የኛ ችግር፤ በተለይ የግንቦት ሰባት፤ “ከኤርትራ ሽሽት” በየኔታ ተክሌ
ከዚያ ወደዚህ ስመለስ፤
ከአንድ ወር ቆይታ በሁዋላ ወደምኖርበት ከተማ ተመልሼ ከአውሮፕላን ዱብ ከማለቴ ነው ከአውሮፕላን ጣቢያ የተቀበለኝ ሰው “ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ ሞቱ እየተባለ ይወራል” ብሎ ያረዳኝ። ይሄ ወዳጄ ዜናውን ሲሰብርልኝ፤ ስሜቴ ሁሉ ተሰባበረ። የኛ አገር ፖለቲካ ሁኔታ የባሰውን ጨለመብኝ። ሰማይ ተደፋብኝ። አዘንኩኝ። ደበረኝ። ለመሆኑ እኚህ 30 አመት ኢትዮጵያን የወጉና ምናልባትም የአገራችንን ያለፉትን 21 አመታት ታሪክ የቀያየረውን ሂደት የመሩ፤ አሁንም በብዙ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ እንደወዳጅ የማይታዩ ሰው ሞት ለምን አስደነገጠኝ? ብዙ ምስጢር የለውም። ባጭሩ የፕሬዚደንት ኢሳይያስ መሞት፤ የኤርትራን ፖለቲካ ሊለውጠው፤ ያ ደግሞ በተራው የኛን ያማራጭ ድርጅቶች (ተቃዋሚዎች የሚለውን ቃል አልወደውም) ጉዞ የባሰ ሊያዘበራርቀው ወይንም ሊያጨልመው ይችላልና የሚል ስጋት ነው።
ኢሳያስ ቢሞቱ የሚተኩት ሰዎች ፕሬዚዳንት ኢሳያስ እስካሁን ሲከተሉት የነበረውን አካሄድ ይገፉበታል ብዬ አልጠብቅም። ከመለስ ጋር መስማማት ወይንም መግባባት ሊኖርባቸው ይችላል። ምንም ከመለስ ጋር ቢስማሙ፤ የኢትዮጵያን ተቃዋሚዎች በሙሉ አሳልፈው ይሰጣሉ የሚል ፍርሀት የለኝም። ቢያደርጉትም ግን አይገርመኝም። ምክንያቱም የምንጠያየቅበት ይሄ ነው የሚባል ይፋዊ ውል የለንምና። ይሁን እንጂ፤ የኢሕአዴግን ተቃዋሚዎች ማስጠለል ይቀጥላሉ ብየም አላስብም። ስለዚህ እኚህ ሰው ድንገት ቢሞቱ ምን ሊውጠን ነው፤? ከኤርትራ/ሻእቢያስ የተሻለ ምን ምርጫ አለን? ለዚህ ነው ባጭሩ የኢሳያስ ሞት ጭምጭምታ ያስደነገጠኝ። በዚህ ላይ ደግሞ፤ ከኤርትራ ጋር በተያያዘ ያለውን የኛን አብይ አማራጭ ፖለቲካ ድርጅቶች ፍራቻ አክሉበት። ስለዚህም …
ኤርትራን እያጣናት ነው፤ በራሳችን ስንፍናና ገብጋባነት
ይሄንን በተለይ ትልቁ ተቃዋሚ ድርጅታችን ግንቦት ሰባት የተረዳው አይመስለኝም። ከተረዳውም ፈርቷል ይሆን? በጸጥታና እጁን አጣጥፎም ባይሆን፤ ባደባባይ ምንም ሳይለንና ሳይጠቀምበት የኤርትራ እድል ሲያመልጠው እየተመለከትን ነው። እንዳቅሙ እየጣረ የሚገኘው ባለ4 አመቱ ግንቦት 7 ደግሞ እንዲሁ እንዳለ ባለ 40 አመቱን ድርጅት ሊሆን ይችላል። አሁን ባለው አካሄድ፤ ኤርትራ እያመለጠችን ነው ብዬ አምናለሁ። ኤርትራን አታንሱብን፤ በኤርትራ በኩል ትግል ከቶም አይታሰብም ብለው የሚያስቡት፤ የዚህ ጽሁፍ ጉዳይ አይደሉም። ይሄ ጽሁፍ የሚሞግተው፤ በኤርትራ በኩል ትንሽ ተስፋ አለ ወይንም ነበር ነገር ግን እነዚህ እነዚህ ችግሮች አሉና መስተካከል አለባቸው ብለው ለሚከራከሩ ወይንም ኤርትራ ውስጥ ሄደን እንዲህ ያለ አፈናና በደል ተፈጸመብን ብለው ምሬታቸውን ለሚዘበዝቡት ነው። ስለዚህ ኤርትራን እንደ እድል ለማትመለከቱ፤ በዚህ ጽሁፍ ላይ ጊዜ አታጥፉ።
አንዳንድ ሰዎች፤ እዚያው ኤርትራ ሄደው የሞከሩትን ጨምሮ፤ በኤርትራ በኩል የሚታገሉ ድርጅቶች ውጤታማ ያለመሆን ችግር የሚመነጨው ከኤርትራ እንደሆነ ይናገራሉ። ከዚህ ቀደም ጥቁር ጫካ እያለ ይጽፍ የነበረ ሰው፤ እንዲሁም አቶ ሙሴ ተገኝ ጥቂቶቹ ናቸው። ይሁን እንጂ በኔና እዚያ ተጉዘው በመጡ ሌሎች ሰዎች አመለካከት ዋናው ችግር ያለው ከኤርትራ ሳይሆን፤ ከኛም ነው። የኤርትራ መንግስት ለኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች የሚችለውን ሁሉ ቢያደርግም፤ ያለውን ሁሉ ቢያቀርብም፤ ከአውሮፓም ከአሜሪካም ወደኤርትራ የሚሄዱት ሰዎች፤ እንዲሁም ከኢትዮጵያም ወደኤርትራ የሚመጡት ርስ በርሳቸው እየተከፋፈሉ፤ እያሴሩና ለሴራ ተባባሪ እየሆኑ መስራት እያቃታቸው፤ በሁዋላ ላይ ወደውጭ የመውጣት እድል ሲያገኙ፤ ሌላ ሰው እንኳን ተራውን እንዳይሞክር፤ ያስጠጋቸውን የኤርትራ መንግስት ወደማውገዝ ይዘላሉ። የኤርትራን ገንዘብ ቁርጥም አድርገው የበሉ ሁሉ በኤርትራ እርዳታ፤ አውሮፓ ወይንም አሜሪካን ሲገቡ ኤርትራን መሳደብ ይጀምራሉ። ችግሩ ግን በከፊል የራሳቸው የተቃዋሚዎች የግል ችግር፤ ወይንም ስልጣን ወዳድነት፤ ጽኑ የስልጣን ፍትወት እንጂ ሙሉ በሙሉ የኤርትራ አይደለም ብዬ አምናለሁ።
ችግሩ የነሱ ብቻ ነው ወይስ የኛም?
የኛ ተቃዋሚዎች ወይንም ግለሰቦች በዚህ በኤርትራ በኩል ስለሚደረገው ትግል የሚያቀርቡት አንዱ ክስ፤ “ሻእቢያ አያፈናፍነንም፤ እንደፈለግነው እንድንሆን ነጻነት አይሰጠንም፤ እንደውም ሀቀኛ ተቃዋሚዎችን ያስራል፤ ይገርፋል፤ ይገድላል” የሚለው ነው። በመሰረቱ ኤርትራም ይሁን ሌላ ሉአላዊ አገር፤ እንኩዋንስ ለትጥቅ ትግል፤ ለጉብኝትም ስንሄድበት፤ ያገራቸውን ልማድና ህግ ልናከብር ተስማምተን ስለሆነ፤ ኤርትራ ገብተን በነጻነት እንዳንንቀሳቀስ አደረጉን የሚለው ክስ ተቀባይነት የለውም። መጀመሪያውንም ስንሄድ ያንን አውቀን ነውና። ችግሩ ወዲህ ነው። ለምሳሌ፤ ኮሎኔል ታደሰ ይፈታ ብሎ መጠየቅ አንድ ነገር ነው። ያሉ ችግሮችን ማስቀመጥና የመፍትሄ ሀሳቦችን መሰንዘርም በጎ ተግባር ነው። እከሌ የተባለው የናንተ መኮንን ተነስቶ በምትኩ ሌላ ሰው ካልሾማችሁ አብረን አንሰራም ማለት ግን አግባብ አይደለም። ከኛ በኩል የምናቀርባቸው አንዳንድ ጥያቄዎች የኤርትራን ሉአላዊነት የሚጻረሩ ናቸው። ኤርትራን እንደመንግስት ካየን፤ ልክ ካናዳን ወይንም አሜሪካን ወይንም እንግሊዝን በምናይበት አይን ማየት አለብን። የነዚህን አገራት ሉአላዊነት የሚጻረሩ ስራዎች እንደማንሰራው ሁሉ፤ ኢህአዴግን ለመውጋትም ይሁን ለመርሳት ወደኤርትራ ካቀናን፤ የኤርትራን ሉአላዊነት ከሚጻረሩ ድርጊቶች መቆጠብ አለብን። በኔና በኛ አስተያየት፤ ትልቁ ችግር ያለው፤ የኛ ሰዎችና ድርጅቶች ጋር ነው።
ከተለያዩ ኤርትራ ደርሰው ከመጡ ታጋዮች ጠይቄ እንደተረዳሁት፤ ከኤርትራ ጋር በተያያዘ ያለው ዋንኛ ችግር፤ እንደ ግንቦት ሰባት ወይም ጥምረት ያሉ ፕሮፌሽናል አገር ወዳድ ፖለቲከኞች ወይም ድርጅቶች በግልጽ በከፍተኛ ልኡካን ደረጃ ግንኙነት ለመፍጠር ከመሞከርና ከኤርትራ ጋር በይፋ በልብ ሙሉነት ከመዋዋል ፈንታ፤ ከመስራትና ከመተባበር ይልቅ፤ ከኤርትራ ጋር ያለውን ግንኙነት በምስጢርና በጥርጣሬ ወይንም በግማሽ ልብ ወይንም ፈራ ተባ እያሉ መያዛቸው ይመስለኛል። እንደግንቦት ሰባት ያለው ተቃዋሚው ሀይል፤ እንደ ድርጅት፤ እንደ አንድ አገር-ወካይ ድርጅት፤ እንደ አንድ ለስልጣን የሚታገል ድርጅት፤ (ከዚህ ቀደም ከግንቦት ሰባት ውስጥ የማይመቸኝ አባባል የምንታገለው ለስልጣን አይደለም የሚለው ነው ብዬ ጽፌያለሁ። ሳይያዝ የሚተላለፍ ስልጣን የለምና)፤ በልበ ሙሉነት ከኤርትራ ጋር ስለሚኖረን የወደፊት ግንኙነት ለሻእቢያና ለኤርትራ ግልጽ ፖሊሲ አላቀረብንላቸውም። ምናልባት ከዚህ ቀደም አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዳመኑት፤ እሳቸው አንድ ሁለት ግዜ ወደ ኤርትራ ተጉዘው ሊሆን ይችላል። እስከምናውቀው ድረስ ግን ያኔም ቢሆን በምስጢርና መጀመሪያ ላልታወቀ፤ በሁዋላ ግን ለተገለጠ ተልእኮ እንጂ፤ ባደባባይ በተለይ ግንቦት ሰባት ከኤርትራ ጋር ስለሚኖረው ግንኙነት ግልጽ አቋማቸውን አሳውቀው አልሄዱም። ይሄ ምክንያቱ ፍራቻ፤ ጥርጣሬና ስጋት ይመስላል። ግንቦት 7 ወኔው አጠረው እንጂ፤ በብዙ መልኩ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን ወክሎ፡ ከኤርትራ ጋራ ወደፊት ሕዝቡ የሚያድሰው ወይም የሚያፈርሰው፤ ውል መዋዋል ይችላል ብዬ አስባለሁ። ምክንያቱም፤ ታጋይ ይመርጣል እንጂ አይመረጥም።
ግንቦት ሰባት፤ ህዝብና ኤርትራ
ከኤርትራ ጋር በተያያዘ አልፍ አልፎ በግንቦት ሰባት አመራር አባላት የተደረጉትን ቃለምልልሶች ተመልክቻለሁ። እነዚያም ድፍን ናቸው። ኢትዮጵያን ነጻ ለማውጣት ከኤርትራም ይሁን ከማንም ጋር እንሰራለን የሚል ጠቅላላ ፖሊሲ ነው። እንጂ፤ የኤርትራን አገርንት አውቀው፤ ሀሰብና የባህር በር ገለመሌ የሚለውን ጉዳይ ትተው፤ አብሮ እንደጎረቤት አገሮች መኖር እንችላለን በሚል ሀሳብ ላይ ሳይሆን፤ ወደፊት የኢትዮጵያ ህዝብ ይወስናል በሚል ሀሳብ ላይ የተመሰረተ ነው። ይሄ እንዳይሆን አንዱ የግንቦት ስጋት ህዝቡ ይመስለኛል። በፖለቲካ ውስጥ ህዝብ ተከታይ ነው። መሪዎቹ በዚህ ሂድ ካላሉት፤ ህዝብ የሚሄድበት መንገድ ወደገደል ወይንም የራሱን ጥቅም ወደሚጎዳም አቅጣጫ ሊሆን ይችላል። በርግጥ ሕዝብ የመሳሳት መብት አለው። ይሁን እንጂ፤ በተለያዩ ታሪካዊ ምክንያቶች የተነሳ ህዝብ ባይቀበለውም እንኩዋን፤ እኛ የኤርትራንም ይሁን ሌላ የሆነን መንገድ ተስፋ ካደረግንበት ወይንም ተስፋ ካየንበት፤ ከመጠቀም ወደሁዋላ ማለት የለብንም። እኛ እርግጠኛ መሆን ወይንም በደንብ ማሰብ ያለብን፤ ያለህዝቡ እሺታም ቢሆን፤ መንገዱ ያስኬዳልን? ለድልስ ያበቃናልን የሚለውን ነው። ህዝብ ቀስ በቀስ እየተቀበለው ሊመጣ ይችላል። አሁን ባይቀበለውም እንኩዋን፤ ካሸነፍን ቀስ እያለ ይቀበለዋል። ከዚህ ቀደም ከሰፊው እውቀቴ ቀድቼ እንደጻፍኩት ደግሞ “ድርጅት ደግሞ ህዝቡን ቀድሞ መምራት አለበት። የኢትዮጵያ ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ የኤርትራን መንገድ ሊያጸድቅ አይችልም። መንገዱን ቀዶ መሞከርና ሄዶ ማሳየት የድርጅቶች ፈንታ ነው። የሚደግፍ ይደግፋል። የሚቃወምም ይቃወማል። ግንቦት ሰባት ግን የኤርትራን መንገድ ማፈርም መፍራትም የለበትም።” አሁንም ይሄን እደግመዋለሁ።
እስካሁን ምን ሆነ? ወደፊትስ ምን ይዘየድ?
