ማህደር

ማህደር ለ February, 2009

መቼ ይሆን ?

February 15th, 2009

ስሜነህ ተሻለ / የካቲት 8 ቀን 2001 ዓ.ም.

በአሜሪካን ምድር አይሆንም ሲባል የነበረው ዕውን ሁኖ የብዙ ዘመናት ትግል ውጤት አስመዘገበ። Read more…

ዜና

ይቅርታ – ከስታሊን እስከ መለስ

February 13th, 2009

ሳምሶን / የካቲት 6 ቀን 2001 ዓ.ም.

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!

ዜና

ሕዝብ እየተራበ ነዉ ! ጆከኛዉ መለስ መቀለዱን ቀጥሏል !

February 13th, 2009

የካቲት 6 ቀን 2001 ዓ.ም

ዛሬ የካቲት 6 ቀን 2001 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴሌቭዝኝ ከአቶ መለስ ዜናዊ ጋር በኢኮኖሚ ጉዳይ ላይ የተደረገ ቃለ መጠይቅ አስተላለፏል። በቃለ መጠይቁ አቶ መለስ በአለም አቀፍ ደረጃ ያለዉ የኦኮኖሚ ችግር የከፋ እንደሆነ ገልጸዉ ኢትዮጵያ 11.8 በመቶ እድገት እንደምታሳይ ገለጸዋል። በአለም የታየዉ የኢኮኖሚ ቀዉስ በሌሎች አገሮች እንጂ በኢትዮጵያ ብዙም ችግር እንደማያመጣ በድፍረት የተናገሩት አቶ መለስ በአለም እየታየ ያለዉ ቀውስ ቢበዛ ቢበዛ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እድገት ከ11..8 በመቶ ወደ 11.2 በመቶ ቢያወርደዉ ነዉ ሲሉም ተናግረዋል። Read more…

ዜና

ለመሆኑ ኢትዮጵያ አሁን አገር ናት ወይ?

February 11th, 2009

በላይነህ አባተ / የካቲት ሁለት ሺህ አንድ ዓ.ም.

ለማንበበ እዚህ ይጫኑ!

ዜና

መቶ ሺዎቻችንን አሰልፉን!! ይቻላል!!

February 11th, 2009

ከዘመድ አገኘሁ / February 10, 2009

ከሀገር ውጭ በአለም ዙሪያ የተበተናችሁ ምሁራንና ሊቃውንቶች፤ መቶ ሺዎች በአንድነት የፍትህ የዲሞክራሲና የጋራ ጥቅምን የሚያስተጋባ ድምጽ እንድናሰማ፤ ከአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ እንቅስቃሲ ለቀረበው ጥሪ፣ Read more…

ዜና

‘በዘር ካላዋጣ በሀይማኖት እንምጣ’ የወያኔዎች የደከረተ ካርታ

February 10th, 2009

ዳኛቸው ቢያድግልኝ biyadegelgne@hotmail.com / ይካቲት 3 ቀን 2001 ዓ.ም.

አቶ መለስ በወጣትነታቸው የካርታ ጨዋታ ይወዱ ነበር ይባላልና ‘ዲካርቴ’ የገባ የመጨረስ ተስፋው የተመናመነ መሆኑን ያውቁታል። ድርጅታቸው እንደዚያ አይነት ዕጣ ላይ መውደቁን ቁማር የማይጫወቱ እንኳ ልብ ብለውታል። ምክንያቱም የወያኔ መሪዎች የፖለቲካ መሰሪነታቸው እንደ ድሮው ቁምጣቸው ሰላሳ ቦታ እየተቀደደ እያስቸገራቸው ነውና ሁሉም ነገራቸው ነው ቀዳዳ የሆነው። መጀመርያውኑ በቡቱቶ ፖለቲካ ነው የተንደረደሩትና ቀዳዳና ቀደዳ መታወቂያቸው ሆኖአል። አንደበታቸው ውሸት፣ እጃቸው ደም፣ የሚረግጡት መሬት ደግሞ የሚናድ ነው። Read more…

ዜና

«የጋዜጠኛዉ ማስታወሻ» የጻፈዉ ጋዜጠኛ እስከአሁን የት ነበር ?

February 9th, 2009

ተስፋዬ ገብረአብ ይባላል። የተወለደዉ ደብረዘይት (ቢሾፍቱ) ሲሆን አባትና እናቱ መንደፈራ ተጋብተዉ ይኖሩ የነበሩ የኤርትራ ተወላጆች ናቸዉ። ለሃያ ቀናት የደርግ ወታደር ሆኖ ደብረታቦር በወያኔ ተማረከ። ወዲያዉ በወያኔ ዉስጥ ትልቅ ቦታ ተሰቶት የወያኔ ቀንደኛ የፕሮፖጋንዳ ሃላፊ ሆነ። ወያኔ ስልጣን ሲጨብጥ በሃያ ምናምን አመቱ የኢትዮጵያ ፕሬስ መምሪያ ሃላፊነትን ጨበጠ። የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ፣ አዲስ ዘመን፣ ኢትዮጵያያን ሄራልድ የመሳሰሉት በርሱ ስር ወደቁ ማለት ነዉ። Read more…

ዜና

«አንድነት» መድረክን ተቀላቀለ – ከአዉደ ኢትዮጵያ

February 9th, 2009

መጋቢት 2 ቀን 2001
አዉደ ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ኅያሎች ሕብረት (ኢዴኃኅ)፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኦፌዴን)፣የኦሮሞ ብሄራዊ ኮንግረስ (ኦብኮ) የሶማሌ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ቅንጅት (ሶዴኃቅ) እና አረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ሉዓላዊነት በደርጅት ደረጃ፣ አቶ ስዬ አብርሃ የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስቴርና ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የቀድሞ የቀደሞ ኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት በግለሰብ ደረጃ፣ ማክሰኞ ሰኔ 17 2007 ቀን የመሰረቱትን «መድረክ ለዲሞክራሲያዊ ምክክር በኢትዮጵያ ተብሎ የሚታወቀዉን አካል አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) አባል ሆኖ ለመንቀሳቀስ ቅድሜ ጥር 30 ቀን 2001 ዓ.ም የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የላዕላይ ምክር ቤት ባደረገዉ ስብሰባ መወሰኑን ለማወቅ ችለናል። Read more…

ዜና

«ግፉ አንገቴ ድረስ ደረሰብኝ !» ብርቱካን ሚደቅሳ – 42 ቀናት በጨለማ ቤት

February 9th, 2009

ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ እንደገና ጠበቃቸዉን እንዳያዩ መከልከላቸዉን አዲስ አበባ ያሉ ምንጮቻችን ገለጹ። ሕገ መንግስቱ በእስራት ያሉ ዜጎች ጠበቃዎቻቸዉን፣ የመንፈሳዊ አባቶችን፣ ሐኪሞችን ፣ ዘመዶቻቸዉን ..የማየት ሙሉ መብትን ይደነግጋል።

እንደዚያም ሆኖ የሕወሃት መንግስት በግፍና በጭካኔ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ለአርባ ሁለት ቀናት ለብቻቸዉ በጨለማ ቤት እንዲኖሩ በማድረግ አሁንም ከፍተኛ “ቶርቸርና” ጭካኔ እየፈጸመባቸዉ ሲሆን ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ «ግፉ አንገቴ ድረስ ደረሰብኝ» ሲሉም ለእናታቸዉ መግለጻቸዉን ለማወቅ ችለናል። Read more…

ዜና

ግልጽ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት

February 8th, 2009

ከኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ / ጥር 30 ቀን 2001 ዓ.ም.

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!

ዜና