የውሸት ችርቻሮ ይቁም! በአበበ ገላው

June 15th, 2012 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

በኢትዮጵያ የሚታተመውና በድረ ገጽ አማካኝነት የሚነበበው “አዲስ አድማስ” በመባል የሚታወቀው ሳምታዊ ጋዜጣ እጅግ ሃላፊነት የጎደለው የፈጠራ ወሬ በዜና መልክ ሰሞኑን አስነብቧል። በዘባው መሰረት ለደህንነቴ ስለሰጋሁ ቤቴን ለቅቄ ከዋሽንግተን ዲሲ እርቄ በሁለት የደርግ አየር ወለዶች እየተጠበኩ በአንድ “ቪላ” ውስጥ እንደምኖር ይሄው “ጋዜጣ” ነግሮናል። ከዚህም በተጨማሪ 250ሺ ዶላር በሽልማት ቃል እንደተገባልኝና ከዚሁም 120ሺ ዶላር ባንክ ማስገባቴን “ዜናው” ያትታል።

ዜና ተብዬዋ ከአስራ አምስት በላይ ውሸቶችን በማካተት ወደር ያልተገኘላት ልብ ወለድ መሆንዋ ብዙም አያጠያይቅም።እውነታው ግን ህወሃቶች በአሜሪካን ሀገር አንገት አቀርቅረው፣ ተሸማቀውና ከህዝብ አይን ተደብቀው መኖራቸው የአደባባይ ሚስጢር ነው። እኔ በዚች ታላቅ ሃገር ተደብቄ ሳይሆን በነጻነትና እንደምኖር የ አደባባይ ሚስጥር ነው።

ሰሞኑን በተቀነባበረ መንገድ በህወሃት የዜና አውታሮች እየተፈበረከ ካለው የሀሰት ውንጀላና በሬ ወለደ ወሬ አንጻር የአዲስ አድማሱም ዘገባ ሆን ተብሎ ዋናውን ጉዳይ በርካሽ ውሸት ለማድበስበስ የሚደረገው ጥረት አካል መሆኑ ማንም ሊዘናጋው አይገባም። ጥያቄው የገንዘብ፣ የቪላ፣ የአጃቢና ተራ መሰል ጉዳዮች አለመሆኑ በግልጽ እየታወቀ፣ በአለም መሪዎች ፊት የተስተጋባው የኢትዮጵያ ህዝብ የነጻነት ጥያቄ በመሰሪ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ለማድበስበስ ከሚደርግ ጥረት ያለፈ ፋይዳ የለውም። የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ የፍትህ፣ የነጻነት፣ የእኩልነት፣ የመብትና የክብር መሆኑ ግልጽ ነው።

በቅርቡም የናሽናል ፕሬስ ክለብ (National Press Club ) አባልነቴና “የጋዜጠኛ ፈቃዴን” መሰረዙ፣ የአሜሪካ መንግስት በአቶ መለስ ላይ ያሰማሁት ተቃውሞ እንዳበሳጨው በህወሃት የተፈበርኩ ዜናዎች በሙሉ ሃሰት መሆናቸው ሊታወቅ ይገባል። በአሜሪካ ትልቁ የጋዜጠኞች ማህበር (ናሽናል ፕሬስ ክለብ) ፕሬዚዳንት የሆኑት ቴሬሳ ዌስርነር በስርአቱ ደጋፊዎች በኔ ላይ ያቀርቡላቸውን በርካታ ውንጀላዎች መርምረው ውድቅ ማድረጋቸውን ይፋ አድርገዋል። ማህበሩም የኔን እውነተኛ ጋዜጠኛነት ጥያቄ ውስጥ እንደማያስገባና ከጎኔ እንደሚቆም አረጋግጠውልኛል።

በእጸገነት ተስፋዬ በዋነኝነት በተፈበረከው የዋልታ ውሸት የህወሃት እውነተኛው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ብርሃነ ገብረክርስቶስ የአሜሪካ መንግስት በየትኛውም ስብሰባዎቹ ላይ “ግለሰቡ” እንዳይገኝ ወስንዋል ያሉት እንደተለመደው አሳፋሪ ቅጥፈት መሆኑ ከማንም የተሰወረ አይደለም። ምንም እንዃን ለበርካታ አመታት አምባሳደር ሆነው በአሜሪካ ቢኖሩም የአሜሪካ ህገመንግስት First Amendment መብቶች እስካሁን ምንነት አለመገንዛባቸውን ያሳያል። ያም ሆነ ይህ ህወሃት ውሸት መቸርቸሩን አቁሞ እውነትን ለመጋፈጥ ቢደፍር ለሁላችንም መልካም ነው። ከዚህም በተጨማሪ ምንም እንኳን የግንቦት ፯ አባል አለመሆኔ ቢታወቅም ለሀሰት ክስ ድርደራ እንዲያመች ሚኒስትሩ የግንቦት ፯ አባል ጋዜጠኛ ስለመሆኔ ያሳራጩት ውሸት አሳፋሪ ተግባር ነው።

በአሜሪካ ጋዜጠኞች ያለአግባቡ ሊታሰሩ፣ ሊዋከቡ፣ ሊታገዱና ለስቃይና ለስደት ሊዳረጉ የሚችሉት አቶ መለስ እንደነበረከት ስሞን፣ ሚሚ ስብሃቱ፣ ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ እና ሽመልስ ከማል አይንነት የጭቆና መሳሪያ የሆኑ ለህሊናችው ሳይኖን ለሆዳቸው ያደሩ ግለሰቦችን የግፍ ስራ እንዲፈጽሙ ከሾሙብን ብቻ ነው። ይህ ደግሞ ሊሆን የሚችል ምኞት ስላልሆነ ነጻነት በተረጋገጠበት ሀገር የምንኖር ጋዤጠኞች በሙሉ ያለስጋት ስራችንን እንቀጥላላን። ይን ሀቅ ህመም ለሚፈጥርባቸው በሙሉ ሃዘን ከመግለጽ ያለፈ ምንም ልንረዳቸው አንችልም።

የህወሃቶች ውሸት ሳያንስ ዶ/ር አባ ኃይለማርያም መለሰ የቅድስት ሥላሤ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዋና ዲን “በኢትዮጵያ የተለያዩ እምነቶች፣ ሃይማኖቶችና በርካታ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ተቻችለው የሚኖርባት አገር መሆኗን”የተቃወምኩ በማስመሰል ውግዘት መሰንዘራቸው የደረቡትን መንፈሳዊ ካባ ምንነት ከማጋለጡም በላይ ህወሃት በእምነት ተቁዋማት እየተሹለከለከ የሚሰራውን እኩይ ተግባር የሚያጋልጥ ነው። የኛ ጥያቄ የእውነተኛ እኩለነትን እንጂ በጠባብ ጎጠኝነት የተመሰረት የበላይንትን ስላልሆነ ዶክተሩ ይህን ሃቅ ተረድተው የህሰት ፕሮፓጋንዳ ከማሰራጨት በተቆጠቡ ነበር።

ህወሃት የሚያወራው የሚያወራውና የሚሰራው ከዘመኑ እድገትና እውነታ ጋር ተጻራሪ ስለሆነ ከዚህ ሃቅ የራቀ ስለሆነ አለኝ የሚለውን የእገዳ ወይንም የተግሳጽ መረጃ ይፋ እንዲያደርግ በዚህ አጋጣሚ ለመጠየቅ እወዳለሁ። ይሁንና ትልቁ የህወሃት ችግር በነበረከት ስምኦንና በብርሃነ ገብረክርስቶስ የሚሰራው የከሰረ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ መረጃ ነጥፎበት ባዶ ሀሰት ችርቻሮ ውስጥ መግባቱ ነው።
——————-

ጋዜጠኛ አበበ ገላው በደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል (ውሽት)
Saturday, 09 June 2012 06:49 administrator