ቀደም ባለው ግዜ ከሞላ ጎደል ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ኤርትራን እንደደመኛና ጸረ-ኢትዮጵያ አድርገው ቢያዩም፤ በዚህ አስር አመት ውስጥ፤ በህዝብ ዘንድ ኤርትራን እንደወዳጅ ባይሆንም፤ እንደ አማራጭ የማየቱ ሁኔታ እያደገ መጥቷል ማለት ይቻላል። ለዚህም የብዙ ኢትዮጵያዊያን የኤርትራን ቴሌቪዥን መመልከት አንድ ማስረጃ ነው። ለሽሽትም ይሁን ለትግል ብዙ ኢትዮጵያዊያን ወደኤርትራ የሚያደርጉት ጉዞም ሌላ ማስረጃ ነው። ስለዚህም፤ ከኤርትራ ጋር ያለን ግንኙነት ይፋዊና በመገናኛ ብዙሀን በደንብ የምንለፍፈው መሆን አለበት እንጂ የምናፍርበት፤ የምደብቀው ወይንም የምንሸማቀቅበት መሆን የለበትም ብለን እናምናለን። የኛ ሀሳብ እንዲህ ነው፤ ከበሰለውና ከመደበኛው ተቃዋሚው ሀይል በኩል፤ በግልጽ ወደኤርትራ ተጉዞ ከኤርትራ መንግስት ጋር የሚመክርና ለህዝብ ይፋ የሆነ ፖለቲካዊ ውል የሚዋዋል ልኡክ ያስፈልጋል። ከኤርትራ ጋር፤ ወደፊት ስራችንን የምመዝንበት፤ የምንለካበት፤ ህዝብም ተከብሯል ወይንም አልተከበረም ብሎ የሚታዘብበት፤ ግልጽ ፖለቲካዊ ውል መግባት አለብን ብለን እናምናለን። ያ ውል ወይንም ሰነድ ወይንም ግልጽ ስምምነት ነው ኤርትራ በርግጥም ከተቃዋሚው ጋር ለመስራት ፍላጎት አላት ወይንስ የላትም የሚያሰኘን። በርግጥ ባዶ ውል ብቻውን የሚፈይደው ነገር የለም። ይሁን እንጂ፤ ለመጪው ጉዟችን ይፋ ውል በጣም ወሳኝ ነው። ያለ ይፋ ውል ወደኤርትራ የምናደርገው ጉዞ ያው ያለፉትን አስራ13 አመታት የተጓዝንበትን አይነት ነው የሚሆነው።
“ሻእቢያ አይረዳም፤ እንዲያውም የኢትዮጵያን ታጋዮች እየጠበቀ ሽባ ያደርጋል” የሚሉትን ሀይሎች ክስ ችላ ባንለውም፤ ሻእቢያዎቹ በይፋ ባይሆንም፤ “እኛ ሁሉን አድርገናል ነገር ግን ተቃዋሚዎቹ ናቸው ደካሞች” የሚሉት መልስም ችላ የሚሉት አይደለም። “እኛ ክላሽ፤ ፓስፖርት፤ ስልጠና፤ ስንቅ አቀረብን፤ እነሱ ግን አልሰሩበትም” ነው የሚሉን። ኮሎኔል መንግስቱ እኛ ትጥቅና ስንቅ ሰጠን፤ እንግዲህ ወኔና ልብ አናስታጥቅ እንዳሉት መሆኑ ነው። በነገራችን ላይ የሻእቢያ ተንኮልና አሻጥር ኤርትራ ደርሰው በመጡ (አንዳንዶቹ የበሉበትን የኤርትራ ወጭት ሰባሪዎች ናቸው) ተነግሯል። የኤርትራ ውለታ ግን እስአከአሁን በብዛት አልተነገረም። ምናልባት የሚያበረውን ተዋጊ ጀት ወደኤርትራ ይዞ የገባውና ካናዳ የመጣው የቀድሞ የአይር ሀይል አብራሪ፤ ሻምበል ተሾመ ተንኮሉ ብቻ ነው የኤርትራን ውለታ የመሰከረው። ኤርትራ ለኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሀይሎች ያደረገችው እርዳታ፤ ሻእቢያና ወያኔ ወደጫካ ሲገቡ ከኢትዮጵያ ጠላቶች ካገኙት እርዳታ የላቀ ነው። ኤርትራ ረዳችም አልረዳችም፤ ኤርትራ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎችን በተገቢው መንገድ ረድታለች አልረዳችም የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል፤ ለዚህም ይሁን ለሌሎች ከኤርትራ ጋር በተያያዘ ለሚነሱ ጥያቄዎች በከፊልም ቢሆን መልስ የሚሆን፤ ነገ ውዝግብ ቢፈጠር የምንከራከርበት፤ ወይንም ከጊዜ በሁዋላ ኤርትራን ራሷን ቃሏን እንዳልጠበቀች የምንከስበት፤ በግልጽ የምንነጋገርበት ይፋ የሆነ ውል ወይንም ሰነድ የት አለንና ነው? የእስካሁኑ ጉዟችን ሰነድ የለሽ ወይንም ውል የለሽ ነው። ይሄ መታረም አለበት።
አሁንም ግልጽና ይፋዊ ውል ያስፈልገናል
በዚህ ከኤርትራ ጋር በሚኖረን ግንኙነት ላይ ከዚህ በፊት ጽፌያለሁ። ይሄ የነዚያ ቅጣይ ተደርጎ ይወሰድልኝ። ከኤርትራ ጋር ያለን ግንኙነት ይፋና በይፋ ውል መሆን ስለሚገባበት አግባብ ብዙ ምክንያት መደርደር እንችላለን። አንዱ፤ ይፋ የሆነ ውል፤ ከዚህ ከምእራቡ ዓለምም ይሁን ከአፍሪካ ወደኤርትራ ለምንሄደውና የምእራብ አገር ዜግነት ላለንም ይሁን ለሌለን ሰዎች፤ ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ ለሚነሳብን ክስ እንደመከላከያ ያገለግላል። ኤርትራ ከአልሸባብም ይሁን ከሌሎች ሽብርተኞች ጋር በተያያዘ በሚነሳባት ክስ አብረን ተከሳሽ አንሆንም። ብንከሰስም እንኩዋን፤ አስቀድመን አላማችንንና ከኤርትራ ጋር ያለንን ግንኙነት ግልጽ ካደረግነው የከፋ ውንጀላ ሊደርስብን አይችልም። ፖለቲካዊ አካሄዳችን ግን ስውር ከሆነ፤ አንዳንዶቻችንን፤ በተለይ የምእራብ አገር ፓስፖርት ወይንም በቤተሰብ፤ ማለትም በሚስቶቻችን ወይንም በልጆቻችን ከምእራብ አገራት ጋር ትስስር የሌላቸውን ለጥቃት ያጋልጣል)። ይልቅስ ከኤርትራ ጋር የሚኖረን ግልጽ ውል፤ ስራችንን ለሚመለከታቸው አለማቀፍ ተቋማት (የተባበሩት መንግስታት፤ የአፍሪካ ህብረት) አሳውቀን በልበሙሉነት ለመንቀሳቀስ ያግዘናል። በኤርትራ ጉዳይ ላይ፤ ለጠላት ህቡእ ብንሆን ለወገኖቻችንና ለምእራባዊያን ህቡእ መሆን ግን የምንችል አይመስለኝም። መሆንም የለብንም።
ስለህቡእነት ሲነሳ፤ ስለኛ ድርጅቶች የሚያናድዱኝ አንዳንድ ነገሮች አሉ፤ ብዙ ነገሮቻችን ከራሳችን ሰዎች ድብቅ ናቸው፤ ከጠላት ግን ድብቅ አይደሉም። ከኤርትራ ጋር ያለን ግንኙነት ራሱ አንድ ምሳሌ ነው። ጠላት በሚገባ ያውቀዋል ወይም ባያውቀውም እንደሚያውቀው በግምትና በስማ በለውም ቢሆን ያስወራል። ወዳጆቻችን ግን ከኤርትራ ጋር በተያያዘ ከጠላት ሰምተው እንደሁ እንጂ ከፖለቲካ ድርጅቶቻች ተነግሯቸው የሚያውቁት ውሱን ነው። ሁለተኛ፤ አንዳንድ ነገሮችን እስመጨረሻው ልንደብቃቸው ካልቻልን፤ ወዳጆቻችን ከኛ ከራሳችን ማወቅ አለባቸው። ለምሳሌ፤ የፖለቲካ መሪዎቻችን በምስጢር ወደኤርትራ ከተጓዙ፤ የፖለቲካ መሪዎቻችን በከፍተኛ ምስጢር የተያዘ የኤርትራ ጉዞ ጉዳይ ይፋ ወጥቶ እኛን መሳቂያ፤ ወዳጆቻችንን ደግሞ ማሸማቀቂያ ከሚሆን፤ መጀመሪያዉኑ ከኤርትራ ጋር የመስራቱን ጉዳይ ምስጢር አለማድረግ ጥሩ መፍትሄ ነው። የተቃዋሚ መሪዎች እንደአመራር ወደኤርትራ ስንገባም ስንወጣም በይፋ ቢሆን መልካም ነው። ሌሎች ሚስጥራዊ ጥብቅ ተልእኮዎች እንደተጠበቁ ሆነው ማለቴ ነው። ለዚህ በይፋ ከሌላ አገር ጋር ስለመስራት ጉዳይ ደግሞ የኤርትራ ተቃዋሚዎች ራሳቸው ጥሩ ምሳሌ ናቸው። ራሳቸው የኤርትራ ተቃዋሚዎች እኮ ከኢህአዴግ ጋር መስራታቸውን ምስጢር አላደረጉትም። ስለዚህ እኛ ለምን እና ከማን ምስጢር እናደርገዋለን??
