ማህደር

ማህደር ለ January, 2009

ቆሞ ከመሄድ በፊት ብዙ ጊዜ መውደቅ አለ

January 15th, 2009

ዳኛቸው ቢያድግልኝ / ጥር 5 ቀን 2001 ዓ.ም.

ኢትዮጵያውያን እንኳን ደስ አላችሁ

አንዳንዶቻችን አቤቱ ወደ ፈተና አታግባን እያልን ዳር በቆምንበት ሰዐት ፈተናችንን እንቀበል ዘንድ ብርታትን፣ በአሸናፊነት እንወጣው ዘንድ ጥበብን አብዝተህ ስጠን ያሉ ፈጥነው እየገሰገሱ ነው።

Read more…

ዜና

በአዲስ አበባ በተለምዶ መርካቶ አውቶብስ መናሀሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በፈነዳ ቦንብ 32 ሰዎች ቆሰሉ፡፡

January 15th, 2009

አቡጊዳ / ጥር 6 ቀን 2001 ዓ.ም.

ዛሬ አንድ ሰአት አካባቢ በፈነዳው ቦንብ ዘጠኝ ሰዎች ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፤ 23ቱ የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ ተደርጎላቸው ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል፡፡ Read more…

ዜና

የወ/ት ብርቱካን መታሰር የአዉሮፓን ፓርላማ አስቆጣ!

January 14th, 2009

የኢትዮጵያ ፎረም ድህረ ገጽ እንደዘገበዉ ዛሬ የአዉሮፓ ፓርላማ ባወጣዉ መግለጫ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ መታሰራቸዉ በጣም ያስቆጣዉ እንደሆነ ገለጸ። ፓርላማዉ የኢትዮጵያ መንግስት ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ ወ/ት ብርቱካን በአስቸኳይ እንዲፈታ ጠይቀዋል።

የአዉሮፓ ሕብረት ዛሬ በቤልጂየም በሉሽማበርግና በሆላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ከፍተኛ ሰላማዊ ሰልፍ ማደረጋቸዉ ይታወቃል። ይህም ሰላማዊ ሰልፍ በመደረጉ ምክንያት የአዉሮፓ ሕብረት የኢትዮጵያ ጉዳይ እንዲነጋገር እንዳደረገዉ ለማወቅም ችለናል።

የሕወሃት አገዛዝ ዛሬ እንደተደረገዉ ኢትዮጵያዉያን በተባበረ ሁኔታ ከተሰባሰቡ በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ሙሉ ለሙሉ እርቃኑን ሊያስቀሩት እንደሚችሉና ከምዕራባዉያን የሚያገኘዉን የልመና ገንዘብ ማስቀረት እንደሚችሉ ብዙዎች ይናገራሉ። አገዛዙ ከዉቭ የሚያገኘዉን እርዳት ካጣ ከአራት ሚሊዮን በላያ ለሚሆኑ ሰላዮቹ፣ ለአጋዚ ወታደሮቹና በገንዘብ ለሚገዛቸዉ ካድሬዎች የሚከፍለዉ አይኖረዉም ሲሉ የፖለቲካ ተንታኞች በዉጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያን በርግጥ ኢትዮጵያን ማዳን እንደሚችሉ ያስረዳሉ።

መንግስቱ ኅያለማሪያም የሶቪየቱ ጎርባቾቭ እርዳታዉን ሲነፍገዉ በአጭር ጊዜ ዉስጥ እንደወደቀ ሕወሃት የሚደግፉት የዉጭ ኃይሎች ድጋፋቸዉን ከነፈጉት ፋጻሜዉ ይሆናል።

ዝርዝሩን ለማንበብ የሚከተለዉ አድራሽ ይመልከቱ ፡

http://ethioforum.org/wp/archives/730

ዜና

የተቃዉሞ አለማቀፍ ሰላማዊ ሰልፎች – LIVE UPDATE

January 13th, 2009

ረእቡ ጥር 6 ቀን 2፡53 PM ሲያትል ዋሺንግተን

ኢትዮጵያዉያን በሲይትል ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ እያደረጉ ነው። በአሁኑ ወቅት በሲያትል ሲቪክ ሴንተር መፈክሮችን እያሰሙ በሕወሃት መንግስት እየተደረጉ ያሉትን ግፎች ተቃዉመዋል። አቶ ሙሉነህ ዮሃንስ የአንድነት ድጋፍ ማህበር በሲያትል አመራር አባል እንደገለጹልን ሰልፉ ከሲቪኽ ሴንተር ወደ ፌዴራል ቢልዲንግ በማምራት በሁለቱም የዋሺንግተን ሴኔተሮች ጽ/ቤት ቀጠሮ እንደተያዘና በዚያም ያለዉን ኣሳዛኝ ሁኔታ በሰፊዉ ያስረዳሉ።