ባለፈው ወር ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በተሳተፉበት የG8 ስብሰባ ላይ የተገኘው ጋዜጠኛ አበበ ገላው ጠ/ሚኒስትሩን በተቃውሞ ከንግግራቸው እንዳቋረጣቸው ከተሰማ በኋላ በርካታ ድጋፎች የጐረፉለትን ያህል ከተቃውሞና ከነቀፋም አልዳነም፡፡ ተቃውሞውን አሰምቶ ሲቀመጥ በአራት የአሜሪካ ፖሊሶች ከአዳራሹ እንዲወጣ የተደረገው ጋዜጠኛ አበበ ገላው፤ ፖሊሶች እስር ቤት እንዳልወሰዱትና ምንም የድብደባ ሙከራ እንዳላደረሱበት ከሚሰራበት ኢሳት ቴሌቪዥን ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ መናገሩ ይታወሳል፡፡ G8 ስብሰባ ላይ ያሰማውን ተቃውሞ በታንዛኒያ በተካሄደ ተመሳሳይ ስብሰባ ላይ ለማድረግ እቅድ እንደነበረው የጠቆመው ጋዜጠኛው፤ ችግር ሊያደርሱብኝ ይችላል በሚል ፍራቻ እንደተወው አክሎ መግለፁም ይታወቃል፡፡

በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በጋዜጠኛው ጉዳይ ላይ ለሁለት ተከፍለዋል የሚሉ ምንጮች፤ አንደኛው ወገን ጋዜጠኛውን እንደ ጀግና በመቁጠር በሙገሳና በገንዘብ ሽልማት ሲያንበሸብሸው (ውሽት) ሌላኛው ወገን በጠላትነት ስሜት የስም ማጥፋት ዘመቻ እያካሄደበት እንደሆነ ይናገራሉ፡፡
ጋዜጠኛውን እንገድልሃለን በሚል የሚያስፈራሩ ሰዎች እንዳሉ የጠቆሙት ምንጮች፤ ደህንነቱን ለመጠበቅ ጥያቄ ያቀረቡ ግለሰቦችም መኖራቸውን ተናግረዋል (ውሽት) ፡፡ ጋዜጠኛ አበበ ገላው በአ.አ ዩኒቨርሲቲ በህግ (ውሽት) ከተመረቀ በኋላ “ኢትዮጵያን ሔራልድ” ጋዜጣ ላይ ለበርካታ (ውሽት) አመታት እንደሰራና በኋላም ወደ ለንደን መሄዱን ምንጮች ይገልፃሉ፡፡ ከለንደን ወደ አሜሪካ የገባው ጋዜጠኛ አበበ፤ በተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ በመግባት መሳተፉንም (ውሽት) እነዚሁ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ የኢሳት ቴሌቪዥን ተባባሪ መስራችና አዘጋጅ እንደሆነም ይታወቃል፡፡

ጋዜጠኛ አበበ ገላው ተቃውሞውን ካሰማ በኋላ በአራት (ውሽት) የአሜሪካ ግዛቶች ጥሪ ተደርጐለት ንግግሮች ማድረጉን የጠቆሙት ምንጮች፤ በሲያትል የተካሄደውን ስብሰባ የኢትዮጵያ ሬዲዮ ዜና አንባቢ የነበረችው ንግስት ሠልፉ (ውሽት) እና የኢቴቪ ዜና አንባቢ የነበረው መኩሪያ ገ/ሚካኤል (ውሽት) እንዳስተባበሩት ገልፀዋል፡፡ የአበበ ገላውን ተግባር እንዳደነቁ የተናገሩት በሲያትል የሚኖሩት አቶ ገ፤ ጋዜጠኛው የጀግና ተግባር መፈፀሙን ገልፀዋል፡፡ ጠ/ሚኒስትሩን “አምባገነን” በማለት እንዳሳጣቸው በመጥቀስ፡፡ እዚያው ሲያትል ነዋሪ የሆኑት አቶ ከበደ ግን የአቶ ገን ሃሳብ ይቃወማሉ – “ጀግና ማርቲን ሉተር ኪንግ ነው” በማለት፡፡ “እኔ ለምን ተናገረ አይደለም ያልኩት፤ ሆኖም የሰደበው ኢትዮጵያን እንጂ ጠ/ሚኒስትሩን አይደለም” ብለዋል፡፡ መቃወም ከፈለጉ ኢህአዴግ መቃወም ይችላሉ ያሉት ግለሰቡ፤ “እሱንም በሚዲያ ማለትም በኢሳት በየቀኑ ሲተቹ እናያለን፡፡ ዛሬ የተለየ ነገሩ ምንድነው?” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ አቶ ገ ግን በዚህ ሃሳብ አይስማሙም፡፡ “ይልቁኑ መመስገን አለበት፤ ችግራችንን ተናግሮ አገራችንን በቅጡ እንድናይ አድርጐናል፡፡ አሜሪካም በነፃነት እንድንኖር ትፈቅዳለች” ብለዋል፡፡ አገሪቷ ላይ መኖሪያ ፈቃድ አግኝቶ ለመኖር ምክንያት እንደሚያስፈልግ የጠቆሙት አቶ ገ፤ የጋዜጠኛው ድምጽ ለጥያቄያችን መፍትሔ ነው ብለዋል፡፡ አቶ ከበደ በበኩላቸው፤ “አገርን ሰድቦ ሌላ አገር ጥገኝነት መጠየቅ መዋረድ ነው” ይላሉ፡፡ ጋዜጠኛው ጠ/ሚኒስትሩ ላይ ባሰማው ተቃውሞ በአሜሪካ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሽልማት መንበሽበሹን የሚቃወሙት አቶ ከበደ፤ ድሮም ጋዜጠኛው ሲናገር ይሄንን እንደሚያገኝ ያውቃል ብለዋል፡፡ አቶ ገ ግን ለጋዜጠኛው የሰጠነው ያንሰዋል ባይ ናቸው፡፡ በአገር ውስጥ ችግሮች መኖራቸውን ማንም አይክድም ያሉት አቶ ከበደ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ችግር የሚፈታው አንድ ግለሰብ በአገር ላይ በፈፀመው ውርደት ሳይሆን በጋራ በምንሰጣት ጥቅም ነው ይላሉ – ሁሉም ለአገራቸው ምን እንደሰሩ ይጠይቁ በማለት፡፡ ጋዜጠኛ አበበ ይሄን ተቃውሞ በማሰማቱ ብቻ እንገድልሃለን እያሉ የሚያስፈራሩትና የሚዝቱበት ጥቂት አይደሉም የሚሉት አቶ ገ፤ ለአምባገነንነታቸው ይሄ በቂ ምስክር አይደለም ወይ ብለዋል፡፡ “አሜሪካ ያለ ኢትዮጵያዊ ከኃ/ስላሴ ጀምሮ ሲቃወም የኖረ ነው፡፡ ሰው ፍፁም ይመስለዋል፡፡ ስህተቱን አይቀበልም፤ ተደላድሎ እየኖረም ችግር ይፈጥራል፡፡ ትክክለኛ ተቃዋሚዎች ጥቂቶች ናቸው” ያሉት አቶ ከበደ፤ “ኢትዮጵያ ውስጥ ይሄ ተደረገ ብሎ ለመረበሽ እና ሠልፍ ለመውጣት የሚደረገው ሩጫ ለአገር ግንባታ ቢውል የተሻለ ውጤት ይገኝ ነበር” ሲሉ አስተያየታቸውን ቋጭተዋል፡፡

ጋዜጠኛ አበበ ገላው በአሁኑ ሰአት ከሚኖርበት አፓርትመንት በመልቀቅ (ውሽት) በአንድ ቪላ ውስጥ የገባ ሲሆን (ውሽት) ሁለት የደርግ አየር ወለዶች በፈቃደኝነት ደህንነቱን ለመጠበቅ ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት እየጠበቁት እንደሆነ የአሜሪካ ምንጮች ጠቁመዋል (ውሽት) ፡፡

በ15 ግዛቶች ንግግር እንዲያደርግ የተጋበዘው ጋዜጠኛው (ውሽት) ፤ እስካሁን ወደ ዋሺንግተን ለመሄድ አለመድፈሩን (ውሽት) የጠቆሙት ምንጮች፤ ምክንያቱ ደግሞ በዲሲ በርካታ የኢህአዴግ ደጋፊዎች በመኖራቸው (ውሽት) እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

