ማህደር

ማህደር ለ ‘ዜና’ Category

የወያኔ ኢኮኖሚ፣ የገበያ ኢኮኖሚ፣ የካፒታሊስት ኢኮኖሚ፣ በመንግስት የሚደገፍ ኢኮኖሚ፣ ወይስ ሌላ !ፈቃዱ በቀለ፣ ዶ/ር

February 4th, 2016

በቅድሚያ ለዚህ ጽሁፌ መነሻ የሆነኝ፣ በአለፉት ሃያ አምስት ዐመታት በአገራችን ምድር „የነፃ ገበያ ፖሊሲ“ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ ወዲህ በተሳሳተ መልክ የሚናፈሰውንና በአንዳንድ መጽሄቶች የሚወጣውን የተሳሳተ አመለካከት ለመዳሰስ ነው። በተለይም በገዢው መደብ አንዳንድ አባላት ወይም ሚኒስተሮችም ሆነ በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ስለ ነፃ ገበያ የተሳሳተ አባባል ስለሚነፍስ እንደዚህ ዐይነቱን የተዛነፈና የአንድን አገር ዕድገት የሚያዛባ አነጋገር ማስተካከል ስለሚያስፈልግ የግዴታ ይህንን አጭር ጽሁፍ ለመጻፍ ተገደድኩኝ። በተጨማሪም ውጭ አገር የሚኖሩ በኢኮኖሚክስ ሙያ የሰለጠኑ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ምሁራን የገበያን ኢኮኖሚ ልቅ እንደሆነ ስርዓትና፣ ለሁሉም ተዋናይ የሀብት ክፍፍልን በእኩልነት ደረጃ እንደሚያዳርስ አድርገው ስለሚያቀርቡ የገበያ ኢኮኖሚ ምን እንደሚመስልና በምንስ ዐይነት ውስጣዊ ህጎች እንደሚገዛ ማሳየቱን አመንኩበት። በሳይንስና በህብረተሰብ ዕድገት ታሪክ ባልተደገፈ መረጃ፣ በአንዳንድ የመንግስቱ ተጠሪዎችም ሆነ በሌላ የነፃ ገበያ ኢኮኖሚ ናፋቂዎች፣ “ በነፃ ገበያ መርህ እዚህ አምርተህ እዚህ ሽጥ የሚባል ነገር የለም። አምርቶ የፈለገበት መሸጥ ይችላል።“ የሚለው አነጋገር ሃላፊነት የጎደለው አባባል ብቻ ሳይሆን ልቅነትን የሚያስፋፋ ነው። ድህነት እንዳይቀረፍና ጠንካራ ኢኮኖሚ እንዳይገነባ የሚያግድ እጅግ አደገኛ አነጋገር ነው። በሌላ ወገን ደግሞ እንደዚህ ዐይነቱ አባባልና ተግባራዊ መሆን ጥቂት ሰዎችን የሚጠቅምና የሚያደልብ ነው። በተግባርም እንዳየነው በዓለም አቀፍ ኢንስቲቱሽኖችና የምዕራብ መንግስታት የተደገፈው ነፃ የገበያ ፖሊሲ አዳዲስ ችግሮችን በመፍጠርና፣ በድሮው ላይ በመደረብ ህዝባችን የባሰውኑ እንዲደኸይ መደረጉ ብቻ ሳይሆን፣ ሌላ ኃይል ስልጣን ቢጨብጥ እንኳ ችግሩን ለመፍታት እንዳይችል ብዙ ምስቅልቅል ሁኔታዎችን የፈጠረ ነው። ዛሬ በአገራችን ምድር የተስፋፋው ድህነትና የጥቂቶች ማበጥ የዚህ የተሳሳተ ግንዛቤና የፖሊሲው ውጤት ነው ማለት ይቻላል። አንዳንድ ባለስልጣናት ይህንን በደንብ ሳይታኘክ፣ ፈረንጆች እንደሚሉት ከጭንቅላት ሳይሆን ከሆድ የወጣ አነጋገር የትኛው የኢኮኖሚክስ መጽሀፍ ላይ ተጽፎ እንዳነበቡ ቢነግሩን በጣም ጥሩ ነበር። ሃሳቡን ከዚህኛው መጽሀፍ ላይ ነው የወሰድነው ቢሉን እንኳ፣ ይህ ዐይነቱ አባባል የተፈጥሮ ህግ፣ ወይም ደግሞ እንደ እግዜአብሄር ቃል ተደርጎ መወሰድ የለበትም። ትምህርት ቤት ገብተን የምንማረው ዝም ብለን የሚነገረንን እንደ ዕምነት ለመቀበልና እሱን መልሰን ለማስተጋባት ሳይሆን፣ ከኮመን-ሴንስም ሆነ ከሳይንስ አንፃር አንድ ነገር ትክክል መሆኑንና አለመሆኑን በመመርመር የራሳችንን ፍርድ ለመስጠትና ትክክለኛውን መንገድ ለመያዝና ለሌላው ደግሞ ለማሳየት ነው። የተማሩ ሰዎችም ዋናው ተግባርና ኃላፊነት አንድን ነገር ከሳይንስና ከተጨባጩ ሁኔታ በመመርመርና በማጥናት ለሰፊው ህዝብ ዕውነትን ከውሸት ለመለየት ይችል ዘንድ ትክክለኛውን መንገድ ማሳየት ነው። Read more…