ሰልፈኖቹ ከሚያሰሙት መፈክሮች መካከል « ብርቱካን ትፈጣ፣ ቴዲ አፍሮ ይፈታ» የሚሉና አሜሪካ፡በኢትዮጵያ ያላትን ፖሊሲ እንድትቀይር የሚጥይቁ በርካታ መፈክሮች ነበሩ።

ረእቡ ጥር 6 ቀን 2፡30 PM ዋሺንግተን ዲሲ አሜሪካ

የዋሺንገትን ዲስ ታላቅ ሰላማዊ ስልፍ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል። በርዱ እጅግ በጣም ኃይለኛ በሆነበት ሁኔታ ይሄን ያህል ወድ ኣንድ ሺህ የሚጠጋ ሰዊ መምጣቱ እጅግ ትልቅ ድል ነዉ ብለዉታል በስፍራዉ የነበሩ ሰልፈኞች። ወረድ ብለን እንደዘገብነዉ በምርጫ ዘጠና ሰባት ወቅት እንደነበረዉ አይነት እንቅስቃሴ እንደተጀመረ የሕወሃት መንግስት ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን ማሰሩ በራሱ ላይ ፍም እንደመነስነስ ነዉ የሚቆጠረዉ የሚሉ በርካቶች ነበሩ።

የዋሺንገትን ዲስ የአንድነት ድጋፍ ድርጅት ሊቀመንበር ለሰልፈኛዉ ያስተላለፉት አንድ ዋና አብይ መልእክት ነበር። እርሱም ይህ አይነቱ የተቃዉሞ ሰልፍ ዛሬ ብቻ ተደርጎ የሚያቆም እንዳልሆነ ነዉ። ሰልፉና ንቅናቄዉ ከአሁን በኋላ እየተጠናክረ እንደሚሄድ ገልሰዉ የሚቀጥለዉ ሰልፍ ማርች ሁለት ቀን እንደሚደረግና ዝግጅቱም ከዛሬ እንደሚጀመር ለሕዝቡ ተናግረዋል።

ረእቡ ጥር 6 ቀን 2:15 PM – ፍራንክፈርት ጀርመን ክፍል ሁለት

«በጣም የሚያስደንቅ ሰልፍ ነበር። ባብር ጣቢያዉ በጣም ተጨናንቆ ነበር። ፖሊሶች ቸግሯቸዉ እንደገና እርዳታ ለመጠየቅ ተገደዋል።ከአራት መቶ እስከ አምስት መቶ ኪሎሜትሮች የነብርቱካን ሚደቅሳን የነቴዲ አፍሮን የነኢንጂነር ኃይሉን ፎቶ በመኪናቸዉ እየለጠፉ ነበር የመጡት። የጀርመን ዜጎች እየተገረሙ የት አገር ነዉ ብለዉ ሲጠይቁ ነበር። » ብለዉ ኢንጀነር ሊሻን ለከረንት አፌር ዉይይት ክፍል የተናገሩት። ኢንጂነር ሊሻን ሲናገሩ በተለይም የሰቶች መብዛት አስገርሟቸዋል። « እንደዚህ ብዛት ያለዉ ሴት ከየት እንደመጣ ሊገባኝ አልቻለም። ከበሮ ጥሩምባ ፊሽካ ይዘዉ ነበር የመጡት » ብለዉ ሴቶች እህቶቻችንና እናቶቻችን የትግሉ ቀዳሚ እየሆኑ መሆናቸዉን ገልጸዋል።