በፈፀመው ተግባር አድናቆታቸውን ለጋዜጠኛው የገለፁ ደጋፊዎች፤ 250ሺ ዶላር ሊሰጡት ቃል እንደገቡለት (ውሽት) ሲታወቅ እስካሁን 120ሺ ዶላር በእጁ እንደገባ ምንጮች ጠቁመዋል (ውሽት፡፡ በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም ለሁለት ተከፍለው መቆራቆሳቸውን ቀጥለዋል ነው የተባለው (ውሽት) – በተቃውሞና በድጋፍ፡፡

የአሜሪካን መንግስት እገዳ የጣለበት አንድ የግንቦት 7 ጋዜጠኛ የሽብር ቅስቀሳውን በቤተክሪስቲያን ጀመረ (የህወሃት ርካሽ የሃሰት ወሬ)
አዲስ አበባ ፤ ሰኔ 6/2004 (ዋኢማ) – በማንኛውም አሜሪካ ውስጥቸ በሚያካሂድ ጉባኤ ላይ እንዳይሳተፍ የአሜሪካን መንግስት እገዳ የተጣለበት አንድ የግንቦት 7 ጋዜጠኛ የሽብር ቅስቃሳውን በቤተክሪስቲያን ጀመረ፡፡

ይኸው ጋዜጠኛ ነኝ ባይ የግንቦት 7 አባል ሰሞኑን የቡድን ስምንት አባል ሀገራት በአሜሪካ ባካሄዱት ጉባኤ ላይ በጋዜጠኛ ስም ከገባ በኋላ ከፍተኛ የስነ ምግባር ጉድለት በማሳየቱ በአሜሪካ በሚያዘጋጅ ማንኛውም ዓይነት ጉባኤ እንዳይሳተፍ እገዳ ተጥሎበታል።

በጉባኤው ተሳታፊ የነበሩት አምባሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ ለዋልታ እንደገለፁት ለጋዜጠኞች ክፍት በነበረ መድረክ በጋዜጠኝነት ስም ገብቶ ተራ ረብሻ ለመፈፀም መሞከሩ ቡድኑ ምን ያህል በተልካሻና በርካሽ ተግባር ላይ እንደተሰማራ ማሳያ ነው።

አምባሳደሩ አያይዘውም ግለሰቡ በፈጸመው አልባሌ ተግባር ከአሜሪካ መንግስት ውግዘት ከገጠመው በኋላ የሃይማኖት ለምድ ለብሶ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሽብር ቅስቀሳ ጀምሯል ብለዋል።

“ሰውየው የገባው አንደ ጋዜጠኛ ሆኖ ገብቶ እንደዚህ ዓይነት ነገር ማድረጉ ሰውየው ራሱን የላከው ግነቦት 7ን ነው ከማዋረዱም ባሻገር የአሜሪካ መንግሥት በሚያዘጋቸው ማንኛውም ስብሰባ እንዳይደርስ ውሳኔ ተወስኖበታል፡፡” ብለዋል አምባሳደር ብርሃነ ክርስቶስ፡፡

አንዳንድ ያነጋገርናቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ሊቃውንት እንደገለጹልን ተግባሩ ከቤተክሪስትያኗ አስተምህሮት ጋር ፈጽሞ ቁርኝት የሌለውና መረን የለቀቀ ድርጊት መሆኑን ተናግረዋል።

ዶ/ር አባ ኃይለማርያም መለሰ የቅ/ስ/መ ኮሌጅ ዋና ዲን በበኩላቸው እንደዚህ አይነት አለማዊ ተግባር በቤተክርስቲያን መፈፀም አለማዊውንና መንፈሳዊን መንገድ ለይቶ አለማወቅ መሆኑን ተናግረዋል።

አባ ኃይለማርያም አያይዘውም በኢትዮጵያ የተለያዩ እምነቶች፣ ሃይማኖቶችና በርካታ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ተቻችለው የሚኖርባት አገር መሆኗን በመቃወም ያስተላለፈው መልእክት የአሮጌው ስርአት ናፋቂነቱን ከማሳየት ባሻገር መንፈሳዊ ፋይዳ የለውም ብለዋል።

“በመንፈሳዊ አለም የሚሰሩ ሥራዎች ፍጹም መንፈሳዊና ሕዝብን ለንስሃ፤ ለፈውስ የሚያበቁ በመሆናቸው ከአለማዊ ጋር የሚያይዘው ምንም ዓይነት ምክንያይት የለውም ብለዋል፤” ብለዋል አባ ኋይለማሪያም፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዳክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሀገሪቱን ህገመንግስት አክብራ የምትንቀሳቀስ እንጂ መረን የለቀቁና የቤተክሪስቲያን አስተምህሮ እውቀት የሌላቸው ፖለቲከኞች የሃይማኖት ለምድ ለብሰው የሚጨፍሩባት አለመሆኗንም ዶክተር አባ ሃይለማሪያም አስገንዝበዋል።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የፐብሊክ ዲፕሎማሲና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው ድርጊቱ አገሪቱ ባሳየችው ልማት በዓለም ሕብረተሰብ እያገኘች ያለውን ተቀባይነት ያሳሰባቸው የግንቦት 7 አሸባሪ ቡድን አባላት ተስፋ ከመቁረጥ የተነሳ የፈጸሙት መሆኑን ገልጸዋል

የኢትዮጵያ ጠላቶች አገሪቱ ትበተናለች የሚል ከንቱ ህልም ዓልመው ቢንቀሳቀሱም የኢትዮጵያ ህዝቦች አንድ ላይ ተባብረው በመስራት አለምን ያስደነቀ ተከታታይነት የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ችለዋል ብለዋል አምባሳደሩ። (
(ይህ ደረጃውን ያልጠበቀ “ዜና” የድርጊቱን ተዋናይ ማንንነት በስም የማገልጽ ሲሆን መሉ በሙሉ ቅጥፈት መሆኑ ግልጽ ነው)

  1. Tulu Oda
    | #1

    Abebe Gellaw! YOU are our epic hero and a brilliant journalist of unquestionable integrity.

  2. መቅደላ
    | #2

    አይ ወያኒ ገና ትቃጠላለህ ተጀመረ እንጅ አላበቃም የወያኒ ይውሺት ካባ ከቢተክርስቲያን እና ከአራት ኪሎ ወጥቶ እስኪደመሰስ አሁንም ይቀጥላል; አትንበጫበጩ ምድረ በጭባጫ የደድቢት መንጋ አገራችን ኢትዮጵያ በአለም ህዝብ ፊት የነበራትን ክብር እድሚ ለልጃ ለአበበ ገላው እውነትን መስክሮ ማናት ኢትዮጵያ የሚሉት የአለም ጋዚጠኞች እውነቱን እንዲያዩ አድርጋታል የወያኒ የውሺት ድሪቶ የትም እንደማያደርሰው አውቆ ቶሎ ንስሀ መግባት ወይም ከዚያው እንደለመደው እስክ እለተፍጻሚው በአለም አደባባይ እየተዋረዱ መኖር አሚሪካን ሀገር አፍሪካ ቢሆን ኖሮ አሁን እምትሉትን ታደርጉት ነበረ አዎ ትገድሉት ነበር ነገር ግን አሚሪካ የሰው ልጅ መብት; የመናገር እና የመጻፍ የተከበረባት ስለሆነች ወያኒ ገና ከቁስሉ ለማገገም የሚፈጅበት ጊዚ አይታወቅም ዝም ብሎ እሱም ዚሮ ዚሮ ብቻ ነው;
    አቢ የኛ ልጅ ;
    የሚያቃጥል የሚፋጅ;
    አንበሳ አንገት የሚያስደፋ
    ወያኒ ከነኮሮጆው አንቀላፋ
    አቢ የኢትዮጵያ ተስፋ
    አወ የኢትዮጵያ ልጅ አቢ
    አኖርሀአለሁ ከልቢ

    በተረፈ አይዞህ በርታ ማንም ቢያቀርሺ ተመልሶ ከአፉ ነውና የወያኒ ቅርሻት ለወያኒ ብቻ ነው;;
    ወያኒ ቅርሻት ተላበት

  3. በላይ
    | #3

    እውንት ነው ውያነ ቢዙ ያውራል በረ ውልድ የውያነጀለዎችህ እንዳፍሩ ይክራሉ አበ ገግናንወ.

  4. በላይ
    | #4

    አበ ጀግና ነው.

