ማህደር

ማህደር ለ December, 2009

አፈናዉ ቢበዛም በአዲግራት ሰባት መቶ፣ በሽሬ ሁለት መቶ ኢትዮጵያዉያን አረና በጠራዉ ስብስባ ላይ ተገኙ !

December 23rd, 2009

አቡጊዳ – ታህሳስ 14 2002 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ አባል ድርጅት የሆነዉ ዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ለሉዓላዊነት፣ ቅዳሜ ታህሳስ 10 ቀን 2002 ዓ.ም በሽሬ እንዳስላሴ፣ እሑድ ታህሳስ 11 ቀን 2002 ዓ.ም ደግሞ በአዲግራት ሕዝባዊ ስብሰባ ማድረጉን ያነጋገርናቸዉ የአረና ሊቀመንበርና የመድረክ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ አቶ ገብሩ ሥራት ገለጹ። Read more…

ዜና

የቃሌ ምሽት – ሻማ ማብራት በመስቀል አደባባይ ለማድረግ አንድነት ማመልከቻ አስገባ !

December 23rd, 2009

አቡጊዳ – ታህሳስ 13 ቀን 2002 ዓ.ም

መድረክ እሑድ ታህሳስ 25 በመስቀል አደባባይ ሊያደርግ ካሰበዉ ሕዝባዊ ስብሰባ በተጨማሪ፣ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ላይ እየደረሰ ያለዉን ግፍ ለማሰብና መታሰሯን ለመቃወም ማክሰኞ ታህሣሥ 19 ቀን 2002 ዓ.ም፣ የሻማ ማብራት ሥነ-ሥርዓት በመስቀል አደባባይ ለማከናወን ይችል ዘንድ፣ ለአዲስ አበባ አስተዳደር ፍቃድ መጠየቁን ያነጋገርናቸዉ አንድ ከፍተኛ የአንድነት አመራር አባል ገለጹ። Read more…

ዜና

አራት ኪሎ ያሉ ባለሥልጣናት ያለባቸዉ ችግር ! – ግርማ ካሳ

December 22nd, 2009

(muziky68@yahoo.com)
ታህሳስ 13 ቀን 2002

ከሁለት ቀናት በኋላ የፈረንጆች፣ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ደግሞ የኢትዮጵያዉያን የገና በዓል ይከበራል። በገና በዓል ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰዉ ልጆችን ሁሉ ለማዳን ከእመቤታችን ድንግል ማሪያም በበረት ዉስጥ የተወለደበትን ታላቅ ቀን እናስባለን። Read more…

ዜና

ከብዛት ጥራት፣ – ከማተቤ መለሰ ተሰማ፡

December 22nd, 2009

ዴንማርክ በተካሄደው፡ የዓለም አየር ንብረት፡ ጥበቃ፡ ጉባዔ ላይ፡ ሕዝብንም፣ ታሪክንም፣ እግዚያብሔርንም፡ የካደው፣ የናቀውና የረገጠው፡ ዘረኛውና፡ የነፍሰ ገዳዩ የመለስ ዜናዊን፡ መሣተፍ፡ በመቃወም በአውሮፓ፡ የሚኖሩ ኢትዩጵያውያን፡ በኮፕን ሀገን፡ ከተማ ተገኝተው፡ በ17 እና 18/ 12/ 09 ድምጹን ለታፈነው፡ የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ ድምጽ በመሆን፡ በሚያስገርም፡ ጽናት ጩኽቱን ለዓለም መሪዎችና ሕብረተሰብ፡ ሲያሰሙ ሰንብተዋል። Read more…

ዜና

ጠቅሊይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በብርቱካን ሚደቅሳ መታሰር ላይ በሰጡት አስተያየት ላይ ከብርቱካንና ሁለም የህሊና እስረኞች ይፈቱ ግብረ ኃይል የተሰጠ መግለጫ !

