የጠቅላይ ሚኒስትሩ የልማት ሠራዊት የሀገሪቱን አንጡራ ሀብት ሲያባክን ታረቀኝ ሙጬ
May 8th, 2012
በትግራይ ክልል የልማት ሠራዊት እንዲሆኑ ተብለው የተመደቡ አካላት የወረዳና የቀበሌ አስተዳዳሪዎች በሕወሓት ካድሬ መሪነት ነው እሚንቀሳቀሱት፡፡ የታዘዙትን የሚፈጽሙ ናቸው፡፡ እነዚህ አካላት የተሰማሩበት የሥራ ዓላማ በገጠር በተመረጡ ቦታዎች በመስኖ የሚለማ ግብርና ማፋጠን የሚል ነው፡፡ ለዚህ ተብሎ የታቀደው የልማት አቅጣጫ ደግሞ በተመረጡ የገጠር መንደሮች እያንዳንዱን ገበሬ በእርሻ ማሣው የውሃ ጉድጓድ መቆፈር እንዳለበት ነው፡፡ በተጨማሪ ከደደቢት የብድር ተቋም የውሃ ሞተር በብድር መልክ በመውሰድ ከጉድጓድ ውሃ እየመጠጠ ወደ እርሻ ማሳ እንዲጠያሰራጭ ታስቦ ነው፡፡ ለዚህ ጉዳይ የተመደበው ባጀት እንደሚከተለው ነው፡፡ ይቀጥሉ…
እነሆ እጅግ የሚመር ሀገራዊ እውነታ በይነጋል በላቸው
May 6th, 2012
አንድ በወያኔው መንግሥት መሥሪያ ቤት የሚሠራ ባልንጀራ አለኝ፡፡ ባለፈው ሰሞን ድንገት ተገናኘንና ሻይ ቢጤ ይዘን ስለዚችው መከረኛ ሀገር ስንጫወት ብዙ ነገር ገረብን፡፡ ዛሬ ጊዜ መገረብ ካልሆነ አዲስ ነገር መቼም አልተገኘም፡፡ በሀገርና በብዙኃኑ ዜጎች የሚወርደው የሥቃይና የመከራ ዶፍ እንደሆነ በዓይነቱና በይዘቱ እየሰፋ ከመሄድ በስተቀር ሲቀንስ አልታየም፤ እናም እሱም አዲስ ሳይሆን ያው የለመድነው ነውና እንደለመድነው ለ‹ሪከርድ› ያህል አሁንም ጥቂት እንገርብ፡፡ ይቀጥሉ…

Recent Comments