የነ ፋሌቅ ወጥመድ – በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

July 7th, 2012 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ
  1. Anonymous
    | #1

    ቃል

    አ ሌ ፍ…………………..

    አስቀድሞ ቃል ነበረ የህይወት ጅማሬ አልፋ

    የጽንፈ-ዓለሙ መነሻ የፍጥረት-ህላዌ ተስፋ

    እ ና ም…………………..

    ቃል ለምድር ለሰማይ ብሎ

    በዘላለም ፍቅሩ ምሎ

    ወደር የለሽ ክብሩን ጥሎ

    ከመኖሪያው ተነጥሎ

    እውነትና ጸጋ አዳብሎ

    ሰላም ሊያዘንብ ጠብን ገድሎ

    ጠፈር ከንፎ ጋራ ዘልሎ

    ስርጉዋጉጡን አስተካክሎ

    አረምርሞ አደላድሎ

    ብርሃን ሊሆን ፍሞ ግሎ

    ሙቀት ሊሰጥ ደብኖ ከስሎ

    አዘቅዝቆ ወርዶ ቀልሎ

    አካል ለብሶ እኛን መስሎ

    እስኪገለጥ ሥጋ – አክሎ…………….

    እንዴት ይሆን ጥበቃችን-የእምነታችን ጽናት ልኩ?

    ቃልን ባካል እስክናየው እስኪገለጥ ጠርቶ መልኩ

    እንኖር ይሆን? ወይ እንጠፋ?

    እንስብ ይሆን? ወይ እንገፋ?

    ሥጋ እስኪሆን የቃል ተስፋ

    እንጠብ ይሆን? ወይ እንሰፋ?

    እናርፍ ይሆን? ወይ እንለፋ?

    እስኪገለጥ የቃል ተስፋ ?

    ደ ግ ሞ ም………………..

    ቃል በራሱ ታምኖ ምሎ

    የኛን ጉዞ ነድፎ ስሎ

    ኃይል አምቆ ብርታት አዝሎ

    ከሰገባው ተነጥሎ

    ህዋን ጥሶ የብስን ዘልሎ

    ተምዘግዝጎ ትንታግ መስሎ

    ባህሩ ላይ መንገድ ተክሎ

    በአቅጣጫችን አይኑን ጥሎ

    ወደ ወንዙ መሃል ክፍል

    ወደ ሰመጥንበት ክልል

    ወደ መርከባችን መጥቶ

    ርኅሩኅ ድምጹን አሰምቶ

    ማዕበል ገርቶ ሰላም ሰጥቶ

    ሥጋ እስኪሆን ያ-ቃል ረግቶ…………………..

    እንዴት ይሆን ጥበቃችን የእምነታችን ፅናት ልኩ?

    ቃልን በአካል እስክናገኝ እስኪታየን ጠርቶ መልኩ

    እንቆም ይሆን? ወይ እንጠፋ?

    እንወስድ ይሆን? ወይ እንገፋ?

    ሥጋ እስኪሆን የቃል ተስፋ

    እንጠብ ይሆን? ወይ እንሰፋ?

    እናርፍ ይሆን? ወይ እንለፋ?

    እስኪገለጥ የቃል ተስፋ ?

    ስ ለ ዚ ህ…………………

    በቃል ልንኖር ቃል ተልኮ

    መስሚያችንን ቀርቦ ታክኮ

    ወደ ልባችን ሥር ሊዘልቅ

    መግቢያ መንገድ ሲያጠያይቅ

    ጆሮ ዳባ እንዳንለው

    በቸልታ እንዳንጥለው

    ትንሽ ቢመስልም ቃል ዘር ነው ! ! !

    ፊት አይቶ የማያደላ

    ወቅት አይቶ የማያሰላ

    የማይጠቁር የማይቀላ

    ሲሞቀው ኃይሉ ማይላላ

    ሲበርደው የማይጣላ

    ያዙኝ ልቀቁኝ የማያውቅ

    የጥበብ የክህሎት እምቅ

    የእምነት-ጽንስ እስትንፋስ መልህቅ

    የጽንፈ-ዓለሙ መገኛ

    አያ – ቃል የፍጥረት ዳኛ

    መሆኑ ይግባን እንወቅ

    ለ ም ን ሰ ማ ው እ ን ጠ ን ቀ ቅ !

    ያ ለ ዚ ያ………………….

    ቃል ሲቃትት ሊታደገን ጆሮ ዳባ ብለን ካልነው

    እንደ ሰዱቅ-ፈሪሳዊ እንደ ጻፎች ከገፋነው

    ችሎት ፈጥረን ዋቢ ቀጥረን አስገድለን ካስቀበርነው

    ይብላኝ እንጂ ላልታደልነው ቤዛችንን ላላወቅነው

    እሱ እንደሆን በሰልስቱ መነሳቱ አይቀሬ ነው ! ! !

