ማህደር

ማህደር ለ May, 2009

አቡጊዳ- ባላገሩ ከተሜዉ በአንድነትና መኢአድ መቀራረብ ተደሰተ !

May 30th, 2009

አቡጊዳ – ግንቦት 22 2001 ቀን 2001

ግንቦት 20 ቀን የቃሌ ምሽት በተሰኘዉ የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን በግፍ መታሰር የሚያስታወስ ምሽት ላይ፣ በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ጽ/ቤት፣ የተከበሩ ኢንጂነር ኃያሉ ሻወልና በርካታ የመኢአድ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ተገኘተዉ ለክብርት ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ያላቸዉን ሶሊዳሪቲ እንዳሳዩ አወደ ኢትዮጵያ የተሰኘዉ የሰሜን አሜሪካ የአንድነት ድጋፍ ድርጅቶች ማህበር መዘገቡ ይታወሳል። Read more…

ዜና

መሬት የመቸብቸቡ ጉዳይ! – ኩችዬ (kuchiye.blogspot.com)

May 29th, 2009

“ችስታ” የመታቸው አገሮች ሰፋፊ መሬታቸውን ለውጭ መንግሥታት በገፍ የመቸብቸባቸው ፈሊጥ በዓለም መድረኮች አነጋጋሪ ሆኗል። በኛው አካባቢም ብዙ ንትርክና ቁጣ እንደጫረ ተረዳሁና ጉዳዩን መመርመር ጀመርኩ። Read more…

ዜና

ኢንጂነር ኃይሉ ሻወል በአንድነት ጽ/ቤት፣ በቃሌ ምሽት ላይ ንግግር አደረጉ !

May 29th, 2009

ልዩ ዘገባ – አወደ ኢትዮጵያ
ግንቦት 21 ቀን 2001 ዓ.ም

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ፣ የፓርቲው ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ በግፍ ለአምስት ወራት ለእስር የተዳረጉበትን ዕለት በማስመልከት የሚያዘጋጀው «ቃሌ የሻማ ምሽት» በትላንትናዉ ዕለት ሐሙስ ግንቦት 20 ቀን 2001 ዓ.ም በጽ/ቤቱ ግቢ ውስጥ አካሂዷል። ጽ/ቤቱ በታዳሚዎች እጭቅ ከማለቱ የተነሳ ቦታ በጣም ጠብቦ እንደነበረ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።

ይህ «ቃሌ የሻማ ምሽት» በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ ያሉትን ኢትዮጵያዊያን በአንድነት እያሰባሰበ ያለ የሰላማዊ ፖለቲካ እንቅስቃሴና በወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ላይ እየደረሰ ያለዉን ግፍ በስፋት ከሚያጋልጡ ዝግጅቶች አንዱ ነዉ። በየወሩ አዳዲስ ክስተቶችን ይዞ የሚመጣው ይህ የ«ቃሌ ምሽት» በግንቦት ሃያ ቀን አንድ አዲስ ተሳታፊ ይዞ ነው የመጣው። Read more…

ዜና

የአስመራ ትዝታዬ ግርማ ካሳ muziky68@yahoo.com

May 28th, 2009

zenawi_issayas_victimsበጠቅላይ ሚኒስትር መለስዜናዊ ወይንም በፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በግፍ የታሰሩ ሰላማዊ ወገኖቻችን መካከል በጥቂቱ ዳኛ ብርቱካን ሚደቅሳ ፣ ፓስተር ሃይሌ ነዕዝጊ ፣ ፓስተር ዶር ክፍሉ ገብረመስቀል ፣ ፓስተር ተስፋጽዪንሃጎስ ፣ አርስቲስት ቴዎድርሶ ካሳሁን (ቴዲአፍሮ) ከግራ ወደቀኝ ስዘረዝራቸዉ። Read more…

ዜና

የደብረማርቆስ እርሻ ኮሌጅ ተማሪዎች በግፍ ተባረሩ

May 26th, 2009

ግንቦት 18 ቀን 2001 ዓ.ም

ደብረ ማርቆስ በሚገኘዉ የእርሻ ኮሌጅ ተማሪዎች በፌደራል ፖሊስ መከበባቸዉን ዘግብነ ነበር።፡ከደብረ ማርቆስ የደረሰን ዜና እንደሚጠቁመዉ ተማሪዎች በጠመንጃ ኃይል እየተደበደቡ ከኮሌጁ ጊቢ በግፍ ተባረዋል።

