ሁላችንም አማሮች ካልሆን ኢትዮጵያ አትድንም በይነጋል በላቸው
እንደዚህ ዓይነት ርዕስ እንኳን አንባቢን ጸሐፊንም ያስደነግጣል፡፡ በተለይ በዚህ ሁሉም ነገር በተወነዠባበረበት የኢትዮጵያ ምድር ‹አማራ ሁን› ብሎ መስበክ ምን ያህል ቂልነት እንደሆነ ማንም አያጣውም፡፡ ‹ላንተም አልበጄ ልጄ› ነበር ያሉት? እኚያ በልጃቸው መቃብር ዘንድ ጧት ጧት እየተገኙ ‹ጥራኝ ልጄ፤ ጥራኝ ልጄ› በማለት ዘወትር ያለቅሱ የነበሩ ሴት – አንዱ የልጃቸው ጓደኛ በመቃብሩ ሥር ተደብቆ ስማቸውን ከተጣራ በኋላ ‹ነይ እማዬ› ባላቸው ወቅት? አዎ! ለነሱም – ለአማሮቹም ባልበጀ ዘመን ‹አማራ ሁኑ› ይቀጥሉ…
“ሰብዓዊነትም” ጀግንነት ይጠይቃል! “ምንም ይዛችሁ ስላልመጣችሁ ምንም ይዛችሁ አትሄዱም” (አኢጋን)
ከደቡብ የኢትዮጵያ ክፍል ቤንች ማጂ ዞን ከተለያዩ ወረዳዎች በክልሉ አመራሮች ትዕዛዝ እንዲፈናቀሉ በተወሰነባቸው 78ሺህ በሚጠጉ የአማራ ተወላጆችና ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ለዓመታት ከኖሩበት ቀዬ በኃይል እንዲወጡ ተደርገው መግቢያ በማጣት እየተንገላቱ በሚገኙት ወገኖች ላይ እየደረሰ የሚገኘውን ግፍ፣ መከራ፣ ስቃይና እንግልት ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) አጥብቆ ይቃወማል፤ ድርጊቱንም ያወግዛል፡፡ የአቶ መለስ አገዛዝ፣ ‹‹ለፍትህ ቆመናል›› የሚሉት ፍርድቤቶችና የደቡብ ክልል አመራሮች ይህንን ሰብዓዊ መብትን የሚጋፋና ዓለምአቀፍ ሕግጋትን የሚጻረር ተግባር ለማስቆም ባለመቻላቸውና ባለመፈለጋቸው አንድም ኢትዮጵያን ለማስተዳደር ፈጽሞ ብቃት ስለሌላቸው ከአመራር መወገድ ያለባቸው መሆኑን ያስመሰከሩበት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ለዚህና ከዚህ በፊት ለፈጸሟቸው ወንጀሎች ለፍርድ የማቅረቢያው ጊዜ ከምንግዜውም በላይ አሁን መሆኑን ያረጋገጡበትም ነው፡፡ ይቀጥሉ…

Recent Comments