ማህደር

ማህደር ለ February, 2012

በሕዝባዊ ንቅናቄ ሠላማዊ ትግል ያሸንፋል! ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)

February 29th, 2012

በአገራችን ኢትዮጵያ ኢህአዴግ በሥልጣን ላይ በቆየባቸው ባለፉት ሃያ አመታት ውስጥ የተፈፀሙ ኢ-ሠብአዊ፣ ኢ-ዴሞክራሲያዊና ኢ-ፍትሓዊ ድርጊቶችን ስንቃወምና ስናጋልጥ ቆይተናል፡፡ ገዢው ፓርቲ ግን አንድም ጊዜ ስህተቱን ሲቀበልና ሲያርም አልተስተዋለም፡፡ ይልቁንም የተለያዩ አሳሪና አስፈሪ አዋጆችን፣ መመሪያዎችን፣ ድንጋጌዎችን እያወጣና ለሕገ-መንግሥቱ እንኳ ሳይገዛ ባደባባይ በተደጋጋሚ በማን አህሎኝነት ከሕግ በላይ እየሆነ ነው፡፡ ህዝብ በኑሮ ውድነት፣ በመልካም አስተዳደር እጦት፣ በሕግ የበላይነት አለመኖር፣ በሙስና መንሠራፋት፣ በዴሞክራሲያዊ መብቶች አለመከበር ወዘተ በሚደርስበት በደል በየእለቱ ይጮሃል፡፡ ስርዓቱ ግን ‹‹ግመሎችም ይጓዛሉ፤ ውሾቹም ይጮሃሉ›› እንደተባለው ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት በድርጊቱ እየገፋበት ይገኛል፡፡ ነገሮች ሁሉ ካቅም በላይ እየሆኑ መጥተዋል፡፡ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) በአገራችን ሠላማዊ የሥልጣን ሽግግር እንዲመጣ አበክሮ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ፓርቲያችን ለሠላማዊ ትግሉ ባለው ቁርጠኝነት በአዋጅ እስካልተከለከለ ድረስ እስከመጨረሻው ይገፋበታል፡፡ ለዚህም በቁርጠኝነት ይታገላል፡፡ Read more…

ዜና

ፍኖተ ነጻነት እትም 31 ከዜናና ልዩ ልዩ መጣጥፍ ጋር

February 28th, 2012
Comments Off

ኢትዮጵያዊያንን ያሰቃየው ግለሰብ በየመን ለፍርድ እንዲቀርብ ተጠየቀ ሀበሻ በየመን በየመን ክፍል 11 በግሩም ተ/ይማኖት

February 27th, 2012

ተንደርድሬ ጥልቅ ሳልሰናበት ውልቅ ማለት አለመደብኝም እና ወደ ዋናው ጉዳይ ከመግባቴ በፊት የዚህ ሰሞኑ ዜናዎች እንደመክፈቻ ላቋድስ፡፡ ታዲያ ዜና ዘገባው ከተለያየ አቅጣጫ በመሆኑ እና በዛ በማለቱ የዜና አምድ እንዳይመስል ስል አሳጥረዋለሁ ስለዚህ ቅድመ ይቅርታ ላቅርብ፡፡ እለት ከእለት ወደ የመን የሚፈልሰው ስደተኛ ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ እንዳሳሰባቸው ቀይ መሰቀል፣ አይ ኦ ኤም እና በጉዳዩ በጥምረት እየሰሩ ያሉ ድርጅቶች አስታወቁ፡፡ በአሁኑ ሰዓት ከሶማሊያዊያን ይልቅ ይበልጥ እየተሰደዱ ያሉት ኢትዮጵያዊያን መሆንቸውን እና ለጉዳት ተጋላጭ እየሆኑም እንደሆነ ጨምረው አስታውቀዋል፡፡ ጉዟቸው በመረጃ ያልተደገፈ እና ህጋዊ ባልሆነ መንገድ /ህገ-ወጥ/ በመሆኑ ለዘራፊዎች ከመጋለጣቸውም በላይ ለሞት እየተዳረጉ መሆኑንም ድርጅቶቹ አስምረውበታል፡፡ Read more…

