የንዱአለም አራጌ የዛሬው የፍ/ቤት ውሎ የመጨረሻ ንግግር

June 27th, 2012 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

ያሳለፍነው ግማሽ ምዕተ ዓመት የኢትዮጵያ ህዝብ ለሰብአዊ ክብሩና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የታገለበት ዘመን ነው፡፡ ይሁን እንጂ የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቹ ባለቤት ለመሆን እስካሁን አልታደለም፡፡ እኔም በተፈጠርኩበት በዚህ ዘመን ለራሴ፣ ለልጆቼና ለኢትዮጵያውያን ሁሉ ዴሞክራሲና ነፃነት እንደሚገባን በማመን አቅሜ በፈቀደው መጠን ታግያለሁ፡፡ ይኼን በማድረጌ በማንም ላይ በክፋት አልተነሳሁም፤ ይኼን በማድረጌ ህግ ጥሼ አላውቅም፤ ይኼን በማድረጌ በደሃዋ ሃገሬ ጥቅም ላይ አልተነሳሁም፤ ይሄን በማድረጌ ፈጣሪዬን፣ የኢትዮጵያን ህዝብም ሆነ ህሊናዬን የሚያሳዝን አንዳች ነገር ፈፅሜያለሁ ብዬ አላምንም፡፡ ፍፁም ሰላም ይሰማኛል፡፡ እኔን እዚህ ያቆመኝ የነፃነት ናፍቆት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶችም ፍትህን ለምኜ ስነፈግ ይኼ የመጀርያዬ አይደለም፡፡ ከሳሾቼ እንድጠጣው የሚፈልጉትን የግፍ ፅዋ በፀጋ ከመጠጣት ውጪ ባልፈረፀምኩት ወንጀል ማቅለያ የመጠየቅን አማራጭ ህሊናዬ ስላልተወልኝ አዝናለሁ፡፡

  1. korojo-Ethiopia
    | #1

    The struggle will continue and the Ethiopian people at last shall prevail ! You all will be remeberd in the golden chapter of our history. Milions of Andualems will take your banner of freedom and democracy high up . Berta Yager lij Ye Ethiopia Deha Hizeb Amlak Kante Gar Yehun!!

  2. Anonymous
    | #2

    የ እመዬ ኢትዮጵያ አምላክ ይታደገክ

  3. ዋሸራው
    | #3

    አሳዛኝ ነው! ለነገሩማ ከዚህ ፍርድ ቤት ሌላ ነገር መጠበቃችን ያስገርመኛል:: ይህ ሥርዓት ካደረሳቸው ብርቱ ጥፋቶች አንዱ ፍርድ ቤቶችን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሩ ሥር አድርጎ የፖለቲካ ዓላማዎቹ ማስፈጸሚያ ማድረጉ ነው:: ከዚህ ጉዳት በተቻለ ፍጥነት የምናገግምበትን መንገድ ማፈላለግ ሥርዓቱን ለመለወጥ ለሚታገሉት ኃይሎች አንዱና ዋነኛው ተግባር ሆኖ መታየት ያለበት ይመስለኛል:: በዚህ ሁሉ መሃል ደግሞ የነአንዱዓለም ቤተሰቦች ችግር ላይ እንዳይወድቁ የሚቻለንን ሁሉ ማድረግ ይጠበቅብናል::

  4. አንበሳ
    | #4

    እጂግ የሚያሳዝን የሚያንገበግብ ነው አገር ያለዳኛ ያለመሪ እንዲያው ሰው ያልሰራውን ሰራ እየተባለ አቤት የሚንልበት ማጣት በ21 ክፋለ ዘመን እጂግ የሚያስቆጭ የሚያንገበግብ ነው እኔ በእውነት የወያኔን ነገር እረጎበዝ ሰውቻችን ጨረሰ እረባካችሁ እንነሳ

  5. መረተ ወርቅ
    | #5

    Injustice Hurts!!Job said: I keep crying for help.but there is no juutice” to day many are crying out for justice,why? The very soul of the wiced one has craved what is bad,his fellow will beshown no favor in his eyes:but The house of wicked people will be annihilated”,but the tent of the upright ones will flourish,!!ስለዚህ የወንድሞቼ መከራ በረዘመ ቁጥር ጭንቀቴ ቢበዛም ለፍትህና ለነጻነት በደል ይቅር ግፍ ይብቃ በማለት መከራ ቢቀበሉም ምን ግዜም እውነት አጠገባቸው ቆማ ትፈርዳለች!!እውነተኛነት አንድን ሕዝብ ታላቅ ያደርገዋል!አመጸኞች ግን በክፋ ስራቸው ይወድቃሉ ደጎች ግን በታማኝነታቸው ይጠበቃሉ!!ውርደት ታሬካቸው አይሆንም!!አመጸኞችም መጨራሻቸው ጥፋት ነው!ታሬካቸውም አሳፋሬ ነው,ለአውነት ለሚንገላቱ ወገኖቼ ብርታቱን ይስጣችሁ!!የምትካፍሉት መሰዋእትነት ቀላል አይደለም ግን የድሉ ባለቤት ናችሁ እግዚአብሔር ጥላ ከለላ ሆኖ ቀንበራችሁን እንዲፋታው የሁል ግዜ ጸሎቴ ነው!!!እስረኞች ይፈቱ በቃ!!!!!!

  6. Mezemer
    | #6

    አንዱ ዓለም አንተስ የራስህን ተወጣህ እኔ ለራሴ አፈርኩ !!

  7. ሙሉ
    | #7

    ይች የኣልታደለች አገር ከነመንግስቱ ና ገርማሚ ንዋይ ጀምራ ከግማሽ ምእተ ዓመት በላይ የመከራ ጉዞ እየገፋች ነዉ. የወያኒን ግፍን ግን የቻልነዉ እኛ እትዮጵያኖች ስለሆን ነዉ. በዚች ዓለም ላይ ያለ የማንም አገር ዚጋ ይህን ወያኒ የሚያወርድብንን ዓይነት ግፍ የሚሸከም ትክሻ ያለዉ ከኛ በስተቀር ክቶ ሊገኝ አይችልም. የግፉ ጽዋ ሞልቶ እየፈሰሰ ስለ መሆኑ በዉስጡ እየኖርንበት ስለሆነ ነጋሪ አያስፈልግም.እኛ ትንሽም እንኩዋ ሰለአልተፍጨረጨን እግዚሩም አልረዳን አለ. ፈጣሪ ምን ያድርገን እንድ መሆን አቅቶን ስናስቸግረዉ. እኛዉ ሳንበረታ እንዲት አድርጎ ይርዳን? መተባበር አቅቶ–ሆ!! ብለን መነሳት አቅቶን ምንም ሕዝባዊ መሰረት የሊለዉ ወያኒ በሳት ጅራፍ ይገርፈናል. በየቦታዉ የድርጅት መፈልፈል እስካሁን ምን ጠቀመን? የአበበ ገላዉን ያክል እንኩዋን ወያኒን አንገት ያስደፋ ጠንካራ ድርጅት የለም. ወያኒ ከተፈጠረ አንስቶ የተቀፈቀፊት ድርጅቶች አንክዋ በአንድ ቆመዉ ይህን ተከፍቶ ቁዋፍ ላይ ያለ ህዝብ መርቶ ለትግልና ለድል የሚያበቃዉ ጠፍቶ እንጂ ወያኒማ የሞተ በ97 ዓ,ም ነዉ- እንደ አንዱአለም የመሳሰሉ እዉነተኛና ሀቀኛ ጀግና ልጆች አልፎ አልፎ ብቅ ሲሉ እንቅ ማድረጉን ደግሞ ወያኒ ተክኖበታል-ግን አንዱአለም አንድ ቀን የነጻነት ጸሀይ ትወጣለች. ወያኒእና መለስ እንዲህ እንዳላገጡ አይቀሩም. ሞት ለማንም አይቀርም ልዩነቱ የመለስ ልጆች በዓለምም ሆነ በኢትዮጵያ አንገታቸዉን ሰብረዉ ሲሂዱ የአንተ ልጆች በአንተ በአባታቸዉ ታሪክ አንገታቸዉን ቀና አድርገዉ በኩራት ይሂእዳሉ. የኢትዮጵያ ሕዝብም ለዘልአለም ለነጻነቱ ስትል የተቀበልከዉን ግፍና መከራ ሲዘክር ይኖራል.ኢትዮጵያም አንተን የመሰለ ጀግና-ሀቀና–ትሁት-ሰዉ መሀጸኑዋ በማፍራቱ ስትኮራብህ ትኖራለች.
    ክብር ለአንዱዋለም!!!
    ክብር ለእስክንድር!!!
    ክብር ለርእዮት!!!
    ክበር ለናትናኢል!!
    ክብር ለሁሉም የህሊና እስረኞች!!
    ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!