ሰልፈኞቹ በወያኔ ቆንሱል ጽ/ቤት ፊት ሰልፍ ያደረጉ ሲሆን ቆንስሉ በዛሬዉ ቀን ተዘግቶ ዉሏል። የቆንስሉ ሰራተኞች ሰልፈኞችን ተደብቀዉ በመስኮት በቪዲዮ ይቀርጹ ነበር። ፖሊሶቹ እስኪገረሙ ድርስ ወያኔ እንዳፈረ ለመረዳት ችለናል። ቪዲዮ ለመቅረጽ ሲሞክሩ ሰልፈኛዉ የቅንጅትን የሁለት ጣት ምልክት በማሳያት «አንፈራም ቅረጹን» እያለ ሕወሃት ምን ያህል የተተፋ ድርጅት እንደሆነ ለማሳየት ተሞክሯል።

አቶ ሊሻን ሲናገሩ በሰልፉ የነበሩት ሴቶች መቼ ነዉ ሰላማዊ ሰልፍ እንደገና የምናደርገዉ ? ይኼ ቂንሱል ለኢትዮጵያ አልተቀመም። መዘጋት አለበት» ብለዋል።

ይህ ቆንስል ከአምስት ቀናት በኋላ ኦባማ ፕሬዘዳንት መሆኑን ለማክበር ግብዣ ያድርጋል። ይህ ግብዣ የሚደረግዉ የኢትዮጵያን ደም ፈሶ እንደሆነ በመጠቆም በዚህ ግባዥ ሰዎኢች እንዳይገኙ ለማድረግ ከፍተኛ ዘመቻ እንደሚደረግ ለማወቅ ችለናል።

ረእቡ ጥር 6 ቀን 1፡00 PM – ጄነቫ ስዊዘርላንድ

«ተከብረሽ የኖርሽዉ ባባቶቻን ደም ባባቶቻችን ደም

እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይወደም የደፈረሽ ይወደም»

እያሉ ነበር በሲዘርላንድ በከፍተኛ ብርድ ኢትዮጵያዉያን ጄጄቫን ያጨናነቁት። በተባበሩት መንግስታት ጽ/ቤት ፊት ለፊት መፈክሮችን በማሳየት ጩኸታቸዉን በማሰማት ነበር የኢትዮጵያ አርንጓዴ ቢቻ ቀይ ሰንደቅ አላማ እያዉለበለቡ ወያኔ በኢትዮጵያ እያደረግ ያለዉን ግፍ የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ የቴዲ አፍሮ የበቀለ ጂራታና ሌሎች የህሊና እስረኞችን መታሰረ ተቃዉመዋል።

BubbleShare: Share photosEasy Photo Sharing

“The International Community Open Your Eyes. The International Community Open your Ears. Do not support dictators, Do not support Tyrants” እያሉ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ድምጻቸዉን እንዲሁም እየተበደለ ያለዉን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያዳምጥ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለዉን ግፍ እንዲመለከት ጥሪ አቀርበዋል።

ሰልፈኞቹ « መለስ ኢትዮጵያን አይወክልም ! መለስ ለፍርድ ይቀርባል» እያሉ አሁን በኢትዮጵያ ያለዉ አገዛዝ እድሜዉ በጣም አጭር መሆኑን በዜማ ገልጸዋል።

የሲያትል ነዋሪና የአንድነት ሲያትል ድጋፍ ድርጅት ዉስጥ የሚሰሩት ጠበቃ ሼክስፒር ፈይሳ እንዳጋጣሚ ሆኖ ዛረ በጄነቫ ስከነበሩ በሰልፉም ተገኝተዉ በሕዝቡ ብዛትና በሰልፍ ድምቀት የተደነቁ እንደሆኑ ለክረነት አፌር ዉይይት መድረክ ገልጸዋል። « ባንዲራ ይዘዉ እንዲህ በዳመቅ ሁኔት ሲንቀሳቀሱ ሳይ በጣም ነዉ ያኮሩኝ ። ይኸዉ ለፍትህ ለዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ እየጮሁ ነዉ» ነበር ያሉት።

ረእቡ ጥር 6 ቀን 12፡40 PM -ለንደን እንግሊዝ

«ብርቱካን ሚደቅሳ የኢትዮጵያ አንበሳ

የወያኔ ኑሮ ይለያል ዘንድሮ»

በለንደን በተደረገዉ ሰላምዊ ሰልፍ እጀግ በጣም በርካታ ኢትዮጵያዉያን በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ንቤት ፊት ለፊት በመገኘት የእንግሊዝ መንግስት በአምባገነንነት ላይ አቋም እንዲወስድ ጠይቀዋል። ከቀረቡት መፈክሮች ዉስጥ የሚከተሉት ይገኛሉ።

«Gordon Brown, the British Parlaiment Stop Supporting The Killers,

Gordon , the British Parlaiment Stop financing Meles, stop supporting massacres.

