ ደግ አደረገ
እትዮፕያ ብቻ ይሰበክ የምሉ ቀለቱ
This article has some truth and prediction. I like it the way you compare Cow for market and OPDO for auction. It is much better to have one cow than all stupid OPDOs.
ቀሽት ጽሁፍ ናት!ተስፋዬ ግን ዓላማህ አልገባ ብሎኛል፡፡አንተ እንደዚህ በአንዴ ኦሮሞ መሆንህ፡የምን ጠጋ ጠጋ የሆን?መቼም አትዮጵያ የምትባለው አገር አንድ ሆና ማየትህ ጋንግሪንህ ሳይሆን አይቀርም፡፡
yehe ye shabiya Qetregna men aregen ?? endesedben edelun yesetut ene
zeHabesha aydelu !!!!!!!!
engida you are more true than tesfaye. lencho is history. He can only negotiate for his ponsion life. He has no command over the oromo people. Afterall who is in his right mind that goes to meles and negotiate over people’s right and freedom. Negotiate with a mass murder and fascist dictator? Only to be yet the other banda like negasso was, like opdo is. If that is the case with lencho, then afterall lencho is what one calls the “banda child” always posing a problem to be a matured banda. Tesfate flatly failed because he was guided by his emotive feelings and feeble desires that conspired to force him speak a warped tale that lies bare on the opposite side of truth.
Free Debebe እንደጻፈ(ች)ው:
የወያኔ ቁጥር አንድ ደላላና ወኪል እንግዳ ይባላል :: እንግዳሸትም ይባላል :: አንዳንድ ሰዎች ቆሻሻ ስራቸውን እንዲሰራላቸው ሲፈልጉ እንግዱ ይሉታል :: የእንግዳሸት እውነተኛ ስም ግን ነዋይ ታደሰ (Newaye Tadesse) ነው :: የሚኖረውም በኦስሎ ከተማ ነው :: ነዋይ ታደሰ የተሳሳተ መረጃ በመስጠት በድርጅቱ ስም ( http://w2.brreg.no/enhet/sok/detalj.jsp?orgnr=984926960 )ከባንክ አጭበርብሮ ገንዘብ ተበድሮ :: በዚህም በማጭበርበር ወንጀል ተከሶ እስራቱን ጨርሶ ከወጣ በኋላ የተበደረውን ገንዘብ ለመክፈል ባለመቻሉ በባለእዳነት በጥቁር መዝገብ (ኢንካሶ ) የተመዘገበ ስለሆነ በስሙ የረባ ንብረት መግዛት አይችልም :: እዳውን እስካልከፈለ ድረስ መኪና መግዛት ስለማይችል ዘላለም እግረኛ ሆኖ ይኖራል :: ከእስር ቤት የተለቀቀውም በማስጠንቀቂያ አመክሮ ስለሆነና ቀለምወርቅ ብሩ በየነን ከማግባቱ በፊት በድሮ ሚስቱ ላይ ከባድ ድብደባ አድርሶ ስለነበር ዳግመኛ ወንጀል ሲፈጽም ቢገኝ ከባድ ቅጣት እንደሚመጣበት ስለምያውቅ ግዴታ ስሙን መቀየር ነበረበት :: በዚህ የስም ለውጥ ዘዴው ፖሊስ ሊደርስበት ስላልቻለ ከብዙ ክሶች ለማምለጥ ችሏል :: ነዋይ የደበደባቸው ወይም ሞባይላቸውን የተቀሙ ሰዎች ፓሊስ ጣቢያ ሄደው በሚያመለክቱበት ጊዜ እንግዳሸት ታደሰ የሚባል ሰው በአገሪቱ ንዋሪዎች ባህር መዝገብ (Folkeregister) ውስጥ ስለሌለ ነዋይ በቀላሉ ሲያመልጥ ቆይቶ በመጨረሻ ላይ ግን በእንግዳሸት ስም ወንጀል ሲፈጽም የኖረው ነዋይ ታደሰ መሆኑን ፖሊስ በፎቶግራፉ አማካኝነት በቅርቡ ደርሶበታል ::
