ማህደር

ማህደር ለ December, 2011

ክፉ ዘመን (ዘመነመንሱት) – በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ‏

December 31st, 2011
Comments Off

የሻማ ማብራት ምሽት ዋሽንግተን ዲሲ

December 31st, 2011
Comments Off

‘ፍርሀቴን አቃጠልኩት’ ለየኔሰው ገብሬ የተፃፈ ዳኛቸው ቢያድግልኝ

December 31st, 2011

እሳት ማቀጠሉን እንዲያውቁ አዲስ አባበን አቃጥለን አናሳይ ነገር። በዳዊት ዳባ

December 31st, 2011

የጥፋት ሀይል ነው፤ ይህ ቡድን ጭራሽ ለሀዝብ ከበሬታና ፍቅር የለውም፤ አገር ሻጭ ነው፤ በጭራሽ የሚታመን አይደለም፤ ጨፍጫፊ ነው። በአጠቃላይ ከሴጣን ነው የምትጋቡ፤ በርምጃችሁ አናንተም ወገኖቻችሁንም ትጎድበታላችሁ። የመለስን መንግስት በሚመለከት እነዚህን በመሰሉ ጉዳዬች ላይ ለያንዳንዳቸው ይዘቱ ቅዱሱን መፀሀፍ የሚያካክል መረጃዎች ሊቀርብበት የሚችል ፍፁም የሆነ እውነትነት ያላቸው ክሶች ናቸው የሚነሱት። ጊዜው ሲመጣ በሀገር ክህደት፤ በዘር ማጣፍት በመሳሰሉ ክብደት ባላቸው ወንጀሎች አስከሳሽ ናቸው። አዲስ ህግ ማርቀቅ ሳያስፈልግ ባወጡት ህግ የመለስ መንግስትም ድርጅታቸውም ወንጀለኛ ይሆናል። ከወንጀለኛ ጋር በምንም ሁኔታ ማበር ወንጀለኛነት ነው። በኛ አገር ሁኔታ ከወያኔ ጋር መሞዳመድ ፍፁም ከሀዲነትም ነው። አስላ ሾሽት አመት ያልሞላው ካልሆነ ይህን የወያኔ ባህሪና የሚያመጣውን ጣጣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በደንብ ማወቅ ነበረበት ያውቃልም። እፉ ነው ተብለው ተደጋግሞ ቢነገራቸውም እጃቸውን ሰደው ተቃጥለው ካላዩ የማይሰሙ የህፃን ባህሪ ያላቸው ዜጎች ግን ሁሌም አሉን። Read more…

ዜና

ረሃብና የኢትዮጵያ ተስፋ በፍሬሰው ፈለቀ

December 31st, 2011

ረሃብ በሀገራችን እንደማንኛውም የዓለም ሕዝብ የሚታወቅ ሲሆን በኢትዮጵያ ለየት የሚያደርገው ባለፉት አርባ ዓመታት ከረሃብ የተለችበት ጊዜ አለመኖሩና መለመዱ ነው። በየአገሩ ያለው ረሓብ እንደማኅበረሰቡ ባህልና የኑሮ ደረጃ የሚገለጽ ሲሆን በኢትዮጵያ ረሓብ አለ የሚባለው በርካታ ሰዎች ሲሞትና ዓለም አቀፍ ዜና ማሰራጫዎች መዘገብ ሲጀምሩ ነው። Read more…

ዜና

የበረከት መፅሃፍ (ከተስፋዬ ገብረአብ)

December 31st, 2011

የበረከትን መፅሃፍ አነበብኩት…
በእውነቱ ህትመቱ ቆንጆ ነበር። ሽፋኑ እንደ ሃብታም ጉንጭ ይለሰልሳል። ከቻርልስ ዲክንስ ታዋቂ መፅሃፍ የተኮረጀ ቢሆንም ርእሱም ቢሆን አሪፍ ነው – የሁለት ምርጫዎች ወግ። የበረከትን መፅሃፍ ያሳተመው መሃመድ አላሙዲ የተባለው ነጋዴ መሆኑን ፍትህ ጋዜጣ ላይ አንብቤ ነበር። መፅሃፉ 314 ገፆች እና 10 ምእራፎች ይዞአል። ዋጋው 90 ብር ነው። Read more…

