ማህደር
አማራ የቀነሰው ህዝቡ ወይስ ቁጥሩ? – እስከ ነፃነት
በቅርቡ የስታትስቲክስ ጽ/ቤት በአማራ ክልል የተደረገው ቆጠራ ትክክል ነበር መድገም አያስፈልግም ብሎ በተወካዮች ምክር ቤት ማጽደቁን ሰምተናል: በዚህም ቆጠራ የአማራ ክልል ህዝብ ከተተነበየው ወደ 2.4 ሚሊየን አካባቢ ዝቅ ብሎ ታይቷል: የስታትስቲክስ ጽ/ቤት ኃላፊዋ ሳሚያ ዘካሪያ የህዝቡ ቁጥር ዝቅ ያለበትን ምክንያት እንደሚከተለው መዘርዘራቸውም ይታወሳል: Read more…
መልዕክተ ኦባንግ – ስለሺ ዘእንግልጣር
“የምንታገለው ለመንደር ወይስ ለሐገር? መታገል ያለብን ለሐገር አነድነት ነው፣ ሐገር ከሌለች መንደር አይኖርምና።”
አቶ ኦባንግ ሜቶ ‘የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የትብብር ንቅናቄ’ መስራች ከተናገሩት ተተርጉሞ የተወሰደ Read more…
የአንድነት ፓርቲ እንቅስቃሴዎችን በሰፊዉ እያደረገ እንደሆነ ተዘገበ
አቡጊዳ – ሰኔ 20 2001
የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ፣ ሕዝቡ በወ/ት ብርቱካን ሚድቅሳ ላይ ከስድስት ወራት በላይ እያየደረገ ያለዉን የጭካኔ ግፍ አስቦ በየአብያተክርስቲያናቱ፣ መስኪዶች እንዲሁም በቤት፣ እሁድ ሰኔ 21 ቀን 2001 ሻማ በማብራት ጸሎት እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።
ጥሪዉ አገር ዉስጥ በሚታተሙ ጋዜጦችና በየክልሉ ባሉ የአንድነት መረብ አማካኝነት በሰፊዉ ለሕዝብ የተነገረ ሲሆን፣ በይዘቱ የፓርቲዉ አባላትን ከማሳተፍ ያለፈ ሰፊዉን ሕዝብ የጨመረ እንቅስቃሴ በመሆኑ በብዙዎች ዘንድ እንደ ትልቅ እርምጃ ተደርጎ እየተወሰደ ነዉ። ሕዝቡ በራሱ እንዲተማመን፣ ባለዉ አቅሙ ሁሉ እንዲንቀሳቀስ ካልተደረገ አንዳች ዉጤት ማምጣት እንደማይቻል የነገሩን አንድ የፖለቲካ ተንታኝ የአንድነት ፓርቲ ተከታታይ ሕዝብን የሚያሳትፉ እርምጃዎች በቀጣይነት መወሰድ እንዳለበት ገለጸዉልናል። Read more…
በቃ፡ በቃን እንበል – ስለሺ ዘእንግልጣር
እስከመቼ በግዞት፣ በግፍ ወከባ እስራት፣
በመባረር ስቃይ ማየት፣ ተሰዶ ከሐገር መውጣት። Read more…
ሁሉ ነገር በእጃችን ነዉ – በግርማ ካሣ
ሰኔ 17 ቀን 2001
ኢትዮጵያን በጽጌረዳ አበባ እመስላታለሁ። ጽጌሬዳ አበባ በጣም ተወዳጅ የሆነች አበባ ናት። ብዙ ጊዜ በማስቀመጫ ዉስጥ ተደርጋ የሚመጡ እንግዶች እንዲያይዋት በሚታይ ቦታ ትቀመጣለች። የክብር የፍቅርና የዉበት ምልክት ናት። ኢትዮጵያ አገራችንም በነጻነቷና በአንድነቷ ታፍራና ተክብራ የኖረች፣ ከተለያዩ ብሄረሰቦች የተወጣጡ ልጆቿ ዉበቷ የሆኑላት፣ ለኢትዮጵያዉያን ብቻ ሳይሆን ለጥቁር ህዝብ ሁሉ ኩራት የሆነች አገር ናት። Read more…
የሌባ ተረት – ብርዞ ፍራንክፈርት
የ አቦይ ስብሃት ግብና አባባል
የሚያቅለሸልሽ ጥሬ ግንፍልፍል Read more…
በቃኝ – ብርዞ (ፍራንክፈርት)
በቃኝ አኔ በቃኝ አዎ በቃኝ በቃኝ
በደል ግፍ ስሰማ አኔን መሰል ስቃኝ
አልንበረከክም አጄንም አልሰቅልም
ህሊና አስገድሎ ሆድ ማዳን አይቀልም Read more…
እሽሩሩ – አስፋወሰን ዓለምሰገድ
እሽሩሩ
እሽሩሩ
እሽርሩ፥ማሙዬ
ልንከባከብህ፥እሽሩሩ ብዬ
አባት ሆኛለሁ፥በተራዬ። Read more…
የደደቢቱ ፕሮፌሰር ተምኔታዊ ካፒታሊዝም – ደቻሳ ነኝ
ማነው እሱ ወያኔዎች አፋቸውን ሲከፍቱ ባዶ አንጎላቸው ይታያል ያለው? አዎ ታየ እንጂ የታየው ግን ደደብነት ብቻ ሳይሆን እርቃኑን የቆመ ከርካሳ እብሪት ነው። ማሌሊት ማጭድ መዶሻዋን አስቀምጣ ሱቅ በደረቴ ሆነችና ስለካፒታሊዝም ትሰብከን ገባች። የወያኔ ‘ጎድ ፋዘር’ በመባል የሚታወቁት አቦይ ስብሀት ኮሙኒዝምም ይሁን ካፒታሊዝም ያለኛ አያምርበትም ብለው ነገር ሊተነትኑ ምድረ አሜሪካ ተገኙ። እኔ ግን ራሴን በርሳቸው ቦታ አድርጌ የነገዪቱን ኢትዮጵያ ተመለከትኳት:: Read more…

Recent Comments