Abugida Ethiopian American Amharic Web Page

ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ 2ኛ ዓመት ቅጽ 2 ቁ 76
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

በላተኛው አባ-መላ ከያሬድ አይቼህ
የፓልቷኩ አባ-መላ ሰሞኑን ገኗል። መግነኑ አልከፋኝም … ይግነን … ለሁሉም ጊዜ አለውና። ግን አባ-መላን ብዙ ጊዜ አዳምጨዋለሁና የአባ-መላን ነገር መዳሰስ ፈለኩ። ሰሞኑን አባ-መላ ገዢውን ፓርቲ መተቸት ጀምሯል። ይህንን የሰሙ የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች በጣም ፈንጥዘዋል ፡ እኔ አልፈነጠዝኩም። ለምን?

አባ-መላ የሚናገረውን ነገር በየሳምንቱ ፡ አንዳንዴ አልፎ አልፎም ቢሆን ፡ አዳምጨዋለሁ። አባ-መላ የሚያረገውን የሚያረግው ለአንድ አበይት ምክንያት ብቻ ነው፦ የግል ጥቅም። አባ-መላ ሌላ ንዑስ ምክንያት የለውም። የሚያደርገው ፡ የሚናገረው ፡ የሚተነፍሰው ፡ የሚስቀው ፡ የሚያለቅሰው … ወዘተ … ለግል ጥቅሙ ነው (ለግል ጥቅሙ መቆሙ መጥፎ ነው ማለቴ አይደለም ፡ ያ ምርጫው ነው)።

በ2008 እ.አ.አ. አባ-መላ ክፍል ውስጥ አስተዳዳሪ የነበረ ሰው (“addis_ababa_1”? በሚል መጠሪያ ስም ሚሳተፍ) ክፍሉ ውስጥ በተነሳ ቅራኔ ምክንያት የክፍሉን ሚስጥር በተቃዋሚ ክፍሎች ውስጥ ገብቶ ሲናገር ሰምቻለው። ከተናገረው ሚስጥር አንዱ ፡ ቃል በቃል ባላስታውስም ፡ አባ-መላ ከሚድሯክ ወይም ከሼህ መሃመድ አልሙዲ በአመት $50,000 ዶላር እንደሚከፈለው ነው። ይሄ ነገር የአባ-መላን ባህሪ እና የፓለቲካ ፕሮፓጋንዳ ትኩሳት ለመረዳት ወሳኝ መረጃ ሆኖ አገኝቼዋለሁ።

አባ-መላ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ከሚድሯክ ጥቅም ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው ነው ብዬ አምናለሁ። የሚድሯክ ጥቅም ሲከበር ፡ አባ-መላ ለኢህአዴግ እስክስታ ይወርዳል። የድርጅቱ ጥቅም ስጋት ላይ የወደቀ ሲመስል ፡ አባ-መላ ደረቱን ይመታል።

አባ-መላ የኢህአዴግ ደጋፊ ሆኖ አያቅም። አባ-መላ የሚድሯክን ገጽታ የሚያሽሞነሙን ፡ የደርግ ስርዓት ያፈራው ፡ አንደበተ ምላጭ ፡ የሚያደርገውን የሚያቅ ፡ ፕሮፓጋንዲስት ነው።

ታዲያ ምነው ሰሞኑን የፓልቷክ ተቃዋሚ ክፍሎች ባዶ ሆነው የሲቪሊቲ ክፍል ሞልቶ የፈሰሰው? ተቃዋሚ ባካችሁን በአባ-መላ አትበሉ። አባ-መላ ሚያደረገው ሁሉ ለአገራዊ ጥቅም ብሎ ሳይሆን ለግል ጥቅሙና ለሚያገለግለው ድርጅት ጥቅም ብቻ ብሎ መሆኑን እንገንዘብ።

ሚድሯክ ለብዙ ኢትዮጵያውያን የስራ እድል የከፈተና ፡ አያሌ ካፒታል ያፈሰሰ ድርጅት በመሆኑ ድርጅታዊ ገጽታውንና ጥቅሙን መንከባከቡ ተገቢና የሚጠበቅ ነው። ሆኖም ግን የገዢው ፓርቲ ተቃዋሚዎች በሚድሯክ እና በኢህአዴግ መካከል ሆነን ልንፈጭ ነውና ፡ በአባ-መላ የፓለቲካ ስልት እንዳንበላ ጠንቀቅ እንበል።

አባ-መላንም ሆነ ሌሎች ገዢው ፓርቲን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚደግፉ ሰዎችን ተስገብግበን ወደ ተቃዋሚው ጎራ መጨመር የለብንም። በጊዜ ውስጥ ሊፈተኑ ፡ አመኔታችንን ቀስበቀስ ሊያገኙ ይገባል እንጂ ተንሰፍስፈን መርዝ ይሁን መድሃኒት እንደያዙ ሳናቅ አንቀበላቸው።

ወቅቱ የህወሃት/ኢህአዴግ መጨረሻ ወቅት ነውና የሚደናበሩትን የገዢውን ፓርቲ በላተኞች ለጥቅማችን እንጠቀምባቸው እንጂ እነሱ አይጠቀሙበን።

ጸሃፊውን ለማበረታታት ፡ ለመውቀስና ለማስፈራራት በዚህ ይጻፉ፦ yared_to_the_point@yahoo.com

የሰማይ ላይ ግንብ የመጽሃፍ ግምገማ ሰለሞን ሃይለ ማሪያም
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የኛ ነገር፡ የኔም ነገር፤ አንድ እንደመግቢያ፤ አሸዋና አለት በልጅ ተክሌ
1.እስኪ ደግሞ ትንሽ ልረብሽ። ጽሁፍ ተሸፋፍነው የተቀመጡ ሀሳቦችን ካልገለባበጠ፤ ያንቀላፉትንም ካልረበሸ አይመቸኝም።

2.አንዳንድ ጠንካራ ምሳሌያዊ አባባሎች በአንድ ሀይማኖት ውስጥ ቢነገሩም፤ መልእክታቸውን የሀይማኖት ድንበር አይወስነውም። ጠቀሜታቸውን ሳይንስና ስልጣኔም አይሽረውም። በአሸዋ ላይና በአለት ላይ ስለሚገነባ ቤት ጽናት ልዩነት ቅዱስ መጽሀፍ የተናገረውን መጥቀስ ይቻላል። ቃል በቃል አላስታውሰውም፤ ግን እምነታችን በጠንካራና በማይናወጽ አለት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን፤ በፈተናና በጥርጣሬ፤ እንዲሁም በጽናት እጥረት እንዳይበረዝ ሲያስጠነቀቅ፤ መጽሀፍ ቅዱስ “በአለት ላይ የታነጸ ቤት በአሸዋ ላይ እንደተገነባ ቤት ንፋስና ወጀብ አያናወጠውም” አይነት ነገር ይላል።

3.ከዚያ የኛ “ትግል” ትዝ አለኝ። የኛ “ትግል”፤ ትግል ካለን፤ በአሸዋ ላይ የታነጸውን ቤት መስሎ ይታየኛል። በአህያ ቆዳ የተሰራ አይነት ቤት፤ ጅብ በጮኸ ቁጥር የሚንቀጠቀጥ። ዛሬ ስለዚያ ነው የምጽፈው። ስለዚያም ብቻም አይደለም፤ እኛንና ጠላቶቻችንን ስለሚለያዩን ወይም አንድ ስለሚያደርጉን ነገሮች እጠቅሳለሁ።

