ኦነግና ተቃዋሚዎች በእውኑ ሕዝባችሁን ታውቃላችሁን? ይነጋል በላቸው
ይሄን ሰሞን የነካኝን እንጃ ተጣላ ተጣላ ብሎኛል፡፡ ምን እሆናለሁ? መጣላቴ ግድ ከሆነ ልጣላ – ዕርቅ አለ አይደል? እንደለመድኩት ልክ ልኬን ሲያቀምሱኝ ብዕሬን እሰቅልና እገላገላለሁ፡፡ ከዚያ ዕርፍ! ባቄላ አለቀ ስንቅ ቀለለ ነው ተረቱ፡፡ ወደዛሬው መጣጥፌ ከመግባቴ በፊት በሰሞኗ ጽሑፌ አንዠታችሁ ‹ቅቤ የጠጣም› ያልጠጣም የተበሳጫችሁም ያልተበሳጫችሁም – በተለይ የምለውን ሁሉ እንደግል ጥቃት ያህል በመውሰድ ‹አንት ‹ፋንድያ› እያለ ከምሩ እየተናደደ ውድ ስድቡንና ዘለፋውን የሚልክልኝና የሚያስቀኝ ወዳጄና በኢሜይል አድራሻየ ትችትና አድናቆታችሁን የላካችሁልኝ አንባቢያን ሁላችሁም ምሥጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡ ጎበዝ – ለማንኛውም ግን ስድብ አይለጠፍምና ከስድብ ይልቅ ለቁም ነገር ቅድሚያውን እንስጥ – በበኩሌ እንደፈንጣጣ ስለወጣልኝ እስቅ እንደሆነ እንጂ በጭራሽ የሚሰማኝ ነገር የለም፡፡
ግራሃም ፒብልስ የተባለ በሀገረ እንግልጣር የአንድ በጎ አድራጎት ድርጅት ዳይሬክተር ስለኢትዮጵያውያን መሪዎች ምሥጢራዊነት የጻፈውን የዜና ትንታኔ አሁን አንብቤ ጨረስኩ – ከኢትዮሚዲያ ድረ ገፅ፤ አንተ አብርሃ እጅህን ቁርጥማት አይንካው – ተባረክ(ውሸቴን እንዳይመስልህ!)፡፡ ዘሃበሻንም ያላነበብኩ እንዳይመስላቸሁ፡፡ ይቺ ድረ ገፅ ግን እንዴት ነው እንዲህ እሳት እየሆነች የመጣችው ጃል? ሳላውቃት ኖሬ እንዴት ቀርቶብኝ ኖሯል! ትደግልን፤ ትመንደግልን፡፡ የየሰዓቱን ዜናና ሀተታ በወቅቱ እያቀረቡ ሕዝብን ያለ አንዳች አድልዖ ማገልገል እንደዚህ ያስወድሳልና ይህ ምግባር እምብዝም ባልተለመደባቸው የሚዲያ ማዕከላትም ተስፋፍቶና ተጠናክሮ እንዲቀጥል እየተመኘሁ ወደጀመርኩት ሃሳብ ልሂድ፡፡ ‹አንዳንድ ሥፍራዎች፣ ጥቂት ቦታዎች…› የሚለውን የሜትሮሎጂ ጥንቅር ለወጥ አድርጌ ‹ብዙዎች ሰዎች፤ አንዳንድ ዜጎች…› የምለው እንደነሱው በቂ መረጃ ከማጣት የተነሳ መሆኑን ዕወቁልኝ፡፡
ብዙዎች ኢትዮጵያውያን ስለሀገራቸው ሁኔታ ቅንጣትም አለማወቃቸው ብቻ ሳይሆን ለማወቅም ፍላጎት የማያሳዩበት አዝማሚያ እየተበራከተ ባለበት በዚህ ፈታኝ ዘመን ስለኢትዮጵያ የሚጨነቁና ጭንቀታቸውንም በሚዲያ የሚገልጡ እንደግራሃም ፒብልስ (ግራሃም ሀንኩክንም አንርሳ) ያሉ አንዳንድ አስተዋይ የዓለም ዜጎችን ማግኘት ያስደስታል፤ የእኛነታችንን ማንነትም እንድንጠይቅ ያደርጋል፡፡ ይህ ለየት ያለ አጋጣሚ የሚያሳየን ምንም እንኳን እኛ ኢትዮጵያን ብንተዋት ፈጣሪና ፍጡራኑ የማይተዋት መሆናቸውን ነው፡፡ ‹በትውልድ እንግሊዛዊ፣ በምርጫ ግን ኢትዮጵያዊ› ያሉትን የሪቻርድ ፓንከረስት ቤተሰብም እናስታውስ፡፡ የዛሬውን አያድርገውና ኢትዮጵያን ከልባቸው የሚወዱና ቤት ንብረታቸውን ነቅለው ወደዚህች ቅድስት ሀገር(እንዳሁኑ ሳትረገም) የተሰደዱ የዓለም ዜጎች በርካታ ነበሩ፡፡ ዐረቦች በየጓሯቸው ነዳጅ እያወጡ እንዲህ በፔትሮ ዶላር ሳይናጥጡና የተቀረው ዓለም ላይ በጥጋብ እንትን እንበል ሳይሉ ኢትዮጵያ ነበረች መጠጊያቸው – ‹ሱቅ› ለማለት ‹ዐረብ ቤት› የምንለውን ስማዊ ጥምር-ቃል ልብ ይሏል፡፡ ያ ዘመን ይመለሳል!! መጽሐፋዊ ብሂሉም ‹ፊተኞች ኋለኞች፣ ኋለኞችም ፊተኞች ይሆናሉ› ይላልና ብዙም ተስፋ አንቁረጥ፡፡
ፒብልስ በጽሑፉ እንደጠቀሰው (እባካችሁን አንብቡት!!) ኢትዮጵያውያንና መሪዎቿ ሆዳቸው የማይገኝ እጅግ ምሥጢረኞች ናቸው፤ ሰውን የማያምኑና ለውጮች ብቻም ሳይሆን እርስ በርሳቸው ተጠራጣሪዎች ናቸው ይላል፡፡ ለነገሩ ያልዘሩት አይበቅልምና ከተጣራጣሪ ሕዝብ የሚወጣ መሪ ተጠራጣሪ ቢሆን አይፈረድበትም፡፡ ይህ ሰው ባወጣው ጽሑፍ የተጠቀሱ ጸሐፍት አሉ፡፡ የአንደኛውንና ስሙን ለማንበብ ሁልጊዜም የምቸገርበትን ፖላንዳዊ ጋዜጠኛና ደራሲ – ሪሳርድ ካፑሺንስኪ(የኔ ነገር – አወላግጄው ይሆን?) – የደረሰውን ‘The Emperor’ የተሰኘ አነስተኛ ጥራዝ ሳነብ የተሰማኝ ስሜት የቁጭትና የንዴት ነበር – ይህንንም ያላነበባችሁ አንብቡት – አንብቡናም ትንሽ ተናደዱ፡፡ መቼ ነው ግን ሰው የሚወጣልን? እኛ ኢትዮጵያውያን ያለን ባሕርይ ከሞላ ጎደል በመሪዎቻችን ላይ ግዘፍ እየነሳ ዞሮ ተመልሶ እኛኑ ያናፍለናል፤ ለማያባራ ሥቃይና መከራም ይዳርገናል፡፡ ስለዚህ ይህን ጠባያችንን – የግልጽነት ጉድለት፣ ለተሾመ ማሽርገድና ማጎብደድ፣ የበላይን በጭፍን መከተል፣ በግልጽ ውይይት ችግርን ያለመፍታት … ለማስወገድ ሱባኤ መግባት ሳያስፈልገን አይቀርም፡፡ ባህላዊ ሥነ ቃላችን ‹ሰማይ አይታረስ፣ ንጉሥ አይከሰስ› እና ‹ዐዋቂ ሲያወራ ልጅ ወደ ጓዳ› እያለ፣ ሃይማኖታችን ‹ለንጉሥህ ሰጥ ለጥ ብለህ ተገዛ› እና ‹የምንላችሁን ተቀበሉ እንጂ የምናደርገውን አትከተሉ› እያለ ከልጅነታችን ጀምሮ ባሪያ አድርጎ ስላሳደገን የምንጠላውን ነገር የመቃወም ድፍረታችንና በነጻ ሃሳብን የመለዋወጥ ባህላችን ድንክዬ እንደሆነ አለ፡፡
