ኢትዮጵያ፡ ወደ ሕገ መንግስታዊ ዴሞክራሲ ጎዳና ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ
ላለፉት ጥቂት ወራት በኢትዮጵያ ከፈላጭ ቆራጭ መንግስት ወደ ዴሞክራሲ በሚል ርዕስ ስጽፍ ነበር፡፡ከነዚህ አስተያየቶች በመጨረሻው ጦማር ላይ ስጥፍ “በዴሞክራሲው መሸጋገርያ ድልድይ ላይ ስልጣንን በሚየነፈንፉ ግለሰቦችና ቡድኖች መሃል ግጭትና ግብግብ አይቀሬ ሲሆን፤ተራው የህብረተሰብ ክፍል ስልጣናቸውን በሚያኮላሹትና ለግል መጠቀሚያ በሚያደርጉት ላይና ሥልጣናቸውን የሙጢኝ ባሉት ፈላጭ ቆራጮች ተሰላችቷል መሮታልም፡፡ይህ ከፈላጭ ቆራጭ ስርአት ወደ ዴሞክራሲ በሚደረገው ሥግግር ወቅት የሚፈጠረው ግርግር ስልጣንን ለመጥለፍ ላቆበቆቡት መንገድ ይከፍትላቸዋል፤ ስለዚህም ዴሞክራሲን አስገድዶ በመጥለፍ በዴሞክራሲ ስም መልሰው ያን አረመኔያዊ ፈላጭ ቆራጭ ስርአትን ሊያስቀምጡ እንደሚተጉ አሳስቤ ነበር፡፡” በዚህኛው ጦማሬ ላይ ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚፈጠረው ሕገመንግስታዊ ዴሞክራሲ ሕገመንግስታዊ ‹‹ቅድመ ውይይት›› አስፈላጊነት አተኩራለሁ፡፡
ለዴሞክራሲ ሰላማዊው አጥር
አብዛኛዎቹ የሕብረተሰብ አባላት ከመራር አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲ በሚያደርጉት ጉዞ ላይ በጣም ፈታኝና ውስብስብ የሆኑ አጥሮች ተጋርጠውባቸዋል፡፡በ1776 አሜሪካ ከግፈኛው የእንግሊዝ ጨቋኝ ስርአት ከተላቀቁ በኋላ፤13ቱ ቅኝ ግዛቶች፤እስከ 1781፤አርቲክል ኦፍ ኮንፌዴሬሽን እስኪፈርሙና ወቅታዊ የሆነ መንግስተ መስርተው ለጊዜው እስኪቀላቀሉ ድረስ በራሳቸው ቆይተው ብሔራዊ መንግስት መሰረቱ፡፡ይህ ሁኔታ ግን አላዋጣም ምክንያቱም ግዛቶቹ ዋነኛ የሚባሉትን የስልጣን ቁልፎች እንደያዙ በመቆየታቸው ግብይትን፤የውጭ ንግድን ስርአትና ሁኔታን በመቆጣጠር መንግሰት ታክስን እንዳየሰበስብ ገደብ ስለጣሉበት ይህንኑ ለማስተካከልና ፈር ለማስያዝ ጦር ማሰለፍ ግድ ሆነ፡፡ ይህንንና ሌሎቹንም ዋነኛ የተባሉትን ችግሮች በመፍታት ለመረጋጋትና ለዴሞክራሲያዊ ሂደት የተማመነ ሁኔታ ያስገኙት አሁን በስራ ላይ ያለውን ሕገ መንግስት በ1787 ከተቀበሉት በኋላ ነው፡፡
የቅርብ ሁኔታዎችም ሃገራት ከፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲ በሚያደርጉት ሽግግር፤ ውስብስብ የሆነ ችግር እንደሚጋረጥባቸው ነው፡፡ ‹‹ከአረቦች ስፕሪንግ››ሂደት በኋላ 1 ዓመት ጊዜ ውስጥ የዴሞክራሲ ማዋቀሩ ሂደት በሊቢያ ግብጽ፤ቱኒዝያ፤የመን እና ሌሎችም የመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ውስጥ በጣም አወዛጋቢና ፈታኝ ፈተና ገጥሟቸዋል፡፡በግብጽ፤ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግስቱ ወደ ሕገ ምንግስታዊ የሲቪል አስተዳደር እየመራው ነው፡፡የግብጹ ወታደራዊ ስብስብ በግብጽ የሚታየውን የዴሞክራሲ ጫጩት ቅፈቅፍ ቤት በመጠበቅ ላይ ነው፡፡ በርካታ ግብጻዊያንም በግልጽ እንደሚያነሱት ጥያቄ ከሆነ፤ ወታደራዊው ባለአደራ በማለባበስ ሂደቱ ግብጽን ወደ አለፈው የሙባረክ ስርአት ለመመለስ እያቆበቆበ ነወይ ይላሉ፡፡ በቅርቡ በሚካሄደው የምርጫ ሂደት ውስጥ የሙባረክ የመውደቂያው ሰአት ጠቅላይ ሚኒስትር የነበረው አህመድ ሻፊክ ለጁን 16-17 ለመጨረሻው ወሳኝ ፍልሚያ ለከተሰለፉት ተወዳዳሪዎች አንዱ ነው፡፡ በታህሪር አደባባይ ከፈነዳው የበቃኝ አብዮት አንስቶ 12000 ግብጻዊያን ለእስር ተዳርገዋል፤ብዙዎችም በወታደራዊው ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ በርካታ ስመጥር የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ድርጅቶች ምንግስትን በግድ ለመለወጥ በሚል በሃገሪቱ የአቃቤ ሕግ ቢሮ ተወንልለዋል፡፡ወደ ዲክተቴርሽፕ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ መንሸራተትና የኋልዮሽ ጉዞ?
በቱኒዝያ ባለፈው ኦክቶበር የተመረጠው የሕገ መንግስት አርቃ ኮሚሽን በአንድ ዓመት ውስጥ ተስፋ የሚያጭር ውጤት እያሳየ ነው፡፡በጣሙን የሚያበረታታው ሂደታቸው ደግሞ የሕገ መንግስት አርቃቂዎቹ በተወሳሰቡ የፖለቲካ ምናምኖች ላይ ያተኮሩ ሳይሆኑ ሥላጣንን በአግባቡ በስራ ላይ የሚያውልና የፈላጭ ቆራጭነትን ስርአት ድጋሚ መከሰት የሚገታ ሕገመንግስት በማርቀቅ ላይ መሆናቸው ነው፡፡ልዩ ል ‹‹ኮሚሽኖች›› በማዋቀር እነዚህ አርቃቂዎች ምን አይነት ምንግስት በሚለው ምርጫ ላይ በማትኮር (በፓርላሜንታሪና በፕሬዜዳንታዊ) የስልጣኑን ሚዛን በመጠበቅ፤ የፍትህ ስርአቱን ሚዛናዊነት ሕዝባዊነት፤ሥላጣንን በአግባቡ በማከፋፈል ስርአት ላይ ትኩረት በማድረግ እየሰሩ መሆናቸው ነው፡፡