4.ለምሳሌ፤ ጠላቶቻችን ርኩስ መሆናቸው፤ እኛም የነሱን ርኩሰት ነቅሰን ማውጣታችን፤ እኛን ደርሶ ጻድቅ አያደርገንም። አንዳንዶች እነደዚያ የሆንን ሊመስላቸው ይችላል። ለምሳሌ ግንቦት ሰባት ወይንም መድረክ፤ ኢዴፓ ወይንም ኢህአፓ የኢህአዴግን ጉድ አጋለጡ ማለት እነዚህን ድርጅቶች በርግጠኝነት ከኢህአዴግ የተለዩ ያደርጋቸው ይሆናል እንጂ ያለቅድመ ሁኔታ የተሻሉ አያደርጋቸውም። ኢሳትም ለኛ ግሩም ሆነ ማለት፤ በርግጠኝነት ከኢቲቪ ይለየዋል እንጂ፤ ያለአንዳች ቅድመሁኔታ ከኢቲቪ የተሻለ ያደርገዋል ማለት አይደለም። (ይሄ፤ ለምሳሌ ያህል ነው እንጂ፤ ኢሳትንና ኢቲቪን አላወዳድራቸውም፤ ስለዚህ አንዳንዶቻችን ይቺን ሀረግ መዘን ወደ መደምደሚያ እንዳንከንፍ ወይም በኢሳት ላይ የተነሳሁ አይነት አድርገን እንዳንተረጉመው)። በአጠቃላይ፤ ከጠላቶቻችን የተሻልን ክፉዎች ልንሆን እንችላለን፤ ነገር ግን ተራችንን የምንጠብቅ መጥፎዎችም ልንሆን እንችላለን ነው ሁለተኛው ነጥቤ። እንጂ፤ የኢህአዴግን ክፋት ስላጋለጥንና ስለተቃወምን ብቻ የተሻልን ነን ማለት አይደለም። ባለፈው ሰሞን እንደቀልድ በወረወርኩት ጽሁፍ የመጣው ጣጣ ያንን ያሳያል። እኛም ከጠላቶቻችን የተሻልን ላንሆን እንደምንችል ይጠቁማል።

እንደማስታወሻ፡ ካለፈው የቀጠለ

5.ለማስታወስ ያህል፤ ያለፈው ጽሁፌ ሁለት ሀሳቦች ብቻ ናቸው ያሉት። አንደኛ፤ በህዝብ ዘንድ እየተወደደ እየታወቀ ተደማጭነት እያገኘ የመጣው ኢሳት የሚያደርገው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ፤ በህዝብ ዘንድ አሉታዊም አዎንታዊም ውጤት ስለሚያመጣ፤ ጥንቃቄ ያድርግ የሚል ነው። ለምሳሌ፤ ከስድስት ከተሞች ውስጥ በአምስቱ ላይ የአንድ ሀይማኖት ብቻ ተወካዮችን መጋበዝ ብልህነት የጎደለው አካሄድ ነው የሚል ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ፤ ከኢሳት ጊዜያዊ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅትም ባሻገር፤ ሀይማኖታዊ ጉዳዮችን የምንመለከትበት ቋሚ መንገድ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል የሚል ነው። ከዚያ ባሻገር ግን የመንግስትና ሀይማኖትን መለያየት በተመለከተ የቅንጦት የሚመስል ነገር ግን አስፈላጊ የሆነ ውይይት ለመጫር ነው ጽሁፉ ሙከራ ያደረገው።

6.የተሰጡትን ምላሾች ሁሉ ለማንበብ ግዜ አላገኘሁም፤ የተወሰኑትን ግን አለፍ አለፍ ብዬ ተመልክቻቸዋለሁ። አብዛኞቹ ስድቦች ናቸው። ብዙዎቹ አስተያየቶች ደግሞ አስፈግገውኛል። ከጨዋዎቹ ተቺዎቼ ውስጥ አባዛኞቹ ያተኮሩት “ይሄንን አደባባይ ይዘህ ባትወጣ ይሻል ነበር” የሚል ሲሆን፤ በጣም ጥቂት ጨዋዎች ደግሞ “እንዴት ኢሳትን ትነካለህ? ትደፍራለህስ?” የሚሉ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ። እንደትልቅ ድፍረት፤ ራስን ከገደል ጫፍ እንደመወርወር፤ ራስን እንደማጥፋትም የቆጠሩትም አሉ። አንዳንዶች ደግሞ ግጭት የተፈጠረ፤ “የከዳሁ” ሁሉ የመሰላቸው አሉ።

7.ካለፈው የፖለቲካ ልምዳችን እንደምናውቀው፤ ሰው ካልተቀየመ ወይንም ካላኮረፈ ወይንም ካልከዳ ራሱንና የራሴ የሚለውን ስለማይተች፤ የበሰሉ፤ የተማሩ፤ በዚህ በምእራቡ ዓለም ለረጅም ግዜ ኖረው የሀሳብን በነጻነትና ያለፍርሀት መግለጽ ፋይዳ ተረድተዋል የተባሉት ሁሉ ያልጠበቅኩትን ተግሳጽ ሰንዝረዋል። በእውነቱ አንድን ጽሁፍ ብቻ መሰረት አድርገን፤ እዚህ ሁሉ ስጋትና ተግሳጽ ውስጥ መግባታችን የሚያሳየው፤ “ጸረ-ኢህአዴጉም ጎራ (የኛ ጎራ ማለት ነው)፤ መንግስት በሚማቅቅበት፤ “ከመንጋው የተለየ ሀሳብን የማስተናገድ ባህል እጦት እንደሚሰቃይ ነው።” ይሄ አደገኛ ነው። እነሆ ቃና ቀይሬ እንደ ንጉስ ላስረዳ ነው።

የትችት ትችት ትችት

8.ባለፈው ሰሞን ወዳጃችን ልጅ ተከሌ ማለፊያ ግሩም ጽሁፍ አንደጻፈ ሰማን። ጽሁፉም ተነበበልን። አሰላሰልነውም። አንዳንድ ሰዎች ለጽሁፉና ለጸሀፊው የሰጡት ምላሽ አላስደሰተንም። ቢሆንም አልገረመንም። ያንዳንዶቹ የተጻፈም ያልተጻፈም ምላሽ ግን አሳስቦናል። የልጅ ተክሌን ሀሳብ ከመተቸትና ከመበለት ይልቅ፤ ልጅ ተክሌን ወደመንቀፍና ወደማጠየፍ አዘንብለዋል። የጽሁፉን ፍሬ ነገር ሳይሆን የጸሀፊው ቁመትና ውፍረት ወርድና ክብደት ላይ የሚወያይ መብዛቱ አጅግ አሳስቦናል። ሀሳቡን ተችተው አስተያየት ለመስጠት የፈቀዱትም ቢሆኑ፤ ያተኮሩት፤ “የራስ ተቋም በአደባባይ አይተችም፤ ለጠላት ደስ ይለዋል፤ ንፋስም ይገባልና” የሚል አይነት ስሜት ይጎላበታል። አንዳንዶች ከቶም የጸሀፊውን ነገር የተገነዘቡ አይመስልም።