ከፒብልስ አቀራረብ እንደተረዳሁት ከአፄ ምንሊክ አሟሟትና የቀብር ምሥጢር በጉልኅ የጀመረው የመሪዎች ድመታዊ ገመናን የመሸፋፈን ምሥጢረኝነት አሁን ድረስ ልንፈታው ያልቻልነው የ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዕንቆቅልሽ ሆኖብናል፡፡ ለዚህም ነው – እንደፒብልስም – በዛሬዋ ዕለት 55ኛ ቀኑን የደፈነው የጠቅላይ ምሥጢር መለስ ዜናዊ ወቅታዊ ሁኔታ አሁንም ሌላ ዕንቆቅልሽ ሆኖብን የሚገኘው፡፡ አፄ ምንሊክ ሞተው በምሥጢር ከተቀበሩ በኋላ – እውነት ይሁን ውሸት አላውቅም – ለሦስት ዓመታት በስማቸው ተገዝቷል ሲባል ሰምቻለሁ፡፡ አሁን መለስ እንደሚባለው በርግጥም ሞቶ ከሆነ በስሙ ለሁለት ወራት ያህል እንደተገዛን ይታወቃል፡፡ ሁኔታዎች በዚህ መልክ ከቀጠሉ አቶ መለስ ይፋዊ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ሳይፈጸም ምናልባትም ቀብሩ መፈጸሙም በባለጉዳዮቹ ግምት አግባብ ሳይሆን እንደቀረ ብንገምት ከእንግዲህ ለስንት ዓመት እንደምንገዛ አላውቅም፡፡ በዚህ ዕንቆቅልሽ ዙሪያ እኔ በበኩሌ እየተማርኩ ያለሁት አዲስ ነገር ወያኔ/ኢሕአዴግ በርግጥም እባብና ምሥጥ መሆኑን ነው፡፡ በዚህ ዘመን እኮ ሰማይ ላይ ሆነህ አብርሃ በላይ ወይም ሄኖክ ዓለማየሁ – እኔስ ብሆን – የበላናት ቁርስ ገና ወደደምነት ሳትለወጥ – ዱባም ትሁን ዕንቁላል – ዓይነቷን ከነ’nutritive value’ የሚለይና ሪፖርት የሚያደርግ ቴክኖሎጂ አለ – አጋነንኩ ይሆን? በሦርያ ዋና ከተማ ደማስቆስ አውራ ጎዳና ላይ በግል መኪናው ሲንሸራሸር የነበረውን የፍልስጥኤም ጦር ሁለተኛ መሪ በትራጀክተሪ ሚሳይል እንደገብረ ጉንዳን ከሚርመሰመሱ ሌሎች መኪኖች መሃል ተለይቶ የተመታውና ሕይወቱ ያለፈው በምን ጥበብ ነው? ታዲያ የታርጋ ቁጥርንና የመርፌን መጠን ከሺዎች ኪሎ ሜትሮች ርቀት የሚመነጥረው የ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የምዕራብና የምሥራቅ ቴክኖሎጂ በመሪያችን መሠወር እንዲህ ክፉኛ ስንጨነቅ ምን ዋጠው ይባላል? በወያኔስ እንዴት ሊረታ ቻለ? ይሄ ምሥጢር አያስደንቅም ትላላችሁ? ግን ‹ዐውቆ የተደበቀ ቢጠሩት አይሰማም›ንና ‹ወርቅ የተጫነች አህያ የማትደረምሰው ምሽግ የላትም› የሚሉትን ብሂሎች አሰላስሏቸውና ምሥጢሩን በነዚህ አባባሎች ውስጥ ተሰንቅሮ ታገኙታላችሁ፡፡ አልኩ ለማለት እንጂ አሁን ይህን ማን ያጣዋል? አይ የኛ ገንዘብ! አስከሬን መደበቂያም ይሁን?
እነሱ ሳያስቡትና ተተኪ ሳያዘጋጁ ፈጣሪ ደረሰና ጉድ አፈላባቸው – እነሱ የምለውን ከሀገር ውስጥ የወያኔ ምንደኞች አውጡልኝ – እነሱ ‹ሲጠሯቸው አቤት፤ ሲልኳቸው ወዴት› የሚሉ የነእንቶኔ ጉዳይ አስፈጻሚዎች እንጂ የራሳቸው ኅልውና የሌላቸው በድኖች ናቸው፡፡ እናም በድንገቴው ተደምመው በፈጣሪ ሥራም ተገርመው በአፍ ትምተማ አንዳቸው ከአንዳቸው በመግባባት ዝምታን መረጡ፤ አለበለዚያስ እውነቱን ያውቁታል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዓመት ፈቃድ ላይም ሆነ ከህመም የማገገሚያ ፈቃድ ላይም ሆነ ወደአካፑልኮ ቤይ ለክረምት ሽርሽርም ይሂድ ሃቁን ያውቁታል፡፡ ያስቸገራቸው አንዱን መርጠው ጠቅላይ ተላላኪው አቶ መለስ ለሚጨነቅለት ሕዝብ ማሳወቅን ነው – እናንተዬ የትልቅ ሰው መርዶ እኮ ይከብዳል – ትልቅ ሰው ‘ in a sense’ ሰውዬው ባለው ፖለቲካዊ ተፅዕኖ ማለቴ ነው – አማርዝኛው እኔስ እያማረኝ ለምን ይቅርብኝ? የሰውየውን የትነት ማወቅ ደግሞ መብታችን ነበር፤ ነውም እንጂ፡፡ እንኳን የሀገሬን መሪ የዕድሬንም መሪ ሁኔታ የማወቅ መብት አለኝ፡፡ ግን ‹ሚስትህ ወንድ ወለደች ወይ› ቢለው ‹ማንን ወንድ ብላ› እንዳለው ቢጤ ሆኖብን ነገሩ የተወሳሰበ ሁኔታ ላይ የሚገኝበት ሁኔታ ላይ ነው ያለው – በወያኔ ቋንቋ፡፡
የፈጣሪን ሥራ ግን ዝም ብላችሁ ተመልከቱ፡፡ ከንቱ ሰው ብዙ ያስባል፡፡ ሊገድልህ ብዙ ያደባል፡፡ ሊያጠፋህ ብዙ ይማስናል፡፡ መሞትህ የማይቀረውን ሞት ቀደም ብሎ ሊሰጥህ ያለ የሌለ ሀብትና ንብረቱን ያባክናል፡፡ ለውድቀትህ መቶ ዓመትም ቢሆን ቆይቶ የሚፈነዳ ቦምብ ይቀብርብሃል፡፡ በመካከልህ ፈርጀ ብዙ ፈንጂዎችን አጥምዶ በራስህ ጊዜ ካምሱሮቹን እየነካካህ እንድትተላለቅ ያሤርብሃል፡፡ በዚያም ሥራው እየተደሰተ በሣቅና በሁካታው ያደነቁርሃል፡፡ ያ መሠሪ ጠላት የማያውቀው ግን የፈጣሪን ፈራጅነት ነው፡፡ አሁን እግዚአብሔር በኢትዮጳያ ጉዳይ በግልጽ እየፈረደ አይደለም ብሎ የሚከራከር ሞኝ አለ? ይኖር ይሆናል – ግን መኖር አልነበረበትም፡፡ በገሃድ እያየነው? ችግሩ ‹ዐይን አላቸው ግን አያዩም፤ አፍንጫ አላቸው ግን አያሸቱበትም፤ እግር አላቸው ግን አይሄዱበትም…› ተብሎ ለኦሪታውያን የጣዖት ቅርፆች እንደተነገረው እኛም ሁሉም የስሜት ሕዋሳት እያሉን የማስተዋል ጥበብን ስለተነጠቅን ነው – ከሞላ ጎደል ሁላችን፡፡ እንዲያ ባይሆን – እንዲያው ለምሳሌ – የነገ ሟች የዛሬን ኅያውና የነገን ሟች ለምን ይገድላል?
እኔ ቀደም ካለ ጊዜ ጀምሮ የተረዳሁት አንድ ነገር አለ፡፡ ኢትዮጵያን ለአጎዛነት እንደሚዘጋጅ ቆዳ ወጥረው የያዙ ሦስት ሰዎች ነበሩ – አሉም፡፡ ከነዚህ ሦስት ሰዎች ሁለቱ በእግዜር እጅ መያዛቸውን እየሰማሁ ነው(እንዲያውም ይህን ደብዳቤ ልልክ ስል አንዱ ወዳጄ ማረፋቸውን ሰማሁ ብሎ መይሎልኛልና እውነት ከሆነ ዘመቻ ሃራ ኢትዮጵያ ተፋፍሞ ቀጥሏል ማለት ነው፤ ቤተ ክርስቲያንም ተዋርዳብን ነበርና እሷም ሕጽበት ያሻታል)፡፡ ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር – ሃሌ ሉያ፡፡ ይህ አጋጣሚ ሰው ሠራሽ ነው ወይንስ ከፈጣሪ? ምን ዓይነት ታሪካዊ ኹነት አገጣጠማቸው? እሺ – አንደኛውስ ዕድሜው በመጫኛ ሥፍርም ስለማይደረስበት በዕድሜው ነው እንበል፡፡ ሌላውና ለተጣለብን የቤት ሥራ ዋነኛው አካል ግን ገና 57 ዓመቱ ነው – ወጣት ሽማግሌ፡፡ ብዙ መሥራት የሚችልበት አፍላ ዕደሜ ላይ ነው የነበረ፡፡ ሞተ አልሞተ ለጊዜው በምሥጢር እንደተያዘ እንተወው – ምርጫም ስለሌለን፡፡ በሽርሽርና በህመም ፈቃድ እንደዚህ ደብዛው ይጠፋል ብሎ ማመን ግን በትንሹ ቡልሃነት ነው – የሞኝነቶች የመጨረሻ ደረጃ፡፡ የዛሬ ሁለት ወር ገደማ ሸርተቴ እንደያዛት ፍየል ሰውነቱ አልቆና ዐይኑ ብቻ ፈጥጦ በቁም የሚንቀሳቀስ ሬሣ መስሎ የነበረ መለስ ዜናዊ እያገገመ ነው ሲባል እውነታው በፈረንጅኛው አገላለጽ ‘is even too faint to give it the benefit of the doubt’. እናም ይቺ የበረከት ስምዖን ጨዋታ ምናልባት ለሁለተኛ የልቦለድ መጽሐፉ መደጎሚያ እንድተሆነው ካላስቀመታት በስተቀር ቅሽም ያለች ቀሺም አመክንዮና እጅግ የመሸባት ቧልታይና ድንቃይ የልጆች ተውኔት ናት፡፡ ይሁን ግዴለም – ለነበረከት መለስ ጤናማ ይሁንላቸው፡፡ ‹ሞኝ እንዴት ያሸንፋል› ቢሉ ‹እምቢኝ ብሎ› ይባላልና፡፡ ሊመከሩበት የሚገባቸው ጉዳይ ግን ይህን ከላይ የመጣንና ቀጣይነቱም አስተማማኝ የሚመስል የእግዜር ዱላ ማንም አይችለውምና ቢቻላቸው አንዳች መፍትሔ ይፈልጉ፡፡ መደናበሩና ለተጨማሪ ጥፋት ደፋ ቀና ማለቱ በፍጹም አያዋጣም፡፡ እባብ ጭንቅላቱ ከተመታ በኋላ በቀቢፀተስፋ የሚያደርገው ሁሉ ሞቱን ያፋጥን እንደሆነ እንጂ የሚጠቅመው ነገር የለም፡፡ ነገር ግን ሌላው ሕዝብና ተቃዋሚ መረዳት ያለበት ቁም ነገር የተመታ እባብ ዝም አይልም፡፡ የነጋበት ጅብም ዝም ብሎ አይሄድም፡፡ የቆሰለ ነብርም ቁስሉን አዝሎ አይቀመጥም፤ ከፍተኛ ጥፋት ያደርሳል፡፡ እየሞተ ያለን ያረጀ ሥርዓት እጅን በተገቢው ጓንት ሸፍኖ አፍንጫንም ጠቅጥቆ በጥንቃቄ መገነዝ ይገባል፡፡ ሃይማኖቱንም፣ ፖለቲካውንም፣ ንግዱንና ኢኮኖሚውንም ለመቆጣጠርና ወደተፈለው ወያኔያዊ የጉዞ አቅጣጫ ለማቀጣጨት የዛሬ 21 ዓመታት ገደማ የተጀመረው ዘርፈ ብዙ ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ ዘመቻ እየተጠቃለለ ነው (ብለን ማመን እንችላለን)፡፡ ይሄኔ አታጋፍጠኝ፣ አታጋትረኝ ነው ማለት፡፡ ከኑግ የተገኘሽ ሰሊጥ አብረሽ ተወቀጭ ነውና ለዚህ በቁሙ በስብሶ ለሞተ ሥርዓት የሚወረወር አንዳች ነገር እንዳይጠልፈን መጠንቀቅ ይገባል፤ እንጂ ሥርዓቱማ ፀጉራም ውሻ አለ ሲሉት ይሞታል ዓይነት ከሆነ ቆየት አለ – ጣር ስንት ቀን ይፈጃል ግን? አይ ጋሽ ፀጋዬ ምነው አሁን በኖረና በዚህችም ላይ በተቀኘባት! ሳልረሳው – ደርግ እኮ በቅጡ መሞት የጀመረው ግንቦት 8 ቀን 2001ዓ.ም ከተሞከረው መፈንቅለ መንግሥቱ ዕለት ጀምሮ ነው፡፡ እናም የወያኔው ሥርዓት ግብኣተ መሬቱ ሊፈጸም በጣም ተቃርቧል፡፡ እንዲህ የምለው እውነቴን ነው አንዳች ነገር በል በል እያለኝ እንጂ – የታሪክን አካሄድ በመረዳቴ እንጂ – የጸሎትንና የልቅሶን የዞረ ድምር ውጤት በመገንዘቤ እንጂ – ያለቀሰ መሳቁ ያስለቀሰም ማልቀሱ ነባራዊ እወነት መሆኑን በማሰብ እንጂ – አንዲት ጠመንጃም ይሁን አንካሤ ይዞ ወደአዲስ አበባ – ወደፊንፊኔ – ፊንፊኔ? – (እመጣበታለሁ) – የሚገሰግስ የነጻነት አርበኛ እንዳለ ከመረዳት ወይም ከመገመት አኳያ አይደለም፡፡ የነጻነት አርበኛ ምን አስፈለገ? የፈጣሪ ጦር ከሰማይ አናት አናቱን እያነጎደ ሲጥለው እያየን ምን ጦር ያስፈልጋል? ራሴኑ ልቃረን – ጦርማ ያስፈልጋል፡፡ ጠንካራ ጦር – ከሁሉም ወገን በብቃትና ችሎታ መሥፈርት የተውጣጣና በአንደነት መንፈስ የተዋቀረ ጦር – የሠለጠነ ጦር – ከዘረኝነት አሮንቃ የወጣ ጦር – በአንዲት ሀገር ጥላ ሥር የሚሰለፍ ጦር – በጎጣዊና ክልላዊ- በነገድና በቋንቋ ስሜት ያልታወረ ዘመናዊ ጦር ያስፈልጋል፡፡ በጎጠኛ ስሜት ተነሳስቶ አንዱን ለአንዱ ለማስገበር ሳይሆን በብሔራዊ ኢትዮጵያዊ ፍቅር የነደደ ሁነኛ ጦርማ ያስፈልገናል፡፡ ያማረ ንግግርና ውብ ተጠየቃዊ አካሄድ በገለልተኛ ጦር ካልታገዘ ጉልበተኞች እየተፈራረቁ ሲፈነጩብን ይኖራሉ እንጂ ወደምናልመው የጋራ ራዕይ ባፋጣኝ መድረስ አይቻለንም፡፡ ስለዚህ በዚህም ረገድ ይታሰብበት፡፡
ሃይ ተቃዋሚዎች! እንዴት ናችሁ? ስንተ ናችሁ ማለቴ አሁን ምን እየሠራችሁ ነው? አሁንም ሕዝቡ እናንተን አንጋጦ ይጠብቅ ወይንስ ሌላ ሙሤ እንዲልክለት ፈጣሪውን ይጠይቅ? የት ናችሁ? አሮጌውን ወይን በአዲስ አቅማዳ ለመገልበጥ እየተዘጋጃችሁ ነው ወይንስ ማርሽ ልትለውጡ አስባችኋል? ሞቱ የሚደበቅ፣ ቀብሩ እማይታወቅ፣ ከቤተ መንግሥት በወጣ በገባ ቁጥር በቅልብ ጦር ሕዝቡን ወደግድግዳ እያዞረ የሚያንቀጠቅጥ ተረኛ ለመሾም ተዘጋጃችሁ ወይንስ እንደነ ዴቪድ ካሜሮን በሕዝብ ትራንስፖርት እየሄደ ህመማቸውን የሚታመምና ደስታቸውን የሚካፈል መሪ እያሰናዳችሁ ነው? እንደስብሰቴው ዘመን በሥልጣንና በጥቅም፣ በቋንቋና በዘር፣ በአብሮ አደግና ባምቻ ጋብቻ እየተቆላለፋችሁ ወደሥልጣን ለመምጣት አቅዳችኋል ወይንስ በብቃትና በዕውቀት፣ በአመራር ጥበብና ዕድሜና ልምድ በሚሰጡት ብስለት ራሳችሁን አርቃችሁ(‹ር› ትጥበቅ) ሕዝባችሁን በቀናነት ለማገልገል ባጭር ታጥቃችሁ ወር ተራችሁን እየተጠባበቃችሁ ናችሁ? የምጠይቃችሁ አንድ ቁጫጭ ዜጋችሁ ነኝ፤ የምወክለው ግን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ድምጽ አልባ ምንዱባን ወገኖችን ነውና በተለመደው ኢትዮጵያዊ ድንቅ ባህላችን ‹እሱ ደግሞ ማን ነው? በሚለው የተዓቢዮ ንግግር ተሸንፋችሁ ጆሮ ዳባ እንደማትሉኝ በመተማመን ነው፡፡ አንዱ ባንዱ እየሳቀ የሚገባው የጀምበር ብዛት የሚያናድደን ወገኖች ብዙ ነንና አስቡልን፡፡
ትናንት ማት አንድ መጠጥ ቤት ነበርኩ፡፡ ብዙ ሰው ያውካካል፡፡ መጠጥ ቤት ውስጥ የማይተዋወቀውም፣ የሚተዋወቀውም፣ ጆሮውም፣ የተቃዋሚ ደጋፊውም ስለሚኖር በራስ ተማምኖ ስለ ፖለቲካ የሚያወራ የለም፡፡ እጅግ ሲበዛ ፈሪ ሆነናል፡፡ ገና ብርጭቆ እንደያዝኩ ምን እንደነካኝም ሳላውቅ አንዱን ኦሮምኛ ተናጋሪ ድንገት አፌ እንዳመጣልኝ ‹ይሄውልህ ወንድሜ፣ አንተ አሁን ኦሮሚያ የሚባል ሀገር ከኢትዮጵያ ተገንጥሎ ብቻውን ነጻ ሀገር ቢሆን ትደግፋለህ?› ብዬ ጠየቅሁት፡፡ መልሱም የሚገርም ነበር፡‹ ‹ምን ማለትህ ነው? የቱ ነው ከየት የሚገነጠልና የራሱን ግዛት የሚያቆም? ማን ከማን ተለይቶ?› ነበር ያለኝ፡፡ የሌሎችን ትኩረት መሳቤን ስረዳ መፈራራት እንደሌለብን፣ የሀገራችን ጉዳይ የኛም መሆኑን፣ ጨዋታችን ሁሉ በስም አይጠሬ የምንትሴ የምንትሴ ብቻ ሳይሆን ቁም ነገር አዘልም መሆን እንደሚገባው ለነገር አሳባቂዎችም በማይጎረብጥ መንገድ አስረዳሁና የሆነ እፎይታ አግኝቼ ጉበቴንም ቢያንስ የአንድ ቀን ዕድሜዋን አሳጥሬ ወደቤቴን ገባሁ›፡፡ እንዴ፣ በምን እንደበቅና ይህን አስጨናቂ ዘመን ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን እንርሳ? ችግሩ የ0.85 ሣንቲሙ ነጠላ ድራፍት አሁን ብር አምስት መሆኑ፡፡ የዋጋ ነገር አይነሳ! ብዙዎቻችን የቅቤ ቅሎቻችንንና የሥጋ ቢላዎቻችንን አታጥበን ሰቅለናል – ደገኛ ዘመን እስኪመጣና የሚመጣም ከሆነ፡፡ ቆሎ ያጣውንማ ቤቱ ይቁጠረው፡፡ ይህን ኑሮ ብለን እየኖርን ነው እንግዲህ፡፡
ሄሎ ኦነግ! የት ነው ያለኸው? ዕድሜህ ስንት ነው? ሎራን ካቢላ በአሥራ አንድ ወራት ጊዜ ውስጥ ኪንሻሳን ሲቆጣጠር አንተ በዚህ ረጂም ዕድሜ ከራስህ ጋር ከመፋለምና ራስህን በአንጃዎች ከመከፋፈል ባለፈ ለኛ ምን ሠራህ? ኧረ ለመሆኑ እኛን ታውቀናለህ? አትኩራ – አናግረኝ፡፡ ግዴላችሁም ዛሬ ነገር ነገር ብሎኛል የደግ ያድርግልህ በሉኝ፡፡ እኮ አሁን የት ነህ – አባባ ኦነግ?
