እንዴ! ወያኔዎች ማበዳቸውን ለማሳየት ይህን ያህል ርቀት መጓዝ ነበረባቸው? ታረቀኝ ሙጬ
ሰሞኑን በአርምሞ ሰነበትኩ፡፡ በሀገር ቤትም ሆነ በውጪው አሳዛኝና አስገራሚ ዜናዎችና ሀተታዎች ግን እየተደነቅሁ፣እየቆዘምኩና እየተሳቀቅሁ ከርሜያለሁ፡፡ በተለይ በተለይ በሁለቱ ጉዶች – መለስና አሳድ፡፡
እንደነዚህ ሁለትና ሦስት ቀናት ግን በሰው ልጆች ከንቱነት ተደምሜ አላውቅም፡፡ በመሠረቱ የኢትዮጵያን ጉዳይ ሸለል ካላሉት በእርግጠኝነት ሊያሳብድ ይችላል፤ ወያኔዎቹ ግን ይህን ይፈልጉታል – ጠቅልለን ጨርቃችንን እንድንጥልና ብቻቸውን ካለገልማጭና ካለቆንጣጭ ካለአሳባቂም ሥልጣንና ሀብት ላይ ፊጥ እንዳሉ ዝንታለማቸውን ሲምበሸበሹ ለመቆየት – በዚያች የመተካካት ቻይናዊ ፈሊጣቸው፡፡ ምኞት አይከለከልም መቼም፡፡
በጥንቱ አማርኛ ያንዠቴን ነው የምላችሁ ወያኔ እንደሰሞኑ አሳዝኖኝም አበሳጭቶኝም የሚያውቅ አይመስለኝም፡፡ እንዴ – ከ85 ሚሊዮን ሕዝብ መሀል ተመስገን ደሳለኝ የምንለውን የፍትህ ጋዜጣ መሥራችና ዋና አዘጋጅና ቆፍጣና የብዕር ወታደር በአልሻባብ ተባባሪነትና የኮንትራት ተቀጣሪነተ ፈርጆ እንዲህ እንደማሽላዋ በምፀት ሣቅ ሆዳችንን ያንፍረው እንዴ? ምን ዓይነት ቀውስ ውስጥ ቢገቡ ይሆን ጃል እንዲህ የተጃጃሉት? በውነት ምን ነካቸው? አንድ ሺህ ከመቶ(1000 ፐርሰንት) ቢታበድ እንዲህ ዓይነት የለዬለት የዕብድ ሥራ ይሠራል እንዴ? በኢሜይል አድራሻየ ቢጠይቁኝ ከዚህ የተሻለ የመወንጀያም ሆነ የማሳደጃ ዘዴ ልነግራቸው እችላለሁ፡፡ የኢትዮጵያን ሥልጣን ይዘው በሀገራችን ስም ይህን መሰል አሳፋሪ ነገር ከሚሰሩና በዓለም ፊት ከሚያዋርዱን ለተወሰነ ጊዜ እምነትና አቋሜን ‹ሰስፔንድ› አድርጌ በነጻ ልተባበራቸው ዝግጁ ነኝ፡፡
እንደውነቱ ከሆነ የማስመሰል ውንጀላ ዓይነትና ልክ አለው፡፡ ማስመሰል ማለት ነጭ ውሸት ማለት አይደለም፡፡ ይሄ ውንጀላ እኮ ሌላ ስያሜ ካልወጣለት በስተቀር የዓለም ቋንቋዎች ሁሉ በጋራ ቢመካከሩ አንድም ገላጭ ቃል ሊያገኙለት አይችሉም፤ ወያኔዎች ለካንስ እንደዚህ ዓይነት ወራዳና ተራ ጩልሌ ኖረዋል? እኔ ይህን ያህል ይወርዳሉ ብዬ በውኔም በልሜም አልጠበቅሁም፡፡ አህያዋ ‹አያ ጅባጅቦ ሳታመካኝ ብላኝ› ያለችው ወዳ አይደለም፡፡ ከዚህ ከዚህስ ‹ተሜ! በይ እስካሁን አየንሽ፤ ጥሩ ትጽፊያለሽ፤ ሀገሬና ሕዝቤ ለምትያቸው ጥሩ የምትቆረቆሪ መሆንሽን ተረድተንልሻል፡፡ ነገር ግን መቼስ ማል ጎደኔ ይባል የለም? አዎ፣ እኛም መኖር አለብን፡፡ 17 ዓመት ታግለንና ተከታይ ጭፍሮቻችንን አታግለን ያገኘነውን ድል በብዕርና በዴሞክራሲ ሰበብ ልናጣው አንፈልግም፡፡ ስለዚህ አደብ ግዢና እንደሌላው ሕዝብ አርፈሽ ተቀመጪ፡፡ አለበለዚያ እንደ አሰፋ ማሩና እንደፕሮፌሰር አሥራት ሮጠሽ ሳትጠግቢ በለጋነት ዕድሜሽ እናጠፋሻለን፡፡ አለዚያም አንዳችም ምክንያት ሳያስፈልገን እንደነ እስክንድርና አንዷለም ዘብጥያ እናወርድሻለን፡፡…› ቢሉ ባማረባቸው ነበር፤ ይህኛው መቶ ዕጥፍ የተሻለና የመሰል አምባገነኖችንም ራሮት የሚያስገኝ ተግባር ነው ፡፡ የአሥመራው ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋዜጣ የለ፣ ፓርላማ የለ፣ ምርጫ ብሎ ነገር የለ፣… የለየለት ፈላጭ ቆራጭ አምባገነን ሆኖ ሕዝቡን እንደከብት ሲነዳ ማን ነካው? የምን ማስመሰል ነው? በነገራችን ላይ በድረ ገፆቻችን ላይ ዛሬ ስለውሸት ያነበብኩት የበላይነህ አባተ መጣጥፍ እንዴት ግሩም ነው?
በርማ እንኳን ከኛ በኋላ ተነስታ በዴሞክራሲ ረገድ የትና የት ስትደርስ እኛ እንደግመል ሽንት የኋሊት እንቅር? ያቺው የነበረችን ብቸኛ የብሶት መተንፈሻ ጋዜጣም እንደሌሎች ጓደኞቿ ልትዘጋ ይሆን? ምን ዓይነት ጉድ ነው? ምን ዓይነትስ ዕድል ነው ያለን? ጨለማው በረታሳ - ሊነጋ ይሆን እንዴ? እኔ ጠርጥሬያለሁ – እናንተስ?
የለየላቸው አምንዣኪ ከብቶች ከሆንን ይሄውና ሰባት ዓመት አለፈን – ከ97 ወዲህ በተለይ ለማለት ፈልጌ ነው፡፡ አንናገር አንጋገር ዝግትግት! መጥኔ ለኛ፡፡
በየትኛው ሀገር ይሆን ስካይፕና ትዊተር መጠቀም 15 ዓመት እሚያሳስር? በየተኛው ሀገር ነው ‹የሀገሬ ፖለቲከኞች ሆይ! እባካችሁን ተስማምታችሁ ለሕዝባችሁ የሚጠቅመውን ሥሩ› ብሎ መናገር የሚያስገድልና ከርቸሌ የሚያወርድ? ወያኔ ምነው በኢትዮጵያውያን ላይ የሚሰነዝረውን በትርና አኮርባጅ እንዲህ አፀናው? በእውኑ ይህ ነገር መነሾው ሥልጣንና ሀብት ብቻ ነው ወይንስ ሌላም አለበት? ያዋጁን በጆሮ አሉ! ሌላውና ትልቁ የወያኔ አጀንዳማ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ከምድረ ገጽ ማጥፋት አይደለም እንዴ? ብቀላውና የሥር በሥር ምንጠራውም ለዚህ ነው፡፡ ኢሳት ወደኢትዮጵያ ከሚገባ የኢትዮጵያ አንጡራ ሀብት እየተሟጠጠ ለቻይና ቴክኖክራቶች ይከፈል – ጃም እንዲያደርጉለት – ብለው ድርቅ ያሉትስ ከዚሁ ከኢትዮጵያዊነት ጋር ባላቸው የታሪክ ቁርሾ አይደል፡፡ በሰው ልጆች ታሪክ እንዲህ ዓይነት የዱርዬና የወሮበላ መንጋ በመንግሥትነት የታየበት ሀገርና ዘመን ፈጽሞውን ያለ አይመስለኝም፡፡
የመለስ አያያዝ በጭራሽ አላማረኝም፤ ለነገሩ መቼውንም አምሮኝ አያውቅም፡፡ የአሁኑ ግን ለይቶለት አብዷል፡፡ እነ በረከት አብደዋል፤ እነ ስብሃት ነጋ አብደዋል፤ እነሳሞራ አብደዋል፤አማካሪም አጥተዋል – ምክር መስማት የማይፈልጉ አፄ እንደልቡዎች መሆናቸው የታወቀ ቢሆንም፡፡ በጥቅሉ ወያኔዎች ይሠሩትን አጥተው በጅምላም በችርቻሮም ከፍተኛው የዕብደት ደረጃ ደርሰዋል ማለት እንችላለን፡፡ ዕብደቱ በነሱ ብቻ ቢቆም ጥሩ ነበር፡፡ ነገር ግን በሥራቸው ያለ አሽከርና ሎሌ ሁሉ እንደነሱው በነሱው የውሻ ዕብደት በሚመስል የተጋቦት ልክፍት ተለክፎ ሕዝቡንም በሁሉም ረገድ እያሳበደው ነው፡፡ የነሱ ዕብደት መነሻው የያዙት ጥቅምና ሥልጣን እንዳይነካና በሠሩትም ወንጀልና ጥፋት እንዲሁም ሙስና እንዳይጠየቁ ነው – የፊት ለፊቱ መነሻ መሆኑ ነው፡፡ የኛ ዕብደት መሠረት በየሴኮንዱ ሽቅብ የሚወነጨፈው የኑሮ ውድነትና አንዳችም ፍትህ የሌለበት ወያኔያዊው መሪር አገዛዝ ነው፡፡ ዋ! የዚህ ሁሉ ግፍና በደል መጨረሻ ሲደርስ ታዲያ ግፈኞች የሚከፈላቸው ምንዳ ይታየኛል፡፡የሠራተኛ ደመወዙ ይከፈለዋል፡፡ የማንም ላብ እንዲሁ አይቀርም፡፡ እናም በሠሩት ልክ ማግኘታቸው የሚጠበቅ እንጂ በአቋራጭ የሚያመልጡት አይሆንም፡፡ እኛም እንዳለቀስን አንቀርም፡፡ የውሻን ደም በከንቱ የማያስቀር ጌታ ዕንባችንን የሚያብስበት ጊዜ ሲመጣ፣ ደማችንን የሚጠርግበት ወቅት ሲብት፣ ቁስላችንን የሚያጠግበትና ስብራታችንን የሚጠግንበት አበቅቴ ሲጠባ፣ የጠገበን ሊያበርድ የተገፋንና ደም ያለቀስን ሊክስ መንበረ ሥልጣኑን ለደጋግና ቅን አሳቢ ዜጎች ሲሰጥ ያኔ እኚህ የአጋንንት ውላጆች፣ እኚህ ሀገርና ወገን ካጆች የሚገቡበትን ለማየት ያብቃን፡፡ ቀኑ ደርሷል፡፡ እንዲህ ያቅነዘነዛቸው የቀኑ መቅረብ መሆን አለበት፡፡ ከተራበ ለጠገበ አዝናለሁ ይላል አማራ – የዛሬውን አያድርገውና፡፡ ዛሬማ ምኑን ተረተው፡፡ እንደእባብ አናት አናትን እየተቀጠቀጡ ተረት የለም ወዳጄ፡፡ ግን ለበጎ ነው፡፡ በዚያውም የንስሃ ማውረጃ ሱባኤ ቢጤ መያዣ ጊዜ ነው፡፡ ሆኖም ቢሆን ግን አብዬ ሙጬ አጠፉ በተባለ ጥፋት እኔ ልጃቸው ታረቀኝ ይህን ያህል ባልበደል ደስ ባለኝ ነበር፤ በእስካሁኑ ካለፈልኝም እሰዬው ነው፡፡ ጥሩ ነው – አንዳንድ አጋጣሚዎች ራስን ለመመርመርና ከመስመር የወጣ ነገር ካለ ወደ መስመር ለመመለስ ይረዳል፡፡ ችግሩ የስሙኒን ስህተት በሚሊዮንና ቢሊዮን በሚገመት ሂሳብ ማወራረዱ ላይ ነው – የላይኛውን – የላይኛውን- የፈጣሪን በመዘንጋት! ‹ታሞ የተነሳ ፈጣሪን እረሳ፡፡
ውድ የወያኔ አገልጋዮች!