9.ቀድሞ ነገር፤ ልጅ ተክሌ የአገራችንንና የህዝባችንን ጥቅም የሚነካ ጽፉህ ይጽፋል፤ አገራችንን የሚጎዳ መንገድ ይሄዳል ብለን አንሰጋም። ይሄ እምነታችን ጥንትም ነበረ፤ አሁንም አለ። በርግጥ ልጅ ተክሌ ብዙም ባልተለመደ መልኩ አፈሙዙን፤ ወደወገን/ወደራሱ ማዞሩ ለብዙዎች ግርታን ቢፈጥር አይደንቀንም። ይሁን እንጂ፤ አንደኛ ልጅ ተክሌ ይሄን ሲያደርጉ የመጀመሪያው አይደለም። ሁለተኛ፤ የኛ የሆነውንና በኛ ምድር ላይ የተተከለውን ልጅ ተክሌ ከሀሳቡ አልፈን እሱን መጠራጠራችን በጎ ሆኖ አላገኘነውም። ስህተትም ነው። ይሄ ጽኑ የተለየ ሀሳብን የመፍራት ደዌም ነው። እስከመቼ የተለየ ሀሳብን እንሸሻለን? እስከመቼስ በራሳችን ድጋፍና ሰልፍ ጫጫታ ተውጠን እንኖራለን የሚል ጥያቄም ፈጥሮብናል? አንዳንዴ ወጣ ብሎ ማየት ያሻል።

የሀሳብ ነውር የለውም፡ የድርጊት እንጂ

10.የተለየ ሀሳብን መፍራት የለብንም። መጋፈጥ እንጂ። ሰው ነፍስ ካወቀ፤ የሀሳብ ነውር የለውም። የሀሳብ ጸያፍም የለውም። የሀሳብ ወንጀልም የለውም። ስለማይናገረው እንጂ ማንስ በጭንቅላቱ የሚያስበውን፤ በልቡም የሚመኘውን እንደምን እናውቀዋለን? ማንም ሰው፤ እንወያይበት፤ እናስበበት፤ እናድግበትም ዘንድ፤ ስህተትም ከሆነ እንዲታረምና እንዳይደገምም ብሎ ባደባባይ በስሙ በጻፈው ጽሁፍ ሲሆን ሲሆን ሊሸለም እንጂ ሊጎሸም አይገባውም። በርግጥ ልጅ ተክሌ ሲጎሸምና ሲዘለዘል የኖረ ወዳጃችን ስለሆነ፤ በአመታት ትችትና ነቀፋ የደነደነው ቆዳው በዚህ ይሰነጠቃል ብለን ከቶም አንሰጋም። የሰዎቻችን ከተለመደው የተለየ ሀሳብን ለማስተናገድ የመፍራትና የመቅፈፍ ነገር ግን ረብሾናል።

11.ደግሞስ በዚህ በምእራብ የነጻነት አጥቢያ የምንኖር ሰዎች ስለምን ትችትን እንፈራለን። ስንት ነገርስ እንፍራ? ስንት ነገርስ ያሸብረን? ኤደን ባህረሰላጤንና ሳህል በረሀን፤ አባይንና ጎጀብን ተሻግረን ተሰደን፤ በንጽጽርም ቢሆን የተሻለ ነጻነት ካለበት ዓለም መጥተንም፤ የተለየ ሀሳብን የመፍራት ሰቀቀን ይከተለን? እንግዲያውስ እላችሁዋለሁ፤ ነጻነታችንና ዴሞክራሲያችን በአለት ላይ እንጂ በአሸዋ ላይ መገንባት እንደሌለበት ህዝባችን ሊያውቀው ይገባዋል። “ይሄን ሀሳብ አንሸራሽር፤ ይሄንን ሀሳብ ግን ከቶም አታንሳው” የሚል ማእቀብና ምክር፤ በአገራችን እንዲሰፍን የምንመኘው ዴሞክራሲና ነጻነት ጸር ነው። ይሄ እስክንድር የታሰረለት፤ ርእዮትም የታጎረችበት፤ ሲሳይም የተሰደደበት ራእይ አይደለም። ደግሞስ፤ ይሄንን የሚፈቅደውስ ማነው? ህሊናችን አይደለምን? ከህሊናችን በላይ የተሻለ ከልካይስ፤ ፈቃጅስ ከወዴት ይገኛል?

12.ለዚህ ነው እኛ ሰው ህሊና ይስጥህ ሲባል እንጂ ልቡና ይስጥህ ሲባል የማይረዳኝ። ህሊና ያለው ሰው ደግሞ ህሊናው የፈቀደውን እንዲናገር፤ ህሊናውን የደረሰበትን ግኝት እንዲመሰክር ልናበረታታው ይገባል እንጂ፤ ልናከላክለው አይገባም። ካልሆነም ደግሞ የጸሀፊውን ሰብእናውን ሳይሆን ሀሳቡን ልንመትረው፤ እይታውን ልንተቸው፤ አመለካከቱን ልንተረክከው እንችላለን። እንጂ የጸሀፊውን ሰብእና ለማጥቃትና ጸሀፊውን ትልቅ ሀጢያት እንደፈጸመ በማነጣጠር የምንናገረውም የምንጽፈውም እኛ የታገልንለትንና ለህዝባችን ልናወርሰው የምንምለውንና የኛን ህልም የሚያንጸባርቅ አይደለም።

የማይጠየቅ ተቋም፤ የማይተች እውቅና

13.ወዳጃችን ልጅ ተክሌ ከዚህ ቀደምም ብዙዎቻችን የምንሸሻቸውን ሀሳቦች ለመናገር የሚጀግን፤ ብዞዎቻችን የምናፍራቸውን ሀሳቦች ለመጻፍ የሚተጋ የስደት ወዳጃችን ነው። ባለፈው ጽሁፍ ያነሳውም ሀሳብ፤ ምንም የሚጣል የለበትም ብለን ባንመሰክርም፤ በራሱ የሚተማመንንና በአለት ላይ የተገነባ ዴሞክራሲን ለመገንባት የሚተጋን ቡድን የሚያስደነግጥ ነገር አላገኘንበትም። ያለበለዚያማ በሚጻፈውና በሚወራው ጠላታችን መደንገጡ፤ የሚናገሩና የሚጽፉትንም ወደእስር ማጋዙ ስህተት አይደለም ማለት ነው። እኛ መንግስትነትን አጥተን በተለዩ ሀሳቦች መንሸራሸር ይሄን ያህል ከበረገግን፤ የመንግስትነትን ስልጣን የያዘው አካል በተቺ ሀሳቦች መንሸራሸር ቢጨነቅና መንገደኛውን ሁሉ ቢያስር ምን ያስደንቃል?