ዜና

በግለሰቦች መብት ያለም የመጨረሻዋ አገር ገለታው ዘለቀ

December 31st, 2011
Comments Off

ባለፈው ጊዜ ሌጋተም የተባለው ድርጅት የ 110 አገሮችን የብልጽግና ደረጃ ሲያጠና ሰንብቶ ባወጣው ሪፖርት ላይ በ አጠቃላይ ውጤት ኢትዮጵያ እንደተለመደው ወደ መጨረሻው ሆና 108 ኛ ወጥታለች:: እንዲህ አይነቱ የመጨረሻ አካባቢ ውጤት የተለመደ በመሆኑ እምብዛም አልተገረምን:: Read more…

ዜና

አቡጊዳ – የአቃቤ ሕግ መረጃ እነእስክንድር ሰላማዊ እንጂ ሽብርተኞች እንዳልሆኑ በገሃድ አረጋገጠ !

December 30th, 2011

አቃቢ ሕግ ሰባተኛ ተከሳሽ በሆነዉ ፣ አቶ እስክንድር ነጋ፣ ግንቦት 20 2002 ዓ.ም የተጠለፈ፣ ከአዲስ ድምጽ ራዲዮ አዘጋጅ አቶ አበበ በለዉ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስን እንዲሁም በከረንት አፌር ፓልቶክ ክፍል በብዙ ወንድማገኘዉ (ሞያዬ ምስክር) አወያይነት የተደረገን ዉይይት፣ ትላንት ዴሴምበር 29 ቀን በተቀመጠዉ የፍርድ ችሎት፣ እንደ መረጃ ማቅረቡን፣ የአማርኛዉ ክፍል ጀርመን ድምጽ ራድዮ ሪፖርተር ከአዲስ አበባ ዘገበ። Read more…

ዜና

አቡጊዳ – ኦነግ ኢትዮጵያዉያንን ሁሉ የጋበዘ ስብሰባ በሜኔሶታ ጠራ !

December 29th, 2011

የኦሮሞ ነጻ አዉጭ ግንባር፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያዉያንን ሁሉ የጋበዛ አገራዊ ስብሰባ በሜኔሶታ እንደጠራ የዘሐበሻ ጋዜጣ ድህረ ገጽ ገለፀ። «እሁድ ጃንዋሪ አንድ ቀን በኢን ሆቴል ሴንት ፖል በሚደረገዉ በዚሁ ስብሰባ ላይ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከሌሎች ኢትዮጵያዉያን ወንድሞቹ ጋር በጽናትና በአንድነት የሚታገልበትን ሁኔታ ያበስራል ተብሎ ይጠበቃል» ሲል ያተተዉ ዘሃበሻ፣ በአካካቢዉ ካሉ በርካታ ስቴቶች ብዙዎች የሰብሰባዉ ተካፋይ ለመሆን እንደሚመጡም ይገልጻል። Read more…

ዜና

አቡጊዳ – ከሳሞራ የኑስ ጋር የማይስማሙ ጄነራሎች ተባረሩ !

December 28th, 2011

አገር ዉስጥ የሚታተመዉን ካፒታል ኢትዮጵያ የተሰኘዉን የእንግሊዘኛ ጋዜጣ ጠቅሰን፣ ወደ ሶስት መቶ የሚሆኑ ከፍተኛ የኢትዮጵያ መኮንኖች ስራቸዉን እንዲለቁ መደረጉን መዘገባችን ይታወሳል። ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ እንደሚጠቁመዉ ከስራ እንዲሰናበቱ ከተደረጉት መኮንኖች መካከል ጄነራል ሳሞራ የኑስ እና ከርሳቸው ጋር ቅርበት ያላቸዉ ሞኮንኖች እንዳልተነኩ ለማወቅ ችለናል። Read more…

ዜና