መነገር ያለበት ቁጥር ሁለት! በልጅግ ዓሊ
አብደላ ኦጀላን(Abdullah Ocalan) የኩርዲስታን የሠራተኛ ፓርቲ (Kurdistan Workers’ Party) መሪ ነበር። ይህ ግለሰብ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1999 ኬንያ ውስጥ ተይዞ ዓይኑ በእራፊ ጨርቅ ተሸፍኖ፣ ሁለት እጆቹ ታስረው ወደ ቱርክ ሲወሰድ በዓለም የዜና ማሰራጫ በወቅቱ ታይቷል። በአሁኑ ወቅት አብደላ በቱርክ መንግሥት የዕድሜ ልክ ፍርድ ተበይኖበት ለብቻው በአንድ ደሴት ላይ ታስሮ ይገኛል።
አብደላ ከመታሰሩ በፊት ድርጅቱን የሚመራው ከኩርድ ሕዝብና ጦር ተለይቶ ሶርያ ውሰጥ ሆኖ ነበር። የኩርዶች ትግል በጠነከረ ወቅት የቱርክ መንግሥት፣ ሲ.አይ. ኤና ሞሳድ በመተባበር ይህንን ድርጅት ለማጥፋት ይታገሉ ጀመር። በሶርያ መንግሥት ላይ ባደረጉት ተጽዕኖ ከሶርያ እንዲወጣ ተደረገ። የቱርክ ጠላት ነች የምትባለውም ግሪክ አልቀበልም አለች። መጨረሻ ኬንያ ሃገር እንዲሄድ ተደርጎ በቱርክ የደህንነት ድርጅት አባሎች ተይዞ ቱርክ ውስጥ ታሰረ። በዚያ ወቅት የሚከላከልለት ጦር፣ የሚደብቀው ሕዝብ አላገኘም። አንድ መሪ ከሚመራው ሕዝብ ከተለየ ከባሕሩ የወጣ ዓሣ ነው የሚሆነው። ከምትመራው ሕዝብ ተነጠለህ የሌላ ሃገር ጥገኝነትን አምነህ መሄድ የሚፈጥረው ችግር አንዱ ይህ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ጥገኝነት የጠየከውን መንግሥት ጥቅም እንድታስጠብቅ ትገደዳለህ። ከዚህ ሁሉ ተጽዕኖ ነጻ ለመውጣት አማራጩ ከሕዝብ ውስጥ መገኘት ነው። የምትመራው ሕዝብ ከወደደህ ይደብቅሃል። የምትመራው ሕዝብ ከጠላህ ያጋልጥሃል። ከዛስ አልፎ ከሕዝብህስ ጎን ሆነህ ብትሰዋ ከዛ የበለጠ ታላቅነት ምን አለና ነው?
በሕዝብህ ማህል መሆን ብዙ ጥቅም አለው። የሕዝብህን ችግር በሚገባ ታውቀዋለህ፣ መፍትሔውንም ትሻለህ። ለሌሎች ሃገሮች ተጽዕኖ በቀጥታ ተጠቂ አትሆንም። በሩቅ ሆነህ በድህረ ገጽ ላይ በእንግሊዘኛ ብትለቀልቅ፣ ታላላቅ ስብሰባ እየጠራህ ሳይንሳዊ ትንታኔ ብትሰጥ፣ የምትኖርበትን ሃገር ታሪክ እያጠናህ ብትጽፍ ብዙም ፋይዳ አታመጣም። የሚሰማህም ላይኖር ይችላል። ይበልጥ ትዳከማለህ። እርስ በእርስ እንደ አሜባ እየተከፋልክ ለሕዝብህ በሽታ ትሆናለህ።
ለዚህ መረጃ የሚሆንን በኢሕአፓ ይደረግ የነበረው የመሣሪያ ትግል በብተና ንቅናቄ አባላቱ ወደ ሱዳን ከተሰደዱ በኋላ ድርጅቱን ከውጭ ሆኖ ለማሰባሰብ የተደረገው ሙከራ በተለይም ከነ ጸጋዬ ደብተራው በወያኔ መታሰርና ከነ ጋይም መገደል በኋላ ሊያንሰራራ አልቻለም። በሌላ በኩል ደግሞ የቅንጅትን ሁኔታ እንደ መረጃ ልንወስድ እንችላለን። የቅንጅት እንቅስቃሴ ከተኮላሸ በኋላ በቅንጅት መሪዎች ከውጭ ሆነው ሕዝቡን ለመምራት ያደረጉት ሙከራ የበለጠ መከፋፈልን፣ የበለጠ አድርባይነትን ነው የወለደው። የቅንጅት ብቻ ሳይሆን በዚህ በጸረ ወያኔ ትግል ከውጭ ሆኖ ለመምራት የተደረገው ሙከራ ሁሉ የተለየ ዕጣ አልነበረውም።
በውጭ ተደራጅተው መታገል በሃገራችን ብቻ የተጀመረ አይደለም። በሌሎች ሃገሮችም ይደረጋል። ችግሩ ግን ከውጭ ተታግሎ ለድል የበቃ አይኖርም። በውጭ ያለው ትግል ምንአልባት በሃገር ውስጥ የሚደረገውን ትግል ያግዝ እንደሆን እንጂ ብቻውን ነጻነትን አያስገኝም። ነጻነትን የሚጎናጽፈው መስዋትነትን የሚጠይቅ የሃገር ውስጥ ትግል ብቻ ነው።