    ታምራት

    ከድንጋያማ ተራሮች ግዛት

    ታህሳስ – 2004 (December-2011)

  2. አ.ዪግዛው
    | #2

    በቅሲስ አስተራየ ጽጌ የቀረበውን ጽሑፍ በጥሞና አንብቤዋልሁ. ይበል የሚያሰኝ ጽሑፍ ነው. በነ ፋሌቅ ወጥመድ ውስጥ የወደቀችው እናት ቤተክርስቲያን ጉዳይ አሁንም አይን እያየ ወደ ሞላ ወንዝ ብዙውን ወገን እያሳሳቀ እየወሰደ ነው. ምናልባት የቀሲስ ጽሑፍ ጥሩ ምስገንዘቢያ ሊሆን ይችላል.

    ጥንተአብሶን በተመለከተ እስካህንም ሲስጡ የቆዩት ማስረጃዎች አንሰው አይደለም. ትልቁ ችግር ከወዲያም ሆነ ከወዲህ የሚጠቅሱት የውዳሴ ቅዳሴ ማስረጃወች, ገታን በድንግልና ጸንሳ በድንግልና
    ስለወለደች መሆኑን በሚገባ አለመገንዘብ ነው. ሰውነቱዋንም ዝቅ ማድረግና ‘ወኮነ ሰባአ ከማነ ዘእንበለ ህጢአታ ባሕቲታ’ የሚለውን መስረታዊ ትስብኣት አለመገንዘብ ነው. የኛ ዋናው የሃይማኖት መምህራችን ቅዱስ ያረድ ብነሐሴ ድጉዋው. ከሶስት ጊዜ በላይ . አንጺሖ ስጋሃ ቀዲሶ ኪያሃ ሐደረ ልእሌሃ. ይላል. ከቅዱስ ያሬድ በላይ ስለ እመቤታችን ተቆርቁዋሪ መስሎ ጥራዝ መንጠቅና ወደ ማያስፈልግ ንትርክ ውስጥ መግባት ይርሱዋን ክብር ከፍም ዝቅም አያደርገውም. የምናመስግናትና የምናከብራት በመላኩ ብስራት ተቀድሳ አምላክን በመውለዱዋ ስለሆነ ወላዲተ አምላክ ከሚለው የክብርና የግብር ስም በላይ የሚይስከብራትም ሆነ ይሚይስወድሳት አስተምህሮ ሊኖር አይችልም. ዋናው ነገር ብርሱዋነቱዋ ብህልዮም ሆነ በገቢር የፍጸመችው አብሶ የለም.

  3. Belehennet
    | #3

    ውድ ቀሲስ አስተርአየ፤

    በየጊዜው የሚያወጡዋቸውን መጣጥፎች በቅርብ ከሚከታተሉትና ከአድናቂዎችዎ ሰዎች አንዱ ነኝ። በዚህ ያቀረቡዋቸውንም ሐሳቦች በአብዛኛው በማክበር እቀበላለሁ። ግን አንድ በተደጋጋሚ የሚያቀርቡት፤ ከካሕን የማይጠበቅ፤ ነጥብዎ የቀረውን መጣጥፍዎን የሚበክል ወይም የሚያቃልል ስለ መሰለኝ፤ እንዲያስቡበት ብቻ፤ ጥቆማዬን በትሕትና ላቀርብልዎ ወሰንኩ።

    ይኸውም፤ ስለ ግለሰቦች እጅግ በሚያስጸይፍ አገላለጽ የሚያቀርቡት ሐተታ ነው። ለምሳሌ፤ በዚህ ጽሑፍዎ፤ ስለ ርእሰ ደብር አብርሃም፤ ያቀረቡት ሂስ ከተራ ስድብ የሚቆጠር፤ እርስዎን ከመሰለ የበሰለ ካሕን የማይጠበቅ ነው። እርግጠኛ እንዲሆኑ የምፈልገው፤ እኔ የርእሰ ደብር ዝምድናም ሆነ ልዩ ወዳጅነት የለኝም። ነገር ግን የቤተ ክርስቲያናችን አባል በመሆኔ፤ ካሕናት እንደዚህ በዘቀጠ ቁዋንቁዋ፤ ሲዘላለፉ ማየት እጅፍ በጣም ያሳፍረኛል። በተጨማሪም፤ ጌታችን ባስተማረን ፀሎት መሠረት፤ “……የበደሉንን ይቅር እንደምንል…” እያልን በእርስዎ መጣጥፍ እንደሚነበበው ጠላትነት በሚያንጸባርቁ ቃላት መጠቀም፤ ሁላችንንም ትዝብት ላይ የሚጥለን ይመስለኛል። አለመግባባት ካለም፤ ተገናኝቶ መፍትሔ ማግኘት አለዚያም በስከነ አነጋገር በይፋ መወያየት፤ ከካሕን የሚጠበቅ ተግባር አይመስልዎትም።

    እባክዎ አዋርደው አያዋርዱን!!!!

    አክባሪዎ፤ ብልሕነት።

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።