Weekly message of Minilik Salsawi – Voice of Ethiopian Youth

December 8th, 2014 Print Print Email Email

Weekly message of Minilik Salsawi – Voice of Ethiopian Youth

YouTube Preview Image

 1. Taye
  | #1

  Ato Salasawi,
  woyane and shabia were having such low level propaganda in 1970 and it was good at the time but you are doing same low level propaganda in 2014.Please upgrade your style.Even Ethiopia molsim laughed in your childish propaganda.

 2. ቢኒያም ከበደ ንጋቱ
  | #2

  የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኃላፊዎችና ፕሬዚዳንቶች ሆይ! ለገዛ ራሳችሁ ክብር፣ ለአካዳሚ ነፃነት፣ ለትውልድ ስትሉ በዚህ መመሪያ ላይ አምጹ! “እንቢ፣ አሻፈረን፣ አንገዛም” በሉ! http://www.ideascale.com ከጎናችሁ ይቆማል።
  ከተገነቡ ተቋማት ምን ዓይነት ትምህርት ይገኛል?
  አንዲት አገር ካለባት ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ወጥታ በስልጣኔ ጎዳና እንድትጓዝ፣ ከሌሎች አገራት ጋር ተወዳድራ እንድታሸንፍ ትምህርት ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡ ያለ መምህር ትምህርት ለውድድርና ለእድገት የሚያስችል አይሆንም፡፡ የዘመናዊ ትምህርት ከመጀመሩ አስቀድሞ ሀይማኖት ለሚያስተምሩት መምህራን ከፍተኛ ክብር ይሰጥ እንደነበር ታሪክ ያስረዳል፡፡ የዘመናዊ ትምህርት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶም ለመምህራን ከፍተኛ ክብር ይሰጥ እንደነበር በቂ ማስረጃዎች አሉ፡፡ በዚህም ምክንያት አገራችን በርካታ ምሁራንን ማፍራት ችላለች፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ ውስጥ በተደረጉት የለውጥ እንቅስቃሴዎች መምህራንና የቀረጹዋቸው ተማሪዎች ቀዳሚውን ሚና ሲወጡ ታይተዋል፡፡
  በአንጻሩ በዚህ ትምህርት ቁልፍ መሳሪያ በመሆነበት የሉላዊነት ዘመን አገራችን በትምህርት ዘርፍ ከፍተኛ ውድቀት ደርሶባታል፡፡ ይህም የሆነው ለመምህራን የሚገባቸውን ትኩረትና ክብር ባለማግኘታቸው ነው፡፡ ባለፉት 24 አመታት ከመምህራን ይልቅ ካድሬዎች የህጻናትን አዕምሮ በፕሮፖጋንዳ እንዲበርዙ ሆን ተብሎ ተሰርቶበታል፡፡ መምህራን በነጻነት እንዳያስተምሩ በካድሬዎች ጣልቃ ገብነት ተማርረዋል፡፡ የመምህራን ማህበራት በገዥው ፓርቲ እጅ በመውደቃቸው መብቶቻቸውና ጥቅሞቻቸው ሊከበር አልቻለም፡፡ በየ መድረኩ በሚያነሱዋቸው ጥያቄዎች ከስራቸው ይፈናቀላሉ፡፡ ኑሯቸው የምትሸንፈውን አነስተኛ ደሞዛቸውን ይቀጣሉ፡፡ ይታሰራሉ፡፡ የገዥው ፓርቲ አባል ባለመሆናቸው ሁሌም በጥርጣሬ አይን ከመታየታቸው ባለፈ የተለያዩ እርምጃዎች ይወሰድባቸዋል፡፡
