አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።
Recent Posts
- ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ 2ኛ ዓመት ቅጽ 2 ቁ 76
- በላተኛው አባ-መላ ከያሬድ አይቼህ
- የሰማይ ላይ ግንብ የመጽሃፍ ግምገማ ሰለሞን ሃይለ ማሪያም
- የኛ ነገር፡ የኔም ነገር፤ አንድ እንደመግቢያ፤ አሸዋና አለት በልጅ ተክሌ
- ኢትዮጵያዊነት እያበበ ነው ወይስ እየጠወለገ? የኢሮብ መብት ተማጓች ማኅበር
- የበረከትና አላሙዲ ልሳን (ከኢየሩሳሌም አርአያ)
- የመለስ ዜናዊ ሌጋሲ ስቶኮልም ስንድሮም በታሪኩ አባዳማ
- የመለስ መታሰቢያ ተቋም (Foundation) – ክፍል 3 ከ 3 ግርማ ሞገስ
- አሸባሪው ማን ነው? ከተስፋዬ ዘነበ
- አጀንዳ! ፍ.አ
Recent Comments
- Tolla on በላተኛው አባ-መላ ከያሬድ አይቼህ
- አበራ ለማ on የሰማይ ላይ ግንብ የመጽሃፍ ግምገማ ሰለሞን ሃይለ ማሪያም
- አስማረ on የኛ ነገር፡ የኔም ነገር፤ አንድ እንደመግቢያ፤ አሸዋና አለት በልጅ ተክሌ
- በላይነሽ on የኛ ነገር፡ የኔም ነገር፤ አንድ እንደመግቢያ፤ አሸዋና አለት በልጅ ተክሌ
- Gerum Tessfa on የኛ ነገር፡ የኔም ነገር፤ አንድ እንደመግቢያ፤ አሸዋና አለት በልጅ ተክሌ
- በለው ! on የመለስ መታሰቢያ ተቋም (Foundation) – ክፍል 3 ከ 3 ግርማ ሞገስ
- ይብሳ on ሁለ ገብ ትግሉና ህዝባዊ አመጽ። ዛሬስ። ከዳኮታ የጥናት ማእከል።
- Gethann on ኢትዮጵያዊነት እያበበ ነው ወይስ እየጠወለገ? የኢሮብ መብት ተማጓች ማኅበር
- ጥሩወርቅ(ጥሩዬ) on ሁለ ገብ ትግሉና ህዝባዊ አመጽ። ዛሬስ። ከዳኮታ የጥናት ማእከል።
- በላይነሽ on የመለስ መታሰቢያ ተቋም (Foundation) – ክፍል 3 ከ 3 ግርማ ሞገስ

Categories
Archives
- May 2013
- April 2013
- March 2013
- February 2013
- January 2013
- December 2012
- November 2012
- October 2012
- September 2012
- August 2012
- July 2012
- June 2012
- May 2012
- April 2012
- March 2012
- February 2012
- January 2012
- December 2011
- November 2011
- October 2011
- September 2011
- August 2011
- July 2011
- June 2011
- May 2011
- April 2011
- March 2011
- February 2011
- January 2011
- December 2010
- November 2010
- October 2010
- September 2010
- August 2010
- July 2010
- June 2010
- May 2010
- April 2010
- March 2010
- February 2010
- January 2010
- December 2009
- November 2009
- October 2009
- September 2009
- August 2009
- July 2009
- June 2009
- May 2009
- April 2009
- March 2009
- February 2009
- January 2009
- December 2008
- November 2008
- October 2008


ቃል
አ ሌ ፍ…………………..
አስቀድሞ ቃል ነበረ የህይወት ጅማሬ አልፋ
የጽንፈ-ዓለሙ መነሻ የፍጥረት-ህላዌ ተስፋ
እ ና ም…………………..
ቃል ለምድር ለሰማይ ብሎ
በዘላለም ፍቅሩ ምሎ
ወደር የለሽ ክብሩን ጥሎ
ከመኖሪያው ተነጥሎ
እውነትና ጸጋ አዳብሎ
ሰላም ሊያዘንብ ጠብን ገድሎ
ጠፈር ከንፎ ጋራ ዘልሎ
ስርጉዋጉጡን አስተካክሎ
አረምርሞ አደላድሎ
ብርሃን ሊሆን ፍሞ ግሎ
ሙቀት ሊሰጥ ደብኖ ከስሎ
አዘቅዝቆ ወርዶ ቀልሎ
አካል ለብሶ እኛን መስሎ
እስኪገለጥ ሥጋ – አክሎ…………….