እናሳ፣ ኦነግም ሆንክ ሌላው ተቃዋሚ ሁላ ቀድመህ ለምን የሕዝብህን ፍላጎትና ስሜት አትረዳም? እግሩን የሚያሳክከውን ሰው ራሱን ቢያኩት ምን ይጠቅመዋል? አሁን የሕዝቡ ችግር ምንድነው? መገንጠል ነው? ራስን በራስ ያለምገዛት ችግር ነው? የሕዝበ ውሳኔ ጣጣ ነው? ቀድሞ የመቀመጫን አለች አሉ ጅንጅሮ፡፡ ይህን መሰሉ ነገር እኮ ለሰለጠነው የዓለም ማኅበረሰብ እንጂ የእግረኛ መቋረጫ ዜብራ መንገድ ላይ ተገናኝቶ ጉንጮቹን አገለባብጦ እየተሳሳመ የቤተሰብ ናፍቆቱን በሚወጣና ምሳውን ቀምሶ ለራቱ የሚጨነቅ የማኅበረሰብ አባል በሞላበት ኋላ ቀር ሀገር ውስጥ አይደለም፡፡ እዬዬም እኮ ሲደላ ነው፡፡ እናንተ ያያችሁት አውሮፓን ነው፤ እናንተ ያነበባችሁት የአሜሪካንንና የመሰል ሀገሮችን ታሪክ ነው፡፡ እኛን ሕዝባችሁን – ሕዝባችሁን ማለትም ከቻልኩ ነው – በጭራሽ አታውቁንም፡፡ አንደባበቅ አታውቁንም ነው የምላችሁ፡፡ ለምሳሌ እንደኔ በዕድርና በሰንበቴ፣ በጽዋ ማኅበርና በዕቁብ ከተለያዩ ዘውጎች አባላት ጋር ትገናኛላችሁ? እየበጠበጠን ያለው ትንሽ ዕውቀት ነው፡፡ ትንሽ ዕውቀት አደገኛ ነው መባሉ ለዚህ ነው – እኔ በትንሽ ዕውቀቴ ቢያንስ ሕዝቡን እንወቀው እያልኳችሁ ነው፡፡ እናንተስ? ሕዝቡ ዳቦና መሠረታዊ ዴሞክራሲያዊ መብቱን እንጂ እናንተ ከሌሎች ሀገራት ኮርጃችሁ ሽቅብ አጡዛችሁ የለቀቃችሁትን እንደደሮ ብልት ሀገርን የሚበጣጥስ የታሪካዊ ጠላቶች አጀንዳ የሚፈልግ ይመስላችኋል? መቼ ነው የሕዝቡን ፍላጎት ከቁብ መቁጠር የምትጀምሩት? መቼ ነው ላለፈ ክረምት ቤት መሥራታችሁን የምታቆሙት? መቼ ነው የነጎበናና ምንሊክ፣ የነአባመላና ባልቻ አፅም በሰላም እንዲተኛ ፈቃደኞች የምትሆኑት? ከአቡኑ በላይ ካቶሊክ መሆን የሚቃጣችሁ ጥቂት የማትባሉ የኦነግ አመራር አባላት ደግሞ ነፍጠኖች ከምትሏቸው የመሀል ሀገር ሰዎች የተካለሳችሁ ናችሁ፡፡ የ‹ክልስ› ደም ደግሞ ሞቃት ነው – በረት ይበጠብጣል፡፡ መለስና ኢሳይያስ ኢትዮጵያን ያመሱት የጥቁር ክልሶች ስለሆኑ ሳይሆን ይቀራል? በአንጻራዊ አነጋገር ከአንድ የትውልድ መስመር በሕጋዊ ጋብቻ የተገኘና በጥሩ ሥነ ምግባር ያደገ ዜጋ በአብዛኛው መልካም ዜጋ የመሆን ዕድሉ የሰፋ ነው (ተብሎ ቢታመን በተወሰነ ደረጃ እውነትነት ያለው ይመስላል)፡፡ ይሄ እየበጠበጠን ያለ የ1940 እና 1950ዎቹ ትውልድ ከባህሉም ከሃይማኖቱም ከቤተሰቡም የተጣላ ፈረንጅ አይሉት ሀበሻ በመሀል ቤት በማንነት ኪሣራ የተዘፈቀ አጉል ትውልድ ነው – መቆሚያ መቀመጫ እያሳጣን ያለው፡፡ ያ የጠፋ ትውልድ ነው እያመሰን የሚገኝ፡፡ ደግነቱ እያረጀና በበሽታም በእርግማንም እያለቀ ነው፡፡…
ብዙ ኦሮምኛ ተናጋሪ ጓደኞች አሉኝ፡፡ እኔ ራሴም ኦሮሞ ነኝ፡፡ ለዝርዝሩ ጊዜ የለኝም፡፡ ከልጆቼ አንዱ 25 በመቶው ኦሮሞ ነው – ቢያንስ በዚህች የሳሳች የምትመስል እኔነት አልደራደርም – ኦሮሞ ነኝ፤ የደም ልጄ መከፋት የኔም ነው፤ የደም ልጄ መጎሳቆል የኔም ነው…፡፡ ኦሮሞ ያልሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ራሱ 80 በመቶው ኦሮሞ ነው፡፡ ምንጭ መጥቀሻ ጊዜ የለኝም፡፡ ታዲያ ማንን ነው ከማን እንገንጥል ብለን ከእውነት ጋር እንደ ዶን ኪኾቴ ምናባዊ የጨለማ ጦርነት የምንገጥመው? ሕዝቤ ተራበ፤ ተጠማ፤ ተበደለ፤ ተጨቆነ ፤ ፍትህን ተጠማ … ብሎ ዘር ቀለም ሃይማኖት ነገድ ሳይለዩ ጫካ መውጣትና መታገል ያባት ነው፡፡ ነገር ግን ለመቶዎች ዓመታት የተጋባን፣ የተዋለደን፣ የተዛመደን፣ የተጋመደንና ልዩነቶቹን አቻችሎ በመተሳሰብና በመፈቃቀድ እየኖረ ያለን ሕዝብ ግለሰባዊና ቡድናዊ የልዩነት ቀዳዳዎችን በላይዳና በመንሽ በማዝራትና ልዩነትን በማራገብ ከታሪክ ጋር ፍልሚያ መግጠም በእጅጉ ያሳዝናል፣ ይዋል ይደር እንጂ ለተጠያቂነትም ይዳጋል፡፡ በቅርቡ የተናገርኩትን የተውሶ አባባል እዚህም ላይ ልድገመው፡- ስህተት በስህተት አይቃናም፡፡ ታሪካዊ ጥፋቶች ከየትኛውም ወገን ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ጥፋት ባጋጠመ ቁጥር እንደሕጻናት የቃቃ ጨዋታ ሀገርን በሚያህል ትልቅ ጉዳይ ‹ጨዋታው ፈረሰ ፤ ዳቦው ተገመሰ› እየተባለ መበታተንን በራሳችን ላይ ልንጋብዝ አንችልም፡፡ በዚያ ላይ በጦርነት ያልተገነባን ሀገር ፈልጉና አግኙ፡፡ ኦሮሞም በጦርነት ነው መላዋን ኢትዮጵያ ያዳረሰው፡፡ ምን አዲስ ነገር አለ? ጣሊን እንኳን ጋሪባልዲ በሚባል ሰው አይደለም እንዴ ከ37 ይሁን ከ38 ቁርጥራጭ ጣሊያኖች የተሠራችው? ሞኝ እንደያዘው ፈሊጥ ከመቶ ምናምን ዓመታት በኋላ ምንሊክ፣ ምኒልክ መባሉ ምን ማለት ነው? የኢትዮጵያ ታሪክ ከሌሎች ሀገራት ታሪክ የተለዬ ነውን? ሳይረፍድ ወደዬኅሊናችን እንመለስ፡፡ አለበለዚያ እኔም ደብረ ታቦርን እገነጥልና እያንዳንድሽ ዋጋሽን ታገኛታለሽ! ስኮላርሺፕ አንሰጥ፣ ዕርዳታና ብድር አንፈቅድ፣ በቃ … የደብረ ታቦርና አካባቢዋ ፌዴራል ዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ፡፡ የኦነግ ምኞትና ሕልምም ከዚህ አይሻልም፡፡ ይህን እውነት ሕዝቡም ያውቃል፤ መናገሪያ ዕድልና መድረክ አታ እንጂ፡፡