በተለይም በ‹ደኅንነት›፣ በፖሊስና በመከላከያ ውስጥ የምታገለግሉ ወገኖቻችን፤
ሁሉም ነገር ያልፋል፡፡ ብትገድሉንም ባትገድሉንም ያው ነው፤ አንዴውኑ ዕጣ ፋንታችን በወያኔው ግዛት ከወደቀ ወዲህ በቁማችን ሞተናል – በተውሶ ዐረፍተ ነገር “አልሞትንም ብለን አንዋሽም” በማለት የሚሊዮኖችን ብሶት መግለጽም እችላለሁ፡፡ በመንፈስ የሞተ ሰው ደግሞ በአካልም ቢደገም ዐረፈ እንጂ አልሞተም – ከሞተ ሰነባብቷልና፡፡ የምትገድሉን ሬሣችንን ነው – ነፍሳችንን እንደሆነ መቼም ቢሆን መግደል አይቻላችሁም፡፡ ከፈጣሪ ባይፈቀድላችሁም ኖሮ በወያኔው የጦር አዛዥነት ይህን ያህል ጥፋትና ውድመት በሀገርና በዜጎች ላይ ልታደርሱ ባልተቻላችሁ ነበር፡፡ ፈጣሪ ሲቆጣ ጨካኝ መንግሥት እንደሚሾም ዱሮውንም እናውቃለን፤ሊክስ ሲፈልግ ደግሞ አለቆቻችሁ እንደወገብ ቅማል ሰግጠው እንደያዟቸው እንደእምዬ ምንሊክ ያለ ፈሪሃ እግዚአብሔር የሆኑና አፍቃሬ ሀገር ወሕዝብ የሆኑ መሪዎችን ያነግሣል፡፡ አዲስ ነገር አልነገርኳችሁም፡፡ ይህን ነባራዊ እውነታ አዛዦቻችሁም እናንተም ታውቃላችሁ፡፡ ይህን ብቻ ሳይሆን በተለይ የጥፋት ሠራዊት መሪ የሆኑት እነመለስና ሣሞራ የመጨረሻ ዕጣቸውንና ፈጣሪ የመደበላቸውን ዋጋም ያውቃሉ፡፡ ለዚህ ነው ጨንገራቸውና ልምጫቸው የጠነከረብን፡፡ የኛንና የእነሱን የመጨረሻ ዋጋ የውስጠኛ ማንነታቸው (ሰብኮንሸስ) ስለሚያውቅ ነው ጭካኔያቸው በቅናት መልክ የበዛብን፤ ሀቁ ይህ ነው ዕወቁት – ይወቁት፡፡ የጋራ ሀገራችን በሁሉም ረገድ ከሞተች ቆይታለች፡፡ አሁን እንዳለን አንቆጠርም፡፡ ፈጣሪን የሚፈራ የሃይማኖት አባት ከጠፋ፣ የወንጀለኞችን ዕኩይ ድርጊት በሰይጣናዊ መስቀል የሚባርክና የሚቀድስ ጳጳስና ፓትርያርክ የመንበረ ጴጥሮስን የነፍስ ማሰርና መፍታት ሥልጣን ከያዘ – በየደረጃው የሚገኙ ተከታዮቹንም በራሱ መልክ ቀርፆ ለጥፋት ካሰማራ፣ ሕዝብ ተበደለ ሀገር ቆረቆዘ ብሎ የሚጨነቅ መሪና የተዋረድ ባለሥልጣናት ከሌሉ፣ ወጣቱን ገደል የሚከት አዲስ ባህልና መጤ ልማድን ይሁነኝ ብሎ የሚያስፋፋ የመንግሥት ተቋም ከተዘረጋ፣ የሞራልና የመልካም ሥነ ምግባር ዕሴቶች ደብዛቸው እየጠፋ አምልኮተ ገንዘብና አምልኮተ ዘውግ በመንግሥትነት ከተሰየመ፣ ሕዝብን ወደ ከብትነትና አልፎም ወደ ግዑዝ ድንጋይነት የሚለውጥ ሰይጣናዊ የመንግሥት አመራር ከተተከለ… አንድ ሕዝብ እንደሕዝብ የመኖር ዕጣው ለጊዜውም ቢሆን ያቆማል፡፡ እኛ ኢትዮጵያውን ያለንበት ወቅታዊ አሳዛኝ ሁኔታ ይህን ይመስላል፡፡ እስከዚያው ብርታትን ይስጠን እንጂ ወደሜዳው እየዘለቅን እንደሆነ ይሰማኛል፡፡
ከፍ ሲል የተጠቀሳችሁ አብዛኞቹ የዚህ ሥርዓት አገልጋዮችም የኛኑ ዕጣ የምትጋሩ እንደሆናችሁ እናምናለን፤ ሌላው ቢቀር እንደኛውና ከኛው ጋር የሚቀጠቀጡ ዘመድ አዝማዶች አሏችሁ፡፡ የሁላችን መሪ ሆኖ በገዛ ጉልበቱና በታሪክ አጋጣሚ እላያችን ላይ የተጎመረው መለስ ዜናዊ ደግሞ ማንንም የማይምር በሰው አምሳል የተፈጠረ ብዔል ዘቡል ለመሆኑ እማኝ መቁጠር ሳያስፈልገን ባለፉት 21 ዓመታት በሀገራችን ውስጥ በዚሁ ሰው የበላይ አመራር ሰጪነት የተከናወኑትን ወገንን የመከፋፈልና ሀገርን የመሸጥ ዕኩይ ተግባራት በመመልከት መረዳት እንችላለን – የፊትን ቅርጽና ባህላዊውን የኮከብ ቆጠራ ውጤት ትተን፡፡
ስለዚህ ዕጣችሁ ከዕጣችን አንድ ከሆነ ዘንድ ለዚህ ለይቶለት ያበደ ለሚመስል ግለሰብና ቦንግል ጎጠኛ ሥርዓት ስትሉ ቋሚ ቅርሳችሁን – ማለትም ሕዝቡን – በምንም መንገድ ልትከዱትና ልትጎዱት አይገባም – የበላችሁበትን ወጪት ከመስበር ታቀቡ፡፡ እናንተ ረዳችሁትም አልረዳችሁትም ፈጣሪና ታሪክ ቅጣቱን በሚሰነዝሩ ጊዜ ይህ የአጋንንት ውላጅ የሰንበት ጽንስ ሰውዬ የሚገባውን ዋጋ ማግኘቱ በፍጹም የማይቀር ነው፡፡ እንዲህ በስሜት ሞገድ ተውጬ በቁጡ ቃላት መናገሬ ሰውዬው ከሠራቸውና እየሠራቸው ካለው መጥፎ ድርጊቶች በመነሳት እንጂ ክፋትን በክፋት ለመቃወም እንዳልሆነ በአክብሮት ልገልጽ እወዳለሁ፡፡
የእናንተ ንስሃ መግቢያ ጊዜ አሁን ነው፡፡ በዘርም ይሁን በጥቅም ከአምባገነኖች ጋር ወግኖ መቆም መጨረሻው እንደማያምር ዓለማችን በተደጋጋሚ እያስተማረችን ነው – መገንዘብና ማገናዘብ አቃተን እንጂ፡፡ በቅርቡ አይሆኑ ሆኖ ከ42 ዓመት የዙፋን አልጋው የተወገደውን ጋዳፊን ማየት ይቻላል፡፡ የሦርያውን ባሽር አላሳደን ማየት ይቻላል፡፡ የየመኑን አብደላ ሳለህን ማየት ይቻላል፡፡ የግብጹን ሆስኒ ሙባረክን ማየት ይቻላል፡፡ እጅግ ብዙ ናቸው፡፡ ዘርዝረን አንጨርሳቸውም፡፡ ከነዚህ የታሪክ አጥቆች መረዳት የሚቻለው ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት ወይም በገንዘቡ ኃይል ወይም በወዳጅ ሀገራት የስለላና ወታደራዊ ትብብር ሊድን እንደማይችል ነው፡፡ ከዘረኝነትና ከሃይማኖታዊ ወገንተኝነት ጋር የተገመደ አምባገነንነት ደግሞ በሕዝብና በሀገር ላይ ብዙ ጥፋትና ውድመት አስከትሎ ነው በእውነት አሸናፊነት ፍልሚያው የሚደመደም፡፡ ለምሳሌ የአላሳድ ጉዳይ የሣምንታት ወይም የጥቂት ወራት ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ያለቀለት ለመሆኑ ከአካሄዱ ያስታውቃል፤ በአንድ ሌሊት የሚፈጸሙ ታሪካዊ ክንውኖች ጥቂቶች ናቸው – ብዙዎቹ በቂና አመቺ ጊዜን ይፈልጋሉ፡፡ ቋቱ አልሞላ ብሏቸው እንጂ ሰውዬው ፀሐያዊ የዘመን አክሊሉን አገባድዶ እሾህ አሜከላዊ የጨለማ ጉዞውን ከተያያዘና የሚገባውን ምንዳ ሊያገኝ የመቃብር ዋሻው ከተከፈተ ትንሽ ሰንብቷል፤ ሰውዬውም ሆነ አድሎኣዊ ሥርዓቱ ያሉ ይመስላል እንጂ የሉም – ፀጉራም ውሻ አለ ሲሉት ይሞታል -ዓይነት ነው፡፡ በተለይ እንደነዚህ ያሉ ትግሎች በባሕርያቸው አስቸጋሪና እልህ አስጨራሽ ናቸው – ዘርና ሃይማኖት ያቆላለፋቸው ጥቅመኞች በትግሉ ውስጥ ስለሚሸረቡበትና ፍጻሜያቸውን በራሳቸው ትርጓሜ አንድ አድርገው ስለሚመለከቱ ነው የአስቸጋሪነቱ መነሻ፡፡ ይህችን የጥቅምና የዓላማ ትስስራቸውን እንደልዩ ሥልት እስከመጨረሻው በመጠቀም ብዙ ውድመት ካደረሱ በኋላ ይወገዳሉ – በመቃብራቸውም ላይ አዲስ ሥርዓት ይዘረጋል፡፡ ችግሩ እነሱ ከተወገዱም በኋላ ትተውት የሚያልፉት ጠባሳና የባለወተራዎች ርኩቻ ወይም የሥልጣን ጠለፋ ነው፡፡ የኛዋን ጨምሮ ብዙዎች ሀገሮች ለዚህ ዓይነቱ ወረርሽኝ ተጠቂ ሆነዋል፤ እየሆኑም ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ ያደርገውን አጥቶ የፈዘዘ መስሎ እሚታየው ለዚህ ዓይነቱ የረቀቀ መንግሥታዊ ሥርዓት ልምድ ስለሌለውና ትግሉ ለሚፈልገው መስዋዕትነት የሚያዘጋጀው የተማከለ የትግል ስትራቴጂስት – በእስካሁኑ ሁኔታና በተለይ በሀገር ውስጥ- ባለማግኘቱ ነው፡፡ እንዲህ እንደሆነ ይቀጥላል ማለት ግን አይደለም፡፡ ጊዜና ፈጣሪ ለሁሉም ችግሮች መፍትሔ አላቸው፡፡ መፍትሔዎች መናፍስት ናቸው፡፡ በሉ ሲላቸው ይከሰታሉ፤ በሉ ካላላቸው ይሠወራሉ – ተገቢውንና ሁነኛውን አስፈጻሚና ፈጻሚ እስኪያገኙ፡፡
እኛ ኢትዮጵያውያን እንደሕዝብ ጥሩዎች ነን፡፡ እንደሕዝብ ይቅር ባዮች ነን፡፡ እንደሕዝብ ሰውኛ ባሕርያችን ጎልቶ የሚታይ በጣም የሚያስቀና ማኅበራዊ ሕይወትም ያለን ታሪካዊ ሕዝብ ነን፡፡ መለስ ዜናዊ ከአንጋቾቹ ጋር ‹ተጋደሉ፤ ተጨፋጨፉ፤ የማን አባት ገደል ገባ፣ አማራ ገዳይ – ትግሬ ገዳይ – አህያ ገዳይ – አይጥ ማራኪ…› እያለና እያስባለ በተለዬ ፀያፍ ስብዕናው ለአካለ መጠን ከደረስ ጊዜ ጀምሮ ቢወተውተንም ሰምተን እንዳልሰማን በመሆን እስካሁን፣ አሁንምና ወደፊትም ቢሆን በዕድር፣ በጽዋ ማኅበር፣ በዕቁብ፣ በጉርብትና፣ በአበልጅነት፣በሰንበቴ፣በቡና ተርቲብ፣በሠርግ፣ በልደት፣ … በጥቅሉ በመከራችንም ሆነ በደስታችን አልተለያየንም – ሃሌ ሉያ! እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፡፡ ይህ ውብና ፈተናን ቻይ ጠባያችን(resilience) የኅልውናችን መሠረት – ጨርሰንም እንዳንጠፋ እየረዳን ነውና በያለንበት አክብረን እንያዘው – በሚገባ ጠብቀነውም ለትውልድ እናስተላልፈው፡፡ ሕዝብ ደግሞ እንደሕዝብ አጥፊ ያለው አይመስለኝም – ጥፋት ካለም በአብዛኛው ከአመራር ጉድለት ነው፡፡ አጥፊው ተማርኩ ብሎ በጥሬና ብስል መካከል ያለው ነገር ፈታይ ዜጋ ነው፡፡ የኢትዮጵያን ሕዝብ በቋንቋና በፊደሉ ገብተው ሊከፋፍሉት የሞከሩት – ለምሳሌ – የሕዝቡን ፈቃድና ይሁንታ አግኝተው ሳይሆን የወያኔን አጀንዳ ለማስፈጸም ዘብ በቆሙ ጥቂት መሠሪዎች አማካይነት መሆኑ ይታወሰኛል፡፡ ይህ ሁሉ ይስተካከላል፡፡ ከልብ እናምናለን፡፡ እስኪያልፍ ያለፋናል እንጂ ኢትዮጵያችን ከቀድሞው በተሻለና በበለጠ ሁኔታ አብባና አፍርታ እናያታለን፡፡