Gordon , the British Parlaiment Stop supporting the Tyrant of Ethiopia,

Gordon Borwn, the Bristih Parlaiment Stop the killing in Ethiopia, Stop the Killing in Ogaden

Meles is the Killer.

We want Justice in Ethiopia.

Unity for Ethiopia.

One Nation, on People On Ethiopia .

Free Birtukan Mideksa.

Free Teddy Afro.

Free Bekele Jirata

ብርቱካን ፍትህ ናት፣ ቴዲ አፍሮ ፍቅር ነዉ ፣መለስ ገዳይ ነዉ

ብርቱካን ፍትህ ናት፣ ቴዲ አፍሮ ፍቅር ነዉ በረከት ስምዖን ገርይ ነዉ>> የሚሉ ነበሩ።

የለንደን ሰላማዊ ሰልፍ አዘጋጆች የአየሩ ሁኔታ በጣም በርድ ሆኖ ይሄን ያህል ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ መቻሉ ኢትዮጵያዉያን በርግጥ አገራቸዉን ነጻ ለማዉጣት ቆረጠዉ እንደተነሱ ያሳያል ብለዋል።

በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ አቶ ወንድሙ መኮንን ልብ የሚቀሰቀስ ንግግር አድርገዋል። ለታሰረዉና ለሚቨቆነዉ ወገናችን ድምጽ እንሆንለታለን ብለዋል። የስላምና የፍቅር መልዕክተኛ የሆነዉን ቴዲ አፍሪኦን ባላጠፋዉ ጥፋት ከሰዉ እርሱን ለማስፈታት እየተዘጋጀን እንዳለ በእንቀርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሚባለዉ የዲሞክራሲ ጀግና የሆነችዉን ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ጠመንጃ የታጠቀ ወንበዴ እንደሚይዘዉ ተረባረበዉ ያዟት « ሲሉ ወያኔ እያደረገ ያለውን አዉግዘዋል።

አቶ ወንድሙ መኮንን በመከተል በለንደን የአንድነት ድጋፍ ማህበር አስተባባሪ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ዘላላም « የወያኔ ጥንካሬ በኛ ድክመት ነዉ። እያንዳንዳችን አሁን ካደረግነዉ የበለጠ ለአገሬ ምን ላድርግ ብለን እየጠየቅን ኢትዮጵያ ለማዳን እራሳችን ለትግል እንድናሰልፍ ያስፈልጋል» ብለዋል።

ረእቡ ጥር 6 ቀን 12፡15 PM – ብራሰልስ

የአዉሮፓ ሕብረት ዋና ጽ/ቤት በሚገኝበት በብራሰልስ ቤልጂየም እጀግ በርካታ ኢትዮጵያዉያን ከሆላንድና ከበልጂየም ተሰባስበዉ ድምጻቸዉን አሰምተዋል። የጀርመን ድምጽ ሬዲዮ እንደዘገበዉ ሰልፉ እጀግ በጣም በርካታ ሰዎች የተገኙ ሲሆን ለአዉሮፓ ሕብረት ባለስልጣናት በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለዉን የዲሞራሲና የስብዓዊ መብት ረገጣ አስረድተዋል።

የሰልፉ አስተባባሪ አቶ ደረጀ ሃብተወልድ ስለ ሰልፉ አላማ ለጀርመን ድምጽ ሬዲዮ ሲናገሩ « በኢትዮጵያ የፍትህ መጓደል እንዳለ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ለማዳከም የሚደረገዉን ተግባር ለመቃወምና እንዲሁም ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማጋለጥና የአለማቀፉ ኮሚኒቲ ጫና እንዲያደርግ ለመጠይቅ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል።

ሰልፈኛዉን ወክለዉ ሶስት ኢትዮጵያዉያን ከአዉሮፕ ሕብረት ባለሥልጣናት ጋር ተነጋግረዋል። ከነዚህ ዉስጥ አንዱ የነበሩት ዳኛ መሸሻ ወልደሚካኤል ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉን ሁኔታ አስረድተናል። ያቀረብነዉን ሁሉ ተቀብለዉናል። » ሲሉ በሕግ ባለሞያዎች ተዘጋጀ ሰነድም ለባለስልጣናቱ አቅርበዋል።

ረእቡ ጥር 6 ቀን 12፡00 PM – ፍራንክፈርት ጀርመን

በፍራንክፈርት ጀርመን አገርም ክፍተኛ ሰላምዊ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል። በጣም ብዙ ኢትዮጵያዉያን የተገኙ ሲሆነ ከስብሰባዉ ተካፋዮ ከግማሽ በላይ ሴቶች እንደነበሩ ለማወቅ ችለናል። ከዲጃ ትባላለች ሌላ ከተማ ለሰልፉ ወደ ፍራንክፈርት የመጣችዉ። «ብርቱካን አለ አጋባ በግፍ መታሰሯን ልቃወም ነዉ የመጣሁት» ነበር ያለችዉ።

«ከአራት አመት ሕጻን ልጇ ቴንጥላ ወደ እሥር ቤት መግባት ትልቅ ችግር ነዉ። እኔም ሴት እንደመሆኔ ይገባኛል። ልጅ አስቀምጦ ወድ እሥር ቤት መሄድ ቀላል አይደለም። እርሷ ይሄ የደረሰባት ለአገሯ ነዉ። ለአገሯ ይህንን ስቃይ ማየቷ ያስደስታታል አገሯን ስለምትወድ። ነገር ግን የደረሰባት ሁኔታ በጣም በጣም ያሳዝናል» ያለችዉ ደግሞ ሌላዋ ኢትዮጵያዊት ሄለን ነበረች።

የአምሳ አምስት አመት እናት ወ/ር ብርክቲ «ዲሞክራሲ እንፈልጋለን። ስደት ሰልችቶናል። ዲሞክራሲ እንዲመጣ እንታገላለን። እንደምናገኝም አንተራጠርም» ሲሉ ሶፊያ የምትባል ወጣት «ብርቱካን የመለሰቸዉ መልስ ትክክለኛ መልስ ነዉ። የዲሞክራሲ መብቷን ነዉ የተጠቀመቸዉ። መታሰሯ ዲሞክራሲ እንደሌለ የሴቶች መብት እንደማይከበር ያሳያል» ብላለች።

በፍራንክፈርት በተደረገዉ ሰልፍ የጀርመን መንግስት ባለስልጣናት ዘንድ በመሄድ በአማራኛ በእንግሊዘኛና በጀርመንኛ መፈክሮችን በማሰማት የጀርመን መንግስት በአምባገነኑ አገዛዝ ላይ ተጽኖ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

በቅርቡ የጀርመን የአለም አቀፍ ተራድኦ ሚኒስተር ወ/ሮ ሃይደማሪ ዊዘር-ዜል ለአቶ መለስ በጻፉት ደብዳቤ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳና ሌሎች የፖለቲካ መሪዎች ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ መፈታት እንዳለባቸዉ ማሳሰባቸዉ የሚታወስ ነዉ።

በሰልፉ ከቀረቡት መፈክሮች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል። <> እንዲሁም በርካታ መፈክሮች ነበሩ”

ቅዝቃዜዉ እጀግ በጣም የበረታ እንደነበረም ለማወቅ ችለናል።

ረእቡ ጥር 6 ቀን 11፡05 AM – ዋሺንግተን ዲሲ አሜሪካ

የዋሺንግተን ዲስ ሰላማዊ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል። «ብርዱ አይጣል ነዉ» ነበር ያሉት በሰልፉ የተገኙ ኢትዮጵጵያዉያን። በአካባቢዉ የነበሩ የዉጭ አገር ዜጎች በዚህ ቆዳ በሚያሸማቅቅ ብርድ ሰልፍ ለማድረግ ኢትዮጵያዉያን መዉጣታቸዉ በጣም ያስገረማቸዉ ሲሆን አንዳንዶቹም አይዟቹህ ሲሉ ነበር።