ዜና

አባ ሆይ! ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

February 26th, 2012

አደገኛ የተቀነባበረ የዘር ማጥፋት ሴራ ክፍል ሁለት በዳኛቸው ቢያድግልኝ

February 25th, 2012

የአለማየሁ እህት (ከተስፋዬ ገብረአብ)

February 25th, 2012

ሳሊምቢኒ ጥቅምት 1 ቀን፣ 1890 በያዘው ማስታወሻ፣ አጤ ምኒልክ ትግራይ በነበሩ ጊዜ የተፈፀመ አንድ ታሪክ አንስቶአል።

በዚያን እለት ምሽት አጤ ምኒልክ ትግራይ ላይ ከተከሉት ንጉሳዊ ድንኳናቸው ተቀምጠው የቀጠሯትን አንዲት ሴት እየጠበቁ ነበር። እንደተጠበቀውም ማምሻው ላይ ወይዘሪቷ በሁለት አሽከሮች አጀብ በበቅሎ እየሰገረች ከአጤ ምኒልክ ድንኳን ደረሰች። በአካባቢው ብዙ ግርግር አልነበረም። ጥቁር ካባ የደረበች፣ በአበሻ ቀሚስ የደመቀች፣ ጠይም ረዘም ያለች ወይዘሪት ከበቅሎ እንደወረደች በጥድፊያ ወደ ንጉሱ ድንኳን እንድትዘልቅ ተደረገ። ይህች ሴት አልጣሽ ቴዎድሮስ ትባላለች። የአጤ ቴዎድሮስ ሴት ልጅ ስትሆን፣ የአጤ ምኒልክ ደግሞ የመጀመሪያ ሚስት ነበረች። Read more…

ዜና

የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አባቶች በዊኪሊክስ ፋይሎች በአብይ አፈወርቂ

February 25th, 2012
Comments Off

የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት “እኔ ከተከሰስኩ ወ/ሮ አዜብ መስፍንም መከሰስ አለባቸው” አሉ (በመምህሩ መልካሙ)

February 25th, 2012

የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በከፍተኛ የሙስና ወንጀል እንዲጠየቁ የክልሉ ፓርቲ ባደረገው ድርጅታዊ ግምገማ ውሳኔ አስተላለፈ።
ፕሬዚዳንቱ “እኔ ብቻዬን መከሰስ የለብኝም። ከተከሰስኩም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር መሆን አለበት” በማለት ስብሰባ ረግጠው መውጣታቸውን ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ምንጮች አስታወቁ። አቶ መለስ ድርጅቱ የወሰነውን ውሳኔ ቀለበሱ። Read more…

ዜና

ትውስታየ በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር

February 24th, 2012

የምድር ፈራጅ ሆይ ከፍ ከፍ በል፤
ለትዕቢተኞች ፍዳቸውን ክፈላቸው።
አቤቱ ህዝብህን አዋረዱ፤
ርስትህንም አስቸገሩ።
መዝሙረ ዳዊት 93/4 ቁ 2-5 Read more…

ዜና

ወገኔን ታዘብኩት… ትዝብቴ ለሚሰደዱ! (ሶሎሞን አ.)

February 24th, 2012

ኢትዮጵያዊ ተዋዶ፣ ተዋልዶና ተዛምዶ ኖሯል ለዘላለምም ይኖራል!
እንዳትሰደድ የሚለውን የወዳጅ ዘመድ ምክር ችላ ብለህ ብትሰደድ ከሁሉ በላይ ሕውሓትን አስደስተህ አንተም ይብዛም ይነስም ችግር ውስጥ ለመባዘን ተዘጋጅ። ከዲያስፖራው ወገን ጋዜጠኛ ወይ ባለጠጋ ካልሆንክ ስለተሰደድክ እምቢልታ አይነፋልህም፣ ነጋሪት አይጎሰምልህም። Read more…

ዜና