ሕዝባዊ ድል ሳይሆን ለሥልጣን መብቃት ግን ከመስዕዋትነት ውጭ ሊሆን እንደሚችል ደግሞ በቅርብ የተፈጸሙ ክስተቶች ያስተምሩናል። ሌሎች በሞቱበት፣ ሌሎች በደሙበት በመጨረሻው ሰዓት ላይ የድል አጥቢያ አርበኛ በመሆን በምዕራብያውያን ሚዲያ ተደግፈው ለሥልጣን መብቃት እንደሚቻል ግልጽ ሆኗል። ለምሳሌ ያህል የአፍጋኒስታኑ አህመድ ካርዛይ እና የኢራቅ መሪ አል ማላኪን መመልከት ይቻላል። የአሜሪካ መንግሥት ከተደበቁበት አውጥቶ ሌሎች በተሰውበት ትግል ለሥልጣን እንዲበቁ አድርጓቸዋል። ያም ቢሆን በአሜሪካ ጦር ተደግፈው ነው። የሚኖሩትም በአሜሪካ ጦር ጥላ ሥር ነው።
እነዚህ ከውጭ ተመርጠው ሥልጣን ላይ እንዲቀመጡ የተደረጉ ግለሰቦች ተመሳሳይ ጠባይ አላቸው። የራሳቸውን ሕዝብ መበደልና ለሥልጣን ያበቃቸውን መንግሥት ጥቅም ማስጠበቅ ነው ። ካርዛይ ዛሬ አፍጋኒስታን ውስጥ በአሜሪካ የጦር አውሮፕላኖች በአሸባሪ ስም ለሚሞቱት ንፁህ ዜጎቹ ለይምሰል ያህል መግለጫ ከመስጠት ያለፈ የሠራው የለም። የኢራቅ መሪዎች በየእስር ቤቶችቻው ውስጥ በአሜሪካ ወታደሮች የሚደርስውን ግፍ ደገፉ እንጂ አልተቃወሙም።
አሁን ባለው የሃገራችን የዴሞክራሲ ትግል ውስጥ ብዙ ካርዛይን፣ ብዙ አልማላኪ ለመሆን የሚያልሙ እንዳሉ ግልጽ ነው። ሌሎች በታገሉበት፣ ሌሎች በሞቱበት በአሥራ አንደኛው ሰዓት ሙሉ ልብስና ከራባታቸውን አድርገው ለሥልጣን ብቅ ማለትን የሚሹ እንዳሉ ይህንን የወያኔ ዘረኝነት ትግል ለተከታተለ የአደባባይ ምስጢር ነው። ይህንን ለማወቅ ለፈለገ ደግሞ <<የታላቅ ስብሰባ ጥሪ>> እየተባለ በሚበተነው ማስታወቂያ ላይ ከረባታቸውን አንጠልጥለው የቁንጅና ውድድር ይመስል የሚደረደሩትን ፖለቲከኞች ማጤን ነው። በፎቶው ላይ ከሚደረደሩት የድርጅት መሪዎች ብዛት አንጻር፣ የሚደረገውን ትግል ላጤነ፣ እውን ይህቺ ሃገር ይህ ሁሉ ታጋይ እያላት ነው እንዲህ በወያኔ ሕዝቡ የሚሰቃየው? ብሎ ቢጠይቅ አያስገርምም።
እነዚህ በዚህ ሃያ ዓመት ውስጥ በተለያየ ወቅት ስብሰባ እየተጠራላቸው የምነውቀውን እውነታ እንደገና በድጋሚ የሚደሰኩሩልን ግለሰቦች በአሁኑ ወቅት የመለስን <<ከዚህ ዓለም መለየት>> በሚመለከት ምን ያስቡ ይሆን? ብሎ መጠይቅ ደግሞ ወቅታዊ ጥያቄ ይሆናል።
መለስ የሥርዓቱ ቁንጮ ነውና መሞቱ ለውጥ ያመጣል ብለው የሚያምኑ ትንሽ አይደሉም። የወያኔን የዘር ፖለቲካንም ሆነ ኢሕአዴግን የሚቀበሉና መለስን እንደ ዋና ጠላታቸው የሚወስዱ ግለሰቦች ወይም ተቃዋሚ ድርጅቶች ትግላቸው ከመለስ መሞት ጋር ያከትማል። የተነሰቡበት ዓላማ ግለስባዊ ጥላቻ በመሆኑ መለስ ከሞተ ሌላ የሚዋጉት አይኖራቸውም። ስለዚህም ከወያኔ ተታርቀው ለመቀጠል ጥሩ አጋጣሚ ነው የሚሆንላቸው። የመሞዳሞድ አቅማቸውና ችሎታቸው እየታየ ወያኔ በፈቀደ ሥልጣን የሚያገኙ ይኖራሉ። ሌሎቹም ታማኝ ተቃዋሚ ሆነው የሚቀጥሉ ይገኙባቸዋል። የመለስ ተተኪዎችም ሁኔታው የተቃዋሚውን ጎራ ስለሚከፋፍልላቸው በደስታ ይቀበሏቸዋል። እነዚህ ወደ ታማኝ ተቃዋሚነት የተቀየሩ ድርጅቶች <<አሁን መለስ ሞቷልና ሰላማዊውን ትግል እናጧጡፍ>> ቢሉን የሚጠበቅ እንጂ የሚገርም አይሆንም። ከእነርሱም ጋር የትግሉ መርዘም ያንገፈገፋቸው ወያኔን ለመደባለቅ ጥሩ አጋጣሚ ይሆንላቸዋልና ትግላቸው እዚህ ላይ ሊያከትም ይችላል፡፡ይህ በተቃዋሚው ድርጅት መካከል ከመለስ በኋላ የመጀመሪውን አዲስ ክፍፍል ሊፈጥር ይችላል።
አንዳንድ የዋሆች መለስ በመወገዱ ብቻ ወያኔ ተንኳታኩቶ ይወድቃል ብለው የሚያስቡ ይኖራሉ። ያ እንደማይሆን ግን ግልጽ ነው። ምን አልባት የመለስ መሞት የሚፈጥረው የውስጥ ክፍፍልን ሊሆን ይችላል። በዚህም ምክንያት ወያኔ መዳከሙ አይቀርም። ይህንን የደከመ መንግሥት በምን ዓይነት መንገድ ማስወገድ ይቻላል? የሚለው ጥያቄ ጎልቶ ስለሚወጣ ማየቱ ጥሩ ነው። በሁለት ዓይነት መንገድ ሊወገድ ይችላል።
1ኛ. በታጠቀ ኃይል
አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የወያኔን ጦር አንበርክኮ ለሥልጣን የሚበቃ የታጠቀ ኃይል አልታየም። ስለዚህ ይህ ኃይል ተጠናክሮ ለሥልጣን ለመብቃት የመለስ ሞት ብቻ በቂ አይደለም። አንዳንድ ፖለቲከኞች በኤርትራ ተረድተን በትጥቅ ትግል ወያኔን እንጥላለን ብለው የሚያስቡ አሉ። ይህ ጉዳይ በተደጋጋሚ በተለያዩ ግለሰቦች ተሞክሮ የከሸፈ ነው። አደገኝነቱንም መጤን ያስፈልጋል።
ተስፋዬ ገብረአብ( ግብረ እባብ) የመለስ ሞትን አስመልክቶ እንደሚያቀነቅነው <<በኤርትራ የሚደገፉት ተስፋ አላቸው>> የሚለው የሻዕብያ መልዕክት እንደሆነ ማመን ይኖርብናል። ይህ ከሆነ ሻዕብያ ለተለያዩ ተቃዋሚዎች አሁን እንደሚደርገው እያስታጠቀ የእርስ በእርስ ጦርነት ለማስጀመር ይጥር ይሆናል። አንዳንድ የዋሆች ኢሳያስን አምንው ከላይ የጠቀስኩት የአብደላ ኦጀላን እጣ እንዳይገጥማቸው ነው። ወያኔ በኤርትራ በኩል ውጥረቱ ከበዛበት ሻዕብያን በጦርነት አስፈራርቶ ተቃዋሚዎች ለመረከብ ጥረት ማድረጉ አይቀርም። አሁን ባለው የኃይል መጠን ደግሞ የኤርትራ መንግሥት ጦርነት ለመግጠም ፍላጎት የለውም። የተስፋዬ ግብረ እባብ አባባል ከልብ ማጥናት ያስፈልጋል።
2ኛ በሕዝባዊ አብዮት
በአሁኑ ወቅት አብዮት በሃገራችን ሊነሳ ይችላል።የዴሞክራሲ እጦት፣ በዘር በጎሳ መከፋፈል ፣ የሃይማኖት ነጻነት ማጣት( በእስልምና ኃይማኖት ተከታይ ወንድሞቻችን ላይ የሚደረገው እንቅስቃሴ ፣ የዋልድባ ገዳም ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ እና ሌሎችም) ኤኮኖሚው፣ በነጻው ፕረስ ላይ የሚደረገው ግፍ፣ በተለይ በሕዝብ ላይ ወያኔ የሚያደርስው ቅጥ ያጣ ግፍ. . . ወዘተ . . . ከመለስ መሞት ጋር ተያይዞ ለውጥን ሊጠራ ይችላል። በሃገሪቱ ውስጥ አብዮት መነሳት ይችላል ብለን ካመንን ይህንን አብዮት ማን ይመራዋል ? የሚለው ጥያቄ ደግሞ መመለስ አለበት።
አሁን ከምንገነዘበው አብዮት ሃገሪቱ ውስጥ ቢነሳ በተቃዋሚዎች በኩል ቅድመ ዝግጅቱ እየተደረገ አይደለም። ተቃዋሚዎች ይበልጥ የሕዝብ ጥያቄ የሆነውን የኅብረት ጥያቄ በትምክህት አሻፈረኝ በማለት የድርጅትን ዝናን፣ የግል ታዋቂነትን የሚቀነቅኑ ሆነው እናገኛቸዋለን።
በአሁኑ ወቅት ተፈጠሩ የተባሉትም ሕብረቶች ወይም ጥምረቶች የይስሙላ ብቻ ናቸው። በውስጣቸውም የሚገኙት ድርጅቶች አባል የሌላቸው፣ ለመሪዎቻው ስም ማስጠሪያ ብቻ የተሰፉ ቁናዎች ሆነው እናገኛቸዋለን። እንዲውም ብዙዎቹ በሃገራችን ውስጥ ቀርቶ በሚኖሩበት ሃገርም ታዋቂነትም ተቀባይነትም የላቸውም።
አስረጅ ፡ http://ethiomedia.com/2012_report/joint_memorandum.pdf
ይህ አዲስ ትብብር ፈጠርን ብለው ከተደረደሩት ድርጅቶች ስንቶቹን ነው አጥርተን የምናውቃቸው? ስንቶቹስ በሃገራችን ውስጥ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ? እነዚህ ለቁጥር ማብዣ ሲባል የተደረደሩ ድርጅቶች ራስን ከማታለል የማያልፍ ብልጠት ነው።
በውጭ የሚገኙትን ትተን በሃገር ቤት የሚገኙትን ድርጅቶች ስንመዝናቸው በደረሰባቸው የወያኔ ጭቆናና ጠንካራ መሪ በማጣት ብዙዎቹ የተካፋፈሉና ወደፊትም ገና ከመለስ ሞት በኋላ የሚከፋፈሉ ሆነው እናገኛቸዋለን። አንዳንዶቹ ሕዝባዊ አብዮትን ለመምራት ጉልበቱም ፍላጎቱም የሌላቸው መሪዎች በውስጣቸው አሉ። አንዳንዶቹ ጥገናዊ እንጂ መሠረታዊ ለውጥም አይፈልጉም። እነዚህ ግለሰቦች አብዮቱን ከመምራት ወደ ማክሸፍ ሊሸጋገሩ ይችላሉ። ይህ አብዮትን የማፈን እንቅስቃሴ ከ 97 ምርጫ ወቅት የሙት ከተማ ንቅናቄ የተመለከትነው ስለሆነ ዛሬ አዲስ አይሆንም። የውጭ መንግሥታትና ቆራጥ ያልሆኑ አመራሮች እንዴት እንዳከሸፉት የምናስታውስው ነው። በሃገር ውስጥ ስለሚገኙ ነባር መሪዎች <<ፍኖተ ነፃነት>> ሁለተኛ ዓመት ቅጽ 2 ቁጥር 54 ገጽ 7 <<የማይጠረቃው የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትግልና የሃገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ>> —- በቀለሙ ሁነኛው ማንበብ ጠቃሚ ነው።