  5. ጥበበ
    | #5

    To be honest, Journalist Abebe Gelaw’s conduct has exposed the true nature of the EPRDF and its surrogates. The people who claim that freedom of speech is respected in Ethiopia are showing us that how Ethiopians who express their views publicly are treated. Thank God that Abebe did what he did in the US. Thank God, he is too far away from TPLF guns and police batons. The Woyane propaganda machine has unleashed its character assassination merciless squad because Woyane is unable to do anything about Abebe other than engage in a petty useless propaganda. It is clear what “EPRDF Style” democracy looks like. All Abebe did was exercise his God given right. I had the opportunity to interview and to have a private conversation with Ambassador Berheane long time ago, he sounded a reasonable man then; to read his statement about Abebe made me realize that there is no honor or a sense of dignity in the TPLF camp. How low can you get? If they cannot tolerate a simple protest by one journalist, what would they tolerate? I feel sorry for those who died under the EPRDF banner for democracy and justice; it is unfortunate that their sacrifice has been betrayed by bunch of hoodlums and opportunists. How do we let such ignorant and intolerant group rule our nation for 21 years?

  6. korojo-Ethiopia
    | #6

    Abe walk the walk leave the talk to them ,they do nothing good to the people.GBU.

  7. ኢትዮጵያዊው
    | #7

    አቤ ለፈጸምከው ተግባር ምስጋናየ ይድረስህ :: የወያኔ ካድሬ ተለጣፊ እና ታጣቂ ቄስ ዋይታ “አፍንጫን ሲመቱት አይን ያለቅሳል”
    እንደሚባለው ነውና ብዙም አይገርም :: እነ ሀሰት ቀለቡ በቅጥፈት ብዙ መጉዋዝ አይችሉም ::

  8. goba
    | #8

    When Abebe Gelaw spoke at that epoch moment, at G8 meeting the woyane gujile leader, whom his opportunist cadres gratify as a brave leader was like a little rat, shuffling around to find a hole in the ground to hide itself. The miscreat gujile leader collapsed to the ground when he was told the truth about who he was.

    We know the woyane for 20 years. These scums of the earth, are well versed in fabricating lies that they have taken it as an art.

    The stories are well known about the woyane even murdering people in broad daylight and blame it on somebody else, and appear on the funeral to appear innocent.

    There is nothing the woyane could gain by fabricating yet another big lie, instead they expose themselves, who they are and speed up their demise.

  9. ማራማዊት
    | #9

    አይ አቤ በመጀመርያ ደረጃ አንቲ ወያኔን ሁሉ አንጀቱን ቂቤ ነው ያጠጣእከው እናም እጅግ ትልቅ ትልቅ ትልቅ ትልቅ ነገር ነው የሰራከው ይህን ጉጅሌ ፓርላማ ተቃዋሚዎች ላይ እይን ድስት አፉን ሲከፍት አንገቱን አስደፋልክልን ተባረክልን!!!!!!!!!!!! አዲስ አድማስ እኮ የታወቀ ነው የወያኔ ነው እናም ወያኔ ስላአፈረ እንሱ ይሆናሉ እንዲህ ብላችው ከጻፋችው ተብለው ገንዘብ ተቀብለው ይሆናል. እያለቀሱ ቢያወሩ የሚያምናቸው የለም በፍጽም ውሸት ነው. ማንም አላመነም የወያኔ ቅጥያ እንደሆነ ማንም ያውቃል . እናም ከወሸትም ውሸት መሆኑ ግልጽ ነው. እዛ እንዳለው አፈና መስሏቸው ነው . ቀና ብሎ የሚያይህ የለም ሊኖረም አይችልም . ምድረ ለሆዱ የተገዛ አጋሰስ ሁሉ አፉን ቢከፍት ንቆ መተው ነው. የሆዳም ጀግና የለም ለሆዳቸው ህሊናችወን የሸጡ እና ሆድ አምላኩ ሁሉ ድንጋይ የመወረውር ልብ የለውም ኢትዮጲያውያን በተልይ አገር ቤት ያለው የዛን ሁሉ ፍላጎት ነው ያንጸባረከው. እናም አዲስ አድማስም ሆነ ሌላው የወያኔ ተቀጽላ ነው እኔ ደሞ ኢሳት ላይ ሰምቼ ያንተን ማለት ነው አገር ቤት ለሁሉም የአዲስ አድማስ ወሬ ውሸት መሆኑን እና ምንም እንዳልተባልክ ስነግራቸው እናውቃለን ውሸት እንደሆነ እናውቃለን የማይል የለም እናም ማንም አላመነም እነሱ ተዋረዱ እንጂ . አሁንም ቢሆን ያላወቅ ጥቂት እንኳን ቢቀር ውሸት እንደሆን እናጋልጠዋለን. ነገ ግን እንዲው ደከሙ እንጂ ያመናቸው የለም አንተ ግን ትልቅ እና ትልቅ ስራ ሰራህ. በርታልን ይህ ጉሌ በቋፍ ነው ያለው . ገና ደጋፊዎቹንም በያለንበት ማንነታቸወን መያዝ አለብን ፍርድ ማግኘት አለባቸው ወያኔ መውደቁ አይቀረማቤ በጣም እንወድሃለን!!!!!!!!!!!!!!!!!! ወያኔ እርሱ ትራሽ ነውና የወያኔን አስተያየት ትራሽ !!!!!