ለነገሩ፤ ወያኔም ነቅቶብናል
ለነገሩ ወያኔዎቹም ከኤርትራ ጋር መስራት ሐጢያት ነው ብለን እንደምናስብና እንደምናፍርበት ነቅተውብናን መሰል እየደጋገሙ የሚከሱን በሁለት ነገሮች ነው፤ ከሻእቢያ ጋር በመስራትና በሽብርተኝነት። ኢህአዴግ ብቻ አይደለም፤ አልፎ አልፎ ኢህአዴግን የሚተቹ እንደሪፖርተሩ አማረ አረጋዊ አይነት የኢህአዴግ ደጋፊዎችም ያገር ቤቱንም ያገርውጩንም ተቃዋሚ የሚከሱበት አንዱ ነገር፤ ሻእቢያን በግልጽ አለማውገዝ ወይንም ከሻእቢያ ጋር መስራት ነው። እኛም በተደጋጋሚ እንዳይታወቅብን የምንሸሸው ይሄንን ከኤርትራ ጋር የመስራትን ጉዳይ ነው። በመሰረቱ እኛ ለኢትዮጵያ ያለን ፍቅር የኤርትራ ተቃዋሚዎች ለኤርትራ ካላቸው ፍቅር የሚያንስ አይመስለኝም። የኤርትራ ተቃዋሚዎች ደግሞ በግልጽና በአዋጅ ከአዲስ አበባ አዋሳ፡ ከአዲስ አበባ መቀለ እየተመላለሱ ይሰራሉ። ስለዚህ እኛ ከኤርትራ ጋር መስራትን ልናፍርበትም ልንሸሸውም አይገባም። በውልና በሰነድ በይፋ እስከሆነ ድረስ። እንጂ ኤርትራንና ሻእቢያን ስንከስ መኖር የለብንም። አንዳንዶቹ የኛ ተቃዋሚዎችማ በተቃራኒው፤ አሁንም ከ21 አመት በሁዋላ፤ ሻእቢያን ነው እንደጠላት አድርገው ቀን ተሌት የሚያወሩት። እነአረና ትግራይን አልፈርድባቸውም፤ የትግራይን ህዝብ የሚማርኩበት ሌላ አጀንዳም የላቸውምና። የመድረክ ግን ምን ይባላል? ጭራሹኑ ብሶበት፤ ከጉራፈርዳ ወረዳ በሺዎች የሚቆጠሩ አማሮች ተባረሩ፤ የተወሰኑትም በመኢአድ ቢሮ ተጠልለዋል የሚል ዜና እየተሰራጨ፤ “በሁመራ አካባቢ ወርቅ የሚያወጡ 250 ኢትዮጵያውያን በሻእቢያ ተጠለፉ” ብሎ መግለጫ ያወጣል። አሁን በማዬ ሞት ይሄ የራሱ የኢህአዴግ እንጂ የመድረክ ችግር ሊሆን ይገባል? የሆነ ሆኖ …
በዚህ ሁኔታ ውስጥ፤ እንደግንቦት ሰባት ያሉ ጠንካራና ታላላቅ ድርጅቶች፤ ኤርትራን በይፋ እንደአጋር አውቀውና ይዘው፤ በግልጽ ውል ወደኤርትራ ገብተው ግንባር ቢመሰርቱና የትጥቁንም የፕሮፓጋንዳውንም ትግል ከዚያ ቢያደርጉ፤ የወያኔ ጦር እየከዳ ወደግንቦት ሰባት የማይገባበት ምክንያት አይታየኝም። ለምሳሌ የዛሬ አራት አምስት አመት አካባቢ እነከማል ገልቹ ከዱ ሲባል ጦሩ ከየግንባሩ መከተል ጀምሮ ነበር። ከዚያ በሁዋላ ግን እኛም አልገፋንበት፤ ጦሩም ብዙ አልከዳም። ይሄ የጦሩን ማስከዳት ስልት አንዱ የትግል ስልት ሊሆን ቢችልም፤ የራሱም ችግር አለው የሚሉም አልታጡም፤ ኤርትራ ውስጥ የተጠናከረ የተቃዋሚ ጦር ካለ፤ ወያኔ ኤርትራን ወሮ ይይዛል የሚል ስጋት። ይሄ በኛ የጦር አማካሪዎች ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነው። ወያኔ ከኤርትራ ቢገጥም በቀላሉ ያሸንፋል አያሸንፍም የሚለው ክርክር እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ወያኔ አለማቀፍ ህግጋትን ጥሶ ኤርትራን ይወራል ወይ የሚለውም አንድ መመለስ ያለበት ጥያቄ ነው። ስጋቱ ቢያስኬድም እንኩዋን፤ አምነን የምንገባበት ስጋት ነው እንጂ፤ ያንን አስበን ከኤርትራ ጋር ለመስራት ወይንም ካምፓችንን በዚያ ለማድረግ የምንተውበት አጥጋቢ ምክንያት አይደለም።
ባጠቃላይ፤ ከኤርትራ ጋር የኤርትራን ሉአላዊነት ያወቀና የኤርትራንም የኢትዮጵያንም ብሄራዊ ጥቅም ያስቀመጠ ውል መግባት አንዱ የትግል አማራጫችን ነው። በኤርትራ በኩል ያለው ትግል ያልገፋው ከኤርትራ ጋር በግልጻና በይፋ የሚዋዋል ጠንካራና ደፋር ሀገር ወዳድ ድርጅት ስላልተገኝ ነው። ያንን ክፍፈት ሊሞላ የሚችል ደግሞ ከግንቦት ሰባት የተሻለ የለም። ግንቦት ሰባት ግን እስካሁን ድረስ በዚህ ጉዳይ ላይ ተሻሸ እንጂ አልቆረጠም። የመቁረጥ ቀን ካለፈ ሰነበተ። ባለአርባ አመቶቹን ድርጅቶች እየተቸን፤ እኛም በነሱ ሰማኒያ ላይ አርባችንን እንዳናከብር አሁን ወደኤርትራ መጓዝ አለብን። ይሄ ለግንቦት ሰባት ብቻ አይደለም። ለሰኔ ሰባቶችም ለሀምሌ ሰባቶች እንጂ። ለዳላሶች። የሽግግር ምክርቤት መቋቋም ያለበትም፤ ኦታዋና ዳለስ ዲሲና ለንድን ሳይሆን፤ አስመራና ምጽዋ ነው። እዚያው አፍንጫቸው ስር። የሕወሀት አፍንጫ ስር። እየተሽለኮለክንና በሽፍንፍን ሳይሆን፤ በግልጽ ካልቀረብናቸው በስተቀር፤ የኤርትራ መንግስትን ሙሉ-እርዳት ልናገኝ አንችልም። በግልጽ አጀንዳ አብረውት የሚሰሩት እነ ኦነግ እያሉም፤ የኤርትራ መንግስት አጀንዳችንን በሆዳችን ደብቀን የምንጠጋውን ሌሎች ኢትዮጵያዊያን የሚረዳበት ምክንያት አይታየኝም። ግልጽና ይፋዊ ፖለቲካዊ ውል ከኤርትራ ጋር አሁኑኑ። ነው ወይስ ግራ ገብቶኛል?
ለማንኛውም ከበረታሁ ይሄንን ርእስ እቀጥልበታለሁ። በተለይም የኤርትራና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሞች ሳይጋጩ ጎን ለጎን መሄድ ይችላሉን? ለኤርትራ ሕልውና የኢትዮጵያ መፈራረስ የግድ ነውን? በሚሉት ርእሶች ላይ እቸከችካለሁ።
የኔታ ተክሌ ነኝ፤ አሁን ደግሞ ሕይወት ቶሮንቶ ጥሎኛል። ሰኔ፤ 2004/2012



thank you an agent from shabia. You’re a lier
EPLF and its leadership wasn’t and won’t have a positive
impact for Ethiopia. Unless the opposition understand the
never ending desire of the mentioned anti Ethiopian junta
and absolutely cut all ties with it, it’s only TPLF/EPRDF
that gets the benefits along side its creator EPLF. You
can down look my idea,but the opposition must wake up and
say no to pro EPLF and TPLF camps at all cost.That is the
only way to divert the destructive direction Ethiopia is
forced to go since the two ethno centric groups controled
the center of political,economic and military power in Addis
abeba and Asmera respectively. Let us divorce them completely
to save Ethiopia.
የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ : እስቲ ያሁኑን የራሱን ድርሻ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ይንገረን:: ከዚያ አስተያየት መስጠት ይቻላል:: በጣት መቀሰር ሁሉም ይችላሉ::
የኔታ ተክሌ:
የኔታ ማለት እኮ መምህር ወይም በዘመናዊው አባባል ፕሮፌሰር እንደማለት ነው:: ታዲያ መምህር ተክሌ የኔን ሀሳብ ያልተቀበላችሁ ተማሪዎች ጥያቄ አልቀበልም:: ለመወያየት የምንችለው ሀሳቤን ከተቀበሉ ጋር ነው የሚለው መግቢያህ እውን ለየኔታነት ያበቃል? እንደኔ አመለካከት ይህ የየኔታ አቀራረብ ሳይሆን የሻምበል ባሻ የአለቃና የምንዝር አቀራረብ ይሆናል:: “… ስለዚህ ኤርትራን እንደ እድል ለማትመለከቱ፤ በዚህ ጽሁፍ ላይ ጊዜ አታጥፉ።” የሚለው አነጋገር ያንተን ንድፈ ሀሳብ ውድቅ ሊያደርግብህ ስለሚችል ብቻ አታንሱብኝ ማለት ከራስህ ጋር ብቻ እንደመሟገት አይሆንብህም:: በፈረንጆቹ አነጋገር My way is the highway አልሆነብህም:: አንድ ግለሰብ ለዚያውም ሱሪውን አስተካክሎ ያልታጠቀ የ80 ሚሊዮን ህዝብ ጉዳይ ከኔ በስተቀር ላሳር ማለት ድፍረት አይሆንብህም? በስታስቲክስ (ሳይንስን ተመርኩዘን) የምንነጋገር ከሆነ የአንተ ድምጽ 1/80,000,000 ማለትም 0.0000000125 % መሆኑን ታውቃለህ? ይህ ማለት ደግሞ ያለማጋነን አልቦ (ዜሮ) ማለት ነው:: ታዲያ በየትኛው ሞራል ነው የህዝብን አጄንዳ በአንተ ወርድና ቁመት ልትለካው የዳዳህ?
