ማህደር

ማህደር ለ August, 2011

ፍኖተ ነጻነት-በኢትዮጵያ ሰዎች በርሃብ እየሞቱ ነው

August 31st, 2011

በአገራችን የተከሰተውን የድርቅ አደጋ የሚዳስስ ጥናት ተደረገ::

- “የተመጣጣኝ የምግብ እጥረት እየተከሰተ ነው”
- “በሴፍቲኔት የታቀፉት በረሃብ ተጋልጠዋል”
- “ለረሃብ የተጋላጮች ቁጥር ብዛት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው”
- “የከብቶች ዋጋ እያሽቆለቆለ ነው” Read more…

ዜና

ፍኖት ጋዜጣ – ጋዜጠኛ ዉብሸትንና ርዮት አለሙን በተመለከተ የቀረበ ሪፖርት

August 31st, 2011

አደራው ቀጠለ! በተፈሪ መንግስቴ

August 31st, 2011

ተውለብልቦ እንዲቆይ ከፍብሎ በድምቀት
ሰንደቅአላማችን ሁሌም ባራት አመት
አቤ ደከም ሲል የማራቶኑ አባት
ማሞን አስቀደመው አደራ ሆኖበት
ሜክሲኰ እንዲቀጥል ሮም የጀመሩት። Read more…

ዜና

ኢትዮጲያን ለግብጽና ለቱኒዚያ የህዝብ አመጽ አድንቆት ተገቢ ነው በዶ/ር አክሎግ ቢራራ

August 31st, 2011

ፍኖት ጋዜጣ – ኢትዮጵያዊነትኔን ማንም ሊነግረኝ አይችልም !

August 31st, 2011

በህይወቴ የማንነት ጥያቄ ችግር ኖሮብኝ አያውቅም፡፡ነገር ግን ክፉዎች፣ የሀገር መምራት ሥልጣነ-መንበሩን ከተቆናጠጡት በኋላ (እግዚአብሔር የሥራቸውን ይስጣቸው) በሚመቻቸውና ሥልጣናቸውን ለማርዘም ሲሉ ብቻ ከፋፈሉን፡፡ ለያዩን፡፡ እኛ ግን እግዚአብሔር ይመስገን እስካሁን አለን፡፡ ወደፊትም ሳንከፋፈል እንኖራለን፡፡
Read more…

ዜና

ዊኪሊክስ ፣ወያኔ ፣አሜሪካ እና የስርዓቱ ስነልቦና ሳ.ግ. እንዳዘጋጀው

August 31st, 2011

ከወራት ቆይታ በኋላ በአውስትራሊያዊው ጁሊያን አሳንጅ የሚመራው የጸረ ምስጢራዊነት ቡድን/ድርጅት ዊኪሊክስ ሰሞኑን በጣም ብዛት ያላቸው የአሜሪካን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምስጢራዊ ቴሌግራሞችን በመረጃ መረቡ ላይ ለቋል:: እ.ኤ.አ. በ 26/08/2011 ከተለቀቁት ሰነዶች ውስጥ በቁጥር በርካታ የሆኑ ከአዲስ አበባው የአሜሪካ ኤምባሲ ወደ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የተላኩ ይገኙበታል:: ምንም እንኳን አሁን የተለቀቁት ሰንዶች ያንንም ያህል አፍ የሚያስከፍቱ ምስጢሮች ባይዙም በውስጣቸው ግን ለትዝብት የሚሆኑ እና የስርኣቱን መሪዎች ስነልቦና ሊያሳዩ የሚችሉ አንዳንድ ቴሌግራሞችን አግኝቻለሁ:: ከተሰደሩት ኬብሎች ውስጥ አይኔ ውስጥ የገቡትን የራሴን አስተያየት አክዬ እንደዚህ አቅርቤላችኋለሁኝ:: እስቲ አንዳንዱን አብረን እንያቸው:: Read more…

ዜና

ሁለተኛው ሕዝባዊ አብዮት ከሳሙኤል ሽፈራው/ዳላስ

August 30th, 2011

በአገራችን ለውጥን ስንመኝ ታሪካዊ ስርነቀል ለውጥን ለማምጣት በግንፍል የተነሳውን የየካቲት 1966 አብዮት ሳናነሳ ልናልፍ አይቻለንም። በቅድመ የካቲት የነበሩ አብዮታዊ ሁኔታወችን ዛሬ ላይ ሆነን ከተዋነያኑ ግምጋሜ ጋር ስናነጻጽር፣ ዛሬስ የተሻሉ ሕሊናዊና ድርጅታዊ ሁኔታወች አሉ ወይ ብለን እራሳችንን ልናይ እንገደዳለን። Read more…

ዜና

ጉራማይሌ ሕዝብና መንግሥት በኢትዮጵያ በነጻነት ዘገዬ

August 30th, 2011

ታርጋ በቀላሉ የሚወጣባት ብቸኛዋ ሀገር

በተለይ በሀገርኛ ባህል ያገባችሁ ይሄ የባህል የሠርግ ዘፈን ትዝ አይላችሁም? ‹እሸት ፣ እሸት፣ የወረት፤ እሸት ቢሉህ…የሽምብራ እንዳይመስልህ፤ እሸት ቢሉሽ… የማሽላ እንዳይመስልሽ…› ይህ ነገር በጽሑፍ ሳይሆን በዜማ ነበር የሚያምረው፤ ታዲያ ምን ዋጋ አለው – የምንገኝበት ሥፍራ ተራራቀ፡፡ Read more…

ዜና

ይድረስ ብዙ ለኖሩ ፖለቲከኞቻችን (ሶሎሞን አብርሃም)

August 30th, 2011

አሁን ያለችው ኢትዮጵያ ከመቸውም ጊዜ በላይ የምታሳዝን ሃገር ሆናለች። በነፃነትና በሰላም ተጠብቆ የመኖር መብታችን ተከብሮ ባያውቅም አሁን ደግሞ ያለገደብ ተጥሷል። ሰዎች በአመለካከታቸው ብቻ ይታሰራሉ፣ ይደበደባሉ፣ ሴቶች የደፈራሉ፣ መኖር ይከለከላሉ፣ በህግ ፊት እኩል አይደሉም፣ ፍትህ ተጓድሏል። ገዢዎቻችን አንብበው የማያውቅትን ህገ መንግስት ማገላበጥ የሚጀምሩት የዜጎችን መብት ለመርገጥ ብቻ መሆኑ እንደተባለው ህገመንግስቱን ህገ አራዊት አስመስሎታል። የሰው ልጅ ሲወለድ ነፃና በክብር፣ በመብት እኩልነት ያለው ነው የሚለውን ድንጋጌ ረስተዋል። ነፃነት፣ ፍትሕ፣ ዴሞክራሲ የሚባሉት መሰረታዊ ነገሮች በኢትዮጵያ ምድር ተሳክተው አያውቁም። Read more…

ዜና

በኢትዮጵያ አለ፡ ብሩሕ ተሰፋ! በታደለ መኩሪያ

August 29th, 2011