  የኢትዮጵያ መምህራን ቀጣዩን ትውልድ ለመቅረጽ ከመጣርና በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰው በደል ላይ ቀዳሚነቱን ወስዶ የትግሉ አካል እንዳይሆን ስርዓቱ ከፍተኛ ጫና እያሳደረባቸው ይገኛል፡፡ ይህም ሆኖ የራሱንና የሌሎቹን ድምጽ በማሰማት የቻለውን ያህል እያደረገ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ በየ ዕለቱ ከሚታሰሩት፣ ከስራቸው ከሚባረሩትና ሌሎች የስርዓቱ አፈናዎች ከሚደርስባቸው ባሻገር አድማጭ ሲያጣ ራሱን መስዋዕት ያደረገው መምህር የኔሰው ገብሬን መጥቀስ በቂ ነው፡፡ ስርዓቱ በመምህራን ላይ ከሚያደርገው ከፍተኛ አፈና አንጻር ያልተነገረላቸው በርካታ መስዋዕቶች እንዳሉም መገመት ይቻላል፡፡
  በአሁኑ ወቅት በመምህራን ላይ የተጫነው ጭቆና የአጠቃላይ አገሪቱ ውስጥ ያለው ጭቆና አንድ አካል ነው፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ነጻ ካልወጡ መምህራን ብቻቸውን ነጻ መሆን አይቻላቸውም፡፡ ነገር ግን ትግሉን በቀዳሚነት የመምራት የሙያና የሞራል ግዴታ እንዲሁም አጋጣሚ እንዳላቸው ግልጽ ነው፡፡ በመምህራን ላይ የተጫነውን ጭቆና ከድሮው የተለየ የሚያደርገው መምህራን ህዝብ ላይ እየደረሰ ለሚገኘው መከራ ይቅርና ለራሳቸውም እንዳይጮሁ፣ በራሳቸው የእለት ተእለት ችግሮችና ፍርሃት ተጠምደው እጥፍ ድርብ ጫና የሚፈጸምባቸው መሆኑ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት መምህራን የሚገባቸውን ሚና እንዳይወጡ ተደርገዋል፡፡
  መምህራን ያልቀረጹት ትውልድ ለራሱም ሆነ ለአገሩ ነጻነትና ክብር ሊቆም አይችልም፡፡ ባለፉት 24 አመታት በመምህራንና ትምህርት ላይ የተፈጸመው በደልም አሁን ላለንበት ጭቆና የራሱን ሚና ተጫውቷል፡፡ በመሆኑም ለራሱም ሆነ በቀሪው ማህበረሰብ በግንባር ቀደምነት የሚታገል ትውልድ ለመፍጠር የመምህራን ሚና ከመቼውም ጊዜ በላይ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
  በአሁኑ ወቅት የ9ኙ ፓርቲዎች የአንድ ወር መርሃ ግብር ቀርጸው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡ ምንም እንኳ አፈናው እየበረታ ቢሆንም መምህራን ቀዳሚ ሚና ሊወጡ እንደሚችሉ እናምናለን፡፡ በመሆኑም ራሳቸውን ነጻ አውጥተው ለህዝብ መብትና ለአገር ክብር ለመቆም ትግሉን እንድትቀላቀሉ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ መምህራን የአንድ አገር ህዝብ ላይ የሚፈጸመውን በደል ለማጋለጥና ህዝቡንም ለማንቃት ካላቸው ተደራሽነት እንዲሁም የሙያ ግዴታ ግንባር ቀደም ሚና በመጫወት ታሪካዊ ግዴታችሁን እንድትወጡ ጥሪ እናደርጋለን፡፡ በተለይ ህዳር 27/28 በተጠራው የአዳር ሰልፍ በመሳተፍና በሙያም ሆነ በሌሎች አጋጣሚዎች የምታገኙዋቸውን ኢትዮጵያውያን በመቀስቀስ ጥሪውን እንዲቀላቀለሉ በማድረግ ግንባር ቀደሙን ሚና እንድትወጡ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ ይህ ቀን ኢትጵያውያን ከፍርሃት ወጥተን ድምጻችን በጋራ የምናሰማበት እንዲሆን ቀዳሚ ሚና እንድትወጡ፡፡
  ዘረኛውና አምባገነኑ የህወሓት አገዛዝ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ከካድሬ ማሰልጠኛ ማዕከላትነት ለይቶ የማያይ ስለመሆኑ በተቋማቱ ውስጥ የሚደረጉ ተግባራት ማረጋገጫዎች ናቸው። ለዚህ ተግባሩ በሰነድ ደረጃ መቅረብ ከሚችሉት የቅርብ ጊዜ ማስረጃዎች ዋነኛው በህዳር 2007 ዓ.ም. በሥራ ላይ የዋለው “የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኢህአዴግ የምርጫ ድል ልማት ሰራዊት ግንባታ አደረጃጀት ማንዋል” የተሰኘው በትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላለፈው ሰነድ ነው። ይህ ሰነድ፣ የህወሓት አሳፋሪ የትምህርት ፓሊሲ ባፈጠጠ መልኩ የተገለፀበት፤ የኢፌዴሪ መንግሥት ተብሎ በሚጠራው የህወሓት አገዛዝ ተቋም እና በህወሓት/ኢህአዴግ ፓርቲ መካከል ለይምሰል እንኳን ልዩነት አለመኖሩ በግላጭ የሚታይበት ሰነድ በመሆኑ በዚህ ርዕሰ አንቀሳችን በስፋት ልንዳስሰው ወስነናል።
  ሰነዱ በትምህርት ሥርዓቱ ላይ መርዙን መርጨት የሚጀምረው ገና በመግቢያው ስለማንዋሉ አስፈላጊነት ሲገልጽ ነው። ማንዋሉ “ከምንም በላይ የብጥብጥና የሁከት መንስኤ የሆነውን ተማሪ በኢህአዴግ አመራር አባላት እየታገዙ ለመያዝ የሚያስችል ነው” በማለት ህወሓት ተማሪውን የሚመለከተው “ከምንም በላይ በብጥብጥ መንስኤነት” መሆኑ፤ ለዚህ መድሀኒቱ ደግሞ ተማሪውን በኢህአዴግ አመራር አባላት “መያዝ” መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ ይገልፃል። ቀጥሎም “በምርጫው ሊፈጠር የሚችለውን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሁከትና ብጥብጥ ለማስቆም በማደራጀት መረጃ ለመጥለፍ አመችነቱ የላቀ እንደሚሆን ታምኖበታል” በማለት መረጃ መጥለፍ የዩኒቨርስቲዎችና የትምህርት ሚኒስቴር ሥራ እንደሆነ አድርጎ ያቀርባል።
  የማንዋሉን ዓላማዎች በሚገልፀው ክፍል ደግም “… የከፍተኛ ትምህርት የትምህርት የልማት ሰራዊት ግንባታን ወይም የፓለቲካ ሰራዊት ግንባታ በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተደራጀና በተናቀጀ ሁኔታ በማቀጣጠልና በማስቀጠል … ምርጫ 2007 ውጤታማ ለማድረግ እና የኢህአዴግን አሸናፊነት ለማረጋገጥ ነው” በማለት ተቋማቱን የኢህአዴግ የምርጫ መሣሪያ መሆናቸውን፤ ግባቸውም የኢህአዴግ አሸናፊነትን ማረጋገጥ መሆኑ ይገልፃል።
