ማህደር
ፍትህ – የፍትህ ጋዜጣ ከወቅታዊ ዘገባዎቿ ጋር
የፍትህ ጋዜጣ አገር ዉስጥ የምትታተም ነጻ ጋዜጣ ናት። የፍትህ ጋዜጣ አምደኛ ርዮት አለሙ ፣ የፍትህ ጋዜጣ ዘጋቢ ሂሩት ክፍሌ፣ ለአሥራ አራት እና ለአሥራ ዘጠኝ አመታት ኢሰብዓዊና ሕግ ወጥ በሆነ መንገድ መሰረተ ቢስ በሆነ የሽብር ተግባር ተሰማርታችኋል በሚል በቃሊቲ እሥር ቤት እየተሰቃዩ ነዉ። Read more…
ፍትህ ጋዜጣ ርዕስ አንቀጽ – በኤርትራ ጉዳይ መመካከር ያስፈልጋል
የአለም አቀፍ ግንኙነት ፖለቲካን የሚያጠኑ ምሁራን በሁለት ሀገራት መካከል ስለሚኖር ግንኙነት ሲገልፁ እንዲህ ይላሉ ‹‹በአለም አቀፍ መድረክ ዘላቂ ወዳጅም ይሁን ዘላቂ ጠላት የለም›› ፡፡ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በአንድ የታሪክ አጋጣሚ በተመሳሳይ ስም በአንድ ገዢ የሚተዳደሩ አንድ ወጥ በሆነ የፖለቲካ ስርዓት ማዕቀፍ ውስጥ የነበሩ ወንድምና እህታማች አገራት ነበሩ፡፡ አሁንም በአንድ የታሪክ አጋጣሚ አንዱ ራሱን ቅኝ ተገዢ ሌላው ቅኝ ገዢ አድርጐ በመቀጠር ላልተፈለገ ጦርነት ተዳርገው መጨረሻውም የሚታወቀው ሆነ፡፡ Read more…
መድረክ የሊዝ አዋጁን የሚቃወም ሕዝባዊ ስብሰባ እጠራለሁ አለ (ሪፖርተር)
ከመቼውም ጊዜ በላይ ከአገሪቱ አነጋጋሪ ጉዳዮች በላይ የሊዝ አዋጁ አወዛጋቢነት ተፋፍሞ በቀጠለበት ወቅት፣ የኢሕአዴግ ዋነኛው ተቀናቃኝ ነኝ የሚለው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ፣ በሳምንቱ መገባደጃ ላይ በአዋጁ ላይ ጠንከር ያለ ተቃውሞ ይዞ ቀርቧል፡፡ Read more…
የጎጠኝነት አጥሩ እየተሰበረ የአገር አንድነት የሚያስከብር የተስፋ ጎህ እየቀደደ ነው!! በዳኛቸው ቢያድግልኝ
ኸረ የፍትህ ያለህ! ከንጉሤ ጋማ
በዛሬይቱ ኢትዮጵያ የህግ የበላይነት እንዲከበር፤ ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲኖር እና በዲሞክራሲያዊ ስርኣት ዉስጥ ዜጎች በእኩልነት ሰብኣዊ መብታቸዉ ተጠብቆ እንዲኖሩ የሚያስቡ፡ የሚናገሩ፤ የሚፅፉና የሚቆረቆሩ በጠቅላላዉ ለነዚህ ፅንሰ ሃሳቦች ዘብ የሚቆሙ በሙሉ የስርኣቱ ጠላቶች ተደርገዉ በመቆጠር ላይ ናቸዉ።
ለአገሪቱ አንድነትና ሉኣላዊነት፤ እድገትና ብልፅግና በጣት ከሚቆጠሩ መሪዎቿና የፓርቲያቸዉ ጠባብ ጎሰኛ ፖሊሲ የተለየ የሚያስቡ ዜጎችና ቡድኖች ሁሉ “የስርዓቱ ጠላት” እና “ሽብርተኞች” ወይንም “አሸባሪዎች” ተደርገዉ ይቆጠራሉ። Read more…

Recent Comments