ማህደር
ቀኑ ዛሬ፡ ሥአቱም አሁን ነው!!
ማተቤ፡ መለሰ፡ ተሰማ / ታህሣሥ ወር 2001 ዓ.ም
አሁንስ በጣም! እጅግ በጣም! በዛ!! ((ሲሞላ ይፈሣል፡ ሲከር ይበጠሣል)) ነው የሚባለው፡ ከሚገባው በላይ፡ ተገፋንም፡ እኛ ኢትዮጵያዊያን፡ ሐገርን የሚያክል፡ መተኪያ የማይገኝለት፡ ታላቅ ንብረት፡ ተዘርፈን፡ ባለሐገርነትን፡ የሚያክል፡ መተኪያ የማይገኝለት፡ ታላቅ ክብር፡ ተገፍፈን፡ ሰባዊ መብትና፡ ተፈጥሮዊ፡ ነፃ ነታችንን፡ ተነጥቀን፡ ተንቀንና ተዋርደን፡ እርቃናችንን በመቆም፡ የዓለም ሕዝብ፡ እጣት መቀሰሬያ፡ መሣቂያና መሣለቂያ፡ በመሆን፡ እንደቦቆሎ፡ እሸት ተሸፍነን፡ በማረርና፡ እንደጉንዳን፡ ሰራዊት፡ እጅ ለእጅ፡ ተያይዞ ባለማቋረጥ፡ የሚግተለተለውን፡ ሥቃይና መከራ፡ ሥናሥተናግድ፡ ወራትን፡ አመታት እየተኳቸው፡ የማያቋርጠው፡ የጊዜ ጎርፍ፡ እያጋፈለ አልፎ፡ ዘመን በነበር፡ ጢሻ ውሥጥ፡ ሲሰርግ፡ በአርምሞ፡ መመልከቱን፡ ከተያያዝነው፡ እንሆ፡ 18 አመታትን፡ አሥቆጥረናል።
እኛ እንተባበር-ይህን ሕግን የሚንቅ ሥርዓት ማስወገድ እንችላለን !(ግርማ ካሳ)
ግርማ ካሳ (ቺካጎ) – muziky68@yahoo.com / ታህሳስ 24 ቀን 2001
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ዋሽንግተን ዲሲ የአንድነት ፓርቲ ልኡካን ቡድን አባል ሆነዉ ለኢትዮጵያዉያን ንግግራቸዉን ሲጀምሩ በጸሎት ነበር የጀመሩት። «አምላክችን ሆይ ኢትዮጵያ ተችግራለች። እኛም ተችግረናል።
«ሳታመኻኝ ብላኝ» – አዉደ ኢትዮጵያ እትም 21
አውደ ኢትዮጵያ / ታህሳስ 24 2001
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከተመሰረተ ከመንፈቅ ብዙም አልዘለለም፡፡ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ግን በርካታ ከቁም ነገር በላይ የሆኑ ተግባራትን አከናውኗል፡፡ ለቁጥር የሚታክቱ ተግዳሮቶችንም አስተናግዷል፡፡ የሰሞኑ ይባስ እንጂ፡፡
የታጋይ መታሰር እልፍ ታጋዮችን ይፈጥራል – ከአወደ ኢትዮጵያ እትም 21
አውደ ኢትዮጵያ / ታህሳስ 24 2001
በኢትዮጵያ ሀገራችን የነፃነትና የፍትህ ተጋድሎ ታሪክ ውስጥ ብዙ፤ እጅግ ብዙ ታጋዮች ተፈጥረዋል። ብዙዎች ለቆሙለት ዓላማ ሲሉ፤ ተሰደዋል፤ ታስረዋል፤ ተገድለዋል። የአባቶቻችን የተጋድሎ ታሪክ ይሄ ነው። ይሁንና የህዝብ ትግል አልታሰረም፤ አልተሰደደም፤ አልሞተም።
ወ/ት ብርቱካን ምግብ አልበሉም !
አውደ ኢትዮጵያ / ታህሳስ 24 2001
ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ የረሃብ አድማ ላይ መሆናቸዉን ምንጮቻችን ከአዲስ አበባ ገለጹ። የቀድሞ የወያኔ/ኢሕአዴግ የደህንነት አዛዥ አቶ ክንፈ ገብረመድህንን ገድለዋል ተብለዉ የተፈረደባቸዉ እሥረኛ ባሉበት እጅግ አስከፊ ቦታ ሲሆን ወ/ት ብርቱካን የታሰሩት፣ የታመኑ ምንጮቻችን እንደገለጹልን የእሥር ቤቱ ሃላፊ በቢሮዉ አስጠርቷቸዉ እንዳነጋገሯቸዉ ለማወቅ ችለናል። የንግግራቸዉ ይዘት እስከአሁን ምን እንደነበረ ለማወቅ ያልተቻለ ሲሆን ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ እስካሁን ከጠበቃቸዉም ሆነ ከቤተሰባቸዉ ጋር እንዲገናኙ አልተደረገም።

Recent Comments