14.በርግጥ፤ ወዳጃችን ልጅ ተክሌ በሰዎች ዘንድ ታምኖ የተነገረውን ምስጢር ያባከነ፤ ወይንም እሱ ለድርጅቶች ባለው ቀረቤታ ያገኘውን መረጃ የተጠቀመ ባሪያችን ቢሆን እኛም ይከፋን ነበር። አንለቀውምም። ለጥፋቱ እንቀጣው ነበር። ይሁን እንጂ ልጅ ተክሌ የተጠቀመው መረጃ ሁሉ አደባባይ በህዝብ ዘንድ በግልጽ ያለ እንጂ፤ የተተቸው ተቋም ጋር በሚሰራበት ግዜ ያገኘው መረጃ አይደለም። ደግሞስ የማይተች እውቅና፤ የማይጠየቅ ተቋም ለመመስረት ነው እንዴ የምንታገለው? እንግዲያውስ ያለፉትን አስር አመታት ብቻ ብንገመግም፤ ትልቁ የጎዳንና እንዳናንሰራራ ቀስፎ የያዘን ጥፋት የምንክባቸውን ለመተቸት፤ የምንቆልላቸውን ለመጠየቅ አለመድፈራችን፤ “ዝም በሉ፡ ጠላት እንዳይሰማ፡ በቃ ይሁንላቸው ይደረግላቸው” የሚለው የተለማማጭነትና የሰቀቀን ባህርይ ነው።

አደባባይ ወይስ ወደጓዳ?

15.በልጅ ተክሌ ላይ ከተሰነዘሩት ትችቶች መካከል፤ “ትችቱ ለምን በአደባባይ ሆነ? ውስጥ ለውስጥ አይሻልም ነበር ወይ” የሚሉት ጥያቄ-ተኮር ትችቶች መልካም እንደሆኑ ይሰማናል። የኛም ሀሳብ ይኸው ነው። ይሁን እንጂ፤ ያ አንድ መንገድ ነው። ብቸኛው መንገድ አይደለም። ልጅ ተክሌም የተከተለውን መንገድ ለመከተሉ ጥሩ ምክንያት ይኖረዋል። ልጅ ተክሌ እንዲህ ያለውን ትችት ይዞ ወደአምባ ሲወጣ፤ ግራ ቀኙን አላየም፤ በቅጡም አላሰላም ለማለት አንደፍርም። መጠየቅ ያለብንን በአደባባይ ባለመጠየቃችን፤ መናገር ያለብን በአደባባይ በግዜ ባለመናገራችን ምክንያት እነሆ ቅንጅት እንደብጉንጅ ውስጥ ውስጡን አብጦ፤ በመጨረሻ አይፈርጡ አፈራረጥ ፈረጠ። ከቅንጅት ቁስል እስካሁንም አላገገምንም። እንደልደቱ አያሌው ያሉ እስካሁንም ያልተካናቸውን ትንታግ ፖለቲከኞች አጣን። (በዚህ ሀሳብ ብቻ የምንበሳጭ እንኖራለን፤ ይሁን እንጂ ልጅ ተክሌ “ልደቱ ናፈቀኝ” የሚል ጽሁፍ እየጻፈ እንደሆነ ጠቁሞናልና ከዚህ ለሰላውም ትችት እንዘጋጅ)።

16.በመሰረቱ በአደባባይ የሚነሱና ውስጥ ለውስጥ የሚነገሩ ሀሳቦች ውጤታቸው አንድ አይደለም። በአደባባይ የሚነገር ነገር ትኩረት ይሰጠዋል። ሰዎች ይወያዩበታል። ተወቃሾችና ተከሳሾች ካሉም ለወደፊቱ ያርሙታል። ተጠያቂ አካልም ወደፊት እጋለጣለሁ ሲል አግባብ ካልሆነ ስራ ይታቀባል። ውስጥ ለውስጥ የሚደረጉ አስተያየቶችና እርማቶች ከስራ ላይ ይልቅ ወደ ቆሻሻ ቅርጫት እንደሚዶሉ የልጅ ተክሌ ምስክርነት አያሻንም። እንጂ፤ የጋዜጠኞቹ ትጋትና ፍጋት እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በየአካባቢው የሚገኙ የኢሳት ደጋፊዎች አስተዳደራዊ ምሬትና ስሞታ ቢጻፍ፤ “ይሄ ድርጅት እስካሁንስ እንደምን ቆመ?” ያሰኛል። “ወደፊትስ ይቆማልን?” የሚለውም ጥያቄ የሰይጣን ጆሮ አይስማው በማለት ብቻ የሚጠፋ አይደለም። እንደ ኢሳት ያለ ህዝባዊና ተስፋ የተጣለበት ተቋም እንዲያድግ የአደባባይ ውይይት፤ የግንባር ትችት፤ የፊት ለፊት እርማት ያስፈልገዋል። የምንፈልገው ተቋም በአደይና በጸደይ (የሰዎች ስም ናቸው) ላይ የቆመ ሳይሆን በአለት ላይ የተተከለ መሆን ነው ያለበት። እስካሁንም ሰዎች መካብ እንጂ ድርጅቶች/ተቋማት መገንባት አልቻልንምና።

በአደባባይ የሚሰራ በአደባባይ ይጠየቃል

17.ደግሞስ ኢሳት በአደባባይ የሚሰራ የአደባባይ መገናኛ ብዙሀን እንጂ የህቡእ ጋዜጣ አይደለም። ሰለዚህ ኢሳት ለሚሰራው የአደባባይ ስራ በአደባባይ መጠየቅ አለበት። ለምሳሌ ባለፈው ሳምንት “የእንወያይ፡” ዝግጅታቸው ላይ ወዳጃችን ፋሲል የኔዓለምና አፈቀወርቅ አግደው ያንጸባረቁትን ሀሳብ በአደባባይ እንጂ በውስጥ ተቹ ማለት ስህተት ነው። ምክንያቱም እነሱ ስህተት ቢሆንም ባይሆንም ሀሳባቸውን በአደባባይ የማንጸባረቅ እድል ሲያገኙ፤ የነሱን ሀሳብ የሚቃወመው ሰው ግን በውስጣዊ አስተያየት ብቻ መወሰኑ፤ የነፋሲልን ሀሳብ የሰሙት ሰዎች፤ የተለየውን ሀሳብ እንዳያዳምጡ እድል መንፈግ ነው። ይሄ ኢሳት የቆመለት ኢሳት የቆመበትም መሰረት አይደለም።

18.የሰማያዊ ፓርቲ በመጪው የአፍሪካ አንድነት/ህብረት 50ኛ አመት ምስረታ በዓል ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ጠርቷል። ከአገራችን ያላግባብ የተነቀልን ተቃዋሚዎች ነን የምንል ሰዎችም ድርጅቶችም፤ እንዲህ ያለውን ሰልፍ፤ ጠሪዎቹ ለምንም ዓላማ ይጥሩት “በርቱ ግፉበት፤ ብቻ እንዲህ ብታደርጉት መልካም ነው፤ ይሄንንም ብታክሉበት ሸጋ ነው” ማለት ነው ያለብን። እንጂ ዓላማቸውን ሙሉ በሙሉ ማራከስ፤ አግባብ አይደለም። ልጅ ፋሲል ግን የሰዎቹ የሰልፍ ጥሪ ሀቀኛ መሆኑን እንደሚጠራጠርና እንዲያውም ትኩረት ለማግኘት ያደረጉት አይነት ጥሪ እንደሆነ ነው የተናገረው። ያ ብቻም አይደለም፤ ይሄ አይነቱ ሰልፍ ቢደረግም እንኳን፤ ስርአቱን በምእራባዊያን ዘንድ ሰልፍና ተቃውሞ ፈቃጅ ሊያስመስለወም ይችላል የሚል ፍራቻ አንጸባርቋል። በርግጥ ልጅ ፋሲል ሀሳቡን የሰጠው በግሉ እንደሆነ ቢናገርም፤ እሱ የኢሳት ዋና ማኔጂንግ ኤዲተር እንደመሆኑ መጠን አንድን ነገር ተናግሮ በግሌ ነው የተናገርኩት በማለት ብቻ ሊያመልጥ፤ ኢሳትንም ነጻ ሊያደርገው አይችልም።