የስለፉ ማስተር ኦፍ ሴሬሞኒ የአዲስ ድምጽ ረድዲዮ አዘጋጅህ አቶ አበበ በለዉ ነበሩ። አቶ አበበ በለዉ ሰልፈኛዉን እንኳን ደህና መጣህ ካሉ በኋላ የዋሺንገትን ዲሲ የአንድነት ድጋፍ ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ዓለማየሁ አበበ ንግግር አደግረዋል። አቶ አለማየሁ አበበ እንደጨረሱ የኢሕአፓ ዴሞክራሲያዊ ተወካይ አቶ በቃሉ አያሌዉ ሲከተሉ በመጨረሻ አርቲስት ታማኝ በየነ ቀስቃሽ ንግግር አድርገዋል።

ፎቶ በቴዎድሮስ መክብብ

ሰልፈኛዉን በመወከል የሰሜን አሜሪካ የአንድነት ድጋፍ ማህበር የዲፕሎማሲ ኤክስፐርት አቶ ንጉሴ ነጋና ወ/ሮ ሙሉ የፖለቲካ እሥረኞች ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ የአሜሪካን መንግስት ከፍተኛ ተጽኖ እንድታደርግ የሚጠይቅ ደብዳቤ በስቴት ዲፓርትመንት የኢትዮጵያ ዴስክ ሃላፊ ለሁኑት በእጃቸዉ አስረክበዋል።

አቶ አበበ በለዉ ሲናገሩ በዚህ ወደ 20 ዲግሪ ፋራናይት በሚደርስ ከፍተኛ ብርድ ወደ አንድ ሺህ የሚጠጋ ሰልፈኛ መምጣቱ በጣም የሚያስደስትና በምርጫ ዘጠና ሰባት አካባቢ ወደነበረዉ የሕዝብ መነቃቃትና መነሳሳት እየተመለስን ነዉ ብለዋል።

ፎቶ በቴዎድሮስ መክብብ

አቶ አለማየሁ አበበን አነጋግረን እንዲህ አይነቱ ስለፍ በተጠናከረና በተደራጀ መልኩ የሚቀጥል እንደሆነ አስገንዝበዉ ከአሁን በኋላ ወደፊት እንጂ ወደ ኃላ አንመለስም ብለዋል።

ረእቡ ጥር 6 ቀን 10፡05 AM ዋቺንግተን ዲስ አሜሪካ

ዋቺንግተን ዲስ ከወትሮ የተለየ እጅግ በጣም ኃይለኛ ብርድ ነዉ። ኢትዮጵያውያን ድምጻቸዉን ለማሰማት የአሜሪካን ስቴት ዲፓርትመንት ፊት ለፊት ታልቅ ሰላምዊ ሰልፍ እያደረጉ ነዉ። እስከአሁን በደረሱን ዘገባዎች ወደ አንድ ሺህ የሚጠጉ ሰልፈኞች በብርድ ድምጻቸዉ እያሰሙ የብርቱካንና የቴዲ አፍሮን ፎቶግራፎች ያሉባቸዉን ታፔላዎች ይዘዉ የኢትዮጵያ አረንጓደ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ አላማ እያዉለበለቡ በአማረኛና በእንግሊዘኛ መፈክሮችን እያሰሙ ነዉ። «ብርቱካን ትፈታ – ቴዲ ይፈታ – በቀለ ይፈታ – Shame on you Rice- Shame on you Bush – What have you done for Africa ?» ከመፈክሮቹ ጥቂቶቹ ነበሩ።

በርካታ የሲቪክ ማህበራት መሪዎች፣ የፖለቲካ ድርጅት ተወክዮች የሴቶች ማህበራት የኪነት ባለሞያዎች በብዛት የተገኙ ሲሆን በሰልፉ የነበሩት ኢትዮጵያውያን ሕወሃት እየአደረግ ባለዉ ግፍ እጅግ መቆጣታቸዉንና መበሳጨታቸዉን በስፍራዉ ላሉ የአቡጊዳ ዘጋቢዎች ገልጸዋል።