በሊቢያ ያለው የዴሞክራሲ ሂደት ግን እስከዚህም ተስፋ የሚታይበት አይደለም፡፡ በኦገስት 2011 ‹‹ለሽግግር መንገዱ የሕገመንግስት ረቂቅ››(እውነተኛነቱን ማረጋገጥ አልተቻለም) በሊቢያ ውስጥ በሰፊው ይዘዋወር ነበር፡፡ ከምእራብያኑ ሊበራል ዴሞክራሲ ሃገራት ሕገመንግስት ላይ ተቆርጦ የተለጣጠፈ፤ ስለየህግ የበላይነት፤የግለሰብ ሰብአዊ መብቶች፤ ስለመናገር ነጻነት ስለሃይሞነት ነጻነት፤ ስለመድበለ ፓርቲ ያወራል፡፡ ሌሎችም የሕገመንግስት ረቂቆች በመዘዋወር ላይ ናቸው፡፡ባለፈው ማርች 60 አባላት ያሉት የሕገመንግስት አርቃቂ ኮሚቴ ተዋቅሮ የሊቢያን ዋነኛ የሚባሉትን 3 ግዛቶች እንዲወክል ተሰይሞ ነበር፡፡ነገር ግን ሊቢያውያን በጣሙን አጣዳፊና አንገብጋቢ የሆኑ የመረጋጋት ችግሮች አሏት፡፡መደበኛ የሆነ ቋሚ ጦር በሌለበት፤ጋዳፊን ለመጣል በዘፈቀደ ተሰባስበው የነበሩት አማጽያን አሁንም እርስ በርስ በመቆራቆስ ላይ በመሆናቸውና እንቅስቃሴያቸውም ባለመገታቱ ችግር አለባቸው፡፡ጨለማ በጋረደው ሕገመንግስታዊ ማርቀቅ ሂደት ውስጥ ብልጭታ የሚያሳየው የነጻው ስብስቦች የሊቢያ ጠበቆች፤ምሁራን፤ ጁሪስቶች፤መምህራን፤ እና ሌሎችም በትጋት በማርቀቁ ስራ ላይ ናቸው፡፡እንደዚህ የተገነጣጠለ አካሄድ ደግሞ የማርቀቁን ተግባር ለብጥብጥና አለመግባባት እንዲያመራ ያደርገዋል፡፡በዚህም ሰበብ በመጨረሻው ላይ ሰፋ ያለውን የሕብረተሰብ አካል በማንቃት ለክርክርና ለተሳታፊነት በመጋበዝ ሕገመንግስቱ በሊቢያ ሲነደፍ በባለቤትነት ይሰለፋል፡፡
ከሌሎች ውድቀትና ስህተት መማር፤ ሕገመንግስትን ለመንደፍ ቅድመ ውይይት በኢትዮጵያ
ከፈላጭ ቆራጩ አገዛዝ መውደቅ ጋር ከምንም በፊት ዋነኛና መሰረታዊ ሆኖ የሚነሳው ጥያቄ፤ አሁን ስላለው ሕገመንግስት መደረግ ያለበት ጉዳይ ነው፡፡አሁን በሥራ ላይ ያለው ሕገመንግስት የአንድ ፓርቲ የአንድ ግለሰብ ስርአት ማካሄጃ መሳርያ ነው፡፡ሕብረተሰቡን ለመከፋፈል በአንድ ሰው ፍቃድና ‹‹እውቀት›› በዘር ላይ፤በጎጥ፤በክልል፤በወረዳ፤በቋንቋ እና በመሳሰሉት ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡ በኢትዮጵያ በሚካሄደው ሽግግር በጣም ጠንካራ የሆነ የሽግግር ሕገመንግስት አስፈላጊነት የሚጠበቅ ነው፡፡(ወታደራዊው ድርጅት ስልጣንን በግርግር ካልነጠቀ) አሁን ስላለው ሕገመንግስት በአብላጫው የሕብረተሰብ ክፍል ከቅሬታ ያለፈ ስሜት ይታያል፡፡ ሕገመንግስቱ በየወቅቱ በገዢዎቹ ይደፈራል፤የገዢውንና የአገዛዙን ግፈኛና የበደል ሁሉ መጋዘን የሆነውን ግለሰብ ስልጣን ለማጠናከርና ለማቆየት የሚጠቅም ሆኖ ነው ያለው፡፡በ2009 የዓለም አቀፍ የክራይስስ የሚባለው በተግባሩ እጅጉን ከበሬታ የተቸረው፤ ለተባበሩት መንግስታት፤ ለአውሮፓ ዩኒየን፤ ለዓለም ባንክ በአደገኛ ግጭትና ሊወሰድ ስለሚገባው መፍትሄ አማካሪ የሆነው ቡድን፤በጣም አሳሳቢ የሆነውን ርዕስ አንስቶ ነበር፡፡
የኢህአዴግ በዘር ላይ የተመሰረተ ፌዴራሊዝም አለመግባባትንና ግጭትን ከማስወገድ ይልቅ በፌዴራል መንግስታት መሃል በመሬት፤በተፈጥሮ ማእድናት፤የግዛት ክልል አያያዝና ከመንግስት በሚሰጥ ዓመታዊ በጀት ላይ ላይ ግጭቶችን አባብሷል፡፡ከዚህ ባለፈም በዘር ላይ የተመሰረተው ፌዴራሊዝም ብሄራዊውን ጥያቄ መመለስ ተስኖታል፡፡የኢህአዴግ የዘር ፖሊሲ የአንዳንድ ወገኖችን ስልጣናቸውን ሲያጎለብት ፤በውይይትና በመነጋገር የተደረሰበት ውሳኔ አይደለም፡፡ ለአማራውና ለብሔራዊ ምሁራን ክፍል የዘር ፌዴራሊዝም የጠነከረ አንድነት ያለው መንግስት ይፈጥራል፡፡እንደ ኦ ኤን ኤል ኤፍ (የኦጋዴን ነጻ አውጪ) እና ኦ ኤል ኤፍ (የኦሮሞ ነጻ አውጪ)የጎሳ ፌዴራሊዝም አርቲፊሻል ነው፡፡
ተጠያቂነትና ስልጣንን አለአግባብ መጠቀም የሰብአዊ መበት መደፈር፤ሙስና፤ ለሽግግር መንግስቱ ሌላ የሽግግር ሕገመንግስቱ መፍትሄ ሊያገኝለት የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው፡፡ይህ ደግሞ በቅርቡ የዩናይትድ እስቴትስ ባወጣው የሃገራት የሰብአዊ መብት አካሄድ በ2011 ባወጣው ዘገባ ላይ ተቀምጧል:
የኢህአዴግ (የገዢው ፓርቲ) አባልነት ለአባላቱ የሚያስገኘው የጠቀሜታ መጠን ሰፊ ነው፡፡ ገዢው ፓርቲ በርካታና መጠነ ሰፊ የሆኑ ስራዎችን ያካሂዳል፤በዚህ ሳቢያም ስራና የስራ ኮንትራት ውሎችን ለአባላቱ ብቻ ይሰጣል፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተደጋጋሚ እንዳነሱት የአካባቢ ባለስልጣናት ፓርቲያቸውን በመተው ወደ ኢህአዴግ ፓርቲ እንዲገቡና መንግስታዊ ድጋፍ ያለውን ማዳበርያ፤የእርዳታ ምግብ ተጠቃሚነትን፤የስራ እድል ማግኘትን፤እድገትን፤ተማሪዎችም በጥሩና ቅርባቸው ወደሆነው ዩኒቨርሲቲ መመደብን፤፤በመጀመርያ ዲግሪም ስራ የማግኘት እድልና ሌሎችም መንግስታዊ የሆኑ እድሎችን ማግኘት እንደሚችሉ ያግባቧቸዋል፡፡ አንዳንድ የመንግስት ባለስልጣናት የፕራይቬታይዜሽን ትግበራውን አለአግባብ ሲጠቀሙበትና ሲገለገሉበት ይታያሉ፡፡
በሕጉ መሰረት ይግል ንብረቶችን ለመመርመር ሕጋዊ ፈቃድ ማግኘት አለባቸው፤ በተግባር ፖሊሶች ይህን ሕግ ሲጥሱት እንጂ ሲያከብሩት አይታዩም፡፡ መንግስት የሚከፈላቸው አሳባቂዎች በመሰማራት በግለሰቦች ላይ ስለላ እንዲያካሂዱ ያደርጋል፡፡የደህንነት አባላት በመንግስት ለጥያቄ የሚፈለጉትን ቤተሰብ አባላት በማሰርና በማንገላታት ላይ ተሰማርቷል፡፡ ብሄራዊ መንግስታትና እና ሪጂናል መንግስቶች ‹‹የመንደር ምስረታ›› በሚል ጋምቤላ፤ ቤንሻንጉል፤ጉሙዝ፤እና ሶማልያ ክልሎች ውስጥ (እንደ ሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ) የስለላው አባላት ነዋሪዎችን በመደብደብ (ለሞት የተዳረጉም አሉ) ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ በማሰር በማጉላላት በመንደር ምስረታው ላይ ጣያቄ ያነሱትን ዝም ለማሰኘት ሞክረዋል፡፡በዚህም የተነሳ ሌሎቹ የአካባቢው አባላት አለመናገርን መርጠዋል፡፡ሕገ መንግስቱ ሃሳብን በነጻ መግለጽን የመናገር መብትን፤ የፕሬስ ነጻነትን ያወጀ ቢሆንም ገዢው ፓርቲና ልዩ ልዩ መዋቅሮቹ ግን በየቀኑ በየሰአቱ በየደቂቃው ይከበር እያሉ የሚጮሁለትን ሕገመንግስት ከማንም በባሰ መልኩ እየደፈሩትና እየጣሱት ይገኛሉ፡፡መንግስት አሁንም ጋዜጠኞችን አታሚዎችን ባለንብረቶቹን፤ኤዲተሮቹን በግብታዊ ውሳኔና በይሆናል አለያም ሌሎችን