እንዴት ይሆን ጥበቃችን-የእምነታችን ጽናት ልኩ?
ቃልን ባካል እስክናየው እስኪገለጥ ጠርቶ መልኩ
እንኖር ይሆን? ወይ እንጠፋ?
እንስብ ይሆን? ወይ እንገፋ?
ሥጋ እስኪሆን የቃል ተስፋ
እንጠብ ይሆን? ወይ እንሰፋ?
እናርፍ ይሆን? ወይ እንለፋ?
እስኪገለጥ የቃል ተስፋ ?
ደ ግ ሞ ም………………..
ቃል በራሱ ታምኖ ምሎ
የኛን ጉዞ ነድፎ ስሎ
ኃይል አምቆ ብርታት አዝሎ
ከሰገባው ተነጥሎ
ህዋን ጥሶ የብስን ዘልሎ
ተምዘግዝጎ ትንታግ መስሎ
ባህሩ ላይ መንገድ ተክሎ
በአቅጣጫችን አይኑን ጥሎ
ወደ ወንዙ መሃል ክፍል
ወደ ሰመጥንበት ክልል
ወደ መርከባችን መጥቶ
ርኅሩኅ ድምጹን አሰምቶ
ማዕበል ገርቶ ሰላም ሰጥቶ
ሥጋ እስኪሆን ያ-ቃል ረግቶ…………………..
እንዴት ይሆን ጥበቃችን የእምነታችን ፅናት ልኩ?
ቃልን በአካል እስክናገኝ እስኪታየን ጠርቶ መልኩ
እንቆም ይሆን? ወይ እንጠፋ?
እንወስድ ይሆን? ወይ እንገፋ?
ሥጋ እስኪሆን የቃል ተስፋ
እንጠብ ይሆን? ወይ እንሰፋ?
እናርፍ ይሆን? ወይ እንለፋ?
እስኪገለጥ የቃል ተስፋ ?
ስ ለ ዚ ህ…………………
በቃል ልንኖር ቃል ተልኮ
መስሚያችንን ቀርቦ ታክኮ
ወደ ልባችን ሥር ሊዘልቅ
መግቢያ መንገድ ሲያጠያይቅ
ጆሮ ዳባ እንዳንለው
በቸልታ እንዳንጥለው
ትንሽ ቢመስልም ቃል ዘር ነው ! ! !
ፊት አይቶ የማያደላ
ወቅት አይቶ የማያሰላ
የማይጠቁር የማይቀላ
ሲሞቀው ኃይሉ ማይላላ
ሲበርደው የማይጣላ
ያዙኝ ልቀቁኝ የማያውቅ
የጥበብ የክህሎት እምቅ
የእምነት-ጽንስ እስትንፋስ መልህቅ
የጽንፈ-ዓለሙ መገኛ
አያ – ቃል የፍጥረት ዳኛ
መሆኑ ይግባን እንወቅ
ለ ም ን ሰ ማ ው እ ን ጠ ን ቀ ቅ !
ያ ለ ዚ ያ………………….
ቃል ሲቃትት ሊታደገን ጆሮ ዳባ ብለን ካልነው
እንደ ሰዱቅ-ፈሪሳዊ እንደ ጻፎች ከገፋነው
ችሎት ፈጥረን ዋቢ ቀጥረን አስገድለን ካስቀበርነው
ይብላኝ እንጂ ላልታደልነው ቤዛችንን ላላወቅነው
እሱ እንደሆን በሰልስቱ መነሳቱ አይቀሬ ነው ! ! !
ታምራት
ከድንጋያማ ተራሮች ግዛት
ታህሳስ – 2004 (December-2011)
በቅሲስ አስተራየ ጽጌ የቀረበውን ጽሑፍ በጥሞና አንብቤዋልሁ. ይበል የሚያሰኝ ጽሑፍ ነው. በነ ፋሌቅ ወጥመድ ውስጥ የወደቀችው እናት ቤተክርስቲያን ጉዳይ አሁንም አይን እያየ ወደ ሞላ ወንዝ ብዙውን ወገን እያሳሳቀ እየወሰደ ነው. ምናልባት የቀሲስ ጽሑፍ ጥሩ ምስገንዘቢያ ሊሆን ይችላል.