ይህችን ኢትዮጵያ ለማየት ግን ከእያንዳንዳችን ብዙ እንደሚጠበቅ መረዳት አለብን – በተለይ ከጦሩና ከደኅንነት ከፖሊሱም፡፡ ሰሞኑን ኃይለኛ የተኩስ ልምምድ ላይ እንደምትገኙ እናውቃለን፡፡ ሌሊትና ቀን በፈረቃ ነው እየተለማመዳችሁ ያላችሁት – ይህንንም እናውቃለን፡፡ የምትለማመዱትም እኛኑ – ደመወዝ የምንከፍላችሁን – የገዛ ወንድም እህት አባትና እናታችሁን – በገዛ ገንዘባችን በተገዛ መሣሪያና ጥይት ልትገድሉ ነው፤ ይህ የግፍ ግፍ መሆኑን ልትረዱ ይገባል፡፡ ዛሬን ብቻ አይደለም ማየት፡፡ ዐይናቸሁን ክፈቱ – ትናንትናንና ነገንም ቃኙ፡፡ ተመሳሳይ ጥፋት የሠሩ የት ገቡ ብላችሁ ራሳችሁን ጠይቁ፡፡ የግፍ ዕዳ ለእናንተም ሆነ ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ አታስቀምጡ፡፡ የቀደመው ስህተታችሁን ፈጣሪ ይቅር ይላችሁ ዘንድ እኛም ስለፈጣሪ ብለን ይቅር እንላችሁ ዘንድ አደራችሁን ከእንግዲህ ወዲህ በቁም የሞተ በድናችን ላይ እየተኮሳችሁ ለብዙ ጊዜኛ አትግደሉን፤ እስኪ እናሳዝናችሁ፤ መግደልም ይሰልቻችሁ፤ ማሰርና ማሰቃየትም ይሰልቻችሁ፤ መግረፍም ይብቃችሁ፡፡ ትውልድ ይትረፍ በእኛም ይብቃ፡፡ ይህን ምክር ባትሰሙ ይበልጥ ተጎጂዎቹ እናንተ እንጂ እኛ አይደለም፡፡ እኛማ ዘጠኝ ሞት መጣባችሁ ስንባልና አንዱን አስገባው ስንል ነው የኖርነው፡፡ ምን ሊቀርብን? እናም አሁንም ልድገመው በፈጠራችሁ ይሁንባችሁ መግደል ይሰልቻችሁ፡፡ መለስ የተፈጠረበት ስለሆነ ካልገደለና ካልዋሸ ጤንነት አይሰማውም – መግደልና መዋሸት ከባሕርይ አባቱ ከዲያብሎስ የታዘዙለት የዕድሜ ማራዘሚያ መድሐኒቶቹ ናቸው፡፡ ደግሞም እኮ ሰሞኑን ስታዩት – ያ አበበ ገላው የተባለ የጋራ እናታችን ልጅ በጌቶቹ መሀል ቀልቡን ከገፈፈው ወዲህ አባቱ ሰይጣን ከድቶት ጤና ርቆታል፡፡ ከአንገቷ በላይ የምትታይ የገረጣች ፍየል መስሎ አላያችሁትም? ያን ምስሉን እስኪ ከባለ አምስት ጫፍ የሰይጣን ዓርማ ጋር አስተያዩት – አንደኛው ጫፍ ወደመሬት ከሚያመለክተውና የፍየልን ምሳሌ ከሚያጣቅሰው የጨለማው ንጉሥ ዓርማ ጋር ስናስተያየው ቆሌ የራቀው ፎቶና የኮከቡ ምስል ቁርጥ ቁምጥ አንድ ናቸው – ራቅ ቀረብ እያደረጋችሁ ተመልከቱት፡፡ ገብቶ እሚወጣው መቼም በዲያቢሎስ እርዳታ መሆኑን ሳታውቁ አትቀሩም፡፡ መግደል፣ መዋሸት፣ማታለልና ማጭበርበር፣ አልጠግብ ባይነት፣ ትምክህትና ትዕቢት፣ ዕብሪትና ማንአለብኝነት… የሰይጣን እንጂ የእግዚአብሔር ገንዘቦች እንዳልሆኑ እናውቃለን፡፡
በሚዲያው ውስጥ ያላችሁትም ብትሆኑ በፍጥነት ከዚህ አሳፋሪ የወያኔ ፕሮፓጋንዲስትነት ውጡ፡፡ በልታችሁ ላትጠግቡ፣ ጠግባችሁ ሰውነት ላይሆናችሁ ስም አይሁንባችሁ፡፡ ብትችሉ ሌላ የተሻለ ወይም ተቀራራቢ ገቢ የሚያስገኝ ሥራ ፈልጉ፡፡ ያም ባይሆን የቀን ሥራ ሥሩና ነፍሳችሁን አውላችሁ አሳድሩ፡፡ የሚያስዋሽና ኅሊናን የሚያስደብቅ ሆድ ነው፡፡ የሆነ ቢሆን ግን ለሆድ ወይም ለማይረባ ወፍ ዘራሽ ወያኔያዊ ዓላማ ብላችሁ ታሪካችሁን አትግደሉ፡፡ ልጆቻችሁ አንገታቸውን ደፍተው የሚሄዱበት ዘመን በሩጫ እየመጣ ነው፡፡ ሁለቱ የኢትዮጵያ ጠላቶች በተመሳሳይ ወቅት የጤና ችግር ውስጥ መገኘታቸው ራሱ ምልክት ይሁናችሁ፡፡ ሰው ጠላ እግዜር ጠላ፡፡ ለየትኛው ጊዜ ብላችሁ እጃችሁን በደም ታጨማልቃላችሁ?ኧረ ወደዚያ ይቅርባችሁ፡፡
በውጪ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ከተኛችሁበት ንቁ፡፡ በረባ ባልረባው ስትጨቃጨቁ ጀምበር እንዳትጠልቅባችሁ አስተሳሰባችሁንና አመለካከታችሁን ለሕዝብ ፍላጎት በሚቀርብ መልክ ቃኙ፡፡ ሕዝቡ ትቷችሁ ሄዷል፤ ግን ለጊዜው ሞኝና ፈሪ ሊመስል ይችላል፡፡ እናንተ – ዛሬ በተመስገን ጦማር እንዳየሁት – እጠቅሳለሁ “(መቼም ከላይ የተጠቀሱትን ሀገርና ድርጅቶች በጨረፍታም ቢሆን የሚያውቅ ግለሰብ እነዚህ ኃይሎች ‹ፍትህን መደገፍ› በሚል አጀንዳ ቀርቶ፣ በሀገሪቱ የቀን አቆጣጠር ሥርዓት እንኳ በጋራ እንደማይስማሙ ይረዳል። ለዚህም ነው አዲስ ዘመን እንዲህ በአንድ ላይ ሊያሰልፋቸው የቻለበትን ምክንያት ከጋዜጣው አለቆች ባሻገር ሰይጣንም ቢሆን አያውቀውም እያልኳችሁ ያለሁት)” ሲል እንደጠቀሰው ከሆናችሁና ይህ አባባሉ ውሃ እሚያነሳ እውነታ ያለው ከሆነ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ የምትገኙ ትመስሉኛላችሁና ጀምበር ሳትጠልቅባችሁ ዕወቁበት፡፡ ለቀን አቆጣጠር ስምምነት አሥር ዓመት፣ ለፊደል አሥር ዓመት፣ ለሀገር ስያሜ አሥር ዓመት፣ ለፌዴራል ክልል አሥር ዓመት፣ ኢትዮጵያዊነት ለመቀበል ለሚደረግ ድርድር ሃያ ዓመት፣… እየተባለ ጊዜ የሚመደብና የሚባክን ከሆነ እንኳንስ ከመቶዎች ዓመታት በኋላ አሁን በምንገኝበት ሁኔታና በወያኔው አያያዝ ከአምስት ዓመት በኋላም ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ከዓለም ካርታ ትጠፋለች(ቋንቋ ለማሳመር ነው ባካችሁ – እንኳን ልትጠፋ ገና የብዙዎች መጠጊያ ትሆናለች!)፡፡ ደግሞም እንዲህ ስል አታኩረፉኝ፡፡ እውነትን እንደወረደ እንነጋገር፡፡ ማኩረፍ በምንም መንገድ መቅረት አለበት – ይህንን ዘመን ሊሻገር አይገባም፡፡ እረኞችና ሕጻናት እንኳን ትተውታል አሉ፡፡ ቃልን በቃል፣ሐረግን በሐረግ፣ ዐረፍተ ነገርን ባረፍተ ነገር፣ አንቀጽን ባንቀጽ፣ ግጥምን በግጥም … በሰላማዊ መንገድ መመለስ እንለማመድ፡፡ ግንፍልተኝነትና ፍረጃ ይቅር፡፡ ‹አሃ! እንዲህ ስለሆነ አይደል?…›ማለት ይቅር፡፡ ምናባዊና እውናዊ የሸሚዝ እጅጌን መሰብሰብ ከእንግዲህ ይቅርብን – አንድ ጋትም ወደፊት ሊያነቃንቀን አልቻለም፤ በዚህ የጀብደኝነትና የእልህ ባህል ተመርዘን ባለንበትም መሄድ አቅቶን የኋሊት ሽምጥ እየጋለብን እንገኛለን፡፡ የምንፈርጀውን ዓይነት ሰው ቢሆንስ? ምን አለበት? የምንቃወመው ሃሳቡን ነው ወይንስ ሰውነቱን?… ሃሳቦቻችን ይጋጩ፤ይፋጩ፡፡ ከዚያም በአብዛኛ ድምፅ ነጥረው አሸናፊዎቹ ወደ አደባባይ ይውጡ፡፡ ኧረ ጥቂት ጥቂት እንሰልጥን! አእምሮኣዊና ቁሣዊ ሥልጣኔ አልናፈቀንም? እስከመቼ ጅራትና የዓለም መሣቂያና መሣለቂያ ሆነን እንኑር?
ለሁሉም ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ ነው ነገሩ፡፡ ከፍ ሲል እንደተጠቀሰው ሁሉም ያልፋል፤ በጥባጩ ይሞታል – በተፈጥሮና በአደጋም ቢሆን – ደህናውም ይወለዳል፡፡ ያኔ ጠማሞቹ የእፉኝት ልጆች ቦታ ቦታቸውን ሲይዙ በጠራው ሰማይ በመላእክቱ ከዋክብት አጀብ የሚወለዱት (የተወለዱት) እነእንስፍስፍ አንጀቶች የሀገሪቱን የሥልጣን ሥፍራ ይረከባሉ – ከየጎሣና ነገዱ፡፡ የዘረኝነትና የሃይማኖት ልዩነት ተንቆ ሰብኣዊነትና ብሔራዊ ስሜት ገዢዎቻችን ይሆናሉ፡፡ ባለፈ አስቀያሚ ታሪክ የምናፍር በአዲስ የጋራ ስብዕና ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የምንተጋ እንሆናለን፡፡ አሁን ያን ምን አስቀላመደኝ ልጄ? ወጡ ሳይወጠወጥ አሉ!
ታምረኛው ረጋ ሠራሽና እጅግ አስቂኙ ወያኔ ለተመስገን ደሳለኝ በቀሺም ደራሲ ተጽፎ የተላከው ኢሜይል ይህ ነው፡-(የቋንቋውን ነገር አታንሱት – በሁሉም ማፈሪያዎች!)
“To Ato Temesgen Desalegne
Chief Editor of Fitih magazine
Ethiopia
It has to be remembered that AlShebab has assigned me secretly to make propagation activities in Ethiopia, Somaliland, Kenya and Uganda. To accomplish the task we have agreed with you through your representative Ato Mamush Sentie in Eritrea to publish propaganda articles against the Ethiopian government, against the interest of the Ethiopian people and the American government. It has to be remembered that we have paid US dollar 24,000 for 30 consecutive editions. Now alshebab has made strategic change to accomplish its tasks. Therefore we need the 14 edition charges US dollar 11,200 dollar to alshebab. We believe that you will return back the money to our organization. If this is not fulfilled on time you will bear a cost on your representative Ato Mamush Sentie and your life according to the rule of the organization.