ዝም ለማሰኘት ያስራቸዋል፡፡ በየትምህርትቤቱና በዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቹ በኢህአዴግ መርህ መሰረት በአብዮታዊ ዴሞክራሲ እየታነጹ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የፈላጭ ቆራጭን የግፍ አገዛዝ መወድቅ ተከትሎ፤አብዛኛዎቹ የጉዳዩ ባለቤቶች በሽግግሩ ወቅት የሚያገለግል ሕገመንግስት እንዲቀረጽና የሚነሱትን አሳሳቢ ጉዳዮች ሁሉ የሚፈታ እንዲሆን መጠየቃቸው አይቀርም፡፡ በቅርቡ የፈላጭ ቆራጭን አገዛዝ ገርስሶ የጣለው በሰሜን አፍሪካ የተከናወነው ሂደት ለኢትዮጵያ የሚቸረው ትምህርት ካለ ሁሉንም የጉዳዩን አካላት ያካተተ ‹‹ባለ አደራ መንግስት›› መፍጠሩ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ በኔ አመለካከት ለዚህ አማራጭ የሚሆነው መጨረሻውን ጊዜ ከመጠበቅና ግብታዊ የሆነ ሁኔታ ከመፈጠሩ በፊት አሁኑኑ ውይይቱን(እኔ ቅድመ ውይይት የምለው) መጀመሩ ነው፡፡የተዋጣ የሽግግር ሂደት ለማምጣት እንዲቻልም በፓርቲዎችና በተደራጁ ሃይሎች ላይ የተወሰነ ሳይሆን ከሁሉም የሕብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ አባላት የታቀፉበት እንዲሆን ማድረጉ ተገቢ ነው፡፡
ከዲክታተር የጭቆና አገዛዝ የተላቀቁትን የአረብ ሃገራት የሽግግር ሁኔታ በመመልከት ኢትዮጵያ ብዙ ትምህርት ልትቀስም ትችላለች፡፡ቀዳሚውና ማነኛው ትምህርትም፤ሰፋ ያለና ዘላቂነት ያለው ቀጣይ ውይይት ሕገ ምንግስቱን በማዘጋጀቱ ርእስ ላይ ማካሄዱ ነው፡፡የአዲሲቱ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ቁልፍ ጭብጥ ምን ሊሆን ይገባል?ካለፉት መንግስታት የግዴት የዘርና የጎሳ አደረጃጀት ወጥተን አንድ ወጥ የሆነና የአንድነታችን መገለጫ ወደሆነ ስርአት እንዴት እንደርሳለን? በሕገመንግስቱ አቀራረጽ ላይ ተገቢ የሆነውን የዜግነት ድርሻቸውን ሊወጡ እንዲችሉ ሁሉንም የሕግረተሰብ ክፍሎች ማስተማርና መስገንዘብ የምንችለው እንዴት ነው፡፡ሁከሉም የዴሞክራሲ ተሟጋቾች በአንድነት የሚሰሩበትን መንገድ በማምጣት የሽግግር ሂደቱን ሰላማዊ ማድረግ የሚችሉበትን ሁኔታስ እንዴት ነው የምንፈጥረው?ውይይትና ድርድርንስ እንዴት እናካሂዳለን፡፡
ከፈላጭ ቆራጭ የአረመኔ አገዛዝ ውድቀት በኋላ የሕገ መንግስት አቀራረጽ
የቅርቡ ታሪክ እንደሚያሳየው ከሰሜን አፍሪካው የአረብ በቃኝ ባይነት ሕዝባዊና ሰላማዊ አመጽ ኢትዮጵያ የምታገኘው ትምህርት፤ከተለያዩ የጉዳዩ ባለቤቶች የተውጣጡ አባላት የተካተቱበት ‹‹የባለአደራ ምንግስት››መሰየም ነው፡፡ይህ አይነቱ መንግስት ደግሞ የሚመራበትና ስራውን የሚያከናውንበት የሽግግር ወቅት ሕገ መንግስት ያስፈልገዋል፡፡ይህም ዘላቂውንና ዋነኛውን የሃገሪቱን መመርያ ሕገመንግስት ለማርቀቅ ስለሚረዳውን በሂደቱም የሚነሱ ጥያቄዎችን መመለስ እንዲያስችለው ነው፡፡በኢትዮጵያ ስላለው ፈላጭ ቆራጭ የድንፋታና የግፍ አገዛዝ መውደቅ ተከትሎ ሌሎች አጋጣሚዎችም ሊታዩ ይችላሉ፤(እንደ ቀጥተኛ የሆነ የወታደራዊ ክፍል ጣልቃ ገብነት) እንደኔ እንደኔ ችግሩን እስኪከሰት ከመጠበቅ ወዲያውኑ ሁሉንም የሚያስማማ ውይይትና ድርድር ማካሄድ፡፡ የሕግ የበላይነትን ማእከል ያደረገ መንግስታዊ ስርአት ይመጣል የሚለውን መላ ምት ኢትዮጵያዊያን በአረቡ ሃገራት ከተካሄደው የዴሞክራሲያው ስርአተ መንግስት ግናባታ መማር የግድ ነው፡፡ በአረኑ ዓለም የበቃኝ ትግል ቅድመ ግንዛቤ ያልተወሰደበት ጉዳይ፤በሽግግሩ ወቅት የሕገመንግስቱን ማርቀቅና መመርመር ሃላፊነት ሊሸከም የሚገባው ማነው የሚለው ነው፡፡ የምእራቡ ዓለማት የሕገመንግስት አነዳደፍ ባለሙያዎች፤ችሎታና ብቃት ያላቸው ምሁራንና ጠበብት፤ የማስተማርያ ዶኩሜንቶች በገፍ፤በመላክ እንከን የለሽ ዴሞክራሲያዊ ስርአት እንዴት መገንባት ይቻላል ለሚለው እገዛ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡በፓርቲዎች የሚወከሉ ሃገራዊ የጉዳዩ ባለቤቶችእና ድርጅቶችበሽግግር መንግስቱና በደጋፊያቸው ወታደራዊ ክፍል ፈቃደኝነት መሰረት የተካፋይነት ሚና እንዲጫወቱ ይፈቀድላቸዋል፡፡ይህ አካሄድ ግን ሌላውን አብላጫ ቁጥር ያለውን ዜጋ፤የሲቪሉን ማህበረሰብ አካል፤እና ከስርመሰረቱ ያሉትን ዜጎች ድምጻቸው እንዲሰማና የውይይቱ አካል ሊሆኑ እንዲችሉ አላካተታቸውም፡፡ የዚህ አካሄድ ደግሞ በይበልጥ ባለቤት ያደረገው ምሁሩን ክፍል ብቻ በመሆኑ ተራው የዜጋ ክፍል የኔነትና የይገባኝ ጥያቄው ባለመመለሱ የራሱ አድርጎ አይቀበለውም፡፡ እርግጥ ቴክኒካል የሆኑ ርእሶች ስለሚነሱ የምሁሩ አስፈላጊነት አያጠያይቅም፡፡በአረቡ ዓለም እንደታየው ከሆነ ግን በኮሚቴው የተካተቱት ምሁራንና ሊቃውንት አማራጮችን በመክፈት በሕገመንግስቱ አቀራረጽ ሂደት እጅግም ጠቀሜታ ያለው ሁኔታ አልፈጠሩም፤ሰፊው ዜጋ ያለተሳተፈበትና ድምጹን በነጻና ዴሞክረሲያዊ በሆነ መንገድ በማሰማት ያልተሳተፈበት የሕገመንግስት አነዳደፍ የብዙሃኑን ፈቃደኝነት የሚያሳይ ሳይሆን የጥቂት አዋቂዎችና ተጠቃሚዎች ፈቃድ የሚያረጋግጥ ነው፡፡የሕገመንግስቱ ማርቀቅ ተግባር ለብዙሃኑ ዜጎች ተሳትፎ መንገድ መክፈት ይገባዋል፡፡
ለዚህ ማሰረጃ የሚሆነውም በአረቡ የበቃኝ ትግል ማግስት የታየው የሲቪል ማህበረሰቡን፤የብዙሃኑን ድርጅቶች፤ሴቶችን፤ ወጣቱን፤ያገለለ ነበር፡፡ሙባረክን መንግሎ ለመጣልና የፈላጭ ቆርጭ ስርአቱን ማክተሚያ በማምጣቱ ትግል ክፍተኛውን ሚና የተጫወቱትና ሕይወታቸውን የሰዉት ወጣቶች አጋር ተፋላሚዎች በማረቀቁ መንደር አለመታየታቸው አየስገርምም?