ጥንተአብሶን በተመለከተ እስካህንም ሲስጡ የቆዩት ማስረጃዎች አንሰው አይደለም. ትልቁ ችግር ከወዲያም ሆነ ከወዲህ የሚጠቅሱት የውዳሴ ቅዳሴ ማስረጃወች, ገታን በድንግልና ጸንሳ በድንግልና
ስለወለደች መሆኑን በሚገባ አለመገንዘብ ነው. ሰውነቱዋንም ዝቅ ማድረግና ‘ወኮነ ሰባአ ከማነ ዘእንበለ ህጢአታ ባሕቲታ’ የሚለውን መስረታዊ ትስብኣት አለመገንዘብ ነው. የኛ ዋናው የሃይማኖት መምህራችን ቅዱስ ያረድ ብነሐሴ ድጉዋው. ከሶስት ጊዜ በላይ . አንጺሖ ስጋሃ ቀዲሶ ኪያሃ ሐደረ ልእሌሃ. ይላል. ከቅዱስ ያሬድ በላይ ስለ እመቤታችን ተቆርቁዋሪ መስሎ ጥራዝ መንጠቅና ወደ ማያስፈልግ ንትርክ ውስጥ መግባት ይርሱዋን ክብር ከፍም ዝቅም አያደርገውም. የምናመስግናትና የምናከብራት በመላኩ ብስራት ተቀድሳ አምላክን በመውለዱዋ ስለሆነ ወላዲተ አምላክ ከሚለው የክብርና የግብር ስም በላይ የሚይስከብራትም ሆነ ይሚይስወድሳት አስተምህሮ ሊኖር አይችልም. ዋናው ነገር ብርሱዋነቱዋ ብህልዮም ሆነ በገቢር የፍጸመችው አብሶ የለም.
ውድ ቀሲስ አስተርአየ፤
በየጊዜው የሚያወጡዋቸውን መጣጥፎች በቅርብ ከሚከታተሉትና ከአድናቂዎችዎ ሰዎች አንዱ ነኝ። በዚህ ያቀረቡዋቸውንም ሐሳቦች በአብዛኛው በማክበር እቀበላለሁ። ግን አንድ በተደጋጋሚ የሚያቀርቡት፤ ከካሕን የማይጠበቅ፤ ነጥብዎ የቀረውን መጣጥፍዎን የሚበክል ወይም የሚያቃልል ስለ መሰለኝ፤ እንዲያስቡበት ብቻ፤ ጥቆማዬን በትሕትና ላቀርብልዎ ወሰንኩ።
ይኸውም፤ ስለ ግለሰቦች እጅግ በሚያስጸይፍ አገላለጽ የሚያቀርቡት ሐተታ ነው። ለምሳሌ፤ በዚህ ጽሑፍዎ፤ ስለ ርእሰ ደብር አብርሃም፤ ያቀረቡት ሂስ ከተራ ስድብ የሚቆጠር፤ እርስዎን ከመሰለ የበሰለ ካሕን የማይጠበቅ ነው። እርግጠኛ እንዲሆኑ የምፈልገው፤ እኔ የርእሰ ደብር ዝምድናም ሆነ ልዩ ወዳጅነት የለኝም። ነገር ግን የቤተ ክርስቲያናችን አባል በመሆኔ፤ ካሕናት እንደዚህ በዘቀጠ ቁዋንቁዋ፤ ሲዘላለፉ ማየት እጅፍ በጣም ያሳፍረኛል። በተጨማሪም፤ ጌታችን ባስተማረን ፀሎት መሠረት፤ “……የበደሉንን ይቅር እንደምንል…” እያልን በእርስዎ መጣጥፍ እንደሚነበበው ጠላትነት በሚያንጸባርቁ ቃላት መጠቀም፤ ሁላችንንም ትዝብት ላይ የሚጥለን ይመስለኛል። አለመግባባት ካለም፤ ተገናኝቶ መፍትሔ ማግኘት አለዚያም በስከነ አነጋገር በይፋ መወያየት፤ ከካሕን የሚጠበቅ ተግባር አይመስልዎትም።
እባክዎ አዋርደው አያዋርዱን!!!!
አክባሪዎ፤ ብልሕነት።