Alshebab wins
Ahmedin Nasir”



ፀሃፊው የመለስ/ወያኔ አገዛዝ በኢትዮጵያና ህዝቦቿ ላይ ላለፉት 21 ዓመታትና በቀጣይም ያደረሰውንና እያደረሰ ያለውን የባእዳን ቅጥረኝነት ዘረኝነት ዝርፊያ ግፍ በደል አፈና ስደት ወዘተ ለእኛም ሆነ ለተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብና ለተቀረው ዓለም ግልፅ ነገር ነው፡፡ስለዚህም ብዙም አዲስ ነገር አይደለም ዋናው ነገር ወደ መፍትሄው መምጣት ነውና፡፡ነገር ግን እንደዚህ ፀሃፊና የተቀሩት ብዙ ኢትዮጵያውያን ፀሃፍት ብዙውን ጊዜ ግማሽ እውነት ግማሽ ሀሰት መናገር የዘወትር ልማዳቸው ነው፡፡ይህ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሚፈፀም ህዝብን በተሳሳተ መረጃ የማሳሳት ተግባር ስር ሳይሰድ በእንጭጩ መታረም ስላለበት የማውቀውንና የሚሰማኝን ጥቂት ልበል፡፡ስለዚህም ከሚፅፉትና እኛም ጠንቅቀን የምናውቀው ግማሹ እውነት የመለስ/ወያኔን አገዛዝ ምንነት የሚመለከተውና ብዙዎቻችንም የምናውቀው ፀሃይ የሞቀው እውነታ ስለሆነ በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙም ስህትት የለም፡፡ሌላው ግማሹ ውሸት ደግሞ ይህንን የመለስ/ወያኔ አገዛዝ አስታከው በቱኒሲያ በግብፅ በሊቢያ በሶሪያ በባህሬን ወዘተ ባለ የህዝብ ዓመፅና ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሚፅፉት ግን ፈፅሞ በጥራዝ-ነጠቅ የፖለቲካ አስተሳሰብ የሚመራና ከበስተጀርባ ያለውን ውስብስብ የዓለም አቀፍ ግሎባል ፖለቲካል ኢኮኖሚና ጂኦ-ፖለቲክስ ሁኔታ ፈፅሞ ግምት ውስጥ ያላስገባ እንደወረደ የሚቀነቀን ያልበሰለ ፅሁፍ ነው፡፡አምባገነን የሚለውን ጥሬ ቃል እንደወረደ እንደበቀቀን በማራገብ ዱባና ቅል አበቃቀሉ ለየቅል የሚለውንም የቆየ የሀገራችንን አባባል ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባ ነው፡፡በአሁኑ ፀሃፊና ተመሳሳይ ብዙ ኢትዮጵያውያን ፀሃፍት ዘንድ የየሀገራቱ አምባገነኖች ሁሉ በቅርብ ከህዝባቸው ጋር ባላቸው የአገዛዝ ግንኙነት ብቻ እየተመዘኑ በአንድ ቅርጫት ውስጥ አምባገነን ወይንም ዲሞክራሲን ያላሰፈኑ ወይንም አፋኝ ተብለው የሚፈረጁና የሚቀመጡ እንጂ ከዚህ በዘለለ ከበስተጀርባቸው ምን አይነት ውስብስብ የሆነ የዓለም አቀፍ ግሎባል ፖለቲካል ኢኮኖሚና ጂኦ-ፖለቲክስ አለ የሚለው ፈፅሞ ከአጀንዳ ውጪ ነው፡፡በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ መለስን ጨምሮ ማናቸውም ቀደምት አገዛዞች ሁሉ እየተወራ ባለው አይነት የምርጫ ዲሞክራሲ አልነበረምና ስልጣን ላይ የወጡት ሁሉም አምባገነኖች ነበሩ፡፡ነገር ግን መለስንም ደርግን ሃይለስላሴንም ምኒልክንም ዮሃንስንም ቴዎድሮስንም ሁሉ በአንድ ቅርጫት ውስጥ አምባገነን በሚለው ሚዛን ብቻ እየመዘኑ በአንድ አይነት ፍረጃ ለማስቀመጥ መሞከር የማህበራዊ ሳይንስ ሀ ሁ ከቆጠረ የተማረ ሰው አይደለም ፊደል በቅጡ ካልቆጠረ ከተራ ሰውም ጭምር አይጠበቅም፡፡ልክ በተመሳሳይ መንገድ የዓረቡን የህዝብ ዓመፅና አብዮት ተከትሎ የተፈጠረው ሁኔታም ሆነ የየሀገራቱን አገዛዞች እንደዚሁ በአንድ ቅርጫት ውስጥ አምባገን ብሎ ማስቀመጥም እንደዚሁ ነው፡፡ብዙ ዝርዝር ሁኔታ ውስጥ ሳልገባ የምናውቃቸው የዓረብ ሀገራትና ሌሎችም ታዳጊው ዓለም አምባገነን አገዛዞች በሁለት የሚከፈሉ ናቸው፡፡
1ኛ)አንደኛው የምእራብ ሀገራትን መንግስታት ፍላጎትና አላማ በታማኝነት የሚጠብቁ ወዳጅ የሆኑ አምባገነን አገዛዞች ናቸው፡፡በዚህ ምድብ ስር የግብፁ ሙባረክ የቱኒሲያው ቤናሊ የየመኑ ሳላህ ከአንድ ዓመት በላይ እስካሁን ድረስ ከፍተኛ የህዝብ ዓመፅ እየተካሄደባት ያለችው የባህሬን ሞናርክና በተያያዘ ያሉት 6 የገልፍ የአረብ ሀገራትና የእኛው መለስ የዬጋንዳው ሙሶቮኒ የሩዋንዳው ካጋሜና ሌሎችም ብዙዎች በዚህ ስር ናቸው፡፡የኤርትራው ኢሳያስ ጉዳይ ግን በየትኛው ውስጥ በግልፅ እንደሚመደብ ለጊዜው አስቸጋሪ ነው፡፡ምናልባት በዚህ ውስጥ ሊሆን ይችላል፡፡
2ኛ)ሁለተኛውና ሌሎቹ ደግሞ ከምእራብ ሀገራት መንግስታት ፍላጎትና አላማ ፍፁም ተገዥነት ያፈነገጡና ቅድሚያ የሀገራቸውን ብሄራዊ ጥቅምና ህልውና በማስቀደም በራሳቸው ገለልተኛና ጥገኛ ያልሆነ ሉአላዊ አመራር የሚንቀሳቀሱ አምባገነኖች ናቸው፡፡በዚህ ዋና መመዘኛ መስፈርት ስንነሳ በዚህ ምድብ ውስጥ የሊቢያው ጋዳፊ የኢራኑ እስላማዊ አብዮት አገዛዝ የኢራቁ ሳዳም የሶሪያው ባሽር አልአሳድ የሱዳኑ አልበሽር የዝምባብዌ ሮበርት ሙጋቤ የቬንዝዋላው ሁጎ ሻቬዝ ወዘተ አምባገነን ቢሆኑም ቅሉ ግን ያን ያህል የምእራቡ ዓለም መንግስታት ታማኝ አገዛዞች አይደሉም፡፡
ይህንን ከላይ ያለውን ምዘናና አመዳደደብ ስንከተል ደግሞ የአረቡን አብዮት ክስተትና በዚህም የተነሳ በየሀገራቱ ያሉትን አምባገነን አገዛዞች ባህሪ እና የምእራብ ሀገራት መንግስታት በየሀገራቱ ላለው ለአብዮቱ ወይንም ለህዝባዊ አመፅ የሰጡትን ምላሽን በቅጡ እንረዳለን ማለት ነው፡፡ለምሳሌ በሊቢያና በሶሪያ ውስጥ ለተከሰተው አብዮትም እንበለው ህዝባዊ አመፅ ምእራባውያን መንግስታት የሰጡት ምላሽ በቱኒሲያ በግብፅ በየመን በባህሬን በሞሮኮ ከተከሰተው ፈፅሞ የተለየ ነገር ነው፡፡ለምሳሌ በሊቢያ ለተከሰተው ችግር ምእረባውያን መንግስታት ወዲያውኑ ጋዳፊ 42 ዓመት የገዙትን የገዛ ህዝባቸውን እንደ ጭራቅ ሊበሉት ነው ብለውና ነገሩን አጋግለውና ትኩረት ሰጥተው ወደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት በመውሰድ በኔቶ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት የጋዳፊ አገዛዝ በምናውቀው ሁኔታ መገርሰስ ብቻ ሳይሆን የጋዳፊም ፍፃሜ ያ አይነት አሳዛኝ የሆነ ኢፍትሃዊና ሰብዓዊነት የጎደለው ፍፃሜ እንዲሆን በቃ፡፡ቢያንስ ጋዳፊ ፈፀሙ ለተባለው ጭፍጨፋ በህግ ፊት ቀርበው እውነቱ እንዲወጣ አልተደረገም፡፡በእርግጥም ከበስተጀርባ ያለው እውነታ ሌላ ስለሆነ እውነቱ እንዲወጣም አልተፈለገምና ጋዳፊ በዚያ አይነት ሁኔታ ህይወታቸው አለፈ፡፡በእኔ እይታ የጋዳፊ ተቃዋሚዎችና የደርግ ተቃዋሚ የነበሩት መለስ/ወያኔ የተወሰነ ተመሳሳይነት አላቸውና ስለዚህም ወደፊት ምናልባት ሊቢያ የኢትዮጵያ አይነት እጣ ፋንታ ነው የሚጠብቃት፡፡በተመሳሳይ ሁኔታም አሁን በሶሪያ ያለው ነገር ከሊቢያው ጋር የሚመሳሰል ነገር ነው፡፡አሁን ስልጣን ላይ ያለው የባሽር አልአሳድ አገዛዝ ልክ እንደ ሊቢያው ጋዳፊ የምእራባውያን መንግስታት ድጋፍ የሌለው ብቻ ሳይሆን ከስልጣን ምእራባውያን መንግስታት ለራሳቸው ጥቅምና ፍላጎት ሲሉ ብቻ ከስልጣን እንዲወገድ አጥብቀው የሚሹት ነው፡፡በዚህም የተነሳ ምእራባውያን መንግስታት የሶሪያን ጉዳይ ልክ እንደ ሊቢያ በተለመደው አካሄድ ወደ ተባበሩት መንግስታት ቢወስዱትም ቅሉ ግን በሊቢያ የተፈፀመው አይን ያወጣ ወረራና ይህንን ተከትሎ የተፈፀመው ቀውስና ስህት ዳግም በሶሪያ እንዲደገም ያልፈለጉት ቻይናና ሩሲያ ድምፅን በድመፅ የመሻር መብታቸው ውድቅ አደረጉት፡፡ይህ በእንዲህ እያለ በተቃራኒው ግን የራሳቸው የምእራብ ሀገራት መንግስታት ወዳጆች የሆኑት እነ የቱኒሲያ ቤናሊ የግብፁ ሙባረክ የየመኑ አብደላ ሳላህ ከስልጣን መልቀቃቸው የማይቀር ግዶ ሆኖ ስልጣን ቢለቁም ቅሉ ግን ግለሰባዊ ደህንነታቸውን በሚመለከት ግን የገጠማቸው ነገር ግን ከሊቢያው ጋዳፊ አሳዛኝ የሆነ ኢ-ሰብዓዊና ኢ-ፍትሃዊ ፍፃሜ ፈፅሞ የተለየ ነገር ነው፡፡እንደዚሁም ምእራባውያን መንግስታት ወዳጅ ሞናርካዊ አምባገነን አገዛዝ ባለበት ባህሬን ያለውን ሁኔታ ስናይ ደግሞ ጭራሽ ሳውዲ አረቢያ ጭምር ጦር አዝምታ የባህሬንን ሞናርካዊ አምባገነን አገዛዝ ስልጣን ለመታደግ ተቃዋሚ ህዝቡን እየረገጠች እያፈነች እየደበደበች እንደዚሁም አንዳንደ ጊዜ እየገደለች ነው፡፡ይህ ነገር በባህሬን ላይ ሲፈፀም አሁን አንድ አመት ነው ያለፈው፡፡ነገር ግን ስለ ሶሪያ ግብፅ ሊቢያ የመን ወዘተ የተወራውን ያህል አንድም ኢትዮጵያዊ ፖለቲከኛና ምሁር በባህሬን ውስጥም ሆነ በገልፍ ውስጥ ስላሉ ስድስት በሞናርካዊ አምባገነን አገዛዝ ስር ስላሉ ሀገራት ሞናርካዊ አምባገነን አገዛዝ ትንፍሽ ያለ የለም፡፡ምክንያቱ ደግሞ ግልፅ ነው እነዚህ ሀገራት የአሜሪካና የምእራብ ሀገራት ዋና ወዳጆች ስለሆኑ ነው፡፡በሶሪያ ወስጥ እየተፈፀመ ያለው ነገር ደግሞ እጅግ ውስብስብ ነገር እንደሆነ ብዙዎቻችን በቅጡ ሳንረዳ ነው በጥራዝ-ነጠቅ አስተያየት የምንሰጠው፡፡የሶሪያ አገዛዝ አምባገነን ነው አይደለም ሌላ ጉዳይ ሆኖ ቅሉ ግን አንድ ሉአላዊ ሀገርና ህዝብ ግን የራሱን የውስ ጉዳይ ቅድሚያ በዋናነት እራሱ ነው ማስተናገድ ያለበት፡፡ልክ እንደ ሊቢያው ጋዳፊ ሁሉ በሶሪያ አሁን ስልጣን ላይ ያለው የባሽር አልአሳድ አገዛዝ ምእራባውያን መንግስታት ከስልጣን እንዲወገድ ስለሚፈልጉ ብቻ ልክ በሊቢያ እንደሆነው ሁሉ ከተለያየ የአረብ ሀገራት የተሰባሰቡና የታጠቁ ቅጥረኛና ሰርጎ ገብ ሽምቅ ተዋጊዎች ናቸው ዛሬ ሀገሪቱን እያተራመሱና ቀውስ እየፈጠሩ ያሉት፡፡እንዲያውም በዚህ አይነት ቅጥረኛና ሰርጎ ገብ ሽምቅ ተዋጊዎች መካከል እራሱ አልቃኢዳ ጭምር ነው ዋና ተዋናይ እንደሆነ ነው እየተወራ ያለው፡፡ይህ የሚሆነው ደግሞ ምእራባውያን መንግስታት በሊቢያ እንዳደረጉት ሁሉ በሶሪያም ለራሳቸው ታማኝ የሆነ አገልጋይና የእነሱን ፍላጎትና ጥቅም የሚያስከብር ወዳጅ አገዛዝ በምትኩ ስልጣን ላይ ለማውጣት ስለፈለጉ ነው፡፡