  8. SAD
    | #8

    ከየካቲት 66 አብዮት ጋር በተከሰተው የአገሪቷ ፖለቲካ
    ውስጥ የተደረገው መስተጋብር ጤነኛ አይደለም::
    ይህ ፖለቲካዊ መስተጋብር ጤንነቱ የተቃወሰው
    ደም የሚሸታቸው አብዮታዊ ፖለቲከኞች ከሚገባው
    በላይ ስለበዙ ነው:: ዲሞክራሲ የሐሳብ ገበያ ነው
    የሚለውን አስተምህሮ እየገረመሙ ለመቻቻል
    ፖለቲካ ጀርባቸውን ያዞሩ እነዚህ ወገኖቻችን
    ናቸው:: ለተለየ አስተሳሰብና አመለካከት አክብሮት
    በመስጠት ሥልጡን የፖለቲካ ዓላማን ከማራመድ
    ይልቅ በፍረጃ ፖለቲካ ማኅበረሰባችንን በተለያዩ
    ጽንፎች ውስጥ እንዲቀረቀር እያደረጉ ያሉት
    እነዚህ ወገኖች መሆናቸውን ነጋሪ አያስፈልግም::
    ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የጥላቻ ፍረጃቸው ወሰኑን
    አልፎ ኢትዮጵያዊነታችንን እስክንጠራጠር ድረስ
    ነውረኛ ደረጃ ላይ ተደርሷል:: ይህ የእኛ ትውልድ
    ከእነዚህ የሚማረው በጎ ነገር የለም:: የትግላቸው
    መነሻ ግብ ሥልጣን ብቻ በመሆኑ ሽኩቻው
    የደራው ሥልጣን ላይ ብቻ ነው:: እነሱ ያነገቡለትን
    ዓላማ ከዳር ለማድረስ የወደቁት ጓዶቻቸው አፅም
    እንደሚፋረዳቸው እንኳን ረስተውታል:: እነዚህ
    ለዚህ ትውልድ ምን ይረባሉ?

  9. atto
    | #9

    We will intensify the struggle until FREEDOM, DEMOCRACY AND JUSTICE prevail in our land. The heroes of our struggle Andualiem Aragie, Eskinder Nega and all the other political prisoners remain the beacons of hope for our people. The woyane can’t kill the aspirations of the people for freedom.

  10. አንድነት ብርሃኔ
    | #10

    ትግል ቀጣይና መራራ በመሆኑ እንዳንተ ያሉ የቁርጥ ልጆች የግፍ ጽዋአ ተጎንጭዎችን የሚተፉበት ቅንና ሰዓት እሩቅ አይደለም ነገርግን ነጻነትን ለመጎናጸፍ የጥቂቶች ትግል ሳይሆን የሁሉም በመሆኑ እያንዳንዳችን የተጫነበችሁን የግፍ ድንጋይ ከኛምጋር የተጫነ ሆኖ ከደረታችን ገፍተን ለማወርወር ጥረት ባለማድረጋችን እናንተን ቆራጦች አስቀድመን ለከንቱ ጊዚያዊ ድሎትና ቅንጦት ራሱን ዋርዶ በሚጣልለት ድርጎ የፍትሕን ወንበር ተቀምጦ ፍትህን ሲያቋንሽሽ የነሱ የመከራ ጊዜ ሲመጣ እንድ አቻዎቻቸው እናንተ በቆማችሁት የነጻነት ፍርድ ሳይሆን ተዋራጅነታቸውን በሚያሳይ በፈረዱበት ሲፈረዱ እንድምታዩ የነጻነት ፍለጎታችሁ ተሟልቶ ታዛቢዎች እንደምትሆኑ ተስፋችሁ ምኞታችሁ እንድሚፈጸም ባጭር ጊዜ ከስር እንድምትለቀቁ ያለኛን ጽኑ እምነት ስገልጽ በተጨማሪ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በነአንዷላም በነእስክንድር በነ ናትናኤል በነውብሸት በነዘሪሁን በነ ሪእዮት ብቻ ነጻነትን ከመጠበቅ ነጻነትን ለማግኘት ሁሉም የቦኩሉን ጥረትና ትግል ሲያደርግ በመሆኑ ከገኦረቤቶቻችን በመማር ሞተን እንጂ ሌላው ሞቶልን ነጻነት መተበቅ ባርነት በመሆኑ የታሪክ አዳሾች እንጂ የታሪክ አጥፊዎች ላለመሆን ሁላችንም ማሰብና መገንዘብ ስለሚገባን ዛሬ የታወጀብን ነገ በየቤኤታችን መጥቶ ሚስትህ ያንተአይደለችም የሚል ሕግ ለማውጣት የማይመለስ ጣምራ ገዥ ይሄው የማገናኛ መስመሮች መቆጣጠር ያለፈቃድ መናገርም እንድምትከለከል በትዝብት መመልከት ሳይሆን መብትህን ለማስከበር የምትችለው ድምጽህን ስታሰማ እንጂ በዝምታ ሰሚ እንድሌለህ ማወቅ ይገባሀል
    ድል ለነጻነት የቆሙ ኃይሎች
    ድል የሕሊና እስረኞች ለጭቁን ሕዝቦች
    ውድቀት ለእምባገነኖች

  11. Shiferaw Tekewashu
    | #11

    Wendu Alem, you did your part it is upto the rest of us to stand for our right or live as slave forever. UDJP leadership has to call its supporters to denounce this verdict. If UDJP is working behidn our back with the coward elderly group to kiss Meles Zenawi stinky shoes for forgivness the Ethiopian people will never forgive you for that. Let the war begins on the streets of Addis Ababa Today !!!! Death for Woyane !!!!

  12. ዳኒ
    | #12

    ዋው!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!! ሞት ላይቀር . መቼም አቶ አንዱአለም አንድ ነገር ቢገጥመው ጥሩ ነገር አይፈጠርም መቼም እኔ ዳኛወን ብሆን ጥንቅር ብሎ ይቅር እንዲህ ነጩን ቀይ አልልም ዳኝነት ምንድነው???????????? የኛ ዳኛ በፈረድክበት ፍርድ ይፈረድብሃል. ደስ የሚል ንግግር ነው . ወያኔዎች እንደልማዳቸው እንዚህን እውቅ ሰዎች ይቀርታ እንዲጠይቁ ብዙ ጥሯል በህዝብ መቀለዱ ማቆም እንዳለበት አቶ አንዱዓለም ጥሩ ምሳሌ ናቸው. ከጀግናም ጀግና!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!! አይዟችው እግዚሃቤር አለ ንጽህ ደም በከንቱ አይቀርም. አቶ አንዱዓለም እስካሁን የደረሰባቸውን መከራ ጥርሳችወን ነክሰው ችለዋል ወያኔ በአማራነታችወም ጭምር ነው እንጂ ምንም ጥፋት እንዳልሰሩ ልቡ ያውቀዋል የመጨረሻ ወራዳ እና ቆሻሾች መሆናቸው ለሁሉም ግልጽ እይሆነ ነው. መውደቅያ ሲደርስ እንዲህ ነው እንሱም በሰፈሩት ቁና ደህና አረገው ይሰፍራሉ.