19.በሀላፊነት ቦታ ላይ ያሉ ሰዎች ብዙውን ግዜ ይሄንን በግሌ ነው ያልኩት የድርጅቱ አቋም አይደለም የሚል ብልሀት ይጠቀማሉ። ልጅ ፋሲል በአስተያየቱ ላይ ከዚህ ቀደም ኢሳት የሰራቸውን ተመሳሳይ የሰልፍ ጥሪ ዘገባዎች እንደምሳሌ አቅርቧል። ከተቀመጠበት የሀላፊነት ወንበር አንጻርም የሚሰነዝረው እያንዳንዱ ሀሳብ የኢሳት ሊመስል፤ ሊሆንም እንደሚችል መረዳት አለበት። እንዲህ ያለውን በአደባባይ የተነገረ ሀሳብ መተቸት ያለብን፤ ኢሳት አንዳንዴ ፈንገጥ ያለ ሀሳብ አይመቸውም እንጂ ሲሆን ሲሆን በራሱ በኢሳት ላይ፤ ያለበለዚያ ግን በተገኘው መድረክ ነው። የለም እንቶኔን አትንኩ የሚለው አስተያየት፤ ለራሱ ለእንቶኔም አይበጅም።

ለነገሩ የኛ ችግር፡

20.ለነገሩ በስደት የምንገኝ ድርጅቶችና ተቃዋሚ ግለሰቦች፤ በአገር ቤት የኛን ስደትና ሚና የሚቀንስ፤ የኛን መኖር ምክንያት የሚያሳጣ እንቅስቃሴ የሚጀምር ሲመስለን፤ ያንን እንቅስቃሴ ለማጣጣልና ለማራከስ እንፈጥናለን። ይሄ እኛም በስደት ወደኬንያ ከገባንበት ጊዜ ጀምሮ፤ ላለፉት 12 አመታት በኢህአፓም በመኢሶንም፤ በቅርቡ ደግሞ በነግንቦት ሰባትም በነከበደም በነገመቹም ላይ ያስተዋልነው በሽታ ነው። ልክ የዛሬ አስራሁለት አመት ተሰደን ወደናይሮቢ ስንገባ የተቀበሉን ደግ ድርጅቶች ከነገሩንና እስካሁንም ከትውስታችን ካልወጣው ነጥብ አንዱና ዋንኛው “አገር ቤት ያሉ ድርጅቶች መኖር፤ በምእራባዊያን ዘንድ፤ አገር ቤት ዴሞክራሲ ያለ ያስመስላል” የሚል ነጥብ ነው። እነሆ ታሪክ ራሱን እንዳይደግምና፤ እኛ ከአመታት በፊት እንከሰሰስበት የነበርነውን፤ ማለትም የአገርቤቱ እንዲህ ነው የሚለውን ክስ፤ እኛም በተራችን እንዳንደግም መጠንቀቅ አለብን። ከፖለቲካ ወንጀሎች ሁሉ የከፋው ሌሎችን የከሰስንበትን ጥፋት ወይም በሌሎች በስህተት የተከሰስንበትን ጥፋት እኛ ስንፈጽም ነው።

21.ይቀጥላል።

እኛው ነን፤ ግንቦት ልደታ፤ 2005፤ ተረንቶ፤ ከናዳ

ኢትዮጵያዊነት እያበበ ነው ወይስ እየጠወለገ? የኢሮብ መብት ተማጓች ማኅበር
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የበረከትና አላሙዲ ልሳን (ከኢየሩሳሌም አርአያ)
በአላሙዲ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት፣ በረከት ስምኦን ከጀርባ የሚመሩት እና በአንድ ኤርትራዊ የሚዘጋጀው ጋዜጣ አለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማደናገር ሲሞክር መታየቱን ተከትሎ ምስጢሩን የሚያውቁ የቅርብ ምንጮች ጉዳዩን አጋለጡ። « ሰንደቅ» የተባለውና በነፃ ፕሬስ ስም የሚያደናግረው ጋዜጣ ፍሬው አበበ በተባለ ዋና አዘጋጅነት እንዲሁም በኤርትራዊው ፋኑኤል ክንፉ ምክትል ዋና አዘጋጅነት የሚሰናዳ ሳምንታዊ ጋዜጣ ሲሆን ቦሌ አትላስ ሆቴል አካባቢ በውድ ዋጋ ቢሮ ተከራይቶ እንደሚሰራ ያስታወቁት ምንጮቹ አያይዘውም ፍሬው አበበ ከዚህ ቀደም የብአዴን ልሳን በሆነው « ማህቶት» ጋዜጣ ላይ ይሰራ እንደነበረና ከብአዴን አመራር አባላትም ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳለው አረጋግጠዋል። በፓርቲው ልሳን ለመስራት ደግሞ የድርጅቱ አባል መሆን ግድ እንደሚል የጠቆሙት ምንጮቹ “ጋዜጠኛ” ፍሬው የፓርቲው አባል እንደሆነና በነበረው ታማኝነት በበረከት ስሞን ተመርጦ አሁን ባለበት ጋዜጣ እንዲሰማራ መደረጉን አስታውቀዋል። በተጨማሪ  «የኢትዮጲያ ነፃ ጋዜጠኞች ማህበር» ተብሎ በሚጠራውና የገዢው ፓርቲ ተለጣፊ በሆነው “ማህበር” ጋዜጠኛ ፍሬው የቦርድ አባል ሲሆን፣ ይህ ማህበር በሃገሪቱ ነፃ ፕሬስ እንዳይኖር ቀን ከሌሊት የሚተጋ ነው ሲሉ ምንጮቹ በመግለፅ ተከታዩን ማስረጃ ያቀርባሉ።

« ማህበር ተብዬው በሚሚ ስብሃቱ ሬዲዮ በኩል « እነእስክንድር ነጋ አሸባሪ ናቸው» ብሎ ተከራክሯል፤ «አዲስ ነገር፣ አውራምባ ታይምስ» ጋዜጦች ሲዘጉ «ከስረው ነው» በማለት የሽመልስ ከማልን መግለጫ የሚያጠናከር መግለጫ በማውጣት ከመንግስት ወግኖ ተሟግቷል፤ እንዲሁም በተመስገን ደሰላኝ ይዘጋጁ የነበሩት «ፍትህ፣አዲስ ታይምስና ልዕልና» ጋዜጦች በነበረከት ቀጭን ትእዛዝ እንዲዘጉ ሲደረግም የነፍሬው ማህበር ተመሳሳይ አቋም በማራመድ መከራከሩን በዋቢነት የጠቆሙት ምንጮቹ አክለውም፥ በአጠቃለይ ጋዜጠኛ ሲታሰር፣ ሲንገላታና ሲሰደድ ልክ መንግስት ተቀጥላ እየፈጠረ ለመወንጀል እንደሚሞክረው ሁሉ ይህም ማህበር ተመሳሳይ አካሄድ የሚከተል ፀረ-ፕሬስ ስብስብ ነው ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ የዚህ ተለጣፊ ማህበር ሊቀመንበር አንተነህ አብርሃም እንደሆነ የጠቆሙት ምንጮቹ የአንተነህ ታላቅ ወንድም አማኑኤል አብርሃ ሲባል የደኢህዴን/ኢህአዴግ ማ/ኮሚቴ አባል መሆኑን አጋልጠዋል።

