ለማጣፈጫ ሃገርን ወረራ! ታደለ መኩሪያ

June 3rd, 2012 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

በ1600ኛው መቶ ዓመታት ውስጥ የኢንግሊዝ ቅኝ ገዥዎች በምዕራብ ኢንደስ (West Indies) እግራቸውን ሲያሳርፉ አላማቸው ትንበሆና ጥጥ ለሃገራቸው ፋፍሪካዎች ለማቅረብ ነበር። ከነዚህ ደሴቶች ከሆነቸው ባርባዶስ (Barbados) ላይ ከአረፉት ቀኝ ገዥዎች አንዱ ጄሚስ ዳራክስ (James Drax) የሚባለው በብራዚል ሃገር ሸንኮራ እንደሚሆን ካየ በኋላ በዚች ደሴት ላይ 1655 ዓ ም የሸንኮራ ተከላ ጀመረ። ተልኮውን ‘ ለማጣፈጫ ፍላጋ’( needs for sweeter) በሚል ሰየመው። የሸንኮራ አገዳ ተከላ ለማጣፈጫ ፍለጋ ለምዕራብ ኢንዲስ (West Indies) ወይም በአሁኑ መጠሪያቸው ለካረቢያን (Caribbean) ሃገሮች መጥፊያቸው ሆነ። ሃገሬው ከአጽም ርዕስቱ ተነቀለ። ያለ ክፍያ በቀለብ ብቻ ለቀኝ ገዥዎቹ በሸንኮራ ተከላውና ቆረጣው ላይ ተሰማራ። ቀኝ ገዥዎች የሃገሬው ጉልበት አልበቃ ብሏቸው አተላንቲክ ውቂያኖስን አቆርጠው ሩብ ሚሊዮን የሚሆኑትን አፍሪካውያንን ለባርነት ወደ ካረቢያን ሃገሮች እንደቃ በሰንሰለት ቀርቅበው በመርከብ ጭነው አመጧቸው። በባርባደሰ (Barbados) የተጀመረው የሸንኮራ ተካላ ወደ ጃሜካ (Jamaica) ሊዋርደ ደሲቶች (Leeward Islands) ተሰፋፋ። የኢንግሊዝ ዜጎች ከቀድሞ አባቶቻቸው የሰኳር ፍጆታ በስድስት ጊዜ ጨመረ። የካረቢያን (Caribbean) ሃገሮች መሬታቸውን አጡ፤ ባህል አልባ ሆኑ፤ የማንነት መገለጫው ዘፈንና ሩጫ ሆነ። ዛሬ በርስታቸው ላይ ሰፍረው የሚገኙት በባርነት ለሸንኮራ ተከላና ቆረጣ የመጡት አፍሪካውያን ናቸው።

ወደ ኋላ ተመልሰን ከአፍሪካ በባርነት ሰም የመጡቱን አፍሪካውያን ሁኔታ ስናየው እጅግ የሚሰቀጥጥ ነው። ትንሽ ጥፋት ካጠፉ ወይም ከበደሉ የተነሣ ለማመጽ ከተነሣሱ አለቀላቸው።ውኃና ምግብ ተነፍገው እንዲሞቱ ይደረጋሉ፤ የደከመው ሰውነታቸው ለውሻ ይቀርባል፤ እዚህ ከመድረሳቸው በፊት በእግር ብረት ይታሰራሉ፤ ይገረፋሉ፤ አካለ ሥንኮላን እንደሆኑ ይደረጋል። የዚህ ሁሉ መነሻው የሰኳር ምርትን አሳድጎ ባለሐብቱ ተደላቆ እንዲኖር የኢንግሊዝም ሕብረተሰብ የሰኳር እጥረት እንደይፈጠርበት ነበር።
በአሁንም ዘመናችን (Caribbean Sugar industry taken as a model of international exchange) በማለት ይወደሳል። ይታያችሁ በካረቢያ ሕዝቦች ላይ ለስኳር ተከላ ሲባል ሃገር አልባ የሆኑትን እንደጥሩ ምሳሌ ይጠቀሳል።እህጉራዊ ንግድ (Globalization trade) የሚባለው ምስጢሩ ይህ ነው።