ዜና

የወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄ “የዘረኛነትን ችግኝ ከሥሩ ነቅሎ፤ በአንድነት ቆሞ ዲሞክራሲያዊ መንግሥትን መመስረት” ከደጀኔ አያኖ

February 2nd, 2016

መቼ ነው በሐገራችን ውስጥ እረሃብ የሚጠፋው? ሰርተን፤ በልተን፤ ጠግበን የምንኖረው?
መቼ ነው በተማርነው መሰረት ያለዘመድ ሥራ የምናገኘው?
መቼ ነው ዘረኝነት የሚጠፋው? እኩልነት የሚሰፍነው?
መቼ ነው ዝርፊያው፤ ሙስናውና ብዝበዛው የሚቆመው?
መቼ ነው የሐገሪቷ ሀብት ወደ ውጭ ሀገር የሚሰረቀው? ገንዘቧ የሚራቆተው? የመግዛት አቅሟ የደቀቀው?
መቼ ነው በሐገራችን ኮርተን መኖር የምንችለው?
መቼ ነው በሐገራችን ውስጥ እንደልባችን ሃሳባችንን መግለፅ (በአፍ፤ በፅሁፍ፡ በራዲዮ፤ በቲቪ) የምንችለው? በተነፈስን ጊዜ ሁሉ ግራና ቀኝ የማናየው?
መቼ ነው በሐገራችን ዲሞክራሲን ዕውን የምናደርገው? በነፃ የመወዳደራችን መብት የሚከበረው? በፈልግንበት የፖለቲካ ድርጅት ሥር ለመሥራት የምንችለው? የፈልግነውን ተወዳዳሪ መምረጥ የምንችለው?
መቼ ነው “አምስት ለአንድ” ተደራጅተህ እኔን ብቻ ምረጠኝ የሚለውን የዲሞክራሲ ባላንጣ በፈቃዳችን መገርሰስ የምንችለው? መቼ ነው ድምፃችን በዲሞክራሲ ሕግ እንደ መራጭ ሕዝብ የሚሰማው?
መቼ ነው በሐገራችን ውስጥ በሰላም የምንኖረው? ያለፍርሃት ወጥተን ያለፍርሃት ተመልሰን ወደ ቤታችን የምንገባው?
መቼ ነው በሐገራችን ውስጥ የሕግ የበላይነት የሚከበረው/የሚሰፍነው? መቼ ነው ሕዝብ ያፀደቀው ሕገ መንግሥት የሐገሪቱን ሕዝብ መብት የሚጠብቀው?
እስከመቼ ነው ተምረን እንዳልተማረ፤ የአምባገነኖች ቅጥር በመሆን፤ በዪና አስበዪ የምንሆን? የአምባገነኖች ፖሊሲ አቀንቃኞች፤ ጠበቆች፤ ዳኞች፤ አስተዳዳሪዎችና ወታደሮች የምንሆን?
መቼ ነው ልጆቻችን እናት ኃገራቸውን ለቀው፤ ሞትን መርጠው፤ ወደማያውቁት ህገር መሰደድ የሚያቆሙት? መቼ ነው እንደአያቶቻቸው በኩራት ኃገራቸው/ቀያቸው ውስጥ በኩራት የሚኖሩት? እንደልባቸው ወጥተው እንደልባቸው የሚገቡት?
መቼ? መቼ? መቼ? መቼ? መቼ? መቼ? መቼ? መቼ ነው። Read more…