በሌላም በኩል ምክትል የጋዜጣው አዘጋጅ ኤርትራዊው ፋኑኤል አንድ ሰሞን በኢቲቪ የህትመት ዳሰሳ ላይ ቀርቦ « የኢህአዴግ ደጋፊ ነኝ » ሲል በይፋ መናገሩን ያስታወሱት ምንጮቹ የስርአቱን ትክክለኛነት በመግለፅና በመከራከር የገዢው ፓርቲ «ቋሚ ጠበቃ» ሆኖ መታዩትን ጨምረው ገልፀዋል። (ከዚሁ ጋር በተያያዘ የፍትህ ጋዜጣ አምደኛ የነበረው አቤ ቶክቻው « የኢቲቪ አምደኛ» ሲል በወቅቱ ተሳልቆበታል)..

ምንጮቹ ከጋዜጣው ጋር በተያያዘ ሲቀጥሉ ይህን አሉ፤ የነፃ ፕሬስ ህልውና በአገሪቱ ጨርሶ እንዲጠፋ በተደረገበት ተጨባጭ እውነታ፣ የህትመት ዋጋ ጣራ በነካበት ሁኔታ ..«ሰንደቅ» የተባለው ጋዜጣ የሚያሳትመው ሁለት ሺህ ኮፒ ብቻ መሆኑ፣ ማስታወቂያ የሌለው መሆኑ፣ በተጨማሪ በሃገሪቱ ውድ በሚባለው ብርሃነ ሰላም ማ/ቤት መታተሙ እንዲሁም አዘጋጆቹ ከፍተኛ ደሞዝ የሚከፈላቸው የመሆኑ ምስጢር ሼህ አላሙዲ መሆናቸውን ያስገነዝባሉ። በዚህን ያክል ኮፒ ትርፍ ማሰብ ጨርሶ የማይታሰብ መሆኑን ያመለከቱት ምንጮቹ፣ አላሙዲ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርጉና ጋዜጣውም በየሳምንቱ ሼኹን ከፍ-ከፍ አድርገው የሚያሳዩና ድርጅቶቻቸውን የተመለከቱ ዜናዎች እያተሙ የማውጣታቸው ምስጢሩ ከገንዘብ ድጋፉ ጋር የተያያዘ ነው ብለዋል።

በዚሁ ጋዜጣ ላይ በረከት የሚፈልጉትና « ህዝብ ዘንድ መድረስ አለበት» የሚሏቸውን ምስጢራዊ ጉዳዮች  ለሁለቱ የጋዜጣው አዘጋጆች የስራ መመሪያ ጭምር ከመስጠት ባለፈ በረከትና ሽመልስ በተለያዩ የብእር ስሞች ፖለቲካዊ ነክ ፅሁፎች እንደሚያወጡ፣ የሚፈልጉትን መረጃ እንደሚያስተላልፉ፣ ምንጮቹ አጋልጠዋል። እንዲህ ሲሉም ያብራራሉ፥ « የእነአበበ በለውና እስክንድር ነጋ ንብረት እንዲወረስ የተለያዩ የብእር ስሞች (ሽመልስና በረከት) በመጠቀም በጋዜጣው ቅስቀሳ ሲካሄድ ከቀየ በኋላ በመጨረሻ በዋና ክስነት ከቀረበው ውጭ «የንብረት ክስ» በሚል ሌላ ክስ ተመስርቶ የንብረት ውርሱ ተግባራዊ እንዲሆን ተደረገ። መንግስት የሰጠውን ግዳጅ በመወጣት፣ ነፃ ፕሬስን ሽፋን አድርጎ የተሰማራው ሰንደቅ ጋዜጣ ከጀርባ ያነገበው «አላማ» እንዲሁም አካሄድ በህዝብ ዘንድ ጥርጣሬ በማስከተሉ የጋዜጣው የኮፒ መጠን ላለፉት አመታት ሊያድግ እንዳልቻ አስታውቀዋል። በተለይ የጋዜጣው ዋና <አላማ> ተቃዋሚዎችን በአለ በሌለ ጉልበቱ ጨፍልቆ በመምታት በይፋ እንደሚታወቅ አመላክተዋል።

ለዚህም ከሁለት ሳምንት በፊት የተፈጠረውን ሁኔታ በአስረጅነት ይጠቅሳሉ ምንጮቹ፤ አብዛኛው አገር ቤት ያሉ ምሁራን አድፍጠው ባሉበት ተጨባጭ ሁኔታ ገዢውን ፓርቲ በአደባባይ ከሚቃወሙና የተለያዩ የመሟገቻ ሃሳቦችን ከሚያቀርቡ በጣት የሚቆጠሩ ምሁራን አንዱ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ነው በማለት ይገልፃሉ። ጋዜጣው « ዶ/ር ዳኛቸው የመኢአድ ቀጣዩ ፕሬዝዳንት ለመሆን ከኢ/ር ሃይሉ ጋር መምከራቸውን» በማስቀደም አያያዞም « የብአዴን አባል ነበሩ» ሲል በተቃዋሚ ክፍሎችና በህብረተሰቡ ዘንድ ጥርጣሬን ለመጫር መሞከሩን የገለፁት ምንጮቹ በረከት ስሞኦን ያጠናቀሩት ዘገባ መሆኑን አጋልጠዋል። ይህ ዘገባ ጨርሶ ከእውነት የራቀ መሆኑን የሚገልፅ ማስተባበያ ዶ/ር ዳኛቸው በጋዜጣው እንዲወጣ ከማድረጋቸው ባሻገር በፌስቡክ ባሰፈሩት መልእክት « እኔ የብአዴን አባል ብሆን ኖሮ ወረቀት በታኝ ሆኜ የምቀር ይመስላችኋል?. አባል ሆኜ ድምፄ ሳይሰማ የእነ ህላዌና በረከት ስምኦን ወረቀት በታኝ ሆኜ ልቀር አልችልም!» ብለዋል።

ምንጮቹ በማጠቃለያ ያነሱት፥ ፍሬው አበበ «ተከሰሰ» ተብሎ የተራገበውን ሲሆን፣ ከስምንት ወር በፊት የተዘገበን እና አዜብ በግልፅ ከቤተ መንግስት እንደማይለቁ በተነገረለት፣ሚሚ ስብሃቱ ሳይቀር ጠ/ሚ/ር ሃ/ማሪያምን የሚያኮስሥና በአንፃሩ ለአዜብ የወገነ ዲስኩር ማሰማቷና እርሷ ምንም ሳትባል «ጋዜጠኛው ተከሰሰ » የተባለው በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ትኩረት ለመሳብ በነበረከት የተቀናበረ « ድራማ» ነው ሲሊ ያጣጥሉታል። ምክንያቱም ሁለት ነው፤ ቀዳሚው በኢትዮጲያ ነፃ ፕሬስ አለ የሚል ስእል በመስጠት እገረመንገዱን <ፍትህ አለ> በሚል እነእስክንድር ነጋ እንዲፈቱ የሚቀርበውን አለም አቀፍ ጥያቄ አቅጣጫ ለማስለወጥ ብሎም «በእነእስክንድር የተሰጠው ውሳኔ በነፃ የህፍትህ አካላት የተወሰነ ነው» ለማለት እንደሆነ ምንጮቹ ያስረዳሉ።

