የእነ አንዱዓለም አራጌን ክስ ሲከታተል የነበረው ፍድር ቤት ሰኔ 20 ቀን 2004 ዓ.ም. በተሰየመው ችሎት፣ ሁሉንም ተከሳሾች ጥፋተኞች በማለት ውስኔ ሰጥቷል፡፡ አቶ መለስ ዜናዊ በተለያዩ አጋጣሚዎች የታሳሪዎችን ጥፋተኛነት በአደባባይ የተናገሩትን፣ ፍርድ ቤቱ በጹሁፍ አንብቦታል፡፡ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ፍርድ ቤቶች ነጻነት የሚባል ፈጽሞ የሌላቸው ተቋሞች መሆናቸውን ከማሳየት ያለፈ ፋይዳ አልነበረውም፡፡ በተጨማሪም የፍትህ ተቋማት ህውሓት/ኢህአዴግ በስልጣን እስካለ ድረስ ነጻ ሊሆኑ እንደማይችሉም ዳግም ማረጋገጫ የሰጠ ሆኗል፡፡ ነገም ቢሆን በተመሳሳይ ሁኔታ በሽብርኝነት ሰበብ ተከሰው ውሣኔ በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ የመድረክ ፓርቲ አመራር አባላት የሚጠብቃቸው ውሣኔ የተለየ ሊሆን እንደማይችል መገመት አሰቸጋሪ አይሆንም፡፡ Read more…
ዜና
ያሳለፍነው ግማሽ ምዕተ ዓመት የኢትዮጵያ ህዝብ ለሰብአዊ ክብሩና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የታገለበት ዘመን ነው፡፡ ይሁን እንጂ የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቹ ባለቤት ለመሆን እስካሁን አልታደለም፡፡ እኔም በተፈጠርኩበት በዚህ ዘመን ለራሴ፣ ለልጆቼና ለኢትዮጵያውያን ሁሉ ዴሞክራሲና ነፃነት እንደሚገባን በማመን አቅሜ በፈቀደው መጠን ታግያለሁ፡፡ ይኼን በማድረጌ በማንም ላይ በክፋት አልተነሳሁም፤ ይኼን በማድረጌ ህግ ጥሼ አላውቅም፤ ይኼን በማድረጌ በደሃዋ ሃገሬ ጥቅም ላይ አልተነሳሁም፤ ይሄን በማድረጌ ፈጣሪዬን፣ የኢትዮጵያን ህዝብም ሆነ ህሊናዬን የሚያሳዝን አንዳች ነገር ፈፅሜያለሁ ብዬ አላምንም፡፡ ፍፁም ሰላም ይሰማኛል፡፡ እኔን እዚህ ያቆመኝ የነፃነት ናፍቆት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶችም ፍትህን ለምኜ ስነፈግ ይኼ የመጀርያዬ አይደለም፡፡ ከሳሾቼ እንድጠጣው የሚፈልጉትን የግፍ ፅዋ በፀጋ ከመጠጣት ውጪ ባልፈረፀምኩት ወንጀል ማቅለያ የመጠየቅን አማራጭ ህሊናዬ ስላልተወልኝ አዝናለሁ፡፡
ዜና
ሰሞኑን በአርምሞ ሰነበትኩ፡፡ በሀገር ቤትም ሆነ በውጪው አሳዛኝና አስገራሚ ዜናዎችና ሀተታዎች ግን እየተደነቅሁ፣እየቆዘምኩና እየተሳቀቅሁ ከርሜያለሁ፡፡ በተለይ በተለይ በሁለቱ ጉዶች – መለስና አሳድ፡፡ Read more…
ዜና
የግብጹ ሙስሊም ብራዘርሁድ በጠባብ ልዩነት አሸነፈ፡፡ እንኳን ደስ ያለው፡፡ ማሸነፍ ደስ ይላል፡፡ እንደማሸነፍ የሚያስደስት የለም፡፡
ይህ እስላማዊ ቡድን በአፄ ሙባረክ ዘመነ መንግሥት ከሕዝቡ 20 በመቶ ብቻ ይደግፈው እንደነበር ሰምቻለሁ፡፡ ዛሬ ግን ሕዝብ ተገልብጦ 53 በመቶ አካባቢ በሚሆን የመራጮች ድምፅ ይሄው እስላማዊ ቡድን አሸነፈ ተብሏል፡፡ ዓለም ዘወርዋራ ስለሆነች ይህ ክስተት አይደንቅም፡፡
የግብጽ ነገረ ሥራ ከኛዋ ከርታታ ኢትዮጵያ ጋር በብዙ የሚመሳሰል እንደሆነ ታዘብኩ፡፡ Read more…
ዜና
መንግስት ለእስረኞቹ የርሃብ አድማ ጥያቄ ምላሽ ይስጥ!!
ወደትግሉ የገባሁት ቅድሚያ ራሴን ነፃ ለማውጣት ነው – ወ/ሮ ላቀች ደገፉ
የዶ/ር ነጋሶን ጤንነት ለመታደግ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥሪ ቀረበ
የአዲስ ዘመን ጋዜጠኞች ስለ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ያቀነባበሩት ማረሚያ ቤቱን አይገልፅም ተባለ
ከሲዖል ያመለጡ የኢህአዴግ አባላት ክፍል 2 -ቀለሙ ሁነኛው
የኢህአዴግ የስለላና የቁጥጥር መዋቅር ከ1 ለ5 ወደ 1 ለ11አደገ
ከስራ የተባረሩ መምህራን ይቅርታ አንጠይቅም አሉ
አንድነት በርዕዮተ ዓለምና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረገ
እነ አንዱዓለም አራጌ ነገ ለውሳኔ ይቀርባሉ
መንግስት ለእስረኞቹ የርሃብ አድማ ጥያቄ ምላሽ ይስጥ!!
አንድነት ፓርቲ በጊዶሌና በጂንካ ከተማ ላይ ህዝባዊ ከስብሰባ ሊያደርግ ነው
ከፍኖተ ነፃነት እስከ ፍትህ ከጋዜጠኞችና አምደኞች የታቀደው የእስር ዘመቻ -ሰለሞን ስዩም
ታላቁን የዓባይ ግድብ የነፃ ሕዝብ ሐውልት የማድረግ ጊዜው አሁንም አልመሸም -ኃይሉ አርአያ (ዶ/ር)
በፓርላማ ቀርቦ የተወሰነው ውሳኔ ለምን ተግባራዊ አልሆነም? -ክፍሌ ኃ/ማርያም
ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ዜና
ከዚያ ወደዚህ ስመለስ፤
ከአንድ ወር ቆይታ በሁዋላ ወደምኖርበት ከተማ ተመልሼ ከአውሮፕላን ዱብ ከማለቴ ነው ከአውሮፕላን ጣቢያ የተቀበለኝ ሰው “ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ ሞቱ እየተባለ ይወራል” ብሎ ያረዳኝ። ይሄ ወዳጄ ዜናውን ሲሰብርልኝ፤ ስሜቴ ሁሉ ተሰባበረ። የኛ አገር ፖለቲካ ሁኔታ የባሰውን ጨለመብኝ። ሰማይ ተደፋብኝ። Read more…
ዜና
Recent Comments