ዜና

የጎሳ ፖለቲካና ፌደራሊዝም ብሩህ ቦጋለ

January 31st, 2016

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ የምትገኝ የረዥም ዘመን ታሪክ ያላት ሀገር ናት፡፡ ማለትም ከአለም መፈጠር ጋር አብራ የሚስተካከል ታሪክ ያላት እንጂ በዘመን ቆጥሮ እና ለክቶ የኢትዮጵያን ዘመን መወሰን ይከብዳል፡፡ ለእዚህም ሁለቱም የታሪክ ማስረጃዎች ማለትም ሳይንሳዊው እና የጥንታዊ ፅሑፎች ማስረጃች ናቸው፡፡ ይህቺ በአፍሪካ ነፀነታውን ጠብቀው ለመዳር ከቻሉ ሁለት አንዷ፣ አሁን አለም የሚተዳደርበት አለም አቀፍ ሕጎችን በአለም ዲፕሎማሲ እኩል ተከራክራ በቀድሞው የአለም ማህበርም ሆነ በአሁኑ የተባበሩት መንግስታት ምስረታ ላይ ፊርማዋን ያስቀመጠች በጎሳ ላይ ሳይሆን ኢትዮጵያ በሚል ጥንታዊ ስሟ ነው፡፡ Read more…

ዜና

‹‹ማዕከላዊ ነው እንዴ ያለነው?›› (ክፍል ፩) በናትናኤል ፈለቀ

January 27th, 2016

እራሳቸውን ድንገት ስተው ‹‹ኮማ›› ውስጥ የገቡ ወላጅ አባቱን ለማስታመም እና በቅርቡ ሕይወታቸው ያለፈውን አሳዳጊ ሴት አያቱን እርም ሊያወጣ ከ15 ዓመት በላይ ወደተለያት ሀገሩ እየተመለሰ ነው፡፡ ለጉዞው ቀና ብሎ ያሰበው መንገድ ከሚኖርበት ሴንት ፖውል፣ ሚኒሶታ ወደካናዳዋ ቶሮንቶ አቅንቶ ከዛ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አዲስ አበባ ለመግባት እና በማግስቱ አውቶቢስ ተሳፍሮ አባቱን ወደሚያገኝበት የሱማሌ ክልል ከተማ ጎዴ ማምራትን ነበር፡፡ Read more…

