ግርማ ካሳ
(muziky68@yahoo.com)
ጥቅምት 21 ቀን 2002 ዓ.ም
ትዝ ይለኛል ከሁለት አመታት በፊት ከአንድ ኢሕአዴግን ከሚደግፍ ወዳጄ ጋር የተነጋገርኩት። የቅንጅት መሪዎች ከእሥር ቤት ተፈተዋል። ወደ ሁለተኛዉ ሚሊየነም ለመሸጋገር እየተዘጋጀን ነዉ፡፡ አቶ መለስ ዜናዊ፣ ኢንጂነር ኃይሉ ሻወል፣ ወ/ት ብርቱካን ሚድቅሳ፣ አቶ ስዩም መስፍን … ሁሉም በአንድ ላይ ጎን ለጎን ቆመዉ፣ እንደ ወንድማማቾች፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሰላም፣ የፍቅር፣ የእርቅና የአንድነት መልእክት በቴሌቭዥን ቢያሰሙን በጣም ጥሩ ይሆን እንደነበረ ለዚሁ ወዳጄ ገልዤለት ነበር። Read more…
ዜና
በጥንቱ ዘመን ኩራት … በሀሜት በአሉባልታ፣
በፈርቶ መኖር ብልጠት …. በመንደር ወሬ ውትወታ፤
ተሳሳትን ማለት ስለማንወድ …. መጯጯህ ነው ሁካታ። Read more…
Poem
ምን ላይ ነር ያቆምኩት? የትግራይ ጉዳይ ላይ። ከዚያ በፊት ግን፡ ማለትም የጀመርኩትን የሚኮሰኩስም የሚለሰልስም፤ ወደድንም ጠላንም ግን ልናመልጠው የማንችለውን ርእስ ከመቋጨቴ በፊት ትንሽ እንቀልዳለን። (በነገራችን ላይ፡ ከዳላስ ወደ ሲያትል በሚጓዘው የአሜሪካን አየርመስመር (አ.አ.) ላይ ሆኜ ነው ይሄንን ጽሁፍ የማስተካክልላችሁ። አየር መንገድ ነው አየር መስመር? ሁለቱስ ምን ለውጥ አለው? ምንም። Read more…
ዜና
ትንሽ ወደኋላ፡ ሌላ ዙር ቅስቀሳ
ቅስቀሳ እወዳለሁ። “ይሄ ቅስቀሳ አይደለም ቁስቆሳ ነው። ለነገሩ አብላጫው ዝምተኛ፡ ያንተን ቅስቀሳ የሚያነብ አይደለም፡ ዝም ብለህ ነው የምትደክመው” የሚል ቀስቃሽና ቀዥቃዥ አስተያየት ደርሶኝ ነበር፡ ሰሞኑን። Read more…
ዜና
Abugida October 29
ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ በሽራተን አዲስ ሊፈረም ታቅዶ መኢአድ በመጨረሻ ሰአት የፖለቲካ እስረኞችና የምርጫ ቦርድ ጉዳይ እንደገና ካልታየ አልፈርምም በማለቱ የእለቱ የፊርማ ስነስረአትና ድርድሩ መቃረጡን መዘገባችን ይታወሳል። Read more…
ዜና
ከ2010 ምርጫ ጋር በተያያዘ ፊት-ለፊትና በሠያፍ የሚወረወሩት ትችቶች ብዛታቸውም ግለታቸውም እየጨመረ መሄዱ በመሀላችን የሰፈነውን የመረበሺና የጥርጣሬ ስሜት ያመለክታል። Read more…
ዜና
አቡጊዳ – ጥቅምት 18 ቀን 2002 -
በወያኔ/ኢሕአዴግ ካድሬዎችና የደህንነት አባላት ከፍተኛ ግፍና ሰቆቃ የደረሰባቸዉና ከተለያዩ የአገራችን ግዛቶች የመጡ 25 የአንድነት ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች፣ የአንድነት ፓርቲ፣ አርብ ጥቅምት 20 ቀን ፣ ለዚህ ተብሎ በኢምፔሪያል ሆቴል ባዘጋጀዉ ሲምፖዚየም ላይ የደረሰባቸዉን ግፍ በማስረጃ እንደሚያቀርቡ ከስፍራዉ የደረሰን ዜና ያመለክታል። Read more…
ዜና
አቡጊዳ – ጥቅምት 18 2002 ቀን
በስዊድን አገር በሚገኝ በአንድ ትልቅ የፖለቲካ ፓርቲ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሆኑት ወ/ሮ ካሪና ሄግ አዲስ አበባ እንደሚገኙ ከስፍራዉ የደረሰን ዜና ያለመልክታል። ወይዘሮዋ ከዚህ በፊት ባደረጉት ጉብኝት ወ/ት ብርቱካን ሚድቅሳን ቃሊቲ ድረስ ሄደዉ ለማየት ያደረጉት ሙከራ ሳይሳካላቸዉ በመቅረቱ፣ የብርቱካን ሚደቅሳን እናት ወ/ሮ አልማዝ ገብረእግዚአብሄርና ልጅ ሃሌ ሚደቅሳን ብቻ አይተዉ መመለሳቸዉ ይታወሳል። Read more…
ዜና
Recent Comments