የፈለግከውን ሃሳብ የማቅረብና የመከራከር መብትህን አከብራለሁ:: ይሁን እንጅ የመከራከርና የመተቸት መብቴን ልትገድብ የምትችልበት አመንክዮ ሊኖር አይችልም:: አዎን የኤርትራን የአሰብና ምጽዋን ባለቤትነት ብታልም ቅዠትህን ለማስጣል ብዙም የሚጨነቅ ያለ አይመስለኝም:: ይህ ደግሞ አንተ ያፈለቅኸው አዲስ የፈጠራ ውጤት ሳይሆን የመለስ ዜናዊና የስብሃት የበኩር ልጅ መሆኑን አገር ያወቀው ጸሐይ የሞቀው ነው:: የወያኔም ኪሳራ የሚቀዳው ከዚሁ የቅሌት ምንጭ ነው:: የበሰልክ የፖለቲካ ተንታኝ ብትሆን ኖሮ ግንቦት 7 በዚህ የኪሳራ ገበያ እንዲዳክር ልትመክረው ባልተገባህ ነበር::
“በፖለቲካ ውስጥ ህዝብ ተከታይ ነው። መሪዎቹ በዚህ ሂድ ካላሉት፤ ህዝብ የሚሄድበት መንገድ ወደገደል ወይንም የራሱን ጥቅም ወደሚጎዳም አቅጣጫ ሊሆን ይችላል” የሚለው አመንክዮህ ከአፍንጫህ ያልራቀ አስተሳሰብ መሆኑን መገመት አያዳግትም:: ግንቦት 7 ያለኢትዮጵያ ህዝብ ድጋፍ በብርሃኑ ነጋና በአንዳርጋቸው ጽጌ ኪስና ዝናር ሀገርን ነጻ ማውጣት ስለሚችል ህዝብ ባይቀበለውም ባፍንጫው ይውጣ ብለህ ልትሰብከን ዳርዳር እያልክ ነው:: ያልገባህ ነገር ግን ህዝብ ሀገሩን ነጻ ለማውጣት የመሪ ችግር ኖሮበት ወይም ማድረግ የሚፈልገውን የማያውቅ እንሰሳ ሆኖ አይደለም:: በጣሊያን ወረራ መሪው ከሀገር ሲሰደዱ በየጎጡ በጎበዝ አለቃ እየተደራጄ ጣሊያንን መውጫና መግቢያ እንዳሳጣው በታሪክ የተመዘገበ ነው::
ሌላው ጥሬ አስተሳሰብህ ጎልቶ የሚታየው የሀገርን ዘላቂ ጥቅም ከጊዜያዊ የአምባገነን ስልጣን ጋር ማያያዝህ ነው:: 1ኛ) የቱን ያህል ጊዜ ቢወስድም አምባገነን ራሱን በራሱ በልቶ መውደቁ ሳይታለም የተፈታ ነው:: ስለዚህ የወያኔን ጊዜያዊ አምባገነናዊ ድርጅት እድሜ ለማሳጠር የሀገራችንን የረዥም ጊዜ ጥቅም መስዋዕት ማድረግ የጤነኛ ባህርይ አይደለም:: 2ኝ) ማንም ሀገር ዘላቂ ጥቅም እንጅ ዘላቂ ወዳጅ የለውም:: ኤርትራም ከዚሁ ሀቅ ልናሸሻት አንችልም:: ዴሞክራሲያዊትና በሀገር ወዳድ የምትመራ ኢትዮጵያ ለዘመናት ንብረቷ የሆነውን ወደቦቿንና የባህር በሯን ለወራሪ አስረክባ እጇን አጣጥፋ ለጂቡቲ ወይም ነገ ወዳጅ ለምትሆነው ኤርትራ ትገብራለች የሚል ቅዠት ለኢሳያስም ሆነ ለሚቀጥለው አመራር ይታያል ብለህ የምታስብ ከሆነ ገና ከአንቀልባ አልወረድክም ማለት ነው::
ባገኜኸው አጋጣሚ ሁሉ ድምጽህን ለማስቆጠር የምታደርገውን ጥረት በውነት አደንቃለሁ:: ይሁን እንጅ ነጥቦችህ ቢያንስ ተራ ግንዛቤ (common sense) እና የፖለቲካ ሀሁ ቢጨመርበት ጥረትህ ፍሬ ያፈራ ነበር:: ምናልባት አነጋጋሪ (controversial) ለመባልና ትኩረትን ለመሳብ (to steal the limelight) የሚል ጉጉት (ambition) ካለህ ቦታው ይህ አይደለም:: የሀገር ጉዳይ የ እልህና የደም መንተክተክ ጉዳይ አይደለም:: ስለሀገር ስናስብ ከ እልህ አልፈን ስለዘላቂ ጥቅም ማሰብ አለብን:: ወደብና የባህር በር የሌላት ሀገር ኤኮኖሚዋ ብቻ ሳይሆን ድህንነቷም በጥያቄ ምልክት ውስጥ የገባ ነው::
ሌላው ኢሳያስ አፈወርቂ ከጭንቅላቱ ላይ ተኝቷል ብለን ብንገምት እንኳን ምዕራባውያን ለምን ከአምባገነኑ የወያኔ መንግስት ጋር ተሞዳሞዱ እያልን እየከሰስን እኛው ራሳችን ከአምባገነን ጋር መተሻሸት ይቅር የማይባል የሞራል ዝቅጠት ነው:: ከአምባገነን ጋር የተቃቀፈ ፖለቲከኛ እንዴት ብሎ የዴሞክራሲ አባዎራ ሊሆን ይችላል? ኢትዮጵያ ደግሞ በንደዚህ ያለው ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ጎዳና ለመጓዝ ፍላጎቱ የላትም:: ዶሮ ብታልም ጥሬዋን እንደተባለው ካልሆነ በስተቀር ሀገሩን በጫማው ስር የደፈጠጠ አምባገነን ጎረቤቱን ዴሞክራሴያዊ ሊያደርግ ድጋፍ ይሰጣል ማለት ጉም እንደመዝገን ይቆጠራል:: ስለዚህ ግንቦት 7 ያለፈውን የተሳሳተ አካሄድ አርሞ ከሆነ እሰየው ሊባል ይገባዋል::
የኔታ ተክሌም በውይይቱ ላይ ልጓም ለማድረግ መሞከር ከወያኔያዊነት በምን ይለያል? በሀገራችን ጉዳይ ሁሉም ዜጋ ያለ ገደብ ሊነጋገር የግድ ይላል::
አመሰግናለሁ::
ዋቆ ዘአጋሮ
‘…የኢሳያስ ሞት ጭምጭምታ ያስደነገጠኝ…’ ነው የሚሉት
እውነት እደነግጥላሁ ነው የሚሉት ኢሳያስ ቢሞቱ? ድብን ይበሉ!!! መለስንም ይጨምሩ ከፈለጉ!!!
የማንኛቸውንም መሞት ከመፈለግ ሳይሆን በአንድ ግለሰብ መኖርና አለሞኖር አምኜም አላውቅምና ነው!!
እንዴት ነው የሚሉት የኔታ? በነዚህ ሰዎች መዳፍ ከሆነ 80 ሚሊዮን የሚተነፍሰው ይኑሩ እላለሁ ግን ዕውነቱ ይሄ አይደለምና
ድብን ይበሉ!!! እኔ አልቃሽ ልሆን አልችልም! የሚያለቅስ ያልቅስ
የኔታታክሌ
ሰለቸኝ መረረኝ እኔን የሚለውን ዘፈን መርጠው
ምንም ርስዎ ቄስ ቢሆኑም በዚህ ዙሪያ ሌላ እንዳይጽፉ ገዝቼዎታለሁ በተክልዬ አይዘባርቁ
ነፍስ ይማር ብለን ልጆቻቸውን እንሳድጋለን
ወይ ቶሮንቶ እብድ ማምረቻ ሆነ እንዴ
አንተ ተከል የተባልክ ስው አንተ እራስክ ለምን ኤርትራ አትሔዽም ዝም ብሎ መለፍለፍ እንዳንተ እማ ቀላል ነው
ጉዳትና ጥቅሙን በተመለከተ አሁን በቁምነገር ላውራ
ከኤርትራ ጋር መሆን ያለው ጣጣ
1. አራት ኢትዮ መሪዎች ሲሰደቡና ሕዝባቸው ንብረትና ወታደሮቻቸውን ሕይውት ሰውተውበታል -
ምንሊክ እስካሁን ይወቀሳሉ ጃንሆይንም እንዲሁ መንግስቱን ለስደት አብቅቶታል መለስን እንጣልበት እያልን ነው
2. የኢትዮ ሕዝብ ንብረቱን ልጆቹን አጥቶበታል በይበልጥ ድሃው
3. ምሁሩ ነጋዴው ባለስልጣኑ ልጁን ለመላክ ፈቃደኛ ሁኖ አያውቅም አልላከም ደግሞ
4. በጃንሆይም ሆነ በደርግ ጊዜ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ግለሰቦች ድርጅቶች ሁሉ ለኤርትራ ነጻ መሆን ታግላል ደግፋል
5. ኤርትራ ሕዝብም ለመገንጠል ክፍተኛ መስዋዕት ከፍለዋል በሕይወት በንብረት በመሰደድ
6. በኤርትራ ጉዳይ ገብተን መደገፍም ሆነ መቃወም ጣልቃ ገብነት ብዬም አስባለሁ
7. መለስን ለመጣል ትግሉ በኢትዮጵያውን እንጂ የሌላ አገር መሪ ጋር አጉል ድርድር ገብቶ ጥቂት ምስኪን ኢትዮ ህይወት ለመስዋዕትነት አቅርቦ 80 ሚሊዮንን ፓለቲካ አቅጣጫ እንቀይራለን ማለት ትርፉ ያው በገሌ ነው ማን ሞቶ ማን ይጠቀማል
8. 80 በላይ ጎሳ ኢትዮ መስማማት አቅቶን የኤርትራን 9 መጨመሩ ችግሩን ይጨምር እንጂ አያሻሻልም
9. እንዲያውም ኤርትራ ያለው ችግር ለኛም እንዳይተርፈን ማሰቡ ጥሩ ነው
10, የውጭ ሃይሎች በጉዳዩ ይበልጥ ገብተው ችግሩን ይባባሳል
11. ኢትዮ በምስራቁ የመሃሉን የምእራቡ አካባቢ ያለውን ፓለቲካ ውጥረት ብንመለከተው መበተናችንን ያሳያል እንጂ ለአንድነት ብሎ መሳሪያ የያዘው አነስተኛ ነው
12. ዓለም ፖለቲካ ሁኔታ መለያየት ላይ ያተኮረ በመሆኑ እንዴት እንድሚቻል አላውቅም
13. ኤርትራ ዓረብ ናት ብሎ የሚያምነው ክፍል በአገሪታ ባህል ኢኮኖሚና ፖለቲካ ስር ሰዶ ይሰራል
ስለዚህም አንድ መሆን አይጠቅምም ሳይሆን የራሳችንን ውስጥ ችግር መፍታት ያልቻልን እንደ ኤርትራ ያለ ብዙ የውስጥ ፖለቲካ ችግር ያለውን አገር ልጨምር ማለት ችግራችንን እናብዛ ማለት ነው
የሃማኖት ቃንቃ ጎሳ ችግር ወጥሮ የያዘውን አገር አሁን እንቀላቀል ማለት ድሃውን የኢትዮ ጥቅም አያስከብርም
እንካንስ ኤርትራ ወንድሞች እህቶቻንን አብሮ መኖር ቀርቶ በማናውቀው አገር ተሰደን እንኖር የለ
ሱዳንን ሱማሌን ጅቡቲን ሆነታ ብትመለከቱ ጎስኝነት ሃይማኖት ፓለቲካ እየበተነው አንዳቸውም ራሳቸውን የቻሉ አገሮች መሆን አልቻሉም ኤርትራም ሁኔታ ከዚህ የተለይ አይደለም
ድሃውን ህዝብ አሳልፈን ላልታወቀ ሌላ ችግር አንስጠው
Do you know the secrete of Weyane (Meles) and Shaebia (Isayas)? G’7 has no the right to sign any agreement with the enemy of Ethiopia. As our past 20 years of Weyane history learned us, we have to be careful to sign any agreement with Shaebia. As Weyane and Shaebia signed an agreement to take some territories from Ethiopia, when they were in the jungle, after they became a government they were forming a hidden border committee without the knowledge of the Ethiopian people. Some of the committee members from Weyane were most of them pure Eritreans and half Eritreans. Their jungle agreement was hidden to the Ethiopians. Mr. Tekle I think this is what you want. Tekur chaka has written the reality happened in Eritrea during the 10 year movement of Arbegnoch Ginbar. After that all the secrete is exposed by the members who were representing Arbegnoch and is already give their witness as Tikur chaka explain it. If Tikur chaka was wrong, why not you oppose at that time. At this time the one who was challenging Weyane that is TPDM is annexed by Shaebia. All its website and radio program is closed. Why? Because TPDM has the power to defeat Weyane but Isayas doesn’t like that. Because he knows that he willn’t survive without Weyane.similarly, Weyane is the same thing. So, I strongly support G’7 the stand he took at this time. What I agree with you is the consequence of the two countries political situation if the rumor of the death of Isayas was true. It is better Meles to go before Isayas.
I am totally confused by Yeneta Tekle “analysis”. One simple question for Yeneta. Do we need permission from Woyane to protest in Ethiopian streets ? The answer is NO !! Why do we need Eritrea to topple Woyane then ?
Who helped us to mobilize million people in Addis streets in Miazia 30 six years ago ? Not Eritrea.
If we have few brave leaders like Andualem let alone Ethiopia we would have been a good example for fellow Eritreans to dump their “King” in Asmara.
Yeneta your analysis is based on the Gurella struggle pf Mao Tstong, from rural to urban Gorilla warfare. That tactic helped Woyane to tople Derg more than two decades ago.If you still believe that we have to follow the same pattern you are naive.
Revolution will be born in Addis by homegrown patriots the rest of us far from home get organized to help out. Yeneta, are you praying for God to give more decades for Isaias to rule Eritrea ?