መለስ ዜናዊም እንደጌቶቹ የኢትዮጵያ ገበሬ ከቀደሞ ይልቅ አሁን የሰኳር ተጠቃሚ ሆኗል አያለ በማሰብ ችሎታችን ላይ ያሾፋል። በገልባጩ ገበሬውን ከርዕስቱ አየነቀለ በሕጋዊነት ሕገወጥ ተግባር እየፈጸመ ይገኛል። እስከ መቼ ይቀጥላል?

በነፃነቷ ኮርታ በጅግኖች ልጆቿ ተከብራ ቅኝ ገዥዎችን አሣፍራ የኖረች ሃገራቸን በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን በአህጉራዊ ንግድ (Globalization) ስም ተደፍራለች። ዘርን መሠረት ያደረገው በትግራይ ክፍለ ሃገር በስልሳዎቹ ዓመተ ምህረቶች እንቅስቃሴ የጀመረው ቡድን ኢትዮጵያን ለባዕዳን ከበርቴዎች ለስያጭ አቅርቧታል።
የትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባር ኢትዮጵያ በማስተዳደር ስም ለባዕዳን ሃገሪቱን እየሸጠ ይገኛል። ምንም አንኳን አንድ ሃገር ላዕላዊነቷን የሚያስጠበቅ የመከላከያ ኃይል ቢኖራትም የኢትዮጵያ ሠራዊት ለዚህ በቂ ሆኖ አልተገኘም። ለባዕዳን ጥቅም አስጠባቂ መሆኑን በጋንቢላ፣ በዋልድባ፣ በአፍር፣ በኦጋዴን፣በአርሲ፣ በወለጋ፣ በከፋ፣ በሻኪሶ መሬታችን ለሸኮራ ተከላ ለባዕድን አይሰጥንም በማለታቸው በሃገሬቱ ሰም የተዋቀረው የመከላከያ ኃይሉ በአጋዚ ሠራዊት ሰም ሕዝቡን እያጠፋ ነው።

የወቅቱ መንግሥት በቁንጮው መለስ ዜናዊ የሚመራው የትግራይን ልጆች በዘር ሐረጋቸው አታሎ፤ ከተራ ወታደር እስከ ጅንራል በሚደርስ የማዕረግ እርከን ፤ ከእግር ጠፍራቸው እስከ ፀጉር ጫፋቸው አስታጥቆ በአጋዚ ስም መሬቴን ለባዕዳን አሣልፌ አልሰጥም ያለውን ሕዝብ ያስጨርሳል።ይህ ሠራዊት ማሰብ ያለበት በእፍሪካኖችና በካረቢያን (Caribbean)ሃገሮች ላይ የደረሰውን ዓይነት ውርደት በልጅ ልጆቹ ላይ እንደሚደርስ ከአሁኑ መገንዘብ አለበት። በዘር አሻክላ ወጥመድ ተተብትቦ በማዕረግና በጥቅማጥቅም ተወጥሮው ዛሬ ቢታይ መጭው ትውልድ ያፍርበታል። የልጅ ልጆቹ ሲወቅሱት ይኖራሉ። የሚታየውን አላየሁም ብሎ ቢክድ ደግሞ የቆም ሞት ነው።
ወታደሩ ሴቪሉም ተማሪው መምህሩ መላው የሃገሬ ሕዝብ ከሊቅ እስከ ደቂቅ በሃገራችን ላይ በልማት ስም ያጃበበውን የውርደት ስንቅ ነገ ዛሬ ሳንል ማስቆም አለብን። የወያኔ ልማት ይዞ የሚመጣው ውርደት ነው፤ በአፍጫችን ይውጣ። ድማቸውን እያፈሰሱ ያሉት ወገኖቻችን ለልጅ ልጆቻችን መሆኑን ተረድተን አብረናቸው እንቁም። በካረቢያን ሃገሮች የደረሰው ውርደት እንደይደርሰብም መነሣቱ ዛሬ ነው።