  10. ማራማዊት
    | #10

    አቤ እንወድሃለን ብዬ የረሳውትን ልቀጥል የመለስን ገጽታ ገና ድሮ ድሮ ጫካ እያለ የነበረው መልክና ወዝ ነው የታየው ያቺ ማን ናት ቂጧ ቀይ እንጣጥ እንጣጥ የምትለዋ እንሥሳ ማን ነበር ስሟ???? ያቺ እንኳን ሙዝ የምትወደድው እንሥሳ???? ቂጧ መላጣ አስታወስካት አቤ ቆንጆ በቃ ልክ እሱን ነው የመሰለው. በጣም ነበር የሚያስቀው. እኔ መለስ ሲስቅ በጣም ያናድደኛል ሲቆጣ ደሞ ያስቀኛል. አሁን ግን እይደጋገሙኩኝ በማይቴ እድሜ ቀጥል ነው የሆነብኝ. የረሳወት ዋናው ቁም ነገር ግን ከታች ይህን አምባገነን መንግስት ተብዬ አምባገነን ማለት እሱን ሳይሆን ኢትይኦጵያን ነው ያዋረደከው ያሉት ፍጥረቶች አንባቢ ይቀርታ አርጉልኝና ይህን ቃል ልጠቀመው ነው. የመጨረሻ የሻገተ እና የጠነባ ጭንቅላት ነው ያላቸው. ለምን?????? የኢትይኦፒያ ገበሬ ከመሬቱ ሲፈናቀል እናም ሲሰደድ ክብር ነበር??????? በጉራፈርዳ የሚኖሩት የአማራ ህብርተሰብ እጻናትን እንደዛ አረገው ሲሰደዱ ያፈሩት ንብረት ተቀምተው ይህ ነው የማይባል ከአውሬ የማይጠበቅ ጭካኔ ሲደረግ ክብር ነበር?????????????የጋምቤላ ህብረተሰብ መሬቱ ሲነጠቅ በገዛ አገሩ ደም ሲያለቅሱ ክብር ነበር??????? እኔን ካልደገፍክ ተብለው ከስራ ህዝብ ሲባረር ክብር ነበር??????????? በድብቅ እስር ቤት በማህከላዊም ሴቶች በኮረንቲ ገመድ ጡታችወን ሲገረፉ ክብር ነበር????????? ወንዶች ብልታችወን በጠረሙስ ውሃ ክብር ነበር????????? መሬ ለባህዳን እይሰጠ ያወም በርካሽ ህዝብን ለማናደድ አይወዱኝም በማለት ብቻ ዜጋወን የበይ ተምልካች አርጎ እንድና ሱዳን ሲንበሸበሽ ይህ ክብር ነበር???????? እረ ብዙ ብዙ እናም እንንተ የከርፋ ጭንቅላት ያላችው አጋሰሰ የውሻ ልጆች ይህን እንዴት አያችወት???????????? የኢትዮጲያ ህዝብ ውርደት የቱ ነው??????????????????? የተኛው ነው ህዝብና አገር መዋረዱን የሚጠቁም????????? ሰው በገዛ አገሩ ከኖረበት እንደሁለተኛ ዜጋ እይታኡ አዲስ አበባን ረግጦ የማያውቅ ሁሉ አዲስ አበባ በህዝብ ገንዘብ ህዝብ በርሃብ እይረገፈ እነሱ ባልህንጻ ሲሆኑ እናም ሌላወን ደሞ ከኖረበት ስፍራህ አይደለም ብለው ሲያፈናቅሉ የቱ ነው ውርደት?????? ወደ መቀሌ የተመለሰ አለ?????????? እወነቱን እንነጋገር. ክብራችው ሆዳችው የሆነ አጋሰሰኦች ኢትይጲያን እና ህዝቡን ያዋረደ ይህ ጉሌ አይደል??????? ባንዲራን ጨረቅ ነው ያለዪትዮጲያን የ100 ዓመት ታሪክ ነው ያለ, የአክሱም ሃውልት ለወላይታ ህዝብ ምኑ ነው ያለ ይህ ክፍታፍ መሪ ተብዬ አይደል ኢትይኦፒያን ያዋረደው????????? ይህ ሁሉ ገንዘብ እይተቀበል ከአውሮፓ እና ከአሜሪካ ከርዳታ ሰጭ ተብዬ ድረጀት ይህን ሁሉ ገንዘብ እይተቀበለ ህዝብ ሲራብ ያ አይደል ውረደት?????????? ቻይና እና ሲዊዝ ባንክ የህዝብ ገንዘብ እያሸሸ በግለሰብ ስም ንብረት እይሸሸ አገሪቴን በበቀል አለንጋ እግረፈ ህዝቡ የወርደት ኑሮ እይኖረ ማን ነው ኢትይኦፒያን ያዋረደው?????????? ከታች ከጽሁፉ ቀጥሎ አንዳንድ አዋቂ ነን ባዮች በሰጡት አስተየአየት ተገረሜ ነው. ነገሩ ውሻ በበላበት ቢጮህ አይገረምም አበበ ገላው ጀግናው ግን የኢትይኦፒያ ህዝብ ሁሉ ነው ነጅግ የተደሰተው አቤ እንዚህን ውሾች ናቃቸው. የኢትዮጲያን ህዝብ ያዋረደወ ያወም 20 ዓመት መለስ ጉጄው እንጂ አቤ አይደለም እናንተ ኦድ አደሮች ይህ ሰው ታላቅ ስራ ሰርቷል እናንተም ነገ በስራችው ታፍራላችው አቤ በርታልን . አቶ መለስዬ ሳውዝ አፍሪካ ጉዟችወን አሰረዟቸው እንኳን ቀሩ ገና ምን አይታችው ሳውዝ አፍሪካ መለስ ገና አንገቱ ላይ ጩቤ ይሰካል ይህ ነው የገረማችው. የወንበዴ እና የሌባ የኦዳም ዘመን ሊያበቃ ነው. አቤ ወያኔን አንጫጫክ እንዲህ ነው ስራ ትልቅ ስራ መስራትህ በወያኔ መንጫጫት እወቅ ወንድ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!! አዲስ አድማስ እወነት ቢናገር ነው የሚገረምኝ አልቅሶ ቢያወራ የሚያምነው የለም አቤ ውሸት እንደሆነ ህዝብ አውቋል ሁሉ እይመስገነህ ነው.ወንድ ኢትይጲያዊው ማንዴላ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  11. ትግስት
    | #11

    አበበ አቦ ይመአችህ…………

  12. ወጋየሁ
    | #12

    አበበ ሰው በሌለብት ሰው የሆነ ጀግና ነው:: እጅግ አስተዋይ ነው እኔ ብሆን ታንዛንያም አግኝቼ እገደል ነብር! አቤ ጀግና ጀግና ለወያኔ ውርደት ያሸከም!

  13. Hana
    | #13

    Abe
    ke 99 maireba tekawami party ante teshlaleh WONDATA !!!!

  14. Anonymous
    | #14

    To be honest, Journalist Abebe Gelaw’s conduct has exposed the true nature of the EPRDF and its surrogates. The people who claim that freedom of speech is respected in Ethiopia are showing us that how Ethiopians who express their views publicly are treated. Thank God that Abebe did what he did in the US.

  15. ቲና
    | #15

    To be honest, Journalist Abebe Gelaw’s conduct has exposed the true nature of the EPRDF and its surrogates. The people who claim that freedom of speech is respected in Ethiopia are showing us that how Ethiopians who express their views publicly are treated. Thank God that Abebe did what he did in the US. አቤ የኔ መከታ እግዛብኤረ ሰላምከን ያብዛው!!!!!!!!!!!አቤ ዘርከ ይባረከ!!!!!!!!!!!!!!!! አቤ ዘርከ ይብዛ ምድሮንም ይሞላት አቤ ውድድድድድድድድድድድድድ……….እናደረገካለን እኝ ኢትዮጵያዌያኖቸ!!!!!!!!!!!!!!ውያኔ ውያኔ እግዛብኤረ ዘረከን አየባረከው!!! ውያኔ እግዛብኤረ ዘረከን እደሶዶም እሳት ያቃጥለው!!!!!!!

  16. Anonymous
    | #16

    Good job hero journalist Abebe Gelaw

  17. ሙሴ ሙላቱ
    | #17

    እናት አየትዮጲያን ደጋግመዉ ደፍረዋት:
    ይሉኝታዉም አይገዛቸዉ በህገ አራዊት:
    መናር ሰለቸን ስለብልግበናቸዉ ብዛት:
    ስልጣንን እያለሙ አገር የሚሽጡት:
    የእንግዴን ልጆችዋ መለስ በረከት:
    ኢሳያስ የሻቢያዉ ከባንዳዎች ቤት:
    ደርቡሾች ካራ ሚስጡሩን የማያዩት:
    ከቱርኮች ከግብፆች ጠብቀዉ ያኖርዋት:
    መቅዳላ ከመተማ ማይጨዉ የወድቁላት:
    በቅኝ ግዛት መዉደቅዋን ተፀይፈዉን ባርነት:
    ሜዳም ይገባሉ የደፋሮቹን መጫወቱን ወደዱት
    ሜዳዉ ዘርዓይ ደረስ ጎራዴዉን ባብድሳ ስጫወቱት

    የታሉ ልጆቹ የአዉራምባዎች አማልክት:
    በእስክንደሬ አበበዉ ስጫወቱ በቃላት:
    በደፋፎቹ ስም ባዓለሙ የርዕዮት:
    ሞገዱ ሲቀምሩ ማዕባላማ ጩኸት:
    ባንዳ ሲያቀርቅር ሆዳሞችን የደነገጡት:
    ሊነጋም ይሆናል ለደቀደቀዉን ጨለማት:
    የደፋራትም ይሙት ድንበርዋንም የቆረሳት:

  18. ቶክችው
    | #18

    አቤ ይህንን እርምጥምጥ ወያኒ ድባቅ መታሕው!!!
    ጀግናው!!!!

  19. ኩማ
    | #19

    የአቶ መለስ ሁለተኛ ሚስት ምን ተስምቷት ይሆን??????? የማታውቋት ካላችው ሰለሞን ተካልኝ(ከዳልኝ) ትባላለች ሰለሞኒቱ ሰው ማለት እንዲህ ነው ገባሽ?????? አበበ ገላው የጀግና ጀግና እንደአንድ ህዝብ ነው ትልቅ ስራ የሰራከው ወንድ!!!!!!!!!!!!!!!!! አሁን ያንተም የሰልሞን ከዳልኝም አባት እኩል አባት ይባላሉ????????ቂቂቂቂቂቅቂቂ ደሚቱ አንቺን አስታወሰኝ ይህ ጀግና. አቤ በተረፈ አዲስ አድማስ ብለህ ትጨነቃለህ ውሸት ከውሸትም በሬ ወለደ እኮ ነው እረ እግርህን አንስተህ መሳቅ ነበረብ ትንሽ ያናደድከኝ ኢሳት ላይ ተናደህ ስትናገር ነው በጣም እይሳክ እና እይተዝናናህ ህዝቡም እንዳላማነ እና እንደሳቀባቸው ሬላክስ አረገህ ማወራት ነበረብህ. ከኢህ በዋላ እይሳክ ሳቅባቸው አድማስ እራሳቸው ከመንግስት ብር ተቀብለው የሚነፉት ነው ማንም ማላመነም. አቶ መለስ ፓርላም ጨዋ ተቃዋሚዎች ላይ እንደዛ አፉን ሲከፍት የምላስ አንበሳ ባአለም መሪዎች መሃል አንገቱን አስደፋከው ገና ባአለም አቀፍ ፍርድ ቤት በጄኖሳይድ እና በስርቆት ገና ይከሰሳል .ለማንኛወም እንውድሃለን!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  20. አንድነት
    | #20