Most Eritreans are shaken by the deteriorating health condition of Meles than Isais. Do you know why Yeneta ? Meles is on loan from Eritrea to destroy Ethiopia. Yeneta you have to confess you are a sinner ?
The whole of your idea is that of a traitor! How can you deliver such stupid idea that those who are killed and abused are the source of their weakness? They were hoping that they can strive for noble causes but the evil shabia intended to make them as tool and they denied to that anti-Ethiopia motives! You can not judge them sitting and talking with your big mouth in Torronto! Crap!!
ትልቁ የወያኔ ሥጋት በኢትዮጵያ የኤርትራን ልዋላዊነት አንቀበልም የሚል ድርጅት እንዳይፈጠር መሆኑን ማውቅ እንዲት ተሳነህ የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ በጭራሽ የኤርትራ ጉዳይ የመገንጠል ጉዳይ እንጅ የነጻነት ጉዳይ ነው ብሎ አይቀበልም እና ህዝቡ በሻብያና በወያኔ የተነጠቀዉን አንድነቱን እስካሁንም ይፈልጋል::
መገነጠልም ካለባቸው በአረብ ሃገር እርዳታና በወያኔ ድጋፍ ያግኙትን መግንጠል እስከመቸውም አንቀበለውም መሆን ካለበት ደግሞ በተባበሩት መንግስታት ፈት ከዚህ ቀደም ኤርትራ የኢትዮጵያ መሆኗን በትርጋግጠበት መልኩ መሆን አለበት ይሂም ሆኖ መገንጠል ካለባቸው የ አስብ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ ከተካለለ በኋላ ነው::
አና አንተ የሚስልህን ጽፈሃል ግን ወንድሜ ስለ ኢትዮጵያ ጉዳይ ለመጻፍ ስትፋልግ ይህን ያህል ከኢትዮጵያኖች ስሜት መራቅ የለብህም::
በቀላሉ አንተ ማለት የፈለከው ኤርትራ የኢትዮጵያ አንድ አካል አይደለችም የአሰብ ወደብም አስፈልገንም ብላችሁ ፈርማችሁ ከሻቢያ ጋር ሁናችሁ ወያኔን ወጉ ነው:: በኔ አስተያየት ምክርህ ምንም ተቀባይነት የለውም::
በውጭም በውስጥም ላሉ የኢትዮጵያ ሚዲያዎች የማሳስበው ዛሪም ድሮም የኤርትራ ጉዳይ የመገንጠል እንጅ የነጻነት ጉዳይ እንዳልሆነ ማውቅ አለባቸው ስለዚህ ኤርትራን በሚመለከት ዚና ሲነበብም ሆነ ሲጻፍ ከኢትዮጵያ የተገነጠለችው ኢርትራ እንደዚህ ሆነች ወያም አደረገች ነው መባል ያለበት ኤርትራ ከኢትዮጵያ ከተገነጠለች በኋላ ወዘት እንደዚህ ተብሎ ነው መነበብ መጻፍም ያለበት አንደራ ለሁሉም የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ዛሪም ነገም የኢርትራ ጉዳይ የመገንጤል እንጂ የነጻነት ጉዳይ እንዳልሆነ ልብ ብላችሁ ተርዱ::
This is the best idea i ever heared.tx.Tekle.they have to do something to work with Eritrean gov.as i think the problem is we can not swall it the Eritrean independense.
ፀሃፊው ከኢትዮጵያ ህልውና ደህንነትና ፍላጎት ይልቅ ይበልጥ ለኤርትራ ህልውና ደህንነትና ፍላጎት በመጨነቅ የፃፉ ነው የሚመስለው፡፡ምናልባትም ከእኔ ሌላ ሰው የሆነ ደግሞ እንዴ እኝህ ሰውስ እራሳቸው የለየላቸው ሻእብያ ወይንም ሻእብያ ደጋፊ ናቸው እንዴ ሊልም ይችላል፡፡ፀሃፊው የኢትዮጵያ ጉዳይና መፃኢ እድል በኤርትራ መዳፍ ስር ብቻ ያለ እንዲመስልም ጭምር ብዙ ጥረዋል፡፡ከታሪክ እንደምንማረው ጊዜ በራሱ አንዳንድ ጊዜ የራሱን ተአምራዊ የሆነ ታሪካዊ ክስተትና መፍትሄ ይዞ እንዲመጣ ይሆናል፡፡ከዚህ በመነጨም ላለፉት 40 ዓመታት ያህል የኢትዮጵያ ጉዳይና መፃኢ እድል በመለስ/ኢሳያስ የባእድ ቅጥረኞች አማካኝነት እንዲወሰን ይሆን ዘንዳ ግድ እንዳደረገው ሁሉ መፃኢው ጊዜ ደግሞ ሚዛኑ ወደየትኛው ባለጊዜ እንደሚያደላ እርግጠኛ ሆኖ ለመናገር አይቻልም፡፡ብዙዎቹ የትግሪኛ ተናጋሪው ማህበረሰብ አባላት የደርግ መውደቅን ተከትሎ ያያዙትን በትረ-ስልጣንና ሃይል ተመክተው አጠቃላዩ የኢትዮጵያ ጉዳይና መፃኢ እድል ለዘላለም በእነሱ አራጊ ፈጣሪ የሆነ ቁጥጥርና መዳፍ ስር ብቻ እንደሚቆይ አድርገው ነው በተሳሳተ መንገድ እየተረዱ ያሉት፡፡የታሪክ አጋጣሚ በፈጠረው ሁኔታም ያገኙትን በትረ-ስልጣንና ሃይል በአግባቡ በማስተዋል ለመጠቀም ባለመቻላቸውና በዚህ በትረ-ስልጣንና ሃይል የተነሳ በከንቱ በመታበያቸውም በመለስ/ኢሳያስ አማካኝነት ላለፉት 21 ዓመታት ያህል በአጠቃላዩ ምስራቅ አፍሪካ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ምስቅልቅና ቀውስ እንዲፈጠር ነው እያደረጉ ያሉት፡፡እውነቴን ነው የምናገረው ነፃነት ወይንም ባርነት ብሎ ነፃነትን እፈልጋለሁኝ ያለ ህዝብና ለዚህም በአስርት ዓመታት ለሚቆጠር ጊዜ እጅግ ደም አፋሳሽና ንብረት አውዳሚ ጦርነት ያካሄደ ህዝብ ሲመኘው የነበረው ነፃነት ሲያገኝ ተመልሶ ሌላ አይነት ባርነት ውስጥ ገብቶ ነፃነቱ ተመልሶ የህሊና ባርነት የሆነበት ህዝብ በታሪክ ብዙም አላየሁም፡፡በታሪክም አንፃር ሲኬድ ከዋናው እናት ሀገር የተገነጠለ ትንሽ ሀገር መልሶ የወጣበትንና የተገነጠለበትን ሀገር ወዲያውኑ ሀብቱን ለመቦጥቦጥና ለመዝረፍ ሲፍገመገም ሲያስጨንቅና ከዚያም ተመልሶ በጦር ሲወጋና ከዚያም አልፎ የባህር በር አልባ ሲያደርግና መውጫ መግቢያ ሲያሳጣም ብዙም አልታየም፡፡አጠቃላዩ የምስራቅ አፍሪካ ውስብስብ ችግር ከህዝቦቹ መልካም ፍቃድና ይሁንታ ይልቅ እንደ መለስ/ሻእብያ ያሉ የባእዳን ቅጥረኞች አማካኝነት በዋናነት የባእዳን ሃይሎች ፍላጎትና አላማ የሚፈፀምበት ቀጣና ነው፡፡
በእርግጥ የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ ላለፉት 40 ዓመታት ያህል በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ በአብዛኛው የተወሰነው በመለስ/ኢሳያስ ብቻ ሳይሆን በባእዳን ሃይሎች መዳፍ ስር ጭምር ነው፡፡ከዚህ በመነጨም ፀሃፊው እንዲህ እንደ ብልጣብልጥ ፖለቲከኛ ይበልጥ ለኤርትራ ህልውና ደህንነትና ፍላጎት በመጨነቅ አቃለው ሊያስቀምጡት ከሚፈልጉት በላይ አጠቃላዩ የምስራቅ አፍሪካ ሁኔታ ከፍተኛ የሆነ የቁማር ጨዋታ የበዛበት እንዲሆን የተደረገ ነው፡፡ፀሃፊው እኛ ኢትዮጵያውያንን በተቃዋሚው በኩል ከኤርትራ ጋር ግልፅ ቋሚና ዘላቂ የሆነ ዘመናዊ የውጫሌ ውል እንድንፈራረምም ጭምር እየመከሩን ነው፡፡ይህንን ብቻም አይደለም የኤርትራና የኢትዮጵያ ጉዳይና መፃኢ እድል የደርግን በሃይል መውደቅ ተከትሎ በመለስ/ኢሳያስ አማካኝነት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በማያዳግም ሁኔታ የተደመደመ ጉዳይ እንደሆነና የአሰብም ጉዳይ ያበቃለት እንደሆነ አድርገን እንድናምን ጭምር ነው እየነገሩን ያሉት፡፡መለስ/ኢሳያስ የተባሉ ሁለት የባእዳን ቅጥረኞች አንዳቸው ትግራይን ነፃ እናወጣለን ሌላቸው ደግሞ ኤርትራን ነፃ እናወጣለን ብለው ኢትዮጵያን እያደሙ ደርግን በሃይል ለመጣል አንድ የሆኑ ሰዎች ይህ ሲሳካ ተመለስው እራሳቸው የጦርነት አውድማ ውስጥ መግባታቸው እነዚህ ሰዎች በራሳቸው ህዝብ ፍላጎት የሚመሩ ሳይሆን በዋናነት በባእዳን ሃይሎች ፍላጎት የሚመሩ መሆናቸው ምን ያህል የእብደት ስራ የሚሰሩ ሰዎች እንደሆኑ ቆም ብለን መጠየቅ አለብን፡፡ስለዚህም ከዝንጀሮ ቆንጆ ምን ይመራርጡ እንዲሉ መለስ/ወያኔ እንዲሁም ኢሳያስ/ሻእብያ ሁለቱም ፈፅሞ ፀረ-ኢትዮጵያ ፀረ-ኢትዮጵያዊነትና ፀረ-ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ያለምንም ጥርጥር ሊሰመርበት ይገባል፡፡ፀሃፊው ያለውን ውስብስብ ነገር ፈፅሞ በማቃለል ልክ በሁለት ተራ ሰዎች መካከል ያለ ተራ ግንኙነት እንደሚመስል አይነት አድርገው ነው ያቀረቡት፡፡ኢትዮጵያ ላለፉት 40 ዓመታት ያህል ከትግሪኛ ተናጋሪው ማህበረሰብ በወጡ መለስ/ወያኔ እንዲሁም ኢሳያስ/ሻእብያ በሚባሉ ሁለት የባእዳን ቅጥረኛ የሆኑና የእብደት ስራ የሚሰሩ አደብ ያልገዙና ያልሰከኑ የአእምሮ በሽተኞች(psychopathic) የተነሳ እጅጉን አበሳዋን ስታይ እንደኖረች ግልፅ መሆን አለበት፡፡እነዚህ ሃይሎች ዘወትር ያለመረጋጋትና ችግር መፍጠር መለያ ባህሪያቸው ነው እየሆነ የመጣው፡፡በጥባጭ ካለ ማን ጥሩ ይጠጣል እንዲሉ እነዚህ ሃይሎችና ድጋፍ የሚሰጡ ተከታዮቻቸው አደብ እንዲገዙ ካልሆነ በስተቀር ኢትዮጵያ ብቻ አይደለችም መላው ምስራቅ አፍሪካ ዘላለም እንደታመሰ ነው የሚኖረው፡፡ፀሃፊው ኢትዮጵያውያን ተቃዋሚዎች (ልክ ኤርትራውያን ተቃዋሚዎች ከመለስ ጋር እንደሚያደርጉት ማለት ነው) ከኢሳያስ ጋር ግንኙነት ለመመስረት ማፈርና መሸማቀቅ የለባቸውምና ግንኙነቱን ይፋ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ህግና ደንብ ተበጅቶለት ዘላቂ ስምምነት ማድረግ ጭምር እንዳለብንም ይመክራሉ፡፡መቼም የሰው ልጅ ክቡር ፍጡር መሆኑን ተረድቶ ለህሊናው ካልተገዛ አዎ ይህ ሊሆን ይችላል፡፡ፖለቲከኛም ቢሆን እኮ ሰው ነውና ከውስጥ የሚጮህ ህሊና የሚባል ነገር አለው፡፡ይገርማል ኢሳያስ/ሻእብያ ማለት እውን በኢትዮጵያ ህዝብ አእምሮና ስሜት ውስጥና በታሪክም ዘንድ ምን አይነት አሳፋሪና አሳዛኝ ቦታ እንዳለው ፀሃፊው ጥንቅቀው የሚያውቁ አይመስሉም፡፡በእርግጥ መለስ/ወያኔም እንደዚሁ ናቸው፡፡እና ታዲያ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን የባእዳን ቅጥረኛ በሆኑና የእብደት ስራ በሚሰሩ አደብ ያልገዙና ያልሰከኑ መለስ/ኢሳያስ በሚባሉ የሚስጥር ባለንጣ/ወዳጆች እና ሁለት የአእምሮ በሽተኞች(psychopathic) የተነሳ እጅጉን አበሳቸውን ስላዩ ብቻ እንዴት የመለስ ተቃዋሚዎች ከኢሳያስ ጋር ይፋ ወዳጅነትን መፍጠር እንደ ኩራት አድርገን እንድንቀበል ይመክሩናል፡፡ይህ አይነት አሳፋሪና አሳዛኝ የፖለቲካ ሽርሙጥና እንዲፈፀም መገፋፋት በታሪክም ብቻ ሳይሆን በፈጣሪም ዘንድ ፀያፍ ይመስለኛል፡፡ዘለቄታዊ መፍትሄ የሚገኘው ደግሞ በእንደዚህ አይነት አሳፋሪና አሳዛኝ የፖለቲካ ሽርሙጥና ሳይሆን ሁለቱንም ቅጥረኞች ፈጣሪ ታሪክና ጊዜ ወጊዱ አታስፈልጉም ብሎ ሲያስወግዳቸው ብቻ ነው፡፡ይህ ደግሞ የጊዜ ጉዳ እንጂ ከመሆን አይቀርም፡፡ፀሃፊው ስለዚህ አይነት አሳፋሪና አሳዛኝ የፖለቲካ ሽርሙጥና ሲመክሩን የረሱት አንድ ሌላው ነገር ደግሞ የኢሳያስ ተቃዋሚዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ጥገኝነት አግኝተው እየተረዱበት ያለው መለስ ዜናዊ የሚባል መሪ እራሱ የለየለት የኤርትራ ደጋፊ የሆነ ብቻ ሳይሆን ከኢትዮጵያ ይልቅ ኤርትራን የሚያስቀድም ኤርትራዊ መሆኑን ነው፡፡ፀሃፊው ስለዚህ አይነት አሳፋሪና አሳዛኝ የፖለቲካ ሽርሙጥና ሲመክሩን የረሱት ሌላም ነገር አለ፡፡ኢትዮጵያውያን ከኤርትራ ሲሰደዱ ኢሳያስ/ሻእብያ ኢትዮጵያውያንን የወርቅ ጥርስ ሳይቀር እየነቀለ ነው ያባረራቸው፡፡በተቃራኒው ግን ኤርትራውያን ከኢትዮጵያ በመለስ/ወያኔ ሲባረሩ ደግሞ ኢትዮጵያውያን እንባ እየተራጩና እያለቀሱ ነው ኤርትራውያንን የሸኙት፡፡ስለዚህም አንድ ኢትዮጵያዊ ተቃዋሚ ኤርትራ ካለው ኢሳያስ ጋር ሲሄድ ሃፍረት መሸማቀቅና መጥፎ ስሜት እንጂ እንዴት ጥሩ ስሜትና ኩራት እንዲሰማው ይጠበቃል፡፡መለስን ለመጣል በሚል ብቻ ከኢሳያስ ጋር ህብረት የሚፈጥር ማንኛውም ተቃዋሚ ሃይል ሁሉ ተገቢው የሰብዓዊነትም ሆነ የኢትዮጵያዊነት ማንነት ትርጉምና ክብር የሚሰማው ነው ለማለት እጅጉን ይከብደኛል፡፡በአጉል ያልሰከነ መፍገምገም ላይ የተመሰረተ ይህ አይነት ተገቢ ያልሆነ የፖለቲካ ሽርሙጥናም በሞራልም ሆነ በታሪክ አሳፋሪና አሳዛኝ ነው የሚሆነው፡፡
እንደዚህ አይነት ከኢሳያስ ጋር የሚደረግን አሳፋሪና አሳዛኝ የሆነ የፖለቲካ ሽርሙጥናን የሚደግፉ ሃሎችም በተዘዋዋሪ ለኢትዮጵያ ለኢትዮጵያዊነትና ለኢትዮጵያውያን ተገቢው ቀናኢነት ከብርና ፍቅር የሌላቸው ሰዎች ናቸው፡፡አልበርት አንስታይን አንድ ወቅት “You can not solve a certain problem by a certain mechanism that has caused the very problem itself in the first place.” እንዳለው ላለፉት 40 ዓመታት ያህል ኢትዮጵያን ከፍተኛ ፈተና አደጋና ምስቅልቅል ውስጥ ከከተተውና የባእዳን ቅጥረኛ ከሆነው ከራሱ ከኢሳያስ/ሻእብያ መፍትሄ ለማግኘት መሞከርም በራሱ አላዋቂነትና ጅልነት ነው፡፡እንደዚህ አይነት የመደናበር መፍገምገም ውስጥ ገብቶ በታሪክና በሞራል አሳፋሪና አሳዛኝ የፖለቲካ ሽርሙጥና ውስጥ ከመግባትም በሌላ አማራጭ አካሄድ ሁሉ ጥረት እያደረጉ እራሱ ጊዜ የሚያመጣውን ነገር መጠበቅም የተሻለ አመራጭ ነው፡፡አንዳንድ የተቃዋሚ ሃይሎች ከዚህ በፊት እንደሰማናቸው ከሆነ ከነባራዊው አለም እውነታ ባፈነገጠ በሚመስል እይታ ኢሳያስ/ሻእብያ እኛን ከረዱን አምቢ አንልም ነገር ግን ኢሳያስ/ሻእብያ የኢትዮጵያን ህዝብ ፍላጎት የሚነካ ነገር አድርጉ ሲሉን ግን ይህንን አንቀበልም ብለውናል፡፡በነገራችን ላይ ግን ኢሳያስ/ሻእብያ አንዳች ሌላ ነገር በምላሹ ሳይጠብቁ መለስ እንዲገለበጥ ብቻ ብለው ለተቃዋሚው የሚረዱበት መሰረታዊ ምክንያት ለነፍሳቸው ነው ወይንስ ለሌላ አላማ ብለው?ጭራሽ ያሁኑ ብልጣብልጥ ፀሃፊ ደግሞ አሰብ ወደብ ገለመሌ ሳትሉ ዝም ብላችሁ ደረታችሁን ነፍታችሁ ከኢሳያስ ጋር ትርጉምና ዘላቂነት ያለው ይፋ ወዳጅነትና ዳግም የውጫሌ ውል አይነት ስምምነት አድርጉ ብለው እየመከሩን ነው፡፡የመለስ/ኢሳያስ የቅጥረኝነት የእብደት ዘመን ማብቂያው እሩቅ አይደለም፡፡መፍትሄውም አጉል መወራጭትና መፍገምገም ሳይሆን የራስን አማራጭ የቤት ስራ እየሰሩ ጊዜ የሚያመጣውን መፍትሄ ጭምር መጠበቅ እንጂ ከንቱ ዥዋዥዌ እየሰሩ በታሪክና በሞራል አሳፋሪና አሳዛኝ የሆነ ከኢሳያስ ጋር ወዳኝነት በመመስረት የፖለቲካ ሽርሙጥና መስራት አይደለም፡፡ኢትዮጵያውያን የእምነት ሰዎች ነን የምንል ከሆነ ደግሞ እምነታችን ይህንን አይነት በታሪክና በሞራል አሳፋሪና አሳዛኝ የሆነ የፖለቲካ ሽርሙጥና ተግባር እንድንፈፅም አይፈቅድልንም፡፡በዚህ አይነት አካሄድ የሚገኝም ስኬት በራስ ማንነት መተማመንን የሚገድልና አሳፋሪ ጭምር ነው፡፡የፈለገውን ያህል ነገሮች ፈታኝ ቢሆኑም እንኳን ይህንን አይነት በታሪክና በሞራል አሳፋሪና አሳዛኝ የሆነ የፖለቲካ ሽርሙጥና እንድንፈፅሞ የሚያደርገን አሳማኝ የሆነ ትርጉምና ፋይዳ ያለው የህይወትና የፖለቲካ ፍልስፍና ያን ያህል ከቶ ሊኖር አይችልም፡፡ሁሉም ነገር የራሱን የጊዜ ኡደት ጠብቆ ያልፋል ስለዚህም የመለስ/ኢሳያስ አገዛዝም እንደዚሁ የተቀመጠለት የጊዜ ገደብ አለው፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ ከኤርትራ ህዝብ ጋር ፍቅር ውስጥ ነው ለማለት ባልደፍርም ግን ቅሉ ያን ያህል በጠላትነት የሚተያይ ህዝብ አይደለም፡፡ችግሩ በዋናነት ያለውም እንደተለመደው በኢሳያስ/ሻእብያና በመለስ/ወያኔ ዘንድ ነው፡፡ነገር ግን መላው ትግሪኛ ተናጋሪው ማህበረሰብ የባእዳን ቅጥረኛ በሆኑና የእብደት ስራ በሚሰሩ አደብ ያልገዙና ያልሰከኑ መለስ/ኢሳያስ የሚባሉትን ሁለት የአእምሮ በሽተኞች (psychopathic) አውቆም ይሁን ሳያውቅ ፈፅሞ አምኖ በመከተሉ የተነሳ እራሱንም ሆነ የተቀረውን ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ ከፍተኛ የሆነ አለመረጋጋትና ቀውስ ውስጥ ነው የከተተው፡፡ስለዚህም የትግሪኛ ታናጋሪው ማህበረሰብ በተለይም ኤርትራውያን ከኢትዮጵያወያን ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ጋር በሰላማዊ ጉርብትና ለዘላቂነት ለመቀጥል ከፈለጉና ቁርጠኝነት ካላቸው ይህ የማይቻልበት ምክንያት ምንም የለም፡፡የኢትዮጵያ ህዝብ የኤርትራን ህዝብ የነፃነት ጥያቄ ወዶም ሆነ ተገዶ እያከበረ ነው፡፡ነገር ግን ጥቅመኝነትና አጉል ብልጣብለጥነት ፈፅሞ ሊወገድ ይገባልና ግንኙነቱ በእውነት በሰጥቶ መቀበልና መከባበር ላይ የተመሰረተ ሊሆን ይገባዋል፡፡እነ መለስ/ኢሳያስ ለዘመናት ሲከተሉት የኖረው የኤርትራን ህለውናና ደህንነት ለማረጋገጥ የተቀረውን ኢትዮጵያን ህልውና መናድ ማናጋት ማዳከምና መበታተን አይነት በሌላው መቃብር ላይ የራስን ቤተ-መንግስት ለመግንባት የማሰብ አይነት የአጉል የጀብደኝነትና የእብደት አካሄድ ፈፅሞ አደገኛ ነገር ስለሆነ ይህ ነገር ፈፅሞ መገታትና መቆም አለበት፡፡ይህ አይነት እሳቤ ፈፅሞ ለሁለቱ ሀገር ህዝቦች የማይበጅና በተቃራኒው ግን በዋናነት የታዳጊውን አለም መረጋጋት የማይፈልጉ የባእዳንን ሃይሎች ፍላጎትና አለማ ለማስፈፀም ሲባል ብቻ በከፋፍለህ ግዛው ስልት የታለመ ህዝቦችን እርስ በርስ የማናከስ ሴራ ነው፡፡በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ትግሪኛ ተናጋሪው ኤርትራ ውስጥ ካለው ትግሪኛ ተናጋሪው ጋር እንዲናከስ ነው እየተደረገ ያለው፡፡እንደዚሁም አጠቃላዩ ትግሪኛ ተናጋሪው ማህበረሰብ አማራው ጋር እንዲናከስ ነው እየተደረገ ያለው፡፡እውነትን መነጋገር ፈጣሪም የሚወደው ነገር ነውና እውን ከዚህ አሳዛኝ ክስተት በዘላቂነት የሚያተርፈውና የሚጠቀመው ማነው?እኛ ወይንስ ባእዳን ሃይሎች?