  13. HAYALE SEW
    | #13

    There is time for everything
    A Time to Cry, A time to Rejoyce.When its all said and done History will rmember these Brave Men and Women for their sacrifice

    God Bless THESE ETIOPIAN HEROS

  14. ኣስተዋይ
    | #14

    አንዱአለም, አንተ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ነህ:: ቆራጥና አዋቂ መሪ ማለት እንዳንተ ያለ ነው:: ኢትዮጵያዊዉ ማንደላችን ነህ:: እስር ቤት ለመኖር ወይም ህይወትህን ለመክፈል በመቁረጥህ እና ለዎያኔ ባለመሽነፍህ ከሁሉም የላቀ መሪ ያረገሃል::ከዚህ አምባገነን መንግስት የካንጋሩ ፍርድ ቤት ምንም ፍትህ ሊጠበቅ አይችልም::የኢትዮጵያ ህዝብ በትግሉ ነጻ ያወጣሃል:: አምላካችን አንተን መሳይ መሪወቻችንን እና ኢትዮጵያን ይጠብቅልን ትግላችንን አጠናክረን ህዝባችንን ነጻ ለማዉጣት ብርታቱን ይስጠን::(It is saddening but I refuse to cry. Today you, not Meles, won the battle. You took the higher moral ground. I celebrate your victory today)

  15. ሙሴ ሙላቱ
    | #15

    ስተከፍለዉ ዕዳህን አደራ ሳትበላ:
    ሳትንበረከክ ስትተኛ ባንዳ ለሚጠላ:
    ፅዋዉን ለመጎንጨት መድፈርህን ነግረህ:
    በአባባሎችህ ቅርፅ በይዘቶቹን ተደነቅነልህ:
    ሞትህን በሞታችን ሆኖልን ግፍ ተቀብለን:
    ሰዉ አለን ሰዉ አለን ይነጋል እያልን:
    አነዱለሜ ብዙዓለሜ የተከበርክልን:
    ሞተን ስንነሳ ስናዬዉ ስንበተን:
    ቀምረን ዉርደቱን የባንዳዉን:
    የእናቱን ከሃዲ የባለገዉን:
    ሳይሞትም የሞተዉን:
    ባንዳዉ የባንዳዉን:
    ፈልገን አስፈልገን:
    መልሰን መላልሰን:
    በእልሃችን ተዉጠን:
    ባንዳ ይሙት እንለካለን:
    በዉስጣችን ነደን ተቃጥለን:
    ፍርደ ገምደል ዳኞችን ጠልተን:
    ለመይሳዉ የነጋ ላንዱዓሌምም ይነጋል:
    እንደ መሸዉም የማይቀረዉ ሲነጋ ይነጋል::