http://ethiomedia.com/2012_report/fnote_fifty_four.pdf
በውጭ የሚገኙትን ድርጅቶች ደግሞ ይህንን ይነሳል ብለን የምንጠብቀውን አብዮት ከውጭ ሆነው መምራት ስለማይችሉ ሃገር ውስጥ ካሉት ጋር በመተባበር ለመምራት መሞከር እንዱ አማራጫቸው ሊሆን ይችላል። ያ ደግሞ ብዙም የሚያወላዳ አይደለም። እንደሚታወቀው ተባብሮ ለዴሞክራሲ መታገልን ለሃያ አመታት አሻፈረኝ ስላሉና አሁን በመጨረሻ ሰዓትም ኅብረት ቢፈጥሩም ኅብረቱ የሚገፋ አይሆንም። ከዚህ ቀደሞ በቅንጅት እንደታየው በትንንሹም ጉዳይ እየተከፋፈሉ ሊጣሉ ይችላሉ።
ተቃዋሚዎች በራሳቸው መፍትሄ የማያመጡ ከሆነ ያላቸው አማራጭ በአፍጋኒስታን፣ በኢራቅ፣ በሶርያ እንደታየው የምዕራብያውን ቡራኬ መጠበቅ ነው። ሃገራችን ውስጥ አብዮት ከተነሳና ወያኔ መወገድ ካለበት አብዮቱን በውጭ ያሉ ድርጅቶች ተከፋፍለው መምራት የማችሉ ስለሆነ የውጭ መንግሥታት እንደተለመደው የሽግግር መንግሥት ለማቋቋም ጥረት ያደርጉ ይሆናል። በዚህ ወቅት አባላት የሌላቸው ድርጅቶቻቸውን ታቅፈው ካለ ምንም እንቅስቃሴ ራሳቸው ብቻ እያስተዋወቁ ይጠብቁ የነበሩ ፖለቲከኞች የትግላቸውን ፍሬ የሚሰበስቡበት ቀን ደረሰ ማለት ነው። በዚህ ወቅት እንደተለመደው መሪዎቹ ከረባታቸውን አድርገው ብቅ ከማለት አይቆጠቡም። ስሞኑን የሚታየው የአትርሱኝ ባይነትም የሚመስለው መግለጫም ከዚሁ ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል።
ይህ በውጭ መንግሥታት የሚደረገው ጥረት ከተሳካ ድርጅቶቹ የተከፋፈሉ ስለሆኑ የአንዱ ድርጅት መሪ እንደ አማራጭ ለሚፈጠረው ኅብረት መሪ መሆን ችግር ሊፈጥር ስለሚችል የድርጅት አበል ያልሆነ፣ ከማንም ያልወገነ ግን በፓለቲካው ጎልቶ የሚታይ ምሁር ሊያስፈልግ ነው ማለት ነው።
እዚህ ላይ ነው የሚቀጥለው የኢትዮጵያ ካራዛይ ማነው? የሚለው ጥያቄ የሚጀምረው።
እንደ አፍጋኑ መሪ ካርዛይ በእንግሊዘኛ የጎለበተ፣ የአሜሪካንን ታላቅነት የተቀበለ፣ የእነርሱን ባሕል የወረሰ ቢሆን ደግሞ አሜሪካኖች ስለሚያስደስታቸው ምርጫቸውን ያውቁታል ማለት ነው። እሁን ከምናየው አንዳንድ ምልክቶቻቸው ቀደም ብለው የተዘጋጁበት ይመስላል።
ዛሬ በዚህ ትግል ውስጥ ካርዛዩች ትንሽ አይደሉም። እነርሱ ባልሞቱበት፣ እነርሱ ባልቆሰሉበት፣ እነርሱ ባልታሰሩበት የይስሙላ ድርጅት እያቋቋሙ በሕብረት ስም ወደ ሥልጣን ለመጓዝ የሚደረገው ጥረት በዚህ ሃያ ዓመት ውስጥ የኋልዮሽ ግልቢያ እንጂ የረባ ትግል አላሳየንም። ይህንን ትግል አሽመድምደው የወረቀት ላይ ነብር ያደረጉት በባዶ ለስልጣን የቋመጡ ብኩን የይስሙላ ድርጅት መሪዎች ናቸው።
ግማሾቹ ትግሉን ሳይጀምሩት የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ከውጭ መንግሥትታት ይጠይቁ ጀምረዋል። የሃገራቸው ሕዝብ የትግላቸውን ጥረትና ውጤት ተመልክቶ እውቅና ሳይሰጣቸው በውጭ መንግሥት ቡራኬ ለማግኘት ጠዋት ማታ የአሜሪካንን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤትንና እጅ መንሳት ከተጀመረ ሰንበትበት ቢልም ሰሞኑን መለስ ታመመ ! መለስ ሞተ ! መለስን ማነው የሚተካው ? የሚለው ጥያቄ መንገዋለል ከጀመረ ጀምሮ ደጅ ጥናቱ እንደጎላ እየተሰማ ነው።