ሰላምህን በውድ ዋጋ ግዛት እንደሚባለው ኤርትራውያን ከእውነት በሀቀኝነት ላይ የተመሰረት ንፁህ የሆነ ነፃነትን ሰላምንና መልካም ወዳጅነትንና ጉርብትናን ከኢትዮጵያ የሚሹ ከሆኑ ደግሞ 80 ሚሊዮን ያለውን የተቀረውን እናት ሀገር ባህር-በር አልባ አድርገውና አንገታችንን አንቀው በተረጋጋ መንገድ ለመዝለቅ እጅጉን ፈታኝ ነገር ነው የሚሆነው፡፡ስለዚህም እነ መለስ/ወያኔ እራሳቸው የለም የትግራይ ትግሪኛን ሀገርና መንግስት ወደፊት ከኤርትራውያን ጋር እንመሰርታለን የሚሉም ከሆነ ወይንም የራሳቸውንም ሀገር ወይንም ከኢትዮጵያ ጋር አብሮ በመሆን ጭምር ሲታሰብ አንደኛው ግንባር ቀደም የሆነው የባህር በር ጉዳይ ከፍትሃዊነት ከተፈጥሮ ህግ ከታሪክ ከአለም አቀፍ ህግ ከሞራል ከመተሳሰብ አንፃር ታይቶ አንድ ዘለቄታዊ እልባት ማግኘት አለበት፡፡ሁለተኛው እነ መለስ/ወያኔ ከወሎና ከጎንደር ነባሩን ህዝብ እያፈናቀሉ ወደራሳቸው የከለሉት መሬት ጉዳይ ነው፡፡ለአካባቢው ዘለቄታዊ ሰላምና መረጋጋት እነዚህ ሁለት ወሳኝ ነገሮች መፍትሄ ካገኙ ሌላው ነገር በቀጣይነት ሊስተካከል የሚችል ነገር ነው፡፡ስለዚህም ፀሃፊው አንገብጋቢ የሆነውን የባህር በርን ጉዳይ በማጣጣል ጭምር ከኢትዮጵያ ህልውና ደህንነትና ፍላጎት ይልቅን ይበልጥ ለኤርትራ ህልውና ደህንነትና ፍላጎት በመጨነቅ ያቀረቡት ፅሁፍ ፈፅሞ ተቀባይነት የለውም፡፡የአሰብ የባህር በር ጉዳይ ፀኃፊው እያቃለሉ እንደሚያጣጥሉት አይነት ሳይሆን ሊወድቁ እየተንገዳገዱ አንድ ሀሙስ ከቀራቸው ከመለስ/ወያኔ እንደዚሁም ከኢሳያስ/ሻእብያ የስልጣን ዘመንና ህልውና በሻገር ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ታሪካዊ አጀንዳ ሆኖ የሚቀጥል ነገር ነው የሚሆነው፡፡ኢትዮጵያን የባህር በር አልባ የማድረግ ሴራ በራሱ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ወይንም አካባቢው ለዘለቄታው ሰላምና መረጋጋት የሰፈነበት እንዳይሆን በባእዳን ሃይሎች ሆነኝ ተብሎ የተሸረበ ተንኮል ነው፡፡ሰላምንና ነፃነትን ስለተመኘነው ወይንም ስላወራነው ብቻ አይገኝም ስለዚህም ሰላምህን በውድ ዋጋ ግዛት እንደሚባለው ሁሉ ሰላምና ነፃነት የሚጠይቀውን ነገር መፈፀም አለብን፡፡ይህንን ለማድረግ ደግሞ ኢትዮጵያውያን የኤርትራውያንን የመገንጠል በነፃነት ነፃ ሀገር የመሆን እውነተኛ ፍላጎት እንዳከበርነው ወይንም ማክበር እንዳለብን ሁሉ ኤርትራውያን ደግሞ የእኛን የባህር በር መብት የማክበር ግዴታ አለባቸው፡፡በሌላው ሰው ቁስል ፈውስን እንደዚሁም በሌላው ሰው ክስረት ትርፍን ማግኘትም በፈጣሪም ዘንድ ሃጢያት ነውና፡፡እውነት እንነጋገር ከተባለ እኛ ኢትዮጵያውን አግባብ ባልሆነ ኢፍትሃዊ አካሄድ የባህር-በር አልባ መሆናችን ከፈጠረብን ህመም በስተቀር የኤርትራ መገንጠል ነፃነት ማግኘትና የበለፀገችና የተጠናከረች ሀገር መሆን መቼም ቢሆን ያን ያህል ስጋት ፈጥሮብንና አበሳጭቶን አያውቅም፡፡ይህ ብቻም አይደለም ወደ ኢትዮጵያ በየጊዜው የሚመጡ ኤርትራውያን ምናልባትም ከኢትዮጵያውያን የተሻለ መብት ከማግኘታቸው በስተቀር ኢትዮጵያዊ በእነሱ ላይ ያን ያህል በመጥፎ ስሜት ፊቱን ከስክሶ አያውቅም፡፡በትግሪኛ ተናጋሪውና ከዚያ ውጪም ባለው ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ መካከል ያለው አጠቃላይ ሁኔታው ሲታይም በመለስ/ወያኔ እንደዚሁም ኢሳያስ/ሻእብያ የተባሉ ሁለት የአእምሮ በሽተኛና እብዶች(Psychopathic) የሆኑ ቅጥረኛ ሃይሎች የተነሳ ጅራፍ እራሱ ግርፎ እራሱ ይጮሃል አይነት ካልሆነ በስተቀር የኢትዮጵያ ህዝብ የኤርትራን ሉአላዊነትና ነፃነት አክብሮ ነው ያለው፡፡ነገር ግን በተቃራኒው መለስ/ወያኔ እንደዚሁም ኢሳያስ/ሻእብያ የተባሉ ሁለት የአእምሮ በሽተኛና እብዶች(Psychopathic) የሆኑ ቅጥረኛ ሃይሎች ግን ላለፉት 40 ዓመታት ያህል የተቀረውን ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብና የኢትዮጵያን ህልውና ደህንነት ፍላጎትና ጥቅም ግን ፈፅሞ በእጅጉ እየተፃረሩ እየተፈታተኑና እየጎዱ ያሉ ሃይሎች ናቸው፡፡ስለዚህም በኢትዮጵያና በኤርትራ ወንድማማች ህዝብ መካከል ብቻም ሳይሆን በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ጭምር ዘለቄታዊ መፍትሄ እንዲመጣ ለማድረግ በዚህ በዚያም በተቃዋሚው በኩል ያለው ከሁለቱም ሃይሎች ዘንድ የሚደረገው የፖለቲካ ሽርሙጥና ቆሞ ሁለቱም መለስ/ወያኔ እንደዚሁም ኢሳያስ/ሻእብያ የተባሉ የባእዳን ቅጥረኞች ለዘለቄታው ስርዓታቸው መወገድና ቅድሚያ ለህዝብ ህልውና ደህንነት ፍላጎትና ጥቅም የቆመ ሰላም ወዳድ የሆነ እውነተኛና ቀናኢ አገዛዝ መተካት አለበት፡፡
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ !!!
“ዜናውን ሲሰብርልኝ” አልክ? ሌላስ ምን ሰበረልህ? የኔታ አሁንስ አላበዛህም? ከኤርትራ ጋር ገና ሌላ አዲስ ውል ትላለህ? ኤርትራ እኮ ሌላ አገር ከሆነች ሃያ አመት ሆኗል:: ታሪክን ወደ ኋላ መመለስ ታስባለህ? ሌላስ ምን ታመጣልን [ይቅርታ ትሰብርልን] ይሆን?
the same old song oh my god what is this people think? eritrea is more powerful than israel forget ethiopia the country lives by aid. eritrea is independent country politicaly and economicaly with out aid from west think the whole world fight eritrea if the west leave eritrea alone i promise you eritrea become super power belive or not
if the west leave eritrea alone foget weak ethiopia eritrea become one of the super power country in the planet eritrean fought to maney battels in every corner alone with out any military and economicaly help so stope talk about eritrea talk about your poor divided nation
ተክሌ!ድፍረትህ ‘ይደነቃል’፤ግን የባለጌ ድፍረት ነው። በተለይ የኢትዮፕያን ዕጣ ፈንታ ከኢሳኢያስ መኖርና አለመኖር ጋር ማያያዝህ ያሳዝናል፤ አሳኢያስ ሲሞት ለቅሶ የመቀመጥ መብትህ የተጠበቀ ነው፤ ከመሞቱም በፊት ጥቁር ልብስ መልበሱንም አንከለክልህም።ግን ኢትዮፕያን ለመግደል ህይወቱን ካሳለፈ ሰው ዘንድ የአትዮፕያን ትንሣኤ ታገኛላችሁ ስትለን ኢትዮፕያውያን አንቀበልህም። በግልፅ አብረውት እንደሚሠሩት እንደ ኦነጎች ለምን አብረን አንሠራም ላልከው መልሱ ቀላል ነው። እኛ በኢትዮፕያዊነታችን ገና የምንደራደር አይደለንም።
ያንተ የፖለቲካ ሰብዕና የሚመነጨው ከአንዲት ነጠላ ሃሳብ ነው፦ መለስን ከመጣል። በቃ። በርግጥ ውሎ ሳያድር መለስ መሄድ አለበት።ከነጓዙ። የመለስ ጓዝ ደግሞ የኢሳኢያስ ጓዝ ነው። ስለዚህ መለስ ሲሄድ ኢሳኢያስ ይቆያል ብለህ የምታስብ ከሆነ ወይንም ኢሳኢያስ ሲሄድ መለስ ይቆያል ብለህ የምታስብ ከሆነ ተሳስተሃል። የሁለቱም ሞት በአንድ ‘ቀን’ነው።የዚህን ሚስጥር ለአንተ ማስረዳት ህመም ነው። ብሽቅ!!!
HATE ON ISSAYAS/MELES :
IT IS ONLY CHIFFIN PERSONAL TILACHA
ON ISSAYAS AND MELES.
BUT POLETICALLY SPEAKING IT IS HOLLOW
AND DEVOID OF ANY SUBSTANCE.
OTHERWISE HOW CAN IT RATIONALIZED.
AFTERALL THEY SYSTEMS THAT COLLAPSED
AND THE LEADERS OF THEM WERE SO HATED
BY THE ETHIOPIAN PEOPLE THAN ISSAYAS
AND/OR MELES.
ACTUALLY ISSAYAS AND MELES ARE MORE
SOFT AND SYMPATHETIC AS COMPARED TO
THE EVILS AND MESS OF THOSE ERA THAN
WHAT THE PEOPLE DEMANDS.
ERITREA LE ERITREANS AND HIZB AND LIB SHABIEA MALET ERITREA MALET EKO NEW ATILEYAYUT WE ARE ALL 6 MILLION ISAIAS AFEWERKI ERITREAN ATIKORESM ATISHETIM ERITRAWIN YENANTE YECHINKILAT BESHITACHIHUN LEMESIMTA GIZERITYACHIN ANATEFAM LIMAT LAY YELENEW ATIBETIBTUN BETELE AMHARA NA GURAGEN ERITRAWIYAN YESUW ANFELIGM YENHNA ANSETIM KALEFEW YEMATIMARU AHYOCH VIVA SHABIEA VIVA JEGNAW TEGADALAY ISAIAS AFEWERKI MOTE LETELACHOCHACHIN
ENHABIEANTES MAN NEW MEBITUN YESETACHU SEL SHNBIAA
ነው ወይስ ግራ ገብቶኛል? yalkew tikikil new gin gra gebtoh gra kemtagaban yemiqetelewn kemetafih befit beqi asbebet.