ደብረ ማርቆስ የሚገኘው የእርሻ ኮሌጅ በየዓመቱ ተማሪዎቹን ለጥናትና ምርምር ተግባር ወደ ገጠር የሚልክ ሲሆን ተማሪዎቹ ወደ ገጠር በሚሰማሩበት ጊዜ ከመኖሪያ ቅጥር ግቢያቸው ርቀው ስለሚሄዱና ተጨማሪ ወጪም የሚያስከትልባቸው በመሆኑ ትምሕርት ቤቱ ለዚህ ማካካሻ የሚሆን የውሎ አበል የመክፈል አሰራርባ ልማድና ነበረዉ። Read more…

ዜና

በደብረ ማርቆስ ተማሪዎች ተከበቡ – የተባረሩ ኤርትራዉያንን ጉዳይ ዉዝግብ አስነሳ !

May 26th, 2009

በጎጃም ክፍለ ሃገር በደብረ ማርቆስ ከተማ በሚገኘዉ የደብረ ማርቆስ የግብርና ኮሌጅ የሚገኙ ተማሪዎች በፌደራል ፖሊስ እንደተከበቡ ምንጮቻችን ከአዲስ አበባ ገለጹ። ዝርዝር ዘገባ እንደሰማን ይዘን እንቀርባለን።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዉጭ አገር በሚገኘዉ የአፍቃሪ ወያኔ የሲቪሊቲ ፓልቶክ ክፍል ተሳታፊ የሆኑ በርካታ የወያኔ ደጋፊዎች፣ ከዚህ በፊት ተባረዉ የነበሩ ኤርትርዉያን እንዲመለሱ የሚፈቅድ ደንብ መዉጣቱን አጥብቀዉ ተቃወሙ ። «ኤርትራዉያን ከኢትዮጵያ ጋር መዋሃድ ከፈለጉ እንቀበላቸዋለን። አለበለዚያ ግን እንደ ሌላዉ የዉጭ አገር ዜጋ መታየት ነዉ ያለባቸዉ» ሲሉ የአቶ መለስ አገዛዝ ከኤርትራ ጋር ያለዉን ችግር ሳይፈታ እንዲህ አይነት እርምጃ መወሰዱን ለምን አሁን እንደፈለገ አይገባንም ብለዋል። Read more…

ዜና

ቀደምት ሊቃውንት ለኢትዮጵያዊነት መንፈስና እምነት የጀርባ አጥንት፦ ከቀሲስ አስተርአየ

May 26th, 2009

ቀደምት፡ምሳሌዎች – ብርዞ ፍራንክፉርት

May 26th, 2009

ባላቸው፡ተሰጥዎ፡መኖር፡እየቻሉ
ገንዘብ፡የሚያዘውን፡ቅንጦት፡ነገር፡ሁሉ Read more…

Poem

የተቃውሞ ሰልፎች እየቀጠሉ፣ የብርቱካን ትፈታ ድምጽ እየበረከተ ነዉ ! -የካናዳ ሰልፍ

May 26th, 2009

በቶሮንቶና በኦታዋ ከበርቱካን መታሰር በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰልፍ ይደረጋል-

ግንቦት 18 ቀን 1፡00 AM

ግንቦት ሰባት 2001 ዓ.ም፣ በተለያዩ የአለማችን ከተሞች ኢትዮጵያዉያን በወያኔ-ኢሕአዴግ ላይ ያላቸዉን ተቃዉሞ ሲያሰሙ እንደነበረ በሰፊዉ ተዘግቧል። የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ፣ አንጋፋዉ የኢትዮጵያዊነት አቀንቃኝ ቴዲ አፍሮ እንዲሁም ሌሎች በርካታ የፖለቲካ እሥረኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ የሚጠይቁ መፍክሮችን እያሰሙ ለትግሉ ያላቸዉን ቁርጠኝነት አሳይተዋል። Read more…

ዜና

የታቀደዉ የአንድነት መስቀል አደባባይ ሕዝባዊ ስብሰባን በተመለከተ – ልዩ ዘገባ አወደ ኢትዮጵያ

May 24th, 2009

ግንቦት 15 ቀን 2001 ዓ.ም

አገራዊ አንድነትና ሉዓላዊነት ተጠብቆ፣ ዜጎቹዋ በሰላምና በነጻነት፣ የሰብዓዊና የዲሞክራሲያዊ መብታቸዉ ተክብሮ፣ በእኩልነት የሚኖሩባትን አንዲት ኢትዮጵያ ለመመስረት የሚደረገዉ ትግል፣ ወሳኝ ምእራፍ ላይ መድረሱን የሚናገሩ ጥቂቶች አይደሉም። Read more…

ዜና