ማህደር
ለውጥ ሲመጣ እኛ ግን …! ሶሎሞን አ.
አንድን ስርዓት አብዛኛው የማህበረሰብ ክፍል ሲደግፈው ያ ስርዓት ጠንካራ ሆኖ ለረጅም ጊዜ ሊቆይ ይችላል። ነገር ግን አንድን ስርዓት ለረጅም ጊዜ የሚያቆየው ይህ ብቻ አይደለም፤ ለምሳሌ ሕዝብ ጠልቶት ነገር ግን ካልተቃወመው ወይም ደግሞ ሕዝብ ተቃውሞት ግን ሕዝቡ ሙሉ ለሙሉ ያልተሳተፈበት ተቃውሞ ከሆነ ያ ስርዓት ለረጅም ጊዜ ሊቆይ ይችላል። ስለዚህ አንድ አምባገነን ስርዓት እንደ ሕዝቡ ሁኔታ ሊወድቅም ላይውድቅም ይችላል። እንደእኛ ሁኔታ ደግሞ በኢትዮጵያ ላይ ተንሰራፍቶ ያለው ጨቋኝ ስርዓት ገና ብዙ ጊዜ የሚቆይ ይመስለኛል። Read more…
ከዳኮታ የጥናት ማእከል የቀረበዉ የሁሉን-አቀፍ ትብብር መፍትሄነት ከእስከመቼ የዝግጅት ክፍል
ሐምሌ ፲፰ ቀን ፳፻፫ ዓመተ ምህረት በዳኮታ የጥናት ማዕከል የቀረበውን የሁሉን-አቀፍ ትብብር መፍትሄነት ተመለከትነው። የዳኮታ የጥናት ማዕከልን ለቀረቦታቸውና ለበሳል ትንታኔያቸው እናመሰግናቸዋለን። በኛ በኩል ደግሞ ይኼን ጨዋነት የተሞላበት የበሰለ የፖለቲካ ዉይይት የኛን ሀሳብ በማቅረብ እንቀላቀለዋለን። እዚህ ላይ ማሳሰብ የምንፈልገው፤ የመወያያ ርዕሱ፤ የትብብሩን መንገድ በሚመለከት የቀረበው ሀሳብ እንጅ፤ አቅራቢዎቹ ግለሰብ ሆኑ ስብስቦች አለመሆናቸውን ነው። ማንም ያቅርበው ማን፤ ውይይቱ በቀረበው ሀሳብ ላይ ነው። በዚህ መግባባት ተመርኩዘን፤ የኛን አመለካከት እናቀርባለን። Read more…
የተደበቁ እውነቶች ! የህግ ከለላ ያጣን ዜጎች እና በህጋዊ የስራ ኮንትራት ወደ ሳውዲ አረቢያ እየገቡ ያሉት ኢትዮጵያውያን አበሳ . . .! ክፍል 11 ነቢዩ በሲራክ – ከሳውዲ አረቢያ
ድርቅ፤ ረሃብ፤ የዉጭ ርዳታና የምግብ ዋስትና የማጣታችን አዙሪት ከንጉሤ ጋማ
በአሁኑ ወቅት በአፍሪቃ ቀንድ አገሮች በሶማሊያ፤ በኬንያ፤ በጂቡቲና በኢትዮጵያ በ60 አመት ታሪክ ዉስጥ ያልታየ በአይነቱ አስከፊ የሆነ የድርቅ አደጋ ተከስቷል። በዚህም 4.5 ሚሊዮን በሚሆኑ ወገኖቻችን ላይ የሞት አደጋ አንዣቧል። Read more…
ዛሬም ሁሉን-አቀፍ ትብብር አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው ዳኮታ የጥናት ማእከል
መግቢያ
ዳኮታ የጥናት ማዕከል በኢትዮጵያችን ለ20 ዓመታት የዘለቀው የትግራይ “ምርጥ” ልጆች አገዛዝ መላውን የሀገሪቱን ሕዝቦች መብት አልባና የበዪ ተመልካች እያደረገ መምጣቱን በማገናዘብ በብሔረሰብ የተደራጁትን ጨምሮ ሁሉን ያካተተ የወያኔ ተቃዋሚዎች ትብብር መመስረት አስፈላጊነትንና መቻልን በራዕይ ደረጃ ከዚህ ቀደም በጻፍናቸው ጽሁፎች ላይ አስፍረናል። የዚህን ዓይነት ሁሉን-አቀፍ ማለትም በተግባር ፀረ-ወያኔ የሆኑትን በሀገርና በብሔረሰብ ደርጃ የተደራጁ ድርጅቶችን ትብብር መመስረት የወያኔን አምባገነን ሥርዓት ፍጻሜ ለማድረስ ከሚኖረው ጠቀሜታ በተጨማሪ የአገርን ህልውናና የህዝብን ደህንነት አደጋ ላይ በማይጥል መንገድ ሰላማዊ ሽግግር ለማካሄድ ዓይነተኛ መፍትሄ ነው ብሎ በማመን የተቃዋሚ ድርጅቶች በዚህ ላይ እንዲሰሩ ሲያሳስብና ሲያበረታታ ቆይቷል። Read more…
የህሊና ሸክም አለባቸው እስክንድር ነጋ
በዚህ ሳምንት የማካፍላችኹ ዛሬ ማክሰኞ ሐምሌ 19 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም አዲስ አበባ ውስጥ ከሚታተመው መሰናዘሪያ ጋዜጣ ጋር ያደረግኹትን ቃለምልልስ ነው፡፡ በዋናነት የሚያጠነጥነው በፀረ ሽብር ሕጉና ባስከተለው የፍርሃት ድባብ ዙሪያ ነው፡፡ Read more…
የኦታዋው ግልጽ ህዝባዊ ስብሰባ፡ በስውር ተጠናቀቀ
“የብሄር ድርጅቶችን፡ አቅርቦ መያዝ እንጂ፡ ሙሉ በሙሉ ማግለሉ አግባብ አይደለም” እኔ።
“የብሄር ድርጅቶችን እንደውም መድረክ በመስጠት ማጠናከር ሳይሆን ማጥፋት ነው” አንድ ተሳታፊ።
“የኢትዮጵያን አንድነት የማይቀበሉ የብሄር ድርጅቶችን እንደውም ወደፊት እንደወያኔ የምንዋጋቸው ናቸው” ዶ/ር ኤርሚያስ ዓለሙ። Read more…

Recent Comments