እኔ በጣም የሚገረመን እጅ እጅ ያለኝ እገር ቢኖር አንድ ነገር ሳይሰሩ የሚሰሩት አይ ውሃ ቀጠነ ጀት ፈጠነ የሚሰነዘረው ነግ ነው. እዚህ ጽህፍ ላይ ጽሃፊው የገረመኝ ግንቦት 7 ስለኤርትራ ህዝብ የሚወስነው ነገር ነው አለ ያለው ነው. ግንቦት 7 እራሱ ይህን ማለቱ እራሱ እጅግ የሚያስደንቀው ነው. በማን ላይ ቆመሽ ማንን ታምያለሽ የሚባለው ነገር ይህ ነው. እንደውም ዝም ማለት ይችላሉ እንደውም የኤርትራ ነገር ያበቃ ነው ቢሉም እንኳን አይገረመኝም. ለምን ምንም መፈናፈኛ ሜዳ በሌለበት አንድ እና አንድ አገር ብትገኝ???? አይ አሰብን የማስመለስ እቅድ አለን ይበሉ???????????????????? አሁን ይሄ አንድ ጤነኛ ነኝ ከሚል ሰው ይጠበቃል???????????????????ሌላው ግንቦት 7 ማንም እይተነሳ እንደፈለገው የሚያንሸራሽረው አይደለም መደረግ ያለበትን ነገር ጠንቅቀው የሚያውቁ ናቸው ሙሉ ለሙል ልብ ያለመጣል ነገር በበኩሌ የሚያስመሰግናቸው ነገር ነው. ሻብያ መሆኑን መርሳት የለብንም. ነገ ከመለስ ጋር እርቅ ሊያረጉ ይችላሉ. እኔ በበኩሌ ይህን ድረጀት አንዳንድ ወያኔ በሚነፋው ፕሮፓጋንዳ የከሰረ ቢሉትም ጆሮም የለኝም. ግንቦት 7 የአቅሙን እና ከአቅሙ በላይ እይሰራ ነው. ወያኔ የዚህን ድረጅት ስም ለማጉደፍ እና ተቀባይነት ለማሳጣት ባጀት እስከመመደብ የደረሰው ቀላል ድረጀት ስላልሆነ ነው. እናም የኔ ወንድም የግንቦት 7 ሻብያ ላይ ሙሉ ለሙሉ ልቡ የለም ላልከው አይገርምም. ጥቂት ሳንሰራ ብዙ የሰሩትን ባንተች ጥሩ ነው.
Well while we are watching Ethiopian demise by vindictive TPLF Junta and racist Meles, not to look at an alternative approach to deal with Cancerous is foolhardy. Here is what We Ethiopians are to deal with and so far we have chosen to bid against our future because we are afraid to say what need to be said about Eritrea. Eritrea is gone –and happy it is gone as well. and it shouldn’t come back. whatever historical condition brought about that is non issue for our reality. Politicians need to clearly state that Eritrea is a sovereign nation and all its sea harbors well be respected by all Ethiopians. In the future as good neighbors we will trade and make whatever national assets we have to the benefit of our people. No interest on Asseb or Messwa only under agreement with strict regulation by both countries. If we make this clear statement as our political stand, Eritrea would not see the opposition as a threat. But here is what the opposition has to understand too , this relation has to start with clear understanding that The Ethiopian political parties don’t want Eritrea to interfere in the internal affairs of Ethiopians. Independence of the Ethiopian party is a must , we don’t need another party that works under Issays. for this to happen we our political assets 80% should be in Ethiopia and else Where. if problem arises with Eritrea the opposition will not be decapitated. relay on Ethiopia clandestinely infiltrating the army which is 85% Ethiopians Not TPLF. Make sure Eritereans understand that we don’t have any evil design against theme. Make it a public statement and defend it. Keep the opposition to be an independent party no influence and interference in its internal affairs. Then it would be beneficial for Ethiopians and Eritreans to get ride of cancerous from that part of Africa. Alamudin is helping this cancerous cell to grow in our midst. There will come a time we have to deal with him as well. it should be an all out war.
የመገርመው የወያነ ረዘራዘ ነው ተካወሞ የትሳፈው.ሃሳቡ ይድግፋል
This is the most obnoxious piece of writing harmful to the vital interest of Ethiopia. የኔታ ተክሌ is a sadist!
ድሮ ድሮ ጽሁፍህና ጨዋታህ ለዛ ነበረው ያሁኑን ሳይ ግን ጤነኛ መሆንህ አጠራጠረኝ;; እውን የድሮው ተክሌ ነህ ወይስ አንተንም አንጎል አደረጉብኝ???????????
ተክሌ ያሻህን በል ግራ ከማጋባት ወደ መምታታት በፍጥነት እየገሰገስክ ነው። የጸሀፊ፣ የተማሪ፣ የተመራማሪም ሆነ የጋዜጠኝነት ጭላጩም የለህም። የምታውቅ የሚመስለህ ነገር ያለማወቅህን ያደምቀዋል። በውስጥህ ግዙፍ ቅዠትና ትልቅ እኔነት አለ። ለመግራት የሚከብድ ለማስተማር የማይመች ሰብዕና አለህ። ቢሆንም ያሻህን አንተ በል ኢሳት ዘንድ ግን አትድረስ። ኢሳትን ታቀላለህ፣ ታሳንሳለህ ሙያ የለሽም ታስመስለዋለህ። አንተ እንዳሻህ ሁን ልጅ፣ ተማሪ፣ አለቃ፣ ዲያቆን ቢሻህ ጀነራልም ሁን ግን ኢሳትን አትሁን። ልትሆን በምትሻው በሌላው በርታ።
አቶ የኔታ መጀመርያ በቂ እውቀት ይኑርህ ግንቦት 7 ለመተቸት:: ናክፋ ደሞ መጀመርያ ትምህርት ቤት ግባ ካልሆነ በቋንቋህ ብትጽፍ ይሻላል. የሰው ቋንቋ አታበላሽ. እስቲ ፊደል ቁጠር መጀመርያ. መልካሙ ደሞ ጥሩ ትጽፋለህ ነገር ጊን ሁል ጊዜ እጅግ ታረዝማለህ አንዳንዴ ከተለቀቀው ጽህፍ በላይ ያንተ ይበልጣል. እናም ሁሌ እጀምረዋለው እንጂ አልጨረሰወም በጣም ሙዝዝዝዝዝዝዝዝዝዝዝ ያለ ነው.ማራማዊት የምትጽፊው በጣም ይጥመኛል ነገር ጊን ታይፕ መሳሳት ታበዢያለሽ . ነገር ግን እጥር ምጥን ያለ ሆን አሪፍ ነው. red sea አንተም ደሞ ፊደል ቁጠር እስቲ የኔ ዶማ በመሰረቱ አስመራ የኢትዮጲያ አካል መሆውን እና የጥቂቶች የስልጣን ጣማት እንዲህ እንዳረጓት የማታወቅ አህያ አንተ ነህ . ኪሳያስ እብዱ ፍርፋሪ ለሆድህ ብለህ የሌሎችን ስቃይ ችላ ያልክ ለሆድህ ብለህ ህሊናህን የሸጥክ አጋሰስ ነህ ወገኖችህማ በየአረብ አገሩ በየሚድያ አትሰማም ደረግ ይማር ሲሉ አንተ ግን አንድ ሆድህን እያየክ ነጩን ጥቁር ትላለህ. መጀመርያ ህሊናህን አጽዳ የኔ አህያ.
@ጂኒ
False. It was being supported by many enemies of Ethiopia and was also supported by Ethiopians, unfortunately by those Ethiopians who were misinformed about EPLF’s true character….
@Gernaw
“ጥቂት ሳንሰራ ብዙ የሰሩትን ባንተች ጥሩ ነው.” ለመተቸት ምን ያህል መስራት ያስፈልጋል? ከላይ ዋቆ አንዳቀረበዉ ትችቱ በመረጃ አና በምክንያት ላይ አለመመስረቱ ነዉ:: ትችትን በደፈናዉ መቃወም ጥሩ አዝማሚያ አይመስለኝም::ኤርትራን ለኢትዮጵያ ፖለቲክኞቸ የቀኝ እጅ አድርገዉ የሚያዩ ሁሉ አንድም ምንም የፖለቲካ ግንዛቤ የላቸዉም::ወይንም የዉስጥ አርበኞቸ ናቸዉ:: ምክንያቶቹ ብዙ ናቸዉ-አንዽ ምክንያት ብቻ ልጥቀስ-የኤርታ መንግስት በአለም የታወቅ አምባገነን ነዉ:: ማእቀብ ኤርትራ ላይ አልተደረገምን? እንዲህ ካለዉ ምን ለማግኘት? የኢትዮጵያ ፖለቲክኞች ከኤርትራ ጋር ሊኖራቸዉ የሚገባዉ ግንኙነት እጀግ ጥንቃቄ ያለበት እና የተለካ መሆን አለበት-የድርጅቶቹ ቢሮዎች በምንም መንገድ በኤርትራ ዉስጥ መሆን የለበቸዉም::…
እንደው ትንሽ ጣል ለማድረግ ነው የኛ ችግር ፍትህ!ነጻነት!ኢዮጲያና ሕዝቦችዋ በክብርና በሰላም ይኑሩ!,እንኑር! ክጫንቃች
ላይ ውረዱ!!ሕዝቦች ከትውልድ አገራቸው አታፈናቅሉ! ሐገራችንን አትሽጡ ነው!!እውነት በተናገሩ ሐገርና ወገን ወዳዶች ላይ እስራት መከራ አታምጡብን ነው!!እንደውም እናት ሐገራችን የብዙ ሕዝቦችዋ ደም የፈሰሰበት እና በአለም ዙሬያ ታላቅነትና ክብራማ ተወዳጅ የሆነች! ለጠላቻቸው የማይመቹ ለወዳጃቸው የሚያኮሩ! ስለሆኑ የዛሬው የኢትዮጲያኖች ጥያቂ ያልለመድነው! የማናውቀው! ባርነት እንቢ ነው!! ስለዚህ በሰላም የቀድሞው ክብራችን እንጠብቅ!! ሕዝቡ መንገላታት የለበትም,ሐሳቡን በነጻነት የመግለጽ መብቱ ይከበር!! የሚሉትን እስክንድርን, አንዱአለምን, ርዮትን, ሌሎችንም ፍቱዋቸው እና በነጻ ለሐገራችን እንወያይ ነው?? እንጂ, ስለ ኤርትርው መሬ ጉዳይ ምን አመጣው እሳቸው የጎራቤት ሰው ናቸው!! በምን መለኪያ ነው በኢትዮጲያ ጉዳይ…የሚገቡት??????አልገባኝም????የግንቦት 7 አመራሮች ጥሩ ራዕይ ያላቸው ቢሆኑም ከሁሉም ፓርቲ ጋር በመስራትና ቅድሚያ የሚሰጡት ለሐገራችን ሉአላዊነትና ለሕዝቦች ደህነትና ሰላም ብልጽግና ስለሆነ የሚመሰገኑና ብቃት ያላቸው ስለሆኑ በርቱ!!ነው የሚባሉት ህዝቡ ስደትና እስራት ይብቃው!!ነው የሚሉት!!በተረፈ እግዚአብሔር የሕዝቡን መከራ በቶሎ በቃ ይበለው!!!!ሰላም!ሰላም!ሰላም!ሰላም!ያምጣልን!!!
የኒእታ ተክሊእ ሳይበስል ያረረ ፍጡር ነውና ብዙም ቂም አትያዙበት
የነታ ተክለ ሳይበስል ያረረ ፍጡር ነውና ራሱን ተራራ አሳክሎ በሚጽፈው ዝባዝንከ ብዙም ባትከፉ ደህና ይመስለኛል::
ችግሩ ኬኛ ጋር ነው! የመጀመሪያ ስህተቱ ጊዘ ልናርመው በተገባና እዚህ ማጥም ውሳጥ ባልገባ!
We will see after some year this guy is going to wayanne like Slomon
Tekalgn.
ምነው ሰውዬው ሃሳቡን ለሱ በሚመሰለው መልኩ አስቀምጦታል ምነው ይህ ሁሉ ውርጂብኝ በርግጥ እውነቱን ነው መቼ ቀን ኢትዮጵያዊ ተስማምቶ ያውቃል በባዶ ሜዳ ትችትን ማብዛት ካልሆነ ለቁም ነገር የሚገኝ የለ ውጭ ያለው በየመንደሩ መጮህ አገር ቤት ያለው ፈሪ ምኑ ቅጡ ወራዳ ህብረተሰብ አሁን ደግሞ ይህንን ግለስብ ሃሳቡን ስላካፈለ ዩ ሁሉ ወቀሳና ትችት ለምን ባስፈለገ ታዲያ ያንን አልነበረም ሊገልጽ የሞካረው ኢትዮጵያዊ ሊስማማ አይችልም ምደረ ከሃዲ ሁላ አየናችሁ ለጥቅም ሚስቱን የሚሸጥ ህብረተሰብ ምንም ቁምነገር ሊኖረው አይችልም ::