ሕዝቡ – ኦሮሞም በሉት ትግሬ አማራም በሉት ጉራጌ ስለግንጠላ ሲነሳ ይስቃል፤ በፖለቲከኞች ጅልነትና መሠሪነትም ይገረማል፡፡ በተለይ በተለይ ኦሮሞ የተሠራጨበትን የመሬት የቆዳ ስፋት ስንመለከት ኦሮሞን እንገንጥል ማለት ህልም እንጂ እውን አይመስልም፡፡ የቱን ከየትኛው? አንድ ወዳጄ ሰሞኑን በመየለልኝ ጽሑፍ ውስጥ የዲማ ነገዎን አንጀት ቆራጭ የጀርመን ሀገር ንግግር ስመለከት ተናደድኩ፤ በእግዜሩ ፍርድ መዘግየትም ተበሳጨሁ – ለኛ ረጂም ለርሱ ግን ተገቢ በሆነው ሰዓቱ መምጣቱ ላይቀር፡፡ ኦነግ ፊንፊኔን ያኔ እንዳለው ‹ሲቆጣጠር› (አሁን ምናልባት ቢቆጣጠር) ኦሮሞ ያልሆኑት ዜጎች ከከተማዋ እንዲወጡ ኮሪዶር ይዘጋጅና ውልቅ ይላሉ ነበር ያለው፡፡ ከፎከረ ቀርቶ ከወረወረ ለሚያድን የኢትዮጵያ አምላክ ምሥጋና ይድረሰው፡፡ የፀሐዬ ዮሐንስ ዘፈን ብልጭ አለብኝ አሁን፡፡ ግጥሙ ጠፋኝ – ግን ፈጣሪ ጠላቶቿን አንድ ባንድ በእግሯ ሥር ያውላል ዓይነት ነው ጭብጡ፡፡ እናሳ? አንድ ሰው ካላበደ በስተቀር የአንድ ከተማን ሕዝብ አሰለፎ ከኖረበትና እትብቱ ከተቀበረበት ሥፍራ ያስወጣል? ሰው መቼ ነው ሰው እሚሆን ጎበዝ? በዚህ ዓይነቱ ሰው ጭንቅላት ውስጥ ያለው ተዝለግላጊ ፈሳሽ በእውነቱ አንጎል ይሆን ወይንስ ሌላ? የጠላትን አጀንዳ እንዳለ አንከርፍፎ አንድም ለውጥ ሳያሳዩ ለግማሽ ምዕተ ዓመት መጓዝ፣ በምናባዊ ጦርነት ሕዝብን ማሸበር – ማሸበር የሚለውን ማስበርገግ በሚለው ልተካው መሰለኝ – አዎ – ለዘመናት ሕዝብን ማደናገጥ ምን ይባላል? ዳቦ የምናገኝበትን ምቹ ሁነታ መፍጠር ይቀድማል ወይንስ ቅርጹን እንኳን በወረቅትም ይሁን በኅሊና ለመሳል የሚያስቸግር ግዛት እየፈጠሩ በአዲስ ብሔራዊ ማንነት ዐዋጅ ተዋህዶ የሚኖርን ሕዝብ ግራ ማጋባት? ለዚህ ነው ኦነግ በስም እንጂ በግብር ሊኖር ያልቻለው፡፡ ለዚህ ነው የኦነግ የትግል ሥልትም ሆነ የፖለቲካ አጀንዳ ወንዝ ቀርቶ ምንጭና የደረቀ ኩሬ ሊሻገር ያልቻለው፡፡ ከኦሮሞዎች ጋር አብረን እንኖራለና! እንተዋወቃለና! ግን የአንዳንድ መጤ አስተሳሰቦች ምርኮኞች ደግሞ ምን እንደሚያስቡና ቢሳካላቸው ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉም ከአንዳንድ ወሰድ መለስ የሚያደርጋቸው የወቅት ንፋሶች በመነሳት እንገምታለን፡፡ ለዚህም ይመስላል አንዳንድ ወገኖች ከኦነግ ይልቅ ወያኔ እንደሚሻል ከፍርሀታቸው የተነሳ ሲናገሩ የሚስተዋሉት – ነገሩ ግን ያው ከጅንጀሮ ቆንጆ ዓይነት ነው፡፡ የፈጣሪን እንጠብቅ ሁሉም የሥራውን ያገኛል፡፡ እግዚአብሔር አይተኛም፤አያንቀላፋምም፡፡ …
ለማንኛውም ከአሁን በኋላ ቀመሩ ሁሉ ይለወጣል፡፡ በዱሮ በሬ ማረስም ይቀራል፡፡ ሕዝቡ የፈረንጅኛውን ፈሊጣዊ ብሂል ተውሶ “Let’s wait until the cat jumps.” ብሎ ሁሉንም እርግፍ አድርጎ ለጊዜ ፍርድ ስጥቶ እንጂ እንደምንገምተው በፍርሀት ተሸንፎ አይደለም፡፡ የ1997ን የቅንጅት መንፈስ ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡ አለመታደል ሆኖ እንጂ ተቃዋሚዎች በተለይም ኦነግ ከዚያ አንገብጋቢውን የኢትዮጵያውያን ፍላጎት አመላካች የሚያዚያ 30/97 የሚሊዮኖች ሰላማዊ ሠልፍ ቢረዱ ወልጋዳና ሸፋፋ አቋማቸውን ሊያስተካክሉ በቻሉ ነበር፡፡ ሕዝቡ ጠላት ወዳጁን፣ ጎጂ ጠቃሚውን አጣርቶ አውቋል – ዕድሜ ላለፉት 21 ዓመታት የወያኔ ከፋፋይና ጎጠኛ አገዛዝ፡፡ ኢትዮጵያ የአጭበርባሪዎች መናኸሪያ መሆኗ የሚያበቃበት ዘመን እየመጣ ነው፡፡ ሴተኛ አዳሪዋ አጭበርባሪ አይተኛኝም ያለችው ለካንስ እንደኛው አንጀቷ ቢያርር ኖሯል! አንጀታችንን እኮ አሳረሩት፤ በዚህ ሲሏቸው ‹የዚህ ብሔረሰብ ንቅናቄ› በዚያ ሲሏቸው ‹የዚህ ብሔር ጥምር ግንባር› እያሉ የምንሰማው መልካም ዜና እንዳይኖር አደረጉን፡፡ አፄ ቴዎድሮስ ካህናቱን ‹አንድሽ አንባቢ አንድሽ ተርጓሚ…› በማለት የካህናቱን መሠሪነት ገልጠዋል አሉ፡፡ መሠሪነት አሁንም ተባብሶ ቀጠለና ይሄውና ውሻ በቀደደው ጅብ እየገባ ሀገራችንን መቅኖ አሳጥተዋት ሊቀሩ ነው፡፡ ግን ዕድሜ ለአንድዬ … እንዲህ እንደሆንን አንቀርም … ስሟ እንደገና በዓለም ይገንናል፡፡መቶ ሃምሳው ባንዲራ ጠፍቶ ቀይ ቢጫ አረንጓዴ የወል ባንዲራችን – እጅግ በርካታ የዓለም ሀገራት በምሳሌነቷ ወስደው የቀለማቱን አቀማመት እያገለባበጡ የኮረጇት ይህች ባንዴራ ወድቃ አትቀርም፤ ትነሳለች፡፡ የማናውቃቸው ሥውር ኃይላት ይህን የቤት ሥራ እየሠሩ እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ እንዳትኮነኑ – የትኛውንም የፖለቲካ ስብስብ ወይም ጉባኤ በአእምሮየ አላሰብኩም፡፡ እንዲሁ ግን የመከራ ደብዳቤያችን እየተቀደደ እንደሆነ በስሜት ደረጃ ሽው የሚለኝ ነገር አለ – አለወትሮየ፡፡- ቢሆንም የኛን ድርሻ ከመወጣት የሚያዘናጋ ነገር እንደሌለ ልጠቁም እፈልጋለሁ፡፡ አቤት ይህን ወረቀትስ የሚያወጣልኝ ድረ ገጽ በጭራሽ አይኖርም እናንተዬ፡፡ እንኳን ከኔ ወጣ እንጂ ምን ተዳዬ? … ግን መናገር ከመጀመሬ ስድስተኛው ገጽ ልግባ? – ፈርዳን ኢንጌሣ መሌ ኢወራኑ – (ፈረስ ያደርሳል እንጂ አይዋጋም)፡፡
አሁንም ለማንኛወም ዘለፋም ሆነ አቃቂር፡- yinegal3@gmail.com



Betam tiru tshuf naw.