ከዚህ በመነጨና እራሳቸው የሶረያ ህዝቦች በሊቢያ የተከሰተው ነገር ትልቅ ትምህርት ስለሆናቸው በአሁኑ ወቅት ህዝቡ በእንደነዚህ አይነት ቅጥረኛ ሃይሎች ጭምር ከሚታገዙና ከማናውቃቸው የበግ ለምድ ከለበሱ ቀበሮ የተቃዋሚ ሃይሎች ከምንገዛ ይልቅ አሁን ስልጣን ላይ ካለው የባሽር አልአሳድ አገዛዝ ጋር ወደፊት ተገቢውን የማሻሻያ ሪፎርም ስራ ተግባራዊ በማድረግ ችግሩን በዚህ አይነት አካሄድ መፍታት ይሻለናል ብለው ተቃዋሚ ነን የሚሉትን ሃይሎች ወጊዱ አናውቃችሁም እያሉ ነው፡፡በሊቢያና በሶሪያ ያለው ክስተት በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ህዝብም ደርግን አምባገን እያለ በከንቱ ሲያወግዝና ይህም አገዛዝ ወደቆ መለስ/ወያኔና ኢሳያስ/ሻእብያ ስልጣን ላይ ሲወጡ ምን አይነት ነገር ሊፈጠር እንደሚችል ፈፅሞ አርቆ ማሰብ ካለመቻላችን ጋር የሚመሳሰል ነገር ነው፡፡አዎ ደርግ እንዲወድቅ ዝም ከምንል ወይንም የደርግ ተቃራኒ ከምንሆን ይልቅ ለጊዜው ከደርግ ጋር ሆነን መለስ/ወያኔና ኢሳያስ/ሻእብያን ድል አድርጎ ወይንም እዚህ ደረጃ እንዳይደርሱ አድርጎ ከዚያ አምባገነኑ ደርግ ላይ ተገቢውን የቤት ስራ መስራት እጅግ አዋጪና አስተዋይነት በሆነ ነበር፡፡ታሪካዊ ስህተት ማለት ይህ ነው፡፡አንድ ህዝብ እንደ ህዝብ በቅጡ ማስተዋል ሲከብደው ወደየት አቅጣጫ እንደሚሄድና ምን እንደሚጠበቀውም ላይረዳ ይችላል፡፡ከዚህ በመነጨም አንዳንዶች በሊቢያና ሶርያ ያለውን ነገር ከእኛ ጋር በምን አይነት ሁኔታ እንደሚያዛምዱት በቅጡ የተረዱ አይመስለኝም፡፡ከዚህ በመነጨም ሶሪያ አሁን ያለው አምባገን አገዛዝ ከስልጣን ወርዶ በባእዳን ሃይሎች እየተረዱ ያሉት ነፍጥ ያነገቱ ሃይሎች ስልጣን ላይ ሲወጡ ሀገሪቱ ምን አይነት ውስብስብ ነገር እንደሚጠብቃት ሁሉ ይህ ፀሃፊና ሌሎች መሰል ኢትዮጵያውያን በቅጡ ያልተረዱ ጥራዝ-ነጠቅ ፖለቲከኞች ናቸው፡፡ከዚህ በመነጨም ዝም ብለን አምባገን በሚለው ጥራዝ-ነጠቅ ጥሬ ቃል እየተመራን ትንተና የምንሰጥ ከሆነ ከፍተኛ አደጋ አለው፡፡ደርግን አምባገነን ብለን በጭፍን ስናወግዝ መለስ/ወያኔ ከደደቢት በረሃ ዳቦና ዲሞክራሲ ጭነው አላመጡልንምና አሁን ያለንበትንም ሁኔታ እያየነው ነው፡፡ስለዚህም መለስ/ወያኔን ብቻ ለመቃወም ብቻ ስንል ስለተቀረው ዓለም ያልበሰለ ጥራዝ ነጠቅ ትንተና ከመስጠት እንቆጠብ፡፡ደግሞም ለሆዳችን ስንልና ከፍርሃት በመነጨ ብቻ አንዱን ለማስደሰት ስንል ብቻ ግማሽ እውነት ግማሽ ሃሰት መናገር በፈጣሪም ዘንድ ሃጢያት ነው፡፡ባህሬን ውስጥ እየተፈጠረ ያለው ህዝባዊ ዓመፅ (ጥሩም ይሁን መጥፎ እራሱ ህዝቡ ነው የሚያውቀው) ልክ ከነየመን እኩል የተጀመረ ነው፡፡ነገር ግን ምእራባውያን መንግስታት (በተለይም አሜሪካ ባህሬን ውስጥ ሚሊታሪ ቤዝ አላት) የባህሬን ሞናርካዊ አገዛዝ ወዳጅ ስለሆኑ ብቻ እንኳንስ እንደ ሊቢያ ሶሪያ ባለ አይነት አገዛዙን ተቃውመው ጣልቃ ሊገቡ አይደለም ጭራሽ አገዛዙን በመደገፍ በሳኡዲ አረቢያና ኳታር በኩል ጦር ልከው ህዝቡን እያፈኑት ነው፡፡ስለዚህም ኢትዮጵያውያን ምሁራንና ፖለቲከኞች ሁሉ እውነትን ለመናገር ካልፈለግንና እውነትንም የምናድበሰብስና የምንክዳት ከሆነ እውነት እራሷ ከእኛ ጋር ፈፅሞ ልትወግንና አብራን ወዳጅ ልትሆን አትችልም፡፡እውነት ከእኛ ጋር ካልሆነች ደግሞ እውነት አርነት ያወጣችኋል ስለተባለ በእውነት በኩል ነፃነትን ወይንም አርነትን ማግኘት አንችልም፡፡ምእራባውያን መንግስታት ጥቅማቸው ነው ዘላቂ ወዳጃቸውና ስለዚህም ዘላቂ ወዳጅነትን አያውቁም፡፡እኛ ኢትዮጵያውያን በየምእራብ ሀገራት ቢሮዎችና ኢምባሲዎቻቸው በራፍ ላይ እንደቁራ ብንጮህም ቅሉ ግን አረመኔ የሆነውን ዘረኛውን ዘራፊውን ቅጥረኛውን አምባገነኑን መለስንና አገዛዙንም ዛሬም ከመደገፍ አልተቆጠቡም፡፡ስለዚህም ምእራባውያን መንግስታትን ላለማስቀየም ብለን አውቀንም ሆነ ሳናውቅ እውነትን እየሸፋፈንን የምንፅፋቸው ፅሁፎች ሁሉ እኛን የትም አያደርሰንም፡፡ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች እንጂ ወደ አሜሪካ ወይንም እንግሊዝ ወይንም ሌላ ምእራብ ሀገር ትዘረጋለች ተብሎ አልተፃፈም፡፡በተዘዋዋሪ እኛ ኢትዮጵያውያንን እየበደሉን ያሉት መለስን በመርዳት እራሳቸው ምእራባውያን መንግስታት ናቸው፡፡
ስለዚህም የነሱን እንደ ሳሙና የሚሙለጨለጭ ወዳጅነት ሳይሆን በዋናነት ቅድሚያ ዘላለም የማይቀየረውን የፈጣሪን ጥበቃ መከታ እናድርግ፡፡ይህ የሚሆነው ደግሞ እውነትን ስንከተል ብቻ ነው፡፡
ስለዚህም እውነትን እንናገር፡፡ከምንም ነገር በላይ መፍራት ማክበርና መገዛት ያለብን በፈጣሪ ሃይል ስር ላሉት ለምድራውያን ሃያላን አገዛዞች ሳይሆን ቅድሚያ ለራሱ ለአንድ አምላክና ፈጣሪ ብቻ መሆን አለበት፡፡በዋናነት በጥቂት ሀብታም ካፒታሊስት ልሂቃን ፍላጎትና አለማ የሚመሩት ምእራባውያን መንግስታት የታዳጊው አለም ህዝብ በአምባገነን ተገዛ በዲሞክራት ተገዛ በዝንጀሮ ተገዛ ዋናው ጥቅማቸውና ፍላጎታቸው እስካልተነካና እስከተጠበቀ ድረስ ፈፅሞ ጉዳያቸውና አጀንዳቸው አይደለም፡፡ብዙዎቻችን ይህ ነገር ፈፅሞ የገባን አልሆነም፡፡
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!!!
I have to say May God end our suffering sooner!! The book of Jeremiah 22,13
Wow to the one building his house but not with righteousness,and his upper chambers,but not with justice,by use og his fellowman who serves for nothing,and whose wages he does not give him, ይህ በቀጥታ ለወያኔ መርዘኛና ዘረኛ ካሀዲ ግፉ ወሰን ያጣ ሰወገንና የህገር ጠላት ማን ይነካኛል ቢልም አምላክ እንደ ባቢሎን ጨካኙ ንጉስ ድንገት ያዎርደዎል!!ሰንጽሆች ደም በክንቱ አፈሰሰ የተክበራችውን አገራችንን አዎራደ ሕዝቡን ለክፋ ስደት ዳራገ የሚሰራው ጭካኔ ፋታ ሰሚሰጥ ስላልሆነ ለሁሉም ኢትዮጲያዊ የምልው ልባችሁን ሰፌ አርጋችሁ እከሌ ተክሌ ሳትባባሉ ቅድሚያ የሕዝቡ መክራ ይታያችሁና በአንድነት ቁሙ አለበዚያ ልጁቻችን ወላጁቻችን ኢትዮጲያ ክምትባል አገር ነው የመጡት እንዳይሆን እደራ!! አንድነት ሀብት ነው ክብር ነው!!!አምላክም ስራችንን ይባርክልናል ጠላትም ያፍራል እንክርዳድ ክሌለ ዘሩ ያማረ ይሆናል!የተረገጥው ክብራችን አንሱት ወንድሞች እህቶች ነን መጤ ፓለቲክ ክጀርባው ማን አንዳለ ተመልከቱ ባህላችንን ክዘመናዊ እድገት ጋር እኛው ለሀገርና ለትውልድ መሰረት እንተውለት ለናታችን ያሉት ልጃቾዎ ብቻ ናቸው በተረፈ የናታችን ጠላት ይጥፋላት ታብብ እንደገና የልጃቻ እንባ ይድረቅ!!አሜን!! ሐገራችን ለዘላለም በክብር ትኑርልን አሜን!!እወድሻለሁ እማምዮ ኑሬልኝ!!!!
ለምንድነው ግን ወያኔ ሰው በገንዘብ መክሰስ የሚቀናቸው ? አበበ ገላው 250 ሺ ዶላር ተቀበለ ተመስገን 24 ሺ ዶላር ተቀበለ ,,,በቃ ይሄ ነው ክሳቸው ሌባ እናት ልጇን አታምንም እንደሚባለው ሲሰርቁ ስለሚውሉ ሌላ ክስ ያለ አይመስላቸውም እነሱ ግፍ የተሰደደው ዜጋ የሚልከውን ብር ወደውጭ አገር ባንክ መልሰው እየላኩ ለሚስኪኑ ይሄን የወረቀት ብር እያተሙ አገር ቤት ያድሉታል መሬት ይሸጣል ሰው ይሸጣል በወያኔ ምን የማይሸጥ አለ ? የት እና እንዴት ይሄሁላ የተዘረፈ ገንዘብ ይበላል? የላይኛው ብቻ ነው የሚያውቀው ም/ቱም ኢትዮጱያዊ እነሱን ጥላቻ ያልተሰደደበት አገር የለም
ሙጨ እንዴት ነው እንዲህ ሙጭሙጭ ያለ ጽሁፍ ለአቡጊዳ የበቃው? ወይስ አስፈራርተሃቸው ነው:: ሎል (በሳቅ):: የሚታረቅ ነገር ታርቆ የሞጨሞጨ እርሳስህን – ብዕር ያርገው እንጂ: ድርቅ ያለ: በውሃ አይደለም በወተት ቢያርሱት አኞ የሆነ የአዲስ ዘመን አይነት ሀተታ ነው:: መቼም ሆድ ይብሳሃል ፓልቶክ ላይም ሆነ ምድር ላይ – እና ልጥፍ ኩርፊያህ “ወያኔ” የሚል ስም መለጠፍ ስለሆነ: ያንን ተወት አርገህ: በሰል – በሰልሰል – ሰልሰል ያለ መጣጥፍ ሞክር – አያ ሙጬ!
አያ መልካሙ! እንዴት እንዴት ይሠራሃል? ልትነግረን የፈለግከው ምን እንደሆነ አልገባኝም። የተረበሸ ሃሳብ፤ የተረበሸ መንፈስ ይዘህ ታረቀኝን ለመተቸት በመነሳትህ ነገር ሁሉ ተሳከረብህ። የሚደንቀው እንደሰባኪም ይቃጣሃል።ኢትዮፕያ ዕጆቿን ወደ እግዚአብሔር ተባለ እንጂ ወደ . . . አልተባለም አልከን? የትግሉ ስፋትና ወርድ አልገባህምና አርፈህ ‘የጀመርከውን’ ጂኦ ምናምን አጥና!
ወንድሜ ታረቀኝ!