ኢትዮጵያ ከአረቡ የሽግግር ሕገመንግስት አቀራረጽ በመነሳት ሌሎች እጅግ አስፈላጊ የሆኑና ኢትዮጵያ ልትጠቀምበት የምትችላቸው ነጥቦች አሉ፡፡ በኢትዮጵያ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ድርጅቶች፤መሪዎች፤ምሁራን፤የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፤ በአንድነት ስርአት ያለው ፐሮግራም በመንደፍ ህብረተሰቡን ማስተማር፤ለዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ትምህርት፤ወሳኝና የተዋጣለት የዴሞክራሲያ ስርአተ ማሕበር ለመመስረት የሚረዳ ተግባር ማከናወን ይጠበቅባቸዋል፡፡ አሁን ስላለው ሕገመንገስት ጭላንጭሉ የሚታየውን ውይይተ በማዳበርና ይፋ በማውጣት በግልጽና በነጻነት ሕዝቡ እንዲነጋገርበትና ጥቅምና ጉዳቱን በመንቀስ በምትኩ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚያበቃ ሕገመንግስት መንደፍ አለባቸው፡፡ሕዝቡን በማስተማሩ ረገድ ተግባብተው፤ለአንድ ግብ በመቆም፤ተስማምተው ሊንቀሳቀሱ የግድ ነው፡፡



ለምን እዛው አዲስ አበባ አትሄድምና ህገምንግስቱን አትነድፍም::አለበለዚያ የዌብ ሳይት ወሬ ሁኖ ነው የሚቀር::የወረቀት ነብርተኝነት ለደሃ ህዝብ ዳቦ አይሆለትምና::
ሊቀ/ጠ አለማየሁ ገ/ማርያም ስለዘወትር የሀገር እና የሕዝብ አለኝታነታቸው በሚጽፏቸው ወቀታዊና መሰረታዊ ጠቃሚ ማብራሪያዎች,ማስተማሪያዎች,ማመሳከሪያዎች,ጠቃሚነታቸው የጋራ ነው::ጉዳዩ በጋራም ሆነ በተናጠል እንደ ዜጋ የሀገራችን ሁኔታ ይመለከተናል ኢትዮጵያ እንደ አንድ ሉዓላዊት ሀገር በጽናት መቀጠል አለባት ለሚሉ, ለገዢውም ፓርቲና ተከታዮቹም ቢሆን,ለተፎካካሪው የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች,ለሁለቱም ወገንና ጉዳዩን ከዳር ሆነው የሚታዘቡም ቢኖሩ ነገ ከማፈር እና ጥፋት ተደግሞ ሀገሪቱ የባሰ የድህነት አረንቋ ውስጥ ከመዘፈቋ በፊት እንደ አንድ ሕዝብ በጋራ ተሰባስበን ካለፈው ተምረን በዘር,በጎሳ,በሃይማኖት,በዕድሜ,በፅታ,በቋንቋ,በክልል ሳንገድብ ከወዲሁ መዘጋጀት እንዳለብን አስተምረዋል::
*”አጥብቆ ያሰረ ዘቅዝቆ ይሸከማል”!!ክቡር አለማየሁ ገ/ማርያም አድናቆቴና ምስጋናዬ እንደተለመደው ይድረስዎ !
የግለሰቡን መልካም ትምህርቶች ለአብዛኛው ኢትዮጵያዊ በሚረዳው መልኩ በመተርጎም ለተባብሩትም አመሰግናልሁ!
ሀገራችን ኢትዮጵያ የተሻለ አመራር ሰላም ብልጽግና ይግጠማት…አዲሱ ትውልድ ተማሪ ተመራማሪ ንቁ ይሁን !!!!
ኢትዮጵያ እጆቿን ዘርግታ ቅን አሳቢ ልጆቿን ትሰበስባለች!! አሜን በለው!ከሀገረ ካናዳ>>>>>>>>>>>>
@ትራስ
ከሌሎች ሃገሮች ተሞክሮ በመነሳት ለሃገራችን መጻኢ እድል ከሁኑ እንምከር ማለቱ መኑ ላይ ነው የወረቀት ነብርነቱ?ወያኔ ኑና ሕገ መንግስት አርቅቁ ብሎኮ አልጋበዘም ሂድ የምትለው? ችግሩ ዳቦ ነው መልካም አስተዳደር እጦት አይደለም ባይ ትመስላለህ በመልካም አስተዳደር እንዃን ችግርን መዋጋት እንዲህ ቀላል ነገር አይደለም
ስለ የትኛው ሕገ መንግሥት ነው የምናወራው? “ላም በሌለበት ኩበት ለቀማ” ነው የሚባለው? ሀገር የለን መንግሥት የለን:: የት ሆነን ነው ሕገ መንግሥት የምናረቀው????
የተከበሩ ፕ/አለማየሁ ከአሚሪካ እስከ አረቡ ዓለም የህገመንግስት ማርቀቅ አስፈላጊነት:ችግሮቹንና መፍትሂውን ገልጸውታል::
ወደ አገራችን ተመልሰው የፌድራል መንግስቱ ህገመንግስትና ችግሩ ለመዘርዘር ሞክረዋል::የሽግግር ህገመንግስት አስፈላጊነት ጠቅሰዋል::
በእኔ አስተሳስብ የመንግስት ችግር አሁን በአለው ሁኔታ የህገመንግስቱ ችግር አይደለም ያለው::ያለውን ህገመንግስት የማስከበር አቅምና ሃላፌነት መሽከም አለመቻል ዋናው ነው::ሁልተኛው ችግር የፌዳራል አወቃቀሩ ነው::መሰረታዊ ችግሩም የጎሳ ፌድራሊዝም በኢትዮጵያ መዘዙ በጥልቀት አለመጠናትና አማራጭ የፌድራል አወቃቀር አለመታየቱ ነው::የችግሩም ምንጭ የጎሳ ፖለቲካውና አተገባበሩ ነው::የፌዳራሉ አወቃቀር ከህጉ በፈት መጠናት የሚገባው ነው::ይህ ደግሞ በፖለቲከኞች ሳይሆን በሞያተኞች ተዘጋጅቶ ለህዝብ የሚቀርብ ነው::
ያለው የአገራችን ህግ የሚሻሻል እንዳለ ሁኖ ብዙ መልካም የሆኑ ህጎች ስላለው ያለውን ህገ መንግስት ማጠናከሩና መተግበሩ ይሻላል::ለሁሉም ወሳኙ ህዝቡ ስለሆነ በሂደት ይታያል::
እንደተረዳሁት በኢትዮጵያ የአርቡ ዓለም አብዮት ዓይነት በአገራችን ሊካሂድ ይችላል የሚል እምነት ያለው ይመስላል::ለዚህም እንዘጋጅ ነው::
በመጀመሪያ ይህ ዓይነት አብዮት የሚካሂድበት ሁኔታ የለም::ችግር ስለአለ ብቻ አብዮት ይመጣል ብሎ ማስብ የዋህነት ነው::ቢመጣም በቀላሉ የሚከሽፍ ነው:: ስለዚህ መነሳት የለበትም::ይህም ለመንግስት አያሰጋውም::
መንግስትን የሚያሰጋው ሊቋቋመው የማይችለው የጉሪላ ተዋጊ ነው::የሚሸነፈውም በጉሪላ ተዋጊ ነው::በዚህ ብዙ ዝርዝር ጥናትም የተካሂደበት ስለሆነ ለእርግጠኝነቱ አያጠራጥርም::ዋናው የህገ መንግስቱ ረቀቃ የሚወሰነው በዚሁ አይል ሊሆን ይችላል::ይህ እንዳይመጣና የተጅመረውም ልማት እንዳይቋረጥ መፍትሂ መፈለጉ ብልህነት ነው::
መንግስትም ከአለፉት የኢትዮጵያ መንግስታት አወዳደቅታሪክ ተምሮ ልብ ይስጠው::ደ/ካሳ/አጼ ቴዎድሮስ ራስ አሊ አሉላን በመፈንቅለ መንግስት አባረው ስልጣን ሲጨብጡ ጠንካራ የማይበገር ሰራዊት ነበራቸው::የመሽ ጊዜ ብቻቸውን ሁነው ሞቱ::
አጼ ዮሃንስ ጠንካራ ሰራዊት ነበራቸው የመሸ ጊዜ ሬሳቸውን እንኳ ማስጣል ሳይችል ቀርቶ በአሳፋሪ ሁኔታ ተበተነ::
አጼ ሃ/ በዱርየ ወታደሮቻቸው ተዋርደው ሞቱ::ኮ/መንግስቱ ይሳሳለትና ይመካበት የነበረው ሰራዊት ሲመሽበት ራሱን እንኳ መከላከል አቅቶት ተበተነ::አቶ መልስ ይህን በድንብ ተረድተው ሳይመሽ ለአገራቸውም ለተከታዮቻቸውም ሲሉ መፍትሂ ያፈላልጋሉ የሚል እምነት አለኝ::