ዜና

የነብርን ጭራ አይዙ ከያዙ አይለቁ! ሚክያስ ግዛው

January 27th, 2016

እነሆ እኛ ኢትዮጵያዉያን ህብረት፣ መደጋገፍ፣ ስምምነትና አርቆ አሳቢነት የሚጠይቅበት ወሳኝ ወቅት ላይ ደርሰናል። ያለፉት ዓመታት የወያኔውን ጥቁር ሥርዓት ምንነት አሳይቶናል። ይህንን ብቻ አይደለም፤ በአምባገነን ሥርዓትና ለቅኝ ገዥዎች በባንዳነት በሚያድር ሥርዓት መካከል ያለውን ልዩነትም በሚገባ አሳውቆናል። የንጉሡ ዘመን ኋላ ቀር ነበር። የደርግ ዘመን አምባገነን ነበር። በሁለቱም ሥርዓት ወቅት ግን ሃገር ነበረች። ኢትዮጵያ እስከ ባህረ በሯ ሉዓላዊ እስከ ሕዝቦቿ ክቡር ነበረች። ዛሬ ለየት ያለ ነው። ወያኔ ዘረኛ ብቻ አይደለም። ወያኔ የሙስናዊ አምባገነን ሥራዓት ቋሚ ተጠሪ ስብስብ ተቋም ብቻ አይደለም። ወያኔ “የአናቁረህ ግዛ” ግፍ አራማጅ ብቸኛ የቀማኞች ድርጅት ብቻ አይደለም። ወያኔ ቅድስት ሃገር ኢትዮጵያን ለውጭ ባለሃብቶች የሸበሸበ የኃጢአተኞችና “የአስረሽ ምቺ” ዳንኪረኞች፣ መዝባሪዎች ስብስብ ብቻ አይደለም። ወያኔ የሁሉም የኃጢዓት ሥርዓቶች ድምር ነው። ወያኔ ድንገት ከተሰባሰበበት ደደቢት ሸለቆ ተንከባሉ ሠይጣን ዋሻ ውስጥ ለአመታት ከርሞ ዲያቢሎስ ሳያኝክ የተፋው የርኩስ ሥርዓት ቁንጮ ነው። እድሏ ሆኖ ቅድስት ኢትዮጵያ የዚህ ሥርዓት ተሸካሚ ሆናለች። እንዲያ እንዳልተከበረች፣ እንዲያ እንዳልተፈራች ሃገራችን ኢትዮጵያ ለቅኝ ገዥዎች ቅርጫ ቀረበች። ሥርዓቱ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ኢትዮጵያን በቁሟ የገነዘ፣ ሕዝቧን ያስጨነቀ መሪር ሥርዓት ነው። ኢትዮጵያ ሃገራችንን ከዚህ ሥርዓት የሚገላግላት ቆራጥነትና በህብረት መነሳት ብቻ ነው። ህዝብን በመርዘኛ ራዕይ ሰልቦ፣ ወጣቱን በሥራ አጥነት አጠውልጎ ለስደትና ሴተኛ አዳሪነት እየዳረገ፣ ነዋሪውን በልማት ስምና በከተማ ማስፋፋት እያፈናቀለ ሕዝብን በቅኝ ገዥዎች ቋንቋና በምጣኔ ኃብት እድገት እያደናገረ የሃገሪቱን ሃብት መዝብሮ ወደ ውጭ በማሸሽና በከፍተኛ ዕዳ ውስጥ በመዝፈቅ በጥቂቶች ስም ሃብት እያከማቸ እስከ ዓለም ፍጻሜ ሊገዛ የሚቃጣ ዘመነኛ የግፍ ሥርዓት አራማጅ ወያኔ ብቻ ነው። Read more…

ዜና

መሬት ገላ ነው በበላይነህ ኣባተ

January 24th, 2016
Comments Off

በቦስተን እና አካባቢዋ ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያኖች በሙሉ የቀረበ የእርዳታ ገንዘብ ማሰባሰቢያ ጥሪ ከወ/ሮ አልማዝ መለስ – ቦስተን

January 22nd, 2016

በቦስተን ከተማ የረጅም ጊዜ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ አልማዝ መሰለ በአጋጠማቸው ችግር ምክንያት ለሕግ አማካሪ ክፍያ $60,000,00 የተጠየቁ ሲሆን Read more…

ዜና

ተደጋጋሚጭፍጨፋዎችእንዲቆሙአስጨፍጫፊዎች አስጨፍጫፊዎች አስጨፍጫፊዎችመወገድአለባቸው እኛምኦሮሞዎችነን ከትግራይ ተወላጅ ኢትዮጲያዊያን