  16. MELKAMU
    | #16

    መለስና ወያኔ አጠቃላይ የስብእና ቀውስ ውስጥ ያሉ የአእምሮ በሽተኞች(Psychopatic) ናቸው፡፡የኔ ሰው ገብሬ በፍትህና በነፃነት እጦት ህሊናው ተነክቶ እራሱን ሲያቃጥል መለስና ወያኔ የአእምሮ በሽተኛ ነው ብለው ሲያስተባብሎ እነዚህ ሰዎች ከራሱ ከጋኔኖች አለቃ ከሳጥናኤል ጋር አብረው የሚሰሩና በእሱም ምክር የሚመሩ ነው የሚመስሉት፡፡እነዚህ ሰዎች ደደቢት በረሃ ሳሉ በያዛቸው ጅኒ የሚመሩ ሳይሆን አይቀርም፡፡መካሪ ሃይ ባይ ያላቸውም አይመስሉኝም፡፡አቡነ ጳውሎስም ፀበል አጥምቀው ከዚህ ጅኒ እንዳያላቅቋቸው እሳቸውም ከእነሱ የተሻሉ አይደሉም፡፡እረ ጎበዝ ሀገርና ህዝብ በእነዚህ በህገ-አራዊት የሚመሩ እብዶችና አረመኔዎች ሲታመስ ዝም ብሎ ቆሞ ማየት ብቻ እኮ ሆነ ስራችን፡፡አይ አሜሪካ አይ እንግሊዝ አይ እስራኤል ፈጣሪ የስራችሁን ይስጣችሁ፡፡ከበስተጀርባ በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ መለስ/ወያኔን እንደዚሁም ኢሳያስ ሻእብያን እየረዳችሁ እዚህ ስልጣን ላይ ያወጣችሁትና አሁንም ጭምር ዋና ተባባሪና ደጋፊ አጋር በመሆን ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን እዚህ አይነት መከራና ፈተና ውስጥ እንድትወድቅ አደረጋችሁ፡፡መለስ/ወያኔ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ላለፉት 21 ዓመታት ለፈፀመው ግፍና መከራ በቀጥም ሆነ በተዘዋዋሪ ምእራባውያን መንግስታት ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ነገሩ እነሱ አንድ የሚፈልጉትን ሃይል ስልጣን ላይ እንዲወጣ ያደርጉና ከዚያም ያ አገዛዝ በህዝቡና በዜጋው ላይ የፈለገውን በደልና ግፍ ቢፈፅም የራሳቸው ጥቅማቸውና ፍላጎታቸው እስካልተነካ ድረስ ደንታቸው አይደለም፡፡ስልጣን ላይ ያወጡትን አገዛዝ እንደ ማስቲካ አላምጠው ጣእሙ ሲያልቅና ሀገርና ህዝብ የሚጎዳ መጥፎ ስራ ሲያሰሩት ኖረው ከዚያም ከራሱ ሀገርና ህዝብ ጋር አለያይተውት ሲያበቁና በዚህም የተነሳ የገዛ ህዝቡ መከራውና ግፉ አንገሽግሾት ወጊድ በቃ ሲለው Sorry ከዚህ በላይ ልንረዳህ አንችልምና ብለው ሌላ ወደ ስልጣን ከሚመጣው አዲስ ተቃዋሚ ሃይል ጋር ወዲያው ግልብጥ ብለው ወዳጅነት ይመሰርታሉ፡፡የእነዚህ ምእራባውያን መንግስታት የፀረ-ሽብር አጋር ነኝ የሚለው መለስ ዛሬ እነዚህን ንፁሃን የህሊና እስረኛ ዜጎች ያለአግባቡና ያለ አካሄዱ አሸባሪ ብሎ ዘብጥያ አውርዶ ከዚያም በዚህ አይነት ኢ-ፍትሃዊነት በጎደለው መንገድ እድሜ ልክ እስራት ሲበይንባቸው አይ የእኛ አሸባሪነት ትርጉምና ይዘት ይህ አይደለምና ተው እኛንም በተዘዋዋሪ ታሳጣናለህ ብለው ሃይ ከማለት ይልቅ ዝምታን መምረጣቸው ምን ያህል በወሬ ደረጃ ለነፃነትና ለዲሞክራሲ እንቆማለን ቢሉም ቅሉ ግን በተቃራኒው የሚያሳየው ለታዳጊው አለም ህዝብ ቅንጣት ታህል ክብርና ተቆርቋሪነት እንደሌላቸው የሚያሳይ ነገር ነው፡፡እነዚህ ምእራባውያን መንግስታት መለስ/ወያኔ በ97 ምርጫ ከ200 ሰዎች በላይ ሲገድልና በሺዎች የሚቆጠሩትን ሲያስር ብዙም ደንታቸው አልነበረም፡፡እነዚህ ምእራባውያን መንግስታት ሁል ጊዜ በአንድ ሀገር ውስጥ ስላለ ሰብዓዊ መብት ፀጉር እየሰነጠቁ ጭምር ተቆርቋሪ የሚሆኑት በዚያ ሀገር ውስጥ ያለ አገዛዝ የእነሱ ዋና አጋር ካልሆነ ብቻ ነው፡፡በቅርቡ የአውሮፓ ዋንጫን እግር ኳስ በጋራ በምታዘጋጀው ዩክሬን ውስጥ ለእነሱ ብዙም ያለተመቸው አሁን ስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ አንድ ወቅት የእነሱ ዋና አጋር የነበረችን የሀገሪቱን የቀድሞ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር በሙስና እስር ቤት ስላሰረ ብቻ የአውሮፓ ዋንጫ በዚህ ምክንያት በዩክሬን መደረግ የለብትም እያሉ ፕሮፖጋንዳ እስከ መንዛት ደረጃ ነበር የደረሱት፡፡ስለዚህም ዛሬ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ስልጣን ላይ ያለውን አገዛዝ ግፍና መከራ ለምን ብለው ስለተቃወሙ ብቻ አሸባሪ እየተባሉ እድሜ ልክ ዘብጥያ ሲወርዱ የእነዚህ ምእራባውያን መንግስታት ዝም ማለት ጥቅማችን ካልተነካ እኛ ምንቸገረን ከማለት የመነጨ ነው፡፡እነዚህ ምእራባውያን መንግስታት ከዚህ አይነት ተቃዋሚዎች እንግልት ጋር በተያያዘ የእኛን ሀገር ምስኪን ዜጋና እረሳቸውንም የሚታሰሩትንና የሚንገላቱትን ተቃዋሚዎች ጭምር የሚያታልሉበትና የሚያዘናጉበት አንድ ትልቅ ስልት ግን አላቸው፡፡ይህም እነዚህን የሚታሰሩትንና የሚንገላቱትን ተቃዋሚዎችና የህሊና እስረኞችና የሰብዓዊ መብት ታጋይ የፕሬስ ታጋይ ወዘተ የሚል ስያሜ በመስጠት ሽልማት መስጠት ነው፡፡እነ ብርቱካንንም እንደዚህ እያደረጉ ነው ከእውነተኛው ትግል ያስወጡትና ህዝቡንም ከእውነተኛ ትግልና ነፃነት የሚያዘናጉትና በሂደትም የሚያርቁት፡፡ስለዚህም እነዚህ ምእራባውያን መንግስታት በአንድ በኩል የመለስ/ወያኔን አገዛዝ በብርቱ ይደግፋሉ በዚህም የተነሳ አገዛዙ ሀገሪቱንና ህዝቡን እየረገጠና እየዘረፈ እየገዛው ነው፡፡በሌላ በኩል ደግሞ ይህ ለምን ሆነ ብሎ ለሚነሳ እንደ እስክንድር አንዱአለም አይነት ዜጋ ላይ ይህ አይነት በደል ሲደርስ ደግሞ አዛኝ በመምሰል የአዞ እንባ እያነቡ የሰብዓዊ መብት ታጋይ የፕሬስ ታጋይ ወዘተ እያሉ ማቀዝቀዣና ማዘናጊያ ሽልማት ይሰጣሉ፡፡እኛም በዚህ ጠባብ እይታ ታጥረን የተነሳንለትን ዋናውን ሀገራዊና ህዝባዊ አላማችንን ያሳካን እንደሆነ አድርገን እየተሰማን በዚህ በመፅናናት ዘወትር በአዙሪት ውስጥ እየዛበቅን ነው ያለነው፡፡የተቃዋሚው ጎራ እራሱ ዋና ማእከል አድርጎ የከተመው አሜሪካና እንግሊዝ ነው፡፡በአሜሪካና በእንግሊዝ የከተመ ተቃዋሚ ጎራ ደግሞ ትርጉምና ፋይዳ ያለው ሀገርንና ህዝብ ለዘለቄታው ነፃ የሚያወጣ ሃይል ይፈጠራል የሚል ብዙም እምነት የለኝም፡፡ምክንያቱም ምእራባውያን ለተቃዋሚው ጎራ ተገቢውን ድጋፍ የሚያደርጉት አንደኛ መጀመሪያ ደረጃ አሁን ስልጣን ላይ ያለውን አገዛዝ አስወግዶ ተተኪ የሚሆነው አገዛዝ ከላይ የሚታየውን የውጪ ገፅታ ብቻ ትንሽ ቀየር በማድረግ አሁን ስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ በዘረጋው የሚሊታሪ የኢኮኖሚ የደህንነት ሲስተም ላይ በመመርኮዝ የእነሱን አላማና ጥቅም በቀጣይነት ተባባሪ በመሆን የሚያስጠብቅና የሚያስቀጥል እንደሆነ እርግጠኛ ሲሆኑ ነው፡፡ሁለተኛ ስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ በህዝብ ብሶትና ተቃውሞ የተነሳ ባለበት ሁኔታ ለመቀጠል የማይችልበትና እነሱም ይህንን ሁኔታ መቀየር የማይችሉበት ከፍተኛ ደረጃ ሲደርስ ነው፡፡በቱኒስያና በተለይም በግብፅ የታየው ይህ ነው፡፡ስልጣን ላይ በዋና መሪነት ያሉትን እንደነ ሙባረክ ቤናሊና አንዳንድ ዋና ሚኒስትሮች ብቻ በመቀየር ከዚያ ውጪ ያለውን የሚሊታሪ የኢኮኖሚ የደህንነት ሲስተም ግን እንዳለ ማስቀጠል ነው የሚፈለገው፡፡በግብፅ ህዝቡ አሁንም የሚሊታሪ ጁንታውና ይህ የሚሊታሪ ጁንታ ከውጪ አለም አቀፍ ኩባንያዎች ጋር በሙስና ጭምር የተቆጣጠረው የኢኮኖሚ መስክ እንዲወገድ ጭምር ነው ህዝቡ ተቃውሞ አያሰማ ያለው፡፡እንደነ ስዬ አይነት የቀድሞ የህውሃት ዋና ቀንደኛ አባላት ጭምር በቅርቡ አሜሪካ ሄደው ትምህርት ሲማሩም ከዚህ በስተጀርባ ያለው አንዱ ዋና አላማ በቀጣይነት ከመለስ የማይቀር ውድቀት በኋላ በአንድ በሄር የበላይነት ቁጥጥር ስር በዘረኝነት የተዋቀረውና ለግሎባል ካፒታሊዝም ስርዓት አመቺ የሆነው የሀገሪቱን የሚሊታሪ የኢኮኖሚ የደህንነት ሲስተም እንዳለ ለማስቀጠል ከታለመ የረቀቀና የተቀነባበረ አላማ በመነጨ እንዳይሆን እጅግ ከፍተኛ ጥርጣሬ አለኝ፡፡ስለዚህም ከመለስ የማይቀር ውደቅት በኋላ በሀገሪቱ ያለው በአንድ በሄር የበላይነት ቁጥጥር ስር በዘረኝነት የተዋቀረውና ለግሎባል ካፒታሊዝም ስርዓት አመቺ የሆነው የሀገሪቱን የሚሊታሪ የኢኮኖሚ የደህንነት ሲስተም ፈራርሶ ህብረ ብሄራዊና ሀገራዊ አጀንዳ ባለው ስርዓት እስካልተተካ ድረስ የኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነት አገኘሁ ብሎ እንደ ህፃን ልጅ በስሜት እንዳይፈነድቅ ከአሁኑ በቅጡ ሊታሰብበት ይገባል፡፡በዚህ አይነት ስሜታዊ አካሄድ የምንሄድ ከሆነ ደግሞ የእነ እስክንድር ነጋ የእነ አንዱአለም አራጌ የእነ ፕሮፌሰር አስራት የእነ አሰፋ ማሩ ወዘተ መስዋእትነት ፍሬ-አልባ ሆነ ማለት ነው፡፡ነገሮችንም በጥሞና የምናይ አስተዋይ ከሆንን እኛ ዛሬ ሊያስደንቀንና ሊገርመን የሚገባው የመለስ/ወያኔ አሳፋሪና አሳዛኝ የዘረኝነት የዘረፋ የአረመኔ የግፍ አገዛዝ ላለፉት 21 ዓመታት በእኛ እርስ በርስ መናከስና ግድየለሽነት የተነሳ እስካሁን መቀጠሉ እንጂ ከዚህ አይነት አሳፋሪና አሳዛኝ አገዛዝ መላቀቃችን ብቻ አይደለም ሊሆን የሚገባው፡፡መለስ ወያኔ ላለፉት 21 ዓመታትና አሁንም በዚህ አይነት አገዛዝ ለመቀጠል የቻለው በአንደኛነት እኛ ይህ እንዲሆን ስለፈቀድን ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የምእራባውያንና የባእዳን ሃይሎች ድጋፍ ስላለው ጭምር ነው፡፡ሊነጋ ሲል ይጨልማል አይነት በእነ አንዱአለም አራጌ ላይ ይህ አይነት አይን ያወጣ ኢ-ፍትሃዊ ፍርድ የተፈረደውም ስርዓቱ የገባበትን የተስፋ መቁረጥና በዚህም የተነሳ የአጥፎቶ መጥፋት እብደትና አባዜ ውስጥ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ይህ ሁሉ በእነ አንዱአለም አራጌና ሌሎችም መሰል ኢትዮጵያውያን እየተከፈለ ያለ መራር መስዋእትነት ለእኛ ለተቀረነው ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ የህሊና እዳ ነው፡፡ስለዚህም ይህ አይነት እየተከፈለ ያለ መራር መስዋእትነት ግልፅ የሆነ ትርጉምና ፋይዳ ያለው ግብና አላማ ላይ ካልተቀመጠ ነገሩ ሁሉ የውሃ ላይ ኩበት ነው የሚሆነው፡፡ከታሪክ እንደምንማረው ብዙ የህዝብ አብዮቶች በጥቂት መሰሪና ብልጣብልጥ ሃይሎች እየተቀለበሰ ለእነዚሁ በአብዛኛው ለጥቂት መሰሪና ብልጣብልጥ ሃይሎች አላማና ፍላጎት ማስፈፀሚያ እንደሆነ ከስኬቱ ይልቅ ውድቀቱ እያመዘነ የመጣ እንደሆነ ማወቅ ጥሩ ነው፡፡ብዙ እሩቅ ሳንሄድ እራሳቸው መለስና ጥቂት መሰል ወያኔዎች ደርግን በመጣል ሂደት ውስጥ ዋና ያስፈፀሙት ትርጉምና ፋይዳ ያለው አላማና ፍላጎት ግን የራሳቸውን የመለስንና ከበስተጀርባቸው ያለውን የባእዳን ሃይሎች አላማና ፍላጎት ነው፡፡በዚህ የ17 ዓመት ትግል ውስጥ ግን ብዙ የኢትዮጵያ ህዝብ ህይወትና ሀብት ጭዳ እንዲሆንና እንዲባክን ነው የተደረገው፡፡በዚህ ትግል ውስጥ የተገኘው ነገር ኤርትራን ማስገንጠል ኢትዮጵያን የባህር በር ማሳጣት ከዚያም የኢትዮጵያን ህዝብ በዘር በሃይማኖት ማናከስና ማዳከም እንደዚሁም የሀገሪቱንና የህዝቡን አንጡራ ሀብት ለጥቂቶች ጥቅም ሲባል መዝረፍና ማደህየት ነው፡፡በአንድ ሀገር ውስጥ ባለ አብዮታዊ ትግል ውስጥ ዋናው መሰረታዊ ትግል ሁል ጊዜ በብልጣብልጥና መሰሪ በሆኑት በጥቂቶችና በተቃራኒው ባለው በየዋሁና ምስኪኑ ብዙሃኑ ህዝብ መካከል የሚደረግ ፍጭት ነው፡፡በዚህም የተነሳ የዋሁና ምስኪኑ ብዙሃኑ ህዝብ በራሱ ልባምና ብልህ ካልሆነና በተመሳሳይ ከውስጡ በወጡ ቀናኢ ልባምና ብልህ በሆኑ አመራሮች ካልታገዘና ካልተመራ በስተቀር አብዮትና አመፅ ሁሉ ባዶ ጩኸትና ግርግር ሆኖ የታመቀ የብሶት ስሜት ከማራገፊያነት የማያልፍና መጨረሻውም የውሃ ላይ ኩበት ነው የሚሆነው፡፡እኔ እንደ ኢትዮጵያዊነቴ እጅግ የማዝነውም ምስኪኑ ህዝብ ለዘላለም አንዱን አስወግዶ ሌላውን በማምጣት ለዘላለም ለውጥ ያመጣ እየመሰለው ዘላለም ድንገተኛ እሳት በማጥፋት ላይ ባተኮረ በከንቱ የመፍገምገም አዙሪት ውስጥ ዘላለም ሲዛብቅ መኖሩን ሳስብ ነው፡፡ከዚህ በመነጨም የእነ እስክንድር ነጋ የእነ አንዱአለም አራጌ የእነ ፕሮፌሰር አስራት የእነ አሰፋ ማሩ ወዘተ ይህ አይነት መራር ትግልና መስዋእትነት ሁሉ ፍሬ አፈራ ለማለት የምንችለው መለስንና ወያኔን በመጣል ላይ ብቻ አላማና ግብ ሲያደርግ ሳይሆን ከዚህ በዘዘለ ለዚህች ሀገር ከዚህ አዙሪት የምትወጣበትን ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ሲችል ብቻ ነው፡፡ይህንን ደግሞ ለማድረግ የምንችለው በሰከነ መንገድ እረጋ ብለን በማሰብ ትርጉምና ፋይዳ ያለው የህይወትና የፖለቲካ ፍልስፍና ተከትለን እርስ በርስ በመከባበርና በመተማመን ላይ የተመሰረተና ማንኛውንም የአስተሳሰብና የአመለካከት ልዩነት ሊያስተናግድ የሚችል ጥልቀትና ስፋት ያለው ሁሉን አቀፍ ማህበረሰባዊ ውይይትና ክርክር (Dialogue) ስናደርግ ብቻ ነው፡፡በእርግጥ ይህንን ለማድረግ ደግሞ ቅድሚያ ይህንን አይነት ኢፍትሃዊ ፍርድ የሚፈመውንና ሰዎችን ገድሎ በድን እሬሳ በመኪና የሚጎትትና ዛፍ ላይ እሬሳ ሰቅሎ የሚያሳድር በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከዚህ በፊት ያልታየ ይህ አይነት ዘረኛ ዘራፊ ቅጥረኛ አረመኔ የመለስ/ወያኔ አገዛዝ ስርዓት ማንኛውንም ያዋጣል የሚባል ተፈጥሯዊ ሞራላዊና ህጋዊ መንገድ ተከትለን በመተባባር በጋራ ለማስወገድ ስንችልና በዚህም ኢትዮጵያን ኢትዮጵያዊነትንና ኢትዮጵያውያንን ከሚመጣው ጥፋትና አደጋ ቅድሚያ ለመታደግና ለማዳን ስንችል ብቻ ነው፡፡ስልጣንና ዲሞክራሲም ሊኖር የሚችለው ቅድሚያ ሀገርና ህዝብ ወይንም ኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊነትና ኢትዮጵያውያን ሲኖሩ ብቻ ነው፡፡የተቃዋሚውም ጎራ ይህ ነገር በቅጡ ሊገባውና ማን ስልጣን ላይ ይውጣ ከሚለው በተከታይ ካለ ተራ አጀንዳ ይልቅ ቅድሚያ ምን ይደረግ የሚለውን ማስቀደም አለበት፡፡አሁን ኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊነትና ኢትዮጵያውያን ያሉበት በታሪክ ከዚህ በፊት ያልታየ አሳዛኝ አሳፋሪና አደገኛ ሁኔታ በራሱ አንድ ጤነኛ አእምሮ ላለው ሰውና ዜጋ ስለ ስልጣንና ስልጣን ስለሚያመጣው ዝናና ጥቅም እንዲያስብና እንዲጨነቅ የሚያደርግ ነገር አይደለም፡፡ስለዚህም ተቃዋሚው ጎራ በስልጣንና በገንዘብ ጊዚያዊ ጥቅም ካልተሸነፈ በስተቀር ደግሞ ይህችን ሀገር ለማዳን ብዙም አይሳነውም የሚል እምነት አለኝ፡፡የተቃዋሚው ጎራና ህዝቡም የመለስ/ወያኔን ስርዓት ለማስወገድ ደግሞ ከምንም ነገር በላይ ቅድሚያ የሚያስፈልገው ቁጥር አንድ ነገር ደግሞ ሌሎች ልዩነቶችን ለጊዜው አክብሮና ወደ ጎን አስቀምጦ በአንድ ልብ ህብረትና አንድነት መፍጠር ብቻ ነው፡፡ሁተኛው ነገር ደግሞ ነገሮችን በጥቁርና በነጭ እየሳሉ ፀጉር መሰንጠቅን አቁሞ ሌሎችን በቀና መንገድ በማዳመጥና በመረዳት ተገቢውን መቻቻልና ዲሲፕሊን መከተል ነው፡፡ሶስተኛው ነገር ደግሞ አጉል ከንቱ አላስፈላጊ መሰሪነትን ብልጣብልጥነትንና ድብቅነትን አሰወግዶ በምትኩ ተገቢውን ግልፅነትንና ብልህነትን መከተል ነው፡፡አራተኛው ነገር ደግሞ ከበሮ በሰው እጅ ሲያዩት ያምር በራስ ሲይዙት ግን ያደናግር አይነት ባላ በአንድ ጫፍ ላይ የረገጠ ምንም ሳይሰሩ ሌሎችን ግን ቁጭ ብሎ ፀጉር እየሰነጠቁ መተቸትና ማጣጣል መገታት አለበት፡፡እንደዚሁም ከዚህ ጋር በተያያዘ በሌላኛው ጫፍ ባለው አይነት እይታ ደግሞ ከእኔ ወዲያ ለዚህች ሀገርና ህዝብ አዋቂና ተቆርቋሪ ላሳር ሌሎቻችሁ ወጊዱ አታስፈልጉም አይነት ከንቱ መታበይና ግብዝነትም መገታትና አለበት፡፡በሀገርና በህዝብ ጉዳይ ላይ ማንም አስተማሪ ማንም ተማሪ የለም ሁሉም ተማሪም አስተማሪም ነውና፡፡ይህ ሲሆን ደግሞ የተመጣጠነ ሚዛን የጠበቀ አካሄድ ይኖራል ማለት ነው፡፡ይህ መሆን ካልቻለ ደግሞ የፈለገውን ያህል መሬትን የሚያንቀጠቅጥ ድንቅ ሃሳብ ቢኖረን ወቅቱ ተግባራዊ እንዲሆን በሚጠይቀው የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ፈፅሞ ተግባራዊ ሊሆን አይችልም፡፡ግንባር ጥምረት ቅንጅት የሽግግር ምክር ቤት ወዘተ የሚባል ለቁጥር የሚታክት የተቃዋሚ አይነት ሁሉ ጠፍቶ አንድ ወይንም ሁለት ተቃዋሚ ብቻ ሆኖ አንድነትና ህብረት እንደፈጠረ በሰሙ ይህንን የሰሙ እለት ፈፅሞ እንደሚርዱና እንዳለቀላቸው አውቀው ተስፋ በቆረጡ ነበር፡፡ጎበዝ የኢትዮጵያ ጉዳይ እኮ ለጉድ ነው የትም ሀገር ብንሄድ በዚህ በአረቡ የነውጥ አብዮት እንኳን ስንሰማ ግፋ ቢል በዛ ቢባል አምስት ተቃዋሚ ሃይል ቢኖር ነው፡፡ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ያለው ከ70 በላይ ነው፡፡ይህ የሚያሳየው ደግሞ በቃ አንድ የሆነ የጎደለን ትልቅ ነገር እንዳለና እንደዚሁም አንድ የሆነ አጠቃላይ የትውልድ ዝቅጠትና አዙሪት ውስጥ እንዳለን ነው የሚያሳየው፡፡እኔ አንዲያውም አንዳንድ ጊዜ ሳስብ እንዴ ኢትዮጵያ ሰው አይብቀልብሽ ወንድ አይብቀልብሽ ተብላ ተረግማለች የሚባለው እየሰራ ያለ እውነት ይሆን እንዴ እንድል ጭምር ነው እያደረገኝ ያለው፡፡ለማንኛውም ሰው በጠፋበት ዘመን ውስጥ እነ አንዱአለም አራጌ ያሉት ላመኑበት ነገር ፅኑ በመሆናቸው ይህ ተስፋዬ ብዙም አልጨለመም፡፡ነገር ግን በአንድ በኩል ደግሞ “ኢትዮጵያ ሀገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ” የሚለውን የቆየ አባባል ሳስብ ይህ እንዳይሆን እየፈራሁኝ ይህ አይነት መከራ ትግልና መስዋእትነት የመጨረሻ ግቡና ፍሬውስ ምን ይሆን የሚለውም እንደዚሁ ያስጨንቀኛል፡፡ሆኖም ግን ጋን በጠጠር የደገፋል እንዲሉ ሁላችንም ታሪካዊ የዜግነት ግዴታችንን ያቅማችንን ጣል በማድረግ እንወጣ፡፡ጎበዝ ቢያንስ ለመለስ/ወያኔ ወደንም ሆነ ተገደን የጥፋት ተባባሪ አንሁን፡፡እንደዚሁም በምእራባውያን መንግስታት ላይም እምነት አይኑረን፡፡ እነሱ የግል ፍላጎታቸውና ጥቅማቸው እስካልተነካ ድረስ በታዳጊው አለም ውስጥ ሰብዓዊ መብት ተከበረ አልተከበረ ዲሞክራሲ ሰፈነ አልሰፈነ ታዳጊው አለም በአምባገነን ወይንም በዲሞክራት ወይንም በዝንጀሮ ጭምር ቢሆነ ተገዛ አልተገዛ ጉዳያቸው አይደለም፡፡ምእራባውያን መንግስታት ጥቅማቸው ሲነካ ብቻ ነው መጮህና ከዚያም ሃይል መጠቀም የሚጀምሩት፡፡የመለስንና የኢትዮጵያንም ጉዳይ በሚመለከት ምናልባት ለእኛ ያዘኑ ለመምሰልና እኛንም ለመሸንገል የአዞ እንባ ማንባት ልማዳቸው ነው፡፡ለተቃዋሚውም ጎራ መወገን የሚጀምሩት መለስ መውደቃቸው የማይቀር ግድ መሆኑን እስከመጨረሻው 11ኛ ሰዓት ጠብታ ድረስ ጠብቀውና አይተው ነው ሌላ አመራጭ ተተኪ አገዛዝ ለመፈለግ ሲያስቡ ብቻ ነው፡፡ መለስም ይህንን ጥንቅቀው ስለሚያውቁ ነው እኛን እንደፈለጉት የሚረግጡንና አበሳችንን የሚያሳዩን፡፡ ለማንኛውም ፈጣሪ ለአንዱአለም አራጌና ቤተሰቦቹ ፅናትንና መፅናናትን ይስጥልን እላለሁኝ፡፡
    ድል ነፃነት ክብር ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
    እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!!!