  ደግሞ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች “በኢህአዴግ ላይ ያላቸው አቋም የወረደ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በማንኛውም ተቃውሞ ድምፅ ከተጠሩ፤ ሰልፍ የሚያደምቁ፤ ተቃውሞን ከግብ ለማድረስ ሁነኛ መሳሪያ ናቸው። ተማሪዎች በየትኛውም ሐገር እንደታየው አደባባይን የመያዝ ህዝብን አስተባብረው ለተቃውሞ የማሳደም እድላቸው የሰፋ በመሆኑ ከዚህም ሲያልፍ፤ የኢህአዴግ ምከታን በመቃወም ለጠላት ጎራ ተሰልፈው የመታጠቅ እድላቸው ከፍተኛ ነው” ሲል “በወጣቱ እጠላለሁ” የሚለው የህወሓት/ኢህአዴግን ስጋት አፍረጥርጦ ያወጣል። ትንሽ ወረድ ብሎ ደግሞ “በተለይ በአሁኑ ሰዓት ፈተና ላይ የጣለን የምርጫ ጉዳይ እንደምናሸንፍ ቃል የተያዘለት ቢሆንም፤ ፈተናዎች የሚፈጠሩት በህዝብ እና በራሱ ታማኝ ባልሆኑ ሃይሎች ማለትም በመንግስት ክንፍ አይቀለበስም ብሎ ማሰብ አይቻልም። በዚህም ቀድሞ መዘጋጀት ያለበት እና ለሁከት እና ለብጥብጥ መሳሪያ ሊሆን የሚችለው የህዝብ ክንፍ የተማረው ሃይል ሊሆን ስለሚችል ሊታሰብበት ይገባል” ሲል በተማረው ወጣትና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሠራተኞች ላይ ያለው ጥርጣሬና ፍርሃት ምን ያህል ከፍተኛ እንደሆነ ይገልፃል።
  የ2007 ምርጫ በህወሓት ሹማምንት ላይ የፈጠረውን ጭንቀት በዚህ ሰነድ ላይ በገሀድ የሚታይ በመሆኑ እያንዳንዱ ዓረፍተ ነገር በጥንቃቄ ሊነበብና ሊተነተን የሚገባው ነው። ለምሳሌ በገጽ 6 ላይ ስለዩኒቨርስቲ ተማሪ ሲገልጽ “የአመፅ እና የብጥብጥ መነሻ ሊሆን የሚችል ሀይል መሆኑን በአክራሪዎች ሲጠለፍ፤ ከመንግስት ሃይማኖቱን እየመረጠ በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ፤ በጅማ ዩኒቨርስቲ፤ በመቀሌ ዩኒቨርስቲ እና በሌሎችም ትምህርቱን ትቶ ሲኮበልል ተመልክተናል” ይላል። ለተማሪዎች፣ ከመንግሥት እና ከሃይማኖት አንዱን እንዲመርጡ ተደርጎ ሃይማኖታቸውን የመረጡ መኖራቸውን እና ይህ ደግሞ አደገኛ ነገር መሆኑን ነው ይህ ዓረፍተ ነገር የሚነግረን። ለመሆኑ ይህ ምን የሚሉት ምርጫ ነው? በእንዴት ያለ ሥርዓት ነው ዜጎች ከመንግስትና ከሃይማኖት አንዱን ምረጡ የሚባለው? እንዲህ ዓይነት ምርጫ ቀርቦ ሃይማኖትን መምረጥ እንዲህ ክፉ ነገር የሆነው ለምንድነው? ይህ ጉዳይ ብቻውን ብዙ የሚያነጋገር ነገር አለው።
  በገጽ 8 ላይ ደግሞ “ከፍተኛ አመራሩ ተቋማዊ ለውጥ እንዲሁም የትምህርት ልማት ሰራዊት ግንባታ ቴክኒካዊ ሳይሆን ፓለቲካዊ ጉዳይ መሆኑን ተገንዝቦ ካለእርሱ ባለቤትነትና ቀጥተኛ ተሳትፎ ሰራዊት መገንባት እንደማይቻል በመገንዘብ የመሪነት ሚናውን ካለምንም ማወላዳት መወጣት ይጠበቅበታል” በማለት እየተሠራ ያለው የፓርቲ ወገንተኛ የሆነ ፓለቲካ መሆኑን ብቻ ሳይሆን የትምህርት ተቋማት መሪዎች ዋና ተልዕኮ ትምህርት ማስተማር ሳይሆን የወያኔ ፖለቲካን ማስፈጸም መሆኑን ምንም ሳይጎረብጠው ፍርጥርጡን ያወጣዋል። ትንሽ ወረድ ብሎም “የጋራ መግባባት የምንለካው በመጀመሪያ ለምርጫው የኢህአዴግ የድጋፍ የድል ሰራዊት ብዛት ነው” በማለት ከላይ ያለውን በማጠናከር ወገንተኛነቱም ለኢህአዴግ መሆኑ ያውጃል። በመጨረሻም “ … ሁሉም የዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች ውጤታቸው የሚሞላላቸው ለምርጫው በሚያዘጋጁት የድጋፍ ሃይል ይወሰናል” በማለት የአካዳሚ ነፃነት ብቻ ሳይሆን የከፍተኛ ትምህርት ሥርዓትን ለቀብር ያዘጋጃል።
