Forever – Berhane Mewa December 8, 2003

October 17th, 2009 Print Print Email Email

He who gave us Love –

——–Who teaches us Love

Love to Humanity
Love to a Country
Love to the People

—to us and to our children
He shall not die

Deep in our heart
Deep in our life
—-in our Love
—-in our literature
Lives with us

——and after us
Defeating death ——-Forever

Dedicated to the Immortal Addis Alemayehu

ሊሞት ለማይችል ስው

ሊሞት የማይችል ስው
ሞቶሽል እያላችሁ
ውሸት አውርታችሁ
ውሸት ተናግራችሁ
እነ ጉዱ ካሳን
ታሸብራላችሁ
ፍቅርን ለመቅበር — ትጣደፋላችሁ

============================================

በቁም የሞተ ሰው
——-ሞቶ የሞተ ሰው
————–ሞቶ የማይሞት ሰው
መለየት ሲከብደን
———–ለጥቂት ዞር ቢል —–
—————–አዲሰ አለምን ሊያይ
እንደማንም ፍጡር
ሞተ እንለዋለን
ላልሞተው አዲስ አለማየሁ
ህዳር 28- 1996

ብርሃነ መዋ

 1. ታዛቢ
  | #1

  አቶ ብርሃነ ስለማለፊያ ግጥምዎ አመሰግናለሁ::ነገር ግን አቶ ሃዲስን በ1996 ግጥምዎ አሁን ለማዘከር በምን ምክንያት ተነሳሱ?ለመሆኑ የኒህ ስመጥሩ ጸሐፊ ድርሰትም ይሁን ሌሎች አይነት ጽሁፎች ሁሉ ተጠቃለው እንደታተሙላቸው የሚአውቁት ነገር አለ?
  እንዲያው ለወጉ የህይወት ታሪካቸውስ ተጽፎ ይሆን? ከቶ እንዲያ ያለ አስተዋይ አእምሮ:ከቶ እንዲያ ያለ ብርእ :ከቶ እንዲያ ያለ የፍትህ ፍቅር:ከቶ እንዲያ ያለ የመንፈስ ንጽሕና :ከቶ እንዲያ ያለ ያገር አገልግሎት…እኒህን ሁሉ ባንድ ላይ እንዴት ሆነውት ኖሩ?
  በእውነት የሚደንቅ ህይወት ነበራቸው አቶ ሃዲስ…እርስዎ እንዳሉትም ስማቸው ክመቃብር በላይ ውሎአል::

 2. መርሶ
  | #2

  ሰላም !!
  የ አቶ ሃዲስ አለማየሁን ስራ ካንድ የግራ አይዲኦሎዢ ብቻ የምንመለከትበት ጊዜ ያለፈ ይመስለኛል:የኢትዮጵያ ግራ በፊትአውራሪ
  መሸሻ ህብረተስብ ላይ የነበርው የሞራል የበላይነት አክትሟል:አሁን በነጻ መንፈስ በስከነ አስተያየት ብንመለከትው የሚበጅ ይመስለኛል.አቶ ሃዲስ አለማየሁ በስራቸው ዉስጥ ሊያሳዩን የሞከሩት የኛን ህብረተስብ ዘርፈ ብዙ ባህርይ ነው:የኛ ህብረተሰብ
  ባንድ ጎኑ ፊታውራሪ መሸሻ ነው :: በሌላ ጎኑ ደሞ ሰብለ ዎንጌል እና ጉዱ ካሳ ነው.(ስብለ ዎንጌል የማን ልጅ እንድሆነች አንርሳ
  ክፉ ዛፍ ቅዱስ ፍሬ ያፈራል ) .ጉዱካሳ እና ስብለ ዎንጌል ደም የኛ ህብረተስብ የስነምግባር ንጽህና ወይም የህሊና ዎቀሳ
  በሌላ አነጋገር የኛ ህብረተስ ደግ ወገኑ ናቸው ማለት ይቻላል::በተገላቢጦሽ ደሞ ፊታውራሪ መሸሻ እንዲሁ ሌላው ያልታዎቀ
  የኛው dark?? ሃይል ነው:ግን ደግ ነገር ሊዎልድ ይቺላ እንደ ስብለ ዎንጌል ::ግጥሙ ጥሩ ነው!!

 3. ታዛቢ
  | #3

  አቶ መርሶ ለርስዎም ስላምታዬ ይድረስዎ::’..የ አቶ ሃዲስ አለማየሁን ስራ ካንድ የግራ አይዲኦሎዢ ብቻ የምንመለከትበት ጊዜ ያለፈ ይመስለኛል:…’ብለው ያመሰጠሩት ቃል እምብዛም አልገባኝም::ይሕ እንዴት ነው የሆነው? በማን ነው የሆነው?? ጨምረውም’..የኢትዮጵያ ግራ በፊትአውራሪ መሸሻ ህብረተስብ ላይ የነበርው የሞራል የበላይነት አክትሟል..’ያሉትስ እንደምን ያለ ፍች ነው ያለው? እባክዎ ፍንትው አድርገው ያብራሩልኝ::እኔ የሃሳብ ምስጢረኛ ዉበት እንደሽግዬ ኮረዳ ከሚያማልላቸው መሃል ነኝ:: ወደ አቶ ሃዲስ ዝክርም ለመመለስ ‘ንዲያው መስፈሪያ ከሌለው ከብዙው ነገር አንዲት ሰበዝ መዝዤ አቶ ሃዲስ በህይወት ቢኖሩና እንዳወጋችው እድል ባገኝ ኖሮ በረዥሙ እንዲያጫውቱኝ የምሻው ስለ ልኡል ራስ እምሩ ነበር::አንድ ግዙፍ መንፈስ ስሌላው ግዙፍ መንፈስ ሲናገር የሚያመጣውን ሰማያዊ ሙዚቃ መስማት ትንሽይቱን መንፈሴን ብዙ ያስደስታታል::