ነዋይ የወያኔ ተቃዋሚ በመምሰል የተቃዋሚው ሃይል የወጣለት ዘረኛ መስሎ እንዲታይ ጥረት የሚያደርግና ሆን ብሎ ለወያነኔ ዱላ የሚያቀብል ሰው ነው። የትርግራይ ህዝብ ባጠቃላይ ተቃዋሚዎቹን ጨምሮ በጠላትነት በመፈረጅ ሁሉም ወያኔ ናቸው እያለ ሲሰብክና ሲጽፍ የሚውል ለተቃዋሚው ጎራ ትልቅ እንቅፋት የሚፈጥር ከወያኔ ከፋፋይ ፖለቲካ ባልተናነሰ መልኩ ዘረኝነትን የሚያራምድ ከፋፋይ ሰው ነው። ባጠቃላይ የእንግዳ (ነዋይ ) አመለካከትና አካሄድ ተቃዋሚው በትግሬ ጉጅሌ ላይ ብቻ ያነጣጠረውን ጠላትን ለይቶ የመምታት ስትራተጂ የሚቃረን አፍራሽ አካሄድ ነው። ነዋይ ከራሱ ከትግራይ ህዝብ የወጡና ለዲሞክራሲ ትግሉ የተሰለፉ የትግራይ ተወላጆች እንደሌሉ በመቁጠር ጠቅላላ የትግራይን ህዝብ ከጉጅሌው ጋር አዳብሎ መምታት አለበት የሚል ፖለቲካ ያራምዳል። ይህ እውር ፖለቲካ የትግራይ ህዝብ ከወያኔ ጋር ከመወገን የተሻለ አማራጭ እንደሌለው አድርጎ ህዝቡን አጣብቂኝ ውስጥ የሚከት መሰሪ ወያኔያዊ ዘዴ ነው። በዚህ እንቅስቃሰው ጉጅሌውን የሚቃወሙ የትግራይ ልጆች ከትግሉ እንዲርቁ በማድረግ ለወያኔ አምባገነን ገዥ ቡድን የማይረሳ ውለታ እየዋለለት ነው ::
ትግሮች ካልጠፉ ሰላም አይገኝም ባዩ አቶ እንግዳ በኖርወይ አገር የትግራይ ተወላጆችን ማሳደድ ዋነኛ ተግባሩ ነው። በዋርካ ራሱን ጅራፍ ብሎ በመሰየም የሚጽፈውን አንብቡ።
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?p=147066&highlight=#147066
በመንገድ ሲያልፉ ልትሰልሉ መጣችሁ በሚል ሰበብ በእንግዳሸት ድብደባ የደረሰባቸው የትግራይ ተወላጆች በጣም ብዙ ናቸው። የትግራይ ተወላጆች በኢትዮጵያውያን ማህበር ቅጥር ግቢ ወስጥ ቢገኙ መደብደብ አለባቸው የሚል መመሪያ ያወጣው ራሱ እንግዳሸት – ነዋይ ነው። በትግራይ ልጆች ባለቤትነት የሚንቀሳቀሱ የንግድ ድርጅቶች የወያኔ ንብረቶች ናቸው እያለ የውሸት ወሬ በመንዛት ቦይኮት እንዲደረጉ የሚገፋፋና የእነሱን ገባያ በማቀዝቀዝ በሚስቱ ስም ሬስቶራንት ከፍቶ የራሱን ገባያ የሚያሞቅ አድርባይ ነጋዴ ነው።
በአንድ የወያኔ ደጋፊ የተዘጋጀው የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ቦይኮት እንዲደረግ ጥሪ በቀረበበት ወቅት እንግዳ ከደጅ ሆኖ ሰው እንዳይገባ ሲከለክል ነበር። ጥፋቱ ግን ሌሎችን እንዳይገቡ መከልከሉ ላይ ሳይሆን በጎን ሚስቱን አሾልኮ በማስገባቱ ነው። ኮንሰርቱ ውስጥ ያያት ሰው ሁሉ ጉድ ነበር ያለው። ወደ ኢትዮጵያ የሚሄዱ ሁሉ ወያኔዎች ናቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይኮት መደረግ አለበት እያለ ሚስቱ ግን አዘውትራ ወደ ኢትዮጵያ የምትጓዝ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ታማኝ ደንበኛ ነች። ለምግብ ቤቱ ጤፍ በርበሬ ሽሮና ቅመማቅመም ለማምጣት የሚሸኛትና የሚቀበላት ራሱ የቦይኮቱ አቀነባባሪ አቶ ነዋይ ነው። እናም የዚህ ሰው እንቅስቃሴ ሂደቱና ውጤቱ ገዥውን ጉጅሌ የሚጠቅም ነው።
ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ ለዘላለም የምትኖርበት ጊዜ ይመጣል !!!
ወያኔና ግብረአብሮቹ ይወድማሉ !!!
THANK YOU HATU. IT IS AN AMAZING PROFILE OF A DANGEROUS MASKED SLOWTER.
