የማይዋሽ አለወይ? አደገኛ ውሸታምስ ምን ይመስላል? በበላይነህ አባተ

June 25th, 2012 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ
  1. ውይ አሳረፍከኝ
    | #1

    እዋሻለሁ አልዋሽም ብዬ ብጀምር ጥሩ አይደለም ሌላው የነ መስተዋት ነውና

    ላመሰግንሁ የምወደው የማውቃውን ሰው ሁሉ በመልክ በመልኩ ማስቀመጥ እችላለሁ
    ነገ እንደማይመጣ እያወቀ ነገ እክፍልሃለሁ ብሎ ዱቤ የወሰደውን ደምበኛዬንና ሰው አያቅም ብሎ በሞቱ እናቱ ስም የሚለውን ከተፎ ጋደኛዬን ቦታቸውን አስይዛቸዋለሁ

    እኔን የቸገረኝ
    ትልቅ ካምፓኒዎች ውሸትና አገር መሪዎች ህዝብ ተወካይ መሪዎች ነው
    አውቆ ስላለገደለህ በሰዓቱ ረፖርት ስላላደረገህ ፓሊሲዎን በድንብ ስላላነብብህ …
    እኛ ከስልጣን ሳንመጣ የነበረ የቆየ ችግር ነው በርግጥ ቃል ብንገባም ይህን ያህል የከፋ አለመስለንም…

    የሚገርመው ከታዳጊ አገሮች ይልቅ ባደጉት አገር ይሄ ጎልበት ብሎ በመታየቱ … ስልጣኔ ያፈራውና የዳበረው ውሸት
    ከጉዳዩ ጋር ያልተያያዘ ስታቲስክስ መጠቀም ወይም ለትንሽ ጉዳይ ሚሊየን ቃላት ማንጋጋት….በጋዜጣ በሬዲዮ መደጋገም
    ልረዳው ነው ልርዳህ ብሎ ማስታወቂያ ማውጣት …
    ከ 5 ብር በላይ ብሎ ማስታወቂያ ውጭ ለጥፎ አንድም ዕቃ በ 5 ብር አይሸጥም…

    ከሁሉ ሁሉ ለስራ ፍለጋ ራስን ከፍ ከፍ አድርጎ ልምድና ሃላፊነት አጋኖ መጻፍ ይጠበቃል…መከራ
    በልዬ ቻው

  2. ውይ አሳረፍከኝ
    | #2

    እዋሻለሁ አልዋሽም ብዬ ብጀምር ጥሩ አይደለም ሌላው የነ መስተዋት ነውና
    የማመሰግንህ የማውቀውን ሰው ሁሉ በመልክ በመልኩ ማስቀመጥ ስላስቻልከኝ ነው

    ነገ እንደማይመጣ እያወቀ ነገ እክፍልሃለሁ ብሎ ዱቤ የወሰደውን ደምበኛዬንና
    ሰው አያቅም ብሎ በሞቱ እናቱ ስም የሚለውን ከተፎ ጋደኛዬን ቦታቸውን አስይዛቸዋለሁ

    እኔን የቸገረኝ
    ትልቅ ካምፓኒዎች ውሸትና አገር መሪዎች ህዝብ ተወካይ መሪዎች ነው
    አውቆ ስላልገደለህ ሃላፊነቱ አነስተኛ…
    በሰዓቱ ረፖርት ስላላደረገህ ልንረዳህ አንችልም… ፓሊሲዎን በድንብ ስላላነብብህ …

    በርግጥ ቃል ብንገባም … እኛ ከስልጣን ሳንመጣ በፊት የነበረ የቆየ ችግር ነው …ይህን ያህል የከፋ አልመስለንም…

    የሚገርመው ከታዳጊ አገሮች ይልቅ ባደጉት አገር ይሄ ጎልበት ብሎ በመታየቱ … ስልጣኔ ያፈራውና የዳበረው ውሸት

    ከጉዳዩ ጋር ያልተያያዘ ስታቲስክስ መጠቀም ወይም ለትንሽ ጉዳይ ሚሊየን ቃላት ማንጋጋት….በጋዜጣ በሬዲዮ መደጋገም
    ልረዳው ነው ወይም ልርዳህ ብሎ ማስታወቂያ ማውጣት …
    ከ 5ብር ጀምሮ ብሎ ማስታወቂያ ውጭ ለጥፎ አንድም ዕቃ በ 5 ብር አይሸጥም…