ስው በሃገሩ
ሰው በወንዙ
ቢበላ ሣር ቢባላ መቅመቆ
ይከበር የለም ወይ! ማንነቱ ታውቆ
ኢትዮጵያ ሃገራችን ከውርደት በቆራጥ ልጆቿና በእግዚሐብሔር ኃይል ትድናለች!

tadele@shaw.ca

  1. Anonymous
    | #1

    ወሬ ከምታወራ ወደሃገርህ ገብተህ ስራ
    ወሬ ሚያወራ ሞልቷል

  2. አንድነት ብርሃኔ
    | #2

    አዮ ዘመናችን
    ታሪክ እንዳልሰራን በዓለም እንዳልታየን
    ያባቶችን ወግ ጀግነት ሀገርና እምነት
    ጠላትን መክተው በደም ባጥንታቸው
    አቆዩን ኢትዮጵያ በታሪክ ግንባቸው
    ተከታዩ ትውልድ አባዜው በዝቶበት
    በፈረንጆች እውቀት ናላው የዞረበት
    መከፋፈል ሲማር አቅቶት ማጋጠም
    ሀገር ሊበጣጥስ እዩት ሲታመም
    ትውልዱ የከፋ የዘር ጌጥ ደርቦ
    መልኩን ለመቀየር የሚጥር አዘቦ
    በስው ማንነት መስሎ ለመታየት
    ሀገሩን የሚሸጥ ካያቱ አልፎበት
    አዮ ዘመናችን ! ጆሮ ዳባ ብለን
    ታሪክ ስናጠፋ ሁላችን ተባብረን
    ለሆዱ ተገዝቶ ሀገር ወዲያ ጥሎ
    ማዳነቅ ጀመረ እሱነቱን ገሎ
    እሱን የመሰለ በሁሉም መጠኑ
    አለሱ የማይሆን የሚለው ውጥኑ
    ራሱን ያልቆጠረ አጣጥሎ ስብእናው
    በሹመት ተገዝቶ የችጋር ቀጠናው
    አይምሮ የሌለው ሚዛን የጠፋበት
    በስሜት ተገፊ ትእቢት ተጭኖበት
    አውንታውን ስቶ አግድሞት አሉታ
    ቅርምት ጀመረ ለባእድ ይዞታ
    ባላባቱ ከፍቶት መሬቱ ተወርሶ
    ስብሉ ትሰብስቦ ሲሄድ ተግበስብሶ
    የምግብ ዋስትና ሲባል የሕዝቦች መብት ጥሶ
    ም እራቡም አያፍር ግፍን አለባብሶ
    ጥቅሙን የሚያስቀድም ዲሞክራሲ ደርሶ
    ጊዜው አያመችም ዓለም ተራምዳለች
    ድጎማ አምባገነን በድምጻ ሽራለች
    ቢን አሊን አብደላን ዳረገች ለስደት
    ገዳፊን ለሕልፈት ሞባርክ ለእስራት
    ሊማሩ ያልቻሉ መለስና ኩራት
    ሲጠፉ እንያቸው ሆነው የሳት እራት

    አንድነት ብርሃኔ

  3. ጉዱ ገና
    | #3

    Anonymous አላሰራ አላችሁን ለኛ መሬት እየከለከላችሁ ለባእዳንና ለደጋፈዮቻችሁ ብቻ ትስጣልኣችሁ ኢትዮጵያዊነት ሳይሆን ትግሬነት ሆነ መመዘኛው ለመኖርም ለመስራትም ወደፊት ለመተንፈስም:: ላንተና ለመሰሎችህ ለጊዘው ለቀንላችሁአል:: ቀኑ ሲደርስ ግን እናንተን አያርገኝ

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።