የሰብአዊ መብት ክብር ቀን በኢቲዩዺያዉያን

August 16th, 2012 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ

በመላዉ አለም ለሚገኙ ለሃይማኖት አባቶቻችንን እና ለሃይማኖት ቤቶች አስተዳደር

ጉዳዮ፦ የሰብአዊ መብት ክብር ቀን በኢቲዩዺያዉያን

ከላይ በርዕስ ለመግለፅ እንደተሞከረው ሀገራችን ኢትዮጲያ በተለያዬ ጊዜያት ከሚነሱት መንግሥታትና የራሳቸዉን አገዛዝ እድሜ ለማራዘም በሚፈጥሩት አስተዳደር ምክኒያት አብዛኛዉ የህብተሰብ ክፍል የተገባዉን የዜግነት መብት ካለማግኘቱም በላይ ላለፉት 40 ዐመታት በተለይም በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ቁጥር ዛሬ ለሃገሪቱ የለዉጥ ሀይል ሊሆኑ የሚገባቸዉ የሃይማኖት መሪዎች ፣ የተማሩ ዜጏዎችዋን እና የሃገሪቱ ሃይልና ጉልበት የሆኑትን ወጣት ልጆችዎን በአገሪቱ ዉስጥ ባለዉ ብልሹ አስተዳደር በሚደረጉት ግድያና እስራት እንዲሁም በስደት የምታጣ የአለማችን ግንባር ቀደም ሀገር መሆንዋ ለማንም የተሰወረ አይደለም። ከዚህም በተጨማሪ ለዘመናት በዋናነት በሃገራችን ዉሰጥ እርስ በእርሳቸዉ በእርቅና እና በሰላም በህብረተሰቡ መሀከል በመቆም ለዘመናት ህዝቡን አከባብረዉ የኖሩትን ለሃገራችንም አንድነት ከፍተኛ ሚና የተጫወቱትን ለሌሎችም ሃገሮች እንደ ምሳሌ የሚጠቀሱትን የሃይማኖታችንን እሴት በአሁኑ ወቅት ያለዉ አገዛዝ እድሜዉን ለማራዘም ይህን ለዘመናት በሃይማኖት አባቶችና በዜግዎችዋ የተጠበቀዉን እሴታችንን እያፈረሰ ተቓማቱን የፓለቲካ ተቓም በማድረግ ሃገሪቱን የማስተዳደር ስልጣኑን ከወሰደ ጀምሮ በአንደኝነት ይሰራዉ የነበረ አሳዛኝ ስራ ይኸዉ 21 ዐመቱን ይዝዋል። ለዚህም አሳዛኝ ሰራዎቹ የሃገራችንን ዳር ድንበር ለማስከበር እና የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የህብረተሰቡ አካል በሆኑት የሃገሪቱ የፗሊስና የጦር ሃይሎች በተለያዬ የሃገሪቱ ክልሎች እንዲሁም አብያተ ክርስቲያኖች እና በተለያዬ መስጊዶች በሰላሚዊ ዜጎች ላይ የተደረጉት ኢሰብዓዊ ዘግናኝ ድርጊቶች ዛሬም ከእኛና ከልጆቻችን አእምሮ አልተዘነጉም።

በመላዉ አለም የሚኖሩ ኢቲዩዺያዉያን ዐርብ ነሐሴ ፲፩ (August 17, 2012 ) በየመስጊዳችን ለሃያሉ ፈጣሪያችን አላህ ዱአ በማድረግ ፤ እንዲሁም እሁድ ነሐሴ ፲፫ ቀን በየቤተክርስቲያኖቻችን ( August 19,2012) በፀሎትና በምልጃ ወደ ህያዉ እግዚአብሔር በመቅረብ የዜግነት መብታቸዉን በሃይል ተገፈዉ በእሰር
ቤት የሚማቅቁትን ወገኖቻቸዉን በማስታወስ እየተባባሰ ያለዉን የሰብአዊ መብት ረገጣ በማስብ የሰብአዊ መብት ክብር ቀን በኢቲዩዺያዉያን የእምነት ቤቶች እንዲያደርግ የእምነት አባቶችን እና አስተዳደሩን በማክበር እየጠየቅን የሃይማኖት አባቶችም የፈጣሪ ፈቃድ ለተጎዱ ማዘን ለተቸገሩ መርዳት ፍርድ ለተጋደለባቸዉ ፍትሕ ማሰጠት ሰለሆነ ምእመናኑ የወገኖቹን ለህዥባቸዉና ለአገራቸዉ ሲሉ የሚደርስባቸዉን መከራ ችላ እንዳይሉ ያሳስባሉን ዘንድ የሃይማኖት አባቶቻችንን እና አስተዳደሩን በማክበር እንጠይቃለን።

ለተጨማሪ መረጃ
(202) 656 8070
joinus@march4freedom
www.march4freedom.com
ወይም
(703) 498 5200
nejashijustice@gmail.com
www.nejashijustice.org

የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች ምክር ቤት በዋሽንግተን
Ethiopian Christian and Muslim Council supported by March4Freedom, and Nejashi Justice Council

አስተያየት መስጫው ተዘግቷል።