    ከሁሉ ሁሉ ለስራ ፍለጋ ራስን ከፍ ከፍ አድርጎ ልምድና ሃላፊነት አጋኖ መጻፍ ይጠበቃል…መከራ

    በልዬ ቻው

  3. በላይነሽ
    | #3

    የበላይነህ አባተ ስለውሽትና የማይዋሽ አለን?በማለት ያቀረበው ከስዕነልቦናና ከማህበራዊ ኑሮ ጋር ሲመዘን በጥሩ አገላለጽ ገልጾታል::አደገኛ ውሽት ምንድን ነው?ውሽትና ውነት አለን?የማይዋሽ ሰው አለን?በላይነህ አባተ በትክክል አስቀምጦታል::
    አንዳንዶቹን እንያቸው::
    አደገኛ ውሽት ማለት የሰውን ልጅ በሃስት ማጥፋት አደገኛ ውሽት ይባላል::የስውን ልጅ ከጥፋትም ማዳን በጥቅሉ ውሽት አይባልም ዋሽቶም ቢሆን::
    ውሽትና እውነት የሚባል ነገር የለም ማለትም ይቻላል::ሁለቱም የሚኖሩት በግዚያቸው ነው::ትናንት ውሽት የነበረው ዛሬ እውነት ሊሆን ይችላል::እውነትም ወደ ውሽት ሊቀየር ይችላል::ውሽትና እውነት ከአመለካከትም ጋር የተጣመሩ ናቸው::
    አንድ ሰው የራሱንም ሆነ የሌላሰው ሕይወት ለማዳን ቢዋሽ ውሽታም አይባልም::ለመርዳትም ከሆነ ውሽት አይባልም::
    ሰውን መወንጀልና መጉዳት ግን ውሽት ነው::እውነት ማንንም ሰው አይጎዳም::ያርማል:ያስተምራል:ይምራል::
    የውሽታም ሰው ባህሪ ምንድን ነው?
    ውሽታም ሰው ጉረኛ:ስዕነመግባር የጎደለው:ዘላፌ ለሰው ክብር የማይስጥ:ፈሪና ደንጋጣ: በራሱ የማይተማመን:ስም አጥፊ ና የመሳሰሉት ነው::ውሽታም ሰው ሆድ አደርና ብዙም ይመገባል::ውሽታም ሰው ጨካኝም ነው::የሚዋሸው ጨካኝ ስለሆነም ነው::
    ሰዎች እንዳይዋሹ ምን መደረግ አለበት የሚለውን ለበላይነህ ልተወው::

  4. ውይ አሳረፍከኝ
    | #4

    ማንኛውም ውሽት ጥሩ ነው ባይባልም
    ስለ ውሸት ስንነጋገር አንድ ሰው እንዲዋሽ ወይም
    ውሸቱ ያስፈለገበት ምክንያት ወይም ሊያስገድደው የቻለውን ሁኔታ ብናይ እኔም ብሆን ከዚህ ውጭ አላደርግም ወይም ፍርድ በራስ የሚያሰኙ ሁኔታዎች እንዳሉ መርሳት አይገባም

    እኔን የሚያስፈራኝ ከአንድ ሰው ውሸት ባህርይ ይልቅ በድርጅት ደረጃ የሚዋሹ ውሸቶች ዓለምን እያጠፉ ይገኛሉ አይን አውጥተውም ይክራክራሉ በሕዝብ መገናኛም ድርቅ ብለው ይዋሻሉ

    የሚያሳዝነው ነገር ደግሞ
    1. ውሸቱ ሲጋለጥና ውሸታሞቹ ሲያዙም ብዙ ማምለጫ አላቸው
    2. ያደረሱት ጥፋት መጠንና ዘለቄታዊነት
    ለቀጣዩ ትውልድ ሲተርፈውና በሰዓቱም ብዙ ሰው ፈርቶ ውሸቱን በመቃወም ፋንታ ለዕውነት አለመቆሙ ነው

    ላነሳሁት ነጥቦች ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው ጣሊያን ኢትዮጵያን ሲወር የተጠቀሙት ፕሮፓጋንዳ ሁለቱን ብጠቅስ
    ሀ. የጣሊያን ፍላጎት ኢትዮጵያን ለማሰልጠን ነው
    ለ. እኛ መስፋፋት እንጂ ጦርነት አንፈልግም ነበር ያሉት

    ይህንን ብለው በዓለም ፊት ሲለፍፉ
    አዎ ጣሊያኖች ኢትዮጵያን ሊያሰለጥኑ ነው ብሎ ለነሱ ምስክርነት የሚቆሙ የአገር መሪዎች ነበሩ

    ስለዚህም ከሰው ብፈራ ፈሪን ነው
    በይበልጥ ግን ከግለሰብ ይልቅ የድርጅት ውሸታም እፈራለሁ ምክንያቱም ብዙ ፈሪዎች በውስጡ አሉና
    ብዙሃኑ ሕዝብም ፈርቶአቸው ስለድርጅቱ ወንጀል ቢያውቅም ማውራት አይፈልግም

    አንዳንዴም ተበዳዩ ፕሮፓጋንዳው የሚያስከትለውን ጉዳት መገንዘብ የሚሳነው ሁኖ ሲገኝ ከማየት የበለጠ የሚጎዳ ነገር የለም

    በእኔ እይታ የአሁኑ ዓለም ሁኔታ በዚህ ደረጃ ላይ ነው!!!!

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።