ነፃነት፣ ዲሞክራሲና የኢኮኖሚ ዕድገት -እንዴትና ለማን እንዲሁም ምን ዐይነት የኢኮኖሚ ዕድገት- በበፍቃዱ በቀለ

July 17th, 2012 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ
  1. በላይነሽ
    | #1

    የዶ/ር ፍቃዱን የኢኮኖሚክስ ጥናታዊ ጹሕፍ በድንብ አንብቤዋለሁ::ከግሩም የቋንቋ ኣጠቃቀም እስከትንታኔው ጭምር ሲታይ ደረጃውን የጠበቀ ነው::በእኔ ደረጃ ብዙ ነገሮችን ከአገራችን ሁኔታ ጋር ያለውን ሁኔታ የቃኜ ነው ብየ አምናለሁ::
    ዝቅ ብሎ የኢ.ህ.አ.ድ.ግን የኢኮኖሚ ፖሊሲ በመተቸም የተዋጣለት ቢሆንም ለኢ.ህ.አ.ድ.ግ ፖሊሲ ስህተት ኢ.ህ.አ.ድ.ግ ብቻውን ተጠያቂ ነው ብየ አላምንም::
    የኢ.ህ.አ.ድ.ግ መሪዎች በወጣትነታቸው ጫካ ገብተው ጠበንጃ ማጮህ ተክነው የመጡ ሰዎች ናቸው እንጂ የአዳም ስሚዝንና የካርል ማርክስን የኢኮኖሚክስ ፍልስፍና እየጨመጨሙ የመጡ አይደሉም/ምህድስና አላጠኑም::ምንም ዓይነት ዕውቀት ሳይኖራቸው በባዶ አስተሳስብ አገሪቱን ችግር ውስጥ ከተዋታል::ባዶ ምንጊዜም ባዶ ስለሆነ ባዶ አደረጉን::አንዳንዶች የተቀላቀሉትም በአምዕሯቸው ተኝተውበታል::እኛ ኢ.ህ.አ.ድ.ጎች እንዲህ ነው የምናስበው ለማለት ኮብል ስቶን ማውራት ጅምረዋል::
    ተቃዋሚዎችም ሆነ ምሁራኖች ኢ.ህ.አ.ድ.ግ ያቦካውን ጭቃ አብረው ከማቡካት በስተቀር በቡድንም ሆነ በግል ፖሊሰውን በአደባባይ በብርቱ ያስጨነቃቸው የለም::እኔ የማውቀው ዶ/ር ብርሃኑ የኢኮኖሚ ማህበር አቋቁሞ ጥሩ ሙከራ አድርጓል::አንዳንድ የኢኮኖሚም ሆነ በሌላው የሞያው ዘርፍ ያሉ ሰዎች ከዳር በመቆማቸው ምክንያት ለፖሊሰው መወላገድና ለኢ.ህ.አ.ድ.ግ ግዝፈት አስተዋጾ አድርገዋል የሚል እምነት አለኝ::
    አሁንም ቢሆን በኢነትርነት ከመልቀቅ ባለፈ በመጽሂትም ሆነ መድረክ አዝጋጅቶ ስህተቶችን ግልጽ አድርጎ ለማስተማር የሚሞክር አልሰማሁም::የአገራችን ችግር ምንጩ የውቀት ማነስ ነው::ሙሁራኖች የጋን ማብራት ከመሆን ወጥተው
    ዕውቀታቸውን ይዘው አደባባይ ቢወጡና ቢያስተምሩ ለውጤት ይረዳል::
    ማስተላለፍ የፈለኩት ከኢተርነት ወጣ ብለህ ይህን ድንቅ ጹሁፍ ልታሰራጭ የምትችልበትን መንገድ ብትፈልግ ጥሩ ነው::

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።