WUKRO
You better call him with his real name yohannes Leta. He is worse than Meles. He is an agent for the Eritrean government. Esayas used him to dismantle OLF so that he can loot the country. Esayas benefited until the Eritreans kicked out of Ethiopia. Now Meles is in trouble and needs Yohannes Leta. As Mandela once said “it is foolish to turn off the heat when water starts boiling.” That is what Yohannes Leta is fond of doing. Merera Gudina in one of his famous articles desribed him and other OLF officials:
kemetsaf qulqulu yileq beshabiya yemiyaminu yeoromo ingidelijoch…oromiyaa yemilewen siyame yawetuten lijoch asgedilew innesu oromiyaa azeffagn honu. Merera oromo aydelem yilallu innesu Kemenzina Bulga iyyetegabu. Enie enquan lemen tegabu aydelem lenegeru anesahut inji. Ennesu Abrham inna Marta iyyawetu Merera oromo iydelem yilallu. Karter senter Amerikan ledirder hedew Amarigna menager anchilem iyalu tiyatir siseru nebber. Abiyu Geleta gin ke 27 kenorew mistu gar yemigbabaw beamarigna new. Meles zenawi yemiseruten yemiyawqu Yemenz quanqa iyetenageru gud seru.
Merera kept on saying these OLF officials have no military and political skills. I think his task has been to make sure the ruler of Ethiopia should be an Enritrean for ever. He has no support among oromo people becuase he sold us for wayane and shabia.
ይገረማል ነገሩ ማንም የማይታመንበት ደረጃ ተደርሷል ለብልጥ ሰው የወያኔን ተንኮል ማወቅ በጣም በጣም ቀላል ነው የዋህ ጋገኙ ነው ችግሩ በመሰረቱ ተስፌዬ ገብርሃብ አኪውሩ የወደቀ ሰው ነው ወደዛ ለሱ ጊዜ ማጥፋት አልፈልግም የአማራ ጠላት ጥላቻቸው ቅናት ነው በቃ የታወቀ ነው. ሌላው ወያኔ ነው አይደለም ለማለት ቀላል ዘዴ አለ የምለይበት የፈለገ ወያኔን ሌባ ነው ቢል አዎ ግልጽ ነው ሌባ ነው ሆዳም ነው ቢሉን አዎ ህዳም ነው. የታውቀ ባህርያችወን ሲነግሩን ተቃዋሚ እይመሰለን ከእውነተኛ ተቃዋሚዎች ጋር ያጣሉናል. እውነተኛ ተቃዋሚዎችን ለማዳከም እና ብህዝብ ተቀባይነት እንዳይኖራቸው በየቦታው ብቅ ብቅ ይላሉ በቅርቡዓንተነህ ሽፍፈራው የትባለ ሰው እዚው ድህረ ገጽ ኢሳትን ሊያማልን ብቅ አለልኛ ኢሳት መለስን ባዋረደ ማግስት እንግዲህ ልብ በሉ የዋሕ ተሸወደ አሪፎቹ ደሞ ነቁበት. ማወቅ ያለብን ነገር ቢኖር ወያኔ እራሱን ገልጦ አይመጣም እንደሚጠላ እና ተቀባይነት እንደሌለው ስለሚያውቁ እናም እውነተኛ ተቃዋሚዎችን ለማዳከም አስመሳዮች ይሰማራሉ ኢሳትን , ግንቦት 7, መድረክ የሚያማ ምንም ጽህፍ ቢመጣ ማሳፈር አለብን . በኢህ እንይዛቸዋለን ኢሳትን ነቅፎ ግንቦት 7 ሊያሞግስ ይችላል ወይም መድረክን ደግፎ ግንቦት 7 ሊአሞግስ ይችላል እናም በተለይ እንዚህን ህዝብ የሚወዳቸው ሚድያ እና ድረጅቶች ስለሚያሰጉት በሬ ወለደ እያለን ነው በበኩሌ አዋረዳቸዋለው ወርደታም ስለሆኑ ፍርፋሪ የነፋው ምድረ መሃይም ሊያታልለን አይገባም. እናም በተለይ ሌሎችም ሊኖሩ ይቻላሉ ግንቦት 7 መድረክ. መኢአድ ዴና ኢሳት ሚድያን ከተቸ ወይኔ ስለመሆኑ ምንም አትጠራጠሩ. ወያኔ ተቸኡ ሳይሆን ቁም ነገሩ ማንን ተቹ ነው ያኔ ማን እንደሆነ መለየት ይቻላል .
ሃቱ ሃቱ የምቀኝነትና የቅናት ወሬ ይመስላል ጽሑፍህ
“Meles has to sell his Horse. Lencho wants to buy it.
¨Lencho: Is this horse faithful ?
Meles: Yes, I have sold it 3 times earlier also. It is so faithful, everytime it returned back to me.