Arengwade,bicha,qeyu bandirachin dagim kef yilal
ለፈጣሪ ምስጋና ይሁን ! የኢትዮጲያ ጠላቶች በአምላካች ን እጅ የሚመቱበት ዘመንን ማየት ጀምረናል
የዚህ ጽህፍ አቅራቢ በጥላቻ የተሞላና እጅግ በጣም የፈራ ግለሰብ መሆን አለበት:: ዛሬም ሃበሾች ሌሎችን ህዝቦች ማክበርና ለፖለቲካ ምርጫቸው ዋጋ መስጠት በጣም የከበዳቸው ነገር ነው:: ማንኛውም ሃበሻ የኦነግን የፖለቲካ አቅጣጫ ይቀበላል ማለት ዘበት ነው:: በግልባጩ ደግሞ ከንግዲህ ወዲያ አንድ ኦሮሞ የሃበሾችን የፖለቲካ መስመርም ሆነ የኑሮ ዘይቤ ከግምት ውስጥ ያስገባል ማለትም የማይታሰብ ጉዳይ ነው:: በመሆኑም ኦነግንም ሆነ የኦሮሞን ህዝብ ሺህ ጊዜ አጥላልተህ (ልክ እንደቀድሞዎቹ የአማራ ደብተራዎች) ብትለቀልቅ ማንም ኦሮሞ ቆም ብሎ የሚሰማህ እንዳይመስልህ:: እድሜ ለወያኔ የናንተን ያረጀ ያፈጀ የተዋረደ ጊዜው ያለፈበት አስተሳሰብ ለአለም ህዝብ ያጋለጠው:: ዛሬ እያንዳንዱ የአገራችን ብሄር-ብሄረሰብ አፉን ሞልቶ ስለራሱ ማሰብና ባህሉን እንዲሁም እምነቱን እየተገበረው ይገኛል:: ይህ የማይዋጥላቸው ጥቂት የነፍጠኛው ስርአት ርዝራዦች ከስደት አገራቸው የፈለጉትን ቢጽፉና ከፋፋይ ፕሮፖጋንዳቸውን ቢነፉ አንዲትም ሰሚ ጆሮ አያገኙም:: በተለይ በተለይ የኦሮሞ ህዝብ እጅግ ቀድሞአችሁ ሔዶአል:: ጊዜው አፍራሽ ፕሮፖጋንዳ በመንዛት የበላይነት የሚገኝበት ሳይሆን ለእውነትና ስለእውነት በመኖርና በመታገል አብሮ ለመኖር የምንሰራበት ዘመን ነው:: ኦነግ በትግል ሂደቱ ስህተት የለበትም አንልም:: እጅግ በጣም ብዙ ጥፋትን የፈጸመ ፓርቲ ነው:: በስህተቶቹም የተጎዳው የኦሮሞ ህዝብ ብቻ ነው:: ነገር ግን ኦነግ ዛሬም ሆነ ለዘመናት የኦሮሞ ህዝብ ብቸኛውና ወደር የማይገኝለት የፖለቲካው አቅጣጫችን ነው:: ኦነግን አልፈልግህም የፖለቲካ አቅጥጫህ አላስደሰተኝም ሊለው የሚችለው የኦሮሞ ህዝብ ብቻ ነው:: ይህ ነፍጠኞችን የማይመለከት የራሳችን ብቻ ጉዳይ ነው:: ኦነግን ካልፈለግነው ከሱ የተሻለ ፓርቲ በአንዲት ጀንበር መመስረት አያቅተንም:: የኦሮሞ ህዝብ የፖለቲከኞችም ሆነ የምሁራን መካን አይምሰላችሁ:: ሁሉም በበቂ እንዲያውም ከበቂ በላይ የተትረፈረፈለት ህዝብ ነው:: በመጨረሻ ላይ ለዚህ ጽሁፍ አቅራቢ አንዲት መልእክት ማስተላለፍ የግድ ይላል:: በጽሁፍህ በስተመጨረሻ አከባቢ እንደገለጽከው ሸፋፋ አመለካከት ያለው ኦነግ ሳይሆን አንተ አባል የሆንክባቸው ከደርዘን በላይ የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ናቸው:: ይህን ከተረዳህ በኋላ እንደቅን አሳቢ ዜጋ መጻፍ ትችላለህ:: አለበለዝያ ግን የሌዲ ጋጋን ዘፈን ቢሰማበት የበለጠ ጊዜየን ለቁም ነገር አዋልኩት ማሌት ነው ያንተን አልባሌ ዲስኩር ከማነብ! ቸር ይግጠመን::
Wako,Instead of working with OLF( except the few who have changed lately), it is better to stay 100 more years with eprdf. Even i some time think that ethiopia should follow chinese rule in some ways but the leaders should be more patriotic who will work for the betterment of the country just like the Chinese.
People,Just imagine dawud ibsa come to power, and shabia using olf to drag ethiopia, what kind of Ethiopia do you see? Most of Olf leaders have never known their people nor the country. For them,any one who calls for democratic and strong country is only the need of few ppl. They dont know that there are millions in all parts of the country who will do what ever it takes to safeguard our motherland. What i always wonder is, these people live abroad, they know how ppl with different languages in other countries live and they still can not learn. If we want to come change to Ethiopia, we should be sure that it will be positive change – a change that will take us some where better than where we are now. If not, it is not only meaningless but against Ethiopia and its people too.
አምላክ ፍርድ እየሰጤ ነው…ኦነጎቺም የጃቸውን ያገኛሉ …ጊዘ ደጉ ገና ብዙ እናያለን…በርታ!!!!
arenguade – bicha – qey malet sigebagn bechikolana besihitet magelebabeten yikrita eteyikalehu. kesew sihtet kenchet ziget yibal yelem? ye’editing chigir new.
