ማህደር

ማህደር ለ February, 2009

ኢትዮጵያ የማን አገር ናት?

February 8th, 2009

በአበበ ገላው / ጥር 30 ቀን 2001 ዓ.ም.

በርካታ ኢትዮጵያዊያን ስለአገራቸው ሲናገሩና ሲጽፉ በኩራት “እምዬ ኢትዮጵያ፣ ታሪካዊቷ አገር፣የሰው ዘር መገኛ፣ የነጻነት ቀንዲል፣ የጥቁር ዘር መኩሪያ…” እያሉ ያቆላምጧታል። አባባሎቹ በሙሉ እውነታ ቢኖራቸውም፣ የኢትዮጵያ የባለቤትነት ጉዳይ ግን “እናት አገር” ብሎ በስሟ ለሚምለው ሆኖም ግን በአገሩ ባይተዋር ለሆነው አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ በተግባር ያልተፈተሸ መሆኑ ብዙ ጊዜ አይወሳም።

Read more…

ዜና

ተስፋ የሚሰጡ ምልክቶች – ግርማ ካሳ

February 7th, 2009

(muziky68@yahoo.com)
ጥር 30 2001

መግቢያ

በወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ላይ የተወሰደዉ እርምጃ ያላስቆጣዉና ያላበሳጨዉ ኢትዮጵያዊ የለም ቢባል አይገርመኝም። በተለይም አገዛዙ ዉስጥ ደህና ልብ ያላቸዉ ሰዎች ይኖራሉ ብለን እንገምት ለነበርነዉ አንዳንድ ሰዎች እጅግ የሚያሳዝን ነበር። Read more…

ዜና

ይድረስ ላንቺ

February 5th, 2009

ከደጉ ሳምራዊ / ጥር 28 ቀን 2001 ዓ.ም.

ከዚያች ዕለት ጀምሮ ሁልጊዜ የማስበው፣
እንግልትሽ አይደለም ባይምሮዬ ሚላወሰው፣ Read more…

Poem

እንቆቅልሽ

February 5th, 2009

ወንድወሰን ሰብስቤ / ጥር 28 ቀን 2001 ዓ.ም.

ሀገር እሳት ወልዳ
ሆነና በሜዳ Read more…

Poem

ከፍተኛ የፖለቲካ ንቅናቄ በመቀሌ- በሺሆች የሚቆጠሩ አረና በጠራዉ ስብሰባ ተገኙ

February 5th, 2009

አቡጊዳ / ጥር 28 ቀን 2001 ዓ.ም.

እሑድ ጥር 24 ቀን 2001 ዓ.ም በአይነቱና በስፋቱ የመጀመሪያ የሆነ በሕወሃት ያልተጠራ ታላቅ ሕዝባዊ ስብሰባ በመቀሌ ከተማ በሚገኘዉ የማዘጋጃ ቤት ጽ/ቤት መደረጉን የአሜሪካን ድምጽ ረዲዮ ዘገበ። ስብሰባዉን የጠራዉ አረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ለሉዓላዊነት የተሰኘዉ ቀድሞ የሕወሃት ከፍተኛ አመራር የነበሩ ሰዎችን ያቀፈ ድርጅት ሲሆን ፣ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ በተለይም ወጣቶች የተገኙበት ስብሰበ እንደነበረ የአሜሪካን ድምጽ ገልጿል።

Read more…

ዜና

የደቡብ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በሙስና ተገመገሙ፤ ሊታሰሩም ይችላሉ

February 4th, 2009

አቡጊዳ / ጥር 27 ቀን 2001 ዓ.ም

የደቡብ ክልል የፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሰለሞን በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡ የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ሽፈራው ሽጉጤም ከስልጣናቸው ሊነሱና እስከ እስር የሚደርስ እርምጃ ሊወሰድባቸው እንደሚችል ምንጮቻችን ከሀዋሳ ገልፀውልናል፡፡ Read more…

ዜና

በቀለ ጂራት ተፈቱ – ብርቱካን ጠ/ሚኒስትር መሆን የምትችል ናት አሉ ዶ/ር ቡላቻ

February 4th, 2009

አቡጊዳ / ጥር 27 ቀን 2001 ዓ.ም

የኦሮሞ ፌደራሊስት ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ዋና ጸሃፊ አቶ በቀለ ጂራታ ዛሬ በዋስ ተለቀቁ። «ከኦሮሞ ነጻ አዉጪ ግንባር ጋር ግንኙነት አለህ» በሚል ክስ ገዢዉ ፓርቲ ሕግ ወጥ በሆነ መልኩ እኝህን የሰላማዊ ትግል አካል የሆኑትን ኢትዮጵያዊ ለወራት ማሰሩ ከኢትዮጵያዉያን ዘንድ ከፍተኛ ተቃዉሞ ማስነስቱ ይታወሳል።

Read more…

ዜና

ሕግ ምንድነው? በሃገራችን የአፍጻጸሙ ጉዳይ እንዴት ይታያል?

February 4th, 2009

ንዋይ ኃይሉ / ጥር 25 ቀን 2001 ዓ.ም

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ።

ዜና

የሰሜን አሜሪካ የአንድነት ድጋፍ ማህበር ሊቀመንበር አቶ አክሎግ ልመንህ በዋሽንግተን ዲሲ ያደረጉት ንግግር

February 4th, 2009

አንድነት ሰሜን አሜሪካ / ጥር 27 ቀን 2001 ዓ.ም.

ለወቅታዊ ጥያቄ ተግባራዊ ምላሽ

የተከበራችሁ ተጋባዥ እንግዶች
የተከበራቹህ የዚህ ውይይት መድረክ አዘጋጆች
የተከበራችሁ በዚህ አዳራሽ የተገኛቹህ የዲሲ እና አከባቢው ነዋሪ ኢትዮጵያውያን

Read more…

ዜና

የአንድነት ድጋፍ ድርጅት በስዊዘርላንድ መሥራች ጉባዔውን አካሄደ

February 3rd, 2009

አንድነት ስዊዘርላንድ / ጥር 26 ቀን 2001 ዓ.ም.

በስዊዘርላንድ የአንድነት የድጋፍ ድርጅት በዛሬው ዕለት በስዊዘርላንድ ዋና ከተማ በበርን የአንድነት ድጋፍ ድርጅት የምሰረታ ስብሰባውን በተሳካ ሁኔታ አካሄደ::

Read more…

ዜና