    የወያኔዎችን ቅጥፈት፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሲያውቀው፡ ገና ከበረሃ ደደቢት ጫካ ሳሉ በሽተኛ ባሕርያቸው ነው። የፋሽስት ወያኔ ቅጥፈትኮ በየደቂቃዋ ትፈበረካለች። ፋሽስት ወያኔዎች በረሃ ሳሉ በስጋት፡ ሕዝብ መሃልም ተቀላቅለው በስጋት የሚኖሩ በሽተኞች ናቸው። አበበ ገላውኮ የሕዝባችን እንግልት፤ የኢትዮጵያችን ጉስቁልና ያንገበገበው ውድ የኢትዮጵያ ልጅ ነው። በዓለም መሪዎች ፊት የፕሮግራም መሪነት የነበሩት ሰው፡ የአበበ ገላውን ንግግር፡ ” መለስ ዜናዊ አምባ ገነን ነው ” ከምግብ በላይ መጀመሪያ ነጻነት( ነጻነት ሳይኖር ምግብ የለም) ” የሚለውን ቃል ስላደመጡ፦ አበበን ያንተንም መልእክት አድምጠናል እናመሰግናለን ነው ያሉት። የኢትዮጵያውያን ድምጽ፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም መሪዎች ፊት ተላለፈልን። ውድ አበበ ገላው፡ እኔም ምስጋናዬ ከምንም ነገር በላይ ነው።
    የሃይማኖት አስተማሪ ነኝ በሚል፡ የወያኔው ሹመኛ በቅድስት ካቴድራል ያሉት፡ የንግግር ቃላታቸው እንዳለ የወያኔዎች ይዘት እንዳለው ግልጽ ነው። ብሔር ብሄረሰብ የሚል የወያኔ ቋንቋና የአበበ ገላው በቤተክርስቲያን ተገኝቶ ያደረገውን ንግግር ተቃውመውታል። የፋሽዝምን ድርጊት፡ ቤተክርስቲያናችን መቃወምና፡ ፋሽስቶችን ስለውድ ኢትዮጵያውያን ብለው የሚቃወሙትን ሕዝብን ለማዳን የዘመቱትን ስትባርክ የነበረች፡ የነጻነታችን እምነት ናት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን። ኢትዮጵያውያንን በግፍ ሲሰቅሉና ሲገድሉ የነበሩትን የሙሶሊኒ ፋሽስቶች፡ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጉልበት ያለው ሁሉ ዘምቶ ኢትዮጵያን እንዲያድን አሳስበው ነበር። ግድ የለሹን ባንዳውን ደግሞ፡፦ ” ውጉዝ ከመ አርዮስ( እንደ አርዮስ የተወገዝክ ) ብለው ካህናቱ የመንፈሳዊ መሪነትን እየሰጡ ኢትዮጵያን የነጻነት ባለቤት እንዳደረጉ የታሪክ መጻሕፍትና አባት አርበኞች ተናግረዋል።
    አሁንም እውነተኛ የተዋህዶ ካህናት፡ ፋሽስት ወያኔዎችን ኢትዮጵያውያን አስወገደው፡ ኢትዮጵያን እንዲያድኑ በተደጋጋሚ ጥሪ ሲያደርጉ አድምጠናል።
    የወያኔው ካህን የቅድስት ስላሤ ካቴድራል ዲን፡ አበበ ገላውንና ካህናቱን ለመወረፍ የወያኔዎችን ቃላት ሲጠቀሙ ተሰምቷል። ብሔር ብሔረሰቦች የሚል። ብሔረስብ እራሱ ብዙሃን ቁጥር የሚገልጽ ስለመሆኑ የግእዝ ተናጋሪዎች ጠንቅቀው ያዋቃሉ፡ ብሔረሰቦች የሚለው ቃል የወያኔ ቋንቋ ነው፡ በመዝገበ ቃላት ውስጥ ያልሰፈረ ማወናበጃ። ኢትዮጵያችን የተለያዩ ብሔረሰብእ ሃገር ናት።

  21. በለው!
    | #21

    * ፳፻፲፪ የ ጂ ፰ ስብሰባ ላይ በተደረገው ለምኖ የማላመን ሥነ-ሥርዓት ላይ ባለድርሻ ለማኝ ሀገሮች አይናቸውን አፍጠው ምላሳቸውን ስለው ‘ከተቻላቸው በላይ’…’ከሚችሉት በታች’…”አፍሪካውያንን በወሬ አጥግቦ በማሳደር እራስ ማስቻል”(…) እየተባለ ሲሞላፈጡ የዋሉበት የቃላት አሰማመር ገበያ ደርቶ ነበር።
    **”እዚያም ቤት እሳት አለ”!ሆነና ነገሩ ጉዳዩ ይመለከተኛል ባይ ተነስቶ የለም “የውሸት ችርቻሮ ይቁም !”በማለት ሕዝብ የሚበላው ብቻ ሳይሆን መሠረታዊ ነፃነቱ መከበር አለበት አምባገነንነት ይቁም !እስረኞች ይፈቱ!በልተሃል እና ተረገጥ ማለት አግባብ አደለም !ሲል አቶ አበበ ገላው መልዕክቱን ጋባዥ አስተናጋጅ በተገኘበት ዕድሜአቸው ለማገናዘብ ለማየት ለመስማት ለሚችሉ በሕይወት ላሉ እና ወደፊትም ይወለዳሉ ተብለው ለሚገመቱ ሁሉ የሚቀመጥን መልዕክት ማስተላልፉ በጣም ተገቢ እና አስፈላጊ ነበር::አንዳንድ ያልተዋጠላቸው “አነስተኛና ጥቃቅን ቸርቻሪዎች” በጅምላ የቀረበውን እውነታ ሳይዋጥላቸው ቀርቶ የተለመደ ቀረርቶአቸውን በተለያየ መልኩ አቅርበዋል::
    ይህ “በኮመዲቲ ኤክስቼንጅ” ሲታይ ‘ተጠንቶ የቀረበ’ያለ አንዳች የኪራይ ሰብሳቢ ጣልቃ ገብነት የተደረገ የነጻ የግብይይት ሥርዓት(በእውነት እና በውሸት መካከል) በመካሄዱ ጥቅማቸው የተነካ ሆድአሳዳሪዎች ከዋናው የውጭ ጉዳይ ሚ/ር,ህዝብ ግንኙነት ተጠሪ አምባሳደሮች,አዳማቂ ኢንቨስተሮች,የሸረሪት ድረ-ገመዶች,ወዶ ገብ የጥቅም ገበያተኞች, አመሳቃይ (አስመሳይ) ጋዜጠኞች, የወንድ አልቃሽ አስለቃሽ ጋዜጠኛ,አርቲስት ሁሉ የስርቆት ጎዳናችን:በዓለም ፊት ያለን ገጽታ የአፍሪካ የዕድገት ተምሳሌነታችን ተዋረደ ሲሉም ይደመጣሉ::ከእንግዲህ “አቶ አበበ ገላው የጋዜጠኝነት መብቱ ይነፈጋልም ይላሉ” ለመሆኑ የኢህአዴግ ሕገመንግስት ድንበር የለሽ ነውን ?? አቶ መልስ ለዚህ ትውልድ አውርሰው ለመጪው ትውልድ መታሰቢያ የሚሆኑበት…”ውሸት,ማጋጨት,ማጭበርበር,ዝልፊያና ንቀት” በራሳቸው በመድረሱ ድሮም መክረናል ” ህዝቡን አትስደቡት ቀን የጣለ ዕለት ለራስ አደለም ወይ ይህ ተንጋሎ መትፋት” ብለን ነበር::
    ***እርካሽ አጃቢ እና አስፎጋሪ ደጋፊዎቻቸው አሁንም የበለጠውን የሕዝብ አመጽ ቀስቅሰው ሌላውንም ከዚህ በበለጠ ሁኔታ እንዲያዋርዳቸው እና ለከረረ ብቀላ አባብሰው ኢህአዴግ ለጥቅም እንጂ ለክብሩ ግድ የለውም ቢባልም እኛ እንደ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ለጠ/ሚ ሆነ ኢትዮጵያን ወክለው “ውሸት በመቸርቸር” ለመዋረድ ለሚሽቀዳደሙ ሁሉ አፈርንባችሁ!!
    ****የ፳፩ ዓመትን ስድብ እና ዝልፊያን በ፳፩ ሴኮንድ ፤ በ፺፮.፮ የሕዝብ ድጋፍ ፣ በቀን ሁለት ድጅት የሚጨምር የወያኔ ደጋፊዎችን የደም ግፊት አስመዝግቦ ፣ ፲፩ ከመቶ የኢህአዴግ የዓመት ባጀት ለጆሮ ጠቢ፣ለማስተባባበያ፣ለሆድ አደሮች መመልመያና ማሰልጠኛ ወጪ እንዲደረግ፣ ፸ ከመቶ አስመሳይ ደጋፊ የኤምባሲ ቅጥረኞች ካድሬዎች ለግምገማ መዳረጋቸው ሁሉ በአቶ(ለገሠ)መለሠ ዜና ማሰራጫዎች ሁሉ የሚወራጩ ቸርቻሪዎች በከፍተኛ ደረጃ በመፈጠራቸው አቶ አበበ ገላውን በከፍተኛ ደረጃ ሊያመሰግኑት ይገባል።አራት ነጥብ። አሁንም በአፋችሁ አትሂዱ ነገር አለ በለው!በቸር ይግጠመን>>>>