ይህ ትግል የሚጠይቀው የመጀመሪያው ነገር በህዝባችን ሃይልና ተዐምር ሠሪነት መታመን ነው።ይህ ሸርተት ካለብን አለቀ።ስለዚህ ተስፋ መቁረጥ የለም።በውጭ ያለው ኢትዮፕያዊም ነገር ሁሉ እየገባው በመታረም ላይ ነው፤ እየተደራጀ ነው፤አይዞን። ኢትዮፕያውያን እናሸንፋለን። የለበጣ አይደለም፤እናሸንፋለን።
It is really wonderful and timely. We can realize the severity of our problems for example by the mere fact that our heroes are sentenced to life due to their efforts to tell the truth and fight tyranny in their ways of preference. What is to be done should be the question of the time; it is good that we express our bitter feelings in any way possible, but we have to also sit down and find any way out to get rid of these ticks and bugs from our marrow. God bless Ethiopia and let the wishes of the writer be realized soon. Let us all pray for divine intervention before we all are lost. Great job abugida to post such enlightening piece and help us know about our country’s current affairs.
ኦ! አያ መልካሙ (ቁ. 1 ከላይ) ከዚህ በታች ያለውን አስተያየትዎን ደግመው ቢያጤኑት መልካም ነው፡፡ እኔን ጨምሮ ብዙ ሰዎች የሚሰማቸውን ይጽፋሉ – ባገኙት መንገድም ለአንባቢ ያደርሳሉ፡፡ አንባቢም የተጻፈውን ነገር የመደገፍ ወይም ያለመደገፍና የመቃወምም መብት አለው፡፡ ይህ ሲሆን ግን ምክንያታዊና አሳማኝ ቢሆን ይመረጣል፡፡ አለበለዚያ ድጋፉም ሆነ ተቃውሞው ከጠንካራና አስማሪ ጎኑ ይልቅ ደካማና አፍራሽ ጎኑ የሚበልጥበት ሁኔታ ሊከሰት ይችላል፡፡ መማማር የሚቻለው ደግሞ በአስተውሎትና የምለው ነገር በማን ላይ ምን ሊያስከትል ይችላል ከሚልም ቢሆን ጥሩ ነው፡፡ በግሌ ይህ መጣጥፍ ሊያስተላልፈው የፈለገው እውነት እንዳለው መረዳት ችያለሁ፡፡ ግማሽ እውነትና ግማሽ ውሸት ስለመያዙ ግን ደግሜም ባነበው ሊከሰትልኝ አልቻለም፤ እናም ይህን ጸሐፊ ወዳጄን ብቻም ሳይሆን በዚህ ረገድ የተቻላቸውን ጥረት የሚያደርጉትን ሁሉ (እኔንም ጨምሮ) ስሜታቸውን ያጎሻል የሚል ጥርጣሬ አድሮብኛል፤ ይህን ስል ግን ጸሐፍት የማይሳሳቱ ብፁኣን ናቸው ለማለት አይደለም፡፡ እንሳሳታለን፡፡ ባልተሳሳትንበት ግን ስንወቀስ ያመናል፤ ‹አርፈህ ብትቀመጥ ኖሮ ማን ይደርስብህ ነበር› የሚል ስሜትም ያጭርብናል፡፡ የዚህ መጣጥፍ ጸሐፊ ምን እንደሚሰማው አላውቅም፡፡ እኔ እሱን ብሆን ግን የተወሰነ ቅሬታ እንደሚሰማኝ ልደብቅ አልፈልግም፡፡ ለዚህም ነው ይህን አስተያየት ልሰነዝር የወደድኩትና ገርሞኝ የአስተያየቱን ባለቤት እርስዎን ልጠይቅ የደፈርኩት፤ ለወደፊቱም መማማሪያ ይሆናል፡፡ እርስ በርስ ስንዘራጠጥ ለወዳጅ ለጠላት ደግ አይመስለኝም፡፡ እባክዎን አይጨክኑብኝ፡- አስተያየትዎን እንደገና ከጽሑፉ ጋር ያመሳክሩና በዳግመኛ ዕይታ የሚሰማዎት አዲስ ነገር ካለ ይግለጡልኝ፤ ከታላቅ ይቅርታ ጋር፡፡
[...ስለዚህም ብዙም አዲስ ነገር አይደለም ዋናው ነገር ወደ መፍትሄው መምጣት ነውና፡፡ነገር ግን እንደዚህ ፀሃፊና የተቀሩት ብዙ ኢትዮጵያውያን ፀሃፍት ብዙውን ጊዜ ግማሽ እውነት ግማሽ ሀሰት መናገር የዘወትር ልማዳቸው ነው፡፡ይህ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሚፈፀም ህዝብን በተሳሳተ መረጃ የማሳሳት ተግባር ስር ሳይሰድ በእንጭጩ መታረም ስላለበት የማውቀውንና የሚሰማኝን ጥቂት ልበል፡፡ስለዚህም ከሚፅፉትና እኛም ጠንቅቀን የምናውቀው ግማሹ እውነት የመለስ/ወያኔን አገዛዝ ምንነት የሚመለከተውና ብዙዎቻችንም የምናውቀው ፀሃይ የሞቀው እውነታ ስለሆነ በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙም ስህትት የለም፡፡ሌላው ግማሹ ውሸት ደግሞ ይህንን የመለስ/ወያኔ አገዛዝ አስታከው በቱኒሲያ በግብፅ በሊቢያ በሶሪያ በባህሬን ወዘተ ባለ የህዝብ ዓመፅና ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሚፅፉት ግን ፈፅሞ በጥራዝ-ነጠቅ የፖለቲካ አስተሳሰብ የሚመራና ከበስተጀርባ ያለውን ውስብስብ የዓለም አቀፍ ግሎባል ፖለቲካል ኢኮኖሚና ጂኦ-ፖለቲክስ ሁኔታ ፈፅሞ ግምት ውስጥ ያላስገባ እንደወረደ የሚቀነቀን ያልበሰለ ፅሁፍ ነው፡፡...]
ሁሌ ማወቅ የሚገባን ነገር ወያኔ ሽብርተኛ እና ሌላም ስም እየሰጠ የሚያስራቸውን ሰዎች የኢትይኦፒያ ህዝብ በፍጽም አያምንም ውሸት እንደሆን በደንብ ያውቃሉ እኔ በዚህ ጥቂትም አልናደድም ምክንያቱም ህዝቡ ሽብረተኛ እንኳን ቢሆኑ እናንተን ያጥፉልን እንጂ ምንም ይሁኑ እያለ ነው ይሄን ያህል እናም ሁሉም ያውቃል ገና ተቅዋሚ እና ጋዜጠኛ ታሰረ ሲባል ዜና እንሰማለን ይቀርታ ጠየቁ, ሲባል በህሰት ሲያስመሰክሩ እያየን መሳቅ ነው ይላሉ እንደህጻን ልጅ እንደሚያስቡ ህዝብ ያውቃል እጻናቶች እንኳን ያቃሉ እናም ይህ ያስቃል እንጂ አይናድድም የፋራ ነገር ሆኖ ሲስተም እንኳን ቢቀይሩ ያዲስ አበባ ህዝብማ እንዴት እንድሚያሾፍባቸው እናም ይህ ምንም አይገረምም እውነት እንኳን ቢያወሩ የሚታመኑ አልሆን ብለዋል. ሌላው እያረጉ ያሉት ነገር መጥፊያቸው ስለደረስ የፈሪ እና የድንብርብር እርምጃ ነው ይህ የሚያሳየው ፈጽሞ አለመረጋጋታችወን ነው.
Mr. Melkamu,
I don’t understand why you are writing another article. Are you insane? What is going on with these woyane bandas? The author wrote everything to the point. Why you are babbling the same word again and again? I’m tired of you. Every body knows you well what you’re doing and what you’re planning to do. Don’t try to confuse us. We had enough for the last 20 years. You are ticks sucking the blood of poor Ethiopian people. Get off our shoulder.
Down with Meles and his puppets!
መልካሙ ተብየው
የወያነ ውሻ ቢጮህ ቢጮህ አይደክመውም: አሁን ደህና የጻፈውን ሰው ልታርመው የምትፈልገው ቆርቆሮ ራስ ስለሆንክ አይደለም: በል አርፈህ ተቀመጥ መጥፊያችሁ ደርስዋል::
መልካሙ ጥሩ ትንታኔ ነው የሶሪያን ጉዳይ በተመለከት ግን ትንሽ ለየት ያለ አመለካከት አለኝ ማለት የሶሪያው መሪ ተቀይሮ ወደ ሕዝባዊ ምርጫ ሶሪያ ብታመራ ስልጣኑን የሚይዙት አክሪሪ እስላሞች ሊሆኑ ይችላሉ ይሄ ሆነ ማለት ደግሞ ሶሪያ በስሪየል የተያዘባቸውን የጆላን ተራራ ጥያቄ ማንሳታቸው አይቀርም ከህዝቦላ እና ከሃማስ ጋር በመሆን የስራየልን ጉዳይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ሊጥለው ይችላላ እንደምታውቀው የአረቦች አቢውት ያመጣው ለውጥ ምእራባዉያን እንደሚመኙት አይደለም አቢወት በተከናወነባቸው የአረብ ሃገራት ቡሙሉ ስልጣኑን የጨበጡት አክራሪዎች ናቸው::
እና በትክክል በሻር አል አስድን መጣል ቢፈልጉ እስካሁን ጨርስዉት ነበር ለነግሩ ሰውየው ያለው አልሞት ባይ ተጋዳይ ሆኖ ነው እንጅ ከስልስልጣኑ መወገዱ የጊዜ ጉዳይ ነው:: ከሩቅም ይሁን ከቅርብ አለም ሁሉ የሚታመሰው ለ እስራየል ሲባል መሆኑን በትክክል መረዳት ይኖርብናል::
ለይነጋል በላቸው(አ.አ)
ይቅርታ ፅሁፌ በተለመደው አካሄድ የለሰለ እንዳልሆነና ትንሽ የሚጎረብጥ እንደሆነ ለመረዳት ችያለሁኝ፡፡ስለዚህም አንተን በዚህ መንገድ የሚሰማህ ሆኖ ካስቀየመህ ግን ይቅርታ እጠይቃለሁኝ፡፡ ነገር ግን ቀስ እያለ በለሰለ ቃላት እያዋዛ ሀሰት ከሚነዛ ፅሁፍ ይልቅ እየመረረም ቢሆን ከረር ብሎ እውነት የሚናገር ፅሁፍ በእኔ በኩል የተመረጠ ስለሆነ ነው፡፡ይህ የእኔ የአፃፃፍ ባህሪ ስለሆነ ነው፡፡
ከአጠቃላዩ ፅሁፍ ውስጥ የእኛን ሀገር ጉዳይ የሚመለከተውን ግማሽ እውነት ያልኩት ስለመለስ/ወያኔ የተፃፈውን ሁላችንም እየኖርንበት ያለ የምናውቀውና የራሳችን ጉዳይ ስለሆነ በዚህ ላይ የተፃፈውን አልተቃወምኩኝም፡፡የፅሁፉ ግማሽ ሀሰት(በቃላት ብዛት አይደለም) ያልኩት ግን ከዚህ ጋር በተያያዘ ስለ አረብ ሀገራት አብዮት የሚፃፈውን በሚመለከት ነው፡፡ይህንንም ያልኩበት ምክንያት እያየነው ያለው የአረብ ሀገራት አብዮትም እንበለው ነውጥ ዝምብሎ እኛ ከምናስበው የምርጫ ዲሞክራሲም ይሁን የአምባገነንነት መስፈርት በተጨማሪ ከበስተጀርባ ብዙ አለም አቀፍ ውስብስብ ነገር አለው ስለዚህም ዝም ብለን አምባገነን እያልን ነገሮችን ሁሉ በአንድ ቅርጫት ውስጥ እንደተመቸን አናስቀምጥ ስፋ አድርገን እንየው ነው ያልኩት፡፡ስለዚህም በዚህ ላይ እውቀትና መረጃ ያለው ሰው ካለ የሚያውቀውንና የሚሰማውን አስተያየት ልክ እንደ ዋጋው ቁጥር-11 አይነት በስርዓት መስጠትና መከራከር ይችላል እንጂ ሌሎች እንዳሉት አይነት የማይሆን ተራ ስድብ መሳደብ ብልግና ነው፡፡