  ይህ ነው የህወሓት የትምህርት ፓሊሲ! የዩኒቨስቲዎች ቁጥር ለማመን በሚቸግር መጠን ቢጨምር፤ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ቅበላ በብዙ መቶኛዎች ቢያድግ ጥቅሙ ምኑ ላይ ነው። በእንዲህ ዓይነቱ ፓሊሲ ከተገነባ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋም ይገኛል የምንለው ፋይዳ ምንድነው?
  ህወሓት በገሀድ በጠላትነት የፈረጃቸው ስደትን የህይወታቸው የመጨረሻ አማራጭ በማድረግ በጅቡቲ በኩል አድርገው ወደ የመን ለመግባት የሞከሩ 70 ኢትዮጵያውያን ቀይ ባህር ላይ ሰጥመው መሞታቸውን የየመን ባለስልጣናት ገልጸዋል።
  ታይዝ በምትባለዋ ግዛት የሚገኙ ባለስልጣናት ለአሶሴትድ ፕሬስ እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያውያኑን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረችው ጀልባ ባጋጠማት ከባድ አውሎ ንፋስና ማእበል አል ማክታ እየተባለ ከሚጠራው ወደብ ራቅ ብሎ ለመስመጥ ተገዳለች። ባለስልጣናቱ እንዳሉት ጀልባዋ 70 ኢትዮጵያውያንን ጭና የነበረ ሲሆን በደጋው ሁሉም ኢትዮጵያውያን አልቀዋል።
  የመን የሚገኘው ጋዜጠኛ ግሩም ተክለሃይማኖት በበኩሉ በጀልባዋ ላይ የነበሩት 81 ሰዎች ሲሆኑ፣ 71 ኢትዮጵያውያንና 9 ሶማሊያዎች አልቀዋል። አይ ኦ ኤም የተባለው የስደተኞች ድርጅት አስከሬን ለመሰብሰብ ሙከራ ቢደረግም እስካሁን ምን ያክል አስከሬን እንደተሰበሰበ ለማወቅ አለመቻሉን ገልጿል
  ግሩም እንደሚለው በአንድ ወር ውስጥ ብቻ 8 ሺ ኢትዮጵያውያን የመን ሲገቡ፣ በ7 ወር ውስጥ እስከ 50 ሺ ኢትዮጵያውያን ተሰደዋል።
  የአገራችን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች፣ መምህራንና ሠራተኞች ይህንን አሳሳቢ ጉዳይ በአጽንኦት እንዲመለከቱ ያሳስባል። ትውልድንም የትምህርት ሥርዓቱንም የማዳን ግንባር ቀደም ኃላፊነት በተማሪዎችና በመምህራን የወደቀ ሸክም ነው ብሎ http://www.ideascale.com ያምናል። መላው የትምህርት ሥርዓት ለአንድ ፓርቲ የምርጫ ውድድር መሣሪያነት ሲውል ማየት እና የዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች የሥራ አፈፃፀም የሚወሰነው ለገዢው ፓርቲ ባስገኙት ድምጽ ብዛት ነው መባሉ፤ እነሱም ይኸንን ተቀብለው መሥራት መቀጠላቸውን የመሰለ አሳፋሪ ነገር በአካዳሚያ ውስጥ የለም። የከፍተኛ ትምህርት ተቋሞቻችን ይህን ውርደት መቀበል የለባቸውም። ሰነዱ ህወሓት ከፍተኛ ትምህርትን የሚመለከትበት ዕይታ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነውና ለምርጫ ወቅት ብቻ የተዘጋጀ የአጭር ጊዜ መመሪያ ተደርጎ መወሰድ የለበትም። ይህ ሰነድ ህወሓት፣ ተማሪዎችንና መምህራንን እንደጠላት፤ ተቋማቱን ደግሞ ጠላትን እንደመቆጣጠሪያ መሣሪያ እንደሚመለከት፤ ይህ ዕይታው ደግሞ ቋሚ መሆኑ በግልጽ ያሳያል። በህወሓት ዕይታ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኃላፊዎችና ፕሬዚዳንቶች ሆይ! ለገዛ ራሳችሁ ክብር፣ ለአካዳሚ ነፃነት፣ ለትውልድ ስትሉ በዚህ መመሪያ ላይ አምጹ! “እንቢ፣ አሻፈረን፣ በዚህ መመሪያ አንገዛም” በሉ! የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጎናችሁ ይቆማል።
  ከተገነቡ ተቋማት ምን ዓይነት ትምህርት ይገኛል?-ከአንድ ዓመት ላላነሰ ጊዜ በአሜሪካን ሀገር በቺካጎ ከተማ በሚገኝ አንድ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሲያስተምሩ ቆይተው በቅርቡ ወደሀገር ቤት መመለሳቸውን የተናገሩት የወቅቱ የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ዲያስፖራውን ወቅሰዋል።
  ፕሮፌሰሩ በዛሬው ዕለት ለንባብ ከበቃው መንግስታዊው ዘመን መጽሄት የጥቅምት 2007 ዕትም ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ «ዲያስፖራው ተስፋ የቆረጠና የተናደደ ነው፡፡ ተስፋ ስለቆረጠና ስለተናደደ ገዥው ፓርቲ የሚሰራው ሥራ ሁሉ ጥፋት ነው ብሎ ራሱን አሳምኖ ቁጭ ያለ ነው፡፡ በዚህም የሚናደድና የሚንቦገቦግ ነው፡፡
  እናም ከእነዚህ ጋር ውይይት ማድረግ አይቻልም፡፡» ብለዋል። ፕሮፌሰር በየነ በዚሁ ቃለምልልሳቸው «ዲያስፖራውን ለመምከር እንሞክራለን» ካሉ በኃላ በአሜሪካ ቆይታቸው ወቅት እርሳቸው ንግግር እንዲያደርጉ የተጋበዙ ሰዎች እንዲበተኑ እንደተደረገ ተናግረዋል።
  መጽሄቱ በእሳቸው ላይ ይህ ለምን እንደተደረገ ጠይቆአቸው በሰጡት ምላሽ «እኔ እውነቱን ስለማወጣ ነው» የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
  ኢህአዴግ በአንድ በኩል እኛን ትክክል ባልሆነ ምስል ያስቀምጠናል ያሉት የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ዲያስፖራው ደግሞ የባሰ በመሆኑ መቸገራቸውን ተናግረዋል፡፡

 3. Nazret
  | #3

  I wonder when Ethiopian politicians in the diaspora ever stop such childish propaganda. Show respect for your audiences. Are you now in support of wearing Hijabs? This kind of dress (for security reasons) should be banned in any civilised country. It has nothing religious about it but is a manifestation of Saudi Arabia dress code. Because of this kind of at your face attitude Islam is the most hated religion on earth these days.

Comments are closed.