ይህ ግን የኢትዮጵያን ሕዝብ ነጻ አያወጣውም። በአፍጋኒስታን፣ በኢራቅ፣ አሁንም በሶርያ እንደምንመለከተው ከሕዝብ ችግር ተለይቶ፣ ለውጭ ባሕል ተገዝቶ፣ ለውጭ ሃገር ታላቅነት የሚሠራ መሪ የሃገራችንን ገበሬ ልጁን እየነጠቀ ወደ ሶማሊያ በመላክ ያስገድልበት እንደሆን እንጂ ችግሩን አያቃልለትም። ለሠራተኛውም ቢሆን ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች የሚቀርብለት ጥያቄ ለመመለስ ያህል ከሥራ ያባርረው እንደሆን እንጂ መብቱን አያስጠብቅለትም። በኢራቅ እንደተመለከትነው አዳዲስ እስር ቤቶች ያሰራ እንደሆን እንጂ ያሉትን አያፈርስም። በሊቢያ ፣ በሶርያ እንደተመለከትነው በዘር፣ በሃይማኖት ከፋፍሎ ያጋድል እንደሆን እንጂ ከወያኔ የግፍ አገዛዝ አላቆ ዴሞክራሲያዊ ሃገር አይመስርትም።
ለዚህ ሁሉ መፍትሄው አንድ ነው። በሃገራችን ውስጥ ያሉ ፖለቲከኞች የወቅቱን ሁኔታ በመገንዘብና፣ ከቀን ወደ ቀን ሕጋዊ ሆኖ መንቀሳቀሱ አደገኛነቱን በማጥናት፣ ሌላ ዘዴ ዛሬውኑ መተለም ይኖርባቸዋል። እየተዘጉ የሚገኙትን ጋዜጦች የሚተካ የህቡዕ ጋዜጣ ማዘጋጀት አስፈላጊ ነው። ልንተማመንበት የምንችለውን ሕዝብ በሕቡዕ ማሰባሰብ አስፈላጊ ነው። በሕዕቡ ሆኖ የሕዝብን አብዮት መምራት የሚቸል ኃይል እዛው ሃገር ውስጥ መቋቋም ይኖርበታል። ተዘጋጅተን ከጠብቅን ብቻ ነው ገዥዎቻችንን ሌሎች የማይመድቡብንና መሪዎቻችንን ራሳችን የምንመርጠው ፣ ስንደራጅ ብቻ ነው ወያኔን የምንጥለውና የሚቀጥለውን መንግሥት የሕዝብ የምናደርገው። ሕዝብ መሃል ስንሆን ነው የሕዝብን ችግር የምረዳው።
<<ይህ ሃገር የኛም ነው>> በሚል መፈክር እዛው ሃገራችን ውስጥ የሚፈጠር እንቅስቀሴ እንጂ ፣ ሙሉ ልብስና ከረባትን አሳምሮ በዓለም ታላላቅ ከተማዎች ውስጥ የሚደሰኮር (ከፍትህ አምደኛ በድሉ ዋቅጅራ ይህንን ቃል ልዋሰውና) አማርዝኛ (አማርኛ + እንግሊዝኛ ) መፍትሄ ያመጣል ብለን ማመንን ከሃያ ዓመት በኋላ ማክተሙን ካላመንን መቼ ልናምን ነው።
በውጭ የሚገኘውም ኢትዮጵያዊ ከወያኔ ጥርስ ተናክሰው ዛሬ በየእስር ቤቱ የሚማቅቁትንና የሚታገሉትን በተቻለው መጠን መርዳት ሲገባው፣ ለሚቀጥለው ካርዛይነት ለሚታገሉ ባለ ከረባት የፖለቲካ ተንታኞች ዲስኩራቸውን የሚያሰሙበት ምርጥ አዳራሽ ፣ የአውሮፕላን ቲኬትና ምርጥ መኪና ማዘጋጀት መቼ ነው የሚያከትመው። እነዚህ የየስሙላ ታጋዮች ትተን ስለ ሃገራቸው በማሰብ እውነትን በመጻፋቸው በእስር ቤቱ ለሚማቅቁ ጋዜጠኞች ቤተሰብ እርዳታን ስናደርግ ብቻ ሌሎች ቆራጥ ታጋዮች እንዲፈጠሩ የምናበረታታው። በዚህ መንገድ ነው በእነዚህ ቆራጥ ታጋዮች የበሰለና ሃገራችንን ነጻ የሚወጣ ድርጅትም የሚፈጠረው፣ መከራችንን በቅርብ የሚያከትመው።
ጎበዝ እውነተኛ ትግልን ከፈለግን፣ የተቃዋሚ ድርጅት መሪዎች ድክምታቸውን መነገር አለበት። ሃያ አመት ኪሳችንን እያራቆትን፣ ተስፋ ባለ መቁረጥ ታገልን። ያገኘነው መከፋፈልልን፣ የባሰ ተስፋ መቁረጥን ነው። ከአሁን ወዲህ ግን << ይህ ሃገር የኛም ነው >> ብለው መከራን ከሚቀምሱት ጋር አብረን መቆም አለብን። በውጭ የሚገኙት ባለ ከረባቶችም ከዚህ በፊት በታሪክ እንዳየናቸው የኢትዮጵያ ቆራጥ ልጆች ወደ ሃገራቸው በሕብዑ በመመለስ ሲታገሉ ብቻ ነው ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉትና ሃቀኛ መሪዎቻችን የሚሆኑት። ይህንን ደግሞ ልንነግራቸው ይገባል።