ይነጋል በላቸው የተምታታ ጹህፍ ነው ያቀረብከው::ታሪክን ከነባራዊ ሁኔታ ጋር አገናዝባለሁ ብለህ ተምታቶብሃል::
ኦነግን ስንመለከት ኦ.ነ.ግ የህዝቡን ሃሳብ ተቀብሎ ትክክለኛ መንገዱ ይህ ነው ብሎ በዱር በገደሉ እየታገለ ያለ ድጅት ነው::
በከማል ገልቹ የሚመራውን ማለቴ ሲሆን አቶ ሌንጮ ለታ በአንድ ሬድዮ ጣቢያ ያደርጉትን ቃለምልልስም አዳምጨው የሚደነቅና የሚደገፍ ሃስብ ነው ያቀረቡት::ከወያኔ በስተቀር የህዝቡን ሃስብ አልቀበልም ያለ ድርጅት በአሁኑ ስዓት ያለ አይመስለኝም::ከአሉም ለማስምንና ለመተማመን ትግል ያስፈልጋል::ያለፈውን ቁስል እየነካኩ ከማድማት ቁስሉ እንዲድን ማከም ያስፈልጋል::
ጋሽ ይነጋል ስትጽፍ እንዳይምታታብህና ግራ የተጋባ ሃስብ እንዳይሆንብህ አንተ በገባህ ቀለል ባለ ቋንቋ ሃስብህን ለማስተላለፍ ሞክር::ጥልቀት ያለው ሃስብ አቀርባለሁ እያልክ ወደ አልሆነ አቅጣጫ እየሂደብህ እንጂ ቅንነቱ አለህ::
Leave Oromo matters to Ormos my friend. You will get your fingers burned. Now Meles is out of the political scene, you Neftegnas seem to sense you will be back in the saddle again. You can dream of course. Oromos won’t settle for anything less than the opportunity to determine their future; that is the least common denominator among Oromo political forces now fighting for Oromian independence. One, and likely outcome, of that process is the formation of their own state. May take years even decades but the wheels of history are already in motion and no matter their machinations, neither Amhara intrigue nor TPLF violence against Oromos, will stop the process of Oromian decolonization. The consummation of this process of course depends on a host of factors…global, geo-political, internal etc. But its happening, doubt you not my friend.And this is from an independent Oromo.
የመጣጥፉ አላማ ቡድኖች የህዝቡን ታሪክ አውቃችሁ ተንቀሳቀሱ አታወናብዱ ይላል ካለፉት 21 አመቶች ት/ት
ለወሰደ ሰው ጎጠኝነት ከትርፉ ጉዳቱ የከፋ ስለመሆኑ መረዳት አያዳግትም ታድያ ዋቆና መሰሎቹ ይለወጣሉ ብሎ
ማሰቡ ዋጋ የለውም ቁም ነገሩ EPLF TPLF OLF ዐይነት ሀይሎችን ባለ ሀይል ተጠቅሞ ቅስማቸውን መስበር
ኢትዮጵያዊ ግዳጅ መሆኑን መገንዘብ ብቻ ነው ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች ጎጠኞች ተራ በተራ ይሰባበራሉ
Ok ‘The OLFian’. You keep dreaming also. Your group(olf) is nothing but a retarded and enemy agents. Shabia said leave the eritrean issue for us and now you see what is going on there. For now, you look like you care for oromos or are full of love for them, You are not my friend. You are only full of hate for a country about which you were badly misinformed. You are eager to come to power – impose your wishes which most likely will be some thing evil for any one.
Keep dreaming untill you suddenly wake up when true ethiopians from all ethencities dominate. That is the time when you will hate your self most!
the oromian and thwe likes are the trojan horses of the owner of the 100 years assignment given to ethiopia thru woyane. woyanes are nearly finished now and the second trojan horse is about to climb the fake and mirage horse to gallop ethiopian. but belive me this is simply dream, we ethiopians by now have come to realize who is who. if any one wants to live in ethiopia, he must accept ethiopianism otherwise he must go to the place from where he came. here aftwer no one has any right nor capacity to stir and create a tide to redistablise our mother. atjajalu ebakachihu, mognoch!jil aymut endiachawut ytebalew lendenante aynetu molefet new. oromia oromia tilaleh, esayiyas saymeta endih yale qal neber? lemin tibeshaketalachihu? angol yelelachihu megajawocvh. ngerugn bay hula. empire, oromia, habesha, gorebet vhager qbitrso eyalachihu yemtjajalut woyanena shabia jaz blew slelakuachihu enji yeetyopia nestanet simeta afachihun tiyzalachihu. ahun edme leshabiana woyane endelbachihu chuhu.
ሰላም ለሁላችን/አርካፉኔ
25% ኦሮሞ ልጅ ያለህ ሰው አንተ ስንት በመቶ ኦሮሞ ዘር አለብህ?የገባር ህዝቦች ኦሮሞዎችን ጭምር በጦቢያ ነፍጠኛ ገዥዎች የዛሬውን ወያኔ ድረስ እጅግ በጣም አከፊ ኢሰባዊ ነው::በትክክል ገባር ህዝቦች ማንነታቸው ቁዋንቁዋቸው የተናቀባት ጦቢያ ተቀብራችለች እርምህን አውጣ::ከተረቱ ሳይቀር የሴትና ያጋላ ቄስ የለውም የሚለው ገደል ገብቶአል ብትሰማኝ እኔ 25%ኦርሞው የበቆጂ ወረገኑ ጀግኖች የልጅ ልጅ በክህነት ስልጣኔ ያንን በዝባዥ አገዛዝና ጀሌዎቹን አውግዣለሁ::አንጋፋው የኦሮሞ መብት አስከባሪ ድርጅት ስህተቱን እያረመ የኦርሞዎች የሚያደርገው ትግል ይቀጥላል::የራስን እድል በራስምወሰን የኦርሞን መብት ማንም ሊቀንስ አይችልም!ከላይ ወገኔ እናድላችሁ የኦርሞን ጉዳይ ለኦርሞ ተዉለት !
“የዚህ ጽህፍ አቅራቢ በጥላቻ የተሞላና እጅግ በጣም የፈራ ግለሰብ መሆን አለበት:: ዛሬም ሃበሾች ሌሎችን ህዝቦች ማክበርና ለፖለቲካ ምርጫቸው ዋጋ መስጠት በጣም የከበዳቸው ነገር ነው::”
What is this Wako?have you read the artcle well? dose it says like that? sayanebu hasab mstet newr new. woy atmaru woy atanebu woy kumneger yelachihu gilblib yalachihu glboch. ahun tehafiw tilacha astlelfal? yeferaws yet lay new? endiawum baygrmeh tehafiu fikir new, jegna new. bendante yale kilras af aynesam, eshi? anete neh jezba fikr yemaygebahna beamara tilacha bado chinkilath yetewotre.
I am deaply sorry for those people who are still praising the develgroup of monster Zenawi,I appriciat the commentetor who gave us clear picture about olf.I also have dout that what kind saff olf leaders have in their mind.This stupied idea was created by one ignorant person called Tadesse biru and followed by those of denbidolo another ignorant group of Dimanegewo and his families.After feudalism the main aim of the revolution was not to dismantle Ethiopia as olf doing now,it was to bring a better life to the Ethiopian people.I have nothing to say because every thing has been told but OLF does not listen or think . IT’s BECAUSE OF THE DITY STAFF THEY HAVE IN THEIR MIND.
ዋቆ ስለራስህ እኒ ያንተ ሃሳብ የኦሮሞን ህዝብ አይወክልም ሊወክልም አይችልም. ወያነ ባሁን ሰሃት የኦሮሞን ህዝብ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እይተዋረደበት ባለበት ዘመን አንተ ነፍተኛ ትላለህ???????????????? ወያነ ስልጣን ላይ ስላለ ነው?????????????? በጣም ትግረማለህ ዘሩ እይተጠራ በየ እስር ቤቱ አስጸያፍ ስዲብ እይተሰደቡኢ ነው ያሉት እና እድሜ ለወያኔ አልክ?????? እንደወያነ የኦሮሞን ህዝን ያዋረደ አለ????? ወሬ አበዛህ እያስተዋልክ ተናገር ጠመንጃ ስለያዘ ነው ወያነ????? በል ዝም ብለህ ነገር ነገር አይበልህ.
derge 2001 yehte niber