ማህደር
የአንድነት የሥራ አስፈጻሚ የሃላፊነት ሽግሽግ አደረገ – ወጣት አመራር አባል የአንድነት ዋና ጸሃፊ ሆኑ !
አቡጊዳ – ታህሳስ 6 ቀን 2002
ዛሬ ታህሳስ ስድስት ቀን 2002 ዓ.ም በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዉስጥ ትልቅ የሃላፊነት ሽግሽግ እንደተደረገ ከስፍራዉ የደረሰን ዜና ያመለክታል።
የድርጅቱ ዋና ጸሃፊ የነበሩት አቶ አሥራት ጣሴ ቁልፍ ከሆነዉ ከዋና ጸሃፊነታቸዉ ተነስተዉ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ ሆነዉ እንዲሰሩ የተደረገ ሲሆን በምትካቸዉ አቶ አንዱአለም አርጌ ዋና ጸሃፊ እንዲሆኑ ተመርጠዋል። አቶ አንዱዓለም አርጌ በጣም አስተዋይ ወጣት የአንድነት መሪ እንደሆኑ የሚነገርላቸዉ ሲሆን በቅንጅት ዉስጥ በነበራቸዉ ሃላፊነት ወያኔ/ኢሕአዴግ በቃሊቲ እሥር ቤት ከነወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳና በርካታ የቀድሞ ቅንጅት አመራር አባላት ጋር አስሯቸዉ እንደነበረ ይታወሳል። Read more…
ወሬና ውይይትን ለእውቀት ለተግባርና ለውጤት እናድርጋቸው ለመወያያ መድረኮቻችን (ክፍል አንድ) – ዳኛቸው ቢያድግልኝ
በፍርሀትና በስለላ መረብ ተተብትቦ አንደበታችን ክፉኛ ተሸብቦ ያሰብነውን መናገር ካቆምን ሦስተኛ ትውልድ መምጣቱ ነው። Read more…
በ 2002 ምርጫ የመራጩ ተሳትፎ ምን መሆን አለበት?! – ሕዝቅያስ ፍቅሬ
የዚህ ፅሁፍ አላማ የተቃዋሚ ድርጅቶች ለምርጫ 2002 እንሳተፍ ቢሉ፤ የመራጩ ድርሻ ምን መሆን እንዳለበት ለመጠቆም ነው። Read more…
ከ92 እስከ 02፡ ልደቱ አያሌው; እሱም አጣን እኛም አጣነው፡ ፡ – አለቃ ተክሌ ነኝ። ቫንኩቨር፡
ትንሽ ወደኋላ፡ የጠፉት በጎች ሲወለዱ
ጥቅምት 1992 ዓ.ም. (መሰለኝ)። አዲስ አበባ ኢትዮጵያ። ሶሰት አራአለቃ ተክሌ ነኝ። ቫንኩቨር፡ት መልካቸው ያመረ፡ ወጣት፡ ሱፍ የለበሱ፡ ቁመናቸው ብቻ ሳይሆን አቋማቸውም ጭምር የሚመሳሰል፡ ግማሹ እስላም ግማሹ ክርስቲያን፡ ግማሹ ጉራጌ ግማሹ አማራ፡ ግን ደግሞ የሚመቹ ኢትዮጵያዊ ወጣቶች/ጎልማሶች የፖለቲካ ፓርቲ አቋቋሙ ተብሎ በሬዲዮና በቴሌቪዥን ሲነገር፡ ከምር የወሰድናቸው አልነበርንም። ብንኖርም ብዙ አልነበርንም። ከተመሰረቱ ከጥቂት ወራት በኋላ፡ አሁን በህይወት የሌለና ሕወሀትን አጥብቆ የሚጠላው ወዳጄ ስንታየሁ፡ ስቴዲየም አካባቢ ወደሚገኝ ቢሯቸው ወሰደኝ። አንዳንዶቹን ነገሮች ረስቼያቸው ይሆናል። አብዛኛውንና ጠቃሚዎን ነገር በሙሉ ግን አስታውሳለሁ። ሲናገር የማይጠገበውን ወጣት ነበር ላገኝ የፈቀድኩት። ልደቱን። ግን ሌላኛውም ያው ነው። ልደቱን ሌላ ሰው ይዞታል። ስለዚህ ሙሼን አገኘሁት። በጠባብ ቢሮዋቸው ተጫወትን። ሰማናቸው። ቅጽ ልሙላ አልሙላ አላስታውስም። ግን ከዚያም በፊት እንደወደድኳቸው በዚያን እለትም ከዚያም በኋላ ወደድኳቸው። ከኢትዮጵያ እስክወጣ ድረስ አንጀቴን የሚያርሱ፡ የልቤን የሚያደርሱ የምወዳቸው፡ ፖለቲካዊ አምልኮ የማመልካቸው፡ የምን ዶ/ር ብርሀኑ፡ የምን ፕሮፌሰር መስፍን፡ የምንስ ሀይሉ ሻውል፡ የኛ ልሳናት፡ የኛ የፖለቲካ አማልክት እነ ሙሼ ነበሩ። እነ ልደቱ። ኢዴፓ። Read more…
የትኛው ባል ያግባት? – ዳግማዊ ዳዊት
ባሩድ ጥይት ጮሆ- ጠመንጃው ተባርቆ
ዱላ ተሰንዝሮ- ዱላ ተመክቶ
አንዱ ራስ አድኖ- ሌላው ተፈንክቶ
ፈሪውም በርግጎ- ዘራፍ ባዩ ገፍቶ Read more…
በግብጽ 17 ኢትዮጵያዊያን በወታደራዊ ካምፕ ታስረዋል – አምስት ህጻናትና ስምንት ሴቶች ይገኙበታል
አስዋን ከተማ በሚገኘው ችላል ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ 17 ኢትዮጵያዊያን ሁለት ወላጅ አልባ ህጻናቶች ጨምሮ ለሁለት አመታት በእስር ላይ እየተሰቃዩ መሆኑን ገለጹ። Read more…
የአንድነት ፖለቲካዊ አቅጣጫ ከሕዝቅያስ ፍቅሬ
ባለፈው የቅዱስ ሚካኤል ክብረ ባህልን ያከበርኩት ቦስተን በሚገኘው ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ነበር። እና በክብረ ባህሉ ላይ ትምህርተ ቡራኬ ይሰጡ የነበሩት ስማቸውን በውል የማላስታውሰው ቀሲስ ነበሩ። ቀሲሱም የማስተማር ፀጋቸው እጅግ የተለየ ነበር። Read more…

Recent Comments