ዛሬ ሃገራችን ካለችበት አደገኛ ሁኔታ አንጻር ከውጭ ብቻ ለውጥ ለማምጣት የሚደረገው ትግል መቆም አለበት። ሕዝብ በውጭ ያሉ ድርጅቶች አንድ ቀን ነጻ ያወጡኛል ብሎ በተስፋ መጠበቅን አቁሞ እዛው ሃገራችን ውስጥ መፍትሄ መፈለግ የሚጀምረው እነዚህ የይስሙላ ድርጅቶች ሲያከትሙ ነው። በእነዚህ የይስሙላ ድርጅቶች ከርሰ መቃብ ላይ ሃቀኛ በሕዝብ ውስጥ ያለ ድርጅት እንዲመሰረት መታገል የሁላችንም ዓላማ መሆን አለበት።
እነዚህ የይስሙላ ሥልጣን ናፋቂ ድርጅቶች በሃገራችን አብዮት ቢነሳ አደገኝነታቸው የጎላ ነው። የኢትዮጰያ ሕዝብ እንደ ግብጽ ሕዝብ አንድ ላይ ሊቆም ይችላል። ግን አሁን ያሉት እርስ በእርስ በመጣላት የቆሰሉ ተቃዋሚ ድርጅትቶችና መሪዎቻቸው በአንድ ላይ ይቆማሉ ወይ? በአሁን በምናየው ሁኔታ ከሆነ ደግሞ በፍጹም እንደማይስማሙ እርግጠኞች ነን። ምንአልባትም የኤርትራን ዓላማ ለማስፈጸም የተነሱ ብዙ ስላሉ አብዮቱን ወደ እርስ በእርስ የጦርነት አውድማ ለመቀየር የሚጥሩም አይጠፉም።
ቀኑ ዛሬ ነውና ሃገራችንን በጠላቶቿ የተዘጋጀላትን ጥፋት ለመከላከል ከድርጅት ጎጆ በላይ ማሰብ ያስፈልጋል። በሚሆን በማይሆነው የተከፋፈሉ ድርጅቶች ይህንን ጥፋት ተመልክተው ቅራኔዎቻቸውን ለማስወገድ መጣር ይኖርባቸዋል። ይይስሙላ ድርጅቶች መክስም ይጠብቅባቸዋል ። . . . እነዚህና የመሳሰሉትን ካላደረግን በታሪክም ተወቃሽ ስቃያችንም የበዛ ዜጎች ሆነን እኖራለን ።
Beljig.ali@gmail.com
ይህች ሃገር የሁላችንም ነች !!!
ስለ ሃገራችን የሚያስብ ሁሉ ሰላም ይክረም!!!
በልጅግ ዓሊ



ቁጥር አንድ ጥሩ ጽሑፍ እንደሆነ በመተማመን እንደተለመደው ይህኛው እጅግ በጣም ግልጽ,መካር,አሳሳቢ,አስተማሪም ሊሆን የሚችል ጥልቀት ያለው የበሰለ የተለያዩ ተሞክሮዎችን ያገናዘበ በመሆኑ መነብብ,ማጤን,መረዳት,መመካከር,ማስረዳት የሚያስፈልገው ነጥብ በመሆኑ ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገን ለነገው ትውልድ እንዴት ጠብቆ በሰላም የፖለቲካ ሽግግር ብቻ ሳይሆን የትውልድ ጤናማ ሽግግር ማድረግን ያስትምራል(…) ይታሰብበት! ይመከርበት!አደራ እንላለን !!!!
ኢትዮጵያ እጆቿን ዘርግታ የተበተኑ ቅን አሳቢ ልጆቿን ትሰበስባለች!!
ሰላምና ጤና ለመላው ሕዝባችን ለሀገራችን አንዲት ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ይሁን !!
መነበብ, መደመጥ እና ግንዛቤ ማግኘት ያለበት አባባል!! ከመጀመርያ እስከ መጨረሻ ከባድ አስተውሎን ያዘለ ነጥብ!!
Well reflected!!
your comment is not positive that carries the woyane various. you said many times about ties.what do you want say. are you interesting to insult some body. I do not know your objective and is not clear to me.please stop write such stupid killer of the moral of unite poetical organization leader.They have an objective to freedom Ethiopia from the Aprtide woyane system. I am sure you knon “unite is power” so please try to advice and write a good thing how to step down TPLF in order to esablish justice and freedom in Ethiopia for all people.Thank you.
