ለተከበራችሁት ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን፣

Poem

ለተከበራችሁት ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን፣

Postby dankira on Thu Jul 24, 2008 10:44 am

አሁን በሀገራችን የሚደረገውን የነፃነትና የዲሞክራሲ ትግል በአለን አቅምና ችሎታ ለማገዝ እና የታላቁ የሥነ ጥበብ አባት የሆኑት የብላቴን ጌታ ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድኅን ስም ከመቃብር በላይ አብቦ ይኖር ዘንድ

" ትውልዳዊ ድርሻችንን እንወጣ ! ! ! "

በሚል መሪ መፈክር መራሂነት የ ፀ ጋ ዬ ድህረ ገፅ http://www.tsegaye.ethio.info ፕሮጀክት አጠናቀን ሰሞኑን በይፋ ተግባሩን ለመጀመር ተሰናድተናል።

በእውነቱ የአእምሮም ሆነ የኑሮ አቅማችን ብቁ ሆኖ አይደለም። ነገር ግን የፀጋችንን መክሊት ዘላለማዊነት እንደ አቅማችን ለማለምለም በቅንነት በማሰብ ነው።

ስለሆነም አስፈላጊውን የእርምት ሆነ ማሻሻያ እንዲሁም ገንቢ አስተያየታችሁን እንድትለግሱን በታላቅ አክብሮትና ትህትና እየጠየቅን፣ ለድህረ ገፁ ዕድገትና የተሟላ አግልግሎት የበኩላችሁንም አስተዋፅኦ እና ተሳትፎ የምታደርጉበት መድረክ እንዲሆንላችሁ ፍፁም በሆነ ኢትየጵያዊ ስሜትና ደስታ እንጋብዛችኋለን።

ከ ም ስ ጋ ና ጋ ር ! ! !

ሀገራችን ኢትዮጵያ ሁሉንም ልጆቿን በእኩልነት ፣ በነፃነትና በዲሞክራሲ አቅፋና ተንከባክባ ለምትኖርበት የሰላምና የፍቅር ዘመን ያበቃን ዘንድ የቅዱስ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ይሁንልን!!!



ሐምሌ 17 ቀን 2000 ዓ.ም.



ፀ ጋ ዬ ድህረ ገፅ ዝግጅት ክፍል
User avatar
dankira
 
Posts: 51
Joined: Mon Apr 28, 2008 9:53 pm

Return to Poem

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest

cron