የመለስ ዜናዊ ሌጋሲ ስቶኮልም ስንድሮም በታሪኩ አባዳማ
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የመለስ መታሰቢያ ተቋም (Foundation) – ክፍል 3 ከ 3 ግርማ ሞገስ
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

አሸባሪው ማን ነው? ከተስፋዬ ዘነበ
ከሳምንታት በፊት በልእለሀያሏ አሜሪካ በቦስተን ከተማ የደረሰውን በአሸባሪዎች ጥቃት ህይወታቸውን ላጡና  ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው የሃገሪቱ ዜጎች በህዝብ ይሁንታ ስልጣን ላይ ያሉት ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ በሰላማዊ ህዝብ ላይ ለደረሰው አደጋ ሀዘናቸውን ለመግለፅና የወንጀሉን ፈፃሚዎች በቁጥጥር  ስር ለማዋል መመሪያ ሲሰጡ ሰዓታት  እንዳልወሰደባቸው ስንመለከት ወራት አልተቆጠረም፡፡በመሰረቱ ይህንን ዘግናኝ ጥቃት የፈፀሙት ፅንፈኛ አክራሪዎች ብዙም ሳይቆዩ በሃገሪቱ የፀጥታ ሃይሎች ታድነው በአጭር ጊዜ ውስጥ መያዛቸው ለሕዝቡ ታማኝ  የሆነ መንግስት ዜጎቹን ከጥቃት ለመታደግ ምን ያህል እረፍት እንደሌለው የሚያመላክት ነው፡፡

ከላይ እንደመነሻ ያነሳሁት ሃሳብ ለዛሬው ፅሁፌ እንደ መንደርደሪያ እንዲረዳኝ እንጂ እውነተኛው የዲሞክራሲያዊ ስርዓት አራማጆች ለዜጎቻችቸው የሚሰጡት ክብር የሚሳት ሆኖ አይደለው፡፡

ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን ከቃል በዘለለ በተግባር የማያውቁት የወያኔ ቡድን፣ ፍትህና እርህትህ፣ ነፃነት ላጣው ሕዝብ ለውጥ ለማምጣት አጥንታችንን ከሰከስን ደማችንን አፈሰስን የሚሉት የዛሬዎቹ አምባገነን መሪዎች፣ የብሄር ብሄረሰቦችን  መብት በኢትዮጲያ፣ ለማስፈን ደከመን ሰለቸን ሳንል ታተርን የሚሉን ጥቂት ዘረኛ ቡድኖች፣ ሃገሪቷንም  ሕዝቧንም በሁለት አሃዝ በልማት አሳደግን ብለው ቀን ከሌት የሚደሰኩሩልን ጥቂት የዘረኛ ቡድን ሞኖፖሊስቶች፣ ከወረቀት ያልዘለለ የመናገርና አሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት አጎናፀፍን የሚሉን የዛሬዎቹ ተሸባሪ ሽብርተኞች በጀሌዎቻቸው የንፁሃን ደም ማስፈሰስ  የሰነበቱበት የሃያ ሁለት አመት ተግባራቸው ቢሆንም በዚህ ሰሞን በባህር ዳር የተፈጸመውን ጅምላ ፍጅት በሙት መንፈስ አራማጁ በአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝም ሆነ እሱን በሚመሩት የህውሃት ቡድኖች ምንም አለመባሉ ይህ እኩይ  ሰርዓት ምን ያህል የሕዝብ ንቀት እንዳለበት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ እውነት ነው፡፡

ስለዚህ  ዘረኛ ስርዓት ብዙ ቢባልም በየጊዜው በህዝብ ላይ በሚያደርሳቸው ግድያዎችና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንዲሁም በሃገር ላይ የሚያደርሳቸውን መጠነ ሰፊ ችግሮች በተመለከተ ከሃገርና ከሕዝብ ወገኖች ተቃውሞ ሲደርስበት ወይንም ሰራሗቸው እያለ ከሚመፃደቅባቸው ልማት ተብዬዎችን አስመልክቶ ከሚሰግድላቸው ምህራባዊያን ሃገሮችም ሆነ ከአበዳሪ አለም አቀፍ ተቋማት ጋር የሚወዛገበው በቁጥር ጨዋታ መሆኑ ስርዓቱ ምን ያህል ግትርና ሞራለ ቢስ መሆኑን አመላካች ነው፡፡

የወያኔ ዘረኛ ቡድን  ከእድሜው መጀመሪያ ጀምሮ በዚች ሃገር ንፁሃን ዜጎች ላይ ለፈፀመው ፍጅት (ግድያዎች) አንድም ጊዜ በህግ የተጠየቀ አካል ካለመኖሩም ባሻገር የሟቾቹን ቁጥር በማሳነስ በዚህ አሸባሪ ስርዓት የተሰዉ ሰማህታት ቤተሰቦችንና ሕዝብን በመናቅ ሲሳለቁ መመልከት አዲስ ክስተት አይደለም፡፡ ሰሞኑን በባህር ዳር ከተማ የሆነውም ካለፈው ያልተማረው የወያኔ አምባገነን ቡድን የሆደበት የማደናገሪያ ተልካሻ ስልት መሆኑ ይህ ስርዓት በማን አለብኝነት የንፁሃንን ደም መጠጣቱ እንደቀጠለበት የሚያሳይ እውነት ነው፡፡

የጠለቀ ጥላቻ በዚች ታላቅ ሃገር ላይ ያለው ዘረኛው የህውሃት ቡድን ኢትዮጲያዊ መንፈስን ከሕዝብ ለመንጠቅ አንዱን ከአንዱ ለመለየት፣ በጎጥና በዘር እንዲሁም በእምነት ለመከፋፈል ሌት ከቀን ዘመኑን ሙሉ ለፍቷል፡፡ ሕዝብ አንድነትና ሕብረት እንዳይኖረው ውስጥ ውስጡን ሲያበጣብጥ፣ በዘር በተለከፉ ጀሌዎቹ አንዱን በአንዱ ላይ ለማስነሳት የሽብር ተግባር ሲከውኑ፣ በሌላ በኩል ደግሞ መጠሪያው የኢትዮጲያ ሕዝብ የሆነ ግን ደግሞ በሆድ አደር ካድሬዎች በሚመራው የሕዝብ ሃብት በሆነው ቴሌቪዥንና ሬድዮ ድርጅት  በኩል የፈጠራ ፕሮፓጋንዳ በመፈብረክ  የብሄር ብሄረሰቦች መብት መከበሩን ለማሳየት የሀሰት አታሞ ሲደልቅ ይታያል፡፡