  22. Allah Akuber
    | #22

    There was not a single lies on Abe telling this killer and the most wanted criminal by Ethopians except it is for the true media out lets
    as the other invited officials are all well aware of his contineous crimes as he paves their national interest since day one and choose to turn a blind eye for our help out cry. Our hoping of president Obama after Bushs years of allying fully with the criminal gang does not achieve much for the suffering of our 80 millions wish which is to see this individual in Den Hague (ICC) not only praising Abe for his heroic action rather trying to be the next Abe by engulfing any thing woyanne.

  23. ይግዛው እያሱ
    | #23

    ለህሌና እንደር

    እኔ ምን ቸገረኝ ምን ጊዜም አልደላኝ
    ከእንግዲህ ተወልዶ ሰው ለሚሆን ይብላኝ:
    እያልን እያዜምን ፀጥ ብለን እያየን
    ህዝባችን በግፍ ሲያልቅ ሁአላ ከሚቆጨን
    ወገን እንደሌለን አገር እንደሌለን ከምንቀር ተሰደን
    ያገባኛል ብለን ካለንብት ሆነን
    አምባገነን መንግስት ማስተናገድ ይብቃን::
    “በቃ” እዚህ ላይ ያቁም ብለን ቃል እንግባ
    ድምጻችን ከፍ ብሎ ለዓለም ያስተጋባ::
    አይኑን በጨው አጥቦ ብቅ ብቅ የሚለው
    ከእውነት ይለቅ ሁሌ ውሽት የሚቀናው
    ተራብን ለሚሉ ጥይት የሚያቀርበው
    ፍትህ የሚሹትን አሸባሪ ሚለው
    ሳያድጉ ማደግን ለአለም ሚተርከው
    ያልሆነን ሆነ ባይ አስምስሎ ፈጥሮ
    ሰው እንዴት ይኖራል ለሆዱ ብቻ አድሮ::
    ሆዳቸው ማሰቢያ ህሌናቸው እግር
    ሆኖ እየመራቸው ሲመኙ ለመኖር
    ምን አገባኝ ሳንል የአገራችን ችግር
    መፍትሔ እስከሚያገኝ ሆነን በሰው ሀገር
    ሆ! እንበል ያገሬ ሰው ለህሌና እንደር::
    ያለፈውን ስራ ታሪክን መጥቀሱ
    አይገባም ባልል ጀግናን ማወደሱ
    ሁሌም በስም መኖር አይበቃም በራሱ::
    እንደ አበበ ገላው ነጻነት እናውጅ
    ጥሩ ስራ እንስራ ለሀገር የሚበጅ::

  24. አንድነት
    | #24

    አቡጊዳዎች ምነው የኔስ አስተያየት? አንዱ የሕዝባችን ድምጽ ነውኮ!!!

  25. በላይነሽ
    | #25

    ጋዜዜጠኛ አበበ ገላው G-8 አገሮች የሬጋን ሕንጻ በአደረጉት ስብሰባ የተገኙትን አቶ መለስ ላይ ያቀረበው ክስ ትክክል ነው ትክክል አይደለም ለማለት ፍላጎቱ የለኝም::ጋዜጠኛ አበበን የሚያስደንቀውን ብቻ ልግለጽ::ብዙ ሰዎች አገራቸው ከወጡበኋላ ሃስባቸውን በንዲህ ዓይነት መድረክ መግለጽ ቀርቶ ሰላማዊ ሰልፍ መውጣት ይፈራሉ::በየትኛውም ስብስባ ለመገኘት ከፍርሃታቸው የተነሳ አይገኙም::ጋዜጠኛ አበበ ይህን በማድረጉ ሊደነቅ ይገባዋል::አቶ መለስም እነ አሞራውን በጀግንነታቸውና በአላማ ጽናታቸው ከአድነቁ ይህም ሊደነቅ ይገባዋል::የሚደነቀው የአላማ ጽናቱ እስከሆነ ድረስ::
    አንዳንድ ሰዎች ጋዜጠኛ አበበ ክሱን ሲደረድር አቶ መለስ ደነገጡ በማለት የሚያጣጥሉ ወገኖች ማወቅ ያለባቸው አቶ መለስ እንደማንኛውም ሰው ናቸው ቢደነግጡ ምን ድነው ችግሩ?
    ሊደነቁና የረጅም ጊዜ ያካበቱት የመድረክ ልምድ ምን ያህል እንደሆነ የታየበት ብቃታቸውን ያስመስከሩበት መድረክ ነበር::
    ጋዜጠኛው ንግግሩን ሲጀምር ዘወር ብለው ማን እንደሆነ ተመልክተው ራሳቸውን አረጋግተው ፌታቸውን ወደ ታዳሚው ከአዞሩ በኋላ የትኩረት አቅጣጫቸውና ሃስባቸው እንዳይበታተን በእጃቸው የያዙትን ማንበብ ጀመሩ::ባያነቡም አምዕሯቸውን ለማስባስብ ማድረግ ያለባቸው ይህን ነበር::ራሱ ንደታቸውን ተቆጣጥረው ምንም ስህተት በአለመስራታቸው ያስደንቃቸዋል::ከዚህ ቀጥለው በሚገባ የተጠየቁትን ጥያቄ በትክክል መልሰዋል::ይህ ራሱ የሳቸውን ብቃት ያሳያል::
    የጋዜጠኛው ንግግር ለስራአቱ መውደቅ/መቆየት የራሱ አስተዋጾ አለው::
    በ16ኛ ክፍለ ዘመን አጼ ንብለድንግል ከግራኝ መሃመድ ጋር በአደረገው ጦርነት ሽንፈት የገጠመው በጦርነት አልነበረም::
    ሊቀሃገራት/ሸዋ አካባቢ በተድረገው ጦርነት ላቅ ያለ ጅግንነት ያሳዩት የንብለድንግል ሰራዊት በፕሮፕጋንዳ ተሽንፎ ያለምንም የረባ ውጊያ በከፋ ሁኔታ አፈገፈገ::
    የግራኝ ማንነትና አጭር ቀጭን መሆኑ በታወቀ ጊዜ ከያለበት በገላድዮስ መሪነት ተስባስቦ ተገተገው::በቀላሉ ራያ-አለማጣ አካባቢ ተሽነፈ::ግራኝም ተገደለ::ሰራዊቱም በቀላሉ ያለምንም ውጊያ ተበተነ::በመላው ኢትዮጵያ የዘመተው ሰራዊት የት እንደገባ አልታወቀም::
    የጋዜጠኛው ንግግር ሊያመጣ የሚችለው መታወቅንና መደፈርን እንድምታ ሊኖረው ሲችል በሌላ በኩል የሚያመጣውን እናያለን::አስተያየት ሲሰጥ ሚዛናዊና አስተማሪ ሊሆን በሚችል መልኩ ቢሆን ይመረጣል::

  26. ተስሃለ መንጊስቱ
    | #26

    Tulu Oda :Abebe Gellaw! YOU are our epic hero and a brilliant journalist of unquestionable integrity.