ከዚያ ውጪ ግን ዝም ብሎ እንደ በቀቀን ተመሳሳይ መዝሙር እየዘመሩ አምባገነን እያሉ ማውራት ያን ያህል አዲስ ነገር አይደለም፡፡አምባገነን ስርዓቶች ለምን ይፈጠራሉ?ሁሉም አምባገነን ስርዓቶች አንድ አይነት ናቸዎይ?አምባገነን ስርዓቶች እንዲፈጠሩም ሆነ እንዳይፈጠሩ የሀገሩ ህዝብና የውጪው አለም ያለው አሉታዊና አዎንታዊ አስተዋፅኦ ምንድን ነው? ወዘተ አይነት ብዙ ሊጠየቁና ሊመረመሩ የሚገባቸው መሰረታዊ ወሳኝ ጥያቄዎች አሉ፡፡አንድ ወቅት የተከበሩ ቡልቻ ደመቅሳ እንዳሉት ገና እርግጠኛ ያልሆንኩበትን ቪላ ቤት በተስፋ እሰራለሁኝ ብዬ ያለኝን የሳር ጎጆ ቤቴን ቅድሚያ አፍርሼ አሁን የገጥመኝ ነገር አውላላ ሜዳ ላይ ሆኜ በዝናብና በፀሃይ መሰቃየት ነው እንዳሉት አይነትና በሬ ሆይ በሬ ሆይ ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ አይነት ከፊታችን ያለውን ስልጣን ላይ ያለውን አምባገነን አገዛዝ እናስወግዳለን ተብሎ በጥድፊያ መፍገምገም በስተመጨረሻ ሀገርን ለባእዳን ተስፋፊዎች ዘመናዊ የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ቁጥጥር ስር ማዋልና ሀገርንም መበታትን ሊከሰት እንደሚችል ብዙዎቻችን የተረዳን አይመሰልንም፡፡ትናንት የደርግን ሃጢያት ስናራግብ የነበርን ምሁራንም የሚመጣው ምን እንደሆነ እርግጠኛ ሳንሆን እነሆ ዛሬ በዘመነ መለስ/ወያኔ እንዲሁም ጎረቤታችን ኢሳያስ/ሻእብያ የገጠመንም ይህ አይነት የሳር ቤት ጎጆውና የቪላው አይነት ነገር ነው፡፡ከዚህ በመነጨም ስለ ሊቢያ ሶሪያና ሌሎች አረብ ሀገራት አብዮት ስናወራ ዝም ብሎ በሀገር ውስጥ ባለው ሁኔታ ላይ ብቻ በሚያቀነቅን የአምባገነንትና የዲሞክራሲ አጀንዳ ላይ ብቻ የሚሽከረከር አይለም፡፡ከሌሎች ብዙ አለም አቀፍ ውስብስብ ነገሮች ጋር የተያያዘ ነው፡፡መለስ በእኛ ላይ እያደረሰ ያለው ግፍ እነ ጋዳፊ ሙባረክ ባሽር አልአሳድ ቤናሌና ሌሎች አገዛዞች በህዝባቸው ላይ አደረሱ ከተባለው ግፍና በደል እጅግ የበዛ ይሆን እንደሆነ እንጂ ያነሰ አይደለም፡፡ታዲያ ምእራባውያን ለምን መለስን አያስወግዱትም?እንዲያውም ጭራሽ እርዳታቸውን እያጠናከሩ አይደለም እንዴ?ይህንን እያነሳሁኝ ያለሁት ብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን ፀሃፍት የምእራብ መንግስታትና ወዳጅ ሌሎች አጋር ሀገራት በተቆጣጠሩት Mainstream ሚዲያዎች የሚነዙትን ፕሮፖጋንዎች ብቻ እየሰሙና እያመኑ ነው በዚህ ላይ ተመርኩዘው አስተያየት የሚሰጡት፡፡አልጀዚራ ጋዳፊ ወይንም ባሽር አልአሳድ ህዝቡን እንደ ጭራቅ ጨረሰው በላው ብሎ ካስተላለፈ ይህንን ፍፁም እውነት ነው ብለን አምነን መልሰን እናራግባለን፡፡ሰላማዊ ሰልፍና ሰላማዊ ተቃውሞ ነው የተባለው እንቅስቃሴ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተቀጣጥሎ የለየለት ከባድ መሳሪያ የሚጠቀም የትጥቅ ትግል ውስጥ ሲገባ ቢያንስ ይህ እነዴት ሊሆን ይችላል ብለን የራሳችንን Commonsense and Common wisdom መጠቀም አለብን፡፡እንደዚሁም ከአንድ አምባገነን ስርዓት አንድ ሀገር ወዲያውኑ ከመቅፅበት በተአምር ዲሞክራሲያዊ ሀገር እንደምትሆን አይነት የቀን ቅዠት ውስጥ ሁሉ ያለን አለን፡፡በአንድ ሀገር ውስጥ ለሚፈጠረው ዲሞክራሲያዊም ይሁን አምባገን አገዛዝ ዋናው ወሳኝ ነገር የዚህ ሀገር ህዝብ የቆየ ስነ-ልቦና ባህል ታሪክ ሃይማኖት የኢኮኖሚ አወቃቀር ስልጣኔ ወዘተ ሁሉ ዋና ተቀዳሚ አስተዋፅኦ አለው፡፡ዝም ብሎ በተአምር ከሰማይ ዱብ እዳ የሆነ ዲሞክራሲያዊም ይሁን አምባገን አገዛዝ ድንገት አይፈጠርም፡፡አንድ ህዝብ ጭቆና ሲበዛበት ብቻ ድንገት ተነስቶ በስሜት ግፊት ስላመፀና ነውጥ ስላካሄደ ብቻም እንደዚሁ ዲሞክራሲ አይመጣም፡፡ስለዚህም አሁን በሶሪያ ያለውም ነገር ከዲሞክራሲና ከአምባገነንት ባሻገር ለራሷ ለሶሪያና ህዝቦቿ ህልውና ጭምር አደገኛ ነገር ነው፡፡ሶሪያ የእስራኤል ዋና ባለንጣ ሀገር ናት በተቃራኒው ደግሞ የኢራንና የራሽያ ወዳጅ ናት፡፡ኢራን ደግሞ የራሽያና የቻይና ዋና ስትራቴጂካዊ አጋር ናት፡፡ዛሬ በሶሪያ ላይ የተቃጣው አደጋ ነገ ኢራንን በሂደት ለማጥቃትና ስልጣን ላይ ያለውን ለምእራባውያን የማይመች አገዛዝ ለማስወገድና በምትኩ በሌላ ተስማሚ አገዛዝ ለመተካት ጭምር የታቀደ የምእራባውያን ስልት ነው፡፡ከኢራን በኋላ ቀጣይ ማነው? ስለዚህም አጠቃላይ ሁኔታው እጅግ ውስብሰብ የሆነ ነገር ነው፡፡አሁን ያለው አጠቃለዩ የአረቡ አለም አብዮት እንበለው ነውጥ ፍፃሜ ገና በቅጡ ጥርት ብሎ የለየት ነገር አይደለም፡፡አጠቃላዩ እንቅስቃሴ ግን የምእራቡ አለምና እስራኤል በአንድ በኩል በሌላ በኩል ደግሞ የራሽያ የቻይናና መሰል ሃይሎች በአንድነት ያለ የሃይል ፍጥጫና የበላይነት ግብግብ ጭምር ነው፡፡እነዚህ በተለያየ ፊና የተሰለፉ ሃያላን ሀገራት የየራሳቸውን ወዳጅ አገዛዝ በየታዳጊው ሀገራት ውስጥ ማስቀመጥ ወይንም ያለውን ማስቀጠል ወዳጅ ያልሆነውን ደግሞ ማስወገድና በምትኩ በሌላ ወዳጅ በሆነ መተካት ይፈልጋሉ፡፡በአረቡ አለም ያለውም አብዮት ወይንም ነውጥ በዚህ ቅኝት ጭምር የሚመራ ነው፡፡የእኛም ሀገር ሁኔታ በዚህ ቅኝትና ማእቀፍ ውስጥ ጭምር ያለ ነው፡፡ከዚያ ውጪ የአሜሪካ ወይንም የአንግሊዝ መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ ሰብዓዊ መብት ተከበረ አልተከበረ ዲሞክራሲ ሰፈነ አልሰፈነ አምባገነን ገዛ አልገዛ ያን ያህል የሚያስጨንቀው ነገር ምንድን ነው?ሁሉም የሚጮኸው ለራሱ ፍላጎትና ትቅም ሲል እንጂ ለህዝቡ አስቦ አይደለም፡፡ስለዚህም እየተፃፈ ያለው ነገር ይህንን ግምት ውስጥ ያስገባ አይደለም ነው የእኔ አስተያየት፡፡ባሽር አልአሳድ ወይንም ጋዳፊ አምባገነን ናቸው፡፡ትክክል እና ግን ምን ይሁን?ይህንን አምባገነንነት ለማወቅ የሮኬት ሳይንቲስት ወይንም የግድ የፖለቲካ ሳይንስ ማጥናት አያስፈልግም፡፡ነገር ግን እነዚህን አገዛዞች ከስልጣን ለማስወገድ በባእዳን ሃይሎችና ቅጥረኛ ተዋጊዎች ጭምር እየተረዱ ያሉት ተቃዋሚዎች ግን አላማቸውና የሃይል አሰላለፋቸው ምንድን ነው? እነሱስ ምንድን ናቸው?የሚመጣው ስርዓትስ ምን አይነት ነው?በአረቡ አለም ስላው አምባገነንትና አብዮት በኢትዮጵያውያን የሚፃፉት ፅሁፎች ውስጥ እስካሁን እንዳነበብኩት በአንዳቸውም ላይ እነዚህንና መሰል ወሳኝ ጥያቄዎች የሚያነሳም ሆነ የሚመልስ ጭብጥ ያለው ነገር እስካሁን ያን ያህል አላየሁም፡፡ግማሽ ውሸት ግማሽ እውነት ያልኩትም በዚህ የተነሳ ነው፡፡ይህ ያን ያህል ካስቀየመህ ግን የማምንበት ቢሆንም ቅሉ ግን የአገላለፅ ችግር ስለሆነ በድጋሚ ይቅርታ እጠይቃለሁኝ፡፡ከዚያ ውጪ ግን በተናገርኩት ነገር ላይ ምክንያታዊ አስተያየት ብትሰጠኝ ግን ደስ ይለኛል፡፡መለስ ወያኔንም በዋናነት እየተቃወምኩኝ ያለሁት የምእራቡ አለም አይነት የምርጫ ዲሞክራሲ እለቱን እንዲመጣ ብዬ በማሰብና በመፈለግ ሳይሆን መለስ/ወያኔ ዘረኝነቱ ዝርፊያው ቅጥረኝነቱና ከሃዲነቱ አሁን ያለውን ሀገርና ህዝብ ጭምር በሂደት ጭራሽ የሚያዳክም የሚበታትንና የሚያጠፋ አደገኛ ስለሆነ ብቻ ነው፡፡
ከምስጋና ጋር፡፡
**************************************************************
ለዋጋው
ዋጋው የተባልከው የተወሰነው ትክክል ነው ያልከው
በአረቡ አለም ካለው እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ የእስራኤል ጉዳይ ከፍተኛውን ቦታ ከሚይዘው ነገር ውስጥ አንዱ ነው፡፡በአረቡ አለም ባለው አብዮት ውስጥ ምእራባውያን እንደሚፈልጉት አይደለም ያለው ምክንያቱም አብዛኛውን አክራሪዎች ናቸው ስልጣን ላይ የወጡት ላልከው ነገር ይህንን አሁን እርግጠኛ ሆኖ ለመናገር ጊዜው ገና ስለሆነ በጣም ይከብዳል፡፡ነገር ግን በእኔ የእውቀትና የመረጃ ደረጃ እርግጠኛ ሆኜ ለመናገር የምችለው ምእራባውያን መንግስታት ጋዳፊን ባሽር አልአሳድን አንደዚሁም የኢራኑን የቀድሞው እስላማዊ አብዮት ሰንሰለት የፈጠረውን ያሁኑን አገዛዝ ፈፅሞ አይፈልጉትም፡፡ከዚያ ውጪ በግብፅ አሁንም በዋናነት ወሳኝ አመራር እየሰጠ ስልጣን ላይ ያለውና ለምእራባውያን ታማኝ ሃይል የሆነው ወታደራዊ ጁንታው ነው፡፡በሚሊታሪ ጁንታው ውስጥ ያሉት ሃይሎች ከአለም አቀፍ ኩባንያዎች ጋር የተያያዘና በሙስና ላይ ጭምር የተመሰረተ ከፍተኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊ መሰረት ያላቸው ናቸው፡፡አክራሪዎች የሆኑ ስልጣን ላይ እንዲወጡ የሚፈለግበትም አካሄድ እንዳለ ጭምር መረዳት አለብህ፡፡ምክንያቱም በዚያ ሀገር ውስጥ ህብረ ብሄራዊ ስሜት ያለውና ሴኩላር(Secular) አገዛዝ ለብዙሃኑ ህዝብ ፍላጎትና አላማ በሚጠቅም አካሄድ የተረጋጋ አገዛዝ እንዲሆን አይፈለግም፡፡ዋናው ነገር ግን በዚህም በለው በዚያ ስልጣን ላይ የሚወጡት አገዛዞች ከባእዳን ሃይሎች ይልቅ ቅድሚያ ለሀገራቸውና ለህዝባቸው ቀናኢና ታማኝ የሆኑ ቅድሚያ ለሀገራቸውና ለህዝባቸው ህልውና ጥቅም ፍላጎትና አላማ የሚሰሩ እንዲሆኑ አይፈለግም፡፡ይህንን ለመረዳት ደግሞ የግሎባል ካፒታሊዝምን ውስጣዊ አወቃቀርና አሰራር በቅጡ መረዳት ይጠቅማል፡፡በ3ኛው ዓለም ውስጥ ያሉ ማናቸውም አይነት ልሂቃን(ምሁራን ፖለቲከኞች ባለሀብቶች ወዘተ) ለህዝባቸውና ወገናቸው ሳይሆን በዋናነት በገንዘብና ጥቅም ላይ ለተመሰረተው ለግሎባል ካፒታሊዝም ህልውና አለማና ፍላጎት እንዲገዙ ለማድረግ የግድ እነሱን ከህዝቡ መርጦና ነጥሎ ማውጣትና አገዛዝ ላይ ማውጣት ግድ ይላል፡፡በኢትዮጵያም ያለው የወያኔ የዘር ፖለቲካና የአገዛዙ ባህሪ ከዚህ የሚመነጭ ነው፡፡ስለዚህም አገዛዞቹን መለየት የሚቻለው በሂደት በሚሰሩት ተጨባጭ ተግባራዊ ስራ ብቻ እንጂ በሚያወሩት ብቻ ሊሆን አይችልም፡፡ለምሳሌ አከራሪው ስልጣን ላይ ሲወጣ ህዝቡ አንድ አይሆንም ማለት ነው ይህ ሲሆን ያንን አክራሪ የተባለውን በሂደት በስልጣንና በገንዘብ በጥቅም በማለዘብ የዚያችን ሀገር የተፈጥሮ ሀብት እንደፈለጉት ለመመዝበር አመቺ ይሆናል፡፡ብቻ አንድ ሀገር ውስጥ ህዝብና መንግስት ሰምና ወርቅ ሆነው ተስማምተው ተከባብረው ተማምነው አንድ ከሆኑ ምእረባውያን መንግስታት የሚፈልጉትን ጥቅምና አላማ እንደፈለጉት ለማስኬድ ይከብዳቸዋል፡፡ለዚህም ነው ምእረባውያን መንግስታት ለህዝብ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም የቆመውን ሶሻሊዝምንና ከዚህ ጋር የተያያዘውን ሶሻል-ዲሞክራሲ የሚባለውን ነገር አጥብቀው የሚጠሉት፡፡ምእረባውያን መንግስታት ዋናው የሚፈልጉት የዚያን ሀገር የተፈጥሮ ሀብትና ኢኮኖሚውንና ይህንን የተፈጥሮ ሀብትና ኢኮኖሚውን እንደፈለጉት እንዲጠቀሙበት የሚፈቅድና የሚያስጠበቅ ተዛማጅ የፖለቲካ የሚሊታሪና የደህንነት ስርዓት ብቻ ነው ከዚያ ውጪ አምባገነን ገዛ ዲሞክራት ገዛ ጉዳያቸው አይደለም፡፡የባሽር አልአሳድን መውደቅ በሚመለከት በእርግጥ እኔም እንደምገምተው አሳዛኝ ፍፃሜ ይኖረው ይሆናል፡፡ምክንያቱም ምእራባውያን በተባበሩት መንግስታት በኩል በቻይናና ራሽያ ተቃውሞ የተነሳ አልሆን ሲላቸው የኔቶ አባል የሆነችውን ቱርክን ተጠቅመው በኔቶ በኩል ወረራ ማድረጋቸው አይቀርም፡፡የቱርክ አውሮፕላን በሶሪያ ክልል ውስጥ መውደቅን ተከትሎ ይህንን እንደ ጥቃትና እንደ ሰበብ አድርጋ ቱርክ የወታደራዊ እንቅስቃሴ በሶሪያ ጠረፍ እያደረገች ነው፡፡ቱርክ የኔቶ አባል ስለሆነች ደግሞ ኔቶ ይህንን ተከትሎ ጠርነት ውስጥ መግባቱ አይቀርም፡፡ብቻ ሁኔታው ፀሃፊውና መሰሎቹ እያቀረቡ ባሉት የአምባገነንት ጉዳይ ላይ ብቻ የሚያጠነጥን አይደለም፡፡እንግዲህ ይታይህ ጠቅላላውን ስደስቱ የአርብ ገልፍ ሀገራት (ሳኡዲ አረብያ አረብ ኢምረት ካታር ባህሬን ወዘተ) አምባገን ብቻ ሳይሆኑ በሞናርክ ጭምር የሚገዙ የአሜሪካና እንግሊዝ አሻንጉሊት አገዛዞች ናቸው፡፡እንግዲህ ይታይህ እነዚህ የአረብ ሀገራት ጭምር ናቸው የባሽር አልአሳድ መንግስት ዲሞክራት ስላልሆነና አምባገነን ስለሆነ ስልጣኑን ይልቀቅ አለበለዚያ ከአረብ ሊግ ይውጣ ብለው ያሰናበቱትና ዛሬ በተዘዋዋሪ ይህንን አገዛዝ ለመገልበጥ ጭምር ጦርና ሽምቅ ተዋጊ ሰራዊት በስውር እያዘመቱ ያሉት፡፡ስለዚህም ይህ እየታወቀ የተለመደው ጥራዝ-ነጠቅ ወሬ በፀሃፋዎቻችን ሲራገብ ዝም ማለት ተገቢ አይደለም፡፡እውነትን መነጋገር ፈጣሪም የሚወደው ነገር ነው፡፡ከላይ ያሉት አስተያየት ሰጪዎች ደግሞ የማይሆን ስድብ የሚናገሩት ይህ እውነት ለምን ተነገረ ብለው ነው፡፡እና ይህ ተደጋጋሚ ስህተት ሲሰራ ዝም መባል አለበትን?ገና ለገና የምርጫ ዲሞክራሲ እለቱን ተግባራዊ ካልሆነ እንደ ባሽርና ጋዳፊ አይነት አምባገነን የተባሉት አገዛዞች በውጪ ባእዳን ወረራም ጭምር ቢሆን ስልጣን እየለቀቁ ታዳጊው ሀገር እለቱን መታመስና የማያባራ ቀውስ መፈጠር አለበት ብሎ የሚያስብ ሰው የፖለቲካ ሀሁ የሚያውቅ ነው ለማለት በራሱ የሚከብድ ነገር ነው፡፡የእኛ የመለስ አገዛዝ ከሌላው ሀገር አምባገነን አገዛዝ ጋር ሁሉ ተመሳሳይ ነው ብሎ በማሰብ ሁሉንም አይነት አገዛዝ በአንድ ቅርጫት ውስጥ ለማስቀመጥ መፈልግም ተገቢ አይደለም፡፡ብዙዎቻችን እኮ ዲሞክራሲ ለታዳጊው አለም ላሉ ህዝቦች ከምእረባውያን በክሩዝ ሚሳይል ጭምር ተጭኖ መሬታችን ላይ እንዲዘራ የምንፈልግ አለን፡፡የአበራሽን ጠባሳ ያየ በእሳት አይጫወትም ነውና ነገሩ ሶሪያውያን ከሊቢያውያን ትልቅ ትምህርት እንዳገኙ መማር አለብን፡፡ሊቢያውያን ከጋዳፊ ውደቀት በኋላ ከአምባገነንት ለስሜታቸው በሚመች መንገድ ለጊዜው ቢላቀቁም ቅሉ ግን ከዚህ በኋላ በጋዳፊ ዘመን ያለው አይነት ሰላም መረጋጋት ልማትና የተንደላቀቀ ኑሮና ሀብትንም ሆነ የተመኙትንና የተወራውን ዲሞክራሲ በቀጣይነት ያገኛሉ ማለት ግን ዘበት ነው፡፡በተመሳሳይ መንገድ በሶሪያም ከዚህ ቀውስ በኋላ ምን እንደሚከተል ለማወቅ ከባድ ነገር ነው፡፡ይህንን ስል ግን የእኛን የመለስ/ወያኔን ቅጥረኛ ዘረኛ ዘራፊና አረመኔ አገዛዝ እንዲቀጥል በማሰብ አይደለም፡፡የእኛ አይነት አገዛዝ በአለም ላይ አሁን የለም፡፡ቢያንስ ሌሎቹ አገዛዞች የጋዛ ህዝባቸውን በመለስ/ወያኔ አይነት አይጠሉትም፡፡
መለስ ወያኔንም በዋናነት እየተቃወምኩኝ ያለሁት የምእራቡ አለም አይነት የምርጫ ዲሞክራሲ እለቱን እንዲመጣ ብዬ በማሰብና በመፈለግ ሳይሆን መለስ/ወያኔ ዘረኝነቱ ዝርፊያው ቅጥረኝነቱና ከሃዲነቱ አሁን ያለውን ሀገርና ህዝብ ጭምር በሂደት የሚያዳክም የሚበታትንና የሚያጠፋ አደገኛ ስለሆነ ብቻ ነው፡፡
ከምስጋና ጋር፡፡
what is melkamu blabbing?can’t he write his own article and get it posted? and what is the tenet of all this confusing and impertinent ideas? my god, it is so long to finish it and it is far off the agenda the writer has tried to dwell on. plz melkamu know what you want first, after identifying what you want, then learn how to express it before throwing your hodgepodge on people. what a confused person u must be!
ምን ነካችሁ? ወያኔዎች ያበዱትኮ እዚያው እደደቢት መሆኑን ከድተው ከወጡት፡ ወይም በእብደት ጠባቸው ተባረው ከወጡትና አዕምርዋቸው የተመለሰላቸውን ቃለመጠይቅ አዳምጡ፡ የሁሉም ዩቲዩብ ውስጥ አለ። እንዴ! 21 ዓመታት በምንሊክ ቤተመንግሥት የተቀመጡት፡ መች በወያኔ ታጣቂ ተቀመጡ? በሆዳም የተቀረው ብሔረሰብ ተወላጆች እንጂ! ባበደው ጭንቅላታቸው በስደትም ካለው በሃገር ቤትም ካለው የሆዳሞች ጥርቃሞ አበዱበት ተንፈላሰሱበት፡ በላብ አደሩ፤ በገበሬው ገንዘብ። ሆዳሞች ለወያኔዎች እጃቸውንና ሆዳቸውን ባያስረክቡ ኖሮ፡ እንኳንስ 21 ዓመታት የግፍ አገዛዝ ሊቀመጡ ቀርቶ 21 ቀናት እንኳ ሊቀመጡ የማይችሉ እብደት አመጣሽ አረመኔዎች ናቸው። ይልቁንስ ህዝበ ኢትዮጵያ ነቃ በሉ። ሆዳሙ በውጭ ሃገርም ይሁን በሃገር ቤት ጭንቅላቱ እንዲመለስ ከተደረገ፡ ወያኔ አብቅቶለታል። መከላክያ ሠራዊቱ ውስጥ ያለው የተቀረው ብሔረሰብ ተወላጅ ነቃ ነቃ እያለ ነውና፡ ሆዳሙን አጋልጦ ማሳፈር፡ በግልጽ መንገር፡ ማለትም የወያኔ አሽከር ሆነው ሃገር እያጠፉ ስለመሆኑ መናገርና ወደኢትዮጵያዊነት መመለስ ወይም ከዕብደት ወደጤንነት መመለስ የኢትዮጵያውያኑ ድርሻ ነው።
ዋጋው ሶርያ ጉዳይ እኛን እሚያሳስብ ሊሆን አይገባም እስራኤል ያላትን የጎረቤቶቿን በመቻቻል መኖር ይገባታል እላለሁ በሰፊው ለዚህ ጉዳይ ለማወቅ ከፈለግክ መራባውያን በሶርያ ላይ የኃይል እርምጃ ለምን አልወሰዱም የሚለውን ጥያቄ ብታነሳ በጣም ጥልቅ የሆነ ሚስጥር የያዘ ነው ይኸውም አሕባሽ የሚባል እስላማዊ እምነት ቤስራኤል እና በምእራባውያን የሚደገፍ Islamic charities እየተባል የሚጠራ sheikh Abdullah al harari al habash የተባለ እምነት በልባነን ተመስርቶ በብዙ ሚሎን የሚመዘን ያለው ድርጅት በሀገራችንን ገብቶ ብጥብጥ ያስነሳ የሙሳእድ ተወናይ የእስላም እምነትን ለማዳከም የተፈጠረ ደርጅት ሲሆን በሰርያ ስልጣን የተቀመጠው የዚህ እምነት ተከታይና አማኝ ባሽር አሳድ ቤተሰብ በመሆኑ እስራኤልን የሚደግፍ ለመሆኑ ማወቅ ያስፈልጋል በሌላበኩል የአክዋን ሙስሊም ማለት የስላም ወንድማማቾች ማለት ሲሆን በሕዝብ ተመርጦ ስልጣን መያዝ አክራሪነት ስላልሆነ ለምንሰጠው አስተያየቶች በማስረጃ የተደገፊ ዐንታ የያዙ እንጂ በምእራባውያን ለራሳቸው ፍልጎትና ተገዥ ያልሆነላቸውን የሚሰጡት ስም መጠመድ ተፈላጊነት የለውም የየራሳችንን ሕልኒያዊ ፍርድ እንስጥ: ይህን ስል እስላም በመሆኔ ሳይሆን እኔም አክራሪ ተውሃዶ ኦርቶዶክስ ነኝ ይህንንስ ምን ልትሉት ነው? ህይማኖት የግል ነው ሀገር ግን የጋራ ነች : ሁሉም በእምነቱ መጽናትና ያመነበትን መከተል ነጻነቱ በመሆኑ የተውሶ ውንጀላ ከማድረግ እንቆጠብ
መልካሙ።
ዋጋው።
አንድነት።
ማራማዊት።
አንድነት ብርሃኔ።
. . .
እንደምን ሰነበትክ? የኔ ጅል!!! ሥራ በዝቶብህ ሰነበትክ።እኔን!!!
እኛ ‘የተውሶ ውንጀላ ከማድረግ እንቆጠብ ‘ ባልከው ተስማምተናል። ሳንዋስ እንወነጅላችኋለን፤ አይዞን የኔ እንደወረደ።
አዘንኩልህ ፤ የተሰጠህ ሥራ ከባድ ስለሆነ። ለአለቆችህ ንገራቸውና ሌላ ጅል ይመድቡ፤ አንተ አልሆነልህም።
ጂኒ ነኝ።
Dear Melkamu !
I fully agree with your analysis but i disagree with your insult. You don´t have to insult the writer Tarekegn Muche or others to make yourself perfect. Please, Melkamu ! Next time just write your comment without your complex. Your complex shadows your effort.