ማህደር

ማህደር ለ September, 2009

ለ2002 ምርጫ የካርተር ማዕከል ሲጋበዝ ለአዉሮፓ ሕብረት ጥሪ አልቀረበም!

September 30th, 2009

አቡጊዳ – መስክረም 20 ቀን 2002

የፊታችን ግንቦት 2002 ዓ.ም ይደረጋል ተብሎ የታሰበዉን ብሄራዊ ምርጫ ለመታዘብ የካርተር ማዕከል መጋበዙን አዲስ አበባ ያሉ ምንጮቻችን ገለጹ። የካርተር ማዕከል የዲሞክራሲ ጉዳይ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ዴቪድ ኤስ ኦቲ፣ ምርጫዉን በተመለከተ ከዉጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባለሥልጣናት ጋር ተነጋግረዋል። Read more…

ዜና

ወያኔ/ኢሕአዴግ መድረክ ባቀረባቸዉ አጀንዳዎች ላይ እነጋገራለሁ አለ !

September 29th, 2009

አቡጊዳ – መስክረም 19 ቀን 2002

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ጨምሮ ስምንት ድርጅቶችን ያቀፈዉ መድረክ ላቀረባቸዉ ጥያቄዎች ኢሕአዴግ ዛሬ መስክረም 19 ቀን ምላሽ እንደሰጠ ከአዲስ አበባ የደረሰን ዜና ያመለክትል።

መድረኩ በምርጫ ስነ-ምግባር ላይ ለመወያየት ፍቃደኛ እንደሆነ በመግለጽ፣ ምርጫዉ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ይረዱ ዘንድ በሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችም ላይ ዉይይት እንዲደረግ፣ ለኢሕአዴግ በጻፈዉ ደብዳቤ ላይ ጠይቆ እንደነበረ ይታወሳል። ሆኖም ግን በወያኔ ኢሕአዴግ በኩል ተቀባይነት ባለማግኘቱ ድርድሩ መቃረጡ ይታወቃል

ኢሕአዴግ ዛሬ ለመድረክ በጻፈዉ ደብዳቤ በምርጫ ስነ-ምግባር ላይ ከመኢአድ፣ ከኢዴፓና ከአየለ ጫሚሶ ቡድን ጋር የተሰማማባቸዉን ሰነዶች እንደገና ከመድረኩ ጋር መልሶ ለማየት ፈቃደኛ እንደሆነ ገልጾ፣ እንዲሁም፡መድረኩ ከምርጫ ስነ-ምግባር በተጨማሪ ዉይይት ይደረግባቸዉ ዘንድ ባቀረባቸዉ አጀንዳዎች ላይ በጋራም ሆነ በተናጥል ለመነጋገር ፈቃደኛነቱን መግለጹን ለመረዳት ችለናል።

መድረኩ ከሐሙስ መስከረም 21 ቀን 2002 በፊት ምላሽ እንዲሰጥ፣ ኢሕአዴግ በደብዳቤዉ የጠየቀ ሲሆን የመድረክ አባል ድርጅቶች አመራር አባላትም በጉዳዩ ላይ ነገ ረዕቡ መስክረም 20 ቀን መክረዉ ዉሳኔ እንደሚያሳልፉ ለማረጋገጥ ችለናል።

በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸዉ አንድ የፖለቲካ ተንታኝ ኢሕአዴግ በምርጫ ስነ-ምግባር ላይ ብቻ ሳይሆን ለምርጫ በሚረዱ ቅድመ ሁኔታዎችም ላይ ለመደራደር ፈቃደኛ መሆኑ አዎንታዊ እርምጃ እንደሆነ ገልጸዉ፣ «ገዢዉ ፓርቲ ድርድሩ አመርቂ ዉጤቶችን እንዲያመጣ ከፈለገ፣ ድርድር የማያስፈልጋቸዉ፣ በሕገ መንግስቱ የተቀመጡ ግልጽ መብቶችን አሁኑኑ ማክበር መጀምር አለበት። » ብለዋል።