ትክክል ብለሃል
ትክክል አንዳንዱ ቢያጋንኑትም ትቃዋሚ ነን የሚሉት አንድ ካልሆኑ ስሚ የላቸውም ህዝቡ ተነስቶ ወያኔ ቢያስወግድ እንኩአን የራሱ መሪ ነው የሚፈለግው አሁንም ግን አማራጭ የሌለው መንገድ አንድ ምሆን ንው:: ጆሮ ያለው ይስማ እውነትም የህገር ፍቅር ካላቸው ዛሬ ይጀመሩ::
You are a good cometator good job
አቶ ቤልጅግ አስተያየትህ ክፋት የለውም።ብዙ ግዜ የምትጽፋቸውንም አነባለሁ።ሁሉም ደህና ነው።የልወደደኩት ነገር ቢኖር ተስፋየ ገ/አብን እንዲህ ጥምድ አድርገህ የመያዝህ ሁኔታ ነው።ምንው ጃል ምን በደለህ ? እርሱ የሂሊናውን ጩኽት አድምጦ ነው ስደትን የመረጠው።እንደ በረከት ስምኦን ሂሊና ቢስ ቢሆን ኑሮ እርሱ አልነበር እንዴ “መለስ አልሞተም ብሎ” ይሞግተን የነበረው።የወያኔ ግፍ በዛ ብሎ ነው ስደትን የመረጠው።የእኔ እምነት እርሱ ነው።ተስፋየ ካንተ በላይ ለኢትዮጵያ ዋጋ የከፈለ ይመስለኛል።ኢትዮጵያዊነቱንም ይወዳል።ገና አገሪቷ ነጻ ስትሆን ደብረ ዘይት ሂዶ ስለቀያዮቹ ዛፎች ይጽፋል።እኔም ጽሁፍን አነባለሁ ያን ግዜም ደስ ይለኛል።ተስፈየን እግረ እባብ ማለትህ ምንም ትርጉም የሌለው ባዶ ስድብ ነው።
አሁን በቃኝ።እንዳልከው ስለአገራአችን ደጉን የሚያስብ ሁሉ በሠላም ይክረም።
ጥሩ ጽህፍ ነው. በርታ አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች ግን የተስፋዬ መሰሪ ባህሪ አልገባቸወም . የመጨረሻ መፍዘዝ ካልሆነ ይህ እንዴት ይጠፋቸዋል???????????????? አንደኛ ደብረዘይት ይደግ እና ይኑር እንጂ ኤርትራዊ ነው. የኢሳያስን እብዱ አጀንዳ ይዞ የሚንቀሳቀስ ነው ኢሳያስ ኢትዮጲያ ውስጥ የዘር ፍጭት እንዲነሳ ይፈልጋል ለዚህም ነው በኦሮሞ ህዝብ ላይ እና በአማራ ህዝብ ላይ አልስፈላጊ ነገር ፈጥሮ እና አጋኖ ሲቀባጥር የነበረው የሚያመጣውን አደጋ እያወቀ ነገር ግን አልተሳካለትም አይሳካለትምም እና ተስፋዬ እባብ ብቻ ሳይሆን ኮብራ እባብ ነው ያውም.
habibe & Anonymous #7,
የናንተን አባባል አነበብኩና, ምናልባት የበልጅግ ዓሊ ጽሑፍ የሆነ አይነት ስህተት ይኖረው ይሆን እንዴ, በማለት ፅሑፉን እንደገና ሙሉ ለሙሉ አነበብኩት:: ግን ምንም ስህተት ላገኝበት አልቻልኩም:: እንዲያውም ተስፋ ሰጠኝ:: ለካስ አእምሮ ያለው ኢትዮጵያዊም አለ ብዬም ትንሽ ተረጋጋሁኝ!!:
No more trash things please, write only such articles like this one! Well done በልጅግ!
ato belejig,
shame on you, i am tired of reading destructive message that is written by eprp and other anti opposition elements,abugida for god sake dont post a non articles that is written by these destructive power and money monger individuals who are not different from weyane, shame on you the writer
አቶ በልጅግ በምታቀርበው ሃሳብ በትንሾቹ ብስማማም ብዙዎቹ በስህተት የተሞሉ ናቸው::መተባበር:በአገርቤት እንቅስቃሴ (ትግል)መኖር አለበትና የታሰሩትን ቤተሰቦች መርዳት አለበት የሚሉት ሃረጎች ብቻ ትክክል ናቸው::
አብደላ የኩርዱ መሪን ምሳሌ አንስተሃል::የአብደላ ድርጅታዊ መዋቅር ትክክል ነበር::ወታደርዊ ክንፉ አገሩ ላይ ሁኖ ፖለቲካ ክፍሉ ውጭ ይንቀሳቀስ ነበር::ይገባና ይወጣም ነበር::በፈጠረው ታክቲክ ስህተት አደጋ ላይ ጣለው::የትም ቢሆን ማምለጫ አልነበረውም::በዚህ የሰጠኽው ሃስብ በር ዝጋና ተቀመጥ ነው::
ለአገራችንም ፖለቲከኞች የፖለቲካ መሪዎቹ ውጭ ሁነው ወታደራዊ ከንፉ አገር ቤት መሆን ነው የሚያዋጣው::ዘመኑ የፈጠረው ቴክኖሎጂ የለት ተለት ስራ እቅዶቹን ለመገምገም ችግር የለውም::የአለህበትን ዘመን ግንዛቤ ውስጥ አስገባው::
ኢ.ህ.አ.ፓን ምሳሌ ጠቅሰሃል::ይህ ድርጅት ከአወቃቀሩ ጀምረህ ተመልከተው::
ሲመሰርት 98%የተማሪዎችና የመምህራኖች ድርጅት እንጂ ሁሉን አቀፍ አልነበርም::በወታደሮች ድርጅት ኢ.ሰ.አ.ፓ በከተማ ሲመታ በትግራይ ተጋዳልይ ትንሽ ተማሪዎችና የገበሬ ወታደሮች የተመታ ድርጅት ነው::
ኢ.ህ.አ.ፓ ለሶሻሊዝም ሲታገል ወያኔ ዘረኝነትን ለማንገስ የታገሉ እንጂ ለኢትዮጵያ ህዝብና አገራቸው የሚታገሉ ስለአልነበሩ
ሶሻሊዝም ሲሞት አብረው ትግላቸውን ገደሉ::ዝነኛው ፖለቲከኛ ልደቱ አያሌው ድንጋይ 40 አመታት በውሃ ውስጥ ቢኖር አርስም እንዳለው የዚህ ድርጂት አወቃቀር በምሳሌነት የምጠቅሰው አይደለም::ስህተቱ አገርቤት በመሆንና በአለመሆን ባቻ የሚወስን ሳይሆን በዕውቀት ላይ ያልተመስረተ የግርግር ድርጂት ነው:: ምኑንም አጨብጠውም::
አገርቤት ያሉትን ድርጅቶች ምክር ለመስጠት ሞክርሃል::የተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ አትሁን::በየት? እንዴት?መቸ?የሚሉትን አጢናቸውና ስህተትህን ታውቃለህ::
በሌሎች ድርጅቶች ፈረስመቃብር ስትል ምን ማለትህ ነው?ጥላትህንና ወዳጅህን ለይተህ ከጎንህ ለማሰለፍ ምን ጥረት አድርገሃል?