በአዉሮፓም በተመሳሳይ ሁኔታ ከፍተኛ ሰላምዊ ሰልፎች ተደርገዉ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቃቸዉ ከአዉሮፓ ምድር የደረሰን ዜና ይገልጻል። ከአዉሮፓ መረጃ ዝርዝር እረጃ እንደደረሰን እናቀርባለን።

ማክሰኞ ጥር 5 ቀን 10፡36 PM

ነገ ረእቡ ጥር ስድስት ቀን የሕወሃት/መንግስት እያደረገ ያለዉን ግፍ በመቃወም በአለም አቀፍ ደረጃ ታላላቅ ሰላማዊ ሰልፎች ይደረጋሉ። በዉጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሥጋቸዉ በባእዳን አገራት ቢሆንም መንፈሳቸዉ ግን ከሚወዱት በኢትዮጵያ ዉስጥ ከሚኖረዉ ሕዝባቸዉ ጋር ነዉ። ንጹህ ኢትዮጵያዉያን ሲታሰሩ እነርሱም ባይታሰሩም ታስረዋል። ኢትዮጵያዊያን ሲደበደቡም እነርሱም ባይደበደቡም ተደብድበዋል። እነርሱም ይሰማቸዋል። እነርሱም ያማቸዋል። ስለዚህ የሕዝቡ ድምጽ ሆነዉ ይጭሃሉ። የሕዝቡን ብሶት ለአለም መንግስታት ያሳወቃሉ።

የሕወሃት መንግስት በኢትዮጵያዉያ ላይ እያደረሰ ያለዉን ግፍ በመቃወም፣ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ፣ አቶ በቀለ ጂራታ፣ ወጣት ቴዲ አፍሮና በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የፖለቲካ እሥረኞች ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፎች በዋሺንግተን ዲስ፣ በሲያትል፣ በስዊድን፣ በለንደውን፣ በፍራንክፈርት፣ በካልጋሪ በብራሰልስ በኖርዌይና በስዊዘርላንድ ይደረጋሉ።

ሕወሃት/ኢሕአዴግ መልቲፕል ፐርሰናሊቲ (በርካታ መልኮች) ያሉት ድርጅት ነዉ። የሚሰራዉ ሥራ ሌላ .. ነገር ግን መልኩን ቀይሮ የዲሞክራሲና የእድገት ማስክ (ሽፋን) አጥልቆ ሕግ እንደሚያከበር፣ ለዲሞርክራሲ የቆመ እንደሆነና ሰብአዊ መብትን እንዲሚያከበር አድርጎ እራሱን ለአለም ያቀርባል። እርዳት የሚሰጡትን ያጭበረብራል። ሊጭበረበሩለት ያልቻሉትን እንደነ አና ጎሜዝ አይነቶቹን ደግም ያጥላላል።

ወ/ት ብርቱካን ይህን የወያኔ ማስክ ገፋዋለች። ወያኔ ሕግ የማያከበር የዱርየ መንግስት እንደሆነ አጋልጠዋለች። ታዲያ እርሷ የጀመረቸዉን ወያኔን የማጋለጥና የማራቆት ሰላምዊ ትግልን ለመቀጠል ፣ የለኮሰችዉን የነጻነት ችቦ የበለጠ ለማቀጣጠል ነዉ ኢትዮጵያዉያን በፉጨት ተጠራርተዉ የሕወሃትን ማንነት የበለጠ ለማጋላጥ ሰልፍ የሚወጡት።

«ዳያስፖራዉ ወረተኛ ነዉ። ለትንሽ ጊዜ ተነፍቶ ይተነፍሳል» እያሉ የሕወሃት ካድሬዎች ማወራታቸዉ አይቀሬ ነዉ። ነገር ግን ዳያስፖራዉ ምንኛ በኢትዮጵያ ለዉጥ እንዲመጣ እንደቆረጠ ከነገ ጀምሮ በየጊዜዉ በሚደረጉ ተከታታይ እንቅስቃሴዎ ያዩታል።

እነዚህ ሰላማዊ ሰልፎች በአጭር ጊዜ ወስጥ የተጠሩ ሰላማዊ ሰልፎች ሲሆነ በአጭር ጊዜ ዉስጥ በዉጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን እንደዚህ መንቀሳቀስ መቻላቸዉ ምን ያህል የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ መታሰር ትልቅ የፖለቲካ ነዉጥን እንዳመጣ ፣ ምን ያህል ኢትዮጵያዉያንን እንዳሰባሰበ አንዱ ሌላዉ ምልክት ነዉ።