በአንዳንድ ተቀዋሚዎች ባህር ማዶ ተቀምጠው ምነው ህዝቡ ፈራ እያሉ በህልማቸው መንግስት በአመጽ ወርዶ ወደ በትረ ስልጣን ለመምጣትቻርተር አውሮፕላን ባይጠብቁ ይመረጣል ይህንም አስተሳስብ መሰረዝ አለባቸው::
ፕ/አለማየሁ ከጠቀሱት ህዝቡን ስለህገመንግስት ማስተማር የሚለው ሲያግባባን ህገመንግስት ማርቀቅ የሚለው አያስኪድም::
ለዚህ ገንዘብም ጉልበትም ከማባከን በሌላ ስራ መዋሉ ይሻላል::ህዝቡም ያለው አገርቤት ስለሆነ አመችም አይደለም::
ከመንግስት ጋር በመነጋገርና በመከራከር የሚመጣ መፍትሂ ከአለም መመልከቱ ጥሩ ነው::ይህም አንዱ የትግል ስልት አንዱ ነው::ምን ሊቀድም እንደሚችል ማስብም ያሻል::
@በላይነሽ
ባልሽው ነገር በተወሰነ እስማማለሁኝ፡፡
ህግ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ህግ ያን ያህል ለሰው ልጅ አዲስ ነገር አይደለም፡፡ማለትም ከህገ-ልቦና ጀምሮ ከፈጣሪ ለሙሴ የተሰጠውን የአስርቱን ህግጋት ጭምር ማለት ነው፡፡ነገር ግን የሰው ለጅ ይህንን አድርግ ያንን አታድርግ እየተባለ በህግ ብቻ ሊኖር ስለማይችል ከዚያ በክርስትና ለሚያምኑት የሃዲስ ኪዳንና በእየሱስ ክርስቶስ የማመንና በፀጋውና በፍቅሩ (በፍቅር ህግ)የመኖር አስፈላጊነት መጣ፡፡ስለዚህም ህግ የሚባለው ነገር ያን ያህል አዲስ ነገር አይደለም፡፡ችግሩ ያለው የህግና የደንብ ትብታብ ከመፍጠርና ከመደርደሩ ላይ ሳይሆን ምን አይነት እሴቶች(Virtues and values) አሉን የሚለውን በጥልቀትና በስፋት ከመረዳት ላይ ብናተኩር ጭምር መልካም ነበር፡፡መለስ/ወያኔ ያወጡትን ህግ እራሳቸው እኮ ለማክበርና ለመተግበር አልቻሉም፡፡እንዲያውም ህገ-ወጥ ስራን በህግ ሽፋን ነው እየተገበሩት ያሉት፡፡አንድን ሊያጠቁት ወይንም ሊጠቅሙት ለሚፈልጉት አካል ብቻ ሲሉ ህግን ያወጣሉ ህግን ይሽራሉ፡፡ውድ እህቴ በላይነሽ ሆይ ክቡር የሆነው የሰው ልጅ በህግ ትብታብ ብቻ አይኖርም አይመራም፡፡አየሽ አንድ የሆነ የዝቅጠት ጎዳና ውስጥ እየሄድን ነው፡፡መፍትሄው ደግሞ ከዚህ የዝቅጠት ጎዳና ወደ ጤናማው ጎዳና መመለስ እንጂ ሰላሳ ሺህ የህግ ዲሪቶ መደርደር ብቻውን መፍትሄ ሊሆን አይችልም፡፡ህገ-መንግስታዊ ዲሞክራሲ ብሎ ፀሃፊው አቀረበ ለመሆኑ በህገ-መንግስት ያልተደገፈ ዲሞክራሲ በየት ሀገር ነው ያለው፡፡እንኳንስ በዘመናችን ትልቅ አጀንዳ እየሆነ እየተራገበ ያለውን ዲሞክራሲን አይደለም ለሌላም አነስተኛ ነገር ሁሉ በህገ-መንገስቱ ውስጥ ያልተፃፈ ነገር የለም፡፡እንደዚህ አይነት ነገር ልክ በቃ አንቺ እኔ በተሰማራንበት የስራ መስክ ላይ ስራችንን በትክክል በቀናነትና በትጋት ለመስራታችን ሁል ጊዜ በሰዓት ፊርማ ለመቆጣጠር የመሞከር ያህል ነው፡፡
እንዲያውም የህግ ድሪቶ ሲባዛ በተዘዋዋሪ የሚያሳየው ነገር አንድ ጥልቅና ሰፊ የሆነ ችግር መኖሩን ነው፡፡ነገሩ ሁሉ ብቻ የማይተማመን ባልንጀራ በየወንዙ ይማማላል አይነት ነው፡፡የዚህች ሀገር ችግር የህገ-መንግስት ችግር አይደለም፡፡የዚህች ሀገር ችግር ማን ስልጣን ላይ ወጣ ማን ወረደ የሚለው ብቻ አይደለም፡፡እንደ ሀገር እንደ ህዝብ እንደ ትውልድ አንድ የሆነ ስር የሰደደና የተስፋፋ አጠቃላይ የትውልድ ዝቅጠት ውስጥ ነው ያለነው፡፡አንድ የሆነ ወሳኝ ነገር ከውስጣችን እንደጎደለብን ይሰማኛል፡፡ዘለቄታዊ መፍትሄው ደግሞ ያንን ነገር በጥልቀትና በስፋት መርምሮ መረዳት ነው፡፡እኔ ህግ አያስፈልግም እያልኩኝ አይደለም፡፡ነገር ግን የሰው ልጅ በህግ ብቻ ሳይሆን ወሳኝ የመንፈስ ፍሬ በሆኑት ፍቅር መተማመን ሰላም ተስፋ ትህትና እራስን መግዛት ወዘተ የሆኑት ፀጋዎችን ከተገፈፈ እንደ ሙሉ ሰው ሊቆጠር አይችልም፡፡እንደሚታወቀው አንድ በሀኪም የታዘዘ መድሃኒት ለመውሰድ እንኳን አንድ የተወሰነ ምግብ ቅድሚያ መመገብ ይኖርብናል፡፡ያለበለዚያ መድሃኒቱ ሊጎዳን ይችላልና፡፡እንደዚሁም በመንፈሱ የተጎዳና መንፈሱ የዛለን ማህበረሰብ በህግ ጋጋታ ብቻ ለማኖርና ለመምራት ይከብዳል፡፡ወጣቱ ትውልድ ራእይ ያለው እንዲሆን ካልተደረገና ስራ ካልተፈጠረለትና ተስፋ ያለው እንዲሆን ካልሆነና ለምግባረ-ብልሹነት የሚያጋልጡት ነገሮች ሳይወገዱለት ለህይወትህ ወጋ በመስጠት ከኤድስ ለመከላከል ለመልካም ህይወት ኮንዶም ተጠቀም እያልን ዘወትር ብንለፈልፍ ዋጋ ያለው ነገር አይንሆንም፡፡ዛሬ የመለስ/ወያኔ ስርዓት ለወጣቱ ትውልድ ራእይን ተስፋንና ስራን ሳይሆን መጤ ባህል ኮንዶምና ጫት ነው ያቀረቡለት፡፡ምናልባት ህግ ያጠኑ ሰዎች ሀገር በህግ ብቻ የምትቀናና የምትመራ ሊመስላቸው ይችላል፡፡ካሁኑ ያነሰ ህገ-መንግስት ባልነበረበት በንጉሱ ዘመን እንኳን በህግ-አምላክ ሲባል ሰው ለህግ የተለየ አክብሮትና ተገዥነት ነበረው፡፡የእኔ እመቤት በዛሬው ዘመን ደግሞ ህገ-ወጥ ስራ የሚሰራው እንዲያውም ህግን ሽፋን ተደርጎ እየሆነ ነው ከዚህ በመነጭም ሰው እየሰለጠነ ሳይሆን እየሰየጠነ የመጣ ጭምር ነው የሚመስለው፡፡ለምሳሌ ክፋትን ስግብግብነትን ጥላቻን ከልክ በላይ ያለ ራስ ወዳድነትን በየትኛው ህግ ነው የምንከላከለው?በህግ ክፉ ነገሮችን ለመቅጣት ብንችልም ቅሉ ግን መልካም ነገሮችን ሁሉ ያን ያህል በህግ አናመጣቸውም፡፡ምናልባት ፀሃፊው ህገ-መንግስታዊ ዲሞክራሲ ብለው ሲሉ አሁን ባለው የኢትዮጰያ ህግ ውስጥ የሌለው ዋና ወሳኝ ነገር እንደ መለስ አይነት አንድ ስልጣን ላይ የወጣ ግለሰብ የስልጣን ዘመኑን የሚገድብ ነገር ነው ሊሆን የሚችለው፡፡
ከዚህ ውጪ እና ከአንዳንድ መለስተኛ ነገሮች ውጪ አሁንም ባለው ህገ-መንግስት ውስጥ ብዙ መልካም የሆኑ ሊያሰሩ የሚችሉ ህጎች አሉ ችግሩ ግን ህጉ የወረቀት ላይ አንበሳ ብቻ ሆነ እንጂ፡፡