እንደምሳሌም ሲያቀርቡ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን በመፍታትና በየክልሉ ያሉ ካድሬዎቹ እየፈጸሙት ካለዉ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትንና ደጋፊዎችን የማወክና የማንገላታት እኩይ ተግባራት እንዲሰበሰቡ በማድረግ፣ ኢሕአዴግ የሚደረገዉን የድርድር መንፈስ የቀና እንዲሆን ማድረግ እንደሚችል በመጠቆም እኝሁ የፖለቲካ ተንታኝ አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል።

ዜና

ሰላም ለሁሉም – እንግዳ

September 29th, 2009
Comments Off

የትናንትናው የወንድማችን ያቶ ኦባንግ የምክክር ሸንጎ በሁለንተናው ዓይነተኛ ነበርና ላይነት ያህል ልጠቃቅሰው ፈቀድኩ። አካሄዴ እንኳን ዓለም አቀፍ ልዩ ፖለቲከኛ ሰው ለማድመጥ ነበር። Read more…

ዜና

ዘፍናችሁ ቅበሩኝ – ዲግማዊ ዲዊት

September 29th, 2009

ቅድስተ-ቅዱሳን ድንግል ማርያም

September 29th, 2009

ሀተታ እና አስተያየት፡ ከቫንኩቨር ንግስ መልስ ወደ ፒስ (ፒትስ) በ(ር)ግ – አለቃ ተክሌ

September 27th, 2009
Comments Off

ፖለቲካና ሀይማኖት፡ የናንተን እንጃ፡ የኔን ግን እነሆ Read more…

ዜና

ለውድ የድህረ-ገጽ አዘጋጆች፤ ለሬድዮ ፕሮግራም ጋዜጠኞች፤ እንዲሁም የተለያዩ የዜና ማሰራጫ አገልግሎት የምትሰጡ ወገኖቻችን

September 27th, 2009

ይህን ደብዳቤ የጻፍነው እኛ በግብጽ ካይሮ ውስጥ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በካይሮ እሥር ቤት ውስጥ ከፍተኛ ስቃይ ውስጥ የሚገኙትን የወንድሞቻችንን የድረሱልን ጩሀት ለሚመለከተውና አቅም ላለው አካል ታሰሙ ዘንድ በእስር ላይ ከሚገኙት ወንድሞች የደረሰንን ፎቶ ከዚህ ደብዳቤ ጋር አባሪ አድርገን ልከናል። Read more…

ዜና

የኦህኮ ወጣቶች አስተባባሪ አቶ ኃይሉ በቀለ በወያኔ ታጣቂዎች ተገደሉ

September 27th, 2009

አቡጊዳ – መስከረም 17 ቀን 2002

በኢትዮጵያ አንድነት የማያወላዳ ጠንካራ አቋም ባላቸዉና በአፋን ኦሮሞ ተናጋሪዎች ብቻ ሳይሆን በተቀሩት ኢትዮጵያዉያን ዘንድም በሚወደዱትና በሚከበሩት በዶር መራራ ጉዳና የሚመራዉ፣ የመድረክ አባል ድርጅት የሆነዉ፣ የኦሮሞ ህዝብ ኮንግረስ ፓርቲ የወጣቶች አደራጆች መካከል ከነበሩት አንዱ፣ ወጣት ኃይሉ በቀለ በኢሕአዴግ የደህንነት አባላት መገደላቸዉን ከሥፍራዉ የደረሰን ዜና ያመለክታል። Read more…

ዜና

ቁጥር ከሆነ ከዚያ ምረጥ – ከእንግዳ ታደሰ (ኖርዌ)

September 26th, 2009

ክብሩንና ህይወቱን ለልጆቹ ሰዋ ! – ከበልጅግ አሊ

September 26th, 2009