ማህደር
“ጥሩ ኢትዮጵያዊነት” የጊዜውቁልፍ ጥያቄ ተጻፈ በፍቅር ግንቦት 2001 ዓ∙ም∙ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
“ጥሩ ኢትዮጵያዊነት” የጊዜው ቁልፍ ጥያቄ ethio.fikir@yahoo.com2
በዚህ ጽሁፍ ጥሩ በሚለው ገላጭ ቃል መጠቀም የተፈለገበት ዋነኛ ምክንያት የምናከብረውንና የምንወደውን በብዙ መስዋትነት የቆየንን የማንነታችንን መገለጫ በቀና መንፈስ ለመግለጽ ያመች ዘንድ ነው። ይህችን አጭርጽሁፍ ለመጻፍ በዋና ምንጭነት እንዲሁም መነሻ ምክንያትነት ያገለገለኝ በ1986 ዓምበፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማሪያም የተጻፈው ኢትዮጵያ ከየት ወደየት የሚለው መጽሃፍ ነው። Read more…
አይ አቤ ቶክቻው! – (ዜማ አብ፡ ከስድስት ኪሎ)
አቶ መለስ – ዉሸቱ ይብቃና ብርቱካንን ይፈቱ ! – አዉደ እትም 28
የሕወሃት/ኢሕአዴጉ መሪ አቶ መለስ ዜናዊ ሃርድቶክ ለተሰኘዉ ታዋቂ የቢቢሲ ፕርሮግራም ላይ ቃለ-መጠይቅ መስጠታቸዉ በሰፊዉ ተዘግቧል። በርካታ ጉዳዮች በቃለ መጠይቁ ላይ የተነሱ ሲሆን፣ በወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ መታሰር ዙሪያ አቶ መለስ ለተጠየቁት ጥያቄ የሰጡት ምላሽ ግን እርስ በርሱ የሚቃረን፣ እራሳቸዉንና ድርጅታቸዉ ያስገመተና በደጋፊዎቹ አፍሪካን ወክሎ በጂ-20 ስብሰባ ላይ ቀረበ ከተባለ መሪ የማይጠበቅ ነበር።
በአንጻሩም ደግሞ በዚህ ቃለ መጠይቅ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ፣ ምን ያህል የአለም አቀፉን ሜዲያ የሳቡ ታላቅ መሪ መሆናቸዉን የታየበት ቃለ መጠይቅ ነበር። Read more…
አገር ወዳድነቷንና ሰላማዊነቷን በተግባር አሳይታለች። እኛስ ? – አዉደ እትም 28
ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ በቃሊቲ እሥር ቤት በጨለማ ክፍል ዉስጥ በግፍና በጭካኔ እንድትቀመጥ ከተደረገ 140 ቀናት አልፏታል። ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን ገዢዉ ፓርቲ ያስረበት፣ «ይቅርታ መጠየቋን ካደች» የሚለዉ ምክንያት ፍጹም ዉሸት የተሞላበት፣ ሕገ ወጥና አምባገነናዊ እንደሆነ በሰፊዉ ተዘግቧል።
ገዢዉ ፓርቲ የ«የይቅርታዉ» ነገር አሳስቦታ ወይንም ለሕግ የበላይነት ተቆርቁሮ ሳይሆን፣ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ የምትመራዉ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሕጋዊነትን ባገኘ በአጭር ጊዜ ዉስጥ እጅግ ትልቅ ተስፍ ሰጪ ህዝባዊ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ በማቻሉና፣ በሚመጣዉ የ2002 ምርጫ ከሥልጣናችን ሊያስወግደን ይችላል በሚል ስጋት እንደሆነ የማያጠራጥር ነዉ። Read more…
አጼ ዮሐንስና አጼ ካሌብ ቢኖሩ አንዴት ያዝኑ! – ሕብረት ሰላሙ
ከጥንቶቹ ጀግኖቻችን፤
እንደሚታውቀው፤ አጼ ዮሓንስን እጅግ በጣም ከሚያስደንቃቸውና ከሚያስከብራቸው ታሪካቸው ዋነኛው፤ ለውድ ሐገራቸው፤ ለኢትዮጵያ፤ ሉዓላዊነትና ዳር ድንበር መከበር በቆራጥነት ይከላከሉ የነበረውና ሕይወታቸውንም የሰዉለት መሆኑ ነው። የጀግናው የአጼ ዮሐንስ ራስ ተቆርጦ ሱዳን ከተወሰደ ልክ 120 ዓመት ሆኖታል። እስካሁን አልተመለሰም! Read more…

Recent Comments