ስለዚህም መልካም እሴቶች(Intrinsic virtues and values) በሌሉበት ሀገር ውስጥ የህግ ድሪቶ ብቻውን በራሱ ምንም የሚቀይረው ነገር የለም፡፡በዘመነ መለስ/ወያኔ ልክ እንደ ዘረኝነትና ቅጥረኛነት ሁሉ ዝርፊያውና ሙስናው ዛሬ እንዲህ የስርዓቱ አንዱ ዋና መገለጫ ባህሪ እየሆነ ሊመጣ ነገር ግን ይህ ስርዓት ህዝብን ለማምታታት አስቀድሞ የፀረ-ሙስና ኮሚሽን መመስረቱ እጅግ የሚገርም የሚደነቅ ነገር ነው፡፡ህገ-ወጥ ስራን ለመስራት ህጋዊ ሆኖ መቅረብ ይህ ነው፡፡መለስ/ወያኔ አስቀድሞ ከበረሃ ሲነሳ አንዱ እቅዱ ይህችን ሀገር መዝረፍና እርቃኗን ማስቀረት ነው፡፡አሁን በሀገራችን ያለው ነገር ግን በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ የኑሮ ውድነትም የዚህ የመዝረፍ ዋና አካል ነው፡፡ነገር ግን ይህ አይነት አሳፋሪና አስነዋሪ ስርዓት ግን የበግ ለመድ የለበሰ ተኩላነቱን ለመሸሸግ በህገ-መንግስት ጭንብል ውስጥ ላለፉት 21 ዓመታት ለመደበቅና ለመንቀሳቀስ አልከበደውም፡፡አሁን ያለው የኢትዮጵያ ችግር ደግሞ ዝም ብሎ ያለ የዲሞክራሲ እጦትና የተራ የአምባገነንነት ችግር ብቻ አይደለም፡፡ኢትዮጵያ ዛሬ መለስ/ወያኔ በሚባል ቅጥረኛ ሃይል አመካኝነት እጅግ በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ ዘመናዊ የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት ውስጥ ነው ያለችው፡፡መለስ/ወያኔ ዛሬ ህዝቡን እየዘረፈ በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ የኑሮ ውድነትና በዚህ የተነሳ ከፍተኛ የሆነ ስነ-ልቦናዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ጭንቀት ርሃብ አለመረጋጋት ቀውስ ውስጥ ነው እየከተተው ያለው፡፡በደርግም ሆነ በንጉሱ የመውደቂያቸው ሰዓት እንኳን ይህ አይነት ሁኔታ ፈፅሞ አልታየም፡፡ስለዚህም ዛሬ ሀገሪቱ በባእድ ሃይል የምትገዛ ነው የሚመስለው፡፡ማንም አምባገነናዊ አገዛዝ የህዝቡን የመናገር የመሰብሰብ ወዘተ የተለመደ ሰብዓዊ ነፃነት በአምባገነንነት ያፍናል ይህም የትም ያለ ነገር ነው፡፡ ነገር ግን አንድ አገዛዝ የገዛ ሀገሩን ህዝብ በበቀል ስሜት በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ በሃይለኛው በኢኮኖሚ ሲቀጣና በዚህም የተነሳ በርሃብ ሲቀጣ ሲያስጨንቅ በታሪክ አልታየም አልተሰማም፡፡ስለዚህም ከዚህ አረመኔ ስርዓት ጋር የመስማማ ፅሁፎች ቢወጡ መልካም ነው፡፡ባብዛኛው የሚወጡት ፅሁፎች የስርዓቱን አስከፊነት አረመኔነት ዘራፊነት በትክክል የሚገልፁ አይደሉም፡፡ይህ የመለስ/ወያኔ ስርዓት በታሪክ ፈፅሞ ታይቶ የማይታወቅ ፈፅሞ ፀረ-ኢትዮጵያ ፀረ-ኢትዮጵያዊነትና ፀረ-ኢትዮጵያውያን ነው፡፡ወደድንም ጠላንም አመንም አለማንም ሀገሪቱ የባእዳን ቅጥረኛ በሆነ አገዛዝ ውስጥ ባለ የተዘዋዋሪ የዘመናዊ ቅኝ-ግዛት ውስጥ ነው ያለችው፡፡
ህዝብ በኑሮ ውድነትና በርሃብ እያለቀ ከህዝብ ጉሮሮ እየነጠቁ ኤክስፖርት ማድረግና በዚህም ጥቂቶች የስርዓቱ ሰዎች እንዲጠቀሙና በብዙሃኑ ስቃይ ሀብት ማፍራትና የተንደላቀቀ ኑሮ እንዲኖሩ ማድረግ ከዘመናዊ ቅኝ ግዛት የሚለይ አይደለም፡፡መለስ/ወያኔ ከምርጫ 97 ወዲህ ስልጣኔን እንዳሰብኩት ሳይሆን ቀርቶ በማንኛውም ሰዓት ልለቅ እችላለሁኝ ብሎ ስለደነገጠ ዛሬ የሀገሪቱን አንጡራ ሀብት በሚችለው አቅም ሁሉ በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ እየዘረፈ ነው፡፡የብር ዋጋ ማጣትና የገንዘብ ግሽበቱና ይህንንም ተከትሎ ያለው በታሪክ ያልታየ የኑሮ ውድነትና የብዙሃኑ ድህነት መንስኤውም ይህ የረቀቀና የተቀነባበረ የመለስ/ወያኔ የዝርፊያ አካል ነው፡፡ዛሬ ሀገሪቱ የጠገቡም ሆነ ያልጠገቡ ጅቦች ከሩቅ ጭምር እየተጠራሩ የሚቦጭቁባት ሀገር ናት፡፡መለስ/ወያኔ በባእዳን ሃይሎች የረቀቀና የተቀነባበረ ምክር እየተረዱ ይህንን አይነት በታሪክ ያልታየ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ ቀውስና አለመረጋጋት ከቆሰቆሱና ካቀጣጠሉ በኋላ የመጨረሻ ግባቸው(ይሳካም አይሳካም ፈጣሪ ብቻ ነው በእርግጠኝነት የሚያውቀው) በዚህ ጦስ የተነሳ ሀገሪቱ እንደ ዩጎዝላቭያ ሶማሊያ እንድትበታተን ለማድረግ ነው፡፡በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ እየተደገሰ ያለው የጣፋት ድግስና የአየሩ ሽታ ይህንን የሚያሳብቅ ነገር ነው፡፡አንድን ሀገርና ህዝብ በሂደት ለማዳከምና ለመበታተን የግድ ጦር ማዝመት አይጠበቅም፡፡ስለዚህም ይህ አይነት ጡዘት ያለበት ሆነኝ ተብሎ የሚተገበር ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ ቀውስ ሁል ጊዜ የመጨረሻ ግቡና አላማው ሀገር ለማዳከምና ለመበታተን ሲታቀድ ነው፡፡
ስለዚህም መለስ በተዘዋዋሪ የዚህችን ታሪካዊ ሀገር መልካምና ጥንካሬ የማይወዱ ጥርስ የነከሱ የባእዳን ሃይሎችን አጀንዳ በመሳሪያነት እያስፈፀሙ ነው፡፡መለስ የማህበራዊና የኢኮኖሚው ቀውሱ ከእለት እለት እየተባባሰ በሄደ ቁጥር ችግሩ 11 በመቶ ያለው የኢኮኖሚው እድገት የፈጠረው ስለሆነ መፍትሄውም የኢኮኖሚው እድገት ነው ስለዚህም እሱን ለሚቀጥለው 20 ዓመት መካከለኛ ገቢ ውስጥ እስክንገባ ድረስ እንጠበቅ እያሉን እንደ ህፃን ልጅ እየቀለዱብን፡፡እድገቱ ግን እሳቸው ባለቤታቸው አዜብ ወያኔዎችና ተከታዮቸው ከሀገርና ከህዝብ እየዘረፉ በሚያከማቹት የሀብት መጠን የሚለካ ነው፡፡ይህንን አይነት እድገትም አልካድንም፡፡እንደዚሁም ለራሳቸው ለወያኔዎች ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥቅም ሲባል በባእዳን ሃይሎች ለሚሰጠው እርዳታና ብድርም እንደ ውለታ ምላሽ ሲባል ኢትዮጵያዊ ገበሬ ከመሬቱ እየተፈናቀለ እየተሰደደ በምትኩ መሬት ለባእዳን ሃሎች እየተሰጠ ነው፡፡ ስለዚህም ዛሬ ሀገሪቱ የተዘዋዋሪ ቅኝ-ግዛት ውስጥ ነች፡፡እውነታው ይህ ሆኖ እያለ ችግሩ የዲሞክራሲ መጥፋት ወይንም የተለመደው የአምባገነንነት ጉዳይ እንደሆነ አድርጎ ማቅረብም በካንሰር ወይንም በኤድስ የተጠቃን በሽተኛ ልክ በጉንፋን ወይንም በራስ ምታት እንደታመመ አድርጎ በተሳሳተ መንገድ ማቅረብና በዚህም እይታ መፍትሄ እንደመፈለግ ይቆጠራል፡፡ብዙዎቹ ፀሃፍትና ምሁራን በዘመነ መለስ/ወያኔ ያለውን ውሰብስብና አደገኛ ችግር በቅጡ ተረድተው ተገቢውን መፍትሄ ከመጠቆም ወይንም ከመስጠት ይልቅ ነገሩን ማድበስበስና ለራሳቸው በሚመችና በማይጎረብጥ አካሄድ የማይሆን ምሁራዊ ትንተና ለመስጠት ነው እየፈለጉ ያሉት፡፡አንዳንዶችም ነገሮችን የሚያድበሰብሱትና ከነባራዊው ሁኔታ የማይጣጣም እርባና ቢስ ፅሁፍ የሚያቀርቡትም በተዘዋዋሪ መፍትሄው የሚጠይቀውን ተገቢውን መስዋእትነት ላለመክፈልና እንደ ጲላጦስ ከደሙ ንፁህ ነኝ በማለት ከሃላፊነት ለመሸሽ ጭምር ይመስላል፡፡