January 22nd, 2016

ህብረት ህብረት ህብረት አሁንም ህብረት በገለታው ዘለቀ

January 13th, 2016

በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ግፍና የፍትህ መጥፋት ስለበዛ ህዝባዊ አመጽ በሁለት መንገድ ሊነሳ ይችላል ሲሉ ቆይተዋል አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች። አንደኛው ህዝብ ራሱ ድንገት የሚያነሳውና የሚመራው (spontaneous አመጽ) ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በፖለቲካ ወይም በሲቪክ በተደራጁ ሃይላት ታቅዶ የሚመራ በቅስቀሳና በጥሪ የሚነሳ ሊሆን ነው። ከወር በላይ የሆነውና በኦሮሞ ክልል ውስጥ በሰፊው የተነሳው ተቃውሞ የአዲስ አበባውን ማስተር ፕላን ተከትሎ የተፈጸመውን ማፈናቀል እንደ ማቀጣጠያ አድርጎ የተነሳ በህዝብ የተመራ ህዝባዊ አመጽ ሆኖ ብዙ ሰው በሚገባ እንደተረዳው የህዝቡ ጥያቄ የመንግስት ለውጥ ጥያቄ ነው። ለብዙ ዓመታት ታምቆ የቆየ የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ እጦት፣ የመሬት ነጠቃው ጉዳይ ናቸው ዛሬ ይህን ህዝብ አስመርረው- አስመርረው ጎዳና ላይ ያወጡት። ህዝቡ በየቦታው ሲጨፍርና መፈክር ሲያሰማ በአብዛኛው ይል የነበረው በመረጥነው እንተዳደር፣ ፍትህ ፣ነጻነት፣ የመሬት ነጠቃው ይቁም፣ መሬታችን የኛ፣ የመሳሰሉትን ነው። ይህ የሚያሳየው የህዝቡ ጥያቄ የስር ነቀል ለውጥ ጥያቄን ያዘለ መሆኑን ነው። ይህ ጥያቄ በርግጥ የሁሉ ኢትዮጵያውያን ጥያቄ ነው። ዛሬ በኦሮምያ ጠንከር ያለ ተቃውሞ እየተሰማ በሌሎች አካባቢዎች ተቃውሞው እምብዛም ያልሆነበት አንዱ ምክንያት የአዲስ አበባውን ማስተር ፕላን ተከትሎ የህዝብ ቁጣ ሲገነፍል የኦሮሞ ወጣቶች በተወሰኑ አካባቢዎች የህዝብ ግንኙነት ስራ መስራታቸውና ወጣቶች ማህበራዊ ድረ ገጾችን እየተጠቀሙ ትግሉን በማቀጣጠላቸው ነው። በሌሎች አካባቢዎች የውስጥ ለውስጥ ስራዎች እምብዛም አልተሰሩምና ተቃውሞውን ማቀጣጠል አልተቻለም እንጂ በደል በሁሉም ክልሎች እስከ ጥግ ድረስ አለ። Read more…

ዜና

በውጥረት ላይ ውጥረት መደራረብ ይቁም! (አፈንዲ ሙተቂ)

January 8th, 2016

ሰሞኑን በኦሮሚያ እና በሰሜን ጎንደር የተከሰተው የተቃውሞ ንቅናቄ ሀገሪቱን ውጥረት ውስጥ ከትቷታል፡፡ አመጹ እየተጋጋለ መሄድ እንጂ የመቀዛቀዝ ባህሪ አላሳይ ብሏል፡፡ አሁንም በልዩ ልዩ አካባቢዎች ቀጥሏል፡፡ በአራቱም አቅጣጫዎች ውጥረት ሰፍኗል፡፡ በህይወት ዘመኔ ይህንን ያህል ዘላቂ ሆኖ የቆየ አመጽ አይቼ አላውቅም፡፡ በዚህ አመጽ ለጠፋው ህይወትና ንብረት እናዝናለን፡፡ በየትኛውም ወገን ሆኖ በትርኢቱ ውስጥ የተሳተፈው የኛው ዜጋ በመሆኑ ነፍሱና አካሉ ታሳዝነናለች፡፡ Read more…

ዜና