 4. መርሶ
  | #4

  የአቶ ሃዲስ አለማየሁ ማህበረሰባዊ ራእያቸው social utopi የነበርዉን ባህላዊ አስተዳደር ጨቋኝ ዎገንኑን
  እንዲስተካከል : ፍርደ ግምድሉ ርቱ ፍርድ እዲይገኝ ህብረተስቡ በአዲስ አልሚ ሃስብ ተሃድሶ እንዲይገኝ
  ታቹም ላዩም በተዋህዶ Harmonie እንዲኖር ነበር እንጂ :የነበርው አተዳድር በመደብ ትግል ጨርሶ
  እንዲደመሰስ አልነበረም ምኞታቸው:እንድያውም ይህ ሃሳብ ያስደነግጣቸው ነበር: ለዚህም የቁሰእቃ ማስረጃ
  ´´የልም እዣት`ነው :: የነበረው ባህላዊ አስተድደር ወደ አንድ ክፍ ከፍ ያለ ፍርደ ርቱ modern
  ህብረተስብ ለመሽጋገር transform ላማድረግ ከበቂ በላይ በዉስጡ ደማሚታዊ ኃይል ነበረው ብለው
  ያምኑ ነበር :: ግን ድንገት አንድ አርድ አንቀጥቅ መሰርት አፍራሽ የግራ radical revolution
  መጥቶ አጨናገፈው :ህብረተስቡ ክዚህ የታሪክ ስብራት አሁን አላገኘም::ዎደፊት አንድ ቀን ያገግም አያገግም
  እርግጠኛ ሆኖ ለመናገር ጊዜው ገና ማለዳ ነው: ምልክቶቺም አይታዩም:አቶ ሃዲስ አለማየሁ በኢትዮጵያ
  ባህላዊ አስተዳደር ላይ የነበራችው አስተያየት ምኞት ትክክል ነበር:መስረትም ነበርው:: ለዚህም ማስረጃ
  ከኢትዮጵያ ጋር ተመሳሳይ ህብረተስብ የነበራቸው የሩቅ ምስራቅ አገሮች በተለይ ጃፓንን መጥቀስ ይቻላል
  ወደ ሞደርን ህብረተስብ ትራንስፎርም ሆነዋል: ጃፓን የሰው ትዝታ ከሚይሳታውሰው ታሪክ ጀምሮ
  በንጉስ የሚተዳደር አገር ነው በነጭ ስንደቅ አላማው ላይ ጠዋት የሚዎጣው ጸሃይ ንጉሱን ነው የሚዎክለው
  በሱ ስር የሚተዳደሩት ሾጉንኦች ሳሙራዮች ሌላ አልነበሩም እነ ፊታውራሪ መሸሻዎች ጆቴዎርቆች
  ራስ አሉላዎች ስባገድሶች የከፍቾ ነገስታቶች አሊሚራሆች የጦና ስረ መንግስት ጂማ አባጂፋሮችቸነ
  እነዚህ ነበሩ የሺ አመት ኦሊጋርሆች እነዚህ ናቸው የተደመሰሱት እነሱ ሲደመሰሱ አብሮ አንድ አስደናቂ
  አለም ጠፋ ሌላ ትልቅ የኩረጃ ዘመን ሰተት ብሎ ገባ: በነሱ ዘመን ርሃብ ነበር ግን ያለ አንዳች
  የምግብ እርዳታ ነው ይህን ሁሉ ሺ አመት የኖሩት : ዛሬስ እምን ላይ ነን ከለት ዎደለት
  ጥገኝነቱ እየባሰ ሄዶ ውደ ፍጹም ጥገኛነት እየደርስን ነው: የዛሬ 60 እና 50 አመት ኢትዮጵያ
  አለም ሁለተኛ ጃፓን ትሆናልች ብሎ ይጠብቅ ነበር ዛሬ ምን ትሆናልች ብሎ ነው አለም የሚጠብቀው

  እስከ ዛሬ ድረስ ጀምሮ በንጉስ ስር የሚተዳደር አገር ነው: በነጭ ስንደቅ አላማው ላይ ያለው ማለዳ የሚዎጣ
  ጸሃይ ንጉሱን ነው የሚዎክለው:ከሱ ስር ያሉ ሾጉኖች ሳሙራዮች ኬጋሙሻዎች ሌላ አልነበሩም እነ
  ፊታውራሪ መሸሻዎች ጆቴ ዎርቆች በገዳ ስር አት ዉስጥ የነበሩት ልዩ ልዩ ባለ አባቶች ራስ አሉላዎች
  ስባገድሶች የከፍቾ ንጉሶች የአዳል

  የሚዎጣ ጸሃይ የሚዎክለው ጽ
  እስክ ዛሬ ድረስ

  እነዚህ ህብረተስቦች ወደ
  እነዚህ ህብረ ተስቦች

  እነዚህ ሃገሮች

Comments are closed.