አንድነት ለፍትህ እና ለዲሞክራሲ ፓርቲ በአንድ ወር ውስጥ ከሰላሳ ሁለት በላይ ቢሮዎችን ለመክፈት አቅዶ እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታወቀ፡፡

October 22nd, 2008 Print Print Email Email

andenet_offices.gif (more…)

andenet_offices.gif

For The PDF Version, Click Here


የድርጅት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ፀሀፊ፣ የማእከላዊ ኮሚቴ አባልና የሰሜን ኢትዮጵያ ማስተባበሪያ ሀላፊ አቶ ይልቃል ጌትነት በተለይ ለአውደ እንደገለፁት በዚህ በያዝነው ወር ውስጥ በአምስቱም ቃጣናዎች ከሰላሳ ሁለት በላይ የዞን ማስተባበሪያ ቢሮዎችን ለመክፈት፣ አባላትን ለመመዝገብና ለማደራጀት እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡ ‹‹በሰሜን ስምንት፣ በደቡብ አስራ አምስት፣ በምእራብ አምስት፣ በምስራቅ ሶስት፣ በመሀል ዋናውን ጽ/ቤት ማደራጀት ነው የዚህ ወር እቅዳችን›› ያሉት አቶ ይልቃል ቢሮዎቹን ለመክፈትና አባላትን አሰባስቦና አደራጅቶ ለመመለስ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ሄደዋል፣ በመሄድ ላይ ናቸው፡፡

በሰሜን ወ/ሪት ብርቱካንና አቶ ተመስገን ዘውዴ የሚመራ ቡድን በወሎ መስመር ወልድያ፣ ከሚሴ፣ ሀይቅና ደሴ፤ ኢ/ር ግዛቸው፣ አቶ ይልቃልና ፕሮፌሰር መስፍን በጎጃም ፣ደብረ ማርቆስ፣ ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ደብረ ታቦር፤ በዶ/ር ሀይሉ የሚመራ ቡድን በምእራብ እንዲሁም ደቡብ በአደራጅ ደረጃ ባሉ አባላቶች አማካኝነት ቢሮዎቹ ይከፈታሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በምስራቅ ሱማሌ ክልልን ጨምሮ ለማደራጀት እንዲቻል ‹‹በስልክ ኔትዎርክ ፈጥረናል›› ያሉት አቶ ይልቃል ቦታው በአውሮፕላን ካልሆነ ስለማይመች ‹‹አመቺ በሆነ ጊዜ ወደ ቦታው በመሄድ ቢሮዎቹ ይከፈታሉ፡፡››

እንደ አቶ ይልቃል ገለፃ እቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ ካለፈው ሳምንት ጀመሮ ወደየአካባቢዎቹ እየተሰማሩ ነው፡፡ የቀድሞ አባላትንና ቢሮዎችን ቀደም ብሎ ለማደራጀት ለምን አልተሞከረም ብለን ላነሳንላቸው ጥያቄ አቶ ይበልጣል ሲመልሱ ‹‹የቀድሞ አባላቶቻችን ምነው ዘገያችሁ እያሉን ነው፡፡ ነገር ግን እዚህ ያለውን ስራ አጠናክረን ድርጅቱ በሁለት እግሩ ሳይቆም ቢሮና አባላት ማብዛቱ ብዙም የማያስኬድ መሆኑን ካለፈው ልምዳችን በማስተዋላችን፣ እንዲሁም ተጠያቂነትና ድርጅታዊ ጥንካሬ እስኪመጣ በሚል ነው›› ብለዋል፡፡ የህዝቡ ፍላጎት በጣም ከፍተኛ ነው የሚሉት አቶ ይልቃል የገንዘብና የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በቀር በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ለመክፈት ያቀድናቸውን ቢሮዎችና ለመመልመል ያሰብነውን ያህል አባል እናገኛለን የሚል እምነት አለን›› ብለዋል፡፡

Comments are closed.