  17. Anonymous
    | #17

    ከዘረኝው ወያኔ የባርነት አገዛዝ የሚያበቃበት ጊዜ ቀርቧል ! እስክንድርና አንዱአለም ለእኝ አሁንም እስትንፋሳችን አሁንም መሪያችን ናቸው ! መለስ ዜናዊ በጋዜጠኝ አበበ ገላው በደነበረ ማግስት በእነ አንዱአለምና እስክንድር ነጋና ሌሎቹም ላይ የተወሰነው ዉሳኔ ለወያኔ የመርዝ ጽዋ ሲሆን ለእኝ ደግሞ የምንጠነክርበት አንድ ሆነን የምንነሳበት ጠንካራ ህብረት የምንመሰርትበት የውዴታ ግዴታችንን የምንወጣበት መራር ፅዋችን ነው !!
    አንድ ህዝብ አንድ ሃገር አንድ ባንዲራ
    ተነስ ተነሽ ነጻነት በሃገራችን ይብራ
    በህብረት ታሪክ እንስራ
    ሰላምና ነጻነት እኩልነት የዜግነት መብት እንዲኖረን እስክ ሂወቴ ፍፃሜ ቃል እገባለሁ !! አንተም አንቺም ለሃገራችሁ ቃል ግቡ!!

  18. ገበየሁ ደስታ ከቤልጄም
    | #18

    ከዘረኝው ወያኔ የባርነት አገዛዝ የሚያበቃበት ጊዜ ቀርቧል ! እስክንድርና አንዱአለም ለእኝ አሁንም እስትንፋሳችን አሁንም መሪያችን ናቸው ! መለስ ዜናዊ በጋዜጠኝ አበበ ገላው በደነበረ ማግስት በእነ አንዱአለምና እስክንድር ነጋና ሌሎቹም ላይ የተወሰነው ዉሳኔ ለወያኔ የመርዝ ጽዋ ሲሆን ለእኝ ደግሞ የምንጠነክርበት አንድ ሆነን የምንነሳበት ጠንካራ ህብረት የምንመሰርትበት የውዴታ ግዴታችንን የምንወጣበት መራር ፅዋችን ነው !!
    አንድ ህዝብ አንድ ሃገር አንድ ባንዲራ
    ተነስ ተነሽ ነጻነት በሃገራችን ይብራ
    በህብረት ታሪክ እንስራ
    ሰላምና ነጻነት እኩልነት የዜግነት መብት እንዲኖረን እስክ ሂወቴ ፍፃሜ ቃል እገባለሁ !! አንተም አንቺም ለሃገራችሁ ቃል ግቡ!!