ስለዚህም ዛሬ ኢትዮጵያ የተለመደው አይነት ምሁራዊ ፖለቲካዊ ትንተና ብቻ ሳይሆን የምትፈልገው ይበልጥኑ ተግባራዊ እርምጃ የሚወስዱ ቆራጥ ልባም ሰዎችን ነው፡፡መለስ/ወያኔ ላለፉት 40 ዓመታት ያህል እየሰሩ ያለው ሀገር የማጥፋት ስራ እኮ ባብዛኛው ካለማወቅ የመነጨ ሳይሆን ሆነኝ ተብሎ በረሃ ጭምር እያሉ የታሰበበት ነገር ነው፡፡ስለ ኑሮውድነቱ ምሁራዊ የተለመደውን የኢኮኖሚ ትንተና መስጠትም ጉንጭ አልፋ ከመሆን ያለፈ አይደለም፡፡እናም ነገሮች በምሁሩ ዘንድ ያለው ነገር ሁሉ ባብዛኛው ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ እየሆነ ነው፡፡ያን ያህል ያልሰማነው የማናውቀው አዲስ ነገር የለም፡፡እረ ጎበዝ ቅጥረኛው ዘረኛው ዘራፊው መለስ/ወያኔ ሀገር እያጠፋና እያተራመሰ እስከመቼ ህገ-መንግስታዊ ዲሞክራሲ ወዘተ እያልን ከተጨባጩ ነገር ጋር ያልተጣጣመና የማይሆን ምሁራዊ ትንተና ስነሰጥ እንኖራለን እረ፡፡ስለዚህም አሁን ኢትዮጵያ ከመለስ/ወያኔ መንጋጋ ለመላቀቅ የሚያስፈልጋት በከንቱ ቁጭ ብሎ በአእምሮው የሚፈላሰፍ እንደ እኔ አይነትና መሰል ምሁር ሳይሆን ልባምና ቆፍጣና ወታደርና ህዝብ ነው፡፡
አቶ መልካሙ አመስግናለሁ:: ቆንጆ አቀራረብና ትንታኔ ነው::
ችግር ጅግንነትን ይፈጥራል::ችግር ብልሃትንና ጥበብን ይፈጥራል::ችግር የፈጠራቸው ጅግንነትም ሆነ ጥበብ ለሰው ልጆች ብርሃንን ይፈጣራሉ::እኛም ችገርን በድንብ አላጣጣምነውም ቀመስነው እንጂ::ስንራብ ሰንዴ እንረዳለን::ርሃቡም ሁሉንም አልነበረም የሚያጠቃው:: መንግስቶቻችን የሚጨቁኑን መለስተኛ ጭቆና ስለነበር ጭቆናና ዘረኝነት አስከፌነቱ አልገባንም ነበር::
አሁን ሁሉም እየገባን ስለሆነ ከምንጊዜውም በበለጠ ሁሉም መፍትሂ ፍለጋ እየሮጠ ነው::
መንግስትን ማሸነፍ ቀላል ነው::መገንባት እንጂ ማፍረስ አይቸግርም::ከባዱ ከተሽነፈ (ከፈረስ)በኋላ ምን ሊመጣ ይችላል? በሚል ሃሳብና ሃላፌነቱን በመፍራት ነበር::ይህ በደንብ ቁልጭ ብሎ በዝርዝር ጥናት እየተካሂደበት ያለ ነገር ነው::
ብዙ ነገሮች እየተስተካከሉ ስለሆነ በሂደት ይታያል::ከሁሉ በፈት የመንግስት ስልጣን የጨበጡት ወገኖች አስበውበት እስረኛውን ሁሉንም ፈትተው ነጻ ምርጫ የሚካሂድበት መፍትሂ ፍልጋው ቢጠናከር ጎን ለጎን ለሁሉም ይበጃል::
በመንግስት በኩል ያሉት ኢትዮጵያዊ ወግኖቻችን ስለሆኑ ቢያስቡበት ይበጃል::
እኔም አመሰግናለሁ አቶ መልካሙ ጥሩ አስተያየት ነው፡፡ልብ ያለው ልብ ይበል
አቶ ያለማየኡ እጅግ የማከብሮት ምሁር ኖት እውቀቶን ተጀቡነው እኔ ከድላኝ ምን ቸገረኝ ሳይሉ መከራወን እያሳየ ያለን መንግስት ካማጋለጥ ወደዋላ ያሉበት ጊዜ አንድም አልነበረም. ቢትዮጲያ ህዝብ ዘንድ እጅግ ታላቅ ፍቅር እና አክብሮት አለዎት እናም በርቱልን የወያኔን አስተያየት ትራሽ እያረጉ ትግሎን ይቀጥሉ. በላይነሽ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ “በመንግስት በኩል ያሉት ኢትይጲያዊ ወገኖቻችን ስለሆኑ ቢያስቡበት ይበጃል” በለው!!!!! እሺ ለዚህ ለዚህ ታድያ መለስን እና ፓርቲውወን ለምን እንቅወማለን???????? ያው ኢትዮጲያዊ አይደሉ?????? ከመንግስት ጋር የቆሙት ኢትዮጲያው ስለሆኑ????? እነመለስም እኮ ኢትዮጲያዊ ናቸው. በግለሰብም ሆነ ከመንግስት ስር በመሆን አገረን የሚያጠፋ እና የሚያደቅ ህዝብን የሚጎዳ እስከሆነ ድረስ ያ ሰውም ሆነ ድረጀት ጠላት ነው. ተላትን ደሞ ከጥፋቱ እንዲቆም መታገል ነው እንጂ ኢትይኦፒያዊ ነው ብለን …….. በተረፈ አቶ አለማየሁ እጅግ ልዩ ሰው ኖት በርግጥ ድንቅ ኖት በረቱልን!!!!!!!!!!!!!
ማራማዊት ኢትዮጵያዊ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ናቸው ማለት ሁላችንም ያንድ አገር ልጆች ስለሆን እርስበርስ መገዳደላችንን ትተን በሰላም አብረን አገራችንን ማሳደጋ እንዳለብን ለመጠቆም ነው::ዙሮ ዙሮ በሃይል መንግስት ቢቀየር እንኳ እነሱም እኛም ሁነን ነው ይህችን አገር መልስን የምንገነባው::
ማራማዊት ምንጊዜም በየትኛውም ቦታ ቁመሽ ፍቅርን አስቢ::ለመንግስት አካላትም ሆነ ተከታዮቹ ከዚህም ቤት ፍቅር እንዳለ አስተምሪ::ወታደሮች በውጊያ ላይ እያሉ እንኳን ፍቅርን ነው የሚስብኩት:እርህራሂን ነው የሚያሳዩት::ፍቅርንና እርህራሂን ያላሳየ ሁሉ አሽንፎም አያውቅም ቢያሽንፍም ጊዜያዊ ነው::ጥላት የሚሽነፈው በፍቅርም ጭምር ነው::
በዓለም ላይ ፍጹም ጥላትና ወዳጅ የለም::ሁለቱም ይቀያየራሉ::ኢ.ህ.አ.ድ.ግ ሃሳቡን ቀይሮ በቀና አስተሳስብ እስረኞችን ፈትቶ በስላም የምርጫ ሚዳ ከአዘጋጅ አሁን ያለው ሁኔታ ሊቀየር ይችላል::