ተስቀለ ሲሉኝ በልጅጉ ነው ብዬ:
ለካስ በላይ ኖሯል ትልቁ ሰውየ::
የሚለውን ሙዚቃ እየሰማህ አስብ::
@ደረጀ
Hello, Mr. or Madam. Habibe. You are really, really selfish. Your writen text reveals you are like a dog who has sit infront its lord gate that it has been barking like a dog or like a tiger or sometimes like a lion when strange one has come or has expressed its love when its lord has come in different action, with a dog action. What the writer says? Was that not true the things that was happend and is being happend in the other countries, people, and indvidual person mentioned in his text? Everything what has been mentioned are perfect and true. Wether you believe or not that is your problem and lack of information of knowledge. The truth can never be changed. It is already happened. He expelained about our futur and politics based on the mentioned contries, peoples and individual persons experience.
Are you the member of Ginbot 7 or any other unworthy political group? Let me tell you one thing if you are that. I am living in one country. I know all Ginbot 7 political members in this country. Some of them have got the resident visa; some are in the refuge status. One of them changed his nationality; he denied his country, people. Because this man wants to be appointed one day in one position when Ginbot 7 come to power, he is trying to be a doctor with out any ability by going to school one Sanbath in a month or in two weeks like he had done for his bachlor and master. He is the executive of the Ginbot 7 money colectors in the country. His friends are doctors only, as he speaks. He came to this country because of his uncle. He has facked his uncle wife. He and the hore and his friends cooperated and rejected his uncle from the party member when it was known by the name KINIJIT. He, she and some other friends have been trying to recurite the members for ginbot 7 when the new assylum seekers come to this country from Ethiopia. What does it mean? If the writers says Ginbot 7 in his written text to answer for your question, what do you say? Even me I did realiz in the recent days from other Ethiopians. To day nobody wants to be the member of Ginbot 7 in this country.
To be a politicaian moral is the main thing to be inquired. How do you think about people, those who never control and lead their own motive in the right way; I mean do you think they can lead the country? Ginbot 7 is full of that kind of orgainzation. So, waht do you say Mr. or Madam, the member or the leader of that kind of orgainzation or itsown.
You have to know one thing if you want to be the politician develop the selfconfidence and try to be genuine and do not try to make such kind of dialogue based on your own compound. You may not know what is going on in other compound in the same area. Therfore, if some body wants to say some thing about the compound, you sould make sure the man speaks concerns about.
have a good day.
@Anonymous
Ato anonymous the truth is the truth. This man mentioned the truth that Tsfaye G/kidan has done. Why do you want to cover it up. Because we have had a bad custom to cover this kind of truth we have come to be a den for some foxes who has woren the sheep fur. He did not say about Tesfaye G/kidan, but he did mentioned what he did or what he did say in his life. This is true. If we are not mentioning some kind of experience how can we learn and shape our future. This is the old style. Those who want to come to power like Hamid Karzay do not like to hear the bad deed of the past of theirown and some other friends or they know. This is the old fashin. Our country need the pure generation for change. we need the change. we need the cange.
Sober analysis of the state of affais of Ethiopian politics. Well meant and articulated.
God bless you! Paper tigers, opportunistic, parasitic and do little Diaspora elite poised to snatch power at the expense of poor Ethiopians willing to Sade blood and tears.
If so, what makes different from the 1974 Ethiopian revolution is that talkative Starbucks cupuccino muggers will replace the role of junior army officers from the fox dens.
Never repeat the injustice made to jerks and heroine of our nation after the defeat of Italian invaders if we aspire to see a democratic, united and strong Ethiopia.
Good day.
Correction (My applogies):
please read the fifth line from the bottom as heroes and heroines of Ethiopia.
በላይነሽ ድምቅ ያለ አስተያየት ነው የሰጠሽው::
ተሳሳተ ቢሉኝ ሌላ ሰው ነው ብዬ:
ለካስ በልጅግ ኑሯል ትልቁ ሰውዬ::
ብለሸው ቢሆን ያማረ ይሆን ነበር::
የበልጅግ ሃሳብ እንደአህያ እርሻ ላይ ታች እየረገጠ እውነትንና ስህተተን እያቀላቀለ የወረደ ቢሆንም በበላይነሽ ጥሩ እርምት ተስጥቶታል::ዘመኑን ተመልከት ያለችውን ስናስብ ሌሎቹ የታገሉበት የቴክኖሎጂ ምጥቀት ልዩነቱን ተመልከት::
አቶ በልጅግ መጫጫርህን አታቁም በርታ::
Well done Belgig. I say my hero of the truth and balanced information. This generation wants to see this kind of analysis and the man with it. Keep it up man. Many Hamid Karzai lusts to replace Meles. These kind of people forget one thing that if they want to be Hamid for Ethiopia, Meles is better than them in the eyes of US. This people scare to hear the truth, because they do have many rug things in theirown background. They are sick and shever when they hear something to be said. If people be aware and can look things in different corner angles, they are able to find idea and make action for the best solution. In which history anybody can see that the truth killed others, the mass. The truth is the world is full of the true story that the false and the father of liars has been killing the mass. At east, we have to develope something special beyond our little and narrow thinking and understanding, if we do have idea that we care about Ethiopia and it’s people.
God incourage some of us to heat the truth. God bless us and Make us better than the tyrant TPLF. God keep our future geverners to hear their mistakes and to ask excuse what they did and they may do infront of their people. God bless us, the ordinary people to accept ourselves as we are and to be honest and to be truth. God bless us to make harmony for the change of our country and innocent people. God keep the orthodox church patriarch Aba Pawlos soul. God bless you all. Than you.
My apology; the phrase ” heat truth” would be read as “hear the truth.”