  19. ጂኒ
    | #19

    መልካሙ! እኔ አግኝቼሃለሁ።የምትጠቀምበትን ዘዴ ልንገርህ።አንድ፦ በአንድ ረጅም አንቀፅ ሃሳብህን የምትዘበዝበው ካለማወቅ አይደለም። ሁለት፦ ጉዳዩ ስለእኛ እየሆነ ስለሌላ ሃገራት የሚአስለፈልፍህ እያወቅህ ነው።
    የመጀመሪያውን የምታደርገው በተንዛዛ ፅሁፍህ ውስጥ የተደበቀ መርዝ ለማስተላለፍ ነው።ለምሳሌ፦ በታረቀኝ ፅሁፍ ላይ በሰጠከው የገለማ ፅሁፍ ልታስተላልፈው የፈለከው
    ወደድንም ጠላንም እኛ ኢትዮፕያውያን የኤርትራን ሉዐላዊነት ተቀብለናል
    ብለህ እኛም ይህን እንድናምን ነው። ኧረ ለመሆኑ የኛን መቀበል በምን አወቅህ? በምን ለካህ? ስለዚህ ስብሐት፤ ስብ’ት ነጋን ትሸታለህ።
    የሁለተኛውን የምታደርገው ትኩረታችንን ለማናጠብ ነው።የጋራ ድምፃችንን፤ የምንጋራውን ራዕያችንን ለመበተን ነው።ለእኛ የገዛ ልምዳችን፤ የገዛ ህመማችን ካወቅንበት ብዙ ወንዝ ያሻግራልና አትጨነቅልን!!!ምዕራባውያን መንግስታትን ስለማመንና አለማመንም አባቶቻችንና ልምዳችን በቂ ነውና የዐረቡን ዐለም እየጠቀስክ ልታስተምረን አትፈልግ። በተረፈ ከአንተ ጋር ድብብቆሽ የሚጫወት የለም። ‘ስለሶርያ ያልከው ልክ ነው፥ ልክ አይደልም’ እያልን ከአንተ ጋር መባዘን መበለጥ ነው።ይበቃሃል።

  20. ሙሴ ሙላቱ
    | #20

    ስያለቅስ የሚያስለቀስ በሽታዬ ህመሜ:
    የጠላትን ፅዋ ሲጣጣዉ አንዱለሜ:
    የሞት ዓይነቱ መልኩ ላይታወቅ:
    በዕምባዬ መሀል ስመጣ ሳቅ:
    ወንድ ልጅም አያለቅስ :
    ዕምባዬን አይፍሰስ:
    መለስ ልቡ እንድፈርስ:
    አይቀረዉን ሞት ልቅመስ:
    ሞራሌ አይዉረድ አይልፈስፈስ:
    ልንጉራደድ ቆሜን አገሩን ልዳስስ:
    ያቢድሳን ደሙን ዉሰጤ ሲተራመስ:
    በጎራዴን የሚጫወት እንደዘራይ ደረስ:
    ለባንዳሰ አልገዛምን የነስ ደሜም ይፍሰስ:
    በዉርደት ላይ ድርብ ዉርደቶች ተሸክመን:
    ግፍ በደለቸዉን ከነ ንቀታቸዉ ችለን:
    ከነድፍድፉ ጋን እንሸከማለን:
    በቃ ማለቱን አቅቶን:
    ተራ በታራ ቆመን:
    ማለቅ ዕድላችን:
    ለባነዶች አየተገዘን:
    ሲያፍረሱተ ጎጆዓችንን:
    ሲቸበችቡት መሬታችንን:
    አረ በቃችሁ ማለት እቅቶን:
    ተራ በታራ ቆመን በተራ አለቅን:
    በቻልኩት እኔስ እነዳርቺሜዲስ ማበዱን:
    ከአሌክሳነደሪያን ተነስቼን ጠቅልዬ ጉዋዜን:
    የተዉለድኩበት ስራኩስ ባደረገዉ መቃብሬን:
    ታጠቁዉ በገመዱን ያንዱላሜ ልጆችን:
    የጠላት ፅዋ ጠጣ አሉት ጨቅላዎቹን:
    ተፈጠሮን ረድታን ማደጉንም ከታደልን:
    አርማህን እናነሳለን የነፃነት ጥማትህን:
    የሕልምህን ፍቺዉን ያገር ፍቅርህን::
    ያንተV መሞት ሞት አይደል:
    ሰዉ በተቅማጥ ይሞታል:
    ትግሉም ይቀጥላል:
    ባንዳም ይሞታል::

    ክብር ላንዱዓለም ክብር ለእስክንድረ ነጋና ለጀግሞቻችን!!

  21. አሳዛኝ ዜና !
    | #21

    እረ ዳኞች ለዳኝነት ኑሩ !

  22. ሙሴ ሙላቱ
    | #22

    ተራ እየጠበቅን:
    በተራ እንወድቃለን;
    ሲመቱት መስፍኔን:
    አዋርደዉትን ጊዳዳን:
    ዉበታማ ልጆች ከተፈጁን:
    በሞተዉ ተገለን ሳይሞት በሞተዉን:
    በዉርደት ላይ ውርደቶች እንጎነጫለን:
    የዉሾች አለቃን መለስን መግደል አቅቶን:
    አንድ ርኩስ አናሰወግድዉ ባንዳ እየቀለብን:
    እናት አየትዮጲያን ደጋግመዉ ሲደፍረዋት:
    ይሉኝታዉም የማይገዛቸዉ የህገ አራዊት:
    መናገር ሰለቸን ስለብልግበናቸዉ ብዛት:
    ስልጣንን እያለሙ አገር የሚሽጡት:
    የእንግዴን ልጆችዋ መለስ በረከት:
    ኢሳያስ የሻቢያዉ ከባንዳዎች ቤት:
    የደርቡሾች ካራ ሚስጡሩን ለማያዩት:
    ከቱርኮች ከግብፆች ጠብቀዉን ያኖርዋት:
    መቅዳላ ከመተማዉ ማይጨዉ የወድቁላት:
    በቅኝ ግዛት መዉደቅዋን ተፀይፈዉን ባርነት:
    ሜዳም ለገቡት ለደፋሮቹን የጨዋታ ስልት ላደነቁት:
    የክብር ሰለምታዉን ቆሜን ነዉ የሰጠናቸዉ:
    ስስላት ነዉ ያድርኩት ካረታ ድብረዋን:
    ከቀይ ባሀር እንድጠጣ ያሉላ ፈረሱን:
    የበላይ ዘለቀ ጋሻ የታቶ ጋኬጉቾን::

  23. ማራማዊት
    | #23

    አቶ አንዱዓለም መቼም በጣም የምትደነቅ ሰው ነህ. ለአንተ እና ለሰጠህው መልስ ትልቅ አድናቆት አለኝ. ደስ የሚል መልስ ሰተሃቸዋል. ጀግና!!!!! ወያኔዎች እራሳቸው በዓላማ ጽናትህ ሳይገረሙ እና ሳይቀኑ አይቀርም. በአንጻሩ ደሞ ለሆዳቸው ያደሩትን እንደሚንቁ እና እንድሚያሾፉባቸው ሁሉ. እናም አንዱዓለም አንተ ልዩ ሰው ነህ በዚህ አጋጣሚ ለእስክንድር እና ለናትናኤል ለሌሎችም አድናቆቴ ታላቅ ነው. አቶ መለስ (አባባ ማሙሽ) ብርቱኳንን እንዳረጓት ደብዳቤ ጽፈው አንቺ አንብቢው እንዳሏት ሁሉ አደራ እንደዛ እንዳይሉህ በዓላማህ ጽናህ!!!!! ሌላው መልካሙ ትክክል ብለሃል የኛ የእጅ አዙር ጥቃት እና ጠላታችን እንዚህ ከይሲ ምህራባውያን ናቸው የእርዳታ ገንዘብ በህዝብ ስም ይገባል ጥቂቷን ስራ ላይ ያውላሉ ከዛ የቀረወን ያሸሻሉ እነመዝረፍ አይሰለቻቸው . እናም ህዝቡ በስሙ ይገባለታል .ህዝቡን ለመጥቀም ሳይሆን ለመቀጥቀጥ እይተጠቀሙበት ነው እናም የርዳታ ገንዘብ ለኛ ጥርቅም ብሎ ይቅር. ለኢትዮጵያ ህዝብ ውለታ ዋልን ሊሉ ነው የወያኔን ባለስልጣኖች አካውንት አደለቡ እንጂ.

