ማህደር

ማህደር ለ August, 2011

ፍኖት ጋዜጣ – “ህዝቡ ሠላማዊ ለውጥ ይፈልጋል፤ ጊዜው የለውጥ ነው” እስክንድር ነጋ

August 23rd, 2011

በዚህ ሳምንት የማካፍላችኹ ዛሬ ማክሰኞ አዲስ አበባ ውስጥ ከሚታተመው ፍኖተ -ነፃነት ጋዜጣ ጋር ያደረግኹትን ቃለምልልስ ነው፡፡ ሙሉ ቃለ ምልልሱን ለማንበብ: www.andinet.org Read more…

ዜና

አቡጊዳ – ሕዝቡ ኑሮ መረረኝ እያለ ነዉ

August 21st, 2011

በኢትዮጵያ የኑሮ ዉድነቱ ከቁጥጥር ዉጭ መሆኑን አዲስ አበባ በሳምንት ሁለት ጊዜ የሚታተመዉ የሪፖርተር ጋዜጣ ዘገበ። እንኳን በድህነት የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ቀርቶ ደህና ገቢ የነበራቸዉ ሁሉ ሳይቀሩ በጣም እያማረሩ እንደሆነ የዘገበዉ ሪፖርተር፣ በዚህ ረገድ አስቸኳይ መፍቴሄ መፈሰጠት እንዳለበትም አሳስቧል። Read more…

ዜና

ማዳመጥ ያልቻለ አድማጭ ያጣል በአሉላ(የዶ/ር ጌታቸው በጋሻው ጽሁፍና የፓልቶክ ውይይት)

August 20th, 2011

የጭቆና ሰንበሮች በአንዱዓለም አራጌ

August 20th, 2011

ከመጀመሪያዋ የብርሃን ብልጭታ ጀምሮ ጊዜ እንደ ጅረት ይተማል፡፡ የጊዜ ጅረት መጠኑ አይሞላም፣ አይጎድልም፣ ሁልጊዜም አንድ ነው፡፡ የማይደርቅ ጅረት ነው፡፡ ትውልድም ከሰው ልጅ የህላዌ ጅማሮ አንስቶ በጊዜ ስጋጃ ላይ ይነጉዳል፡፡ የትውልድ ጅረት ግን አቀበትና ቁልቁለት፣ የበጋ እና የፀሐይ ወራት አሉት፡፡ የትውልዱ ዘመን ትርጉም፣ ማጠሩም መርዘሙም ከዚህ አንፃር ሊቃኝ ይገባዋል፡፡ የአንድ ትውልድ ዘመን የበልግ ወራቶች ካልበረከቱበት የሰኮንድ፣ የደቂቃ፣ የሰዓታት፣ የቀናትና የዓመታት እብቅ ክምር ከመሆን አይዘልም፡፡ ፍሬ አልባ ገለባና ዱካአልባ ጉዞ ይሆናል፡፡ Read more…

ዜና

መገንጠል ለዴሞክራሲና ለፍትህ መስፈን ዋስትና አይሆንም በገለታው ዘለቀ

August 20th, 2011

አርአያነታቸው የሚያኮራ ፍጡራን በይነጋል በላቸው

August 20th, 2011

እንደምን ሰነበታችሁ ውድ አንባቢያን፡፡ የሰሞኑ የሀገራችን የፖለቲካ ንፋስ እንዴት ይዟችኋል? እኔማ አንዱን ስሰማው እያደነገዘኝ ሌላውን ስሰማው ደግሞ እያደነዘዘኝ ፈዝዤላችኋለሁ፡፡ ለደግ ያድርግልህ በሉኝ፡፡ አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ የምንገኝ ይመስለኛል፡፡ አንዱ ከአንዱ መማርና ካለፈ ታሪክ ዕውቀትን ገብይቶ የወደፊቱን ለማስተካከል መሞከር ዕርም የተባለበት ጊዜ ላይ ሳንደርስ የቀረን አይመስለኝም፡፡ ትርምስምስ ያለ አኳኋን ላይ የመገኘታችን ምሥጢር ግልጽ ሊሆንልኝ አልቻለም፡፡ ኧረ አንድዬ አስተዋይ ልቦና ሰጥቶን በቃችሁ ይበለን እናንተዬ! ነገራችን ሁሉ እኮ የእምቧይ ካብ እየሆነ በጣሙን ተቸገርነ፡፡ Read more…

ዜና

የጎሳ ፖለቲካና አንድነት በካሳሁን በጋሻው

August 20th, 2011

የሚበጀን በጎደለው መሙላት እንጂ ጎዶሎውን መድፋት አይደለም በዳኛቸው ቢያድግልኝ

August 20th, 2011

ታየኝ እኮ፡ ሀረርና ወለጋ ገጥሞ፡ የ“ኦሮሚያ”ን ሪፐብሊክ ሲመሰርት ችግሩ ግን፡ ግንቦት ሰባትና እኛ ጋር ነው በተክለማሪያም

August 19th, 2011

ብሄርንና ሀይማኖትን መሰረት ያደረገ ክርክር አስቸጋሪ ነው። ሀይማኖት ይብሳል። በንጽጽር፡ ከሀይማኖት ደግሞ ብሄር ለክርክር ይቀላል። ለጥቂት ጽንፈኛ ኦሮሞዎች የምንወረውረው ትችት ወይንም ስላቅ፡ አያሌ ለስላሳ ኢትዮጵያዊ ኦሮሞዎችን ሊያስቀይም ይሆንብናል። በመርህ ደረጃ፡ ከማናቸውም ብሄር-ቀመስ ድርጅቶች ጋር የሚደረግ ውይይት ባያስደነግጠኝም፡ መጀመሪያ ይሄ የግንባር/ህብረት ምስረታ ጉዳይ፡ ለጥቆ ደግሞ ከኦነግና ኦብነግ ጋር የሚደረገውን ውይይት ያመጣው ግንቦት ሰባት ነውና፡ ማምጣትም ብቻ አይደለም፡ የተወሰኑ የኦነግ አባላት የሚናገሩትን ሰባራ አረፍተ ነገሮች ይዞ፡ በግነት “ኦነግ የመገንጠል ሀሳቡን ጥሏል” ብሎ ለነገር ያሰፈሰፉትን በባዶ ሜዳ አስጮኋልና፡ መጀመሪያ ግንቦት ሰባትን ትንሽ ለኮፍ አደርገዋለሁ። ከዚያ ወደ ኦነግ እወርዳለሁ። Read more…

ዜና

ቅራኔዎች ግጥም በፍሬው አንተነህ

August 18th, 2011