በመሰረተ ሃሳብ ደረጃ ሸብር ማለት በማንም ይፈፀም በማን ሰላማዊውን ሕዝብ የሚያውክ፣ የተረጋጋ ህይወትን የሚረብሽ፣ የንፁሃንን ህይወት የሚቀጥፍ፣ ሕዝብን ያለፈቃዱ ከቀዬውና ከመንደሩ የሚያፈናቅል፣ የሰው ልጅ በተፈጥሮ የተቸረውን ነፃነት የሚቀማ፣ በሕዝብና በሃገር ላይ ጥፋትና ውድመትን የሚያስከትል . . . . .ወዘተ ከላይ በመጠኑ የተዘረዝሩት ሁሉ የዚህ ዘረኛ ቡድን መገለጫዎች መሆናቸው እንኳን ከሕዝብ ወገን ለተሰለፉ ነፃነት ናፋቂዎች ቀረቶ ስብእናቸውን ሸጠው ለሆዳቸው ላደሩት ለስርዓቱ ጀሌዎችም ቢሆን የሚጠፋቸው አይደለም፡፡  የሚገርመው ግን  ይህው እኩይ ስርዓት በሕዝብና በሃገር ላይ የሚፈፅመውን በደልና ግፍ እንዲሁም ዜጎች የሚደርስባቸውን የመልካም አስተዳደር ችግርና የሰብአዊ መብት ጥሰትን በብእራቸው ነቅሰው የሚዘግቡትን ለሞያቸው ስነምግባር እንዲሁም ለሕዝብና ለሃገር ቅድሚያ የሚሰጡትን ጋዜጠኞች፣ በህግ አግባብ የመደራጀት መብታቸውን ተጠቅመው አማራጭ አሳብ በማስቀመጥ በሰላማዊ መንገድ የታገሉ የህዝብ ልጆችን፣ በተጨማሪም በሃገሪቱ ህገ-መንግስት በተደነገገው መሰረት የእምነት ነፃነታቸውን በዚህ ከፋፋይ ስርዓት ለመነጠቅ ፈቃደኛ ያልሆኑ፣ መብታቸውን ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እየሞቱና እየተገረፉ ትግላቸውን ከአንድ አመት በላይ ያራመዱ የሙስሊሙ ማህበረሰብ የመፍትሄ አፈላላጊ መሪዎች፣ እነዚህ ከላይ ልዘረዝር የሞከርኳቸው ፍፁም ሰላማዊ የህብረተሰብ ክፍሎች በአሸባሪውና ተሸባሪው ዘረኛ ቡድን በተቆጣጠረው ነፃነት አልባው የፍትህ ስርዓት በአሸባሪነት ተፈርጀው በየማጎሪያው ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን በሃገሪቱ የተለያዩ ክልሎች የንፁሃንን ህይወት በጠራራ ፀሃይ የሚነጥቀውና የሕዝብን ሰላማዊ ኑሮ ላለፉት ሃያ ሁለት አመታት የሚያውከው የህውሃት ዘረኛ ብድን በምግባር አሸባሪነቱ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡

መቼም ህውሃት ውጥረት በነገሰበትና በደል ፅዋው ሞልቶ ተቃውሞ ሲበረታበት የሕዝቡን አመለካከት ለማስቀየር በስልጣን ዘመኑ ብዙ ተልካሻ ምክኒያቶችን ሲሰራ እንደ ነበረ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ በተለይ በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጲያ አንድነት ለማፍረስና ለመበተን የስርዓቱ ሴረኝነት የበልጥ አግጥጦና አፍጦ የታየበት  ጊዜ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ በተለይ በአማራው ብሄር ተወላጆች ላይ የከፈተው ጥቃት ኢትዮጲያን እንደ ሃገር ያላት ታላላቅ እሴቶች ለማጥፋት የታለመ መሆኑ ማስረጃ አይቻውም፡፡ ይህንን ተከትሌ የተነሳውን በአለም አቀፍ  ደረጃ  በነፃ ሃገር ላይ የመናገርና ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብታቸውን ተጠቅመው በሃገራችውና በወገናቸው ላይ የሚደርሰውን በደልና ግፍ የስቆጣቸው ኢትዮጲያዊያን ያሳዩት ተቃውሞና ሆነ ውግዘት አንገቱን ያስደፋው ዘረኛ ቡድን ሰሞኑን ደግሞ የሕዝብን መነሳሳት አቅጣጫ ለማስቀየር የመጣበት መንገድ ግርምትን የሚፈጥር ነው፡፡ በመሰረቱ የአሳ ግማቱ ከወደ አናቱ የሚለውን የአበው ብሂል ያስታውሰናል፡፡ እንደሚታወቀው የስርዓቱ ቁንጮዎች ከራስ ፀጉር እስከ እግር ጥፍር የሰጠሙበት ሙስና፣ ከድሃው ሕዝብ ጉሮሮ ነጥቀው የበለፀጉበት ሙስና፣ ገዢዎቻችን በስልጣን ዘመናቸው በደሃው ሕዝባችን ስም ለምነው ካገኙት ገንዘብ 11ቢሊዮን ዶላር በላይ ነጥቀው ያሸሹበት ሙስና፣ እነኚሁ ዘረኛ ገዢዎቻችን በኢፈርት(EFFORT-Endowment Fund For the Rehabilitation of Tigray)ስም የሃገሪቱን የንግድ እንቅስቃሴ እንደ ሸረሪት ድር ተብትበው የንግድና እንደስትሪውን ካፒታል ሳይጨምር ከ50ቢሊዮን ብር በላይ ቋሚ ሃብት ባለቤት የሆኑበት በጥቂት የህውሃት ሰዎች የሚሸከረከር ሙስና፣ ይህንንና እጅግ ብዙ የሙስና ንቅዘቶች ያለበት ስርዓት የተወሰኑ ጭፍሮቺን የውም በብሄር ለክቶ አስሮ ሙስናን አጠፋለሁ እያለ የዛን መከረኛ ሕዝብ ጆሮ ያደነቁራል፡፡

የአፍሪካን አንድነት ስንመሰርት ነፃ የነበርን ዜጎች ከአምሳ አመት በሗላ የሗሊት ተጉዘን በዘረኞች መዳፍ ስር ወድቆ መገኘት በዜግነት ክብራችን ላይ አሉታዊ ተፅኖ ያሳድራል ስለሆነም በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ የሃገርና የሕዝብ ጥቃት የሚሰማን እስከ ወኔያችን እስከ ቤሄራዊ ስሜታችን ያለን እራሳችንን ሃገራችንን ከግዞት ነፃ ማውጣት ይጠበቅብናል፡፡

በተጨማሪም ግንቦት 17 ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በመገኘት የሕዝብ ይሁንታ በሌለው ዘረኛ ቡድን የሚደርስብንን አፈናና የሰብአዊ መብት ጥሰት ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ እናጋልጥ፡፡ ከአመት በላይ ድምፃችን ይሰማ እያልን በሰላማዊ መንገድ ስንታገል በአሸባሪነት ተፈርጀን መብታችንን የተነጠቅን የሙስሊሙ ማህበረሰብ ይህንን ሰልፍ በመቀላቀል ለለውጥ በአንድነት መቆማችንን እናረጋግጥ፡፡

ድል  ለኢትዮጲያ  ሕዝብ!!!!

ሞት  ለወያኔ!!

Ethiocenter.blogspot.com

አጀንዳ! ፍ.አ
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