የዋሺንግተን ዲሲና ሌሎች ሰላማዊ ስለፎችን እየተከታተለን ያሉ አበይት ዜናዎችን እናቀርብላቹሃለን።

ዜና

ለዉጥ የጠማዉን ሕዝብ በኃይል ማንበርከክ አይቻለም – ከትግራይ ተወላጆች

January 13th, 2009

ወይዘሪት ብርቱኳን ሚዴክሳ የአንድነት ፓርቲ ሊቀ መንበር በፓሊስ ተይዘው መታሰራቸውን አስመልክቶ ከዓለም አቀፍ የትግራይ ተወላጆች ሕብረት ለፍትሕና ዲሞክራሲ የተሰጠ መግለጫ::

Read more…

ዜና

ወ/ት ብርቱካን ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ ትፈታ ሲሉ ሴኔተሮች አሳሰቡ!

January 13th, 2009

አቡጊዳ / ጥር 4 ቀን 2001 ዓ.ም.

የሴኔት የአፍሪካ ጉዳይ ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ የዊስኮንሲኑ ሴኔተር ራስ ፋይንጎልድና የሴኔት ፍትህ ሙሉ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት የቨርሞንቱ ሴኔትር ፓትሪክ ሌሂ፣ የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን መታሰር አስመልክቶ ደብዳቤ ለአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዶ/ር ኮንዶሊሳ ራይስ ዛሬ መጻፋቸዉን ከኮንግረስ አካባቢ የደረሰን ዜና ያረጋገጣል።

Read more…

ዜና

አዎ! ለኢሮብ ህዝብ ኢትዮጵያዊነቱ የማይገሠሥ ክብሩ ነው።

January 13th, 2009

የችግሩ ጥልቀት ካሳሰባቸው የኢሮብ ተወላጆች / ጥር 4 ቀን 2001 ዓ.ም.

እ.ኤ.አ 22 Dec. 2008 “Tiny Ethnic group claim Ethiopian allegiance in border row with Eritrea” በሚል ኤ. ኤፍ. ፒ (AFP) ያወጣውን ዘገባ በአንክሮ ተመልክተነዋል።

Read more…

ዜና

በእውነት የታመመ ድረ-ገጽ

January 13th, 2009

ከታዛቢ / ጥር 4 ቀን 2001 ዓ.ም

ሰሞኑን “ደብተራው-በግማሸ የሰድብ ድረ-ገጽ” በሚል ርእሰ ሰለ ድረ-ገጹ ጥቂት ጠቃሚ ወቀሳዎችን ስንዝሬ ነበር። የወ/ት ብርቱካንን መታሰር አሰመልክቶ በአንድ ገለሰብ በድረ-ገጹ ቀርቦ የነበረው ርካሽና ባለጌ ጽሁፍ የወቅሳዬ ዋና መነሻ ቢሆንም፤ ሶሰት ተቀራራቢ ጉዳዮችን በጽሁፌ ጠቅሻለህ። እነሱም ደብተራው፦

Read more…

ዜና

ኢትዮጵያ በመለስ እጅ – ኢትዮጵያ በጠላት እጅ

January 12th, 2009

ጽሁፍ፦ በ ተስፋይ አፅብሀ እና ካህሳይ በርኽ

ውርስ ትርጉም – ታሪኩ አባዳማ – ክፍል 5 የመጨረሻ / ጥር 3 ቀን 2001 ዓ.ም.

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!

ዜና

ከአዲስ አበባ የደረሱን ዜናዎች

January 12th, 2009

አቡጊዳ / ጥር 3 ቀን 2001 ዓ.ም.

የሕወሃት መንግስት በግፍና ሕገ ወጥ በሆነ አኳኋን የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ከወሰደ አሥራ ሁለት ቀናት ሆነዋል። በነዚህ ቀናት በአገር ዉስጥም ሆነ ከአገር ዉጭ አገዛዙ ከፍተኛ ተቃዉሞና ወገዛ እየደረሰበት መሆኑ በየጊዜዉ የሚወጡት መግለጫዎች ያሳያሉ።

Read more…

ዜና