    @በለው!

    @አንድነት

  27. genet
    | #27

    አቤ አንውድህለን ይሕንን ባንዳ የባንዳ ልጅ አስከ አለተ ሞቱ ይሚበቃውን ውርደቱን አክናንበህልናል በዚህ የተንሳ ለጥቂት ፍርፋሪ ስእብናቸውን የሸጡ አድር ባዮች ስሚ የሌውን ጩኽት ከግራ ውድ ቀኝ ቢያስተጋቡ የተካኑብትን ውሽት ቢደረድሩ ምንም አይስደንቅም ማንስ ቢያምናቸው የኢትዮጵያ ህዝብ አንደሆነ የያዘ ይዞት አንጀ አውነቱ የት አንዳለ ጥንቅቆ ያውቃታል ካሀዲዋች አንሱ ቢሆን መች አጡት አና በጥቅም ታውረው አንጅ, አቤ አጅግ አናመስግናልን ደስታችን ስላበዛህልን ረጅም አድሜ አና ጤና አንዲሆንል ምኞታችንን ነው

  28. ደያሳ
    | #28

    ቅድሚያ የ 20 ዓመት ትንፋሻችንን ኡፍ ላሰኘን ለጀግናው አበበ ገላው!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!! ምስጋናዬ ካለህበት ይድረስህ!!! በመቀጠል ማራማዊት በሁለተኛ ጽህፏ ( አስተአየቷ) የሰጠችው አስተያየት አንጀት አርስ ነው ይቀረታና ይህን ቃል ጠቀመው ያልሽውም ይቀርታ አያስፈልገውም ይህ ጉጅሌ መሰቀል የሚገባው ነው. አስተአየት ሰጭዎችን በተመለከተ እናውቃለን ባዮች አገ ተደፈረ ብለው ያሉትን ደህና አረገሽ ነው ማነነታቸወን ያስቀመጥሽው ይበል የሚያሰኝ ነው. በጣም አዝነሽ እና ተናደሽ መሆኑ ግልጽ ነው. የፈለገ ቢሰደቡ ሲያንሳቸው ነው. ደሞ ስድብ ሳይሆን እወንተኛ እንሱነታቸው ነው. ኢትዮጵያ መቼ ጀምሮ መዋረድ የጀመረችው ?????? ምን ያረጉ ፍርፋሪ አይናችወን አሳውሮት እንጂ . ፓርላማ አጋዚህ ተማምኖ ሲያቀረሻ ምነው ዝም አላችው. ተቃዋሚዎች እኮ አገር ለምን ይጠፋ እያሉ ሲሟገቱ እንዚህ ሰዎች ልጅ እናም የልጅ ልጅ ያዩ ናቸወ እኮ በግለሰብ ደረጃ ከተኬደ አዋራጁ ማነው????? ህዝብ ላይ የይደረሰ ያለወስ ነገር አልደግመወም ማራማዊት ገልጻዋለች. ያልገለጸሰችው ጎንደር ውስጥ ተገለስ አስክሬናቸው በመኪና የተጎተተ ሰዎች አሉ. ይህ ውረደት ብቻ ብቻ ሳይሆን ምን እንበለው??????????????????? የዚህ የጥንብ መንግስት ጉድ ጊዜው ደርሶ እናያለን ደርግ አረገ እያለ የማይናገር አጽም እያወጣ እራሱ የገደላችውንም ደረግ የገደላችወንም አስክሬን እያስወጣ መለፍለፍ ሳይሆን ሰው እራሱ ወቶ ለጆሮ የሚሰቀጥጥ ስራወን ለመስማት ያብቃን. እውነት ነው አበበ እንደውም እውነት ነው እኔም ምነው ባልክ እያልኩኝ ነው በህዝብ በእርዳታ ገንዘብ እሳሪያ መግዛት አቁም!!!!!!! የህዝብ ገንዘብ ስዊዝ ባንክ እና ቻይና እና በግለሰብ ስም አብት ማካበት ይቁም!!!!!!! በየስር ቤቱ ሰቆቃ እና ቶርች ይቁም!!!!!ባለ ጥሩ ነበር ይህን ቢልም ሃሰት አይደለምና አይስጠይቅውም. አቤ ላረምህ አይደለም ማንም ከሰራው በላይ ሴትሃል በዚህ አጋጣሚ ታማኝ በየነን ግን ጥረቱ እና አለመሰልቸቱ ጥንካሬወን ሳላድንቅ አላልፍም ታማኝን ምን አመጣው እንዳትሉኝ በየአጋጣሚው ማድነቅ ስለምወድ ነው. በርታ. አዲስ አድማስ?????? መለስ ስለመለስ ምን ሊል ትጠብቃለህ. መሳቅ ነበረብህ ማራማዊት እውነቷን ነው.

  29. የበላይነሽ?
    | #29

    ምንድነው የምትይው?
    የውሸት ችርቻሮ ይቁም ከሚለው ጋር ያንቺ አስተያየ ግንኙነቱ ምንድነው?
    ማድነቅ ትችያለሽ ግን ምነው መስመር ሳትሽ?

  30. የበላይነሽ?
    | #30

    ምድነው የምትይው?
    አስተያየትሽ የውሸት ችርቻሮ ይቁም ከሚለው ጋር ምን ግንኙነት አለው?
    ማድነቅ መብትሽ ብሆንም መስመር አልወጣሽምን?

  31. ደንድር
    | #31

    አቤ ጀግናወን አድንቄ የጻፍኩትን አስተያየት ወዴት ወሰዳችወት????? በላይነሽ የአቶ መለስ መደንገጥ ኖርማል ቢሆንም ለየት ያለው እኮ ቅንደባቸው ጸጉራቸውን ሊነካ ምንም አለመቅረቱ ነውናንገቱን መድፋቱ እንኳን ማስኬ ተላጠ ብሎ ነው.ለማንኛወም አቤ ከታሪክም ታሪክ ሰራህ.

  32. በላይነሽ
    | #32

    የበላይነሽ በድንብ አድርገሽ አንብቢው::ጋዜጠኛ አበበ የጻፈውን በተመለከት ለተቃዋሚዎቹ የሚሆን መልስ እናንተ አሞራውን ከአደነቃችሁ አበበንም አዲንቁት::ሁለቱም ለዓላማቸው የጸኑ ናቸው የሚለው መልስ ነው::
    ሁለተኛው አቶ መልስ ደነገጡ አልደነገጡ ከሚለው ይልቅ መተኮር ያለበት ምን እንድምታ ያመጣል የሚለውን መመልከቱ ይሻላል::ለዚህ የስጠሁት አስተያየት አንብቢው::
    አቶ ደንድርም የአበበ ክስ ምን ሊያመጣ ይችላል የሚለውን ተመልከተው::መድንገጥ ጊዜአዊ ነው::

  33. smtm
    | #33

    Abebe:
    For those who love the unity of Ethiopia, for freedom of speech, for those who are against tyranny, for those whose blood shed with no justice, for those who are starved without any aid, for those who are suffering under racist black tribal dictator-you are the role model. The day I saw you confronting a dictator, I say to myself, YES. Dictators love to bully, lie,inflate their ego, live in a dream world where no one lives,and anything that come against them make them terrified. You are a true Ethiopian who stand for human right, justice for all, and a united Ethiopia. Thank you, and we will follow you foot step!!!!

  34. ምንድነው ነገሩ???
    | #34

    አስተያየት ለምን ታነሳላችው??????????????????????? ያማችዋል????? ሁለቴ አነሳችወት በሉ ደህና ሰንብቱ ስራም አላጣው ሁለተኛ . ዞር ብዬም አላያችው. ለማንኛወም አቤ በጣም አድናቂህ ነኝ. ይህን ጦጣ ጭላዳ አስመሰልከው.

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።