ኪነ ጥበበኞችን እንካን ብዕር ሆድ ይፍጀውም ጨርሶ አይገልጻቸውም በበላይነህ አባተ

June 3rd, 2012 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ
  1. በላይነሽ
    | #1

    አቶ በላይነህ ኪነጥበብ ምንማለት እንደሆነ በትክክል አብራርተህ በህብረተስቡ ውስጥ ሊጫወቱ የሚችሉትን ሚና በመግለጽ በኩል የተዋጣለት አገላለጽ ነው::የኪነጥበብ ሰዎች ሰዎች በመሆናቸው ምክንያት የተለያየ አስተሳስብ ሊኖራቸው እንደሚችል መዘጋት የለበትም::የሁሉም የኪነጥበብ ሰዎች አስተሳስብ ሊደመጡና ሊከበሩም ሊነቀፉም ይችላሉ::ሲነቀፉም ሃሳባቸውን በነጻነት የመግለጽ የመቃወምና የመደገፍ መብታቸው ሊከበር ይገባዋል::እኛን ብቻ ደግፉን ማለትም ሞኝነት ነው::
    ኪነጥበብ የሚያድገውም ከውድድርና ከሃስብ ፍጭት ነው::
    አቶ በላይነህ ይህን ክእኔ በበለጠ የምትገነዘበው ስለሆነ ሁሉንም በአንድ መውቀጫ መውቀጡ ተገቢ አይደለም እላለሁ::
    እንኳን ብዕርና ሆድ ይፍጀው አይገልጻቸውም የሚለው አባባል አስተካከለው::በዓልም ላይ እስካሁን ብዕርን የሚወዳደረው አልተገኘም::ብዕር የማይገልጸው ነገር የማያቃናውና የማያኮላሸው ነገር የለም::ሆድ ይፍጀው ምንንም አይገልጽም:: ዝም ያለ ዝም ብሎ ይሞታል::ተው ቻለው ሆዴ ሲቀር ለሚቀረው ምነው መናደዴ ማለት ነው(ዝነኛ አያሌው መስፍን)::
    በሙዚቀኛው አመለካከት የተለ ትርጉም ሊኖረውም ይችላል::
    ስለዚህ የተለያየ ሃስብን አከብራለሁ ከሚል በተለየም አንተን ከመስለ ጥልቅ ሃስብ ከአለው ሰው ይህ የሚጠበቅ አይደለም::
    በተረፈ የምታቀርባቸው ሃስቦችና የምጽፋቸው ግሩም ስለሆኑ በርታ::በሚቀጥለው ከዚህ የተሻለ ይዘህ እንደምትቀርብ አምናለሁ::

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።