December 21st, 2009

የአፍ ልቀት ፤ የመለስ ቅትፈት

December 21st, 2009

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በብርቱካን ሚደቅሳ መታሰር ላይ በሰጡት አስተያየት ላይ ከብርቱካን ትፈታ ግብረ ኃይል የተሰጠ መግለጫ !

December 21st, 2009

ታህሳስ 12 ቀን 2002 ዓ.ም

በዚምባብዌና በኬንያ እንደታየዉ የጥምር መንግስት መመሥረት የሚቻልበት ሁኔታ ሊኖር ይችል እንደሆን በቅርቡ ከጋዜጠኖች ተጠይቀዉ ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ሲመልሱ፣ የቀለም አብዮት በኢትዮጵያ እንደማይሰራ በማስረዳት ከምርጫ በኋላ የሚነሳ ማናቸዉም አይነት ሕገ ወጥ እንቅስቃሴ የትም እንደማያደርስና መዘዙ የከፋ እንደሚሆን ለማስጠንቀቅ ሞክረዋል። አንዳንድ የተቃዋሚ መሪዎች፣ አሁንም ካለፈዉ ስህተት እየተማሩ እንዳልሆነና አሁንም ምርጫዉን በመጠቀም አመጽ ለመቀሰቀስ ሃሳብ ሊኖራቸው እንደሚችሉም ያላቸዉን ግምት ሰጥተዋል። Read more…

ዜና

ሕግን እየጣሱ ሕግ እናስከብራለን በአንድነት ፓርቲ ውስጥ – ዜግነት ከኦስትሪያ

December 21st, 2009

አንድ ፓርቲ የሚተዳደርበት ህግና ደንብ አለው ። አባላቱም ለመተዳደሪያ ደንቡ ፍፁም ተገዢ ሆነው ፓርቲው ለቆመለት ዓላማና ግብ ይታገላሉ ። Read more…

ዜና

ከኮፐንሃገን መልስ – ክንፉ አሰፋ፣ ከአምስተርዳም

December 21st, 2009

የአፍሪካው “ተደራዳሪ” ከኮፐንሃገን መልስ እንደወትሮው በቴሌቭዢን ብቅ አሉ። የአፍሪካን ተደራዳሪ ቡድን በመምራትም ድል ተቀዳጅተው መመለሳቸውን አወሱ፡ እሳቸው ያቀረቡት ሃሳብም በበለጸጉ ሃገሮች ተቀባይነትን እንዳገኘ አበሰሩ። Read more…

ዜና

በመስቀል አደባባይ መድረኩ ታላቅ ሕዝባዊ ስብሰባ ሊጠራ ነዉ !

December 20th, 2009

አቡጊዳ – ታህሳስ 11 2002 ዓ.ም

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ጨምሮ ስምንት የፖለቲካ ድርጅቶችን በቅንጅትነት ያቀፈዉ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ አንድነት መድረክ ምክር ቤት፣ ታህሳስ 25 ቀን 2002 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ ታላቅ ሕዝባዊ ስብሰባ ለመጥራት ዉሳኔ እንዳሳለፈ አዲስ አበባ ያሉ ምንጮቻችን ገለጹ።

የአዲስ አበባ አስተዳደር ከዚህ በፊት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በመስቀል አደባባይ ሕዝባዊ ስብሰባ ለመጥራት አቅዶ በነበረበት ጊዜ፣ የአገሪቱ ሕገ መንግስት የሚደነግገዉን የዜጎች የመሰብሰብ መብትን በመርገጥ፣ የከተማዉ ፍቃድ መከልከሉ ይታወቃል። ነገር ግን አሁን መድረኩ የጠራዉ በመቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን ይገኙበታል ተብሎ የሚጠበቀዉ የመስቀሉ አደባባዩ ሕዝባዊ ስብሰባ እንዳይደረግ፣ የኢሕአዴግ ባለሥልጣናት ላይከለክሉ ይችላሉ የሚል ግምት እንዳላቸዉ ብዙዎች እየተናገሩ ናቸዉ። Read more…

ዜና