በቅድሚያ ለፕሮፌሰር ያለኝን አክብሮት አድንቆት እና ጀግንነት አደንቃለው. ከዛም ማራማዊት ደስ የሚል አጭር የመልስ ምትሽ ደስ ይላል. ሁሌም አስተያየትሽ ሸቀቅ ያለ ነው. በጣም እናውቃለን ባዮችን ሁሌ የመልስ ምትሽ ይመቸኛል. ነገር ግን ብዙ ጊዜ አትሳተፊም .ለምን???? አንዴ ለተስፋዬ ገብርሃብ የሰጠሽው መልስ አይረሳኝም. ተስፋዬ እራሱ በሰጠው ታስተየት ላይ ጻህፊወን አይለኛ መስቀለኛ ነገር ውስጥ የሚከት ጥያቄ መሳይ ትችት በጻፈ ጊዜ እኔም ተገረሜ ነበር ሌሎችም አንድ ሁለት ሰዎች ተስፋዬ በጻፈው ላይ በትችቱ ተደንቀው አስተያየት በጻፉት ላይ. ማራማዊት ደሞ ወገን ምን ነካን . እንዲህ ከሆነማ እንዴት እንዲህ ሆነ??? ነገር እና ተስፋዬ ይህን ያለበት ምክንያት እንዴት ተሰወራችው እንዲህ ነው የሚል ብቻ ነገር በትክክል አልስታውሰወም ነገር ቁጭ የሚያረገው መልስ መስጠቷ እጅግ ሳደንቃት ነበር. አሁንም ደስ የሚል መለስ. ጠላት እስከሆነ ድረስ ……….. ለዚህ ለዚህማ አቶ መለስም ፓርቲውም ኢትይኦፒያዊ ናቸው. ወንድ!!!!!!!!!!!ሌላው በላይነሽ ላርምሽ እና ችግር ስላለ አብዮት ይመጣል ብሎ ማሰብ ሞኘት ነው ያልሽው , በመሰረቱ ለአብዮት ትልቁ ነንደአንደኛው ምክንያት ችግር ነው. 2ተኛየተጀመረው ልማት እንዳይቋረጥ ያልሽው አሳቀኝ. ማንም መንግስት ቢመጣ ልማቱን ይቀጥላል. ችግር ይኖራል. ሌላው ይህ መንግስት ልማት የጀመረው ከኪሱ አይደለም ለልማት የሚገባ ገንዘብ አለ ያ ደሞ ብዙን እያሸሸ ጥቂቱን ያውላል እያቃረው ሳይወድ በግዱ. ለምን ይጠየቃልና. እናም ህዝቡ የነጻነት አየር ያግኝ, ህዝቡ ጠግቦ ይብላ ዋናው የሰው ልጅ ክብር ይቀድማል . መንግስታቶች ሲሸነፉ ወታደሮቻቸው ይሸሻል ያልሽው ምንም አይደንቅም ኖርማል ነው እንዳጋነንሽወም አይደለም የተቻላችወን የሞከሩም አሉ.ቀፎ ሲመታ ንቦች ተበተኑ ብለን መደነቅ የለብንም .መሪ ከተመታ ተስፋ የሌለወ ነገር ነው ብዙ ጊዜ , የደረግ ወታደር እንደተፈራወም ባይሆን ትንሽ ተፋጠዋል የትም እንደማያደረስ ሲታወ ቅ ያለው እድል መሸሽ ወይምከጅ መስጠት. ለምን ይሙቱ???? ሁሉም ማለቅ አለባቸው ብሎ ነገር አስቂኝ ነው. ማን ያውቃል ለዳግም ድል ይሰለፉ ይሆናል ለምሳሌ ከሚሞቱ ከሌላ ተቃዋሚ ጎን በመሆን የግል አስተዋጽ ማረግ ይችላሉ. ሌላው በጣም ያሳቀኝ ነገር አቶ መለስ ይህን በደንብ ተረድተው ሳይመሽ ለአገራቸው ለተከታይቻቸው ሲሉ መፍቴህ ያፈላልጋሉ ያልሽው አንድ በጣም የዋህ ነሽ. ወይም ደሞ በመለስ የሚጨክን ልብ የለሽም እንጂ በግልጽ የተናገሩትን አሁን አንቺ እዚህ ምን እያልሽ ነው???? እኛ ከሌለን አገሪቷ አትኖረም ያሏት ቅኔ አልገባሽም ለነጮቹ በደንብ የሚመራት የለም የሚል መልህክት ሲሆን ለኛ ደሞ የደም ምድር ትሆናለች ነው. ለምሳሌ ልንገረሽ ቅንጅት አዲስ አበባን ሊረከብ ሲል ምን አረጉ??????? አዲስ አበባ የኦሮሞ ነው አዲስ አበባ ኦሮሚያ ናት አሉ እስከዛሬ ያያሉትን ኦነግ አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት ብሎ ሲንቀሳቀስ አይደለችም ብሎ ቀንዱን መቶት ነበር አሁን ግን ልንለቅ ነው ብለው ህዝብን የአዲስ አበባን ህዝብ በዝረራ ስለጣልቸው ደም ለማፈሰስ ኦነግን ያንተ ናት አሉ ሲ????ክፋታቸው እንዚህ ሰዎች እጅግ እባቦች ናቸው እንዲህ የዋህ ካገኙ. ቅንጀት ደሞ ክፋታቸእን በደንብ ስላወቁ እንረከብም ብለው ቁጭ ወያኔ ያን ብቻ አይደለም ወስጥ ውስጡን ብዙ ነገር ሰራ .ቅንጀት ይረከባል ብሎ መልሶ መከራወን አየ እናም የኔ እህት ለአገራቸው መፍቴህ ያፈላልጋሉ ያልሽው አሳቀኝ. እሳቸው አገሬ ብለው የማይቁትን????? የምታቂ ይመስልሻል ብዙ ነገር ትሳሳቻለሽ እና አሁን አንቺ ነሽ የእኝህን ምሁር የምትጋፊው???? በይ አታድክሚን.
መራማዊት!
በላይነሽ!
ተዳከማችሁ ሳ! ዋይ!አነ ግን ልቤ ሸረር አይልም፤ጂኒ ነኛ!
ምሁሩ ምን አሉ? እንዘጋጅ አሉ። ለሽግግሩ የሽግግር ሕገ መንግስት አሉ። ታዲያ ይንደፉታ!!! ለህዝባቸው ያላቸውን ፍቅር በቃልና በአንደበት ሳይሆን በተግባርና በውነት ይግለጡታ!!!ይንደፉታ!!!
ፕሮፌሰሮች ብዙ መፃፍ ይወዳሉ፤ በተለይ የኛዎቹ። ብዙ በመፃፍ ህዝብን አቅጣጫ ያሳዩ እየመሰላቸው!!!ክስተት እየተከተሉ ይነፍሳሉ። ቆም ብለው አያስቡም።’የብርቱካን አብዮት’ በምሥራቅ አውሮፓ ተነሳ።በኛም እንደዛ ይሆናል ብለው ብዙ አሉ። የዐረብ ዐመፅ ታየ፤ ተዘጋጁ አሉ። ቆም ብለው ሳያስቡ።
እናንት የተዳከማችሁ እህቶች! እስቲ ልጠይቃችሁ።ሊበራል ዲሞክራሲ የጠበቀ ነገር አይስማማውም።ማህረሰቦችና ብሔረሰቦች የራሳችን መንግስት ይኑረን ቢሉ፤ ዳርቻ ላይ ያሉ ማህበረሰቦች ከአጎራባች ሃገሮች ካሉ ወገኖቻችን እንቀላቀላለን ቢሉ እምቢ፤
አይደረግም አይልም።ባህርዩ እንደዛ አይደለምና።ለመሆኑ እናንተና በዐለም የተከሰተውን ሁላ እንገልብጥ የሚሉት ምሁራኖቻችን ሁላ ምን አላችሁ?
ስለዚህ እኔ እንኳ ጂኒ ሳስብ እናንተ እንዴት ጊዜ ወስዳችሁ አታስቡም? ብቻ ምሁር ሁላ መሪ ሊሆን አይችልምና ይሁን!!!
ጥሪዬ ቀላል ነው፦ የተለየ አስቡ።
አሜን።
በኢትዮጵያውያን ዘንዳ የመንፈስና የግንዛቤ መዝናናት እየጀመረ ነውን!? ፎርሙ ደግ ነው, እንግዴህ ደግሞ ይዘቱም በዚሁ መልክ ሲጨመርበት, ሁሉም ነገር ሁለመናው የተሟላ ይሆናል:: ከዚያማ ለወድያውኑ የሚያዘልቀውን መንገዳችንን በስነ ስዓቱ ተለምን ማለት ነው!!
ይበልከስ ጂኒ ወዲ ዓዲ, እምብኣርከስ ንገፍ-ነጋግፍ!
ጅኒ በመሰረቱ ጅኒ አሜን አይልም.ቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቅቂቂ ሌላው ደሞ አንተን ብሎ ተቺ ጅኒ ያደከመክ ይልቅ አንተን ነው. በላይነሽ እና ማራማዊት በጨዋ መልክ ነው ማራማዊት ጥሩ ጠየቀች በላይነሽ ደሞ ሲያርሟት አትወድም. በርግጥ ዛሬ አልተሳደበችም ዛሬ ደሞ ፍቅር ሰባኪ ሆንሽ ????? በጣም ስትሳደቢ ነው በበኩሌ እዚህ መድረክ ላይ የማውቅሽ. ማራማዊት ያለችሽ ትክክል ይመስለኛል ከመንግስት ጎን ያሉት ወገኖች ስለሆኑ…… አልሽ እሷ ደሞ ለዛማ ለዛማ መለስም ወገን ነው አገር እስካጠፋ ድረስ ግን ጠላት ነው ግልጽ እና ፐርፌክት የሆነ መልስ ነው. አንቺ ደሞ የሌለ ነገር ለተሰጠሽ ትችት አፍረሽ ያልሆነ መልስ ሰጠሽ. አንቺ ለመሆኑ ፍቅርን የምታስተምሪው የሸዋ የደሴ እያልሽ ስትሳደቢ ያውም የድሮ ጀግኖችን ስትሰድቢ ነው የምናውቅሽ እና የማታረጊወን ሰው አትምከሪ ማራማዊት ደሞ አልተሳደበችም በደንብ ሳይገባሽ አትጻፊ. አቶ ጅኒ ምን እንደጻፍክ ለጅኒ አስነብብ. ያንተው ጉጄ ነው አገር እመራለው እያለ ያላዋቂ ሳሚ ሆነ እናም አንተ እንኳን ትንሽ ቀውስ ነገር ትመስላለህ .ፕሮፌሰር አለማየሁ እጅግ የተከበሩ ኖት በርቱልን ጽሁፍ ማር ነው. ወያኔ የሚያስበረግግ እናም አናመሰግኖታለን.