  24. ዳግም
    | #24

    ያልፋአል አንተ ግን ጀግና ነህ ታአሪክም ሰርተሀአል ነገም ቀን ናትና

  25. አንድነት ብርሃኔ
    | #25

    መልካሙ የወያነን እብደት ከማውሳት እኛን መርበትበትና የራሳችንን መብትና ማንነት ለማረጋገት ሳንጥር ከማንኛውም የትግል ጎራ ተካፍሎና ተሳትፎ ሳናደርግ በሩቅ ሆንን በትግል ወስጥ ገብተው የቤተስብ ኃላፊነት የኑሮ ውድድር ስይማርካቸው በሕዝባቸውና በሀገራቸው የወደቀውን ታላቅ ጫና ያለአንዳች ፍራቻ ይህን እምባገነን የወገን ጠላት በግምባር የሱን የጦር ማሳርያ ሳይምበረከክኩ በጽናት በትባት ቆመው በሰላማዊ በረጋና በሰለጠነ የሀገር አንድነትና ሕላዌን ሲታገሉ ያንተ የቆጥርካቸው ተለጣፊ የፖለቲካ ድርጅቶች ወያነ ለማምታታት የፈጠራቸው አሻጉሊቶች ሳይሆኑ:በእውነተኛ የሀገርና የወገን ፍቅር ወያነን ገትረው የያዙትን ታላላቅ የቁርጥ ልጆች ባንተ መለኪያ ሊነገርላቸው በማይቻል በመሆኑ; እውነት ያለውን የሀገርና የወገን ጥፋት ሕሊና ያለው ማንኛውም ዜጋ; በዳር ሆኖ የሚታገሉትን ብርቅዮ የኢትዮጵያ የቁርጥ ልጆች በተደጋጋሚ ያሳዩትን እያሳዩም ያሉትን ቆራጥ ጀግኖች; ወያኔ ባቆመው የካንጋሮ ፍርድቤት ፍትሕና ርትእ ያልተላበሱ በሆድ ለተገዙ የስራቱ ሎሌዎች በግምባር ያለፍራቻ የነሱን ሳይሆን በሰማንያ ሚልዮን ለሚቆጠረው የኢትዮጵያ ሕዝቦች የመናገር የመጻፍ ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ በዜግነቱ በሁሉም ቦታ ተሳትፎና ተካፍሎ መብትና ነጻነቱ የተጠበቀ የሀገሪቱን ሀብት እውቀት ሀገራዊነቱ እንዲረጋገት ወያነን ያለውዴታ ተቀብሎ የሕግ በላይነትን እንዲቀበል ቁጥጥርና ሚዛን ተጠያቂነትን እንዲቀበል በማድረግ በዓለም ሕብረተሰብ ፊት በድብቅና በውሸት ሲራመድ የቆየው የምእራባውያን የጥቅም ማሯሯጥ የወያነን ቁንጮ በመድረክ አንገት ለማስደፋትና ቀውሱም ለጤንነቱ አደጋ ላይ ለማድረሰስ የበቃው በተቃዋሚው ጥረትና ቆራጥ ትብብር መሆኑን እንዲገባህ ያስፈልጋል:: እንዲሁም የትግል መስመሮቻቸው በጋራ ለመስራትና ውጤታማ ለማድረግ የሚቻለው ሕዝቦች የትግሉ ተሳታፊዎችና ታጋዮች ሲሆኑ ብቻ ነው አገርቤት ያሉት በችግር ምክንያት ከለባቸው ተጽእኖ ያለውድ በግዴታ ለኢኅዴግ በስለላም ሆነ በሎሌነት ለማደር የተገደዱ አንዳንዶቹ በጽናት ላለመገዛት በመወሰን በድብቅ ያለባቸውን ሀገራዊና ወገናዊ ኃላፊነት በመታገል ያሉ ቁጥር ስፍር የላቸውም እንግዲህ በውጭ ያለው ዜጋ ኢትዮጵያዊ ነኝ ማለት በቂ አይደለም ማስመስከርና ሀገራዊ ኃላፊነቱን አቅሙ በፈቀደው መወጣት ይጠየቅበታል እንዲሁ በባዶ ሜዳ አሉታዊ ትችት ውይንም ወረፋ ተገቢነት የለውም በመጀመርያ ተሳትፎና ሀገራዊ ኃላፊነታችንን በማሳየት ለምናደርገው ማንኛውም አስተዋጽኦ ለመጠየቅና ስሕተቶችም ካሉ እንዲታረሙ የማድረግ ሙሉ መብቶች አሉን እንዲሁም ድርጅቶችን የወከሉ ግለሰቦች ለተጠየቁት ጥያቄ አጥጋቢና ተጨባጭ የሆነ ድርጅቱን የማያነጋ ተሰላፊውን የማያስኮርፍና በትጋት ለሚጠየቅበት ምንኛውንም ግዴታ እንዲወጣ ሞራላዊና ስነአይምሯዊ ድጋፍ መስጠት ይጠየቃቸዋል ይህን ካደረግን ያለውን የግፍ ስራአት በመገርሰስ የሁሉም እኩል የሆነች መብትና ነጻነት የተረጋገጠባት ሁሉም ጠግቦና ተደላድሎ የሚኖርባት ሀገር ኢትዮጵያ በአንድነትና በሰከነ በተረጋጋ በመቻቻል ላይ የተመሰረተ አክብሮትና መተሳሰብ ከሌኤላው ዓለም በመወዳደር ራስን በመመገብ የቻልን ከረሀብና ከልመና ተላቀን የምንኖርባት ሰፊመሬቶቻችንን በማልማት ወንዞቻችንን ለጥቅም በማዋል ቡሉም በተሰጠን ተፈጥራዊ ስጦታ አሁን ሊሆን ነው ከሚባለው በበለጠ ሁሉም ዜጎች የተሳተፉበት እድገትና ክንንውን ለማድረግ አውንታዊ በሆነ ፍላጎት እንነሳ: ወንድም መልካሙ ከቁጥር ብዛት ትግል ውጤታማ እንዳልሆነ በመረዳት የሚደረጉትና እየተደረጉ ያልሉትን የቅርብ ጊዜ የመድረክን ውጤት ተመልከት የወያነንም መደናበር አስተውል ካልደፈረሰ አይጠራም የሚለውን ብህሄል አጣጥመው: ያለኝን መልክት ለሁሉም ወገኖቼ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት በወያነ ሎሌዎች የሚነፋውን የሃሰት የማስፈራራት ወሬ የሌለው እድገት ሊሰራ እተባለው ግድብ የገንዘብ ምሰብሰቢያ በመሆኑ በእውነት ካበርንና ሕዝባችንን ካለበት የመብት ረገጣ ሀገራችንን ከውድቀት ለማዳን በገንዘብም ሆነ በእውቀት በቂ የሆነ ኃይል በማቀናጀት ለመስራት የምንችለው ሀገሪቱ የሁሉም ዜጎች ስትሆን ብቻ መሆኑን ስንቀበል በመሆኑ አሁንም ለሀገርና ለወገን እኛም በስደት ያለነው ሀገራችን በመሄድ ለመዝናናት ለማልማት ለመነገድ ለማስተማር በጠቅላላው ሀገርና ወገን ለመርዳት ነጻና ፍትሃዊ የሆነ ስራአት ሲኖር ብቻ ነው: ይህን ላማምጣት ሌሎች ተታግለው ሳይሆን እኛው ታጋዮች ስንሆን ብቻ ነው ትግልም አታጋይና ታጋይ ከሌለ ላለው እምባገነን ስራአት በፍርሃት ቆፈን መገዛት ሊሆን ነው: እውነተኛ የሀገር የወገን ፍቅር ያለው ካለፈው የታሪክ ባለቤቶች ከሃይማኖቱ ሊቅውንቶች የወረሰውን ኢትዮጵያዊ ወኔ በድጋሚ የሚያሳይበት የሚፈተንበት ወቅት በመሆኑ እያንዳንዱ ዜጋ ተዘጋጅቶ በጽናት ለዚህ ሁለገብ ትግል መሰናዶና ቤዛነቱን ማሳየት ይጠበቅበታል: ምክንያቱም ያለ ሕዝቦች ተሳትፎ ትግል ውጤት አያመጣም ለዚሁም የቅርብ የትግል መራፎች የሆኑትን የአረብ ጸደይ (አብዮት) ማለት ቱኑዚያን,ግብጽን,ሊቢያን,የመንን,መትቀስ በቂ መረጃዎች ናቸው: ሞተው የፈለጉትን ነጻነት አግኝተዋል እኛም ሞተ ላማግኘት ላኛ ሳይሆን ለተከታዩ ትውልድ ለሟቾች መታወሳቸው ሃወልት ማቆም ብቻ ነው:ትግልን ማየት የምንችለው ለሚልዮን የሚቆጠሩ ዜጎች መብት ለማስከበር ጥቂቶች ሕይወታችንን መክፈል ይኖርብናል ለዚሁም አንዱና ታላቅ ምሳሌ የሚሆነን ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ሃጥያት ለማዳን ሲል ቤዛ ሆነ በሱ ደም በሱ መከራ በሱ ግርፋት እኛን አዳነ ታሪኩና ያደረገው ተግባሩ ዘላለም እንደ አዲስ በያመቱ ስናወሳውና ስናስበው እንኖራለን ስለዚህም የነጻነት ድልድዮች ለመሆን የምንችለው ስለራሳችን ሳይሆን ስለሌኤሎች በማሰባችን በመሆኑ ሌሎች ነጻነትን እንዲያገኙ ነጻ የሆነ አስተሳሰብ ያላቸው ማሳየት አለባቸው
    ድል ለኢትዮጵያ ሕዝቦች

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።